የያሚ ግጥሞች.....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Fri Dec 22, 2006 6:30 pm

ተፈጥሮ የለገሰሽ
ካካላትሽ የለሰለሽ
ከወንዱ ጎን ተገንብተሽ
ሴት ሆነሽ የተፈጠርሽ
የወንድነታችን ደስታ
የኛነታችን እርካታ
የፍቅራችን ምሳሌ
የደስታችን ሎሌ
የጽንሰታችን ቤት
በውልደታችን ያለም ሁሉ እናት:.


ሾተል........ሴቶችም ወንዶችም እኩል መሆናቸውን የሚያምን አማኝ::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ቤቲ_13 » Fri Dec 22, 2006 9:59 pm

:oops: ያሚቲ ሳልስበዉ ከቤትሽ ዘልቆ ያየሁትን ሰዉ ሳላደንቅ መሄዱ አልሆንልኝ አለኝ እና በድፍረት እንግዳሽን ላደንቀዉ ደፈርኩ
critque--እንግዳዉ አስተዋይ በጣም አሪፍ ነዉ በርታልን እንግዲህ በድፍረት ከያሚ ቤት ገብቼ ምስጋንዬን ሳቀርብ ለሚመጣዉ ክስ አብረን እንቋደሰዋለን
ቶታዉ---አንተም በዕርህ እንደገና ሾላ ብቅ ማለቷ አስደስቶኛል በርታልን
ያሚቲ
አከብርሻለሁ
እንግዲህ ቅጣቱን በግዜ ተናገሪ ልቤን አታንጠልጥይ
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby ክርስትያን06 » Fri Dec 22, 2006 10:18 pm

ድንጋይ ቅልን መስበሩ
አይገርመኝም ለነገሩ
ድንጋይ በቅል ተመትቶ
አይነተነው ተፈንክቶ
ብንል ጊዜ ሰጠው
እላለው በተራው
ድንጋይ ጊዜ ከዳው
ክርስትያን06
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 601
Joined: Fri Sep 08, 2006 5:15 pm

Postby yammi » Sat Dec 23, 2006 5:18 pm

ቤቲ....ኸረ ጥሩ አድርገሻል...critque ግሩም ግጥሞች ናቸው::ጥሩ ሀሳቦችን አንስተሀል......ከሁሉም በላይ የናፈቀንን የጦጣውን ብእር ለማግኘት ግጥሞችህ አግዘውናልና እናመሰግናለን::ሌላም እንጠብቃለን::

ጦጥ.....ደግሞ በዚያው እንዳትጠፋ....አደራ

ክሪ.....ጥሩ መልስ ነው::

ሾተል.....አንተንም አመሰግናለሁ

ያሚ
Last edited by yammi on Sat Dec 23, 2006 6:43 pm, edited 1 time in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sat Dec 23, 2006 5:43 pm

እስቲ.....እኔም


ጊዜ አብሮ ካደረ
ጊዜ አብሮ ካበረ
እንኳን ቅል ድንጋይን
መሰባበር ቀርቶ
አፈርም ብረትን
አጋድሞ ይበላል
ጊዜን ተወዳጅቶ...


ብያለሁ


ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby Critique » Sun Dec 24, 2006 11:26 am

የፈረንጇ ጸሀይ . . .

የፈረንጇ ጸሀይ
አንዳንዴ ሲያሰኛት
ዉላ ትገባለች
ማንም ሰው ሳያያት
ብቅ እንኳ ብትልም
ምንም አትሞቅም
ብርሀን ብቻ ናት
እንደ ፍሪጅ መብራት::
Critique
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Thu Dec 21, 2006 10:58 am

Postby Critique » Mon Dec 25, 2006 12:00 pm

የራሴ ላይ ጸጉር . .

የራሴ ላይ ጸጉር
ከጥንት የነበረ
ጸሀይን ፈራና
ሽሽቱን ጀመረ

ሸሽቶ ሸሽቶ ሄዶ
ወርዶ ወርዶ ወርዶ

ወጣ ደረቴ ላይ
ከሌለበት ጸሀይ::
Critique
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Thu Dec 21, 2006 10:58 am

Postby ቤቲ_13 » Mon Dec 25, 2006 6:07 pm

:x -- :x -- :x
ኡ ኡ ኡ አለች ምድር
ትናጋዋ በ አጥንት ሲሸነቆር
ስትቀበል ስጋ የከዳዉን
ወጣት ሸጋ ጎማላላዉን
ኮረዳዉን
እንቅ ቢያረጋት
የአጥንት መአት
ኡ ኡ ኡ
አይ ምድር
**ጥንቃቄ!!**
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby Critique » Wed Dec 27, 2006 6:14 pm

ቤቲ . . ድንቅ ግጥም ድሮም ያለደረጃዬ እንደቀባጠርኩ አውቄአለሁ : ሁለተኛ አልጽፍም አርፌ ጥሩ አንባቢ ሆናለሁ::
Critique
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Thu Dec 21, 2006 10:58 am

Postby ቶታአው » Thu Dec 28, 2006 10:41 am

አረ ተው አንተም/ችም ድንቅ ጸሀፊ ነህ/ሽ ጃል ዝም ብለህ/ሽ ጻፍ ጻፍ ማረግ ነው:: ደሞስ አንተን/ችን ማን የግጥም ደረጃ መዳቢ አርገህ/ሽ? ግጥም ቡና ነው እንዴ ታጥቦ የተቀሸረ አይነት ደረጃ ማዉጣትም ያሪፍ አይደለም ::በል/ይ ልጄ ልብህ/ሽ የሚልህን/ሽም ቁጭ:: እኛ እናንብብ ባይሆን::

አድናቂ የዋርካ ጦጣ
ቶታአው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Mon May 31, 2004 12:39 pm

Postby ቤቲ_13 » Thu Dec 28, 2006 9:21 pm

critique መልካም ነጭ-ገና ብያለሁ ሰላም!!ጭራሽ እኔን ቀጥ አድርጊ ብትል ያምርብሀል:: በግጥም ከሆነ ጥሩ እጅግ ብስል እና ድንቅ አይነት አገጣጠም ነዉ እረ ቶሎ ቶሎ ብቅ በል
ያሚቲ ፈቃድ ስትሰጪኝ ይኸዉ ፈነጨሁበት
ወዳጃችሁ
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby ቤቲ_13 » Fri Dec 29, 2006 7:45 pm

ጮቅ
እኔስ መች አወቅኩት መስሎኝ ነበር ዕዉነት
ተዋዶ ተፋቅሮ..ተከባብሮ ህይወት
አንዱ ባንደኛዉ ላይ እዛዉ ተደብቆ
ፈልፍሎ ሰርስሮ ሲገኝ ተወሽቆ
ሌላዉን ሊያጠቃ--መቼ አስቤ ነበር
ለካ እሱ''ጮቅ''ነዉ
የማይገባዉ ክብር
ለመጻፍ ያህል
የ13ወር ጸጋዋ ቤቲ
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

መልካም ገና

Postby እሪኩም » Sat Dec 30, 2006 4:15 pm

ሠላም ያሚ!

ያምሮቴ ልበልሽ አዋቂ ነሽና:
በሠላም በፍቅር እንጨዋት ገና::
Image
ጢሰኛው ገበሬው እንደልቡ አርሶ:
ማረስ አልቻለም እየበላ በሶ:
የሆዱን ያገኛል መልሶ መላልሶ::

መልካም ገና
እሪኩም
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby yammi » Sat Dec 30, 2006 5:50 pm

ቅቅቅቅ እሪኩም.......የልጅነት ፎቶህ መሆን አለበት :lol:

አመሰግናለሁ ለአንተም መልካም የገና በአል ይሁንልህ::

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sat Dec 30, 2006 5:57 pm

ልብህን በሰለሞን መቅደስ መስላ
ካህን ቀሲስ መልምላ
በውብ ድምጽህ ቅላጼ
በፍቅር ቃል ውዳሴ
ማህሌት ቆመች ነፍሴ::


30/12/2006

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 11 guests