የቦሬ ልጆች በዋርካ ጥላ ስር:

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የቦሬ ልጆች በዋርካ ጥላ ስር:

Postby ማርና ወተቴ » Fri Oct 13, 2006 10:03 pm

ተወልደን ያደግንባትን የቦሬ ከተማን ታሪክ ለማወቅና እንዲሁም በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ የሚገኙ የቦሬ ና አካባቢው ልጆችን አላማው በዚህ መድረክ በማገናኘት የበለጠ እንድንቀራረብ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር በመሆኑ ሁላችሁም እንድትሳተፉ ይሁን እያልኩ---
ለዚህ ያነሳሳኝ ዋና አላማ በዚሁ ዋርካ ላይ የክብረመንግስት ልጆች እንዲሁ ጀምረው አሁን ብዙ ሰው ተሰባስቦ,ስንት ታሪክ ና ልምድ እየተለዋወጡ መሆኑ በጣም ያስደስታል::እኔ አዶላን አንድ ሁለቴ ከማየት በቀር ምንም ስለ ከተማው ባለማወቄ ነው እንጂ ገብቼ ብሳተፍ ደስ ይለኝ ነበር:ሆኖም ሁሌ ስለ አዶላ ከማንበብ ሳልቆጠብ ብዙም ነገር ስለ ቦሬ እያነሱ በማዬቴ ና ጥቂት የቦሬ ልጆችም እንደሚሳተፉ ስለአወኩ ብዙሀኑን ለማሳተፍ በሚል ነው: በዚሁ አጋጣሚ ይህንን ለምታዩ በዋርካ የአዶላ ልጆች ብዙ ልምድ አካብታችኋልና ብቅ እያላችሁ እንድትጎበኙን ይሁን::
ኢጆሌ ቦሬ!
Last edited by ማርና ወተቴ on Mon Dec 03, 2007 2:32 am, edited 2 times in total.
az
ማርና ወተቴ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 72
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:21 pm
Location: england

Postby ሲሞሎ » Fri Oct 13, 2006 11:45 pm

የትነው ቦሬ : ሱዳን ውስጥ ነው ወይ ?
ENTEYAYALEN
ሲሞሎ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Tue Oct 10, 2006 10:18 pm
Location: baku

Postby ቺኮኩባኖ » Sat Oct 14, 2006 3:35 am

ሲሞሎ ቦሬ የሚገኝው ከአዋሳ 150 ባልሳሳት ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው እንደዚህም ስልህ አዋሳ ደግሞ የትነው ኬንያ ነው ? እንደማትለኝ ነው
ቦሬ በጣም ቀዝቃዛ የአየር ጸባይ ያላት ስትሆን የወተት የነጭማር [ገተሜ] የቅቤ የገብስ እና የጥራጥሬ አገር ናት እስከማውቃት በተለይ የቦሬ ጠጅ ምን ልበልህ ብቻ ተወው አንተ አረቄ ይሆናል የምትወደው ቅቅቅቅ በተጨማሪ የቦሬ ልጆች በደንብ ያስረዱህ
ቺኮኩባኖ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 279
Joined: Thu Sep 14, 2006 12:16 am
Location: usa

Postby አዋሳው » Sat Oct 14, 2006 2:54 pm

የቦሬ ነጭ ማር እና ቆሎ ባይኔ ላይ መጣብኝ
አዋሳው
አዋሳው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 646
Joined: Tue Apr 19, 2005 11:03 pm
Location: ethiopia

Postby ማርና ወተቴ » Sun Oct 15, 2006 12:13 am

በመጀመሪያ ሁላችሁንም ምላሽ በመስጠታችሁ እያመሰገንኩ:
ምነው ወንድሜ ሲሞሎ? እኔ እንኳ በአረቢኛ አልጻፍኩ ቦሬ ሱዳን ነወይ ምትገኘው ስትል ትንሽ ባዝንም ደግሞ በተሳታፊነትህ የበለጠ ተደስቻለሁ::
ሁሉም ሰው ትውልዶ ያደገበት አካባቢ አለው:ያሰው ደግሞ ቦታዋ ትንሽም ትሁን ትልቅ, ከምንም ከማንም አስበልጦ ይወዳል::እኔ ለምሳሌ ከኒውዮርክ , ከፓሪስ ና ከቦሬ ማንን ትወዳለህ ብትለኝ ማንን የምል ይመስለሀል? አንተስ ተወልደህ ያደክባት የምትወዳት አካባቢ የለህም?
ወንድሜ ቺኮ ኩባኖ=ለሰጠኸው አስተያየት በጣም አመሰግንሀለሁ ቦሬን በደንብ እንደምታዉቃት ነው;እንዳልከው ቦሬ ከአዲስ አበባ 385 ኪ/ሜ ከአዋሳ 110 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ,ደጋማ የአየር ጸባይ ያላት,በገተሜ ነጭ ማር, በወተት, በቅቤ, በገብስ ,እንዲሁም በንጹህ የማር ጠጅ የምትታወቅ ናት::እንዲሁም ይህቺ ትንሽ ከተማ ብዙ ድንቅ የሆኑ ልጆችን ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ(ከዚያ ትንሽ ከተማ የወጡ በማይመስል) ማለቴ ነው ያፈራች ናት::ከኔ በበለጠ ወደፊት ብዙዎች ስለ አካባቢው እንደሚያጫዉቱን አምናለሁ::
ወንድሜ አዋሳ= አኔኪራ ከስምህ የአዋሳ ልጅ እንደሆንክ አልጠራጠርም! አዋሳ ከትዉልድ ቦታዬ ቀጥሎ የምወዳት ምርጥ ከተማዬ ናት::አንተም የቦሬ ማርና ቆሎ ትዝታን በማንሳትህ ቀደም ሲል አዋሳ ቶታል(ሀይሌ ጋሼ) ምሽት ክበብ ቴዎድሮስ ቬንቼንዞ የሚባል ዘፋኝ የተጫወተዉን <ያየ ሰው ይናገር>የሚለዉን ዘፈን መርጬልሀለሁ::
ሀገራችንን እንወቅ!
ኢጆሌ ቦሬ!!!!
az
ማርና ወተቴ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 72
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:21 pm
Location: england

Postby ነጭ ማር » Sun Oct 15, 2006 1:40 am

በጣም ይገርማል ኬንያ ያለ ወንድሜ ይህ አምድ መጀመሩን ደውሎ ሲነግረኝ ማመን ነው ያቃተኝ;;በእውነት ለማርና ወተቴ ምስጋና ይድረሰው;;እኔም እንዳንተው ያዶላዎቹን ትዝታ እከታተል ነበር ;;ይሁንና ከአንደ በላይ መጻፍ አልቻልኩም ;;ምክንያቱም ትዝታው ብዙም የለኝምና ነው;;አሁን ግን ያለኝን ትዝታ ሁሉ እተረትረዋልሁ;;እድሜ ለማርና ወተቴ;;በሉ አሜሪካ ካናዳ አውሮፓና አፍሪካ እንዲሁም ሀገር ቤት ያላችሁ ሁሉ ተነቃነቁ;;ነገ በትዝታ እመለሳልሁ እስከዚያው ደህና ሁኑልኝ;;
ነጭ ማር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Sun Oct 15, 2006 1:24 am
Location: america

Postby ሞፊቲ » Sun Oct 15, 2006 5:32 pm

እንደምን አላችሁልኝ የወንዜ ልጆች;;የአዶላ ልጆች የተሰባሰቡበት ገጽ ላይ ስገባ ነው ይህንን ርእስ እንደዋዛ ያየሁት;;እንደው ለመሆኑ ማርና ወተቴ እውነት የቦሬ ልጅ ነህ? በጣም ነው የተደሰትኩት;;በል ብዙ ብዙ የምተረትርልህ ነገር ይኖራልና በርታ;;አዋሳው ቺኮኩባኖና ነጭ ማር የደመቀ ሰላምታ አቅርቤአለሁ;;ማርና ወተቴ እስከዚያው የዝናየ ታፈሰን(ቦኔያ ኪቹ) የቦሬዋ የሚለውን ዜማውን እያዜምክ ጠብቀኝ;;
ሞፊቲ ነኝ;;ቸር ያሰንብተን
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ማርና ወተቴ » Sun Oct 15, 2006 8:14 pm

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! እያልኩ ነጭማር ና ሞፊቲን በጣም አመሰግናችኋለሁ::በሉ እናንተም ላልሰሙት አሰሙ ና ሞቅ ሞቅ እናድርገው::
ሞፊቲ-ለመረጥክልኝ የቦኔያ ዘፈን አመሰግናለሁ:የሚገርመው ያልከው ልጅ ዝናዬ ታፈሰ(ቦኔያ) ድንቅ ችሎታ እያለው,ችሎታው እዚያው ተዳፍኖ የቀረ ልጅ ሲሆን:ቀደም ሲል በሰራዊቱ ኪነት ዉስጥአገልግሎ ከዚያ በህዋላ ቦሬ ገብቶ ቀረ:በአንድ ወቅት ከአ/አ ማዘጋጃ ቤት ትያትርና ዉዝዋዜ ክፍል ሰዎች ስለ እርሱ ሰምተው ሊወስዱት ቦሬ መጥተው እሱ ለሊቱን ቡቂሳን ተሻግሮ ቡሌ መግባቱን በሚገባ አዉቃለሁ::እኔ በግሌ የምወድለት ቡሉኮ ለብሶ,ጦር ይዞ እንደ ገጠር ሰዎች የሚሆነው:ዘፈን ደግሞ ገመቹ(የአሊ ቢራን) ሲጫወት እንዲሁም ማእበል ነው የሚለዉን(የንዋይ ደበበ) ዘፈን በተሰባበረ አማርኛ ሲለው እጅግ እደሰት ነበር::እኔም አንዳንዴ እንደርሱ ትዝ ሲለኝ የቦኔያ ማላበል እያልኩ አንጎራጉራለሁ::
በተረፈ ቦኔያ የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ትንሽ አሞት አዲስ አበባ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተኝቶ ቀዶ ህክምና ተደርጎለት በሚገባ ተሽሎት መመለሱን አዉቃለሁ::
ሞፊቲ የቦሬ ስለምትለዋ ዘፈኑ አላዉቅምና እስኪ አጫዉተን::
ሰላም ሁኑ!
az
ማርና ወተቴ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 72
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:21 pm
Location: england

Postby ቺኮኩባኖ » Mon Oct 16, 2006 3:51 am

ሰላም ሞፊቲ እንዳንተ አካባቢወን የሚወድ አላየሁም
የአዶላልጆች ፔጅ ላይ አይቼሀለሁ የምትሰጠው አስተያየት የሚደነቅ ነው . ምናልባት እነጸግሸት ወርቁን ግዛቸው ሴይፉ ሙላቱንታውቃቸው ይሆናል ጥሩ ወዳጆቼ ናቸው
በተረፈ ይህን ሀኒከን እየጠጣው ሰለቦሬ ሳነብ የታንጉት ቤት የገተሜ ጠጅ ባይኔ ዞረብኝ በተረፈ ቸርያቆየን ያለኝን ተዝታ በሚቀጥለው እጽፋለሁ.
ቺኮኩባኖ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 279
Joined: Thu Sep 14, 2006 12:16 am
Location: usa

Postby ሞፊቲ » Mon Oct 16, 2006 5:09 am

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን;;ቺኮኩባኖ ለሰጠኸኝ አስተያየት በጣም አመሰግናለሁ;;የጠራህልኝ ልጆች በሙሉ እጅግ እጅግ በጣም ወንድሞቼ ናቸው;;ከጸግሽት ጋ ከ ኢለመንተርይ ጀምሮ ክብረመንግስት ሀይስኩል ድረስ ክፍላችን ሁሉ ሳይለያይ አብረን ነው የተማርነውና ያደግነው;;እኔም ለሱ እሱም ለኔ የመጀመርያ ጓደኛማሞች ነን;;እስካሁንም ድረስ እንደዛው;;ወርቅየም የጸግሸት ወንድም ነው;;ግዛችው(ግብጣ)ን ቴኒስ ሲያከራይ ካዲስ አበባ ራኬት ገዝቼ ስጦታ ሰጥቸዋልሁ;;የሚገርምህ ይህንንጽሁፍ ፖስት ከማረጌ በፊት ለሙላቱ ሁሉ ደውየለታለሁ;;ሰይፉም ቤተሰባዊ ቅርርብ አለን;;በጣም የምወዳቸውን ልጆች ስም ነው ያነሳህልኝ;;እጅግ ሲበዛ አመሰግንሀለው;;

ማርና ወትቴ ስለቦኔያ ዜማ የጠየከኝ ላስነብብህ;;ደርግ እንደወደቀ ጦሩ ሲበተን ወደቦሬ ይዞ የመጣው እንደሌላው ክላሽንኮፍ ሳይሆን የራሱን ዜማ የያዝ አንድ ካሴት ብቻ ነበር;;በኦኬስትራው ከሚያዜማቸው ዜማዎቹ አንዱ የቦሬዋ ቆንጆ የሚለው ዜማው ልዩ ነው;;ድርሰቱም ግጥሙም የራሱ ናቸው;;ያንን ለመስማት በወቅቱ ወረፋ ይዘን ነበር ካሴቱን እንደመጻፍ ስንዋዋስ የነበረው;;


ሌላው እንዳልከው የቦኔያ ፈጠራዊ ችሎታው የሚያስደንቅ ነበር;;ኮሜዲው ያፈነዳል;;ኦ.. በጣም ብዙ ትዝታዎች ያሉት ሰው ነው;;

ቸር ያቆየን;;
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby አዋሳው » Tue Oct 17, 2006 7:59 pm

ማር እና ወተት ስለዘፍን ግብዣህ በጣም ነው የማመስገነው
እንደተረጠርከው እኔ የዋሳ ልጅ እና አዋሳዊ ነኝ
ሰላም ለቦሬ
አዋሳው
አዋሳው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 646
Joined: Tue Apr 19, 2005 11:03 pm
Location: ethiopia

Postby ነጭ ማር » Wed Oct 18, 2006 4:00 am

ጤና ይስጥልኝ; ቺኮኩባኖ ስለነጸግሼት ስታነሳ እኔም ደንገጥ አልኩኝ;;በጣም የምወደቸው ልጆች ናቸው;;ባክህ አንተና እኔም እዛች ታንጉት ጠጅ ቤት ጎጆዋ ውስጥ ሳንጠጣ አልቀረንም;;ምልክት ልንገርህ እንዴ? ለማንኛውም ግን ወደአዲስ አበባ ስትደውል ያ በጣም የምትወደውንና እሱም የሚወድህን ጓደኛህን ጌቱን(መርካቶ) በጣም ሰላም በልልኝ;;
ነጭ ማር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Sun Oct 15, 2006 1:24 am
Location: america

Postby ማርና ወተቴ » Fri Oct 20, 2006 12:51 am

ሰላም!ሰላም! እንደምን ሰነበታችሁ?
ሞፊቲ,ቺኮ ኩባኖ,አዋሳው-ሁላችሁም የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ:
ያነሳችኋቸዉን ልጆች እኔም በሚገባ አውቃቸዋለሁ:
ጸግሸት ተስፋዬ(አላቲ),ወርቁ ተስፋዬ(ዲቡ), ግዛቸው(ግብጣ),ሰይፉ ማእረግ, ሙላቱ ተሾመ እና ሌሎችም ብዙ ታሪክ ያላቸዉን ልጆች አንዳንዴ እያነሳን መጫወታችን አይቀርም::
ቺኮ ኩባኖ- እነዚህን ልጆች ካነሳህ ዘንዳ: ነፍሱን ይማረዉና ሳህለ ማርያምን ታዉቀው እንደነበር አልጠራጠርም:እና ስለእሱ ብዙ የሚገርሙ ነገሮች ሚያስቁ,ሚያዝናኑ ሰምቼ በጣም ደንቆኝ ነበር እስኪ አንተም ወይም ሞፊቲ ምታስታዉሱትን አጫዉቱን::
ሌላው ቦሬ በተነሳ ቁጥር ሳይነስ የማይቀረው የታንጉት ቤት ነው::መቼም ማንኛዉም ወደ ክ/መ, ሻኪሶ, ወይም ቦረና የሚሄድም ሆነ ሚመለስ ሰው ቦሬ ላይ ቆይታ ሳያደርግ የሚያልፍ የለም:ዋናው ማረፊያ ደግሞ የታንጉት ቤት ነው::
እስኪ ስለ ወ/ሮ ታንጉትና ስለባለቤትዋ ስለ አስር አለቃ በላይ ቦሬ እንዴት እንደመጡ ላጫዉታችሁ::
አስር አለቃ ለበኑ የተባሉ ፖሊስ በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ቦሬ ፖሊስ ሆነው እያገለገሉ እያለ አንዲት በቅሎ ከባለቤትዋ ግቢ በሌባ ትሰረቃለች:ታዲያ ይሄው ሌባ ከቦሬ ወረዳ የሰረቃትን በቅሎ እንደያዘ ይርጋ ጨፌ ከተማ አካባቢ ይያዛል: ሌባዉም ከነሰረቀው ኢግዚቢት በወቅቱ ይርጋ ጨፌ ፖሊስ ሆኖ ይሰራ በነበረው በአስር አለቃ በላይ ተበጀ አጃቢነት ተይዞ ይመጣል:እንግዲህ ይህ አጋጣሚ የጥንት ጓደኛዎችና የአንድ ኮርስ ምሩቅ የሆኑትን ለበኑን ና በላይን ያገናኛል ከዚያም በላይ ቦሬ በቆያበት ትንሽ ጊዜያትና በጓደኛው በተደረገበት ግፊት እንደተመለሰ ዝዉዉር ጠይቆ ከነቤተሰቡ መጣ:
መጀመሪያ ቤታቸው ኬላው አካባቢ ሲሆን ከዚያም መጨረሻ ወደነበሩበት የአቶ ጋሻው በዛ ቤት ጎን ገቡ የምግብ ስራዉም የተጀመረው የ ሀምሳ ሳንቲም ሽሮ ና የአንድ ብር በያይነቱ በመስራት ነበር የአቶ ጋሻው በዛ ባለቤትም ይህንኑ ትሰራ ስለነበር ፉክክሩ ከጥንት ነበር የጀመረው::የነታንጉትን ቦሬ አመጣጥ በላይ ና ለበኑ በአጋጣሚ እኔ ባለሁበት ሲጫወቱ የሰማሁትን ነበር ወደፊት ስለ እነዚሁ ሰዎች የምለው ይኖረኛል::
Give respect Get respect!
az
ማርና ወተቴ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 72
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:21 pm
Location: england

Postby ማርና ወተቴ » Fri Oct 20, 2006 5:05 pm

ይቅርታ! <ማረሚያ> ስላለኝ ነው የተመለስኩት;አስር አለቃ ለበኑ ሳይሆን አስር አለቃ በላይ ነው ቀድሞ ቦሬ የነበረው እና የተሰረቀችዉን በቅሎ ይዞ መጥቶ የቀረው ለበኑ መሆኑ ይታረምልኝ::ለበኑም ጡረታ ከወጣ በህዋላ ቤቱ ምርጥ ጠጅ ይሸጥ ነበር:እርማቱንም በግል አድራሻዬ የሰጠኝ ዉስጥ አዋቂ ና የሁለቱም ቤቶች ደንበኛ የሆነዉን ወዳጄን አመሰግናለሁ::
az
ማርና ወተቴ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 72
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:21 pm
Location: england

Postby ነጭ ማር » Sun Oct 22, 2006 8:17 am

አካም ኦልታኒ ኢጆሌ ቦሬ?/ማርና ወተቴ ጫወታውን አመጣኸው አቦ//ነፍሳቸውን ይማርና ጋሽ በላይ እጅግ እጅግ ሲበዛ የዋህ ሰው ነበሩ;;ለዚህም ይመስላል በዚያ አካባቢ የሚመላለሱ የጭነት መኪናዎች ሰው ጠቅጥቀው ጭነው የቦሬን ትራፊክ የማይፈሩት;;ታንጉት ጠጅ ቤት ደግሞ እሳቸው ካሸር ወንበር ላይ ከተቀመጡ ለኛ ቢጤዎቹ ዝልዝል ጥብስ ቦነሳችን ነበር;;<<እስቲ ያለ ይናገር እስቲ የነበረ ያውጋ>>ነው ነገሩ;;

ደግሞ ያነሳሀቸውን ልጆች ቅጽል ስማቸውን እንዴት አስታወስከው ባክህ? እኔም ልጨምርበት;;ሙላቱ -ቀዮ ሴፉ -ጬንጌሬ ዘውዱ _ቡሱሩ ደረጀ-ከባ ንጉሴ-ኡሞ ዮናስ -ቡታ ቴውድሮስ _ገንቢቲ መርእድ-ቦጃ እርቂሁን-ሀርጫው ውነቱ-ደንደሶ ሳሙኤል-አክትም(አባ) ሳሙኤል ሰሙ-ወይ ፍንክች ኤፍሬም-ዶቢቾ መላኩ-ቴቤሾ ለግዜው የማስታውሳቸው ሲሆኑ ቀሪውን አንተ እንደምትጨምርበት ተስፋየ ነው;;ይሁንና ግን ምንግዜም የማልረሳውን ወንድሜን ታደሰ ቡርንዶን ነፍሱን ይማረው እያልኩ አብሬ አስታውሰዋለሁ;;

እንግዲህ ከላይ የተጠቀሱት ቅጽል ስሞች ያለምክንያት የተሰጡ አይደሉም;;ለምሳሌ ያህል ሙላቱ -ቀዮ የሚለውን ስም ያገኘው አዲስ አበባ መጥቶ ካዛንችስ ሙሉ ሆቴል ሲዝናና ያስተናግደው ለነበረው ፍቅሩ የተባ ልጅ አስር ብር ቲፕ ስለሰጠው ከዚያን ግዜ ጀምሮ ልጁ ቀዮ መጣ ስለሚል በዚያው ያገኘው ስያሜ ነው;;አሁን ግን አጅሬ አጠቃሎ አዲስ አበባ ስለገባና የአዲስን ኑሮ ስላልተቋቋመ አስር ብር ደፍሮ ቲፕ የሚሰጥ አይመስለኝም;;እንጊዲህ የሌሎቹም እንድIህ እያለ ይቀጥላል;;ደህና ሁኑልኝ;;
ነጭ ማር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Sun Oct 15, 2006 1:24 am
Location: america

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests

cron