የያሚ ግጥሞች.....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby yammi » Sun Aug 20, 2006 10:47 pm

Last edited by yammi on Thu Aug 24, 2006 7:27 pm, edited 1 time in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Wed Aug 23, 2006 7:41 pm

ኮሽ አታድርግ እባክህን
...................እንዳትባንን
እረጭ
ጭጭ
ይበልላት
የእውነት አለሟ የነሳትን
የህልም አለሟ ያውርሳት
የእውን አለሟ የቀጨውን
የህልም አለሟ ያርዝምላት
እዘንላት
ህመሟን ላትጋራት
አትቀስቅሳት
እረጭ ይበል
ምድር ምድረ በዳ ትምሰል
ዝምታ ራሱ ዝም ይበል
አደራ
ወዲህ ወዲያ አትላወስ
ወደ ውጪ አትተንፍስ
ምድር ታኩርፍ ሰላም ይንገስ
መልአክ መስላ እንደተኛች
የምጽአት ቀን ይድረስ


17/8/2006
FI
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Thu Aug 24, 2006 5:32 pm

ከልሳኔ ተናንቄ
በዝምታ መድመቄ
ሌላም አይደል.......
ጆሮዬ ቢሆነኝ ነው ምስክር
ምላስ አጥንት ባይኖረውም
አጥንትን እንደሚሰብር

24/8/2006
FI
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Thu Aug 24, 2006 6:16 pm

ወገግታውን
በመስኮቴ ስንጥቅ የገባውን
የወፎቹን ዝማሬ
የአዲስ ቀን አዋጅ ወሬ
መች አምኜ
ለኔ............
የስስት እይታህ
የጠዋት ፈገግታህ ነው
ንጋትን አብሳሪዬ
የብሩህ ቀን መክፈቻዬ


24/8/2006
FI
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Fri Aug 25, 2006 5:10 pm

አየሁህ...
በሽርፍራፊ ህልሞቼ ውስጥ
በፀሀይ ብርሀን ቀልጠህ
ጅረት ሆነህ ቁልቁል ስትሮጥ
የእንስት ዘር ሲከተልህ
ተጎንጭቶህ ጥሙን ሊቆርጥ
አየሁህ.....

25/8/2006
FI
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sun Aug 27, 2006 4:45 pm

ልቤ.....................በፍርሀት መረብ ቢታሰር
አእምሮዬ .........ግራ ገብቶት ቢደናገር
አንደበቴ.............በቃል እጥረት ቢታመስ
ምላሴ..................ቃል ላይወጣው ቢላወስ
አካሌ...................ራሴን መሸከም ቢያቅተው
መንፈሴን.............ጭንቀት ቢያስቃትተው
አይኖቼ...............የእንባ ዘለላን ቢቋጥሩ
ልሳኔ....................ባይሰማ ድርድሩ
ፈገግታዬ.............እንደ ሀምሌ ክረምት ቢዳምን
እምነቴ................እንደ ጻድቃን ቢመናመን
ጨዋታዬ...............ወዙ ጠፍቶ ቢያሰለቸኝ
ልጅነቴ..................ትርጉም አልባ ቢሆንብኝ
ሰላሜ.....................የጨረቃን ያህል ቢርቅ
ከራማዬ.................ወደ ሌላኛው አለም ቢመጥቅ
እስትንፋሴ............ህቅታውን ቢናፍቅ
ሀሳቤ.....................ከግማሽ መንገድ ቢሰናከል
ፈተናዬ..................ከጻድቁ እዬብ ቢስተካከል
ማንነቴ...................ትርጉም አጥቶ ቢያከራክር
የመኖሬ..................የከንቱነት ዜማ ቢከር
መረበሼም..............ምንም ያህል ቢከፋ
ይገርማል
ከቶ አላጣም የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ተስፋ


13/3/2006
casa
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ዋናው » Sun Aug 27, 2006 11:40 pm

ትላንት-በትዝታ
ነገንም በተስፋ
ዛሬን ደነባብረን
-ውል ገፁ ሲጠፋ
ያጮልቃል ዓይኔ
-ጉልበቴ ሲለፋ
ነገን ከነገወዲያን ያያል አሸጋግሮ
የዛሬን መብረክረክ በእድል ስም አኑሮ
ይደረጋል ተስፋ እንደምንም ተኑሮ
ዕድሜውም ሳያዶፍ ምናምን ቆጣጥሮ_______(ሳያዶፍ-ዶፍ ሳይጥል)

__________________________አመሰግናለሁ::

ዋናው___________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby yammi » Mon Aug 28, 2006 4:40 pm

ዋናው .....ለተሳትፎህ በጣም አመሰግናለሁ .....እስቲ እኔም ልጨምር

እይታን ከልክለኝ
ጉልበቴንም እሰር
ግዛቴንም ውሰድ
በሀብቴም ተከበር
ያሹፍብኝ ሰማይ
ታላግጥብኝ ምድር
ተስፋን ብቻ አትንሳኝ
ነገን እንድቆጥር....

28/8/2006
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Mon Aug 28, 2006 5:11 pm

.......
Last edited by yammi on Sat Mar 14, 2009 9:43 am, edited 3 times in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Wed Aug 30, 2006 1:22 am

በዚያ ውድቅት
የጣር ለሊት
ጠቀሰችኝ ጨረቃዋ
የጨለማ ቆማሪዋ
የሩቅ ፍቅር አራቂዋ
ነፋሱም እጅ ነሳኝ
ስለደግነትህ እያወሳ
ናፍቆትህን ሊያስረሳኝ

30/8/2006
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ዋኖስ » Wed Aug 30, 2006 1:36 am

በቅድሚያ በኪነ-ጥበብ ሥም ይቅርታሽን እንደ ማትነፍጊኝ ተሥፋ ዐለኝ:: በመቀጠልም የመድብልሽ ዋና ርዕስ "የያምሮት-ግጥሞች" እስከሚል ድረሥ በሥድ ንባብ መፃፉ የግጥምሽን ዉበት ሊያሳጣው ና ሊነፍገው ሥለሚችል ኃሳብሽን በተቻለ መጠን በግጥም ለመጨረሥ ብትሞክሪ ምንኛ ደሥ ይል ነበር!!


ለቤተሰቤ ብቸኛ ሴት ልጅ በመሆኔና ከጎረቤት ልጆች ጋር እምብዛም ተቀራርቤ ባለባደጌ አበባየዎሽ ሳልጨፍር ነው ያደኩት::ግን አሁን እንዴት ይቆጨኛል::ያኔ ትንሽ ልጅ እያለሁ የመጨፈሩ እድል ባይሰጠኝም እቤታችን ገና ጎህ ከመቅደዱ ጀምረው አበባዬዎሽ ሊሉ የመጡትን ህጻናት ራቅ ብዬ እጄ እስኪዝል እያጨበጨብኩ አጅባቸው ነበር::ጸጉራቸውን ተሰርተው....አዲስ ልብስና ጫማ አድርገው....ጥፍር ቀለም ተቀብተው.....በጠዋቱ ካሰባሰቧት ሳንቲም ላይ የገዙትን ማስቲካ እያላመጡ ሲጨፍሩ ሳይ እነሱን ባደረገኝ ብዬ ያልተመኘሁበት ቀን አልነበረም::

ያኔ እኔና ወንድሞቼ የአካባቢው ልጆች ያመጡትን የስእል ወረቀት ተቀብለን እንደገና ለወላጆቻችን በመስጠት ገንዘብ እንቀበል ነበር::ይሄ ሁሉ ታድያ ልጆች እያለን ነበር::ከፍ እያልን ስንሄድ ይሄም ግሩም ባህል እየጠፋ...እንዚያም የመልካም አዲስ አመት አብሳሪ ህጻናቶችም እየተመናመኑ ሄዱ.....

ትዝ ይለኛል ካደግን በኍላ ነው....ይህንን ባህል እንዳካባቢያችን ልጆች ሳናጣጥም ማደጋችን የቆጨን እኔና ወንድሞቼ በወቅቱ ትንሽ የነበረውን ወንድማችንን ለጎረቤት የስእል ወረቀት እንዲሰጥ ልከነው በውሻ በመነከሱ አዲሱን አመት በሆስፒታል ያሳለፍንበት አመትም ነበር::የበአል ትዝታ መች ያልቃል........ብዙ ጊዜ ትዝታ ባይኖር ኖሮ ህይወት ምን ትርጉም ይኖራት ይሆን ብዬ አስባለሁ::
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby yammi » Wed Aug 30, 2006 1:48 am

ዋኖስዬ.
.ልክ ነህ.....መቼም ነገርን ነገር ያነሳዋል ይባል የለ......ግጥሜን ከተየብኩ በኍላ በጭንቅላቴ ሲብላላ ለነበረው የትዝታ ቁራጭ አዲስ ርእስ ከምከፍት ብዬ ነበር.....ሌላ ጊዜ እንድልምዴ በስንኝ ልሸርበው እሞክራለሁ........አመሰግንሀለሁ ለአስተያየትህ

ያሚ
Last edited by yammi on Thu Aug 31, 2006 5:06 pm, edited 1 time in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Thu Aug 31, 2006 5:05 pm

አስቴር የሚለውን በመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ፊልም ካየሁ በኍላ የጫጫርኩት ነው::


አስቴር
በታደግሻቸው ህዝቦችሽ ቀናሁ
እናም እኔም አምላኬን ደጅ ጠናሁ
ከግብረ ሀማ ትታደጊው ዘንድ
ትውልድ ቃር የሆነበትን ወገኔን
ጩኸቱን የተቀማውን ህዝቤን
ስጋሽን ነስቶ ከወገኔ
ደግሞ እንዲፈጥርሽ በዘመኔ
አመድ ባናቴ ነስንሼ
ልብሴን ቀድጄ ማቅ ለብሼ
በጉልበቴ ዳዴ ድሄ
እስቲ ኤሎሄ ልበል ኤሎሄ

31/8/2006
Last edited by yammi on Fri Sep 01, 2006 8:58 pm, edited 1 time in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ማኖር » Thu Aug 31, 2006 6:15 pm

በጣም በጣም ልዩና ተወዳጅ የግጥም ተሰጥኦ ያለሽ እህታችን ያሚ :በውነት ግጥሞችሽ የትፈለገውን መልክት ከማስተላለፋቸውም በላይ ለኔ ረቀቅ ያለ ያጻጻፍ ዘይቤ የሚከተል አይነት ሆኖብኛል::በጣም ጎበዝ ገጣሚ ነሽ::እስቲ እኔም አንድ ግጥም ልለጥፍ::ግጥም ከተባለች

አስፈሪ ጨለማ- እጅግ የራቀበት
ትንሽ ቦታ ስጡኝ- ሰላም የበዛበት
ደስ ሲለኝ ልኖር- ቢያሻኝ ልሙትበት
ተዉኝ ለቀቅ አርጉኝ- እኔም ልኑርበት

ደስ ሲለኝ ስቄ- ስከፋ አልቅሼ
ከሄድኩበት አለም- ብችል ተመልሼ
እንደ ልጅነቴ- ብወድቅ ብነሳ
ኑሮ እየኖረብኝ- ብቆጥረው አበሳ
ተዉኝ ልሞክረው- ለውደቅ ተፈትኜ
እንደናንተው ሳይሆን- እንደ ራሴው ሆኜ
-ራሴን ተማምኜ
ጣልቃ ገብ አልፈልግ- አፈር ድሜ ልብላ
እኔው ለኔው እንጂ- አልጠብቅም ሌላ

08/30/06
"Great minds discuss ideas;Average minds discuss events;Small minds discuss people" Eleanor Roosvelt
ማኖር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 300
Joined: Mon Feb 13, 2006 6:14 am
Location: US America

Postby yammi » Fri Sep 01, 2006 7:44 pm

ማኖር............

ስለግጥሞቼ ለሰጠኸኝ አድናቆትና አብረህ ላዳበልከው ግጥምህ እጅግ በጣም አመሰግንሀለሁ::

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests