የያሚ ግጥሞች.....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby yammi » Fri Sep 01, 2006 8:39 pm

እህቴ..........
ባንገትሽ ድሪ
በእጆሽ አምባር
ደርድሪ
"ወጣት እያለሁ" የሚለውን
ዛሬ ቋጥሪ የወግ ስንቅሽን
ወጣትነት ጥሎሽ ሲነጉድ
አትሰሚውምና ቃጭሉን
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sun Sep 03, 2006 5:00 pm

ለካስ ጨረቃዋ ናት
በግዛቷ የሾመችሽ
በደብዛዛ ብርሀኗ አክስማ
ከእይታዬ ያራቀችሽ
ለካስ ጨረቃዋ ናት
ለነፍስሽ የድረሱልኝ ጥሪ
ምላሽ የነፈገችሽ
ከቅንዝረኛ ወግና
በዝምታ ያጀበችሽ
ለካስ.... ለካስ.... ጨረቃዋ ናት
የበላችው አደራ
በስቃይሽ ትንፋግ ሰክራ
የረገጠችው ዳንኪራ
በንጋት
ውብ ነፍስሽን አየኍት
በብርሀን ጭንብሏን ተገፋ
አንድ ቀን ላያጎርሳት
እድሜዋን ሙሉ ካሳቀቃት
ከአዳም ወ ሄዋን ዘር ሽሽት
ከቅራቅንቦ ስር ተወትፋ


3/9/2006
(በሴተኛ አዳሪነት ለሚተዳደሩት እህቶቼ ሁሉ)
Last edited by yammi on Sun Sep 03, 2006 10:29 pm, edited 1 time in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Sun Sep 03, 2006 5:05 pm

ሲለኝ ስቀኝላት
ሲለኝ ስሞግታት
የታዘበኝ አምላክ አውጫጭኝ ሳቆማት
እንደው ላንድ ጀንበር ልሳንን ቢያድላት
ጨረቃ ምን ትለኝ ያቺ ግኡዝ ፍጥረት

3/9/2006
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ቶታአው » Mon Sep 04, 2006 3:48 pm

ዬሚዬ በቃ ዝም ብለሽ ፍስስስስስስስስስስስስስ

አቤት ተሰጥኦ::


ሑኚበት አንቺስ የምር ተፈጥረሽዋል ለዝሁ::


አድናቂ ጦጣሽሽሽ
ቶታአው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Mon May 31, 2004 12:39 pm

Postby yammi » Mon Sep 04, 2006 4:36 pm

ምን ላድርግ ብለህ ነው ጦጥሽ ይህ የስደት ኑሮ እንኳን እኔን ዱዳስ ያናግር የለ እንዴ.............. በጭንቅላቴ ላለፈ ላገደመው ሀሳብ ሁሉ ግጥም ካልገጠምኩ ብዬ ትንቅንቅ ይዤልሀለሁ....

ለአድናቆትህ በጣም አመሰግንሀለሁ

ያንተው ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Mon Sep 04, 2006 4:51 pm

ፍ..ል..ቅ...አለ
እንባዬ......
ቁልቁል ተንደረደረ
ከጉንጮቼ ላይ ነጠረ
አንዱ ካንዱ እየተጣመረ
ደረቴ ላይ ደነከረ::
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby sleepless girl » Tue Sep 05, 2006 12:32 am

[quote="yammi"]ውብ ከናፍርቶችህን ቀምሼ
በአይኖችህ ብርሀን ነግሼ
ልሙት
ጥንቅር ይበል
ቀሪው ህይወት
ሞልቶ የማያውቅ ጎዶሎ
ክዳን የለሽ አክንባሎ
ይሄም ኑሮ ህይወት ተብሎ
ይቅር ሁሉም ጥሎኝ ይሂድ
ራዕይ ሆኖ ከሚቀር
ባይተዋር አርጎኝ ይንጎድ
ግድም የለኝ
ኖሮ አይጠቅመኝ
ሄዶ አይጎዳኝ
ከሰላሳ የምኞት ቀን
አንድ ሰከንድ ይበቃኛል
ሰፊው ትከሻህን ተንተርሼ
ውብ ከናፍርቶችህን ቀምሼ
በአይኖችህ ብርሀን ነግሼ
ከዚያ ብሞት ይሻለኛል


yammi ግጥሞችሽን በጣ........ም ነው የምወድልሽ:: "ምን ጻፈች" ዛሬ ደግሞ ብዬ ነው ሰፍ የምለው ከምር:: በጣም ታለንትድ ነሽ::
በተለይ ....በተለይ ግን ከላይ "quote" ያደረኩት ግጥምሽ ህምምምምምምምም በቃ ቆሜ ያጨበጨብኩለት ነው:: :wink: ትዝታ...... የሆነ ቦታ......ምናምን በሀሳብ ይወስዳል::

አድናቂ
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Postby Jossy1 » Tue Sep 05, 2006 5:33 am

ሻንጣዬን ጠቅልዬ
ጓዜንም አዝዬ
እዚህ ኑሮ በቅቶኝ
እዚያ እያጓጓኝ
ከዚህ ተነስቼ
ለእዚያ በቅቼ
እዚያ እዚህ ሲሆን
እዚያኛው ናፈቀኝ::

ሁሌም ከእዚህ እዚያ ይሻላል የተሰኘ አባባል መነሻ ሀሳብ ሆኖኝ
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby yammi » Tue Sep 05, 2006 5:00 pm

to sleepless girl

ግጥሞቼን እየተከታተልሽ በማንበብሽ ምስጋናዬ የላቀ ነው...ምርጫሽም እኔም ከምወዳቸው ግጥሞቼ አንዱ ነው::ትክክለኛውን የውስጤን ስሜት በቃላት መከተር የቻልኩበትን ግጥሜን ከሁሉም አብልጬ እወደዋለሁ...አንቺ "quote" እንዳደረግሽው አይነቱን ማለቴነው::

አክባሪሽ ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Tue Sep 05, 2006 5:16 pm

]
ሻንጣዬን ጠቅልዬ
ጓዜንም አዝዬ
እዚህ ኑሮ በቅቶኝ
እዚያ እያጓጓኝ
ከዚህ ተነስቼ
ለእዚያ በቅቼ
እዚያ እዚህ ሲሆን
እዚያኛው ናፈቀኝ::

jossy1.....እኔስ ስትጠፋ አዝኜ ነበር:jossyን የበላ ጅብ ብልም አ...ው የሚል አጣሁ:: በሰላም እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ::

ከላይ "quote" ያደረኳትን ግጥምህን ውድድድድድ ነው ያደረኳት..ትክክለኛ የህይወት ቅንጫቢ ናት....

እባክህን አትጥፋ

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Wed Sep 06, 2006 10:47 pm

ያባቷ አባት የናቴ
"ልጄ" አለኝ ቅም-አያቴ
አሁን...............................
ከእሾህ የተጠጋ ቁልቋል
እድሜውን ሙሉ ቢያለቅስ
ምን ይገርማል?
ግርታን ለብሶ ፊቴ
አልኩኝ...............

እንዴት አይገርምም አያቴ
እድሜውን ሙሉ ያለቀሰ
እንባው ካምላክ ዘንድ ካልደረሰ
የመጽሀፉ ቃል እኮ ተጣሰ!!!

አይ ልጄ......
ለካስ ልብ አላልሽምና
የዚችን አለም ገመና
ቁልቋል በእሾህ ታጥሮ
ለእሾህ ካለቀሰ
ከራሱ በላይ ማን ሆነና
የአኗኗርን ህግ የገሰሰ
እሾህን በእሾሁ እንደመውጋት
በእንባው ጠላቱን ያነገሰ
6/9/06
HELVETIA
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

ቆንጆ ነው

Postby ሩሃማ » Thu Sep 07, 2006 1:51 am

.
.
.
.
.እንዴት አይገርምም አያቴ
እድሜውን ሙሉ ያለቀሰ
እንባው ካምላክ ዘንድ ካልደረሰ
የመጽሀፉ ቃል እኮ ተጣሰ!!!

አይ ልጄ......
ለካስ ልብ አላልሽምና
የዚችን አለም ገመና
ቁልቋል በእሾህ ታጥሮ
ለእሾህ ካለቀሰ
ከራሱ በላይ ማን ሆነና
የአኗኗርን ህግ የገሰሰ
እሾህን በእሾሁ እንደመውጋት
በእንባው ጠላቱን ያነገሰ!!


ያሚ


Image
ሩሃማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 145
Joined: Mon Aug 14, 2006 11:12 pm
Location: Magnetica

Postby Jossy1 » Thu Sep 07, 2006 7:59 am

አሁን ምን ማለት ነው ያለብኝ እንዲህ አይነት ውብ ግጥም ሲያጋጥም? ገጣሚ ይሉዋችሁዋል ያሚ

ራሴን ናቅኩት
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby yammi » Fri Sep 08, 2006 4:55 pm

ሩሀማ

ለግጥሜ ውበት ስለሰጠሽው ከልብ አመሰግንሻለሁ::

ጆሲ

አንተንም ለአድናቆትህ እንዲሁ....ከልቤ አመሰግናለሁ::

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ዋናው » Sun Oct 22, 2006 10:36 pm

ያሚያችን እቺን የግጥም መድብልሽ ከሣሎኑ ብዙም ባታሪቃት መልካም ነው::

ዋናው________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests