የቦሬ ልጆች በዋርካ ጥላ ስር:

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Dec 15, 2012 9:44 am

Gosa wrote:
ሰላም ቦሬዎች !
ስለ ቦሬ ት /ቤት መምህራን እና ት /ቤቱ እኔንስ ምን ትዝ ይለኝ ይሆን .....ስለምንወዳቸው አንቱታውን ለዛሬ ላስቀር :: አንጋፋ መምህራንን እነ መ /ር ተስፋዬ ኃይለጊዮርግስ ብርሀኑ ላቀው ነገራ ሙለታ እና ላቀው በጋሻውን ማንም ስለማይረሳቸው እዘላቸዋለሁ ::
አንደኛ እና ሁለተኛ ክፍል ስማር ምንም የማስታውሰው ነገር ያለ አይመስለኝም :: ወደ ሶስተኛ ክፍል አካባቢ ነው ትንሽ ጭላንጭሉ የሚመጣልኝ
መ /ርት አበበች ሔራንጎ A B C D ያስቆጠረችኝን አልረሳትም :: በዚያ ወቅት ደግሞ ደምሴ አንገሎ የሚባል መምህር ከሱታ እየተመላለሰ እንግሊዘኛ ያስተምረን ነበር :: ለሁለት ተራ በተራ ያስተምሩን ወይም እኔ ተቀባዥሮብኝ ይሆን እርግጠኛ አይደለሁም :: ሌላም ደምሴ አለ ....መ /ር ደምሴ ብዙነህ :: ቀላል አይጋረፍም :: ታዲያ አንድ ቀን ይገዙ ጉሚ ዱካሌ የሚባለውን ልጅ ቢገርፈው ቢገርፈው ልጁ አንድ አላለቅስ ይላል :: ኮቱን አውልቆ አስተኝቶት በልምጭ ጀርባውን ቢለጠልጠውም ልጁ ወይ ፍንክች :: ከዚያም መ /ር ደምሴም በመገረም በኦሮምኛ "Firri keeti maan?" ብሎ ሲጠይቀው ልጁ "maaf sitti himadha?" ብሎ ጥያቄን በጥያቄ መለሰለት :: ከዚያ መምህሩም በመገረም "ወንድ ነህ አልገርፍህም በቃ ተነስ " ብሎት ተወው :: በሆነ ወቅት በክላሰር (ዶሲ ) ላይ ስማችንን በትልቁ በፓርከር ጽፈን ማንገቻ ገመድ አበጅተንለት ገና የህብረተሰብ ክፍለ ጊዜ ሲደወል አንጠልጥለን እንጠብቀዋለን :: የልጆችስ ይሆን ባለትዳር እና የልጆች እናት የነበሩት ሴቶችንም ማሰቃየቱ ..እንደዚያው ትልቅ ክላሰር አንጠልጥለው ሲታዩ ፍርድ የሚጠብቁ እስረኞች ነበር የሚመስሉት :: የሳይንስ አስተማሪያችን የነበረች ደግሞ መስታወት ስትሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ሱሪ ለብሳ ያየኌት ሴት እሷን ነው :: ያኔ ግርም ይለኝ ነበር እንዴት እንደማታፍር :: ጅል እና ልጅም ስለነበርኩ ይሆናል :: ዛሬ ዛሬ ደግሞ ረጃጅም ሱሪዎቹም ፋሽኑ አልፎባቸው በጣም በረቀቀ እና በማይክሮስኮፒ ብቻ በሚታዩት ጥቃቅን አልባሳት ተተክተው ሳይ ተመስገን ስልጣኔ እና ቴክኖሎጂ እላለሁ ቅቅቅ :: ማይክሮስኮፒ የምለውን ስጽፍ ማን ትዝ አለኝ መሰላችሁ ...መምህር ጋሻው :: መነጸር የሚያደርጉ አፍሮ የሚያበጥሩ የሳይንስ አስተማሪያችን ... ግራጫ አይዶል ሱሪ ነበረው ::ድምጹ አሁን ይሰማኛል ...ሪፍራክሽን ..ኮንኬቭ ሌንስ ...ይሉ ነበር አብዝተው :: መምህር ግርማ መገንታንስ ታስታውሱት ይሆን ? ሁሌ ንጹህ እና ዘናጭ አስተማሪ ነበር ከእጅ ጽሁፉ በስተቀር :: ግብዴ ባለአራት ማዕዘን የጃፓን ሴኮ ሰአቱ ዛሬም ትዝ ይለኛል :: በምን አወቅክ እንዳትሉኝ የጃፓን መሆኑን ቅቅቅ :: ሳይጠይቁ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው :: ታዲያ እሱን ሳስታውስ አንተነህ ለበኑ ትዝ ይለኛል :: በጣም ተንኮለኛ ልጅ ነበር :: ክፍል ውስጥ አማርኛን ሲያስነብበው "መልመጃ " የሚለውን ቃል እራሱ ሆን ብሎ "ሞልሞጃ " እያለ እያነበበ ጋሽ ግርማን ያናድደው ነበር :: ዬት ይሆን አሁን ያ ልጅ ? በተቃራኒው የእጅ ጽሁፉ ከታይፕ የሚያስነቀው ደግሞ የመ /ር ግርማ ቦጋለ ነው :: አቤት ጽሁፍ ! ይህ ጽሁፉ ሳይሆን አይቀርም ማዕከል ውስጥ አስገብቶት ያስቀረው :: ሌላው ግርማ ደግሞ ጋሽ ግርማ ጉዳ :: ሁሌ እንደሳቀ :በህይወቴ አንድ ቀን ተማሪን ሲቆጣ አይቼ አላውቅም :: ግርማዎችን እዚሁ ትተን ወደ ላይ ከፍ እንበል :: መ /ር አሰፋን (ስከለተን ) የማያውቅ ያለ አይመስለኝም :: በህይወቴ ፊቱ ተፈቶ ሲስቅ አይቼው አላውቅም ካለ አንድ ቀን በስተቀር :: አንድ ልጅ ይረብሽና አስነስቶት ከተማሪዎቹ ፊት ያስቆመዋል ::
"ስምህ ማነው ?"
"ተስፋዬ "
"ተፋዬ ማ ?"
"ተስፋዬ ዲንቃ "
መምህሩ በሳቅ ወደቀ :: ደጋግሞ ስሙን እየጠያየቀው ብቻውን ይስቃል :: በመጨረሻም "ማን ይሆን አንተን ተስፋዬ ዲንቃ ያለህ ? ጅል ! ተስፋዬ ዲንቃ እንዳንተ ጅል ነው ? ና ውጣ !" ብሎት በካልቾ አንዴ ደህና አድርጎ አስገብቶለት ከክፍሉ አስወጣው :: ኌላ ነገሩን ሳስበው ተስፋዬ ዲንቃ የሚባል በወቅቱ ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣን (ጠቅላይ ምንስትር ) ነበር :: ከሱ ጋር አገናኝቶት ነበር ይስቅ የነበረው :: ወይ ጤንነት !
ሞት ይርሳኝና ማንን እንደረሳሁ ታውቃላችሁ ? ጋሽ መንግስቱ ታደሰን :: አቤት ...ሶቭዬት ኅብረት : ሌኒን : ኢምፔሪያሊዝም እና የሰርቶ አደሩ ፓርቲ ድሮ ቀረ :: ግርም የምለኝ ..."ዛሬ ሶቭዬት ኅብረት ውስጥ አንድ መኪና ቢገለበጥ መኪናው "ሾፌሩ እንዲህ ማድረግ ሲገባው እንዲህ ሳያደርጎ ቀርቶ ነው የገለበጠኝ " ብሎ ለሚመለከተው ክፍል መልዕክት ይልካል " ብለው የዛሬ ስንት አመት የነገሩንን :: በዚያ አይነት ያ መኪና አሁን ዬት ደርሶ ይሆን ? ወይ ፖለቲካ ! ከልቡ ፖለቲካ ነበር :: ሌላ ማን ነበር ፖለቲካ ያስተማረን .... አስታወስኩ ... ጋሽ ደመረው :: ጋሽ ደመረው እንኳ ሂሳብ ነው በጣም የሚያምርባቸው :: ያኔ ከኢሰፓው ካኪ ልብስ ጋር የሚያደርጉት ሀይለኛ ጥቁር ቡሽ ጫማ ነበራቸው :: ከጀርመን ነው የገዙት እየተባለ ይወራላቸው ስለነበር አንዳንዴ ትምህርቱን ሳይሆን የጫማውን አካሄድ ነበር እንከታተል የነበረው :: ይኼኔ እኮ እሱም አልቆ ተጥሎ ይሆናል :: ሲያሳዝን ! የአማርኛውን አስተማሪ አያለውን ማን ያስታውሳል :: "ሽልንጌን ሽልንጌ ...ፋጤ ወጂን ዴማ " የስንተኛ ክፍል አማርኛ ይሆን ? አቦ አሁን አግኝቼው ያንን ሽልንጌን ባነበብኩ :: አንድ ቀን ተክኤ ጉልበት ተመስጠው ሂሳብ ካስረዱን በኌላ ጥያቄ እንዳለን ሲጠይቀን ደረሰ ከበደ የሚባል ተማሪ እጁን ያወጣል :: የመጠየቅ ዕድል ሲሰጠውም "ጋሼ ነገ ትምህርት አለ እንዴ ?" ብሎ በመጠየቁ መምህሩ ተበሳጭተው "እንደው አንተ የምትጠይቀውንም አታውቅም ::"ከካም ! ብሎ ልጁን አስደነገጠው :: ልጁ በዕድሜ ከሁላችንም ይበልጣል :: ሀይለኛ ነጋዴም ስለነበር ቀኗን ለሽቀላ ነገር አስቦ ሳይሆን አልቀረም ::
ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ጸጉረ ሉጫ ወንድ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ ? የሂሳብ አስተማሪውን ዘውዱ :: ሴት ኢዝ ዘ ኮሌክሽን ኦፍ ቲንግስ ኦር ግሩፕ ኦፍ ኦብጀክትስ " ሀይ ሽምደዳ :: ሸመደድን ድሮ :: በኛ ጊዜ ሽምደዳ ነበር አሁን ችከላ ሆኖ ቀረ እንጂ ቅቅቅ :: ካሜራማን እና የሳይንስ መምህሩ ጋሽ ጥሩነህ ደግሞ በጣም ከምወዳቸው ጥቂት መምህራን አንዱ ነው :: ከልቡ ያስተምር ነበር :: ሀቢታት .. ኢንቫይሮመንት ...ኮሚዩኒቲ ...ምን ያላስተማሩት ነገር አለ :: እጅግ በጣም የምወደውን መምህሬን መቋጫዬ ላደርገው ነው እስካሁን ያላነሳሁት ... መምህር ጸጋዬ ፍሰሐን :: ማነው ዛሬ በ TTI ሰርቲፊኬቱ ሀይስኩል ገብቶ እንግሊዘኛን ለማስተማር የሚደፍር ! ባንድ ወቅት በስመ ሴርቲፍኬት ከሀይስኩል ወደ ጁነር ሲመልሱት ተማሪው አምጾ ነው እንደገና ወደ ሀይስኩል የተወሰደው :: በጣም ትልቅ ቦታ መድረስ የሚችል ሰው ስንቱ መንገድ ላይ ቀርቷል መሰላችሁ :: ለዛሬ እዚሁ ላይ ላቁምና በሚቀጥለው ትዝ ስለምሉኝ ተማሪዎች ትንሽ እጽፋለሁ ::

ሠላም ታላቅ ሰው Gosa

የማስታወስ ችሎታህን ከፅሁፍህ ምጥቀትና ጥልቀት ጋር በጣም በጣም አድንቄያለሁ.......በዚህ ግሩም የጽሁፍ አሳሳል ተስጥዖህ አንድ ሁለቴ ጨምረህ ከጻፍክልን; እኔም የቦሬ ልጅ ነኝ ብዬ በልበ-ሙሉነት ማውራት እጀምራለሁ :D

አክባሪህ
ዳግማዊ ዋለልኝ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby Gosa » Mon Dec 17, 2012 9:58 am

ወንድሜ ዳግማዊ ዋለልኝ!
እንደምን አለህልኝ

የስራህን ይስጥህ ልልህ አስቤ ነበር: አሁን ግን ተውኩት:: እኔ ራሴ በቀበሌ የታሸገ ቤት ሰብሬ ስለገባሁ ሌላ ማንም ፖስት የሚያደርግ አልመሰለኝም ነበር:: ታዲያ "ዋርካ ባህል እና ሥነ ጽሁፍ "ከፍቼ ለመጨረሻ ጊዜ ፖስት ያደረገ በሚለው ኮለም የራሴን ስም ብፈልግ ስሜን አጣሁ:: ምናልባት "ዋርካ ፍቅር" ውስጥ ይሆናል ቤቱ ያለው ብዬ እዚያም ከፍቼ ብፈትሸው የለም:: እነሞፊቲ "ተው አትክፈት ይህንን ቤት" እያሉኝ ስለነበር ከአድሚኖቹ ጋር ተነጋግረው አንስተው ይሆን እንዴ ብዬም ትንሽ ተጠራጠሬ ለመጨረሻ ጊዜ ባርስቱ ስፈልገው ነው ያገኘሁት:: እዚህ ትገባለህ ብዬ በፍጹም አልገመትኩም ነበር::
ስለ አድናቆትህ እግዜር ይስጥልን:: እኔም ዋርካ ውስጥ ከምከታተላቸው ሰዎች መሀል አንተ አንደኛው ስትሆን በዚሁ አጋጣሚ ደግሞ ክቡራን ደጉ ሐያት ጌታ ሙዝ እና ሾተል የሚጽፉት ይመቸኛል:: አቀራረባችሁ አይሰለችም:: አንባቢን ይስባል(እኔን ልበል እዚህ ላይ :D አንዱ አንዳንዴ ትንሽ ወጣ ይላል እንጂ :D :D ማን እንደሆነ ግን አልነግርህም :wink: መቼም የፈረደበት ሾተልን ነው የምትጠራጠረው አይደል :D እኔ አላልኩም :D
አንድ ሁለቴ ጨምረህ ከጻፍክልን ; እኔም የቦሬ ልጅ ነኝ ብዬ በልበ -ሙሉነት ማውራት እጀምራለሁ

:D :D ቀላል ነው:: በኦሮሞ ባህል መሰረት የሆነ ስር መሳይ ነገር ታኝክና በቅርቡ የቦሬን ዜግነት ትወስዳለህ :D :D ከዚያማ በኔና ባንተ መሀል ምንም ልዩነት አይኖርም:: ቦሬ ተወለድኩ ሁሉ ልትል ትችላለህ :D

ይመችህ ወንድሜ!

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:

We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Wed Dec 19, 2012 9:41 am

በድጋሚ ሠላም ታላቅ ሰው Gosa

Gosa wrote:ወንድሜ ዳግማዊ ዋለልኝ!
እንደምን አለህልኝ

የስራህን ይስጥህ ልልህ አስቤ ነበር: አሁን ግን ተውኩት:: እኔ ራሴ በቀበሌ የታሸገ ቤት ሰብሬ ስለገባሁ ሌላ ማንም ፖስት የሚያደርግ አልመሰለኝም ነበር:: ታዲያ "ዋርካ ባህል እና ሥነ ጽሁፍ "ከፍቼ ለመጨረሻ ጊዜ ፖስት ያደረገ በሚለው ኮለም የራሴን ስም ብፈልግ ስሜን አጣሁ:: ምናልባት "ዋርካ ፍቅር" ውስጥ ይሆናል ቤቱ ያለው ብዬ እዚያም ከፍቼ ብፈትሸው የለም:: እነሞፊቲ "ተው አትክፈት ይህንን ቤት" እያሉኝ ስለነበር ከአድሚኖቹ ጋር ተነጋግረው አንስተው ይሆን እንዴ ብዬም ትንሽ ተጠራጠሬ ለመጨረሻ ጊዜ ባርስቱ ስፈልገው ነው ያገኘሁት:: እዚህ ትገባለህ ብዬ በፍጹም አልገመትኩም ነበር::

ለፈጠርኩት የቴክኒክ ችግር ይቅርታ ጠይቄያለሁ :lol: ከዚህ በኻላ የኔን ስም ዋርካ ስነፅሁፍ ውስጥ ካየህ ጠቋሚ ይሁንህ :D

ስለ አድናቆትህ እግዜር ይስጥልን:: እኔም ዋርካ ውስጥ ከምከታተላቸው ሰዎች መሀል አንተ አንደኛው ስትሆን በዚሁ አጋጣሚ ደግሞ ክቡራን ደጉ ሐያት ጌታ ሙዝ እና ሾተል የሚጽፉት ይመቸኛል:: አቀራረባችሁ አይሰለችም:: አንባቢን ይስባል(እኔን ልበል እዚህ ላይ :D አንዱ አንዳንዴ ትንሽ ወጣ ይላል እንጂ :D :D ማን እንደሆነ ግን አልነግርህም :wink: መቼም የፈረደበት ሾተልን ነው የምትጠራጠረው አይደል :D እኔ አላልኩም :D

የሚገርምህ ነገር የጠቀስካቸው ዋርካውያን በሙሉ እኔም የሚመቹኝ ናቸው.....ፅሁፋቸው ውስጥ የሆነ ሀሳብ ወይንም መልዕክት አለ...ሌሎችም አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉ ጥሩ ሐሳብ የሚያቀርቡ/የሚፅፉ አሉ

:D :D ቀላል ነው:: በኦሮሞ ባህል መሰረት የሆነ ስር መሳይ ነገር ታኝክና በቅርቡ የቦሬን ዜግነት ትወስዳለህ :D :D ከዚያማ በኔና ባንተ መሀል ምንም ልዩነት አይኖርም:: ቦሬ ተወለድኩ ሁሉ ልትል ትችላለህ :D

የቦሬን ዜግነት ላግኝ እንጂ የኦሮሞ ባህል የሚያዘውን የሚታኘክም ሆነ የሚቆረጠም ነገር ለመፈፀም ደስተኛ ነኝ :D

ሠላም ሁን :!:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest