እጦተ-ልብ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:24 pm

የሰው ልጅ ይህንን ማድረግ ይችላል::ራሱን ከርቀት ሆኖ ማየት ይችላል::ጉልበቱን ከራሱ እንደተለየ አድርጎ ከርቀት ለመመልከት ይችላል::እናም ስሜቱን መጨቆንም ሆነ መቀየር ይችላል ማለት ነው::ጭቆና ማለት በተፈጥሮ የተሰጠንን ጉልበትና ስሜት ተፈጥሯዊ መልካቸውን እንዳይይዙና እንዳይገልጡ መደበቅ ነው::መለወጥ ማለት የተፈጥሮን ጉልበት ወይም ስሜት ወደ ሌላ አቅጣጫ መቀየር ነው::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:29 pm

ለምሳለ የወሲብ ስሜት አለ::ስለ ወሲብ ስሜት ሲነሳ እንድንሸማቀቅ ወይም እንድናፍር የሚያደርገን ነገር አለ::ይህ የአፍረተ ስሜት ህብረተሰቡ የሚያሳፍር ነገር አድርጎ ስላስተማረህ ብቻ የተፈጠረ ነገር አይደለም::በአለም ዙሪያ ብዙ አይነት ማህበረሰብ ኖሯል::አሁንም ይገኛል::ነገር ግን የየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል ወሲብን በቀላሉ ያየው የለም::በወሲብ መሰረታዊ ክስተት ውስጥ የሚያሸማቅቃችሁና የጥፋተኝነት ስሜት የሚፈጥርባችሁ ነገር አለ::ስለወሲብ የስነምግባር ስብከት እንኩዋን ባጸሙም ነጻ የማያደርጋችሁ ነገር አለ::ይህ ስሜት ምንድነው?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:35 pm

ለምሳሌ የወሲብ ስሜት አለ::ስለ ወሲብ ስሜት ሲነሳ እንድንሸማቀቅ ወይም እንድናፍር የሚያደርገን ነገር አለ::ይህ የአፍረተ ስሜት ህብረተሰቡ የሚያሳፍር ነገር አድርጎ ስላስተማረህ ብቻ የተፈጠረ ነገር አይደለም::በአለም ዙሪያ ብዙ አይነት ማህበረሰብ ኖሯል::አሁንም ይገኛል::ነገር ግን የየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል ወሲብን በቀላሉ ያየው የለም::በወሲብ መሰረታዊ ክስተት ውስጥ የሚያሸማቅቃችሁና የጥፋተኝነት ስሜት የሚፈጥርባችሁ ነገር አለ::ስለወሲብ የስነምግባር ስብከት እንኩዋን ባትሰሙም ነጻ የማያደርጋችሁ ነገር አለ::ይህ ስሜት ምንድነው?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:41 pm

በመጀመርያ ደረጃ ወሲብ ጥገኝነታችሁን ያሳያል::ለናንተ ደስታ ሌላ ሰው እንደሚያስፈልግ ያሳያችሁዋል::ሌላ ሰው ከሌለ ደስታው ሊገኝ አይችልም::እና ራስን መቻልህ ቀርቶ ሌላ ሰው ላይ ጥገኛ ትሆናለህ::ይህ ደግሞ ለራስህ ያለህን አመለካከት ይሸረሽራል::በመሆኑም የአንድ ሰው ራስ ወዳድነት በጨመረ ቁጥር ከወሲብ ጋር ያለው ተቃርኖም የዛኑ ያህል ይጨምራል::ራስ ወዳድነቱ ከወሲብ ጋር ተቃርኖ ይፈጥርበታል::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:48 pm

መነኩሴዎች የምትሉዋቸው የወሲብ ጠላቶች ናቸው::ጠላት የሆኑት ግን ፍትወተ ስጋ መጥፎ ሆኖ ሳይሆን ከራስ ወዳድነታቸው የመነጨ ነው::ሌላው ላይ ጥገኛ መሆንንና አንዳች ነገርን ከሌላ ሰው መለመንን ጭንቅላታቸው ሊቀበለው የሚችለው ነገር አይደለም::በሁለተኛ ደረጃ ስለ ፍትወተ ስጋ ወይም ወሲብ በሚወራበት ጊዜ ለመስማት አለመፈለግም አለ::ለዚህ ደግሞ ምክንያት አለው::በተቃራኒው ጾታ ተቀባይነትን ላታገኝ ትችላለህ::በዚህ ክስተት ውስጥ ተቀባይነትን ለማግኘትህና ላለማግኘትህ እርግጠኛ የምትሆንበት ነገር የለም::ትልቁ የተቀባይነት የማጣት ስሜትም አንድን ሰው ለፍቅር ቀርባችሁ ጥያቄአችሁ ወድቅ ሲደረግ የሚመጣ ነው::ተፈላጊነትን ማጣት ደግሞ ፍርሀት ስለሚፈጥር ውስጥህ ያለው በራስ የመታበይ ስሜትህ ድጋሚ ከመሞከር ቢቀር ይሻላል ይላል::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 3:59 pm

ከጥገኝነት ካለመፈለግና የተተወ ከመሆን ስጋቶች እንዲሁም አጋጣሚዎችም የሚብስ ነገር አለ::በፈቃደ ስጋ ተራክቦ ጊዜ እንደእንስሳ ትሆናላችሁ::ይህም በራሱ የራስ ወዳድነትን ስሜት ይጎዳል::ብክንያቱም በናንተና ፍቅር በሚሰራ ውሻ መካከል ልዩነት አይኖርማ::ስለዚህ ይህን የሚያዩ ሰባኪዎችና የሞራል አስተማሪዎች እንደእንስሳ አትሁኑ ይሉዋችሁዋል::ከዚህ ግን የከፋ እርግማን የለም::በመወረቱ ከግብረ ስጋ ግንኙነት ውጪ የሰው ልጅ እንደ እንስሳ የሚሆንበት ነገር የለም::ምክንያቱም የሰው ልጅ እንደተፈጥሮው የሚሆነው በወሲብ ሰአት ብቻ ነው::በሌላ ድርጊቱ ላይ ተፈጥሯዊነት ሊያስቀር ይችላል::ለምሳሌ ምግብ በምንበላበት ጊዜ የምንፈጥረው የጠረዼዛ ስነ ስራትና ሌሎችም ጣጣዎች እንደእንስሳ አይደለንም ብለን ስለምናስብ ነው::እነዚህ ስነስራቶችና ባህሎች ያስፈለጉት መሰረታዊውን ነገር"መብላት"ን እንደ እንስሳ ተደርገው ከሚቆጠሩት ተግባራት ለየት ለማድረግ ነው::አራዊቶች ብቻቸውን መመገብ ስለሚወዱ ህብረተሰቡ በያንዳንዱ ሰው ላይ ለብቻ መመገብ ጥሩ አይደለም የሚለውን አመለካከት ያሰርጻል::ስለዚህ በማካፈል እንግዳ በመጋበዝ አብሮ በመብላት እራሱን ለየት ያደርጋል::አንድ ሰው ብቻውን መብላት ከፈለገ እንደእንስሳ ሆነ ትላላችሁ::የመብላት ልማዱ ተፈጥሯዊ ሆኖ ሳለ ውስብስብ ሆኗል::በምግብ በኩል ትልቁን ቦታ የምጸጡት ላመጋገባችሁ እንጂ ምን እንደምትመገቡ አይደለም::ረሀብ ቦታ እንደሌለው ሁሉ ትልቁ ነገር ጣእምና ስነስራት ነው::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 4:04 pm

የሰው ልጅ በዙሪያው ከወሲብ በስተቀር አርቴፊሻል አለምን ፈጥሯል::እንስሳ ልብስ አይለብሱም::ለዛ ነው እኛ እርቃናችንን መሆን የማንፈልገው::እርቃን መሄድ ለዘመናት የተገነባውን የስልጣኔ መሰረት የሚንድ በመሆኑ ራቁቱን በሚሄድ ሰው ላይ ከፍተኛ ውግዘትን ሊፈጥር ችሏል::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 4:12 pm

ማንንም ሰው ሳትነካ ሳትጎዳና አመጽ ሳታስነሳም እንኩዋ በመንገድ እርቃንህን ብትሄድ ፖሊስ ይዞ እስር ቤት ይከትሀል::ወንጀል የሚፈጠረው አንዳች ነገር በማድረግህ ነው::ነገር ግን ምንም ነገር ሳታደርግ ህብረተሰቡ ይናደድብሀል::ለምንድነው ህብረተሰቡ የሚበሳጭብህ?ህብረተሰቡ ወንጀል ሲሰራ እንኩዋን የዛን ያህል አይናደድም::ይህ በጣም እንግዳ ነገር ነው::የሰው ልጅ እራቁቱን መሄድና የማህበረሰቡም መሸበር የሚያስገርም ነገር ነው::ይሁን እንጂ አንድ ምክንያት አለ::ወንጀል የሰው ልጅ ባህሪ ነው::ለሎች እንሰሶች ለመብላት ይገድላሉ እንጂ ወንጀል አይሰሩም::ከሰው ልጅ በስተቀር የራሱን አምሳያ የሚገድል እንሰሳ የለም::ወንጀል የሰው ባህሪ መሆኑም የተነሳ ህብረተሰቡ ተቀብሎታል::እርቃን መሆን ግን የሰውን ልጅ የራሱን ውስጣዊ እንሰሳነት የሚያስታውሰው ስለሆነ ህብረተሰቡ አይቀበለውም::እርቃኑን የሚሄድ ሰው ስታዩ እንስሳነታችሁን ስለምታውቁ ልትቀበሉት አትችሉም::የፈለገውን ያህል በልብስ ብንሽቀረቀርም እንስሳነታችን ግን አለ::እርቃኑን ያለን ሰው የምትጠሉት ግለሰቡ ራቁቱን ስለሆነ ሳይሆን የናንተን እርቃንነት ስለሚያስታውሳችሁ ነው::የለበሰ ጥሩ ያመጋገብ ባህል ያለው ሰው እንሰሳ አይደለም::በቁዋንቁዋ በግብረገባዊነት በፊሎዞፊና በሀይማኖት ከሆነ የሰው ልጅ እንሰሳ አይደለም::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 4:17 pm

ትልቁ ሀይማኖተኛነት ወደ ቤተክርስቲያን ወደአማልክት ቤተ መቅደስ መሄድ ወይም መጸለይ ነው::ለምንድነው እነዚህ ነገሮች በጣም ሀይማኖታዊ የሆኑት?ምክንያቱም ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄድ የሚጸልይ እንስሳ የለም::ወደ ቤተክርስቲያን ወደ አማልክት መሄድ በሰውና በእንስሳ መሀከል ያለውን ልዩነት ፍጹም ያደርገዋል::እነዚህ ድርጊቶች ፍጹም የሰው ናቸውና::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 4:24 pm

ስጋዊ ተራክቦን ግን እንስሳም የሚተገብረው ነው::ምንም ብታደርግ ምንም ብትፈጥርበት እንዴትም ብትደብቀው መሰረታዊው አንተነትህ ግን እንስሳነቱን አይቀይርም::ወደሱ በሄድክ ቁጥርም እንደእንስሳ ትሆናለህ::በዚህም ምክንያት ብዙ ሰው በወሲብ መደሰት አይችልም::ወሲብን መደሰት ያቅተዋል::ሙሉ ለሙሉ እንስሳ እንዳትሆን ራስ ወዳድነትህ አይፈቅድልህም::ስለዚህ ግጭቱ በራስ ወዳድነትና በወሲብ መሀል ነው::ፍትወተ ስጋን ብትቀናቀኑት ራስ ወዳድ ትሆናላችሁ::ራስ ወዳድነት በበዛ ቁጥር ደግሞ ለተራክቦ ያለው ተጻራሪነት ስለሚጨምር ወሲብን የማስወገድ ፍላጎት ከፍተኛ ይሆናል::የራስ ወዳድነት ስሜትም ባነሰ ቁጥር በወሲብ ውስጥ ያለው ተሳትፎ በአንጻሩ ይጨምራል::ነገር ግን አነስተኛ የራስ ወዳድነት ስሜት ያለው እንኩዋን ቢሆን ጥቂትም የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማዋል::የተሳሳተ ነገር አለ የሚለው ስሜት ግን እንዳለ ነው::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 4:25 pm

አንድ ሰው በተራክቦ ውስጥ ጠልቆ ሲገባ የራስ ወዳድነት ስሜት ይጠፋል::የዚህ ስሜት መጥፊያ ሰአት ሲቃረብም ፍርሀት በላያችሁ ይነግሳል::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 6:14 pm

ሰዎች ፍቅር ይሰራሉ::ወሲብ ውስጥም ይገባሉ::ነገር ግን ጤልቀው ወይም የእውነት አያደርጉትም::ፍቅር እየሰሩ እንደሆነ ለማስመሰል ሲሉ የማስመሰያ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ::ምክንያቱም ወሲብ የእውነት ከተሰራ ስልጣኔ በሙሉ መኖር ይኖርበታል::ጭንቅላታችሁ እምነታችሁ ፍልስፍናችሁ በድንገት በውስጣችሁ አውሬ እንደተፈጠረ ይሰማችሁዋል::ነገሮች እንዲከሰቱ ከተዋችሁም ቁዋንቁዋዎች ይጠፋሉ::እንደእንስሳ መጉዋራትና መጮህ ልትጀምሩ ትችላላችሁ::ነገር ግን ፍርሀት አለ::በዚህ ፍርሀት የተነሳ ፍቅር የማይታሰብ ሆኗል::የሚፈጠረው ፍርሀት ደግሞ እጅጉን ገሀድ በመሆኑ የተነሳ ከራስ ወዳድነትህ በምትወጣበት ሰአት እራስህን እስከመርሳት እንደእንስሳም እስከመሆንና አስፈላጊ ነገሮችን ልታደርግ ትችላለህ::ስሜትህን የምትቆጣጠርበት መንገድ በመወገዱ ወንጀል ልትፈጽም የፍቅረኛህንም ገላ በጥርስህ ልትዘነጥል ብሎም ልትገድላት ትችላለህ::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 16, 2007 11:37 pm

ይህንን ሁሉ ችግርና ስጋት ለማስወገድ ታድያ ስሜትን መጨቆን(ጭቆና)ቀላሉ አማራጭ ሊመስልህ ይችላል::ነገር ግን ወደ አደጋ እስካልመራህ ድረስ መጨቆንም ሆነ መልቀቅ ወይም መተው ትችላለህ::መልቀቅ ያለብህ ግን ሁሌም ልትቆጣጠረው የምትችለውን ነገር ነው::ስሜትህን መቆጣጠርና እንደፈለከው ማድረግ እስከቻልክ ድረስም መሄድ እስከቻልክበት ርቀህ ማስቆም ትችላለህ::ጭቆና በመከላከያነቱና በደህንነት መጠበቂያነቱ ነው የሚታወቀው::ሀይማኖቶች ይህንን የደህንነት መጠበቅ ለመግዛት ተጠቅመውበታል::ሀይማኖቶች የወሲብን ፍርሀት በተሳሳተ መንገድ ስላዩት እናንተንም የበለጠ እንድትፈሩ አድርገዋችሁዋል::ሀይማኖቶች ወሲብን የሀጢአት መሰረት አድርገውት ወሲብ ካልተወገደ መንግስተ ሰማያትን አትወርሱም ይሉዋችሁዋል::እውነታቸውን ሊሆን ይችላል::ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ካልተቀበላችሁት ለመክሰስም አይቻልም::በመጨቆን ሳይሆን ወደ ሌላ ነገር በመቀየር ግን መክሰም ይችላል::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Nov 12, 2007 10:41 pm

ጊዜ ሲኖር እንደጊዜው ፍሰት ጽሁፎችም ይፈሳሉና ለጊዜው ከፎረሙ ጫፍ ለማውጣት ነው::


ሾተል....ማን የማንን ስራ ይረሳል
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Dec 15, 2007 6:09 pm

አንዳንድ የኦፒኒየም ግው`አደኞቼ እናነብህ ዝንድ ከፊት ለፊት አድርገው` ባላችሁኝ ማመላከት ይሄው አድርገው`አለሁና መልካም የንባብ ጊዝኤ...ሾተል.....ከ ኦፒንየን ፋክቶርይ ሩም
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9638
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 5 guests