Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by yammi » Sun Feb 10, 2008 5:40 pm
ሞላጪት
አይኖቹን ሰረቅሁት
ማረፊያ ሲፈልግ
ከጎዳናው ወሽመጥ
ከሰማይ ጥግ ጥግ::
ያሚ
Last edited by
yammi on Wed Feb 27, 2008 1:08 am, edited 2 times in total.
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ቤቲ_13 » Sun Feb 10, 2008 5:41 pm
ቀብራሪት ቅቅቅቅቅቅ ስልጣን ስታገኚ ፓል ላይ ጠፋሽብን ኮራሽብን ብዬ ነበር አጀብ ብያለሁ ስለሁሉም ጽሁፍሽ
የፓል ኮፍያዉን ደግሞ ታዉሺኛለሽ አንድ ቀን
ለሰርግ አቦ
አክባሪሽ
-
ቤቲ_13
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 795
- Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
- Location: ethiopia
-
by yammi » Sun Feb 10, 2008 5:47 pm
ገድል
በጠቋሚ ጣቴ
ጠንቁዬ ከህይወቴ
ከጠቆረው ቀለም
..ጠቀም ያለ ሙሾ
...ወፈር ያለ ቁርሾ
..............ኡ..ኡ!
..............አዬ!
..............ኡ...ኡ
ፈካ ካለው ቀለም
....የሰለለ እልልታ
....ያልተጣራ 'ስክስታ
.........ደልቅ!
..........ውቃ!
...........ምታ!
...........ውሰድ!
...........እሰር!
...........ፍታ!!!
ያሚ
10/2/2008
Last edited by
yammi on Wed Feb 27, 2008 1:11 am, edited 1 time in total.
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Sun Feb 10, 2008 6:16 pm
ቤቲዬ የኔ እመቤት እንዴት ነሽ? ተጠፋፋን አይደል.......ለመልካም አስተያየትሽ አመሰግንሻለሁ:: ለኮፍያ ነው ደግሞ ....ያው የቤቱን ባለቤት ቆንጂትዬን ወይንም የቤቱን ዋና አስተዳዳሪ ዋንሽን አስፈቅጄ ማዋስ አይደለም እሸልምሻለሁ::
ያቺን ዝብርቅርቅሽንም እየተከታተልኩልሽ ነው ........ዋርካ ሩም ለመምጣት ባለመቻልሽ ግን በጣም አዝኛለሁ:: የአንቺ አለመኖር ብዙ ነገር አጎደለ :( :( :(
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Thu Feb 14, 2008 9:18 pm
ቫለንታይን
በፍቅር እለት
ምሽት ያረበበ'ለት
ጸዳል ለብሰው
ጧፍ ለኩሰው
ጨረቃ እያቀነቀነች
ከዋክብት እያረገዱ
ከጎጇችን ወረዱ::
.
.
ፍቅረ-ቅኔ ሲቀኙ
ምሽቱ ተዳረ!
ለሊቱም ተሞሸረ!!
ንጋትም ተቀጠረ!!!
ምኞትም ተቋጠረ!!!!
...............ለፍቅረኞች በሙሉ::
ያሚ
14/2/2008
Last edited by
yammi on Fri Feb 15, 2008 5:18 pm, edited 2 times in total.
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ጦምኔው » Thu Feb 14, 2008 10:34 pm
........ንግስቲቱ ተመልሳለች::............. :roll:
እመቤቲቱ እንኳን መጣሽ እንጂ ካሁን ብኍላ አንለቅሽም::.......የነብርን ጭራ አይዙትም.......አለ አቡቲ ሲቀባጥር :lol:
ደሞ ሀፒ ቫላንታይን ዴይ!!!.......ለሁሉ!!!
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
by yammi » Fri Feb 15, 2008 9:13 pm
ጦምን........ቅቅቅቅ ጭራ ስለሌለኝ ተመስጌን ልበላ :lol: :lol: አመሰግንሀለሁ ለመልካም ምኞትህ ላንተም እንዲሁ::..........እስቲ ጣፍ ጣፍ አድርግ እንጂ እንዴት ነው :roll: :roll:
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by አቡቲ » Sat Feb 16, 2008 6:23 am
ያም...ሰላምታ
ጦምን ሰላም አለህ ? ልንጦም ሰላምን ፍለጋ ስናኮበኩብ ድንገት በድር መስኮት መሰደርህ...ክስተት..ጋበዘኝና ብቅ አልሁ
:)
-
አቡቲ
- ኮትኳች

-
- Posts: 138
- Joined: Wed Mar 09, 2005 2:59 am
- Location: ኢትዮጵያ
by yammi » Sun Feb 17, 2008 1:29 pm
ጦምን አልገባኝም ማለት እኮ ሀጥያት አይደለም :lol: :lol: አቡዬ ምን አገባሽ እንዳትለኝ እንጂ እኔ ከምር ምንም አልገባኝም :: የሆነ የምታወቁትን ነገር በወፍ ቋንቋ የምታወሩ ይመስላል::
ቂም
ወኔ--- ቆርሶ
ልሳን ---ወርሶ
አንጀት ---ለብሶ
ልብ--- ነክሶ
መኖር የለመደ
የስሜት ሽል
ግግር
ድድር ያለ ....
የጣር-ቁልል::
ያሚ 16/2/08
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Fri Feb 22, 2008 10:11 pm
የውሸት እውነት
አይ........ እዳ!!!
ከጭብጦ ለማር-እንጎቻ ስትል
ከማያውቋት ለምዳ
ሳትስቅ ስቃ
ሳትወድ ወዳ
ሰጠች ቃሏን
ቃል ተቀብላ
የውሸቱን በእውነት ጠቅልላ::
22/2/08
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Wed Feb 27, 2008 12:48 am
ከቤት የመነነች ነፍስ
ደግመው ደግመው
የጽድቅ መንገዱ ምጽዋት
የልብ መንገዱ አይን ሲሏት
የጓጓች ነፍስያዋ
ሚስጥሩን ልትፈታ
ከእለታት አንድ ቀን
ድንገት ቀረች ወጥታ
በእራፊ እንጀራ
የነፍስ እህል ሸመታ::
26/2/08
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ባቲ » Wed Feb 27, 2008 7:06 am
እየመነዘርኳት
ተቸግራ እንጂ
እያጎሳቆልኳት
ተቸግራ እንጂ
ከኔ በላይ አውቃዋ__
ናት ለኔ የምትበጂ::
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
-
ባቲ
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 942
- Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
- Location: ethiopia
-
by yammi » Tue Mar 18, 2008 1:08 am
የበደሉንን ይቅር እንል ዘንድ
የወቀሰን አንደበት:
እደጉ:
ተመንደጉ:
የታዘበን አይን:
ሊያስተዛዝን:
ክፍት ክድን:
ያልዳሰሱን እጆች:
ካይን ሊገቡ:
ሲራገቡ:
ያለመድነው ጉርሻ:
ተሰንቅሮ:
ከጉሮሮ:
የታቀፍነው ይቅር ባይነት:
ከኛ ሲሸሽ:
ሙሽሽ::
18/3/08
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ትርንጎ 123 » Tue May 27, 2008 12:51 am
ያሚታን ያላችሁ...እስቲ እንያችሁ::
-
ትርንጎ 123
- ኮትኳች

-
- Posts: 253
- Joined: Sun Feb 03, 2008 6:14 am
-
by ጦምኔው » Thu Aug 21, 2008 4:59 pm
ይድረስ በጣም ለጠፋሸው ግን ደግሞ ለተገኘሽው እህታችን ያሚታ....ቦኒታ :roll:
ናፍቀን ነበር
አንቺን እና ብዕርሽን
እንኳን ደህና መጣሽ::
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 3 guests