እጦተ-ልብ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Wed Aug 30, 2006 4:14 pm

ከዚህ በመነሳት የሰው ልጅ የተፈጥሮ የበላይነት ምንጭ የስነ-ወሲብ ጥበብ ነው ሲል ደምድሞዋል::ወደ ራሴ ልመልሳችሁና እያንዳንዱ ሰው በድብቅ የሚፈጽመው ወሲብ ስለራሱ ትቶ የሰውን ጉዋዳ ለማሰስ ሲጥር ይታያል::ለምሳሌ ጎረቤት የሆነ ሰው ጥቂት የእርካታ ድምጾችን ቢያሰማ ምን አይነት ወሲብ እየተፈጸመ ይሆን እንዴት እየተሳሳሙ ነው ስንል እንቅልፍ ላይወስደን ሁሉ ይችላል::የሰው ልጅ ስለወሲብ የመስማትና የእማየት ጉጉቱ የሚበረታው ህይወቱ ያለወሲባዊ ተራክቦ ላንዳፍታም ቢሆን ደስታ አልባ እንደምትሆን ስለሚገነዘብ ነው::በአንድ ወቅት ከአንድ ፊሎሶፊ አስተማሪ ጋር በተገናኘሁበት ወቅት የሰው ልጅ ወሲብን የሚጀምረው ካደገ በሁዋላ ሳይሆን ከናቱ ጡት ሳይላቀቅ ነው::ለምሳሌ ጡትዋን በመመጥመጥ ከፍ እያለ በሄደ ቁጥር እቃ በመስበር እርካታን ያገኛል ብሎኝ ነበር::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed Aug 30, 2006 4:21 pm

በሲግመን ፍሮይድ የስነ ልቦና ትንተና ንድፈ ሀሳብ ሲተነተንየሰው ልጅ ህሊና ከፍትወተ ስጋ ጋር በተቆራኘ በሶስት አበይት ክፍሎች ይከፈላል::
ኢድ;ሱፐር ኢጎ ና ኢጎ በመባል ይከፈላሉ::አንዱ ያለሌላው ላይኖር ይችላል::የየደቂቃው ገጠመኞችን በህሊናችን ከቀረጽነው የተቃራኒ ጾታ እርቃነ ምስል ጋር ሲላተም ተፈጥሯዊ የፍትወት ስሜታችን ይላላል::ለዚህ ምክኒያቱ ሊቢዶ የተሰኘው በሰውነታችን ውስጥ ያለው ኢንዛየም ነው::ፍሮይድ ይሄንን ኢንዛየም ሰክሽዋል ኢነርጂ ይለዋል::ሶስቱን አብያተ ክፍሎች በአጭሩ እንመልከት::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed Aug 30, 2006 4:26 pm

ኢድ

በዚህ ስሜት የሚመራው የህሊናችን ክፍል ከምንም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ለስሜት እርካታ ነው::በአካባቢው ያለ ነገር ምንም አይመስለውም::ያሰበው ወይም የተመለከተውን ለመፈጸም ምንም አያግደውም::ግቡ የስሜትን እርካታው በመሆኑ ለመፈጸም ቅጽበት አያስፈራውም::ለምሳሌ አጭር ቀሚስ አድርጋ የተመለከታትን ጉብል ምንም ያህል ሰው አጠገቡ ቢቀመጥ እግሮችሽ ያምራል ከማለት አይመለስም::ያ ወደፊት እንደሚያንደረድረው ያውቃልና::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed Aug 30, 2006 4:33 pm

ሱፐር ኢጎ

ህሊናችን በሱፐር ኢጎ መመራት ሲጀምር በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍ ያለ ዋጋ ለሚሰጣቸው ነገሮች ቅድሚያ ይሰጣል::እንደ ኢድ አያፋትንም::በነውርነት የተፈረጁትን የማህበረሰቡን እሴቶች አይዳፈርም::ስሜቱ ቢፈታተነውም እንኩዋን ለአካባቢያዊ ሁኔታዎች ተገጂ ነው::ልቡ ቢፈልግም ስሜቱን አምቆ ፍጹም ያልፈለገ ለመምሰል ይጥራል::ለምሳሌ ይህን ጡትዋን የሚያጋልጥ ልብስ መልበሱዋ ምን መሆንዋ ነው?አጭር ቀሚስ ማድረጉዋንስ አታፍርም?ግን እኮ አምላክ አስተካክሎ ነው የፈጠራት::አሁን አጠገብዋ ያለው ሰውዬ ቢያየኝስ አቤት ብተዋወቃት ይህን ውብ ከንፈሩዋን እጎርሰው ነበር::ብጠቅሳት ምን ትለኛለች?ታዋርደኝ ይሆን?የሚሉ ከማህበረሰቡ ላለማፈንገጥ የሚያደርገው የውስጥ ክርክር ያህል ይሆናል::ያን የተከራከረበትን ወሲባዊ ተራክቦ ባገኘው አጋጣሚ ማድረግ ይሻል::ግን ባህላዊ ወግ ጠፍንጎ ይዞታል::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed Aug 30, 2006 4:38 pm

ኢጎ

ይህ የህሊናችን ክፍል ለሽምግልና የተቀመጠ እስኪመስለን ድረስ አስታራቂ ነገሮችን ሲያነሱ ይታያል::የኢጎ ቀዳሚ ግብ እንደ ኢድ እርካታ አልያም እንደ ሱፐር ኢጎ ማህበራዊ ነውር አይደለም::እጎ ምክኒያታዊ ነው::ለሚያደርገው ነገር ሁሉ በቂ ምክንያት ይፈልጋል::አንድ ነገር ለማድረግ ሲሻ ለምን በማለት ይጠይቃል::ይሄ ግን የሁሉም ሰው ችሎታ ነው ብሎ ፍሮይድ አያምንም::

ሲግመንድ ፍሮይድ ግንቦት 6 1858 እ.ኤ.አ ሞንሮቢያ ውስጥ ተወለደ::መስከረም 23,1939እ.ኤ.አ ለንደን ውስጥ አረፈ::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed Aug 30, 2006 5:05 pm

ስለዚህ የ እጦተ-ልብ ተከታታዮች ጽሁፉ እንዲገፋ አስተያየት እፈልጋለሁ ማለት ልቀጥለው ወይስ ልተወው?
ከጻፍኩ በማህበራዊ ህይወት ዙርያ ግልጽነቴን መቀጠሌ ስለማይቀር ምርጫው የናንተ ነው.....አብላጫውን አይቼ እስከ ግቡ አደርሰዋለሁ.

አክባሪያችሁ ሾተል ነኝ
ከእጦተ-ልብ የአውነት ጠቁዋሚ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby እድላዊት » Thu Aug 31, 2006 7:13 am

:
ለምን የሴት ልጅ ሆነ የወንድ ልጅ ገላ እንደወረደ አይገለጽም::[/quote]ቃላትን እንደወረደ መጠቀም መች ጋሽ ስብሀትንስመች ጎሽ አስባለው ሾተልዬ ለኝኣ አገር ድንገት ያንተ የልጅ ልጅ ቃላትን እንደወረደ ማስፈር ይቀለው ይሆናል ትንሽ ባህልና ካልቸር የሚይዘው ህዝብ ከመጋረጃው በስተጀርባ ነው ህምምም

መልካሙን ሁሉ ላንተ

እድል
hany
እድላዊት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 283
Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
Location: united states

Postby Misale » Fri Sep 01, 2006 6:01 pm

እኔ እንደሚመስለኝ ትረካህ የcontemporary ኢትዮጽያዊት ሴቶችን mind set እና internal coflict ያሳያል. ግሩም ማህበረሰቢያዊ ሂስ እና አስተዉሎት ነው. በምታገኘው አስተያየት ተስፋ ቆርጠህ እንደማታቋርጠው ተስፋዬ ነው.

የረዝም ግዜ ተከታታይ እና የመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ
Misale
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Fri Sep 01, 2006 5:48 pm

Postby sleepless girl » Tue Sep 05, 2006 1:16 am

ሾተል........................

የሰው ልጅ መልክ እንደሚለያይ ሁሉ
አስተሳሰባችን...አመለካከታችንና ጸባያችንም በዛው ልክ ይለያያል:: እርግጠኛ በሲግመንድ ፍሮይድ ፊሎዞፊ የምታምን
ከሆነ በዚህም ሀሳብ እንደምትስማማ::
የፈለከውን ጽሁፍ ጻፍ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ አስተያየት ይኖረዋል..ገንቢም ይሁን ተስፋ የሚያስቆርጥ::

ጽሁፍህን ከመጀመርህ በፊት ባይሆን የጽሁፍህን ይዘት
ባጭሩ (pg14, pg, graphic......)ምናምን እያልክ ብትገልጽ
ምናልባት ዲስከሬጅ የሚያደርጉ አስተያየቶች ላይኖሩ ይችሉ ነበር:;

አሁን ግን ጽሁፍህን ጀምረህ መተው ማለት....ልጅን ወልዶ ዝም ብሎ መጣል እንደማለት ነው የማየው:: "ልቦለድ የገሀዱ አለም ነጸብራቅ ነው" ይባልስ የለ??? ግልጹን መጻፍ ምን ያስወነጅላል????

እኔም " ቀጥልበት" ከሚሉት ወገን ነኝና ምርጫው ያንተው ነው::!!!!!!!!!!!!!!! :roll: :roll:

ቅር የተሰኘችብህ አድናቂ
:cry:
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Postby ሾተል » Thu Apr 05, 2007 1:19 pm

ሾተል በድሮ ጊዜ ንፋስ ከባለጌዎች ጋር ሳይቀላቅለው....
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:08 pm

እኛ ሾተል ስንሆን ዝም ብለን አይደለም...አላስፈላጊ ባህሎችን ለማስወገድ,ስነጽሁፋችንን ባለችን ጥቂት ችሎታ አንድ እርምጃ ለማራመድ,እውነትን እያሰስን ለማሳወቅ ወዘተ ሲሆን በለላው ደግሞ ጠላት ሲመጣ ለመመከትም ጭምር ነው::ስለዚህ በነጻ የማሰባችን መብት ከምንወደው ና ከምንጨነቅለት ህዝባችን ምንም ተቀባይነት አጥቶ ቢጨቆንም ወደዱም ጠሉም መጅገሮቻችንን በተለያየ አይነት ቅርጽና መልክ እየመጣን እውነትን እንደኮሶ በግድ እንግታቸዋለን::ደግሞ ይህ ይበቃል ብለን ስለማናስብ በቃ እንደወቅቱና ሙዳችን እንደእስስት መልካችንን እየቀያየርንና እያሰብን ለህዝባችን የምናደርገውን ነገር ለማድረግ ጊዜአችንን ያለክፍያ መስዋእት እናደርጋለን::


ሾተልና ክብርነቱ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:13 pm

ሁለት የዚን መነኩሳት ወደገዳማቸው ሲመለሱ መንገድ ላይ ስላጋጠማቸው የሚነገር ታሪክ አለ::መነኩሳቱ የፊት የፊታቸውን እየሄዱ ሸምገል ያለው መነኩሴ ወደወንዝ ይወርዳል::በወንዙ ዳር ለመሻገር የፈራች ቆንጆ ወጣት ሴት ቆማ ይመለከታል::ሽማግሌው መነኩሴ ደንብሮ ትቷት ወንዙን በፍጥነት ይሻገራል::ማዶ ሆኖ ወደሁዋላ ሲመለከት ወጣቱ መነኩሴ ሴቲቱን በክንዶቹ አቅፎ ወንዙን ሲያሻግራት ያያል::ሁለቱ መነኩሳት አጠገብ ላጠገብ ሆነው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ::ከገዳሙ የውጭ በራፍ ላይ እንደደረሱ ሽባግሌው መነኩሴ ልጅ እግሩን መነኩሴ "መልካም አላደረክህም::ህግ ተላልፈሀል::እኛ መነኩሳት ሴትን እንነካ ዘንድ አልተፈቀደልንም::"ይለዋል::ወጣቱም መነኩሴ መልሶ; "እኔ እኮ ሴቲቱን ከወንዙ ወዲህ ትቻት መጥቻለሁ:አንተ አሁንም እንደታቀፍካት ነህ?"አለው::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:15 pm

ኦሾ

ስሜታችንን አምቀን መያዝ ወይም መግለጽ ላይ ምርጫችን የትኛው ሊሆን ይገባል?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:18 pm

ጉልበቱን ወይም ስሜቱን ለመጨቆን የሚችል የሰው ልጅ ብቻ ነው::ወደ ሌላ ነገር ለመቀየር የሚችለው የሰው ልጅ ነው::ሌሎች ፍጡራን መጨቆንም ሆነ መቀየር አይችሉም::ጭቆናና ወደሌላ ነገር መለወጥ የሰው ልጅ በራሱ ላይ ሊያደርጋቸው የሚቻላቸው የአንድ ክስተት ሁለት ሁኔታዎች ወይም ገጽታዎች ናቸው::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:21 pm

ዛፎች ይኖራሉ:እንስሶችም,አእዋፋትም ይኖራሉ::ነገር ግን የኑሯቸው አካል ከመሆን በስተቀር ስለ ህልውናቸው ምንም ነገር ማድረግ አይችሉም::ከማንነታቸው ሊወጡ አይችሉም::አድራጊዎች ለመሆን አይቻላቸውም::ከስሜታቸው ወይም ከጉልበታቸው ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ስላላቸው እራሳቸውን ነጥለው ማውጣት አይችሉም::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests