ጥላ ዓልባ__________(ልብ ወለድ)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዋናው » Sun Aug 13, 2006 3:16 am

.
.
.
ዘካሪያስ በድንጋጤ ወደ ቫኔሳም ወደ ሠባዊትም እያየ ዓይኖቹን አቁለጭለጨ:: ሠባዊት ዓይኖቿን ወደመሬት ተክላለች

''ዘካር ይቅርታ አንዴ ላናግርህ እችላለሁ ....ይቅርታ ...''
አለቻት ቫኔሳ ወደ ሠባዊትም ዞራ የእንጊዝ ደረቅ ሳቋን ብልጭ እያደረገች:: ዘካሪያስ ተርበትብቶ በፍርሀት ተራመደ

''ዘካር....በፊትም እነግርህ የነበረው ይሄንን ነው ግልፅ እንድትሆንልኝ ...ለምን ራስ ወዳድ ትሆናለህ? ፍቅርህ ሲያልቅ ልታሳውቀኝ ይገባል ''

''ቫኒ ሁሉም ነገር አንቺ እንዳሰብሽው ላይሆን ይችላል''

''አውንም ድጋሚ ልትዋሸኝ እየሞከርክ ነው ዘካር ቢያንስ የእሷን ዓይኖች ማንበብ እችላለሁ እኔ ሌላ አትውደድ አላልኩህም ግን ለእኔም ሆነ ላንተም ነፃነት ሲባል ፍቅርህን መጨረስህን ልትነግረኝ ይገባል::''

''ቫኒ ፍቅሬ ቢያልቅ አላሰርሽኝ ወይም አላስገደድሽኝ ለምን ካንቺ ጋር ጊዜዬን አጠፋለሁ....?''

''እወድሀለው ዘካር ይሄንንም ታውቃለህ ካንተ ጋርም ብዙ ዓላማ ነበረኝ አምናለሁ ፍቅርህን ሰጥተከኛል ....ግን ውስጥህ እኔን እንዳትፈልግ የሚያደርግህ አንድ ነገር አለ ....ያንን ደግሞ ስጠይቅህ አትነግረኝም ::''

ቫኔሳ ስታወራ ሲጋራዋን ከንግግሯ የእጆች እንቅስቃሴ ጋር እያወናጨፈችው ነበር:: ዛሬ ደግሞ ቆንጅታለች

.''ቫኒ ዛሬ የፒካሶ ፕሮግራም ነው ይህንን ርዕስ ነገ እናውራው?''

የቀጨሙ ዓይኖቿ እምባ ሲያዡ በእጆቿ ጀርባ ጠራርጋ ዘካሪያስን በስስት ዓይታው ከንፈሯን የእልህ ሳይሆን በተለየ ስሜት ነክሳው ወደ ጋለሪው ገባች::ትንሽ ቆይቶ እሱም ገባና ሠባዊትን በዓይኑ ፈለጋት አላገኛትም::

አንተነህ ይዋከባል ጋዜጠኞች ይጠይቁታል ,ታዳሚያኑው የአድናቆት ቃላት ይወረውሩለታል, ከፊሉም ጥያቄ ይሰነዝራል:: አንተነ ዛሬ ሙሽራ ነው ድግሱን ያቋድሳል

''ሠባውትን አየካት ፒካሶ?''

''ሄደች ዘኪ እንድትቆይ ብለምናት እንደምትቸኩል ነግራኝ ይቅርታ ጠይቃኝ ነው የሄደችው::''

''እና ዝም አልካት ፒካሶ እንግዳ'ኮ ነች?''

''ልጠራህ ሁለቴ ብመጣ ከቫኒ ጋር የጦፈ ወሬ ይዛቹዋል::''

''ወይ ወሬ ፒካሶ.....''
የሞባይል ስልኩን አወጣና ደወለላት ለሠባዊት ግን ስልኩ እንደተዘጋ የሚያሳይ ምልክት ሰጠው ደጋግሞ ሞከረላት ግን ሊያገኛት አልቻለም:: ውስጡ ደስ የማይል ስሜት ተሰማው የራሱን ስሜት ለማዳመጥ ግራ ተጋባ ምን እንደሚፈልግ ምን እንደማይፈልግ....ሁሉ ጠፋበት ኤግዚቢሽኑን እየተዘዋወረ ሲያይ የሠባዊትን ምስል ቫኔሳ ቆማ እያየችው ነበር::
ከቫኔሳ ጋር አብሯት ስዕሎቹን የሚያይ አንድ ፈጠንፈጠን የሚል አጭር እንግሊዛዊ ሰውዬ የሠባዊትን ምስል አተኩሮ እና ተመላልሶ ካየው በዋላ ሊገዛ እንደወሰነ ለአንተነህ ነገረው::

''ዛሬ ደስተኛ የሆንክ አትመስልም ዘኪ? ''
ኤልሳ ቤት ነበረች ፈገግታዋ እንኳንስ ፈገግታዋን ለለገሰችለት አይደለም ከሩቅ ላያትም ሁሉ ደስ ትላለች

''ዕዕዕዕዕዕ እኔንጃ ኤልሳ...በፕሮግራሙ በጣም ደስተኛ ነኝ ግን ያጋጣሚ ሆነና ደስታወን የሚያባርር ሙድ ገጠመኝ::''

''አመሰግናለሁ ግን ስለጋበዝከኝ እንደዚህ ዓይነት ስሜት ያላቸው አበሾች ለንደን ውስጥ የማገኝ አልመሰለኝም ነበር: ''
ወዲያው አንተነህ መሀላቸው መጣና የኤልሳቤትን ትከሻ ባንድ እጁ መዳፍ እያቀፈ

''በጣም የምትገርም እንግዳ ነው ዛሬ ይዘህልኝ የመጣከው ዘኪ እቺ ቆንጆ ውስጧን ብታየው ብዙ ብዙ ስዕሎች ይወጣዋል::''
አለ የዛሬው ደስታው ፊቱ ላይ ግንፍል ብሎ ይታያል::

''ኸረ ያንን ያህል አትካበኝ''
አለች

''እንዲህ ነኝ ታውቃለህ እኔ ተራ ሰው አላውቅም::''
አለ ዘካሪያስ ለተሳትፎ ያህል እንጂ ልቡ እዛ አልነበረም::

''ማታ የት ነን ዛሬ?''
አንተነህ ጠየቀ ሰሃቱን እያየ

''እኔንጃ''

''እኔ ኤልሳ ስዕል ስትሸጥ አይቼካለሁና እራት ሳልበላ አልለቅህም ብላ ይዛኛለች''
አለ አንተነህ ወደጎን እያስተዋላት

''ኖ..... መሄድ አለብኝ ዛሬ ፒካሶ...አንተነህ....ይቅርታ ግን ፒካሶ ልበል አንተነህ?''

''ደስ ያለሽን''
.
.
.
ይቀጥላል::

ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Aug 13, 2006 10:23 pm

(-27-)
.
.
.
አዲስ አበባ

ገዛህኝ ከቤቱ ማልዶ ሲወጣ አዲሳባ ቀድማው ነቅታልች:: የታክሲ ወያላዎች እሪታቸውና የታክሲውን በር ቅብቀባቸው አካባቢው አዳምቆታል:: ሠኞ ሁሉም ራሱን ላዲስ ሳምንት ያዘጋጃል:: ሠራተኛው ነጋዴው ተማሪው ሁሉም የትላንትናውንና የትላንትና ወዲያውን የሰንበት ትኩስ ወሬ ይዞ ረጅሙን ሠኞ ይጀምራል:: ገዛህኝ ካሮጌው ቄራ ሠማያዊ ቀለም ያላትን ቢ ኤም ደብሊው መኪና እየሾፈረ የመንገዱን መቦርቦር እየታዘበ ወደ አቢዮት አደባባይ አቀና::
አርብ ወደሠባዊት ቢሮ ቢደውል እንዳልመጣች ነገሩት:: ሦስተኛ ወሯ ሊመጣ ነው እንግሊዝ ከገባች:: ገዛህኝ ሠባዊት ወንድሟን ፍለጋ መሄዷን ሠምቷል: ለዓመታት ሲከጅለው የነበረው ከቤተሰቧ የምትወርሰውን ሀብት ከወንድሟ ጋር ሕይወቷን መምራት ከጀመረች በምንም መልኩ እንደማያገኘው ያውቃል:: ግን እጅ መስጠት አልፈለገም:የሠባዊት ለስላሳ ጸባይ እየተቀየረ መምጣቷ አስገርሞታል እንደበፊቱ እንደፈለገ ሊያጃጅላት አልቻለም:: የፀባቸውን ዕለት ድንገት አስታወሰ

የዛን ዕለት የልደት ቀኑ ነበር: እጮኛው ትርሲት የምሳ ግብዣ በኢትዮጲያ ሆቴል አዘጋጅታለች ጥሩ የፍቅር ቀን አሳልፎ ዋለ:: ትርሲት ስለሁለቱ ግኑንኙነት ታውቃለች እንዴት አድርጎ ሊያጠምዳት እንደሚችል ብዙ ብዙ ነገሮችን የምትመክረም እሷው ነበረች::
ማታ ላይ ስልክ ደወለላት አላነሳችም ደጋግሞ ደወለላት አልመለሰችለትም:: በማግስቱ ቤት ሲሄድ በኩርፊያ አብጣ አገኛት

''ትላንትና ስደውልልሽ ስልክሽን አላነሳሽም አንቺም መልሰሽ አልደወልሽልኝም ምነው?''

''አውቄ ነው::''

''ለምን?''

''ስለማልፈልግ ስለማትፈልገኝ ::''

''ምን ማለት ነው?''

''ገዝሽ ሁሉንም ነገር ደርሼበታለሁ ግን የሚገርመው በጣም የተዋጣልህ ተዋናኝ ነህ ፕሊስ ሠው ሲነግረኝ ማመን አልፈለኩም ነበር በፍቅር መሀል ለወሬ ክፍተት ላለመስጠት....እኔ ግን የተፋቀርን መስሎኝ ነበር ግን አይደለም''
አለችው እየተነፋረቀች

''ምን ሆነሻል? ለምን በግልፅ አትነግሪኝም ያደረኩሽ ነገር አለ?''
አላት ቆሞ ወደ ጊቢው በመስኮት እያየ

''ትላንትና ካንዲት ሴት ጋር ልደትህን እያከበርክ ነበር እኔ ግን ሰርፕራይዝ ላደርግህ ጓደኞቼን ሁሉ ሰብስቤ ደግሼ መዘጋጀቴ....ያቺ ሴትም ንፁሕ ጓደኛዬ የምትላት ትርሲት ናት ብዙ ብዙ ተጃጃልኩኝ ትላንት ግን ነቃው::ይሄው ይህንን ነው መስማት የፈለግከው አይደል? ውሸትሽን ነው ካልከኝ ግን ካሁን በዋላም ልታሞኘኝ እየተዘጋጀህ ነውና ጠላትነትህ እየበዛ ነው::''
ገዛህኝ ግን የነገረችውን ዕውነት መቀበሉ ሽንፈቱ ስለሆነ ሊያሳምናት የሚችልበትን መንገድ እየፈለገ ነበር:

''ስለማን ነው የምታወሪው?''
ከዚህ ጥያቄ በዋላ ምልሻም አላገኘም ቤቱን ጥላለት ወጣች::

ገዛህኝ በሃሳቡ ወደዛ ቀን ተጉዞ እንደተከዘ አቢዮት አደባብይን, ሪቼን አልፎ ላንቻ ደረሰ ወደ ሮማን ቢሮ አመራ::
ሮማን ሠባዊትን ምን ያህል ውስጧን እንደጎዳው ስለምታውቅ ለገዛህኝ ጥሩ ስሜት የላትም ሽቅርቅር አቋሙን እያየችው በፈገግታ ተቀበለችው ውስጧ ያለውን ጥላቻ እንዳይወጣ ታግላ

''ጤና ይስጥልኝ ሮማን''

''ሀይ ገዛህኝ ሠላም ነህ ጠፋህ ?''

''ሠላም ነኝ እንዴት ነሽ አንቺ?... ምን ሩጫ ሆነ ባክሽ ጊዜም የለም ''

''ስራ እንዴት ነው?''

''ጥሩ ነው ሮማን..አንቺስ እንዴት ነሽ ቤተሰብ ሠላም?''

''ሠላም ነው እግዚያብሔር ይመስገን::''
ትንሽ በዝምታ ፊት ለፊት ከተናበቡ በዋላ

''ዛሬ ምን እግር ጣለህ ?''
አለችው ሮማን ጠይም የደስ ደስ ያላት ነች ያፍንጫዋ አወራረድና የግንባሯ ተረተር ወንድሟ ዘካሪያስን ትመስላለች

''ስለ ሠባዊት ልጠይቅሽ ፈልጌ ነበር ብደውል እንዳልመጣች ነው የሚነግሩኝ እና ሁሉንም ካንቺ ብሰማው.....''
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው_________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ናርዶስ-1 » Mon Aug 14, 2006 5:42 pm

ኢንተርስቲንግ የሆነ ልብ ወለድ ነው በተለይ ሰአሊውና እነ ዝካሪይስ ፈቅር ይሲዛሉ ኤኒዌይ የተዋጣለት ፅሁፈ ነው በዚሁ ቀጥል ግን ፕሊስ ቶሎ ቶሎ ፃፍ ልባችን ጥል ጥል አታድርገው አንባቢይንህ እየተሯሯጠ ነወ ለማንበብ በርታአንባቢህና አድናቂህ ናርዶስ-1
ናርዶስ-1
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Sat Aug 12, 2006 4:14 pm
Location: ልብህ ውስጥ

Postby ዋናው » Fri Aug 18, 2006 12:06 am

.
.
.
''ሠባዊት የምትመጣበትን ጊዜ ለተወሰነ ጊዜ ማራዘሟን በቀደም ዕለት ደውላ ነግራኝ ነበር:''
አለችው የሠባዊትን መምጫ የናፈቀውን ፊቱን ወዳቀጨመው ገዛሕኝን እያየች

''በትክክል የምትመጣበትን ቀን ልትነግሪኝ ትቺያለሽ ሮማን?''

''እኔንጃ ገዛህኝ ምናልባት ካንድ ወር በዋላ ...ምነው በሠላም ነው?''

''ናፍቃኝ ነው ሮማን የእኔና የሠባዊት ጉዳይ በእንጥልጥል እንደቀረ ታውቂያለሽ...?''
ሮማን በውስጧ ተገረመችና እያመናታች ደፍራ..

''ጓደኛህስ ሰላም ነች?''
አለችው ወደ ያዘችው ብህር አንገቷን ደፍታ

''ሠላም ነች እሷ ምን ትሆናለች ...''
ተነፈሰና ወደጣሪያው ዓይኖቹን እይቁለጨለጨ
''...በባዶ ልቤ አብሬያት ስኖር ሰለቸዋት በሠባዊትም ምክኒያት ነጋ ጠባ ጭቅጭቅ ነው::''

''የረጅም ጊዜ ጓደኛህ ነች ይሄንን ተስማምታችሁ ልትፈቱት የምትችሉት ጉዳይ ይመስለኛል ካንተ ባልውቅም...''

''አንድ ነገር ልንገርሽ ሮማን አውቃለሁ የልብ ጓደኛዋ እንደሆንሽ... ምንም ይሁን ምን...ሠባዊት የእኔ ነች እሷ የተፈጠረችው ለእኔ ነው::''

''ይቅርታና በዚህ ጉዳይ ልትወስን የምትችለው ራሷው ሠቢ ነች ...ግን ባለፈው እኔ ሳናግርህ ጎድታሀታልና ይቅርታ ጠይቃት ብልህ ጥፋትህን ክደህ ነበር ...ያኔ አልረፈደም ነበር...''
ገዛህኝ በሮማን ተስፋ ቢስ ንግግር በሽቆ

''እና አሁን ጊዜው ያለፈበት ሃሳብ ነው ልትይኝ ነው?''


''ይቅርታ ገዛህኝ በዚህ ጉዳይ ላይ እኔ ምንም መወሰን አልችልም በእርግጥ እንደ እህታዊ ስሜቴ ሠቢ ቢያንስ ቀጣዩዋ የፍቅር ዘመኗ የተሳካ እንዲሆንላት እመኝላታለሁ::''
በንዴት ከተቀመጠበት ተነሳና ወደ በሩ እያመራ
''...እሱን አንቺ አትወስኚላትም ደግሞ እኔ ገዛህኝነቴን አሳይሻለሁ: በአጭር ጊዜ ውስጥ ወንድምሽ ጋር እንደላክሻት ደርሼበታለሁ ለንደን እንደ እኔ ልቡ የሚያሻውን ለማግኘት ለሚሮጥ ሠው ቅርብ ነው:: እቺህ ዓለም በጣም ጠባብ ነች::''
በሩን በሀይል ዘግቶ ሲወጣ ከውስጥ የሮማን ድምፅ ተሰማ
''...ፍቅር የሚያውቅ ልብ ቢኖርህ እንኳንስ ለንደን እዚሁም ሳትለፋ ታገኛት ነበር::''
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Aug 20, 2006 10:50 am

(-ሃያ ስምንት-)
.
.
.
ዘካሪያስ ግራ ገብቶታል ሠባዊትን ሀሰባት አስፈልገዋለች ሕዋሳቶቹ ሁሉ የእሷን ውህደት ከጅለዋል :: እዚህ ጨለማ ምድር ውስጥ እየተደናበረ ዓመቶችን አነባበረ ሕይወቱን ሁሌም ወድውኃላም ወደፊትም ለማየት ሲሞክር ደብዙ ይጠፋበታ ሁሉም ነገር ጭጋግ ነው መኖር ድካም ነው በነዚህ የፈዘዘ ስንክሳር ውስጥ ሆኖ...ግማሽ ብረሐን ሲንጨለጨልለት ለነፀብራቁም ለጥላውም አልመብቃቱን ሲያውቅ...... በንዲህ ያኮረፈ ስሜት ውስጥ ሲዋዥቅ ፈጣሪ የሸለመውን የሠባዊትን ፍቅር ከምንም በላይ ማሳለፍ አልፈለገም::
ከሁለት ቀናት የስልክ መዘጋጋት በኌላ ዛሬ እሷው መልሳ ደወለችለት::

''ሠቢ..........?''

''ሀይ ዘኪ''

''ሀይ የእኔ ቆንጆ አለሽ ግን?''

''ምን ትሆናለች ብለህ ነበር?''
ትንሽ የመዘጋጋታቸውን መንስሔ ጨረፍ አድርገው አወሩና ማግኘት መፈለጉን ጠየቃት

''አስፈላጊ ነው ዘኪ?''

''ቢያንስ ባለፈው ቃል የገባውልሽ ወንምሽን የማፈላለጉን ጉዳይ ከጎንሽ ሆኜ ላግዝሽ እፈልጋለሁ''
ሲላት ትንሽ አንገራግራ እሺታዋን ነገረችው:: ስልኩን ሲዘጋው ደግሞ ያ ተጨነቅ ያለው ጭንቀታሙ ሀሳቡ ወደ ቫኔሳ ማሰብ ጀመረ ቫኔሳን አስቀይሟታል:: እሷ በመጨረሻው ሰሃት'ንኳን ግልፅነቱን ስትፈልግ 'ሁሉም ነገር አንቺ ባሰብሽው መልኩ ላይሆን ይችላል' ብሎ ሸንግሏትል በዚህ ሃሳቡ ራሱን ሲጠይቅ ምናልባት ቫኒን ላለማጣት ይሆን እያለ ያስባል: ግን አንድ ልብ ነው ያለው::

በማግስቱ ተገናኙ::

ትከሻዋ ላይ ቁጭ ያለው የጃኬቷን ኮፍያዋ እንደበረዳት ሁሉ ወደ አንገቷ እያስጠጋችው ዘኪን አየችው: ስሞ ተቀበላት ፈገግታዋን ሲያይ ውስጡ የማያውቀው ስሜት ሲወረው ተሰማው ፀጉሯን ፍሪዝ አድርጋዋለች ከናፍርቷ ምንም አልተቀቡም በራሳቸው ውበት እንደሚኮሩ ሁሉ የኮራ ፈገግታን ተላብሰዋል::
ሠባዊት ዓይኖቿ ደፍረው ዘካሪያስን የሚያዩት የእርሱ እይታ ወደሌላ ሲሆን ብቻ ነው::

''ሠቢ ዛሬ ሁለት የኢቲዮጲያ ኮሚኒቲ ሄደን ሊረዱን የሚችሉበትን መንገድ እንጠይቃቸዋለን...በተረፍ እዚሁ ለንደን ውስጥ እየታተመ የሚወጣ አንድ የአበሻ መጽሔት አለ ትላንትና እነሱን አናግሬያቸው ነበር ከሁለት ሳምንት በኌላ ለእትመት የሚበቃው መፅሔታቸው ላይ የወንድምሽን ምስል በማውጣት ያፋልጉኝን መልህክት እንዲረዱን ጠይቄያቸው መጠነኛ ፓውንድ ጠይቀውኝ ከፍዬ መጥቼያለሁ::''
አላት ዘካሪያስ: ወደ ለንደን አንደርግራውንድ የባቡር ጣቢያ ይዟት እያመራ

''በጣም አመሰጋናለሁ ዘኪ የከፈልከውን ገንዘብ እሰጥሃለው::''
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው_________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Aug 20, 2006 12:24 pm

.
.
.
አንተነህ ባለፈው በእለተ ኢግዚብሽኑ ላይ ከኤልሳቤት ጋር ያሳለፈው ምርጥ ምሽት ውስጡ ተርቦ የነበረውን ስሜት የመገበበት ነው:: ከጥቂት መግደረደር በኌላ እሺታዋን ነግራው አብረው አመሹ ውስጧን ወዶታል በሚኖርበት ለንደን ከተማ ውስጥ አበሻ ሴት ጋር አነፃጸራት በእርግጥ አንተነህ ማነፃጸርን አይወድም ነበር ሁሉም በራሱ ምክኒያት አለው የሚል መላ ምት አለውና:
አንተነህ ላለፉት አራት ዓመታት በፍቅር የተወዳጃት እንስት አልነበረችም:: ከአራት ዓመታት በፊት ይሳተፍበት የነበረ የስዕል ክበብ ውስጥ አንዲት ብራዚላዊ ይተዋወቃል ውበቷ አስክሮት ነበር ፓናሎፒ ትባላለች:: ቀለሟ እንደነጭ ያልገረጣ እንደጠይምም ያልሆነ ነው: ትከሻዋ ላይ የሚነሠነሠው ጥቁር ጸጉሯ የበዛ ነው የቅንድቧ ቅርጽ የዓይኖቿን ቅድ አንተነህ ሁሌም ሳያያትም እንደፊርማ ሁሉ ይስላት ነበር:: በዚህ ላይ አልጋ ላይ ፈረስ ነች ስለምንም ግድ የላትም ትንሽ ሃሳቧ ወጣ ያለ በመሆኑ ከአንተነህ ጋር የባጥ የቆጡን ስትዘባርቅ እሷም ሳታገኘው ስትቀር ናፍቆት ያንገበግባት ጀመር: አብረ በፍቅር አንድ ዓመት ቆዩ የነበራትን የሥዕል ችሎታና ዕውቀት ከፍ አድርጎላታል::

አንድ ቀን እንዲህ ሆነ
አሁን የሚማርበት የትምሕርት ተቋም ሙሉ የእስኮላር ሺፕ እድሉን ከሁሉም ቁሳዊ አቅርቦት ጭምር እና ከበቂ የኪስ ገንዘብ ጋር እንደተቀበለው የምስራች ደብዳቤ ከተቋሙ ይደርሰዋል ደስታው ደስታዋ ነበርና ወደምትኖርበት ቤት ይገሰግሳል
መጥሪያውን ተጫነው አይሰራም ነበር ስልኩን ለመደወል ከኪሱ ካወጣ በኌላ ውስጡ ምንም ክሬዲት አልነበረውም በሩን ገፋ ሲያደርገው ተከፈተ: ወደውስጥ ገባ ይሔኔ የሚዘገንን ተዕይንቱን ተመለከተ ፓናሎፒ ከራሷ ፆታ ጋር ዕርቃኗን ሆና በስሜት ሰምጣለች ባለወርቃማ ፀጉሯ የፓናሎፒን ዕርቃን ሁሉ በምላሷ እያዳረሰች ጥልቅ ስሜቱ ውስጥ ተዘፍቃልች
ከዚያ በኌላ ሊያያት እንደማይፈልግ ነግሯት ተለያዩ በተለይ እሱ ከበቀለበት መሐበረሰብ ውስጥ ሌዚቢያን ሴትን መወዳጀቱ ዘገነነው .............ይሄንን የፍቅር ታሪኩን ሁሉ ለኤልሳ ነገራት ዛሬ ቤቱ ሆና ኪችን ገብታ ምሳ ልትሰራለት ስትደራገም እዛው ሆኖ የልብስ ማጠቢያ ማሽኑ ላይ ሆኖ ሲጋራውን እያጨሰ ነው::
በእርግጥ በሦሥትና ባራት ቀናት ትውውቅ የዚህን ዓይነት ገደብ ያለፈ መቀራረብ ያልተለመደ ነው: ኤልሳቤት አንተነህን ከዚህ በፊት ፈልጋው እንዳጣችው ሁሉ ነበር የሚመስለው ግን ሁለቱም ስሜት ተጠምተው ነበር:
የለንደን የጾታ መውሀድ የተወሳሰብ ነው አንዱ አንዷን አይምንም አንዷም አንዱን አታምንም ግን ስሜትን የደስታ ያህል ለመጋራት ብዙ መለማመኑ ያለፈበት ነው የተባለ ይመስል እግረ መንገድ ሁሉ መሆኑ ላንዳንዶቹ በጣም ያስቃቸዋል:
ፍቅርስ?
ፍቅርን መለዋወጥ ግን በጣም አድካሚ ነው ልብ ለፍቅር ፍፅሞ አይከፈትም በስደት ጠባሳ ተዥጎርጉሯል: ሤቷ ወንዱን በፍቅር ለመተሳሰር ስታስብ ሌላ የተሻለ ወንድ ማግኘቷን አለማግኘቷን እርግጠኛ መሆን ትፈልጋለች ወንዱም ብዙ ምርጫ እንዳለው በልበ ሙልነት እያሰበ የዛሬ ስሜቱን ብቻ ሽምጥ ይላል::

''አንቱሽ?''
አለችው እንደዚህ የሚጠራው ጆኒ ዘ- ገዳም ብቻ ነው

''ከነገርከኝ ከዛች ብራዚላዊ በኌላ ግን ሌላ ሴት አልሞከርክም?''

''በተለያዩ አጋጣሚዎች አንሶላ የተጋፈፍኳቸው ጥቂት ሤቶች አሉ እንጂ በፍቅር ጓደኝነት ኖ!''

''አበሾች ናቸው?''

''አይደሉም....እዚህ አገር ከመጣው ካበሻ ሴት ጋር በዚህ መልኩ ስቀራረብ ምናልባት አንቺ የመጀመሪያዬ ነሽ''

''ለምን አበሻ አትወድም?''

''አለመውደድ አይደለም ኤልሣ................''
ኤልሳ ቤት እንጀራና ስጋ ገዝታ መጥታ ከቤቷ ቋጥራ ያመጣችውን በርበሬ ወጥ እየሰራችበት ነው የአንተነህ ድስቶች ወጣወጥ እንደናፈቃቸው ሁሉ ቺስስስስስስስስስስ ብለው የቁሌቱን ሽታ ያዳምቃሉ::

''......አንደኛ አበሾች ወደአሉበት ስፋር ባለምሄዴም ነው እነሱም እኔ የምውልበት ስፍራ አይመጡም ታዲያ አበሻ ሴት ፈልጌ የግድ የማልወደውን ያዝማሪ ቤት ጭፈራ አልሄድ...?''

''ምናልበት አንድ ነገር ከፈለግክ ያንን ነገር ለማግኘት ብዙ መስዋትነት ትከፍል የለ?''

''እኔንጃ ኤልሣ እኔ የዚህ አይነት ተፈጥሮ የለኝም ሙሤ የሚባል ጓደኛ አለኝ ባለፈው ኤግዚብሽኔ ላይ ባጋጣሚ ስላልተመቸው በማግስቱ ነበር የመጣው አንቺ አላየሽውም....እና እሱ የአበሻ የሴት ጓደኛ እንዲኖረኝ ብዙ ጊዜ ወዳሉበት አብሬው እንድወጣ ይጋብዘኝ ነበር''

''ማን የሚባል?''
ወጡን ማማሰሏን ትታ ደንግጣ ጠየቀችው

''ሙሤ ምነው ታውቂዋልሽ?''

''ምን ዓይነት ልጅ ነው?''

''ልጅ እንኳን አይደለም አደልት ነው ቅቅቅቅ በጣም ሽቅርቅር ሸበላ.....ምነው ታውቂዋለሽ?''

''ጓደኛህ ነው?''

''አዎ ምነው ታውቂዋለሽ?''
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው__________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Aug 25, 2006 1:53 am

.
.
.
''የእውነት የቅርብ ጓደኛህ ነው?''

''እ እ ........አ_____ዎ ምነው...ነገሪኝ?''

_______________________________በጣም ይቅርታ አንባቢያን እመለሣለሁ::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዝንቦ » Fri Aug 25, 2006 3:43 am

ለምን ቶሎ አትል :twisted: :o
ዝንቦ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Fri Aug 25, 2006 3:29 am
Location: u.s.a

Postby ዋናው » Fri Aug 25, 2006 10:31 pm

.
.
.
''ልቤን ቦጫጭሮት ያቆሠለው እሱ ነው አንቱሽ....''
አንተነህ እንደመገረም ብሎ

''ልብሽ መቁሰሉንም አልነገርሽኝም ነበር ደግሞስ ለምን ?''

''ታሪኩ ትንሽ ረዘም ይላል ለነገሩ አሁን የሱን ስም አንስተህ ራስህ ጀመርከውንጂ ያንተን የፍቅር ሕይወት ከመጠየቄ በኌላ ወደዚህ ታሪክ ልመጣ ነበር...''
አለችው የተደናገጠ ስሜቷን ወደምታበሥለው ምግብ ደብቃው በተለየ ስሜት'ንኳን መዐል ለፈገግታ የሚሰረጉዱት ጉንጮቿ ውበቷን ያፈኩታል::

''ሙሤ ምን አደረገሽ ?''
አላት አንተነህ የሙሤን የእንስት መውደድ በውስጡ እያስታወሰው

''ይቅርታ አንቱሽ የፈለገ ጓደኛህ ቢሆን እሱን ከመዝለፍ ውደውኃላ አልልም::''
አለችው:

''እኔንም ቢሆን የሚያዘልፍ ስራ ከሠራው የሚገባኝን እቀበላለሁ ኤልሣ...''

''ሙሤ ማለት ልክስክስ ነው....''

''ሤትነትሽን ተጠቅሞ ነው የጎዳሽ ?''
.
.
.
ሙሤና ኤልሳ ቤት በንዲህ ሁኔታ ተዋውቀው ነበር
ኤልሳቤት ወደ እንግሊዝ ምድር መጥታ የፖለቲካ ጥገኝነት በጠየቀች በ5ተኛ ወሯ ነበር በድንገት በወጣ የሳይለም አዲስ ሕግ ሣቢያ ከቤት እና ከሚሰጧት ሣምንታዊ ድጎማ የተፈናቀለችው::እዚህ ለንደን ውስጥ ብዙም የምታውቀው ሠው አልነበራትም ባልጠበቀችው መንገድ ሻንጣዋን ይዛ ወደጎዳና እንድታድር ተገደደች ዕምባዋን ያዩ ብሪታኒያ የምታስተዳድራቸው የህግ የቢሮ ሠዎች ያደረጉላት ነገር አልነበረም
በጣም ግራ ተጋባች አብረዋት የተፈናቀሉ ሌሎች የሌላ አገር ሠዎች ነበሩ: ስፍራው ብሪክስተን የሚባል ቦታ ነው ቀኑ ሲጨልምባት የማያልቅ ዕንባዋን አነባች ይሄን ጊዜ ነበር ሙሤ ያገኛት

''አበሻ ነሽ?''
አንገቷን ነቀነቀች በአዎንታ

''ምን ሆነሽ ነው የእኔ እመቤት የምታለቅሽው?''
ነገረችው ስለጉዳይዋ ስለምፈናቀሏ በአበሻነቱ የመርዳት ግዴታ አንዳለበት ነግሯት ከትኝሽ ማባበል በኌላ ይዟት ወደ ቤቱ ወሰዳት: በሚገርም የዋህነት አስተናገዳት
.
.
.
ይቀጥላል::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Aug 27, 2006 11:07 pm

.
.
.
ጉዳይዎቿን እየተከታተለች ሙሤ ዘንድ ስትቀመጥ ሙሤ ያስቀመጣት ቤት ውስጥ አይኖርም ነበር ብቅ እያለ የጎዳደለውን ይሞላላታል: ኤልሣቤት መንገድ ላይ የሚያቃት ሙሤ ስለማንነቷ እና ስለምንነቷ ሳያውቅ የዚህን ያህል መርዳቱ አስገረማት በሚሰጣት ፈገግታና በሚያደርግላት እንክብካቤም ቀስ በቀስ ወደ ፍቅሩ ውስጥ መግባት ጀመረች:: ሙሴ ልክ ልቧን ከፍቶ ያነበበው ይመስል እንደወደደችው አወቀ:: ብዙም ሳይቆዩ ሊያሰጠጋት የቸራትን አልጋ መጋራት ጀመረ: ሽቅርቅርነቱ ያነጋገሩ ለዛ እና ቁመናው ከሠጣት ደግነት ጋር የኤልሣቤት ልብ ለሙሤ ብርግድ ብሎ ተከፈተ:: የቋጠረችውን ሳንቲም እየፈታች ጣፋጭ የሆኑ ምግቦች አብስላ ትጠብቀዋለች አብዛኛው ጊዜ ግን አይመጣም ነበር::
በእንዲህ ሁኔታ 1ወር ከሳምንት ቆዩ:: አንድ ማታ ቀን ሙሤ ስክር ብሎ ከአንዲት የአበሻ ሴት ጋር መጣ ሴቲቷም ሰክራለች:: ኤልሣቤት ደነገጠች የሞቆጣት ያህል የሚቅርብ የፍቅር ትስስር አልነበራቸውምና ታዝባ አየችው:: ሣሎኑ ውስጥ ቲቪ እያየች ነበር:

''እሷ ምንህ ነች?''
አለች ሴቲቷ::ቀጭን ነች የተሰራ ፀጉሯ በላብ ተበታትኖ እንደጉም ቡዝዝ ብሎዋል

''እሷ እኔ ዘንድ እጅ የሰጠች ስደተኛ ነች:''
አላት አቅፏት ሸሚዟን ገፍትረው ያጎጡትን ጡቶቿ እየጨማመቅ

''ምን ትሰራለች?''

''ጥገኝነት ከጠየቀችው አካል ቤኔፊት ትቀበላለች ካጣችም አርፋ ትተኛለች ቅቅቅቅቅ''
የሙሤ ሳቅ የምታውቀው ዓይነት አልመስልሽ አላት::
ሴቷ ስካሯ ዓይኗን ሊጨፍነው እየታገለ...
''አንተ ቤትህ ሌላ ሴት አስቀምጠህ ነውንዴ እኔን ቁም ስቅሌን አብልተህ የምታመጣኝ?''
አለችው::

ሙሴ አባብሎ ወደመኝታ ቤቱ አስገባት: በሩን ከዘጋው በውኌላ ድጋሚ ከፍቶት
''ኤልሢ ይቅርታ ዛሬ መኝታቤቱን ነጥቄሻለሁ:''
አላት

''ምን እየሆንክ ነው ግን?''
አለችው የቲቪውን ሪሞት ይዛ ያቀፈችውን ትራስ በንዴት ጨምቃ

''ምንም ........ገና ልሆን እየገባው ነው ምነው ከፋሽ እንዴ''

''አልገባኝም ሙሤ?''

''አይዞሽ አያልቅም ቅቅቅቅቅቅ''
በሩን ዘጋባት::

ከዚህ ምሽት በኌላ ለንደን ወደሚገኘው የሪፊውጂ ፅሕፈት ቤት ሄዳ እየተከታተለችና የችግሩ ሠለባ ከነበሩት ሌሎች ሠዎች ጋር እዛው በሩ ላይ እያደረች የእንግሊዝ መንግስት ቤት ሰጣት:: ኤልሣቤት የለንደንን ሠዎች መፍራት ጀመረች ሁሉም የእሷን ስቃይ ሊያባብስ መረበሿን ይባስኑን ሊረብሻት የተነሳ ያህል ፈራች ለተከታዩ አንድ ዓመት ሙሉ ራሷን አግላ ትምሕርቷን ትከታተል ጀመር:: ዛሬ በጉብዝናዋ እንግሊዛዊያን የተገረሙባት ተማሪ ነች ስለነ ሙሴ መጥፎነት እያነሳች በውስጧ መገረምን ወይም ማዘንን አትፈልግም ግን አልፎ አልፎ ብቸኝነቱ ሲበዛባት በሃሳቧ ወደ አገሯ ትሸፍታለች ጥላው ወደመጣችው የደመቀ ቤተሰብ ትተዝታለች :
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው____________________________________::

(ኢ-ዘ-ጥልሥም)
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Aug 28, 2006 11:41 pm

.
.
.
(-29-)

ቫኔሳ እየተከዘች አከታትላ ያጨሰችውን የሲጋራ ጉማጆች በመተርኮሻው ላይ አመድ ተፍተው ብታያቸው ጉሮሮዋን ዳበሰች ዛሬ ስሜቷ ተረብሿል:: የሠማችው ዜና ጥሩ ይሆን መጥፎ በውል ለማወቅ ተስኗታላ ደብዳቤው እንኳን ደስ አለህ!!ይል ነበር የዛሬ ወር ገደማ ከዘካሪያስ ጋር የሞሉት የስራ መጠየቅ ፎርም ተቀባይነት አግኝቶ ነው በእሷ አድራሻ የመጣው ዘካሪያስ ባቀረበው የትምሕርቱ ብቃት እና በመረጠው የስራ መስክ ሊቀበሉት ፍቃደኛነታቸውን ነው የገለፁት: የ ቻናል ፎር ቴሌቭዥን ጣቢይ አርማ የሆነው በደብዳቤውና በፖስታው ራስጌ ላይ ሰፍሮዋል :: ደብዳቤውን ይዛ ሳሎኗ ሶፋ መደገፊያ ላይ ቁጭ ብላ እግሯን መቀመጫው ላይ አኑራለች::
ስልኳን አነሣች ቁጥሮቹን ከመታች በኌላ ድጋሚ ትታው ወረወረችና ወደ ኪችን ገብታ የቆርቆሮ ቢራ አመጣች: ስላሳለፈችው የፍቅር ጊዚያት ኣሰበች ጣፋጭ ነበሩ ዘካሪያስ ጥሩ ፍቅር ሰጥቷታል ሁሉ ነገሩ ይመቻታል በመጨረሻ ግን ፍቅሩ ወደሌላ ሄደባት ከመቀበል ሌላ ምንም ማድረግ አልቻለችም ሊሸነግላት ይሁን ቁርጡን ሊነግራት ይሆን ይቅርታ ሊላት ደጋግሞ ቢደውል ስልክ ዳባ ብላው ዘግተዋለች ያስቀመጠላት የድምጽ መልህክት ...እንገናኝ ነበር: ግን መርሳትን መረጠች
እቺን ሁለት ቀን ደግሞ የወሲባዊ ስካሯ ሲቀሰቀስ የቤቱን ዕቃዎች እስከመናድ ደርሳ ነበር::
ደወለ ዘካሪያስ.......ይጠራል......ይጠራል.....ተዘጋ:: ድጋሚ ደወለ ጠራ..... ጠራ......
አነሣችው

''ሀይ ቫኒ አውን'ኮ ሚስድ ኮልሽን ሳየው...?''
ሳታስበው መደወሏን አስታውሳ እያመነታች

''ይቅርታ ተሳስቼ ነው ::
አለችው

''ሠሞኑን ደውየልሽ ነበር መልዕክቴንም ሠምተሽ መልሠሽ አልደወልሽልኝም...ምነው?''
ግራ ተጋባች ቢራዋን ተጎንጭታ ሲጋራውን ማገችና

''እኔጋ መልካም ዜና የያዘ የሥራ ደብዳቤ አለህ አሁን መጥተህ ልትወስድ ትችላለህ?''
አለችው ፀጉሯን ሲጋራ ባሊያዙ ሦስት ጣቶቿ እየፈተለች ወደ ሶፋው ዓይኖቿን ተክላ

''የምን ደብዳቤ ቫኒ...?''

''ቻናል ፎር የላክንላቸው የስራ ማመልከቻ ጥሩ ዜና ይዞ ተመልሷል ዘካር''

''ዕውነትሽን ነው?''

''ዕዕ...''

''ቤት ነሽ አሁን ልምጣ?''

ስልኩን ዘግታው በጀርባዋ ሶፋው ላይ ተኛች ዓይኖቿን ጨፈነች ስሜቷ ከውስጥ ይጨፍራል ...የትላንትና የአባቷ የስልክ ምልልስ ጆሮዋ ላይ ያቃጭላል::

''የኔ ልጅ ለንደን ውስጥ ከጥቁር ማሕበረሰብ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ እንግሊዛዊያን በወንጀልና በአጓጉል ሱሶች ተዘፍቀው የተከበረችው እንግሊዝ የማታውቀውን ቅይጥ ሕብረተሰብ እያሰፋች እና ኑሮዋ እንደአሜሪካ ታሪክና ባሕል አልባ ሊሆን እየተቃረበ ነው የሚል ፅሑፍ ጋዜጣ ላይ አንብቤ ነው የደወልኩልሽ .............''

እጇን ተመለከተች ከዛም ሶፋው ላይ አኖረችው ሶፋው ጥቁር ነው እጇ ነጭ ነው ያንዱ መጥቆር ያንዱን መንጣት ያጎሎዋል
''እኔ ነጭ ነኝ ዘካር ጥቁር ነው ሁለታችን ስንዋሀድ የሁለትነት ልዩነታችን ይሠፋል ግን ሁለታችንም ሠዎች ነን ማናችንም የበላይ ማናችንም የበታች አይደለንም: እኔ በጥቁር የደረሠብኝ ጠባሣ የለብኝም ከቤተሰቦቼ ማሽሟጠጥ በቀር እነሱ ደግሞ ወልደው ማሳደግ ብቻ ነው አላፊነታቸው .....ግን'ኮ በጥቁሩም ዘንድ ነጭ መገለሉ የሠፋ ነው...? ለምን...? ''
ሳቀች ቀና ብላ የቤቷ ግድግዳ ላይ የተሠቀለውን የቦብማርሊ ምስል አየች ብዙ ብዙ የዕኩልነት አቢዮተኛነቱን በግጥሞቹ አድርጎ አቀንቅኗል
''የሠው ልጅ ሞኝ ነው:''
አለች
''............እቺህ አለም ውስጥ ምን ያህል እንቆያለን?''

ከረጅም የራሷ ተመስጦ እና ትካዜ በኌላ የበሯ ደውል አቃጨለ:: ፀጉሯ ተንጨባሯል ለማስተካከል ሞከረች
ከፈተች ዘካሪያስ በዝናብ የረሰረሰ ጃኬቱን እያወለቀ የፍርሀት ሠላምታ አቀበላት ያገሯን ፈገግታ ሰጥታው በሩን ለቃው ወደሶፋዋ አመራች::
ስታየው የወሲብ ስሜቷ ተቀሰቀሰ ቀና ብላ አይታው ዓይኖቿ ከተርገበገቡ ሊያውቅባት ሆነ አንገቷን ወደ ሶፋው ደፍታ ሌላ ሲጋራ ለኮሠች

''ቤትሽ የጠራሽኝ ስታጨሺ እናዳይሽ ነው የእኔ ፍቅር?''

''በጣም ስቱፒድ መሆንክን ታውቃለህ ግን?''

''አዎ አውቃለሁ ቫኒ''

''አትየኝ ደግሞ .....''
ያገሬውን ነውርኛ ስድቧን አዘነበችበት
ዕንባዋ ሲተናነቃት ዕና በእልህ ውስጧ ሲርድ ተነስቶ አቀፋት ለአመል መነጫጭቃው ደረቱ ስር ሆና አነባች:: ጠረኑን ሳግ ባንፈቀፈቃት ትንፋጓ ስር ሆና ብትምገው ለአፍታ በንዴት ሳቢያ ጋብ ብሎ የነበረ ስሜቷ አሻቀበ:: ጣቶቿ ጆሮ ግንዱን ሲፈትሉ እና ጀርባውን ሲቧጥጡ ዘካሪያስ አዝማሚያዋ ገባውና ከንፈሯን በከንፈሩ ፈለጋቸው: ከዛም ወእሶፋው በስሜት ስበት ተደፉ ከጥቂት ማቃሰት በኌላ ዘካሪያስ እምር ብሎ ተነሣ ድንገት አንድ ነገር እንዳስታወሰ ሁሉ
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed Aug 30, 2006 9:59 pm

ሠላም ውድ አንባቢያን
ጥሎብኝ እቺህ ድርሰቴ ካንደኛው ገፅ ስትጠፋ ደስ አይለኝም::
ነገ ልመለስ ከይቅርታ ጋር?

________________________ዋናው::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Sep 01, 2006 9:30 pm

.
.
.
በ''ምነው?'' ዓይነት አስተያየት አፈጠጠች ቫኔሣ ስሜት ያነፈረ ትንፋሿ ዓይኗን እያስለመለመች

''የምናገረው ቢኖርም አፍ ግን የለኝም ቫኒ...''

ሠሃቱ የፍቅርና የመወቃቀስ አልነበረምና ዳግም ወደሶፋው ተደፉ: ሶፋው ሳቀ አቃሰተ::

_________________________________________

ዘካሪያስ ውስጡ በሚያሳስቡት የሃሳቦች ጥርቅም ግራ ተጋብቶዋል በጨፈገገው የዳመናው ግላጭ ስር ብቅ እንደምትለው የለንደን ውድ ፀሐይ አልፎ አልፎ ስሜቱን በቢራዎች ጎርፍ ሞቅታ ኪልኪላ ይለዋል ...ኪሊኪላው ሲያይል ውስጥን ይፈነቅል ይሆንና በለሆሳስ አንደበት ያወጋል

''ዘኪ ሣታስበው የፍቅር ቁማርተኛ ሆንክ አይደል...?''
አለው አንተነህ የጠቀለለውን ሲጋራ መምላሱ ልሶ ካጣበቀ በኌላ እሱም ዓይኖቹ መቀላላት ጀማምረዋሉ

''ምን ይደረግ ብለህ ነው ፒካሶ ሕይወት ራሷ ቁማር ነች የመበላላቱ ሚስጥርም ያው የሕይወትህ ስኬትና መቃናት ነው::''

''ምርጥ አባባል ነው ቅቅቅቅ ዘኪ'ኮ የምትገርመኝ በማንበብ የማታከማቻቸውን ዕውቀቶች የምታወጣቸው ውሀ ሲያሳስቅህ ብቻ ነው...ለዚህ ነው አንተን ፐብ ሳገኝህ ስካር የሚያምረኝ...ታውቃለህ መስከርን ማንም አይጠላም መጠጣትን ነው እንጂ...''

''ስካር ፋይልህን አገላብጦ ያተራምሳል ...በማግስቱ ግን ያ ፋይል ስታስታውሰው ይደብራል ፒካሶ...''

ሁለቱ ጓደኞች ብዝሁን ጊዜ ሲገናኙ በራሳቸው የመግባባት አቋም እያወሩ ይቆያሉ:

''ኤልሣበት እንዴት ነች ፒካሶ?''

''በሕይወትህ ዘንድሮ ቁምነገር ሠራህ ዘኪ ...እቺህን የመሰለች ብርቅዬ እንስት ከየት ፈልቅቀህ እንዳመጣሀት....?''

''እቺህ አጋጣሚ ናታ...ፒካሦ''

''ደስ የምትል ልጅ ናት አጋታሚ ስትል መቼም ካንተ የምደብቅህ የለኝም አይደል ...ለነገሩ እሷም ሚስጥር ብላ አይደለም ያወራችኝ ኤልሢ ማለት ሙሴ ኸርት ያደረጋት ልጅ ነች አሳዛኝ ታሪኳን አጫውታኝ ያንን የሰራት ሙሴ እንደሆነ ነገረችኝ...''

''እሱ...ልጅ ግን ፒካሶ ስሌ'ን አናግረነው ትንሽ ብንመክረው የሚመለስ አይመስልህም የሴት እንባ መጥፎ ነው ''
አለ ዘካሪያስ የሙሴ የእንስት በደለኛነት እያወሳ

''ሱስ ሆነበት'አውንማ....ዘኪ''

''እሷ ግን ጓደኛችን ነው ስትላት ምን አለችህ?''

''የምትገርምህ ኤልሣ....ውስጧ በጣም ጠንካራ ነው በእሱ ደደብነት ነው ያዘነችው እንጂ ...''
በሙሴ ስነልቦናዊ ችግር ትንሽ አወሩና ውስጡ አንድ የመሸገው በቀል ስለመኖሩ ደምድመው ርሕስ ቀየሩ::

''.....እስቲ ባለንጀራዬ....ላዲሱ የስራህ መሣካት ጥዋችንን እናንሳ ''
አለና አንተነህ ብርጭቆውን አጋጨው

ሠው ሲደሰት ደስታውን በብቅል አጅቦ ያዳምቃል...ባንድ ስኬት ላይ'ም ለመልካም መሳካት ተብሎ ጥዋዉን ያነሳል...ውስጥ ሲረበሽና ሃሳብ ተነባብሮ ሆድ ሲንቦጫቦጭ አሁንም መለኪያውን ያነሳል::
.
.
.
ዋናው________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Sep 04, 2006 11:08 pm

.
.
.
ትላንትና ማታ እሕቱ ሮማን ከአዲሳበባ ደውላ ከጥቂት የናፍቆት ሠላምታዎች በኌላ ስለሠባዊት ጠየቀችው: ባለፈው በደብዳቤ ግልፅ ያልሆነለትን ሁሉ ጠየቃት:: ቢችል ፀባያዋና ምግባሯ ጥሩ በመሆኗ ከእርሷ ጋር ያለውን ቅርርብ እንዲገፋበት መከረችው ::የእሕታዊው ምኞቷን ቢቀበልም ጠቃሚ ነች ብላ ያሳሰበችበት ምክኒያት ደጋግሞ ቢጠይቃት አገር ሁሉ የሚቋምጥለት ሀብቷን አወጋችው::
ዘካሪያስ የሠባዊትን በቂ ሀብት ስለሰማ አይደለም ግን የወደዳት ቀድሞ ማንነቷን አጣርቶ ሳያውቀውም ሠባዊት ልቡ ውስጥ ቦታ ስታመቻች ሠፊ ስፍራ አመቻችቶላታል::

''አንድ ገዛህኝ የሚባል ባለጌ እጮኛ ነበራት ለነገሩ ከተወችው ቆየች...ልጁ ግን በጣም ባለጌ ነው አፈላልጎ ሲያጣት በጣም በሽቋል... በቅርቡም ወደ ለንደን እሷን ፍለጋ እንደሚሄድ ቢሮዬ ድረሰ መጥቶ ነው ዝቶብኝ የነገረኝ ተጠንቀቅ::''
ዘካሪያስ ሳቀና
''አይ ሮሚ ...ለንደን ቄራ መሰለው ወይስ ጨርቆስ የሚዝተው...?''
ምንም ሊያደርግ እንደማይችል አሳምኗት ስልኩን ዘጉ::
ዛሬ ዘካሪያስ ስራ ለመጀመር ቃለ መጠይቅ ያደርጋል በጠዋት ተነስቶ አንድ ማግ/ሢኒ ቡና ሲጠጣ ነቃና ስለቀኑ ማሰብ ጀመረ:: ትከሻው ሡፍ ይቀበላል አንገቱ ላይ ክራባት ሲያጠልቅ ፍፁም ይቀየራል: አንቱታነትን የሚጋብዝ ሞገስ ይላበሳል ደንዳና ሠውነቱ ይጎላና የሚመለከቱትን ዓይን ያንከራትታል::
እግሩን አነባብሮ በሞባይል ስልኩ ሰዓቱን ገልመጥ አድርጎ እጁ ላይ ያጠለቃትን የወርቅ ሠንሠለት ነቅንቆ ወደ እይታው ሳባትና ሢጋራውን ለኮሠ:: ወዲያው ስልኩ ተንጫረረች

''ዘኪ...?''
የሠባዊት ድምፅ ነበር

''ሀይ ደህና አደርክ ...ለዛሬው ኢንተርቪህ ጉድ ላክ ልልህ ነው የደወልኩት.....''
አለችው ሠባዊት በወፍ ድምጿ እያዜመችለት

''ቴንኪው የእኔ ቆንጆ''
ያያት ይመስል ተቅለሰለሰ

''ዘኪ አንድ ነገር ልነግርህ ፈልጌ ነበር.......?''
አለች ሠባዊት የሚያዜመው ድምጿ ላንዳች ዜና ይሁን ወሬ ዜማውን እየቀየረ...ዘካሪያስ ስለ ነገሩ በመጓጓት..

''ምን የእኔ ቆንጆ.................?''
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው___________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Sep 08, 2006 12:04 am

.
.
.
ሠባዊት እንደፈራች ሁሉ በስልኩ የሚቆራረጠው ድምጿ ለዘካሪያስ አጓጓው::

''በመጀመሪያ ለባለፈው ትብብርህ በጣም አመሰግናለው ትላንትና ከኢትዮጲያ ኮሚኒቲ ተደውሎልኝ ነበር አንድ ወንድሜን የሚያውቀው ሠው ማግኘታቸውን ነገሩኝ ከዛሬ አመት ተኩል በፊት በምስራቅ ለንደን ይኖር እንደነበርና ...ከተቻለ አድራሻውና ስልኩ የሚገኝበት መንገድ እንደሚፈልግ ጠቋሚው ቃል መግባቱን ነገሩኝ....ደስ አይልም...ዘኪ'ዬ?''

''ሰቢ ነግሬሻለሁ እኮ ተስፋሽ እንደሚለመልም ...አየሽ እኔ ነብይ ነኝ ሁሉም ነገር ፍንትው ብሎ ይታየኛል''

''ጉረኛ.....ስማ ዘኪ ግን ከመሄዴ በፊት የማገኘው ይመስልካል?''

''እሱን ለእኔ ተዪው ሰቢ...''

ስልኩን በመልካም ምኞቷ አሳርጋ ከዘጋች በኌላ ፈገግ ብላ ስለ ዘካሪያስ ማስብ ጀመረች: የገዛህኝ የፍቅር ጠባሳ ውስጧ ይሻክራታል በጤነኛ ሀሳብ ስታሰላው ወደፊት አንድ የራሷ ሠው ያስፈልጋታል...ያ ሰው ዘኪ ይሆን...???????ብላ ታስባለች ያለጥርጥር ውስጧ እንደተቀበለው አምናለች እዚህ የተውሶ አየር ውስጥ ሆና የነገ ተስፍዋን ስትናፍቅ ከጎኗ ሆኖ ያባበላት ተስፋዋን ያበራላት ዘኪ ነበር:: ለደንቡ ብታመሰግነውም ...ለግብሩ ሲል ደግሞ ልቧ ሸፈተለት....ቫኔሣን ታስባታለች ያለችበት አገርም ሆነ አገሩ ያግባባትን ዘኪን ጭምር የእርሷ ነው:: አንዳች ስሜቷ በራሱ መንሰላሰል ውህደት ሊቀማት ቢዳዳም እሷ ባሰበችው መልኩ ምን ያህል መብቱ እንዳላትም አታውቅም::
ከወደአገርቤት ከጓደኛዋ ሮማን ጋር ሰሞኑን ስልክ ስታወራ
''አኒቺ ጉረኛ እኔ እንድሆን አማችነቱን እፈልገዋለው እንጂ አልጠላውም ...ምነው ደበቅሽኝ?''
አለቻት ከወንድሟ መስማቷን በመጠቆም: ሠባዊት አፈረችና ትንፋሽ የበዛበት ፈገግታ እያሰማቻት

''ሮሚ...ደብቄሽ አይደለም'ኮ ስመጣ ሁሉንም ታሪክ አወጋሻለው ብዬ'ንጂ''

''ዝምበይ ጉረኛ እኔስ እድሜ ለወንድሜ ነገረኝ ይብላኝ ላንቺ ......ግን እንዴት ናችሁ?''

''እንዴ ገና'ኮ ምኑንም አሊያዝነውም ሮሚ...ምነው ታውቂ የለም'ንዴ ነጭ ሚስት እንዳለው ራስሽ ነግረሽኝ..''

''እሷን ተያት ሁሉንም አውቃለሁ ድሮም የእኔ ወንድም አጠገቡ ጥሩ ያበሻ ሴት ስላላገኘ ነው እሷ ጋር የሄደው ይልቅ አደራ ወንድሜን ተንከባከቢልኝ::''

ሠባዊት እየተሽኮረመመች ርህስ አስቀየረቻት ግን ርህሱ ብዙም ስለሷ አልሸሸም ስለ ገዛሕኝ ዛቻ በረጅሙ ተንትና አስረዳቻት::
.
.
.

ይቀጥላል

ዋናው_____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 2 guests