የያሚ ግጥሞች.....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዝርዝሩ » Fri Oct 27, 2006 2:22 pm

የያሚ ግጥሞች ከነዜማችው ቢሆኑ እንዴት ውበታቸው በጨመረ ነበር :lol: :lol: :lol: :lol:
ለማንኛውም በርቺ በዚሁ/በበለጠ ቀጥይበት ::
መልዕክትና ለዛ ያላቸው ግጥሞች ናቸው::
ዝርዝሩ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 311
Joined: Sat Mar 18, 2006 10:47 am

Postby yammi » Tue Oct 31, 2006 5:23 pm

ዋናው............................ከፍ ያለ ምስጋናዬ ይድረስህ

ዝርዝሩ........................ ስለ አስተያየትህ በጣም አመሰግናለሁ::

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Tue Oct 31, 2006 5:27 pm

ከአመታት በኍላ ዛሬ
ካንተ መራቅ መጀመሬ
አሁን ገና ታወቀኝ
ትዝታህን አደብዝዞ
ገጽህን ጊዜ ሲሰርቀኝ


(ለአባቴ)
31/11/2006
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ክርስትያን06 » Tue Oct 31, 2006 6:15 pm

ይህ ወንዝ ምን ያጮህዋል? ሲባል መልሱ... የውስጡ ድንጋይ አሉ.::

ያሚቲ ውስጥሽ የሚነግርሽን ታፈሽው ጀመር አይደል!

ግሩም ናቸው ሁሉም
ክርስትያን06
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 601
Joined: Fri Sep 08, 2006 5:15 pm

Postby ሾተል » Mon Nov 06, 2006 7:36 pm

ያሚዬ....አንጎልሽ ከገደብ በላይ ይስፋ....የሚጽፉ እጆችሽ ይለምልሙ....ክብረ ሰውነትሽ ለዘላለም ይኑር....

ምንም አይወጣልሽም....ጥልቀትሽና እይታሽ ከግምት በላይ ነው.....በህሊና ህይወትን የምትዳስሽበት የመናብ እጅሽ እርዝመቱ በመለክያ አይመተርም.....ምን እላለሁ ቅጥያሽን ሳታቆሚ እየቀጠልሽ ከግጥም ምግብሽ እንዳንራብ አደራ መግቢን....ድርቅና ውርጭ አታስመችን...ታስፈልጊናለሽ...

ከማይቆጠረውና ከማይወሰነው አክብሮትና ፍቅር ጋር

ቾተል ነኝ ከአድናቂዎችሽ አንዱ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Nov 06, 2006 7:46 pm

ያልተገባደደው ህይወቴ
ያልደረጀው አካላቴ
ያልበሰለው እኔነቴ
ሲናከስ ይውላል
ከኔ ሌላ የለም ይላል
ማፈር እንኩዋን አይዳዳኝ
ከሰው ማነሴን አያበስረኝ
ሁሌም ከኔ በላይ ላሳር እላለሁ
እፍረቴን ሸጬ በልቻለሁ
ተስፋ አስቆራጭ ፍጡር
በምቀኝነት አለም ምግተረተር
ውስጤ በሰው ኑሮ ይነዳል
ሰላም እየነሳኝ ይውላል
የሌላውን ህይወት ሳይ በአይኔ
አለም ሸሸችኝ ከኔ
አሁን ባዶ ቀርቻለሁ
ነገር ሁሉ ጨልሞብን እውላለሁ
አቤት ምን ይሆን መጨረሻዬ
ሳልኖር የኖርኩ ድንክዬ
መቼም ተኖረ ተብሎ ይሞታል
በምስጥ ተበልቶ ሁሉም ያልቃል


ሾተል ነኝ ግጥም የማይችል
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ጉዱ ካሳ » Tue Nov 07, 2006 1:35 am

ውድ ያሚታ!

ሁሌም ቤትሽ ገብቼ የግጥሞችሽን መድብል እያነበብኩኝ እየወጣሁ ከዛሬ ነገ ጥልቅ ምስጋና አቀርባለሁ ስል ይኽው ቀናቶች ተቆጠሩ! በእውነት የምትጽፊያቸው ግጥሞችሽ ውብና ጥልቅ ስሜት የሚፈጥሩ ናቸው!

ያሚታ ምናለ እነዚህን ግጥሞች የሚጽፉት ጣቶችሽን አግኝቻቸው በሳምኩዋቸውና አድናቆቴን በይበልጥ በቸርኳቸው!

እስቲ በአብዱረህማን ሰኢድ "የኑሮ ቀለም" ከሚለው የግጥም ስንኞች ከተቋጠረው አንዱን "ፍለጋ' በሚለው ከቤትሽ ለጊዜው ልስናበት::

ፍለጋ

ሳነበው ሲያነበኝ
ኖረን ስንናበብ
ስጠበው ሲጠበኝ
ከርመን ስንጣበብ
አጥቦ ለቀቀኝ
ፈለገና ጥበብ


ጉዱ ካሳ
ከፒያሳ
ጉዱ ካሳ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 356
Joined: Wed Oct 22, 2003 6:22 pm

Postby ሾተል » Tue Nov 07, 2006 5:15 pm

ባይኔ ብረት አይቻት
በፍላጎት ህሊናዬ ተመኝቻት
ልቤን እንድትመታው-
ከፍቼ ሰጠሁዋት.....


ቅቅቅቅ ሾተል?!
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue Nov 07, 2006 5:22 pm

በፍቅሯ ኢላማ አልማኝ
ነግቶ እሷን በማብሰልሰል መርዝ አድምታኝ
ልቤን ስልብ ብታደርገው
ሀይል አልባ ሆኜ ቀረው


ሾተል እናስ?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue Nov 07, 2006 6:44 pm

የልብ እጦቴ ትውስ ባይለኝ
አንጎሌን ደደብነት ሰልቦት ባገኝ
ኧረ ማን ይንገረኝ በሞቴ
የቱ ነው ሰውነቴ


ሾተል!አቤት!....እመት!
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby yammi » Tue Nov 07, 2006 7:34 pm

ክሪዬ ....የልቤን ታውቀው የለ::


ጉዱዬ...........የናፈቀኝ ሰው

በጣም አመሰግናለሁ:: ያዳበልከውም የአብዱራህማን ሰኢድ ግጥም ግሩም ነው:: በሚቀጥለው ግን የአንተን ግጥሞች ነው የምጠብቀው::

ሾተል.....
..

እንዲህ አይነት ድንቅ ተሰጥኦ እያለህ አታሹፍ ...............ጥበብ በቤትህ እንዳለች ግጥሞችህ እማኝ ናቸው:: የዛሬዎቹንማ ውድድ አድርጌያቸዋለሁ:: እስቲ ጨምር...................እኔም ትንሽ ጫር ጫር አድርጌ እመለሳለሁ............ምስጋና መሆኑ ነው

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby yammi » Tue Nov 07, 2006 9:04 pm

እድሜ ከጠገበችው
ከባለቀለሙዋ ሙዳዬ
ከክት ጌጦቼ ጋራ
የሰነቅሁህ እዳዬ
ትዝታዬ
ጌጦቼ
ደረቴን ቢሳለሙ
ከጡቶቼ መሀል ቢሰየሙ
አድማቂ
የክት-ክት መዋቢያዬ
ማን እንዳንተ
ትዝታዬ
ትዝታዬ::7/11/2002

ፖ....ሬ
Last edited by yammi on Tue May 08, 2007 11:00 pm, edited 1 time in total.
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ሾተል » Wed Nov 08, 2006 4:43 pm

yammi wrote:ሾተል.....
..

እንዲህ አይነት ድንቅ ተሰጥኦ እያለህ አታሹፍ ...............ጥበብ በቤትህ እንዳለች ግጥሞችህ እማኝ ናቸው:: የዛሬዎቹንማ ውድድ አድርጌያቸዋለሁ:: እስቲ ጨምር...................እኔም ትንሽ ጫር ጫር አድርጌ እመለሳለሁ............ምስጋና መሆኑ ነው

ያሚብለሽ ነው አሚዬ....ይሁን እስቲ.....
አንድ ጀባ ልበልሻተከፋፍለን
ተቧጭቀን
ተቋርሰን
በፍቅር ሆነን
ለፍቅር አድረን
እንዳልበላን
እንዳልጠጣን
ተዋውሰን
እንዳልለበስን
ምነው ዛሬ ፍቅር ርቆ አራራቀን.....

ሾተል ነኝ አዎ ነኝ...
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ቤቲ_13 » Fri Nov 10, 2006 1:28 pm

ቅቅቅቅ----ለሾተል.....c/o ያሚቲ
የፍጥረታት-- ህጉን
የወጣትነት--- ግዜዉን
ጠብቆ ---ተጣብቆ
ተዋህዶ---ወድቆ
ተዕዛዙን---አክብሮ
እሳት-ሆኖ-ነዶ
ተፈጥሮ--ሊፈጠር
ዕንደዛ--እንዳልነበር
የሆዴ መገፋት--ሚስጥሩን ሊያበስር
የኤዶም ገነት ጭቃ--በሆዴዉስጥ ያለዉ
እንደዉ ቅርት ቢል--ወሩን ቢያሳልፈዉ
ወደምድር አምጥቼ--ዕንደ እኔ ከማሰቃየዉ
ብዬ.......አስገደልኩት
ራሴዉ ፈርድኩበት
....ፍቅርንም አብሬ ቀበርኩት.....
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby Naturelle » Fri Nov 10, 2006 2:11 pm

በእውነት ጥሩ ጥሩ ግጥሞች ናቸው! በተለይ yammi እለታዊ ስሜትሽን የምትገልጭባቸውና ከልብሽ የምታፈልቂያቸው ግጥሞች መሆናቸውን በደንብ ስለሚያሳይ ቆንጆ ነው: ቀጥይበት እላለሁ!

አድናቂሽ: ናቱሬለ
Naturelle
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 72
Joined: Thu Jun 15, 2006 3:49 am
Location: S. America

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest