እኔና እኛ ......

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ቫይኪንግ » Sat Dec 20, 2008 9:17 pm

ስልክም መደወል አያስፈልግሽም :: እዚሁ ቤት ( ካልቸርና ሊትሬቸር ክፍል ) መጥቶ ዱቅ ብሎልሻል ....................... ከኮታኮት ሰዕሎቹ ጋር ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ
ትትና wrote:እረ በናትህ መስማማት!! በአንድ ጊዜ ምን ሊሆን ይችላል:: ምን አልባት የውጪ አገር በሽታ ዲፕረሽን ነካክቶት ሊሆን ይችላል ግን እንዲህ ለክፉ የሚሰጠው ሊሆን አይችልም:: ካነጋገሩ ደሞ ጠንካር ይመስል ነበር:: ማለቴ ሰልፍ ሴንተርድ የሆነ ፕሮተክቲቨ ነገር አለ አይደል:: ለማንኛውም ማንኛውም ሰው የሚያስብለት ሰው እንዳለ ሲረዳ በቀላሉ መጽናናት ይችላል ባይ ነኝ:: ኖ ማተር ዋት ሾተል ያገር ልጅ ነው!! አይዞህ ልንለው ይገባል::

te="መሰማማት"]ትትና አንቺ ደሞ ዝምብለሽ ነው::ሾተል እኮ ለይቶለታል በጭጯል::ከበጬ ጋር ምን ልታወሪ ነው ?
[/quote]
ቫይኪንግ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 95
Joined: Mon Nov 03, 2008 10:42 pm

Postby ትትና » Sun Dec 21, 2008 8:47 am

:D :D ቫይኪንግዬ:-
ችግር እኮ ነው ጋይኒኮሎጂስት/ፎቶግራፈር ሁለቱንም የሆነ ሰው ሆቢው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም:: እኔ የምፈራው ግን............... ብቻ ይቀር::

:D መልካም ሰንበት
ትትና
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ሾተል » Sun Jan 18, 2009 3:02 pm

እንዴው በክብርነቴ ሆኜ በጣም ግርም ይለኝና የመታዘቢያ ቴሌስኮፔን ወደ ሚነጣጠረው አነጣጥርና ትክት እስኪለኝ ድረስ እየተገረምኩ እታዘባለሁ::
ምን አይነት የተወሳሰበ ነገር ነው ሰው የመሆን ሚስጥር?ግራ የሚገባ.....ሚስጥሩን ፈልገው የማይደርሱበት በረቂቅ ሚስጥራት ተወሳስቦ የተገነባ ፍጥረት::ይህ ነገር ከመግረምም አልፎ ይደንቀኛል::እስቲ አንድ ሰው አንቱ የሚያስብል ፕሮፌሽን,ማንም የሚኮራበትና የሚቀናበት አንጎል,ዳጎስ ያለ ኪስ,ማንኛውንም ነገር ማድረግ ሲፈልግ የማድረግ አቅም,ውበት,ቁመና,እንዲሁም ሰው በመሆን የታደለ ስጦታ እያለው እንዴት እራሱን ይጠላል?እንዴት በራስም መተማመን ጠፍቶት ከሰው በታች የሆነ ይመስለዋል?በመኖርና ባለመኖር ያለው ሚዛን ወደ አለመኖር አዳፍቶት እራሱን ካላስወገድኩ ይላል?እራሱ በፈጠረው እራስን ትንሽ አድርጎ በማየት አባዜ ከሰው እኩል ወይም በላይ ሰው ሆኖ ትንሽ ነኝ ሰዎች አይቀበሉኝም እኔ እኩል እንደሰው መቆጠር የለለብኝ ውዳቂ ነኝ ብሎ እራሱን ለሽንፈት ይዳርጋል?ለምንስ የመኖር ትርጉም ጨርሶ ይጠፋዋል?


ውበት በህይወት መኖር መሆኑን ዘንግቶት ይሆን ወይስ ሰው መሆን በራስ መተማመን መሆኑ ጠፍቶት?እራስን ተፈጥሮ እንደሰጠችው እራስነት አድርጎ በደስታ መቀበል የሚሉት ሚስጥር ተሰርቆበት ነው ወይስ ለፍቶ ያገኘው ፕሮፌሽን,ተሰጥኦ ወይም እድል ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ሳያውቅ ቀርቶ?አንቱ የሚያስብል ፕሮፌሽን,ትምህርት,ተሰጦ ባይኖረውስ በዚች ደስታዋና ስቃይዋ የትየለሌ ከሆነባት አለም መፈጠሩና የማየት እድለኛ መሆኑ በቂ መሆኑን የነገረው ኢንስትኒክት ደብዝዞበት ይሆን?

ብቻ የሰው ተፈጥሮ አይገባኝም ሊገባኝም አይችልም::ግን ለእራሴ ፈልጌ ያገኘሁት ነገር ቢኖር እራስን መቀበልና እራስን ሆኖ በራስ አለም መሽከርከርን,እያንዳንዱዋን የተሰጠችን ሴኮንድ ሳይኖሩባት እንዳታልፍ ማድረግን,ለነገ አለመጨነቅን,....በቃ ሳይጨናነቁ በደስታ በዘፈቀደ መኖርንና ነገር ግን መሰራት ያለባቸውን ነገሮች ሳይሰሩ አለማለፍን,ሀላፊነትን በአግባቡ መወጣትን........በሀዘንና ስቃይ ጊዜም ቢሆን ደስታን ፈልጎ ማግኘትን....በማንኛውም ቦታ ተመሳስሎ መኖርን.....ወዘተ ተረፈ....በቃ...

ግን የሰው ምናምንቴው አይገባኝም::ከአስቀያሚ ነገር ሁሉ እራስን መጥላት የከበደ አስቀያሚነት ባይኖርም ይበልጥ ደግሞ እራስን አለመሆን በቁም መሞት ነው::ግን ለምን?ክብርነቴ አይገባውም...

ምን ቸገረኝ....የራሳችን ጉዳይ::እኔ ግን እኔ ነኝ::ማንም ደስታዬንና እራሴን መሆኔን የሚቀማኝ ሀይል የለም,አይኖርምም::አቅሜን አሰባስቤ እራሴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁዋ::

ግን የማይገቡኝ ነገሮች ስላሉ መቼም አይገቡኝም::አይግቡኛ::እንዲገቡኝ ግን ጥሬያለሁ::ከአቅሜ በላይ ከሆነ የእኔ ችግር አይደለም::ግን እኔ እያንዳንዱዋን ሰኮንድና ደቂቃ እየተደሰትኩ እየኖርኩባት ነው::

አብረን እንደሰት

ሾተል...........ዛሬን እየኖርኩ ስለሆንኩ በጣም ደስተኛ ነኝ...ነገንም ደግሞ እንደጉድ እኖራለሁ....ባልኖርስ?ነገ መች መጥቶ ያውቃልና ነው ለነገ ክብርነቴ የሚጨነቀው?
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sun Jan 18, 2009 3:19 pm

በህይወት ድኩም መዳፍ ላይ ዝርግት ብዬ እንድኖር ከተፈቀደልኝ መወራጨትም የመፍቀጃው ውል ላይ አብሮ ስላለ ውርጭት ዘርጋ ኮፈስ ብል መብት አለኝ::ዋናው የህይወቴን ሆነ የሰው ህይወትን መዳፍ ይሁዶች ክርስቶስን በሚስማር እንደነደሉት እኔም የሰውን የህይወት መዳፍ አልጫር,አልነድል,አልውጋ እንጂ አጥንትና ተንቀሳቃሽ አካላቴን በዛች መዳፍ ውስጥ ባንፈላስስ መብቴ ነው::ነገ በተወሰነች ከምስጥ በማታስጥል ሳጥን ውስጥ ተወስኜ እቀር የለ....ታድያ ከዛ በፊት የህይወት ምሬት ባፍንጫዬ ይውጣ ብዬ ምችትችት ዝርግትግት ብዬ በህይወቴ ብዳክር ምን አለበት?አግበስባሽነትን ወድያ ከልቼ ለዛሬ የምትበቃኝን ብቻ ይዤ በለት በለቱ እየተጠቀምኩባት ብኖር ስህተት ይመስለኝ ይሆን?

ስለዚህ በህይወቴ መዳፍ ላይ እየቧረቅኩ ነው::በቃ እነ ያ ነኝ::ያንን ስለሆንኩ የፈጠረኝ አምላክ ይክበር ይመስገን::ክብርነቴም እንዲሁ::

ሾተል.......የውጩ ቅዝቃዜ ሲሸክክ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Jun 13, 2009 6:21 am

እራሳችንን እናለማለን ብለን ባልናችሁ መሰረት እዚህ ክፍል በሀሳብም በምክርም በመጨነቅም በማሰብም የረዳችሁን በሙሉ ውለታችሁ ስለከበደን ከኢትዮዽያ ምን ይዘንላችሁ መጥተን ውለታችሁን እንክፈል?
እኛ ለምሳሌ ከኢትዮዽያ የሚያምረን በቆሎ እሸት የተጠበሰው ነው....እናንተስ?

በሉ ያማራችሁን ጠይቁን....ይዘንላችሁ ከች ነው....

ሾተል ነን....ውለታን የማንረሳ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jun 19, 2009 11:30 pm

ጣት አላርፍ አለችና ስትቅበዘበዝ ሳትወደው በግዷ አሩን ጠንቁላ ገምታ አፍንጫን አገማች......ጉድ እኮ ነው....ሲቀሉ ወያ ሲሰሉ አለ ያገሬ ኦሮሞ ....እውነቱን ነው ....ብቻ ቅኔ ነው....ወይም ቅኔ መሆኑ...በቃ ይሁን ....ማንንስ ይገዳል....ብቻ ለመቀኘት መሞከር እራሱ እንደመቀኘት ስለሚቆጠር ከ 1 ቁጥሩ እስኪያመራ ድረስ እንቆጥራለን:....

መቼም ትንሽነት ከተጠናወተን ሁሌም ትንሾች ነን....ሁሉም ከኛ በላይ ትልቅ የሆኑ ስለሚመስለን በትንሽነታችን እናደፍጥና ትልቅ ያልናቸው ፍጡሮች ለጊዜውም ቢሆን ሸተት ሲሉ ከተደበቅንበት ጉራንጉር ወጣ እንልና አካባቢውን ለመቆጣጠር በፍርሀት ብርድ እየተመታን በቁር እየተመዘመዝን አልሞትንም አለን ቅኔም ቢሆን ድፍረት በሌለው ልብ ለመቀኘት እንሞክራለን ብለን ያቅማችንን እንውተረተራለን.....አይ እኛ ምስኪኖች....ሰው መሆን ደስ ይላል...ምስኪንም አድርጎ ልምስምስ አድርጎ ስለሚያስቀምጥም ጭምር....

መሬቱ ለም እስከሆነ ድረስና በስፋቱ መንጠራራት እስኪያስችል ድረስ ማን ደክሞ በቃኝ ይላል?ችግሩ እኛ ውስኖቹ ባንድ ቦታ ላይ ማላዘን ስለምንወድ ከድሮው ቀየር ብለው በሁሉም ቦታ ታየት ታየት ሲሉ በእፍረት የተሸበለሉ ወይም ባቅም ማጣት የተሰናበቱ ይመስለንና ሊታዘቡን ሲገባ የታዘብን መስለን እንሸወዳለን....

ጦጣን ማን ያታልላት ይሆን?ልሳቅ እስቲ....መሳቅ ጥሩ ነው...እንዴውም ጤንነት....ስለዚህ እስቃለሁ....መሳቅ ደስ ስለሚለኝ....ተፈጥሮዬ ደግሞ ሳቅ ሳቅ ተደሰት ተደሰት ስለሚለኝ ባለሁበት በገባሁት በወጣሁት ዳገትም ሆነ ቁልቁለት ለጥ ያለ ሜዳም ሆነ ለስላሳ እደሰት ዘንድ ታድያለሁ....ክብር ለአምላኬ ይግባውና....ግን እኮ በቃ ይቅር...ግን ሳቅኩ....አይ ቅኔና ባለቅኔ....ቅኔ ወደዚህ ባለቅኔዎች ወደዚያ....ፍየል ወደዚህ ቅምዝምዙ አቅጣጫ ስቶ የሆነ ቆንጥር ላይ ተሰቅሎ ቀረ.....
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jun 19, 2009 11:42 pm

ውብ የሆነ እግር አለኝ....ታድያ ሁልጊዜ ይሄንን እግሬን አተኩሬ በፍቅር ህሊና ስመለከተው እኔን ተሸክሞ የማይወስደኝ ቦታ የለም.....በቃ በፈቀደው ቦታ ሁሉ እየወሰደ አዲስ ነገር ሳይቀር ያስተዋውቀኛል.....ማወቅ ጥሩ ነውና መተዋወቅን ሁሌም እወዳለሁ......ታድያ እንዴት በደከመ ፍጡር መሀል ያ ሁሉ ጉልበት እያለኝ አንድ ቦታ ላይ ልልመስመስ?ጭራሽ የሚመጥን ሲጠፋና ድክመትን አሜን ብሎ ከማይቀበል ነፈዝ ሁላ ጋር....ጊዜ ወርቅ ሆኖ ሳለ ጊዜን እምሽክ አድርጎ ባልባሌ ቦታ ማስበላት ነውና ትርፉ....

ምን ችግር አለው በየሄዱበት ቦታ ራሳቸውን ጎልያድ አድርገው የሚኮፈሱትን ሁላ መለሽለሽ ነው....አሮጌዎቹማ ተገምተው ኪሎዋቸው ቀሎ ስለተገኙ እነሱን በጭንቅላት አንጎላቸው እየመገቡ ካዲሶቹ ጦረኞች ጋር መለሻለሽ ነው እንጂ.......ቀሎ ያገኘነውንማ በትዝብት የሚያደርገውን መውተርተር እያዩ አይ ምስኪን ላይሆን መላላጥ ምንኛ ያሳዝናል ብሎ አዝኖ መተው ተመራጭነቱ አንዳች ስለሆነ እንደዛ ማድረግ ነው እንጂ ምን ይደረግ ይሆን?

አለም ምንኛ ጣፋጭ ነች ግን?ልኑርባት ብለው እያንዳንዱዋን ደቂቃ ከኖሩባት እውነቴን ነው የምለው ጥእምናዋና ማእዛዋ ዋው ነው......ግን በእሱዋ ውስጥ ተደስቶ ለመኖር እራስን መሆን ምን ያህል ተመራጭነት ይኖረው ይሆን?ዋናው መምረጣችን ነው....ካለዛማ አለም ለዝቅጠት ህይወት ትመርጠንና ህመሙን ሊሸከሙት የማይችሉት ሀዘኑን ሊወጡት ከሚያቅት አይነት የዳገት መንገድ ያህል ነው...
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Jun 20, 2009 12:11 am

ያለምክንያት በስሜታዊነት ብኖር ብዬ እራሴን ብጠይቀው እራሴ መልሱን ለራሴ ከመመለሱ በፊት ዝግንን ይለዋል....እንዴት ይሄንን ስሜት የሚሉትን ነገር እኔ ሰው የሆንኩት ሰውዬ መቆጣጠር ያቅተኛል?ቀላል ነው....ስለዚህ መልሱን ከራሴ ከማግኘቴ በፊት እያንዳንዱዋን ኑሮ ከምክንያት ጋር ልኖራት ስለምሞክርና ስለምኖር ከራሴ መልስ አያስፈልገኝም...እኔው እራሴ መልስ ነኝና......ስለዚህ እያንዳንዱዋ ስራ ምክንያት አላት ነው የምለው.....ስለዚህ ለምክንያቴ ምክንያት የሌለን በምንሰነዝራቸው ቅኔዎች ብንሸወድ እኔ ምን ግድ አለኝ....ለምን ምክንያት ነኝና.....ብቻ አንዱ ወጣ ሲል አንዱ ይከተላል....ግን ያው አንደኛውም ያኛውም እንዲሁም ያኛውም ባለቀ ሰአትና ተለክቶ ቀሎ በተገኘ ሰውነት ከጎሬ ወጣ ወጣ ቢሉ ያው መልሶ ወደድብኝት ጉርጉዋዳቸው ነው....

ብቻ ትዝ ይለኛል የአራሙቻን መአት ከሰብሉ ለመንቀል የተደረገው ፍልሚያ......መቼም አረም አረም ነው ሰብል ሆኖ አያውቅም....ስለዚህ አረሙን በጠራራ የእውቀት ጸሀይ አስጥቶ ማድረቅ ነበርና ስራው ያው አድርቀን ስር ሰዶ ሰብልን እንዳይቆጣጠር አድርገን ቀዬውን ሰላም አሰፈርንንበትና ............ወደሌላ ቀዬ ተሄደና ያው እዛም የተከማቸውን አረም መንቀል የአደራነት ሀላፊነት ስለሆነ አላፊነትን እንደጉድ ......እስቲ አልጨርሰው....ሁሉን ከተናገሩ ሆድ ሲጮኽ ያድራልና ቁርጥ ነው...በጎደለ ሙላ...

ጥሩ ነው ብያለሁ.....ብቻ ቅኔ ነው.....የሚፈታ የረገበ የላላ የተዝለፈለፈ ያልጠነከረ ቅኔ

አቤት ጊዜው እንዴት በደስታ ሮጦ ሊያልፍ እኩለለሊት ሆነ...

የሰው አገር ሰው መሆን አሪፍ ነገር ነው....ብቻ ከበቀሉበት ቦታ ሲከሰቱ እንዴት ደስ ይላል...እንደገና መወለድ ነው.....ብቻ ሁሉም ነገር ልውጥውጥውጥውጥውጥውጥውጥውጥ......

እኔን አማረኝና እኔ ጋር ሄጄ በእኔ ውስጥ ሆኜ እኔን ሆኜ እኔ ውስጥ ተገገሁ.....እሰይ እሰይ ለኔ...

ይሄኔ እኔን ይሆን ብዬ የምደነግጠው ድንጋጤ ታየኝ....ደግሞ ጀመረኝ ወይም ጀመረን ልል ለህሊናዬ መልክት ላኩለት......አይ አንቺ ጣት ምናለ አርፈሽ ብትቀመጪ....አር አርቶ ከጨረሰ ቂጥ ጋር ማን ተነካኪ አለሽ....በራስሽ ላይ ጉድ ልትፈጥሪ....እራስሽን ልታገሚና በቅርናትሽ ልታስገምቺ......እንግዲህ የራስሽ ጉዳይ ነው....እንዲህ በቂም ተመርዘሽ ነገር እየበላሽ የምትገኚ ከሆነ አይበጅሽም......ደቦ ገቦ አሉ እነዛ ባለቅኔዎቹ.....እንግዲህ እንጉረጥረጥ....ብቅ ጥልቅ....

የት ልንሄድ አለን.....አለምን ባይናችን ስናያት ነው የምንውለው....መኪናው ሲያልፍ እናያለን....አውሮፕላኑ ሲበር እያየን እናደንቃለን....አህዛብ ሲርመሰመሱ እናያለን....ህይወት ስላለን ደግሞ እየኖርም ጭምር ነው...እዚህም ነን....እዛም ነን....ብቻ ሁሉንም አሳፍተን ይዘነዋል.....እኛስ የተሳፋን አይደል....ታድያ ቢቀርብህስ.......

ተመላሽ ይኖራል

መመለስ ነዋ....ገበያ ሲገኝ ማን አይቶ ያልፋል.....ቅኔ ከስድ ንባብ ጋር አይደል....በል ቅኔ ዝረፍ....ወርቁን ከሰሙ ለይና በየጉርባው ሸክፍ....

ሾተል ነን....አለና አለና እንደምን ሰነበትን...ሆያ ሆዬ ሆ....
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ኤFRM » Sat Jun 20, 2009 1:00 am

አይ ሶተል ምን ይሆን እንዲህ የሚያሰለፈልፍህ .....ደህና ነህ ግን.
ለመኖር ስትል አውነትን ዘ ንግተሀ የሉንታ ዐታብዛ.
ኤFRM
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Fri Jun 19, 2009 10:09 pm
Location: sheger

Postby ሾተል » Sat Jun 20, 2009 1:15 am

ኤFRM wrote:አይ ሶተል ምን ይሆን እንዲህ የሚያሰለፈልፍህ .....ደህና ነህ ግን.


አይ አማርኛው ከእንግሊዘኛው ጋር ተጣምሮ ያሰብከውን ሆነህ ባዲሱ ስምህ ለመጠራት E ይቀረዋል......ምን አስቸኮለህ ለመመዝገብ.....እንደማትችልበት አውቀኽ ሰውን አታማክርም?ለየት ብሎ ለመምጣት ስለተፈለገ ብቻ ተቻኩሎ ለመሳሳት መሮጥ የግድ አያስፈልግም ነበር.....ብቻ የስም ብዛት አዋቂ አያሰኝ...

እኔ ደህና ነኝ......ምን እሆናለሁ ብለህ ነው.....ያው ሰው ጥራ ሲሉት እራሱ እየተቀያየረ የሚመጣውንም ባንድ ያለውንም እየጠበቁ ማጫወት ነው እንጂ....ሰው ሲያረጅ ውጭ ውጭ ማለቱን ስለሚቀንስ በስተርጅናዬ ከዋርካ ሌላ ምኑን ጉልበት ኖሮኝ እሄድና.....የሚሄደውን መሸኘት ከዛ ከች ሲል ደግሞ እንዳመጣጡ ማስተናገድ የአባልነት ግዴታችን ነው.....

ለዚህ ነው የለፈለፍኩ መስሎህ የመሰለህ.....የገረመኝ ግን አማርኛና እንግሊዘኛ ተምረሀል?ላንተ ስለማይሆንህ አደራ እንዳትማረው.....ይዞህ ነው የሚጠፋው.....ስህተት ስለሆንክ እንደተሳሳትክ ትኖራለህ....

እስቲ ሄጄ ልገላልብ ሜን...

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

ኤፍረም

Postby ኤFRM » Sat Jun 20, 2009 1:57 am

ወንድም ሶተል እኒ እንዲህ ከምትለፍልፍ ልገላግልህ ብየ እንጀ .....ማን አስተምረኝ አለህ ....እንኩዋን እንግሊዝ ኖርጅ አስተረጉምልሀለው..አትጃጃል
ለመኖር ስትል አውነትን ዘ ንግተሀ የሉንታ ዐታብዛ.
ኤFRM
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Fri Jun 19, 2009 10:09 pm
Location: sheger

Re: ኤፍረም

Postby ሾተል » Sat Jun 20, 2009 2:34 am

ኤFRM

ተንተባተበ
ወንድም


እረ አንተ ወንድም

ሶተል


ሶተል ሳይሆን ሾተል ነው

እኒ

ይሄንን የተከበረ አኩሪ አማርኛችንን አታበላሽ...እኔ እንጂ እኒ አይባልም...ተብታባ...ቆራጣ ምላስ...ቅቅቅእንዲህ ከምትለፍልፍ ልገላግልህ ብየ እንጀ


የሆንክ አንጃ ግራንጃ ነገር ነህ....እንጂ እንጂ እንጀ አይባልም...አማርኛችንን አክብር....

....ማን አስተምረኝ አለህ
.

ቆራጡ መሪያችን መሀይማንን በማስተማር አጥፉ ብሎ ባዋጅ ስለነገረኝ ነው....ስለዚህ መጻፍ በደንብ የማትችል መሀይማን ፊደል በግድ እየቆጠረ ያለ መሀይም ሆነህ ስላገኘውህ የቆራጡ መሪያችንን አዋጅ ለማክበር ስል አንተን ሞደርን መሀይም ለማስተማር አላፊነት ወስጄ ስለሆነ ነው ያስተማርኩህ....

...እንኩዋን እንግሊዝ


ስለቁዋንቁዋ እያወራን የምን እንግሊዝ አመጣኽብኝ...እንግሊዝ አገር እንጂ ቋንቋ አይደለም....ስለዚህ እንግሊዘኛ ነው የሚባል አንተዬ...የሆንክ የኖርዌይ አለሌ ፊደል መጻፊያ ኪስህን ዘርፈውህ ጭብርብር ያለብህ

ኖርጅ


ኖርዌይ አገር አዲስ እግር የሰጠኽ እንደኔ ምስኪኑ ስደተኛ ነኽ እንዴ?ምነው ኖርዌይ የኒርቬዥን ቋንቋ ኮርስ በነጻ የለም እንዴ?የቁዋንቁዋውን ስም እንኩዋን በደንብ ያላወቅክ እንዴት እኔ ጀርመንኛ ተናጋሪ አገር ሆኜ ጀርመንኛን በምልክትና በጠቀሳ ለሚገባኝ አንድ ስደተኛ አንተ የማላውቀውን ቋንቋ ታስተረጉምልኛለኽ?የኖርዌይ ቋንቋ ምን ይባላል?እስቲ ይሄንን መልስልኝ የኛ አቴንሽን ሲከር......አዲስ ስም አውጥተኽ ታጥበህ ታጥነህ ቫዝሊን በጠራራ ጸሀይ ተለቅልቀኽልኝ መጣኽ?የእኛ እሳት እራት.....ለመዋብ ነው ወይስ ለመቃጠል ነው እሳት ዳር ዳር የምታንቁዋልጠው....አንተ ከናትህና አባትህ ጋር በቋንቋ ተግባብተኽ የማታውቅ እንዴት የእኔ ጽሁፍ ይገባሀል?

ትንሽ አታፍርም?ጭንቅላትህን የማይመጥነው ነገር ካጋጠመህ አይተው እንዳላዩ ማለፍ ታላቅነት እኮ ነው ወንድም.......ይሄ ሩምና እዚህ ቤት ያለ ጨዋታ እንኩዋን ላንተ ላስተማሪህም አይመጥንም....ይሄ በጣም የረቀቀና ሚስጥሩ የትየለሌ የሆነ ጽሁፍ ያለበት ቤት ነው....እያካበድኩ እንዳይ<መስልኽ....የሚጻፈው ሲገባህ አይ የኔ ነገር እንደዚህ ሳይገባኝ ልፎገር እንዴ ብለኽ መቼም ዋርካ ውስጥ እድሜ ለነያየህራድ ባለቤቶቹና ለኛ አድሚኖቹ አይከለከልም አዲስ ስም ስታወጣ እንዳትውል....እንደለመድከው ማለቴ ነው.......

አስተረጉምልሀለው..አትጃጃል


እስቲ ልፈትንህ....ሾተል ማለት ባማርኛ እንዲሁም በእንግሊዘኛ ሲልም በኖርቬዥንኛ ምን ማለት ነው?በታትነህ አስረዳኝ እስቲ...አንተ ማወቅ የሸወደህ....የተጻፈ የማይገባህ....የሚጻፍ ጽሁፍ ወደዚ አንተ የምታነበው ወደዛ.....ያገሬ ወላይታ ምን አለ መሰለህ....የለምለሚትዋ ወላይታ ልጅ.....ኒያዬ ዳምፖ መሌስ እንደዚህ አለ እልሀለሁ.....

ያው ባዲሱ ስምህ ቁም ስቅልህን በማሳየት በክብርነታችን የተነሳ በዋርካዊያኖች እንድትታወቅ ብለን እንጂ ምን ችግር አለው ይሄም አልሆንልህ ሲል ስም በሽ በሽ ነው እንደወለቀው ጥርስህ ፊደል እያጉዋደልክ ስም ታወጣለህ...የኛ ኤፍሬም....ቅቅቅቅቅቅ....እስቲ ኤፍሬም ብለህ በአማርኛና እንግሊዘኛ ጽፍ...

መጻፍ አምሮኝ ነበር ዛሬ የሆቴላችን ኮምፒውተር ነጻ ሆኖ አግኝቼ ወረድኩበት....

ለማንኛውም ሥፓሲቫ.....እንዳንተ ባለ ካልተደበርኩ በማን እደበራለሁ....ተለጫጭተኽ የቀረብክልኝ የጅል አሻንጉሊት

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ኤFRM » Sat Jun 20, 2009 2:57 am

እንዼት ትመቻለህ ጃል..አንተ ኖርዊይ ለማለት..ምነው ኖርቭዝን ትላለህ..ክቡርነትህ በዛረው እለት በ ቅምቀማ ወርዶዋል...ምነው ቺክ አለጥበስክም
ለመኖር ስትል አውነትን ዘ ንግተሀ የሉንታ ዐታብዛ.
ኤFRM
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Fri Jun 19, 2009 10:09 pm
Location: sheger

Postby ሾተል » Tue Jun 23, 2009 11:48 pm

ሁላችንም አንድ አይደለንም.....አንድነት ይጎለናል....ግን አንድም ነን....ካልተጉዋደልን ያው ሰው ተብዬዎች ባንድነት አንድ ሆነን የምንጠቃለል አንድያዎች....ቢሆንም በጣም አንዳችን ካንዳችን እንለያያለን....መለያየታችን ይለየናል...ለይቶ ያለያየናል....ግን አንድ የሆንን መስሎን እንቡዋደናለን....ተቡዋድነን ሲለን እንለያያለን....ተለያይተን እንከፋፈላለን.....ስንከፋፈል አይጣል ነው....

ፈሪዎች ነን.....ይፈልጉናል....ያገኙናል ወይም ሊያገኙን ሲፈልጉን እንገኝላቸዋለን....ሲያገኙን ይደሰታሉ....መደሰታቸውን ባለማሳየታቸው ይደሰታሉ.....መደባበቃቸው ከራሳቸው ጋር መደባበቃቸው ሲገባቸው ይሸማቀቃሉ...

ፈሪዎች ነን....ደፈር ልንል እንሞክርና ሲዳፈሩን ድፍረታችንን አብነን ድብቅ....ግን ለምን እንፈራራለን?ስንቴ ሊኖር?ተኑሮስ ?ከዛስ?በቃ ሰው መሆን ይሄ ነው ማለት ነው....እድሜ ለቴክኖሎጂ....ቴክኖሎጂ ሰውን ደብቆ የባህሪ የስም ሀብታም አደረገው....በራሱ ውስጥ እንዲደባበቅና እራሱን እንዲያታልል አደረገው.....አፈር ይብላ ይሄ የስም መአት....ግን ያው እኛው እኮ ነን?


ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jun 04, 2010 8:47 am

ሳናስበው ገባን.....እራሳችንን ከደደቦች መሀል አግኝተነው እያነስን እየወለቅን እየከሳን ሄደንና ብናኝ ሊያበነን የሚያስችል ክብደት ይዘን ቁጭ አልን......ለሰሚው ግራ ነው ይሉ የለ ያገሬ ሰዎች....እውነታቸውን ነው ለሰሚ ግራ እስኪሆን ድረስ በማይዋልበት ቦታ ይዋላል....ተውሎ ወይ ሊያስደንቅ ወይ ሊያስገርም.....እሱስ ያስቆጫልም.::

ግን ምን የሚሉት ትግል ይሆን?ወሬ ወሬ በቃ ወሬ የፈታው ትግል....ውጤቱ ጠብ የማይል ጥፍጥናው ተቀምሶ የማያውቅ ብቻ መማሰን መታሰስ መቆለል መማሰል እረ በቃ ብቻ ውጤት አልባ የዶለተው ልፋት::

እውነት እኛ የጉልት እቃ እንሆን?ካላነሱን ያስቀመጡን ቦታ ተቀምጠን የምንጠነዛ የምንሸጥ የማንለወጥ እቃ?

ብቻ ነቅተን ተመልሰናል::አንዴ ከጠፉ አንዴ ከርጥቡ አንዴም ከምኑና ምናምኑ ልንሰየም ምልስ ብለናል::ስለምንፈለግ ስለሚፈልጉን ስለምናስፈልግ ስለተፈለግንም በቃ ምልስ እያልን ፍላጎታችንን እየሰረሰርን ልንሰየም ሊሰይሙን ልንሰይምም ምጥት ብለናል::

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest