የያሚ ግጥሞች.....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ጦምኔው » Thu Aug 21, 2008 4:59 pm

ይድረስ በጣም ለጠፋሸው ግን ደግሞ ለተገኘሽው እህታችን ያሚታ....ቦኒታ :roll:

ናፍቀን ነበር

አንቺን እና ብዕርሽን

እንኳን ደህና መጣሽ::
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ጦምኔው » Thu Aug 21, 2008 5:00 pm

ይድረስ በጣም ለጠፋሸው ግን ደግሞ ለተገኘሽው እህታችን ያሚታ....ቦኒታ :roll:

ናፍቀን ነበር

አንቺን እና ብዕርሽን

እንኳን ደህና መጣሽ::
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby yammi » Wed Oct 15, 2008 11:55 am

ጦምን..........ንፍቅ ያልከኝ ልጅ:: አመሰግናለሁ:: ፍጥነቴ ይደነቃል መቼም :lol:
Last edited by yammi on Wed Oct 15, 2008 12:01 pm, edited 1 time in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Wed Oct 15, 2008 11:59 am

ርዕስ --- የለውም


ታዘብኳቸው
ጥርሶቼን
ከሳቅህ ሳቅ ሊሰርቁ
ከከንፈሬ ውስጥ ሲያጮልቁ
ታዘብኳቸው::ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Thu Oct 16, 2008 10:25 pm

ህይወት

ከቀን የተረፋትን
ቀን ሰጥታኝ
እንዳልሸሻት
ተጎራብታኝ
እንዳላማት
አፌን ይዛኝ
እኔ አቅፌያት
እሷ ነቅፋኝ
ከሰማይ ምሰሶ ስር
የመቀናጆ ኑሮ
ከህይወት ጋር አምባጓሮ::


ተብሎ ተስተካከለ::


ያሚ
Last edited by yammi on Sun Oct 19, 2008 9:46 pm, edited 2 times in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ጣዝማዊት » Fri Oct 17, 2008 12:18 am

ያሚታዬ እንኩዋን በሰላም ተመለስሽ ጠፍተሽ ነበር በጣም
ጣዝማዊት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 92
Joined: Sun Mar 07, 2004 6:51 pm

Postby ትርንጎ* » Fri Oct 17, 2008 1:11 am

ያሚታዬዬ እንኩዋን ደህና መጣሽ እሙ:: ይቺ ብእርሽ ናፍቃኝ ነበር:: በይ ካሳ 5 ግጥሞችና አንድ ትረካ ተጥሎብሻል :wink: አቤት ትእዛዝ ሲቀል::

እባክሽ አትጥፊብን!
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 716
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ጉዱ ካሳ » Fri Oct 17, 2008 2:26 pm

. . ያሚሻ እንኳን በደህና መጣሽ የኔ ቆንጆ! ካሁን በኍላ የተለኮሰው የግጥምሽ ብርሐን ይንቀለቀላል እንጂ አይጠፋም! ዋ ታዲያ. . . .ቅ ቅቅቅቅ

. . .ዕውነትም 'ትዕዛዝ ሲቀል' አለች ትርንጎዬ
ጉዱሻ
____________________________________
የምንወደውን ብንጠላ የምንጠላውን ብንወድ በራሳችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የባህሪ ለውጥ አመጣን ማለት ነው!
ጉዱ ካሳ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 356
Joined: Wed Oct 22, 2003 6:22 pm

Postby ጦምኔው » Sat Oct 18, 2008 3:36 pm

ሠላም ያሚታ!

በመልካም ቅዳሜ
ከግጥምሽ ታድሜ
አሼሸ ገዳሜ
.............ሜ
...............ሜሜ!!! :lol: :lol:

እኔን ብሎ ደሞ ገጣሚ!
በይ አትጥፊ......የሆንሽ ቆንጆ ነገር!! :roll:
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ዋኖስ » Sat Oct 18, 2008 4:02 pm

ወይ አያ ጦምኔዉ ቅቅቅቅ! በጣም ግሩም ስራ ነች::

ያሚ ታዲያስ! ደህና ነሽ?
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby yammi » Sun Oct 19, 2008 3:31 pm

ጣዝሚት .....ድጋፍሽ የማይለየኝ ልጅ በጣም አመሰግናለሁ...እኔም ዋርካ መለስ ቀለስ የምልበት ቀን ናፍቆኝ ነበር:: ትርንጎዬ አንቺንም አመሰግናለሁ .....ካሳው ከበድ ቢልም ይግባኝ የሌለው ፍርድ ይመስላል:: .........ጉድሽ ደግሞ ያው ታዛዥ መሆኔን ታውቅ የለ እንዴ የምን ማስጠንቀቂያ ነው :D :D ጦምን.....ያንተ ነገር.....ብቻ ይቅር :: :evil: :evil: ሁሉን ቢናገሩት ....... ምናምን.........ዋኖስ ሌላው የጠፋ ሰው:: አንተም እንኳን ደህና መጣህ:: እኔ በጣም ደህና ነኝ :: ዋርካ ላይ ተመልሰህ ስላየሁ ደስ ብሎኛል::

ሰላም ለሁሉም ዋርካውያንና ዋርካውያት::

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ጦምኔው » Sun Nov 09, 2008 4:22 pm

ቤትሽን ወደ ጋቢና ለመመለስ ያደረኩት ወገናዊ ድጋፍ ነው :lol:
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby yammi » Sun Nov 09, 2008 7:10 pm

ጦምን አሁን በዚህ ጊዜ ይህ ወገናዊ ድጋፍ ይባላል ወይስ ወገናዊ .........ተውኩት:: ደሞ ......ይህንንም ተውኩት :lol: :lol: ፈሪ ለናቱ አይደል::
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sun Nov 09, 2008 7:15 pm

ህህምምንም እንኳን ከጉድቢያው መጋጠሚያ ላይ ስንጋጭ
በተፈጠረው የብርሀን ፍላጭ
በእይታችን ብንፋጭ
በዝምታ ብናፉዋጭ
አንተ ፍለጋ የወጣኸው ውሀ አጣጭ
እኔ ፍለጋ የወረድኩት ውሀ አማጭ
አልተገናኘንም::
9/11/08


ያሚ
Last edited by yammi on Sat Nov 29, 2008 8:25 pm, edited 2 times in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sun Nov 09, 2008 7:25 pm

ንገሩልኝ
ፈርታ አይደለም በሉልኝ::
መፍራት በዘሬም የለ
የጀግና ልጅ ጀግና አይደለ!!
አደራ.......
ስታገኙት ንገሩልኝ
አይኗን ከመጫሚያህ ስር ያዋለችው
የረገጥከው መሬት እንዲደላህ እንጂ
አፍራ አይደለም በሉልኝ::
ንገሩልኝ::9/11/2008

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests