የያሚ ግጥሞች.....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby Truth... » Mon Mar 16, 2009 1:43 pm

yammi wrote:ልንገርህ


ቃልህን
አለሙ እንዳያይብኝ አልነበር
ከብብቴ ሽጬ መጣደፌ
ለካስ የመትነኑን ምክንያት
ገና ሳልደርስ ከደጃፌ
ግፍ ኖሮልሀል ስስቴ
ሳይደርቅ ይዤው መክነፌ
አይገርምም::


16/3/09

ያሚ


ሰላም ያሚ ለመሆኑ የት ነው የጠፋሽው? በጣም ; በጣም; በጣም..... ነው ግጥምሽን የወደድኩት ደግሞ ዌብ ሳይት እንዳለሽም ሰማሁ መን አለበት ብትልኪልኝና እኔም እንደ ትርንጎ....

ቸር ሰንብቺ

ትሩዝ
Yes
Truth...
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 175
Joined: Mon Dec 22, 2008 2:47 am

Postby ትርንጎ* » Mon Mar 16, 2009 5:01 pm

:D ለፊርማ ነው::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 716
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby yammi » Mon Mar 16, 2009 8:51 pm

ባህልዬ አንቺ ደግሞ በስድስት ወር አንዴ ነው የምትታይው...ድምጽሽንም ከሰማሁ ቆየሁ....እስቲ ብቅ በይ ወይ እኔ እላለሁ::

ትርንጎዬ ደግሞ ምን ችግር አለ....ሁሉ ሞልቶ ተርፎ...የሚያስፈልገውን ብቻ ጠይቂ::

ትሩዝ.....አንተስ እንዴት ነህ?እኔማ የት እሄዳለሁ ብለህ ነው:: እውር ቢሸፍት ነው ነገሩ.....ብዙ ስጽፍ ባልታይም ግጥሞችህን ከማንበብ ግን አልቦዘንኩም:: በርታ..... ዌብ ሳይቱ ደግሞ የኔ ቢሆን ኖሮ ደስ ቢለኝም ግን የሚያሳዝነው የትርንጎ መሆኑ ነው :lol: :lol: ትንጎዬ ለነገሩ ያንቺ ማለት የኔ አይደል::

ሁላችሁንም ስለ አስተያየታችሁ ከልቤ አመሰግናለሁ::
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby MoonLight » Mon Apr 06, 2009 1:46 am

ይተናል ወይ ፍቅርሽ
...................በጨረቃ ብርሀን የዘራሽው?

በጉያሽ ሳይሆን በልብሽ ይዝሽ
................... ኮትኩተሽ እንደ አረም የጣልሽው::

በድልድይ ላይ ዜማ; በትኩስንት ግለት
..............የሰራሽው ጤዛ
የፅሀይቱን ሙቀት አልፎ
............በለሊት ጨረቃ ጠፋ እንደዋዛ

ስስትም ግፍም አይደለም ውቤ
.................... በባህር ላይ የተነሰነሰን ፍቅር
በፍንትዌ ጨረቃ ቀስምሽ
.................እየናፍቅሽው ግን: ታየ በልብሽ ሲቀበር::


yammi wrote:ልንገርህ


ቃልህን:
አለሙ እንዳያይብኝ አልነበር:
ከጉያዬ ሽጬ መጣደፌ:
ለካስ የመትነኑ ምክንያት:
ገና ሳልደርስ ከደጃፌ:
ግፍ ኖሮልሀል ስስቴ:
ሳይደርቅ ይዤው መክነፌ::
አይገርምም::


16/3/09

ያሚ
MoonLight
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Mon Apr 06, 2009 1:17 am

Postby MoonLight » Mon May 11, 2009 10:55 am

ሰማዩም ጠራልን..... ጸሀይቷም ሳቀች
ምሽቱም ደስ አለ .....ውብ ጨረቃም ወጣች

ንፋሱም አዜመ .... የ ፍቅርን ውዳሴ
ተፈጥሮ ተዋበች... ልትሰርቀው ነብሴን

ታድያ ምን ያድርጋል .....ልእልቲቱ ጠፋች
የፍቅርን ጣኦት .... ወዳ ደሞ ጠላች

ወቤ ሆይ ወቤ ሆይ ......እያት ጨርቃዋን
በፀደዩ ወራት ፍቅርሽን ገብሪላት ::
MoonLight
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Mon Apr 06, 2009 1:17 am

Postby ግደፉ » Wed May 13, 2009 1:24 am

ጥፋት ስናጠፋ አናልፍ አድበስብሰን
በድብቅ አማነው መልሰን መላልሰን
በሰፈርነው ቁና እስኪሰፈር ድረስ
እንደው በፈጠረን ከሰይጣን አንድረስ
ነገሮች ተጣርተው ነጻ እስኪያወጣን
እስኪ ለቀቅ አርጉት ምናረገ ሰይጣን?

05/11/2009
"Suicide is a way of saying to God 'you can't fire me' ,I quit."
ግደፉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 380
Joined: Fri Oct 26, 2007 4:08 pm
Location: from Talakuwa Tigray

Postby ግደፉ » Wed May 13, 2009 1:27 am

yammi wrote:ሂሳብ

እሱ እርምጃዋን ሲቆጥር
እሷ የቆጠረውን ስታሰላ
የውህደታቸው መጋጠሚያ
ታየኝና ሲላላ
ጠየቅሁ
መደመርና ማባዛቱ ካሰለሰ
መቀነስና ማካፈሉ የት ደረሰ?15/1/09


ያሚበጣም ድንቅ ግጥም በርታ/በርቺ
"Suicide is a way of saying to God 'you can't fire me' ,I quit."
ግደፉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 380
Joined: Fri Oct 26, 2007 4:08 pm
Location: from Talakuwa Tigray

Postby ትርንጎ* » Wed May 13, 2009 2:51 am

ግደፉ wrote:ጥፋት ስናጠፋ አናልፍ አድበስብሰን
በድብቅ አማነው መልሰን መላልሰን
በሰፈርነው ቁና እስኪሰፈር ድረስ
እንደው በፈጠረን ከሰይጣን አንድረስ
ነገሮች ተጣርተው ነጻ እስኪያወጣን
እስኪ ለቀቅ አርጉት ምናረገ ሰይጣን?

05/11/2009


:lol: :lol: :lol: ያሚታዬ ደግሞ ጠፋች:: ግደፉ ተበረክ/ኪ ቤትዋን ወደፊት ስላመጣኸው/ሽው::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 716
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ጦምኔው » Sat Aug 29, 2009 2:54 pm

yammi wrote:ርዕስ --- የለውም


ታዘብኳቸው
ጥርሶቼን
ከሳቅህ ሳቅ ሊሰርቁ
ከከንፈሬ ውስጥ ሲያጮልቁ
ታዘብኳቸው::ያሚ


የት ጠፉ?
እነኚያ ጥርሶችሽ
ከሳቄ ሳቅን የሰረቁ
በልቤ ሀሴትን ያፈለቁ
.
.
.
.
.
እያለ ይቀጥላል....... :lol:


እባክሽ ያሚታ እስኪ ተመለሽና እንዲህ ያሉትን ውብ ግጥሞችሽን አስነብቢን::

አመዳም ቢጤ....መቼም እንደማታሳፍሪኝ ነው :lol:
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby yammi » Mon Aug 31, 2009 9:49 pm

:lol: :lol:

መቼም በአንተ እንደማልጨክን ልብህ ያውቀዋል:: ናፍቆቴን ለመግለጽ ያህል ነው:: ነገ በቀጭኑ ሽቦ ጠብቀኝ::

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ዶማው2005 » Mon Aug 31, 2009 9:53 pm

ያሚ...የኔ ሳቂታ...ኦ አንች ወይስ ቤቲ አሪፍ ሳቅ ያላቹ?

ደህና ነሽ ግን? ያ ዋናው ደግሞ እኔ ኢንተርኔት ሳስገባ ቻት ሩም ዘጋ...
ዶማው2005
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1650
Joined: Sat Jun 04, 2005 11:19 pm
Location: United States

Re: የያሚ ግጥሞች.....

Postby Konjit » Sat Nov 07, 2009 4:38 am

ቆንጅዬ ዛሬ በትዝታ ፈረስ እየጋለብኩ የጠፋትን ጓደኞቼን ወደፊት እያመጣሁ ነው :)
ከብዙ ማድነቅ ጋር:)

yammi wrote:ይሁንልህ

ላንተ ሲሉኝ
ደ-ካ-ማ- ነኝ
አቅመ ቢስ ጎስቋላ
እለተ ሞቷ የተሰላ
ባዶ ወና
የቀለለ ከዳመና
ወፍ-ዘራሽ ነኝ..........
አመጣጤ ያልታወቀ
ዘራ-ዘሬ የደረቀ::
እድለ ቢስ....
ውስጤ ውጬ የጨለመ
ራዕዬ የከሰመ::
ወልጋዳም ነኝ........
አይን አይገባ
መሰረቷ የተዛባ::
ቃል-አባይ ነኝ.......
የእውነትን ደጃፍ ያልረገጥኩ
በክህደት የመከንኩ::
ዘላንም ነኝ.......
እንደ እፉዬ ገላ በራሪ
መንገደኛ አገር ዟሪ::
ተሽከርካሪ::
ላንተ ሲሉኝ
ቀልቤ የራቀ ከላዬ
የደረቀ ወዘናዬ
የከሳሁ የገረጣሁ
ሙት አስከሬን ቀባሪ ያጣሁ::
ይሁንልህ ውድ ወዳጄ
ላንተ ሲሉኝ ሁሉንም ነኝ
የዚህች አለም ክፉ እድል የሞላብኝ::

9/8/2006 20:55
Faith is putting all your eggs in God's basket, then counting your blessings before they hatch. ~Ramona C.
Konjit
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 473
Joined: Sun Sep 07, 2003 6:59 am

Postby ጦምኔው » Sat Nov 21, 2009 8:13 pm

ኧረ ፍሬንድ ቋጠርሽብን:: ከምር ይቸክካል.....ግጥም የጠማው ሰው አታርፊም እንዴ? ከምር እንደጉድ ለማመንሽ እኮ......ሰገድን ሁላ ልስሽ::........ሚኪያኤልን ሼም ነው:: :lol:

አንድ ሁለት ጣል አድርጊብን እስኪ: በጉጉት ግጥሞችሽን እየጠበቁ ካሉ አንባቢዎችሽ አንዱ እና ቀንደኛው ጦምኔው ነኝ::

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር

ፊርማ::
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby yammi » Mon Nov 23, 2009 1:34 am

:lol: :lol: :lol:
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Mon Nov 23, 2009 2:01 am

ማብራሪያያላንቺ ህይወቴ
ፒሪሪም ፓራራም
ፓራራም ፒሪሪም....
አወድሰኝ አይደል
ስቀለኝ ካንገትህ
ነገ ስትጫማኝ
ግራ ከሚገባኝ
ወደድኩህ ማለቴን
አርገህ ውሰድልኝ
በጎደለ ሙላኝ ::
ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests