የያሚ ግጥሞች.....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ማሳሳ » Wed Jan 14, 2009 4:48 pm

ድንቅ ነው ያሚ ድንቅ ነው:: ባጭር ሰአት ይሄን የመሰለ የጠለቀ እይታ ያለው ግጥም መጻፍ ያስደንቃል:: ጉድ ነው:: ጉድ ባማርኛ Good በእንግሊዝኛ ቅቅቅ:: በርቺ!!
ማሳሳ ነኝ::
Tomorrow is another day
ማሳሳ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Mon Oct 27, 2008 6:20 pm

Postby yammi » Thu Jan 15, 2009 3:12 pm

ማሳሳ..........ለአስተያየትህ ምስጋናዬ ይድረስህ::
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Thu Jan 15, 2009 3:15 pm

ሂሳብ

እሱ እርምጃዋን ሲቆጥር
እሷ የቆጠረውን ስታሰላ
የውህደታቸው መጋጠሚያ
ታየኝና ሲላላ
ጠየቅሁ
መደመርና ማባዛቱ ካሰለሰ
መቀነስና ማካፈሉ የት ደረሰ?15/1/09


ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sat Jan 17, 2009 3:44 am

የሰንበት ደወልይማርልሽ የሚል ጠፍቶ:
ይግደልልሽንም ሳትሰማ::
ሁለት አስር ስትወጣ:
ከጥጋቱ ተሰይማ:
ማን ሊፈርድባት ያቺን እናት:
ዛሬ የሰንበቱን ደወል ባትሰማ:
ጆሮዋ ያለው ከእስትንፋሱ:
ሞት መጣሁ አይልማ:
ከሰሞናቱ......................
ሲስቅላት እሰይ ስትል:
ስትደፋ ከመሬቱ:
ሲቃትት እንባ ስትረጭ:
ለአርባ አራት ታቦታቱ:
ልሳኑ ውታፍ ጎርሶ:
አካሉ ዝሎ ከቄጤማ:
ተስፋ የናፈቁ ጆሮዎቿን:
ተስፋ ለሌለው ሸልማ:
ማን ሊፈርድባት:
ያቺን እናት:
የሰንበቱን ደወል ባትሰማ::
ጆሮዋ ያለው ከስትንፋሱ:
ስጋዋን ከነሳው ጨቅላ:
አትይዘው ነገር ጨብጣ:
መንፈስ ነው የሞት ጥላ::
አይኗስ እንዴት ይልቀቀው:
የእናት ሆዷ እንዴት ይቻል:
በአንዲት ጀንበር ፈክቶ:
እንቡጥ ሊከስም ሲዘናፈል::

17/1/09


ያሚ


የአንዲት ልጇን በማስታመም ላይ ያለችን ኢትዮጵያዊን እናት ለአፍታ በአንድ ዶክመንተሪ ውስጥ አይቻት.....
Last edited by yammi on Mon Nov 23, 2009 4:02 am, edited 3 times in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ቤቲ_13 » Sat Jan 17, 2009 3:03 pm

ቸብ ቸብ ቸብ ስለሁሉም መጣጥፍ አንቺ ዕኮ ቅቅቅ......እንደተለመደዉ,,,,በርቺልን እህታችን ይበልጥ ይበልጥ ,,,
Image
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby ዋናው » Wed Mar 11, 2009 3:11 am

አሁን ማን ይሙት ጃኑአሪ 17 የተከደነ ብሕር እስካሁን ሳይከፈት ቀርቶ ነው?
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2804
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby yammi » Wed Mar 11, 2009 12:03 pm

ዋንሽዬ አይገርምም............ ጊዜው ፊ.......ው ነው እንዴ የሚለው......... እንግዲህ ጊዜ ጠፋ ወይም ብእር መግዣ ጠፋ እንዳልልህ ሁሉንም የኔን ያህል ታውቀዋለህና ለመዋሸት አይመችም.......... ለምን ይህንን ቤት እርግፍ አድርጌ እንደተውኩትም ጭምር::ሚስጥረኛዬ አይደለህ እንዴ :roll:

ልመለስበት መሰለኝ::
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Wed Mar 11, 2009 12:06 pm

ቤቲሽ አመሰግናለሁ የኔ ቆንጆ ........ እኔስ መሄድ መምጣት ለምዶብኛል አንቺን ግን ያለአመልሽ ምን አስኮበለለሽ በሞቴ?
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Wed Mar 11, 2009 12:24 pm

ቀለም ሲገነፍል


ያ ምሁር አጎቴ......
ብእር ያነሳበት እጁ እስኪዝል ድረስ:
................ቀለም ዝቆ ዝቆ:
የአምሮውን ጓዳ ስርጣስርጡን ሁሉ
............. ለቅልቆ ለቅልቆ:
ማእረጉን ጭነው:
አስመርቀው ሸኙት:
.........ዱካና ማነቆ!ከተጻፈ ሰንበት ያለ::

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ትርንጎ* » Wed Mar 11, 2009 2:24 pm

ያሚታዬ ትላንት ማታ ዋንሽን ተከትዬ "እኮ" የምትል ቃል ብቻ ፅፌ ወጣሁና መልሼ አጠፋሁዋት:: አየሽ እግሬ እርጥብ ነው:: :D ሰሞኑን ዋርካ ውስጥ በአንድ እጄ አጨበጨብኩባት ነው የሚባለው... እንኩዋን መጣሽልኝ ቆንጆ:: አቤት ብእር!

እኔ የምለው ሚስጥር እኮ እኔም በጣም እወዳለሁ...እስቲ ሹክ በይኝ በጉዋሮ:: :wink:
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 716
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby yammi » Thu Mar 12, 2009 3:42 pm

ትርንጎዬ...........ታድያስ እንዴት ነሽልኝ? የኔ ነገር እኮ ሄድ መጣ ነው........ዋናው በዛው ሄጄ አለመቅረቴ አይደል:: ሚስጥሩም ይነገርሻል ደግሞ ካንቺ ምን እደብቃለሁ....ደግሞ ደግሞ ዌብሳይትሽን ጎበኘሁልሽ...........ነፍስሽን አታውቂም ከምር:: ዝንጥ ያለ ነው:: ቱ ቱ ቱ ብያለሁ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Thu Mar 12, 2009 4:07 pm

ስልስል ሀቆች
የደለቡ እብለቶች:
የእውነትን ለምድ የለበሱ:
ተዛዝለው ተዛዝለው:
ከሹም ዘንድ ቀድመው ሲደርሱ:
አነባሁ ለኒዚያ
በጥቁር ምድር ላሉ
የሹሙን ደጃፍ መርገጥ ላልቻሉ
ደቂቃቅ እ-ው-ነ-ቶ-ች
የሳሱ .........ግን ያልተበጠሱ
ከዛሬ ነገ ........እፍኝ ሊሞሉ
.........ለሚታገሉ
ስልስል ሀቆች::
ያሚ12/3/2009
Last edited by yammi on Mon Nov 23, 2009 4:00 am, edited 5 times in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ባህል » Thu Mar 12, 2009 8:03 pm

እዚህ ቤት እንዴት ነው ዝም አላችሁ ሞቅ አርጉት እስኪ
ያሚዬ በተስህ ተከፍቶ ሳይ ሰላም ለበልሽ በዬ ነው .
በይ ጣፍ ጣፍ አርጊ ድውውውውውውውውውው
ባህል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 16
Joined: Fri Aug 04, 2006 3:42 pm
Location: Canada

Postby ትርንጎ* » Fri Mar 13, 2009 4:22 am

yammi wrote: ዌብሳይትሽን ጎበኘሁልሽ...........ነፍስሽን አታውቂም ከምር:: ዝንጥ ያለ ነው:: ቱ ቱ ቱ ብያለሁ


ያሚታዬ እኔም ብርቅ ሆኖብኛል...ግን እንደምታይው የቤት እቃ ብታግዥ ይሻልሻል::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 716
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby yammi » Mon Mar 16, 2009 9:27 am

ልንገርህ


ቃልህን:
አለሙ እንዳያይብኝ አልነበር:
ከጉያዬ ሽጬ መጣደፌ:
ለካስ የመትነኑ ምክንያት:
ገና ሳልደርስ ከደጃፌ:
ግፍ ኖሮልሀል ስስቴ:
ሳይደርቅ ይዤው መክነፌ::
አይገርምም::


16/3/09

ያሚ
Last edited by yammi on Wed Mar 18, 2009 8:35 am, edited 2 times in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests