የያሚ ግጥሞች.....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby yammi » Mon Dec 18, 2006 11:49 pm

የህይወት ገመድ


የላስቲክ ቤት
ቤት ተብላ
ከድንጋዩ አጥር
ተከልላ
መሰረት ከሌለው ቋሚ
ተማምላ
በለሊት ቁር
ዝናብና ውሽንፍር
ተጠልፋ እንዳትሰግር
ዙሪያዋን ከቧት
የአለት ክምር
ከውስጥ
የኔ ቢጤዋ
በድሪቶዋ ቀዳዳ
በቀጭ የቆረፈደ እጇን ሰዳ
ከወየበው አኮፋዳ
ዝግን
ጭብጥ ፍርፋሪ
የቃረመችውን
ከነፍስ አዳሪ
ብትን..............
ከደጃፉ
ለአእዋፉ....


ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ክርስትያን06 » Tue Dec 19, 2006 3:55 pm

ያሚቲ... እኔም የላስቲክ ቤት ብሶቴን ባንቺ ቤት ልወጣው.. ፍቀጂልኝ..................................

እህምምምምም.... የላስቲክ ቤት
እውነትም የቆመች ያለመሰረት
ለሺዎቹ መጠጊያ
መኖሪያ መጠለያ
አመት ባል ማሳለፊያ
ፋሲካ የአዲስ አመት ግርግር
ገና ኢድ አልፈጥር

የንፋስ ቁጣን ታግላ
የዝናብ ውርጅብኙን ችላ
በድንጋይ ክምር ተከባ
ባናቷ ዝባዝንኬውን ደራርባ
በውስጧ አቅፋ የህይወት ድማም
የኛው ፍጡርን ምስለ-አዳም
ሰጥታ የኑሮ ተስፋ ጭላንጭል
ለሚሊዮኖች ሆና የህይወት እንክብል
ተቖቁማ የሹማምንትን ማእበል
አለች ዛሬም በዚህ ዘመን
አለኝታ ሆና ለወገን::
ክርስትያን06
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 601
Joined: Fri Sep 08, 2006 5:15 pm

Postby yammi » Wed Dec 20, 2006 6:41 pm

ክሪ

ቆንጆ ግጥም ነው::ጨምርበት እስቲ


ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Wed Dec 20, 2006 11:34 pm

ይነጋል


ንፉቅ ልቤ
ሩህሩህ ልቤ
በሰው ማጀት
እንደ አጎዛ
ስትጎተት
ዘነጋኸኝ ያልኩት አምላክ
በባድ መሬት ረሳኸኝ
ከነበልባሉ ነጥሎ
ሽልሞኝ በአመልማሎ
ለእማኝነት ሲያጨኝ
አታዩም
ደም የለበሰችብኝ ጨረቃ
ዛሬ የብርሀን አጸድ አጥልቃ
ስታየኝ አጮልቃ
ልብ አትሉም
የመከራ ለሊት አይነጋም ያለው ማነው
ይነጋል
ይነጋል
የኢትዮጵያ አምላክ እንደኔ
እህቶቼንም ይታደጋል
ይነጋል::


ለቤቲ


አንደበትሽን ተዋስኩት

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ዋናው » Wed Dec 20, 2006 11:34 pm

.
.
.
ውጪሽ ቁር ቢያደብነው
-ውስጥሽ ግን ይሞቃል
ከንፈር ቢያስመጥጥም
-ትንፋሽ ቆጥበሻል
ላስቲክም ብትሆኚ
-ነፍስ አሳድረሻል::

ድንጋይም ጉዑዝ ነው
ላስቲክም ጉዑዝ ነው
አፈርም አፈር ነው::
ቤት የመሆኑ ሚስጥር
-የውስጡ ሠላምሽ ነው::

ከጨረቃ ጥላ
ከሥካር ጭልጭላጭ
-ከብሦት አተላ
ከውሻ ልዛኔ
-ከእብዳዊያን የራስ መላ

ሕያው ትዕይንትሽ
-ከደጃፍሽ አድሮ
-መዝጊያ በርም ባይኖር
በእምነት ተቀርቅሮ

ነፍስ ውስጥሽ አለና
-ቤት ነሽ ያው እንደድሮ
የሚቀይርሽ ካልመጣ
-ምናልባት ሌላ ዘንድሮ


ዘው ብዬ ቤትሽ ገባው ይሁን ያሚ.... ምን ላድርግ የሥንኝ ልክፍት አለብኝ አይደል?

ዋናው___________________________________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby yammi » Wed Dec 20, 2006 11:42 pm

ዋናው
ወይ ጉድ----------ግጥምህ አፈዘዘኝ::እጹብ ድንቅ ነው

ውጪሽ ቁር ቢያደብነው
ውስጥሽ ግን ይሞቃል
ከንፈር ቢያስመጥጥም
ትንፋሽ ቆጥበሻል
ላስቲክም ብትሆኚ
ነፍስ አሳድረሻል::


አረካኝ

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby Critique » Thu Dec 21, 2006 1:04 pm

ካገሩ የወጣ ካገሩ እስኪመለስ
. . . . . . .


መከራ ቢገፋው
ችግር ቢያባርረው
አገር ጥሎ ቢሄድ
ሰው ሀገር ቢሰደድ
ተከትሎት መጣ
ችግር ካገር ወጣ
ለካስ ሲቸግረው
ችግርም ይሄዳል
ካገር ይሰደዳል::
Critique
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Thu Dec 21, 2006 10:58 am

Postby ቤቲ_13 » Thu Dec 21, 2006 7:00 pm

ዋዉ ያሚታ ተንቀራፈፍኩና ዋናዉ ቀደመኝ ሳላመሰግንሽ
ድንቅ ነዉ!!
የማይረሳ ትዉስታ!!
የሚሞገስ ችሎታ!!
አከብርሻለሁ
የ13 ወር ጸጋዋ
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby ቤቲ_13 » Thu Dec 21, 2006 7:10 pm

ይሁና ይሄም ያልፋል
ግዜ ነዉና..ይለወጣል
እንደጃንሆይ አባባል
<<ከመጀመሪያ ሳቅ የመጨርሻ ፈገግታ ይሻላል!!>>
ወጣቱ ከግብ ይደርሳል
ባንዲራዉም ከፍ ብሎ ይሰቀላል
ይዉለበለባል
**አረንጓዴ-ቀ-ቢጫ**
አረንጓዴ--ከላይ ከሰማይ ገነት
ቢጫ--ለአዳም ተስፋ የተሰጠበት
ቀይ--የፈጣሪያችን ደም ያየንበት
ትርጉሙ የሚታወቅበት
እሱም ቀን ይመጣል
ግን እስከዛ ያለፋል
ምሽቱም አይቀር ይነጋል
ይነጋል
ይበራል
የ13ወርዋ ቤቲ ከስደት አምባ
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby Critique » Fri Dec 22, 2006 2:03 pm

ቀን የሰጠው ቅል . . .

ቀን የሰጠው ቅል ነው
ድንጋይ የሚሰብረው?
ወይስ ድንጋዩ ነው
ድንገት ቀን ቢጥለው
ቅል የሚያሰቃየው::
Critique
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Thu Dec 21, 2006 10:58 am

Postby ቶታአው » Fri Dec 22, 2006 2:39 pm

ቀኑ ምን ቢሰጠው

ደርሶ ተሰባሪ

ቅል እንደሁ ያው ቅል ነው

ድንጋዩ ነው እንጂ

ድንገት ቀን ቢጥለው


እንዳይሆን እንዳይሆን

ከቅሉ ተላትሞ

ፍርክስክስ የሚለውጦጣውውውውውው
ቶታአው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Mon May 31, 2004 12:39 pm

Postby ሀዋሪያ 5 » Fri Dec 22, 2006 4:44 pm

ለምንድነው ግን ሰቶቹ የሚጽፉት ግጥም በጣም የሚደብረኝ አምሮብናል ብላቹ ከሆነ ...ቅቅቅቅ

ፕሊስ ለምን አርፋቹ አንባቢ ብቻ አትሆኑም በጣም የሚያስጠሉ ስራዎች ናቸው::
just for fun
ሀዋሪያ 5
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Fri Dec 22, 2006 4:36 pm

Postby Critique » Fri Dec 22, 2006 5:36 pm

የሰው ልጅ ሰልጥኗል . . . .

የሰው ልጅ ሰልጥኗል
ኑሮ ተሻሽሏል
ሴት ከሴት ይተኛል
ወንድ ወንዱን ያገባል
እንስሳቱ ናቸው
ከቶ ያልሰለጠኑት
ወደ ኃላ የቀሩት
ጾታቸው ካለየ አብረው የማይተኙት::
Critique
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Thu Dec 21, 2006 10:58 am

Postby ሾተል » Fri Dec 22, 2006 6:03 pm

Critique wrote:የሰው ልጅ ሰልጥኗል . . . .

የሰው ልጅ ሰልጥኗል
ኑሮ ተሻሽሏል
ሴት ከሴት ይተኛል
ወንድ ወንዱን ያገባል
እንስሳቱ ናቸው
ከቶ ያልሰለጠኑት
ወደ ኃላ የቀሩት
ጾታቸው ካለየ አብረው የማይተኙት::እንዴት ጠልቀህ አይተሀል?


ይመችህ,

ሾተል
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Dec 22, 2006 6:25 pm

ሀዋሪያ 5 wrote:ለምንድነው ግን ሰቶቹ የሚጽፉት ግጥም በጣም የሚደብረኝ አምሮብናል ብላቹ ከሆነ ...ቅቅቅቅ

ፕሊስ ለምን አርፋቹ አንባቢ ብቻ አትሆኑም በጣም የሚያስጠሉ ስራዎች ናቸው::የወለዱህ እናትህ ሲደብሩህ ስላደክ ነው....እህትህንማ እንዴት ትጠላት እንደነበረ የነገርከኝ ለታ ነው ከሴት መፈጠር የለብህም ነበር ያልኩት...

ሴት ሚስት ነው የምታገባው ወይስ ያው ውጮቹ ያሰለጠኑህን ክሪቲክዊ እንደጻፈው ግጥም አይነትን ነው?

ሾተል.....ሴትን አክባሪ...
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests