ጥላ ዓልባ__________(ልብ ወለድ)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby እህምም » Mon Apr 27, 2009 5:20 am

:twisted: ከምር i've never been this pissed about a thread b4.

:lol:
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Postby ifa » Wed Apr 29, 2009 2:26 am

በፈጠረህ ግፍ እንዳይሆንብህ....የአድናቂዋች እንባ
Ethiopians are: " THE BLAMELESS RACE "

Homer (Greek poet of the 8th century B.C.)
ifa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 135
Joined: Mon Jul 09, 2007 6:24 am

Postby Tጂ » Wed Apr 29, 2009 7:51 pm

እህም እንደ ጻፈችው

ከምር i've never been this pissed about a thread b4.


አንቺ ደግሞ you piss me off እኮ ደህና የረሳሁትን ወደፊት ጎትተሽ በማምጣትሽ
“Love is like the wind, you can't see it but you can feel it."
Tጂ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 301
Joined: Sat Aug 11, 2007 3:59 am

Postby ifa » Thu Jul 23, 2009 6:17 am

እባክህ ተለመነን......ወይስ ጥላ አልባዋ ራስዋ ኪድናፕ አድርጋሀለች..
Ethiopians are: " THE BLAMELESS RACE "

Homer (Greek poet of the 8th century B.C.)
ifa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 135
Joined: Mon Jul 09, 2007 6:24 am

Postby የግልነስ » Fri Jul 24, 2009 2:24 am

ifa wrote:እባክህ ተለመነን......ወይስ ጥላ አልባዋ ራስዋ ኪድናፕ አድርጋሀለች..

******************************************
አይፋቺን ምን ታደርጊያለሽ ደሞ እዚ ቅቅቅቅቅቅቅቅ ደህና ነሽ ግን ??? ዋንቾ እኮ ጥላ አልባን በተንጠልጠል ጨርሶታል ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ገደለኝኝኝ አሁንማ ጨራሽ ከዋርካም ጥፍቱ ብላልልል ጉድ እኮ ነው............................

ስላም ላንተና ለቤትህ ዋንቾ
የግልልልልልልል
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

Postby ኤልሳ* » Mon Jul 27, 2009 4:40 pm

ይሄ ቤት እንዴት ያሳዝናል..... :( :( :(
ኤልሳ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jul 27, 2006 10:30 pm

Postby ዞብል2 » Mon Jul 27, 2009 6:51 pm

ኤልሳ ካንቺ ብሶ :?: :cry: :cry:


ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2370
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ዋናው » Tue Nov 17, 2009 3:12 am

ጥላ-ዓልባ ምናልባትም በረጅም ወጥ ስራ የኔ የበኩር ልጄ....
በ19 04 2006 ተጀመረ
በ09 12 2008 ተቋረጠ...
ከ221ሺህ በላይ ምልከታን ያስመዘገበ
ከ495 በላይ ያንባቢያን አስተያየቶች ምልልስ ያስሠፈረ... ይህ ልብ-ወለድ በተቋረጠ በ1 ዓመቱ ከ8ኛው ጓሮ አዋራዉን አራግፌ ሳሎን አመጣዉት::
እርግማናችሁ ቢደርስብኝ ቆሜም አልሄድም ነበር ዳሩ በአፋችሁ እንጂ በሆዳችሁ ስላልረገማችሁኝ ይሄው ብቅ አልኩ::
እጅህ ከምን?
ጥላ-ዓልባን ልቀጥል ነው መልሴ... ዓመታት ውስጤ ሳፋጫቸው የኖሩ ምናቦች ስጋ ለብሰው ማስፈራራት ከጀመሩኝ ቆዩ ነገ ዛሬ እያልኩኝ ቢሮክራሲ ሳበዛባቸው'ንጂ...
አንባቢ አያሳጣኝ የዘውትር ፀሎቴ ነውና ለናንተ አንባቢያኖቼ ያለኝ ብዙ ብዙ ማክበር በአፍ ብቻ እንዳይሆን ከጥላ-ዓልባ ፍፃሜ ጋር እጅ ነስቺያለሁ::

ጭልጭላጭ ፖስቶችን እዚህ ሰቅዬ ''ለዚህ ነው'ንዴ'' በሚል ስላቅ ራሴን ላለማስወቀስም ከአጓጉል ሆሄያት ግድፈት ለመጠንቀቅም እስከ ዲሴምበር ልመለስ
የፀና ቃል ልግባና ለአሁኑ ልለያችሁ

በድጋሚ ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር

ዋናው
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2804
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ደጉ የት ገባ » Tue Nov 17, 2009 3:55 am

እልልልልልልልልልልል !!!!!!!!!!!!!!!!!!
ዋናውን የበላ ጅብ ጮህ

ይሄ ዲሴምበር ቀረ እንዴ ?????

አፍጥጬ ብቻ ሳይሆን እየትቁለጨለጭኩ እየጠበኩ ነው :shock: :shock: :lol: :lol:
ደጉ የት ገባ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 548
Joined: Wed Feb 22, 2006 4:02 am
Location: usa

Postby ዋኖስ » Tue Nov 17, 2009 3:57 am

ጎሽ! ድንቅ ኃሳብ!! መጽሐፍም ልጅ ነው ሲባል እሰማ ነበር ድሮ! ታዲያ "የገሀዱ መፅሐፍ" (ደቦሉ) :lol: መጣና ጂምር "የምናብ መፅሐፉን" አስረሳብን ብዬ ተቆጭቼ ነበር:: :lol: :lol:

ዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ሺውሺው » Tue Nov 17, 2009 1:54 pm

እልልልልልልልልልል
እስቲ እኔም መነጥሬን አዘጋጅቼ ልጠብቅ :shock: :shock:
ሺውሺው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Thu Dec 27, 2007 8:12 pm

Postby ወንዳታ25 » Tue Nov 17, 2009 4:02 pm

ዋናው እንኩዋን ደህና መጣህ...ጥላ እልባን ለመቀጠል በመምጣትህ ደስ ብሎኛል....በርታ
እባክህ ጀምረህ እንዳታቅዋርጠው :idea: አደራ, አደራ
The future belongs to those who believe in the beauty of their dreams......dream big & live big.
ወንዳታ25
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 145
Joined: Tue Oct 20, 2009 11:19 am
Location: zendirom ezaw

Postby ifa » Wed Nov 18, 2009 2:04 am

እድሜ ያለው ብዙ ያያል....እሰይ ይሀው አፍጠን አፍጠን ብቅ አልክ...እስይ እሰይ...
Ethiopians are: " THE BLAMELESS RACE "

Homer (Greek poet of the 8th century B.C.)
ifa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 135
Joined: Mon Jul 09, 2007 6:24 am

Postby ዋናው » Wed Dec 02, 2009 3:36 am

በትዕግስት ጠብቃችሁ ስመጣ ፈገግ ላላችሁልኝ አንባቢያኖቼ ሁሉ ምስጋናዬን ባየር ልኪያለሁ::....

መሪጌታ እስቲ ባክህ አንድም ያነቃቃኝ ዘንድ አንድም መማማሪያዬ ይሆን ዘንድ ፈቃድህ ሆኖ ያቺን ያስተያየት መስጫ ሳጥን ከሳሎን አምጣልኝ ባይሆን አብዋራዋን እኔው እፍፍፍ እለዋለሁ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2804
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed Dec 02, 2009 3:38 am


ከብዙ ጊዜ በኌላ የቀጠለ
.
.
.


አልተግደረደሩም ፀጉሯን የጎንዮሽ ወደውኃላዋ እየመታች ወደባርቴንደሮቹ ስታመራ አንተነህ ከውኃላዋ አይቷት የዮሐንስን ዓይኖች አይቶ የማብሸቅ ዓይነት ፈገግታ አሳየው : ዮሐንስም ድፍርስ ዓይኖቹን ሠብሮ በያዘው ብርጭቆ ለመማታት እንደቃጣ ሆኖ ቀለደ ::
''ወንድ ልጅ ሆነህ ሴት ልጅ ሙቀት ውስጥ ስትቀልጥ ማንነትህ ይቀየራል ... ይገርመኛል አንቱሽ ...''
አለው የካትሪንን የአንሶላ ገፈፋ ትዝታው እየታየው ::
''አውሬ መሆን ሚያምርብን ያኔ ብቻ ይመስለናል ስንጣላ ስንናደድ እና ተንኮል ስናስብ አውሬ ስንሆን ያስጠላብናል ...''
አለ አንተነህ ዘና ብሎ ለመቀመጥ ትከሻዉን ወደ ውኃላ ለጠጥ እያደረገ ...
ልክ በተባለው ሠዓት ዶክተር ኤደዋርድ ጥቁር ካፖርቱን በአጭር ቁመናው ላይ እያዘናፈለ ብቅ አለ የአፍንጫው ስር ፂሙ በቄንጥ ጎፍረው የላይኛው ከንፈሩ ላይ ተደፍተዋሉ :: የእጁን ጓንት አውልቆ ጨበጣቸውና በፈገግታ ተቀላቀላቸው ::
''ካንተ ጋር በአካል ተገናኝተን ስናወራ ይሄ... የመጀመሪያ ነው’’
አለ ኤድውዋር አትኩሮት ወደ ዮሓንስ እያየ በመጠኑም ቢሆን ዮሓንስ ሽቁጥቁጥ ባለማለቱ የተገረመ ይመስላል ወይም ጠብቆት ነበር። ዶ/ር ኤድዋርድ የተወሠነ ብር ተሠጥቷቸው ከዛም ሌላዉን ብር አንተነህ ከካትሪን ጋር ማሊዢያ ከሄደ በኋላ እንደሚሠጣቸው ተናግሮ አሳመናቸው።
‘’ከእኔ ጋር ማሊዢያ አብረህ በመሄድህ ኤልዛቤት ብዙም ቅር እንደማይላት ተስፍ አለኝ’’
አለች ካትሪን ማታ ላይ ዶ /ር ኤድዋርድ ተሰናብቷቸው ከተለየ በኌላ ከመጠጥ ቤት እየወጡ

ከጎን የዮሐንስን ክንድ ይዛለች አንትነህ ትንሽ ከሲጋራው ጋር ከቆዘመ በኌላ
''እኔና አንቺ ነን የምንሄደው ?''
አላት እሷም ከዮሐንስ ሢጋራ ተቀብላ አንድ ሁለቴ ሳብ ካደረገች በኌላ
''እኔማ ጆኒ አብሮን እንዲሄድ እፈልጋለሁ ...''
አለች ወደ ዮሐንስም ዞራ እያየች
አንተነህ ዮሐንስን ጠቀስ አድርጎ
''እሱ እዚሁ ቢቆይ ምናልባት የሚረዳን ነገር ይኖር ይሆናል ... ግን ካትሪን የኔ ማሊዢያ መሄድ ለምን እንዳስፈለገ ዶ /ር ኤድዋርድ ግልፅ አድርጎ አላስረዳኝም ''
አለ አንተነህ።
''ላንተ ጥሩ ዕድል ነው የምታከብረው ሙያህን ወደፊት ለማስፋፋት ስታስብ ወደተለያዩ ክፍለ -ዓለማት መሄድ አለብህ :''
አለችው’’።
ማታ ላይ ሁሉም ሲለያዩ አንተነህ ለዮሐንስ አንድ ነግሮት የማያውቀው ነገር እንዳለና ያንን ነገር ሊነገረው እንደሚፈልገው በቀጠሮ ተለያዩ::
ቤቱ ሲደርስ ኤልሣቤት ሶፋው ላይ ሆና እንቅልፍ እያዳከማት ዓይኖቿ ተስለምልመዋሉ::

ከባለስኬታማ ወንዶች ጀርባ ብርቱ ሚስቶች አሉ::
የሚለው አባባል ትዝ አለው::


_______________________________________

ሠፊው የለንደን ሂትሮው ዓየር ማረፊያ እንደሁሌም በሸኚና ተቀባይ በተመላሽና ሂያጅ እንዲሁም በማረፊያው ሠራተኞች ብዙ ሕዝብ ግርግሩ ነግሷል::

''አሁን'ኮ ስንለያይ በምን መልኩ እንደምንለያይ እራሱ አልገባኝም....''
አለች ሠባዊት የዘካሪያስን ጃኬት ኮሌታውች በእጆቿ እየጎተተች ፊቷ ላይ የተረጋጋ ሀዘን ይታያል:: የሚቀበሉት ሃዘን ... በተስፋ የሚሸነግሉት ናፍቆት....

''እንዴት ሠቢዬ...?''
አላት ስትጎትተው ከናፍርቷ ላይ እያፈጠጠ ይህኔ እሷም የአፍረት አንድ ትከሻው ላይ ትደፋና...

''በቃሀ.... ተመልሼ ልምጣ አልምጣ.... አንተ ትከተለኝ አትከተለኝ.... በትክክል የማውቀው ነገር የለም ዘኪ''

''በአንድ ነገር ግን 2ታችንም እርግጠኞች ነን ሠቢ... ተራርቀን ብዙ መቆየትን አንፈልግም ስለዚህ ማድረግ ካሉብን ነገሮች አንዱን አመቻችተን እናረጋለን::''
አላት በእቅፉ እያሞቃት::
ራሷን ከፍና ዝቅ አድርጋ ወንድሟን አሻግራ አየች ከአንተነህ እና ከዳኒ ጋር ያወራል ሮማን ሻንጣዋን ደጋግማ እየከፈተችና እየዘጋች አንድ ነገር ባስታወሰች ቁጥር ባሏ ላይ ትደነፋለች::
ዘካሪያስ እና ሠባዊት መላቀቁ ሞት እንደሆነባቸው ሁሉ ደጋግመው የሞባይል ሠዓታቸውን ሲያዩ
''...በሉ ተላቀቁ ሸኚ ቤት አያደርስም ወንድም ጋሼ''
አለች ሮማን መጥታ
.
.
.
ይቀጥላል
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2804
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests