እኔና እኛ ......

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Fri Jun 04, 2010 9:31 am

በተለነቆጠው እኔነቴ ሆኜ መለላዬን ሆኜ እንዳልታይ ልጠብቅሽ የሚያስችለኝን ትግስት እንዲሁም ድፍረትና መቀበልን ይዤ ተሸፋፍኜና ተሻፍኜ እየጠበቅኩሽ ነው::ብትመጪልኝና ብይዝሽ የእኔ ብትሆኚ ካጌጥኩት የበለጠ እጌጥብሽ ይሆን?ግን ምን አጥቼ የግሌ ትሆኚ ዘንድ ማስኜ ፈለግኩሽ?ባንቺ ካለኝ ምኔ ይለወጣል?ምኔስ ይዋባል ወይስ ይገረጣል?ቢሆንም በአሁንዋ ሰአት ልይዝሽ ልጨብጥሽ የግሌ ላደርግሽ እርምጃየን ልጀምር .ከቤቴ እንደነገሩ ሆኜ ልወጣ ነው::ግን አንቺን ይዘውብኛል::ሸክፈውሽ አላስነካ ብለውኛል::ምን ሊያገኙ ይሆን?አላወቁም እንጂ ስለለፋሁብሽ የእኔ የግሌ ነሽ....አቁዋርጬ ላቁዋርጥብሽ....እንደ ወንዝ ፍስስ ልልብሽ....ካሻኝ ልሰየምብሽ.....ግን ይዘውሻል......እኔም ታገስኩዋቸው.......እኔም ጠበቅኩሽ.....አንቺም አልመጣሽ.........ልቤ አንዳች ተሰቅሎ እንደተስፋ ዳቦ እላዬ ልይ አቃንተሽ ተሰቅለሽ አንገቴ እስኪሰበር እይታዬ እስኪቦዝ ድረስ ታንጋጥጪኛለሽ.....

አሁን ከቤቴ ልወጣነው....የት እንዳለሽ ላይሽም እንደነገሩ ተበጣጥሬ ተሽሞኝሙኜ የያዙብኝል ቁልፎች ላስፈታ ልወጣ ነው::ንፋሱም ውጣ አንሳፍፌ ልውሰድኽ እያለ እያሽካካና እያፉዋጨ በጉጉት ይጠብቀኛል::አንሳፎ ሊያንሳፍፈኝ.....ስጋልብ ሊጋልበኝ....ስሞቅ ሊያቀዘቅዘኝ ሿ ሿ ሿ እያለ ኢንቢልታውን እየነፋ ድምጹን እያንሿሿ ሿ ሿ እያለ የእኔን መውጣት ይጠባበቃል::

ብርማውስ ቀን መች ለእኔ ሊተኛ መች ተፈቀደለት?መንገዴን አይ ዘንድ ማያዬን አብርቶ መጪና ሂያጁን እያሳየ ሲለኝ ቁልቁል ሲያሻኝ ሽቅብ እጋልብ ዘንድ ሊያግዘኝ....ሲያሻውም ሊደፋኝ ወይም ሊያነሳኝ......

እኔም ልወጣ ነው አንቺም ተዘግቶብሽ የግሌ ከመሆን ዘግይተሻል.....እኔም ላረጋግጥሽ ነው....አንቺም ምን እንደምትመልሽልኝ አላውቅም....ግን ወጣሁ.....ልከንፍ አቆበቆብኩ......ተስፋ ሰንቄ በፈገግታ ታጅቤ ተስፋ ባለመቁረጥ ታጥቄ ልቀርብሽ መጥቻለሁ::

ሾተል ነን....እውነት እጄ የገባሽ ቀን ምን አደርግሽና አደርግብሽ ይሆን?
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jun 04, 2010 9:49 am

አያድግም ብሎ ያሰበ ማን አለ.....ሁሉም አደገ.....ቁመትም ጨመርን....ገደባችንን ሳትን::ውስጧ ያለውን አውጥታ ባለማካፈሏ ከውስጧ በወበራውና በተማሰለው የውስጧን ሳታወጣው የውስጣችን ፈንድቶ አጠፋን::ሁላቸውም በራሳቸው ውስጥ ተደብቀዋል.....ባህልና መተዳደርያ ደንብ አድርጎ የያዘው ብሂል እንደ ግመል ሽንት ወደሁዋላ እንድንሸና አደረገን.....ስለዚኽ እድገቱ እንደ ካሮት እድገት በውስጣችን ሆነ::እኛም ሁላችን አደግን::በመለክያ ሲለኩን ካመት አመት ቁመናችን ጨመረ::ወፈረችም ተዘረጠጠ ከሳንም ቀጠንኩ ብቻ አንድ ጎተራ ውስጥ የታጨቅን መውጫችን እያለ መውጪያው የጠፋው ሆነን እንደ እንደኮመጠጠ እርሾ እርስ በርሳችን ትባላለች...ይተማመሳል...እንናጫለን::

ግን እድገት አለን...እድገታችን ከመለኪያ የዘለቀ እድገት::ውስጣችን የተጎማለለ ስንለብስ የሚያምርብኝ ስትቀባባ የሚያስደንቅ በእድገት መሀል ቆመን ወደ ሁዋላ ቁልቁል ያደግን::ውስጣችን ታምቆአል......ስላላወጣነው እየበላን ነው::የበላንን በላነው...የበላነው በላችን...ከዛማ ተበላላን....ስለተባላን ጠረቃና አገሳች.....እድገታችን ነዋ ያሳደገን::ማደጋችን አበላላና አጣገበን::እኔም አምቄያለሁ....ደብቄው ጊዜዬን በልቻለሁ::ጊዜያችን ተመሸከ.....ምሽክሽክ ብሎ አንዳች ልጅ እግር አደረገን.......ልጅነታችን አባላን....ከልጅነታችንም አደግንና ጎለመስን::እኛም አደግን::ግን እውነት አያድግም ብሎ የተነበየ ሰው ነበር?ባያድግ ኖሮ ምን ትሆን ነበር?ምስኪን ነች....እድገት እንደፈለገች ይኼው ለማደግ እንደማሰነች አለች....በርግጥ አድገናል......እድገታችን አሳክኮ አኮማትሮናልማል::ግን አያድግም ስላልተባለ አድጎአል::እድገት እድገት ነውና ትንበያው ሰርቷል::

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jun 04, 2010 10:05 pm

በተከመረው በረዶ ስር ስር እየተጉዋዝኩ ከታቼ ያለችውን የምታቃጥል ጸሀይ እየረገጥኩ ያየኋት ቀን ትዝ የሚለኝ በደስታ አለም እየተደሰትኩ ማዛጋቴን ነው::የተዛጋው አፌን ደጋግሜ አንጋጥጬ እንዳየሁት ልቤ በስሜተ ብዙዎች ተማትቶ ያረገርግ ነበር::ታድያ ሲያረገርግ የተላበሰው ውበት ፈካ ብሎ እንዳጎጠጎጠ የህይወት ጡት ፊት ለፊቴ ተቀስሮ ልወጋኽ ቢለኝ እንዳሻኽ ልለው አሰብኩና ሳልለው ብተወው ልጨብጠው ያልኩትን ሁሉ አምጥቶ አስታቀፈና ምናምኑን ሁሉ አቅልዬ እንዳይ አደረገኝ::እኔም ቀልዬ ነበርና የጠበቅኩት ሸክሜ አልከበደኝም::ያም ይመጣና ይጫነኛል እኔም ቀልዬ አቀለውና እንዳመጣጡ እሸከመዋለሁ....ዳግም ይጫነኛል እኔም ትንፋሼን ሰንጌ አጋፈጠዋለሁ....ሊያሳዝነኝ ይሞክራል እኔም ተደስቼ እጠብቀዋለሁ....ልትተሻሸኝ ትፈልጋለች.....እኔም ቀድሜ እተሻሻታለሁ.....ልታስለቅሰኝ ትሞክራለች....ከልቤም ስቄና ፈግጌ እጠብቃታለሁ.......በቃ አልተደሰቱም.....አላገኙኝምም::ግን አውቄ ይዣቸዋለሁ::በጭብጦዬ ተሰንገዋል...ቢሆንም ውድድር ላይ ነን....እንሮጣለን....አለክልከናልም::ግን ድካም ካንዳችንም አልተሸነፈችም::ብቻ ውድድር ላይ ነን...አሀ አሀ አሀ....እዚኽም ይተነፈሳል...እዚያም ይገሳል......ጸሀይዋም ተረግጣልኛለች....በረዶውም ከላዬ ሆኖ ይሞቀኛል::እኔም እሄዳለሁ.....መሄድ መሄድ አሁንም መሄድ.......ረጅምም ይሁን አጭር መንገድ እሄዳለሁ......ጸሀዬን ቦታዋ ላደርግና ከበረዶው በላይ ሆኜ እንደተፈጥሮዋ ልረገጣት::ድምጿ ናፍቆኛል...ስረግጣት ኮሽ ኮሽ እያለች አዳልጣ ልትጥለኝ ስትፈታተነኝ ማየት ናፍቆኛል.....እኔም ወድቄላት ስለማላውቅ ባለመውደቄ ጉልበቴን ልፈትን ሰስቻለሁ::

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed Jul 20, 2011 3:57 pm

በመስታወቱ መስኮቴ ዛፎቹን ቁም ስቅል የሚያሳያቸውን የነፋስ ሽውታ አሻግሬ ስመለከት ለምን ሰየኸኝ ብሎ ነው መሰል ንፋሳማው ነፋስ ሳላስበው እኔንም በሀሳብ ሰረገላ እያናፈሰ አንድያዬን እያማተረና እያካለፈ ወደ ድርዬና አሁንነቴ አቋልፎ ተላይ ታች ያማምሰኝ ገባ ::የሱ እኔን ማስገባት ልቀበለው ባልፈቅድም ያስነካካኝ መንገዶች ውስጤን ተቆጣጥረውት ስለነበር እንዴው ወልፈስ እያልኩ በዛው ስሜት እቆይ ዘንዳ ማንነቴን እመረምር ጀመርኩ ::እኔነቴን ያልመረመርኩ ማን ሊመረምርልኝ ነው ብዬ የዶክተርን ነጩን ልባስ ተላብሼ እምኔ ጋር እምን ሰርቼ እንዳለፍኩና እምኔ ግብ ላይ እንዳዳረሰኝ ቀድጄ እኔነቴን ሳየው አቤት ያለፉት የኮረብታ መንገዶች ...አቤት እነዛ ከኤቨረስት ተራራ የገዘፉት ተራሮች ...አቤት እነዛ ገደላ ገደል ኮረብቶች ....ብቻ ያ ሁሉ መንገዴ ሆኖ በመንገዴ ዳንግላሳ ስጋልብ ቆይቼ ለጥ ካለው ውድማ እፈልጋቸው ስጓዛቸው የነበሩትን ነገራ ነገሮች እውድማው ተነጥፈው በጄ ገብተው አርፈው በደስታ እያስደሰቱኝ ታዩኝ::ተንግዲኽ ወዲህ ድካም ወድያ ግድምም የሚል ጥሁፍ በደህና ቀራጭ ተከትቦ አነበብኩ::ሁለንተናዬን መርምሬ ተጨረስኩ በሁዋላ የበረገድኩት እኔነቴን እሰይ ብዬ ተመስጌን አምላኬ ሁሉንም እፈልግ ነበርና እንደፍላጎቴ ለግሌ አደረከው አልኩና መልሼ እኔነቴን ከከፈትኩበት እቦታው ላስቀምጥ ሰፍቼ ሽውታውን በል ወደ ነበርኩበት መልሰኝ ብዬ ተመልሼ ቅድሚያ ተቀምጬ በት የነበረው ቦታ ላይ ተሀሳቤ ተላቅቄ እተቀመጥኩበት አሁንም ውጩን እያጮለቅኩ ሳይ ንፋሱ ዛፎቹን ማወዛወዙን አላቆመም ነበር:: ጠሀይም ወጥታለች ግን ዝናብ ይዘንብ ይሆን ዛሬ?

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Aug 30, 2012 5:02 pm

አቤት ጊዜ.....መጥኔ ለጊዜ.....ጊዜ ይመጣል.....መጥቶ ይሄዳል.....ሄዶም ይመጣል.....ከዛ ይመጣና ሄዶ ተመልሶ ይመጣል....ግን ጊዜ አሁንም ይሄዳል....ይበራል....ይከንፋል....

ጊዜ በመጣና በሄደ ጊዜ ከጊዜ ጋር የሚበስል የሚሰልል ሞልቷል....ያም የጊዜ ቀመር ስለሆነና ጊዜም ከተፈጥሮ ጋር የተዋሀደ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ስለሆነ ከጊዜ ጋር ተፈጥሮ ሲራመድ ባለጊዜዎች ደግሞ ከነዚህ ሁለት ነገሮች ጋር አብረው ይነጉዳሉ.....

ብቻ ጊዜ ጥሩ ነው::ጊዜ ውስጥ ያስኖራል.....ቢሆንም ጊዜ ይመጣል.....ጊዜ ይሄዳል.....

ሾተል ነን........ጊዜ ለኩሉ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Sep 21, 2012 11:08 pm

ኢትዮዽያዊነት ስንል ጥበብነት .....ባህልነት .....ታሪክነት ....እምነታዊነት ......መከባበርነት ....አንድ መሆንነት እያለ መረዳዳትነት ይመስለኛል ::

ጥበብነት ኢትዮድያዊነት ከሆነ በጥበብ ኢትዮዽያዊነት ተገልጦ ተገላልጦም ያውቃል ::ያለ ጥበብነት ባህልነት ያለ ባህልነት ጥበብነት እንዲሁም ያለ ባህልነት ታሪክነት ሳይወሳሰቡ ሳይጠላለፉ ሳይተሳሰሩ አይሄዱም እንጂ የየቅል ሆነው በኢትዮዽያዊነት ውስጥ ከሌሉ እንኩዋን ኢትዮዽያዊነት አይደለም እራስነት ወይም መምጫ አልባ ይሆናል ::

ከዛ ከነዚህ ትስስሮሽ መወራረድ እራስነትና ከየት መጡነት ይከሰታል ::የዛኔ ሁሉንም ሽክፍ አድርጎ የያዘ በመጣበት ይኮራል ....እራስን ይኮናል ::እራስን ከተሆነ ደግሞ የራስን ነገር መጠበቅ እራስ እንደ ጉም ብን ብሎ በለላ ዲቃላ እራስነት እንዳይጠፋ በጣም አድጎ ይረዳል ::

ታድያ እራስነትን ከሆኑ እራስነትን ማክበር ይገባል ብዬ አምናለሁ ::እራስን ሲያከብሩ ደግሞ በራስ ውስጥ የተገነቡትን እነዛን ጥበብ ,ባህል ,ታሪክ ,ጀግንነት ,እምነት ,አንድነት ወዘተ የሚሉዋቸው ቅመማ ቅመሞችን አከበሩ ማለት ነው ::

እነ ጥበብ ,ባህል ,ታሪክ ወዘተ ያልናቸውን ስናከብር ደግሞ የጥበብ እድለኛውን ,ባህል አክብሮ ጠብቆ ለመጪው ትውልድ የሚያስተላልፈውን ,ታሪክ ሰሪውን ,ለአንድነት ታጋዩን ወዘተ ማክበርና መጠበቅ አለብን ::

ያንን ጠበቅን ማለት እንክብካቤ ሲያስፈልገው እንክብካቤን .......እርዳታ ሲሻ ከጎኑ መሆንን ....ሰደሰት መደሰትን ....ሲያዝን ማስተዛዘንን አውቀን ስንተገብረው ነው ::

ታድያ አለመታደል ሆነና ስንት በጥበቡም ,በጀግንነቱም ,በተለያዩ አገራዊና አለማዊ መድረኮች ላይ እኛነታችንን በልፋቱ ያስታወቀንን ጊዜ ጥሎት እላይ እንዳልነበር በችግር ምክንያት መሬት ላይ ከአፈርና ጭቃ ጋር ሲለዋወስ ዝም ብለን የሰማነውን ጆሮ ዳባ ልበስ ...አይተንም ከሆነ አይኔን ግንባር ያድርገው አላየሁም ....በማለት አይተን እንዳላየን ....ሰምተን እንዳልሰማን እንሆንና ታሪክ ሰሪውን ስናጣው ግን ስሙን ወደ ላይ ሰቅለን ስራውን ወይኔ እንደዚህ ሳላደርግለት አመለጠኝ እያልን እየተቆጨን ከሞቱ በሁዋላ ለሚያስፈልጉ የእሬሳ ማውጫ ,የሳጥን ,የንፍሮ ,ለሀውልት ....ወዘተ ለማውጣትና ለመቅበር እያለቀስን ስንቻኮል ይኼው መስከረም መጥቶ መስከረም ሄዶ መስከረም በሙሻ ዙሩ ዞሮ ግጥም እስኪል ድረስ አንድ አይነት ነገር ደጋግመን ስናደርግ እንታያለን ::

ይኽን ከላይ በክብርነታችን ሆነን የተፈላሰምነው ነገር እንዴው ወይም ጦዘን ወይም በአንቡላ ደብዛችን ጠፍቶ አይደለም .......በግላችን እፍረትን ,ቁጭትን ,እፍረትን ,ውለታ በይነትን መላበስ ስለጀመርን ነው ::ሰውም ሆነ ህሊናችን ሲጠይቀን እኔ ከኢትዮዽያ ምድር የተፈጠርኩ በደም ኢትዮዽያዊ ነኝ እላለሁ ::ቀጠልም አድርጌ ይኸው ባህሌን ,ቋንቋዬን ,ታሪኬን ,ጥበበን እዩልኝ እላለሁ ::ታድያ ይኼንን ስል እራሴ በሰራሁት ታሪክ ,በተሳተፍኩት ጥበብና ለባህሌ መኖር አስተዋጽኦ ስላደረኩ አይደለም ::ሌላው ደክሞ ጥሮ ግሮ በሰራው እንጂ ::ይኽ እራሱ ለእኔ እፍረት እየሆነብኝ ጸጸትን እየፈጠረብኝ ወደ ህሊናዬ ስሆን እርብሽብሽ ያደርገኛል ::

እራሴንም እጠይቃለሁ ::

እውነት ለምኮራበት ኢትዮዽያዊነት ምን ሰርቻለሁ እልና እራሴን በመጠየቅ መልስ ካንጎሌ ውስጥ ስቤ ላመጣ ስል የፈለኩትን መልስ አጣለታለሁ ::ከዛ ጠላቶቻችን እፍር ይበሉና እፍር እልና ሽምቅቅ እላለሁ ::

ለምን ቢባል ኢትዮዽያዊነት ውስጥ ያለውን ጥበብ ወይም ጥበበኞችን ኢትዮዽያዊነት ውስጥ ያለውን ባህል የሚሉትን ቅመም ኢትዮዽያኢነት ውስጥ ያለውን ታሪክና ጀግንነት ወዘተ ተረፈ ስጠብቅና ስንከባከብ አላየሁማ ::

ብቻ አሁንም ምንም ለኢትዮዽያዊነት አስተዋጽኦ ሳላደርግ በኢትዮዽያዊነቴ መቼም አላፍርም እኮራለሁ ::

ግን እኔ በባዶ ያለምንም አስተዋጽኦ በዚህ ግብዝነት በሚሉት ነቀርሳ ስለተቋጠርኩ ጎብለል ጎምለል እያልኩ ደግሞ ኢትዮዽያዊነት ከኔ በላይ ላሳር እላለሁ ::

ግን በዚች ሰአት ታሪክ የሰሩና እኔን ኢትዮዽያዊነት ያደረጉ ልክ በአሁንዋ ሰአት ህይወታቸውን ለማቆየት ከኔ ከምችለው ካቅሜ ጢቆ ነገር ይፈልጋሉ ::በኢትዮዽያዊነት ተግባብቻቸው የሰሩትን ጥበባዊ የፈጠራ ስራ ሰርተው አቅርበውልኝ ሲያበቁ በነሱ ጥበባዊ የኢትዮዽያዊነት ባህላዊ መግባቢያዊ መዝናናት ተዝናንቼበታለሁ .......ግን ልክ በአሁንዋ ሰአት እኔን ኢትዮዽያዊነቴን ያሳቁ ያዝናኑ ያስደሰቱ በኢትዮዽያዊነት ጥበባዊ ባህል ያስገዘፉ ጥበባዊያን በአሁንዋ ሰአት የእኔን በኢትዮዽያዊነት እንደኔ ካለው ዜጋ ለህመማቸው ማስታገሻ ለራባቸው መጥገብያ ለትማቸው መቁረጫ ለበሽታቸው መድሀኒት ለስቃያቸው መተንፈሻ እጄን ይላሉ ::

እጄን ስል ከምችለው እርዳታዬን ነው ::እርዳታዬን ከሚሹ በኢትዮዽያዊነታቸው እኔን ጀምሮ ስንቱን ሚልየን ህዝብ ያሳቁ ....ያዝናኑ ....ያስደሰቱ ....አገር አገርኛ ያሸተቱ .....ባደግንበትና በምንወደው የኢትዮዽያ ራድዮ መዝናኛ ፕሮግራም ለዛ ባለው የአገርኛ ጥበባዊ ስራቸው ለ 20 አመት እኔንና ኢትዮዽያዊያንን ካዝናኑ ከቁጥር በላይ አገር ወለድ ጥበባዊያን አንዱ በአሁኑ ሰአት አልጋ ላይ ውሎ የእኔንና የእናንተን እጅ ...እርዳታ .....ድጋፍ ይፈልጋል ::

እንዲህ ሆነ ::ከትላንት ወድያ ነው አንድ የሳይበር አለም ወንድሜ ካለበት የአውሮፓ አገር ይደውልልኝና ሾተል የደወልኩልኽ ስለ አንድ ነገር ነው ::እሱም አንድ ታላቅ ኢትዮዽያዊ የጥበብ ሰው በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል ::ተሯሩጦ ስንት እንዳልሰራ ዛሬ አልጋ ላይ ውሏል ::ልክ የሱን ችግር እንደሰማሁ ወድያው ስልክ ደውዬ ያቅሜን ወደ 200 ዩኤስ ዶላር ላኩለት ::እና አንተም እባክህ የምታደርገውን ነገር በግልህ አድርግለት ....እንዲሁም ላልሰማ አሰማ ይለኝና አንድ ሊንክ ይጠቁመኝና አንጋፋው የጥበብ ሰው ከአንድ የኢትዮዽያ ትዩብ ላይ ያደረገውን ቃለመጠይቅ እንዳይ ይጠቁመኛል ::ከዛም ሌላ ለሌ ጨዋታዎችን ተጫወትንና ስልኩን በመሰነባበት ዘጋነው ::

ከዛ እነም ወድያው እየተቻኮልኩ ወደ ሰጠኝ ሊንክ ስሄድ እንዴው እግዜር አብዝቶ ጨምሮ ይስጣቸውና ድሬ ትዩቦች ይኼንን አንጋፋ የጥበብ ሰው ያለበት ድረስ በመሄድ የጠየቁትን ቃለ መጠይቅ ,ጭውውትና ያየና የሰማ እርዳታ እንዲያደርግለት የተማጸኑለትን ቪድዮ አይና በጣም እረባበሻለሁ ::ከዛ ማድረግ ያለብኝን እድሜ ለደወለልኝ ወንድሜ ለማድረግ ቃል በመግባት በመጀመርያ ሳይበር ዋርካ ላይ ላልሰሙና ላላዩ ይሰሙ ዘንድ እጠቁማለሁ ስል ይኼው በጣም ባተሌ በመሆን ሶስት ቀን ፈጀብኝ ::

ግን የሚገርመው ዋርካ ላይ አሁን እየተነፈስኩ ያለሁዋት እስከምተነፍስ ድረስ ይኼንን ሶስት ቀን ሲቆጨኝ ጊዜ በማጣቴ ሲጸጽተኝ ዋለና ይኼው ላልሰማ ላሰማ አዋጅ አዋጅ በማለት እጮኻለሁ ::

ስለምድነው ወይም ስለማን ነው የምታወራው ትሉኝ ይሆናል ....

የማወራውማ ከታች ስለምታዩት ክሊፕ ነው ::

ክሊፑ ብዙ ስለሚናገር እኔ ሊንኩን ሰጥቻችሁ ስለማወራው ብትረዱ አብሮ ምን ይለናል ?

http://www.diretube.com/diretube-exclus ... 20c4f.htmlለወገን ደራሽ ወገን ነውና ለወገናችን ለጥበበኛው እንድረስለት ::

ስዊዘርላንድ ላለኸው ወንድሜና ለድሬ ትዩብ ምስጋናዬን ከልቤ አደርሳለሁ ::


ሾተል ነን ........"የሞቀው ሟሙቆ ....ያበጠው አባብጦ ."....(አብረኻም አስመላሽ )
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby Gosa » Tue Nov 06, 2012 5:43 pm

ሾተል ወንድሜ!!!
በህይወቴ ስለ ፍቅር ማንበብ እና መጻፍ ደስ ይለኛል:: ስለ ሞት ብዙም አንብቤ አላውቅም:: ዛሬ አብዛኛውን ጊዜዬን የጨረስኩት ይህንን ያንተን ቤት ተመስጬ በማንበብ ነው:: ገና ብዙ ገጽ ይቀረኛል:: የጽሁፍህን መልዕክት ተከትዬ በሀዘን ስሜት ተውጬ በምናቤ ወደማይታይ ምስጢራዊ የሞት ዐለም ነጉጄ እንኳ ስነጽሁፍ ወዳዱ ውስጤ በእርካታ እና በደስታ ሲሞላ ይታወቀኝ ነበር:: ደስ አሰኘኽኝ:: በዚሁ አጋጣሚ ወንድሜ ሙዝንም ላደንቀው እወዳለሁ:: ተባረኩልኝ::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Re: እኔና እኛ ......

Postby ሾተል » Wed Sep 26, 2018 10:46 am

መጣን፡፡

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Re: እኔና እኛ ......

Postby ዳዊት1 » Sun Mar 17, 2019 8:42 pm

ሾተል የጥንቱ የጥዋቱ ወዳጀ እንዴት ነህ ? ከብዙ እመታት በኋላ ዋርካ ናፍቃን ብንገባ እንተ ከዋርካ ገዝፈህ አገኘን ፡፡ አቤት ቃላት መረጣ አቤት ስሜት አገላለጥ ፤ እንዲህም ይጣፋል ፡፡ ይበል ብለናል ፡፡
ሾባዳቢንግ
piss and love
ዳዊት1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 542
Joined: Sat Nov 27, 2004 1:49 pm
Location: israel

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests