የያሚ ግጥሞች.....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የያሚ ግጥሞች.....

Postby yammi » Thu Aug 10, 2006 6:44 pm

ይሁንልህላንተ ሲሉኝ
ደ-ካ-ማ- ነኝ
አቅመ ቢስ ጎስቋላ
እለተ ሞቷ የተሰላ
ባዶ ወና
የቀለለ ከዳመና
ወፍ-ዘራሽ ነኝ..........
አመጣጤ ያልታወቀ
ዘራ-ዘሬ የደረቀ::
እድለ ቢስ....
ውስጤ ውጬ የጨለመ
ራዕዬ የከሰመ::
ወልጋዳም ነኝ........
አይን አይገባ
መሰረቷ የተዛባ::
ቃል-አባይ ነኝ.......
የእውነትን ደጃፍ ያልረገጥኩ
በክህደት የመከንኩ::
ዘላንም ነኝ.......
እንደ እፉዬ ገላ በራሪ
መንገደኛ አገር ዟሪ::
ተሽከርካሪ::
ላንተ ሲሉኝ
ቀልቤ የራቀ ከላዬ
የደረቀ ወዘናዬ
የከሳሁ የገረጣሁ
ሙት አስከሬን ቀባሪ ያጣሁ::
ይሁንልህ ውድ ወዳጄ
ላንተ ሲሉኝ ሁሉንም ነኝ
የዚህች አለም ክፉ እድል የሞላብኝ::

9/8/2006 20:55
Last edited by yammi on Sat Feb 23, 2008 12:29 pm, edited 2 times in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ባቲ » Thu Aug 10, 2006 10:30 pm

yammi
እጅግ በጣም ቆንጆ ግጥም ነው!!! ሲያነቡት ለልብና አዕምሮ የሚገራ......በዚሁ ቀጥይ::
ባቲ::
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Postby yammi » Thu Aug 10, 2006 11:02 pm

ላላስበው ባስብም
ላወጣው ከምናቤ
ኧረ እሱ መች በጄ ብሎ
ተከተመ እንጂ ከልቤ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Thu Aug 10, 2006 11:56 pm

የሩቅ የትዝታ ስንቄን
ፍቅርን በተራበው ልቤ አንቄ
የልቤን ድምድምታ ጩኧት
በይሆናል ተስፋ ደብቄ
ከጥላዬ ጋር ስማከር
በትዝታዬ ምልሰት
ስዋኝ ስንሳፈፍ ስዳክር
ከኔነቴ ስደራደር
በስተመጨረሻ............
እነሆኝ ብዬ ስዘክር
እሱ ግን.......................
እንዳላወቀ ሆኖ ለይምሰል ቢዋዥቅም
በአፉ እየደለለኝ በስሜቴ ቢሳለቅም
ገና ካፋፉ ሳይደርስ
አውራ መንገዱን ሳያጋምስ
ፊቱን አዙሮ ቢቃኘኝ
ሩጭ ድረሺብኝ ቢለኝ
ያ ቆራጡ ልቤ
ስሜቴን ተጭኖ
የአመታት ናፍቆቴን
ህልሜን አደፋፍኖ
ዘግይተሀል አለው
በቀልን ተመኘ
የልምዱን ቁልቁለት
አሻግሮ እየቃኘ

12/3/06
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Fri Aug 11, 2006 5:03 pm

........
Last edited by yammi on Tue Mar 04, 2008 5:01 am, edited 2 times in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ቶታአው » Fri Aug 11, 2006 5:32 pm

በርግጥ ግጥም ተገጥሙዋል:: Yammi መልክትህ/ሽ ገብቶኛል ግጥም እንዲህ ነው ሚገጠመው እናንተ ዝም ብላችሁ አታምቦጫርቁ ነው ያልከው/ሽው??

ሁለተኛ አላንቦጫርቅም::

መአት ግጥም እጠብቃለሁ ::

ጦጣው
ቶታአው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Mon May 31, 2004 12:39 pm

Postby yammi » Fri Aug 11, 2006 6:04 pm

ጦጣው አመሰግናለሁ.......
እንደኔ እንደኔ ግጥም እስከገጠመ ድረስ ግጥም ነው.እኔም
ከአድናቂዎችህ አንዷ ነኝ .....ግጥሞችህ ፈገግ ያሰኙኛል በግጥም እምብዛም ያልተዳሰሱ ርዕሶችህም እንዲሁ... .......ትምህርት እስከሰጠና እስካዝናና ድረስ ሁላችንም እናምቦጫርቅ አይመስልህም
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Fri Aug 11, 2006 6:11 pm

..........
Last edited by yammi on Tue Mar 04, 2008 5:02 am, edited 1 time in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ዋናው » Sat Aug 12, 2006 12:31 am

ሠላም ያሚያችን::

ልደተ ዋርካሽን ባየው የወራት ዕንግዳ ነሽና እንኳን ደሕና መጣሽ እላለው እዚች ጥበብ ሰፈር:: መቼም እቺህ ሰፈር አንዱ ሲፈረጥጥ ሌላውን ደግሞ ማፈናጠጥ የሁሌ ግብሯ ነውና ዛሬም ለ እኛነታችን ትሕፍሰት አንቺን ማግኘቷ ምንኛ ደስ ይላል::

ከዓይን ዕይታ አልፎ ዜማዊ መልህክቱ ወደ ውስጥ የሚዘልቀው ጉንጉን ቃላቶችሽ ያዝ አድርገውኝ ነው መምጣቴ ለእዚች አስተያየት::
እስቲ አሰልሺና አስነብቢን ግሩም ቃላት ማነባበር ታውቂበታለሽና::

ከብዙ አድናቆት ጋር

ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2804
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ያሚ!

Postby ዋኖስ » Sat Aug 12, 2006 4:00 pm

ያሚ... እንሕን ሥንኞች በማነብበት ጊዜ ምን በሕሊናዬ እንደመጣ ልንገርሽ! ቅቅ ጣቶችሽን ከጣቱ ዓይንሽን ከዓይኑ እንደ መነፀር ሰክተሽ በፊቱ ተንበርክከሽ ጣምራ-ዘለላ እምባዎችሽን በፊትሽ ከኮረብታ መሬት የምትፈልቅ ጪላንጪል ምንጪ አሥመሥለሽ ግጣምሽን ሥትማፀኝ አየሁሽ:: ግሩም ነዉ:: YUMMMMMMMMMMMMMMMM ነዉ:: Not YUKKKKKKKKKKK


እኔንማ አትጠርጥረኝ
ጥሩ ምግባርህ ያሰረኝ
የህይወትህ ግዞተኛ ነኝ
ማን አለ ያላንተ
በልቤ ደጃፍ የቆመ
የመታመንን ሚስጥር
በሁለንተናዬ ያተመ
ከሞት መንጋጋ ፈልቅቆ
እ-ፍ ዳግም ህይወት ያለበሰኝ
ሞቴን በሞቱ ሊተካ
ቃልኪዳን የገባልኝ
እኔ ያላንተ ማን አለኝ
ይልቅ ጠርጥር
ሌላኛውን ማንነቴን
ውስጠ-ጩኧቴን
ድብቅ ድምጼን
መንታ ልቤን
እሱን ጠርጥር
እንደሆነ ያወቀውን
ውለታና ፍቀር ለየቅል
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby Jossy1 » Sat Aug 12, 2006 4:48 pm

ዋኖሴ

አሁን ያሚን አንብቤአት ዝም ብዬ ባልፋት እውነት ጥበብ አትቀየመኝም? ወይም ቅናት ያስመስላል! የጥበብ ቅናት! ኤጭ ቅናት ሲያልፍም አይነካካኝ:: ይልቅስ እዚህ ዋርካ ላይ አንድ አሪፍ ስራ ባነበብኩ ቁጥር ገጣሚያን ጠቢባን መበርከታቸውን ስለሚያሳየኝ ልቤ እልል ትላለች

ያሚ
ግጥምሽን ሳነበው ውስጡ የታየኝ እኔን የተሰማኝ ነገር አለ:: በቤትሽ ልክ በቤቴ እንዳደረግሽው እስቲ አንድ ለመንገድ ልበል:: የዋኖሴ የጥበብ ቡራኬ ሞራል ሆኖሽ ውስጥሽን እናም ውስጣችንን ወይም ውስጣቸውን እንዲህ በሚያምሩ ቃላቶች ስትገልፃቸው እያማረን መለስ ቀለስ ማለታችን; አንቺን መናፈቃችን መች ይቀራል ብለሽ ነው:: እነሆ በረከት; የልቤን እልልታ በቃላት

ትላንት ፍቅርን ተርቤ
ኦና ሆና ያቺ ልቤ
አጥታ ሰው የሚያይላት
ኡኡታዋን የሚሰማት
አጥታ-ትእግስትም ሰውም አጥታ
ፍቅርን ተርባ ቆይታ
ከርማ-ቆይታ
ሲነጋላት የማታ የማታ
ስታገኘው ተደስታ
ፍቅርን ሳትረካ ጎንጭታ
ደሞ ለያት ጊዜ ቦታ::

ለሩቅ አፍቃሪያን
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby yammi » Sun Aug 13, 2006 1:43 am

ውድ ገጣሚያን ወዳጆቼ ዋናው,ባቲ,ዋኖሴ እንዲሁም ጆሲ
ምስጋናዬ ወደር ይለውም...... ዋናው እንደፈራው በወራቶች ብቻ ላለመወሰን እጥራለሁ ስነጽሁፋዊ ሂሳችሁ ለረጅሙ ስነጥበባዊ መንገዴ ደጋፊ ነውና አጋርነታችሁ አይለየኝ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sun Aug 13, 2006 2:07 am

አይንህ ደጃፌን ሲለቅ
ኮቴህ ከጆሮዬ ሲርቅ
የአትለየን ሙሾ ሲደምቅ
ዘወር ብዬ ራሴን ባየው
ግማሽ እኔን አጣሁት
አሀ......................
ገና ዛሬ ተሳካልኝ
ሰምና ወርቁን ፈታሁት
እኔ ማለት ለካ አንተም ነኝ
የእኔነትን መንታ ትርጉም
ሰማያዊ ጉዞህ ፈታልኝ
እኔ ልሙት
ስምል ስገዘት
መሀላዬ አንተንም መጨመሩ
መች አወኩት ከጅምሩ
አሁን ገባኝ ቅኔ ህብሩ
የእኔነት ሚስጥሩ
እኔ አንተን መግለጹን
መንታ ትርጉም ውስጠ-ቅርጹን
በእኔነት የብቻ አለም ውስጥ
እኛነት መሸሸጉን
እኔ ማለት--አንድነት
እኔ ማለት--እኛነት
እኔ ማለት ህብር ጥምረት
መሆኑን
ገና ዛሬ ልብ አልኩት
ሰምና ወርቁን ፈታሁት
ለካስ እኔ ማለት አይደለም
አንድ አካል አንድ ህሊና
አንድነት እንጂ ስብስብ
ሁለት ሶስት ሰብዕና

ለአሴ....13/8/06
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ዋናው » Sun Aug 13, 2006 8:58 pm

ሠላም በድጋሚ
ባንቺ ሠፈር ሥንኞች መሾረብ ይፈቀዳል ቢሉኝ ትንሽ ልጠልስም ብዬ ብቅ አልኩኝ::

ውስጤ ነው የተቃኘው
ወርቅ ሠም ያበጀው
ዕይታን ጎልጉሎ ጠርዝ ገፅ የሰጠው
በመላምት ቀልብ
-ብረሐን ያጮለቀው

ዓይኔማ ፈዘዘ
በማይረባ ዕይታ እየደነዘዘ
ስሜት ስሜት ብሎ ዛሬን እየጦዘ
በትዝታት ፈረስ የውኃሊት ተጓዘ::
በቅኔ ሸብሽቦት ልቤ እንደተከዘ

እስቲ ልቃኝ ዛሬ
ወርቁን ያግኝ ዘሬ
በቃላት አንካሴ ዘልዬ ባንድ እግሬ
እንደዶሮዬ ጭሬ
አገኝ እንድሆን ጥሬ
.
.
.
እስቲ
ዕይታዎቼን ላስታርቅ
ቃል ምስል ልሰንቅ
የነገው ሻማዬ
-ሣይሎከስ እንዳያልቅ

________________________አመሰግናለሁ ::

_______________________________ዋናው::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2804
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby yammi » Mon Aug 14, 2006 12:18 am

ውድ የኔ ቢጤው የጥበብ ምርኮኛ ዋናው

እስቲ ልቀኝ ዛሬ
ወርቁን ያግኝ ዘሬ
በቃላት አንካሴ ዘልዬ ባንድ እግሬ
እንደ ዶሮዬ ጭሬ
አገኝ እንደሆን ጥሬ

ውብ ስንኞች ናቸው.................................ህይወት ቅኔ ናት ለኔም......... ሰሟን እንጂ ወርቋን የሸሸገች....

ህይወት የኔ ቅኔ
የኑሮዬ ሸማኔ
የእድሜዬ መታሪ
ሸንጎ አዳሪ አሳዳሪ
ከሳሽና መስካሪ
ፈራጅና አጋፋሪ
ሰሟ ከላይ ሰፍሮ
ወርቋ እንዳይገኝ ተቀብሮ
ብዙ ለፋሁ ታከተኝ
አፈታቱ ተሳነኝ
ብዕሬ እ-ን-ት-ፍ በል ታደገኝ
የህይወትን ወርቅ አፋልገኝ
14/8/06 2:48
Last edited by yammi on Mon Aug 14, 2006 7:13 am, edited 1 time in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests