የያሚ ግጥሞች.....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Yammi

Postby እቴነሽ » Mon Aug 14, 2006 6:25 am

ዕእ
Last edited by እቴነሽ on Wed Aug 16, 2006 1:14 pm, edited 1 time in total.
እቴነሽ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 91
Joined: Thu Mar 17, 2005 4:19 am

Re: የያምሮት ግጥሞች.....

Postby ሾተል » Mon Aug 14, 2006 3:14 pm

yammi wrote:ላንተ ሲሉኝ
ደ-ካ-ማ- ነኝ
አቅመ ቢስ ጎስቋላ
እለተ ሞቷ የተሰላ
ባዶ ነኝ ወና
የጠቆረ ከዳመና
ወፍ-ዘራሽ ነኝ..........
አመጣጤ ያልታወቀ
ዘራ-ዘሬ የደረቀ
እድለ ቢስ....
ውስጤ ውጬ የጨለመ
ራዕዬ የከሰመ
ላንተ ሲሉኝ
ቀልቤ የራቀ ከላዬ
የደረቀ ወዘናዬ
የከሳሁ የገረጣሁ
ሙት አስከሬን ቀባሪ ያጣሁ
ወልጋዳም ነኝ...አይን አይገባ
መሰረቷ የተዛባ
ቃል-አባይ ነኝ.....
የእውነትን ደጃፍ ያልረገጥኩ
በክህደት የመከንኩ
ዘላንም ነኝ.....
እንደ እፉዬ ገላ በራሪ
መንገደኛ አገር ዟሪ
ተሽከርካሪ
ይሁንልህ ውድ ወዳጄ
ላንተ ሲሉኝ ሁሉንም ነኝ
የዚህች አለም ክፉ እድል የሞላብኝ

9/8/2006 20:55


ልብን ይሸነቁራል::ጥልቀቱ ከውቅያኖስ ይበልጣል::ድንቅና የሌላውን የህይወት እውነታ አቆልጮ የሚያሳይ ስራ ነው::
ቀጥይበት::

ሾተል ነኝ::ከአድናቂዎችሽ አንዱ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 14, 2006 3:35 pm

ውስጡዋ በኖ
ስሜትዋ ንሮ ገኖ
አሳምሞዋት
አጎሳስሎዋት
ውስጠትዋን ጎድቶ አሳምሞዋት
ጥሎዋት በሮ
ላያያት ዞሮ
ፍቅሩን አሸክሞዋት
ሲከብዳት ላያግዛት
አስጀምሮ ላያስጨርሳት
ታማ አለች በትዝታ
በሱ ፍቅር እድምታ
አስኖራት ትላንትን ለማታ::
ተስፋ በውስጡዋ በና
ኑሮዋ እንፋሎት ሆና ተና
በባዶ ኑሮ ትኖራለች
ከሞተው እኩል ያላነሰች
ከኖረው ተሰውራ የጠፋች
በጨለመ ተስፋ ታቅራራለች
እየናፈቀችው ታለቅሳለች......

ይቅርታ ገጣሚ አይደለሁም::
አይ ሾተል...ቅቅቅቅ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 14, 2006 4:07 pm

መኖርን ልኖር
ላልሞት ስጥር
በመጉዋጉዋት ስግተረተር
በህልም አለም ስስለመለም
ባልተጨበጠ ተስፋ ሳስገመግም
አቤት እኔ ያልታደልኩኝ
እኔን ትቼ ሌላ የሆንኩኝ
የሌላውን_ ኑሮ ሩዋሪ
በማያገባኝ ቀባጣሪ
ከራሴ የወጣሁ ውጭ አዳሪ......

ሾተል ነኝ.....ግጥም ጀማሪው
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 14, 2006 4:19 pm

ዝናብ ዘንቦ ውስጤ ርሶ
ሁለንተናዬ አረስርሶ
ስውተረተር በጎርፍ ናዳ
በመብረቅ ጩኸት ልቤ ሲከዳ
ጭቃ አዳልጦኝ
ከመሬቱ_አደባይቶኝ
ነጩ ጥርሴን አስለቅሞኝ
በቅዝቃዜ አወራጭቶኝ
ሞቴን ዛሬው አስመኝቶኝ.......

አሁን ዝናብ እየዘነበ ነው እዚህ...ቅቅቅቅ

ሾተል ነኝ......ሲገጥሙ አይቼ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 14, 2006 4:28 pm

ለምን ናቅሽኝ
ምን አጥፍቼ አጣጣልሽኝ
ያለኝን ሁሉ ላካፍልሽ
እንዴውም ካብላጫው ልመትርልሽ
እራሴን አሳምኜ ተነስቼ
ፍቅርን ልሰጥሽ_ጉዋጉቼ
ቀድመሽ ገደልሽው ሥቶታዬን
የሚስማማሽ ቡራኪዬን
ሊያፈቅርሽ የዳዳው ንጹህ ልቤን.....


ሾተል ነኝ....ያለውን የሚወረውር
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 14, 2006 4:46 pm

መለየቴ ድሮ ሆኖ
ቀኑ ጉኖ
በትዝታ ስብሰለሰል
በናፍቆትሽ ስቅጠለጠል
በእድሌ ተረግሜ
ካንቺ በመለየት ረጅም እድሜ
ውስጤ ናፍቆት አብሰልስሎት
የተስፋ ኑሮ አደካክሞት
ሊያይሽ ሁሌም ይከጅላል
ስለት ተስሎ ይጠብቃል
መች ይሆን ያ ቅዱስ ቀን
አንቺ እና ኔን ሚያገናኘኝ......

ሾተል ነኝ.......ማን ግጠም ብሎት ነው?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 14, 2006 5:16 pm

ሲያደርጉ እነሱን አይቼ
ከራሴ ጋር ተሙዋግቼ
አብሬ ልኖር ውሻ አግኝቼ
ይኸው ዛሬ እግማማለሁ
ሽንቱዋን ስጠርግ እውላለሁ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby yammi » Mon Aug 14, 2006 11:20 pm

ሾተል....
ግጥሞችህ ደስ አሰኙኝ....ውቦች ናቸው..መቼም ገጣሚ አይደለሁም የምትለው ለጨዋታ ያህል ነው....ለጥሩ ገጣሚነትህ ምስክሮችህ እኛ ነን......ተመላለስበት
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Mon Aug 14, 2006 11:26 pm

የቀለሜ ትንሽ መድመቅ
ለመለያዬ ሰንደቅ
የባህሌ መዥጎርጎር
ለአመጣጤ ምስክር
መሆኑን ልብ ሲሉ
የረሀብተኛ ምሳሌ መሆን መጥላቴን
የሰላም የፍቅር ናፍቆቴን
ለአንድ ቀን በጀርባዬ
ጧ--ብዬ ለመተኛት መሻቴን
መች ልብ አሉ
14/8/06
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Mon Aug 14, 2006 11:46 pm

ውብ ከናፍርቶችህን ቀምሼ
በአይኖችህ ብርሀን ነግሼ
ልሙት
ጥንቅር ይበል
ቀሪው ህይወት
ሞልቶ የማያውቅ ጎዶሎ
ክዳን የለሽ አክንባሎ
ይሄም ኑሮ ህይወት ተብሎ
ይቅር ሁሉም ጥሎኝ ይሂድ
ራዕይ ሆኖ ከሚቀር
ባይተዋር አርጎኝ ይንጎድ
ግድም የለኝ
ኖሮ አይጠቅመኝ
ሄዶ አይጎዳኝ
ከሰላሳ የምኞት ቀን
አንድ ሰከንድ ይበቃኛል
ሰፊው ትከሻህን ተንተርሼ
ውብ ከናፍርቶችህን ቀምሼ
በአይኖችህ ብርሀን ነግሼ
ከዚያ ብሞት ይሻለኛል


14/8/06
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sat Aug 19, 2006 4:36 pm

እፍ

የነገር እንካ ሰላንቲያ አጡፈን
የቀዬውን ሰላም ገፈን
እኔም
የቤትሽን ማማ መዝመም
አንቺም
የውስጤን ስብራት ህመም
እኔም
የድንበርተኛሽን እንጉርጉሮ
አንቺም
የአማቶቼን እሮሮ
እኔም
ስላልከፈልሽው ስለት
አንቺም
ስለነፈግሁት ምጽዋት
እኔም
የልጅሽን በእጅ አመል ማደፍ
አንቺም
የልጄን ከባለትዳር ጋር መክነፍ
ለማያውቁን ለመለፈፍ
መንሰፍሰፍ
መጣደፍ
ምክንያት ፍለጋ ጠብ እርግፍ
ከቂመኞች ጎራ ለመሰለፍ

16/8/2006
FI
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sat Aug 19, 2006 5:08 pm

ይኸው ለእኔም ወግ ሆኖ
አትሸኟትም ወይ ተባለልኝ
ችላው ምንድነው ተቀኘልኝ
ለአመታት ችላ መባሌን ላይተካልኝ
ምትክነቷን ዘንግታ
ከአብራኳ ፍሬዎች ለይታ
እይታዬን አጥቁራ
ልጅነቴን ተቀራምታ
ዛሬ ብታየኝ
እንባዬ መንታውን ሲንደረደር
ጉልበቴ በፊቷ ሲውተረተር
ድምጼ በሲቃ ሲታጠር
ወግ ነው አለችኝ
ሲዳሩ ማልቀስ
እንባን መርጨት
አይንን ማበስ
ኸረ ይሄ የወግ እንባ
የተባለለት ወግ ነው
በደስታ ሲቃ እያረገደ
በአራት መንታ ከወረደው
ከእኔ እንባ ጋር
አንድ ያደረገው
ከቶ ማነው?

16/8/2006
Helvetia
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sun Aug 20, 2006 7:50 pm

እኔ ለሱ
እሱ ለሷ
እሷ በሱ
እሱ በሷ
ተነባብሮ
ተቆጣጥሮ
ወይ ዘንድሮ

20/8/2006
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sun Aug 20, 2006 7:56 pm

ላላከረው
....ብፈትለው
ላላረጋው
....ብንጠው
ላላደምቀው
....ባቀልመው
ላላጌጠው
....ብሸልመው
ምን ዋጋ አለው

20/8/2006
9:01 casa
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests