የቦሬ ልጆች በዋርካ ጥላ ስር:

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሞፊቲ » Thu Aug 28, 2008 2:40 am

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ሄይ ራስ ብሩ!=በጎ ስለነበረው መልስህ ከልብ አመሰግናለሁ::ባልከኝ መሰረት ከዋናው ሰውዬ ጋ
በስልክ ተነጋግሬ በጣም ተደስቷል::ያለኝን ሁሉ ብነግርህ በሳቅ ትሞታለህ::ከስምምነቱ
በኌላ መጨረሻ ላይ ምን አለኝ መሰለህ በኮንፈዴሬሽን ነው ወይስ በፌዴሬሽን ብሎኛል::
እና እዚህ ያለው ነገር አልጋ በአልጋ ስለሆነ አንተ ጋ ያለውን ጨርሰህ እንደሚሆን እናደርጋለን::

አዶቆርሳ=ፎክረህ ፎክረህ ምነው አቀባበሉ ላይ በቴሌቪዥን አላየሁህም?
ባንዲራ የያዘ ይወዩ ልጅ ወድያና ወዲህ ባፈላልግ ላይህ አልቻልኩም; ከዱቤ ጂሎ ውጪ::

ትንሽ የደበረኝ ነገር ኤርፖርት ላይ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሲቀበሏቸው ሻንጣ እየጎተቱ መውረዳቸው
ፕሮቶኮሉን ያበላሹት ይመስለኛል::በተረፈ የህዝቡ አቀባበል ያው መሰረት እንዳለችው ምንም አዲስ ነገር የለውም::
የተለመደ የድል አቀባበል ነው::

ቸር እንሰንብት!!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ራስብሩ » Thu Aug 28, 2008 9:35 pm

ሞፊቲ ሠላም ላንተ ይሁን
መልክቴ እንደደረሰህ መልሱን ላክልኝ::
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Postby ራስብሩ » Fri Aug 29, 2008 11:12 am

የነሀሴ ወር በሚያበቃበት ዕለት ማለትም ዕሁድ
በ 31.08.2008

በአውሮፓውያን የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 15:30 (ከሰዓት በኍላ ) በፓልቶክ ሩም ውስጥ እንድንገናኝ በታላቅ አደራ እጋብዛለሁ ::
ይህ ሰዓት ለካናዳ ጠዋት ለጃፓን ደሞ ማታ ይሆናል ነገር ግን አመቺው ሰዓት ይሄ ስለሆነ አስቤበታለሁ ::
ለምሳሌ ሞፊቲጋ ጠዋት 7:30 ሲሆን ባለሱቅ ጋር ደሞ ምሽት 22:30 ነው የሚሆነው ይህንን ለማጠጋጋት ስለማይቻል ምርጫ ያደረኩት ይሄንን ሰዓት ነው ::
የምንገናኝበትን ሩም ዛሬ ክርኤት አደርጋለሁ ነገ አሳውቃለሁ :: በቅድሚያ ሩም ያለው ወይንም ሌላ ዘዴ ያለው ቢያሳውቀን ሰዓት ይቆጥብልናል ::

አንፈራራችን
አደቆርሳ
የቦሬ
ሽልንግዬ
ቺኮ
የግልዬ
ቅሩንፉድ
ወቤ (ጃሎ )
ባለሱቅ
ሞፊቲ
መናኸሪያ
ሌሎቻችሁም የቦሬና የክብረመንግሥት ልጆች በሙሉ እንድንገናኝ በድጋሚ አደራ እላለሁ ::
Image


አክባሪያችሁ ራስብሩ ወልደገብርኤል ::

አንፈራራችን ትናንት ስላቀረብክልኝ ምስጋና በጣም ከመደሰቴም በላይ ጎንበስ ብዬ ተቀብያለሁ ::[b]
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Postby ራስብሩ » Fri Aug 29, 2008 2:09 pm

ከዚህ በፊት የነበረኝን ሩም አፕዴት አድርጌው አሁንም ባለቤትነቴን አረጋግጦልኛል:: እና እሁድ እዛው ሩም ውስጥ እንድንገናኝ በአደራ አሳስባለሁ::
ፓልቶክን ሎግ ኢን ካደረጋችሁ በኍላ
EthioAdola የሚለው ሩም ውስጥ በር ላይ ቆሜ እጠብቃችኍለሁ::
ወቤ እንዳትቀር ያለበለዚያ ከሞፊቲ ጋር ብዙ የምናወራው ነገር አለ::
የቦሬም እንዲሁ እንዳትቀሪ :: አንዳንድ የልጅነትና የሚያስቅ አጋጣሚዎችን ይዘሽ ነው ታዲያ:: ለቁንዝሮም አስታውሱልኝ::
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Postby ሞፊቲ » Fri Aug 29, 2008 11:25 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::
ራስ ብሩ መልክትህን በሚገባ ተቀብያለሁ::ባልከው ሰአት ለመገኘት በተጠንቀቅ ላይ ነኝ::
የዚህ የፓልቶክ ውይይት ምን ጉዳይ እንደሆነ ባልጠረጥርም ሁኔታው ግን አስቸኳይ የብሄራዊ ሸንጎ
ስብሰባ አይነት ነገር መሰለኝ::ለማንኛውም የኔ ሰአት ስለተመቸኝ ችግር የለብኝም::
አመሰግናለሁ ራስ ብሩ::

ቸር እንሰንብት!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ወቤ(ጃሎ) » Sat Aug 30, 2008 12:17 am

ወንድሜ ራስብሩ= ለተደረገልን የዉይይት ጥሪ በጣም አመሰግናለሁ!
ሆኖም እኔ በአንድ ምክንያት ስለማልገኝ ሙሉ ዉክልና ለሞፊቲ የሰጠሁ በመሆኑ ማንኛዉንም እኔን የሚመለከት ጉዳይ ላይ እሱ ስለአለ ከይቅርታ ጋር እንድታዉቁልኝ ነው::
አመሰግናለሁ!!!
ወቤ(ጃሎ)
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Wed Jul 28, 2004 6:57 pm

Postby ሞፊቲ » Sat Aug 30, 2008 2:35 am

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ወቤ ያ ያልከኝ ነገር ለካ በአሁኑ እሁድ ነው እንዴ? ዋርካ ላይ እንዳነበብኩህ ደውዬልህ ነበር::
እኔ እኮ በወዲያኛው እሁድ መስሎኝ ነበር:;ለማንኛውም አንተ ባትገኝም ለኔ ውክልናውን ስለሰጠኧኝ
እቀበላለሁ::እሁድ ያው ወደ ሼፊልድ ከሄድክ እጅህ ላይ ባለው ስልክ እደውላለሁ::

ቸር እንሰንብት!!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ወቤ(ጃሎ) » Mon Sep 01, 2008 12:41 am

ሞፊቲ- ምነው የዉክልናዉን ሪፖርት ከአሁን አሁን ታቀርባለህ ብዬ አፍጥጬ ብጠብቅ ምንም የለም! ለማንኛዉም ወዳጅህ ቀነኒሳ በቀለ ዛሬም Aviva British Grand Prix(Gateshead) በተደረገው የ 3000ሜ የሩጫ ዉድድር ያንን ሁሉ ተፎካካሪዎቹን አስከትሎ 7.31 በመግባት የስታዲዮሙን ሪከርድ አሻሽሎ 1ኛ በመዉጣት ድልን ተጎናጽፏል::
ይህንን ዜና ካንተ በፊት አዲስ አበባ ልዩ ስሙ ቀበና; ለልጅ አመሀ አድርሼ ደስታዉን አብሬ ተቛድሻለሁ:ከሁሉም ግን የገረመውለከንቲባዋ ከዚህ በፊት በሱ በኩል የተደረገው ጥረት ሳይሆን እግዚብሄር በፈቀደው መንገድ ተሳክቶ ለዚህ መድረሱ እጅግ በጣም ነበር ያስደነቀው!
ሰላምታዬ ለሁላችሁ ይድረስ!
ወቤ(ጃሎ)
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Wed Jul 28, 2004 6:57 pm

Postby ሞፊቲ » Mon Sep 01, 2008 4:56 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ጤና ይስጥልኝ ለሁላችሁም::
ትላንት እሁድ ከክብረመንግስት ልጆች ጋ ባደረግነው ውይይት ከዛሬ ጀምሮ የቦሬን
መድረክ በማጠፍ አንድ ላይ በክብረመንግስት መድረክ ለመጓዝ ተስማምተናል::
በመሆኑም ከአሁን በኌላ የምንገናኘው የስም ለውጥ በተደረገበት የክብረመንግስትና
የአካባቢው ልጆች በሚለው ፔጅ ውስጥ ነው::
ወቤ= ደውዬልህ ስልክህን አታነሳውም::ለማንኛውም በዋናው ቤት እንገናኝ::
የቦሬ
አይፋ
ቁንዝሮ
ሰኚ ናማ
ገተሜ ና ሌሎቻችሁም ዋርካ ጄኔራል ውስጥ የክብረመንግስትና የአካባቢው ልጆች ፔጅ ውስጥ እንገናኝ::

ቸር ይግጠን!!ባይይይይይይይይይይይይይይይይይ
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ኮሎኔል » Mon Sep 01, 2008 5:48 pm

ትልቅ ነገር ነው መቼም እያደረጋችሁት ያላችሁት
ከተዘጋ በኍላ መጻፍ ባይገባኝም በሽማግሌ እንዲዘጋ ይህንን ቤት ለመሰናበት ብየ ነው:: በሉ ከዚህ ጽሁፍ በኍላ እዛው ቤት እንመጣለን::
አምላክ ይባርካችሁ::
አክባሪያችሁ ኮሎኔል ነኝ
Ethiopia
ኮሎኔል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 229
Joined: Fri Apr 07, 2006 7:19 pm
Location: zimbabwe

Postby ዋናው » Thu Sep 11, 2008 12:03 am

በጣም ለማከብራቹ ቦሬዎች እንኳን ለዕንቁጣጣሽ በሠላም አደረሳችሁ::

Image
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby Gosa » Fri Oct 12, 2012 4:44 pm

የተዘጋውን ሰብሮ የሚገባ ሁሉ ሌባ ሳይሆን የናፈቀም ልሆን ይችላል:: ሰው የማይረባ ነገር ጎብኝቷሊያም ዝም ብሎተራ ስነስራት ላይ ተገኝቶ ስም እና ፊርማውን በክብርም ይሆን በቅሌት መዝገብ ላይ እንዲያስቀምጥ ይጠየቃል:: እኔስ ለምን እስከዛሬ እዚህ ቤት ውስጥ ስሜን እንዳልካኖርኩ የከነከነኝ እዚህ ኪቦርዱ በተለያዩ ፊደላት ተጨመላልቀው ግራ በሚያጋቡት ነጻ ኢንተርኔት ባገኘሁበት የዱባይ ኤርፖርት ውስጥ ነው:: ቦሬን ለቅቄ ከወጣሁ አስር ስእአት እንኳ ሳይሆነኝ ለጉድ ከተማዋ እና ህዝቧ ሲናፍቀኝ ይህ ቤት ትዝ ብሎኝ ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ:: ብዙ ከተዝናናሁበት በኋላ ምንም ሳልል መውጣቱን ቀልቤ ስላልወደደው ቢያንስ ስሜን ማስቀመጥ ፈለኩ:: ስለቦሬ ትዝታዬ በቅርቡ ብቅ ብዬ ከተማዋን በደንብ ለሚያውቆአት አጫውታለሁ:: ለዛሬ እዚሁ ላቁምና እዚያኛው ቤት ባለሱቅ መኖሩን ቼክ ላድርግ::
በቅርቡ እመለሳለሁ:ብታነቡኝም ባታነቡኝም ደስ ይለኛል ቅቅቅ
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby Gosa » Tue Oct 16, 2012 2:14 pm

ሰላም ቦሬ ለምትኖሩት ቦሬዎች እና ከቦሬ ውጭ ለምትኖሩ የድሮ ቦሬዎች:: ባለፈው ከንጉሴ ጋር በርጫ ነገር እየነካከስን እያለን ቦሬ ተወልደው አድገው ባሁኑ ሰአት ባለም ዙሪያ ተበታትነው የሚኖሩት የቦሬ ልጆች ስንት ይሆኑ ይሆን ብለን ላይጠቅመን በቁምነገር ከመካነ የሱስ ግቢ ጀምረን መቁጠር ጀመርን:: እኔ እንኳ የተወሰኑትን ነው ባካል የማቃቸው: ንጉሴ ግን ምርቃናው እያላበው በጫቱ እንጨት በእጁ ጀርባ ላይ ጽፎ ይደመር ጀመር:: እኔም ባካል የማውቃቸውን እነ ሞፊቲን ዝማምን እና ደረጀ ከበደን እየጠቆምኩት ሳናስበው ሀምሳ ስምንት የቦሬ ልጆችን በመቁጠራችን በጣም ተገረምን:: እኔ ድሮ ባጠቃላይ ከአስራ አምስት የምንበልጥ አይመስለኝም ነበር ከዚያ ከትንሽ ከተማ ወጥተን የተበታተንነው:: ጧት ውጭ ያሉት የቦሬ ልጆች 58 እንደሚሆኑ ለBR (መምህር ፈለቀ) ስንነግረው

"ትቀልዳላችሁ እንዴ?"
"በእውነት 58 እንሆናለን BR:: ማታ እኮ በቁምነገር ቆጠርናቸው" አልኩት::
"ከመቶ በላይ ይሆናሉ እንጂ!! ምን ማለትህ ነው...የነ ጋሽ አየለ በላይነህን ልጆች ሁሉንም ቆጥረሀቸዋል?"
"አዎን ደብሪቱ እና መርዕድን"
"በቃ? ሁለቱ ብቻ ናቸው የተቆጠሩት?"
"ሌሎችም አሉ እንዴ?"
"አንድ ፓይለት እና ሌሎች ሶስት አሉ:: የዮናስ ቡታን ቤተሰብ ስንት ቆጠራችሁ?"
"ዮናስ: ቴድሮስ: ሮዛ እና አንዲት እህታቸው ኖርዌይ ያለች ይመስለኛል::"
"በል ተወው አንተ ምንም አታውቅም:: ብዙ ናቸው እነሱም:: አንዷ አለም ባንክ ውስጥ ትሰራለች ይባላል:: የነ ሞፊቲስ ስንት ቆጠራችሁ?"
"የሞፊቲ እናት: ሞፊቲ: እና መታሰቢያ(አሰቡሽ በሂሳብ በጣም ጎበዝ ተማሪ ስለነበረች አስተማሪው ወንድሜ በጣም ይወዳት ነበር) ከዚያ በላይ የነሱን ቤተሰብ በጥልቅ አላውቅም::"
"ጉድ ነው:: ጫት ባልተው ኖሮ ጫቴን ይዤ አንድ ሙሉ ቀን በቁምነገር ስማቸውን ጽፌልህ አስጠናህ ነበር: አላማችሁ እነሱን ማጥናት ከሆነ"
"እንዴ...ቆየህ እንዴ ከተውክ?"
"ወር ሊሞላኝ ነው::" ንጉሴ እስካሁን ብዙም አልተሳተፈም ነበር በኔና በBR ወሬ:: የBRን ጫት መተው ሲሰማ ግን በመገረም እያየው
"እና አትናገርም እንዴ ትቻለሁ ብለህ? እናንተ የጥንት የጧቶቹ ካፈገፈጋችሁ እኛ ታዲያ ለማን ብለን ነው አንድ የውሻ ክራንቻ እስኪቀረን ድረስ የምንቅመው? ልክ አይደለህም BR!!"
"ለፈለቀ ነው እንዴ የምትቅመው? ለምን የቀረቿንም አንዷን ጥርስ አቶ አብደላ(የእጅ ባለሙያ ቀጥቃጭ) ጋ ሄደህ አታስነቅልም ጉዳዬ አይደለም!! አሁን ክፍለ ጊዜ ስላለብኝ መሄዴ ነው:: ስመለስ ልክ ልክህን እነግርሀለሁ"
"እስክትመለስ ድረስ ማን እብድ አለ ቁጭ ብሎ የሚጠብቅህ? ያኔ መርቅኜ ጫት ሊያስተውህ የቻለ ሚስጢር ምን እንደሆነ ደርሼበታለሁ::ምን አጨቃጨቀኝ ካንተ ጋር: ቻዎ!"

አይገርምም?? እኔ ላወራችሁ የፈለኩኝ ከአዲስ አበባ እስከ ቦሬ መንገድ ላይ ያጋጠመኝን ነበር:: ሳላስበው ሌላ አርዕስት ውስጥ ገብቼ ዳከርኩ አይደል:: ለማንኛውም ልጀምርላችሁ:: ግን ብዙ ሰአት የለኝም::

ንጉሴ ነበር አዲስ አበባ የጠበቀኝ:: ለባለትዳር: የልጅ አባት እና ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ለመቆየት ጊዜ ላልነበረኝ ለኔ አንድ ቀን እንኳ ብቻዬን አዲስ አበባ ማደሩ (ንጉሴ ምን ይጠቅመኛል አሁን ከሱ ጋር ባድር ቅቅ) ምንም ስላልታየኝ ንጉሴን

"በል ከዚህ ከተማ ወጥተን መሄድ አለብን:: በምን እንሂድ ይሆን አዋሳ?" አልኩት::
"ክሩዘር እንኮናተር እንዴ?"
"ክሩዘር ተኮናትሬ መች ልመልሰው ነው? ምን አጨናነቀኝ ከሰው መኪና ጋር! አልፈልግም ነጻነቱ ይሻለኛል"
"በል በቃ በአባዱላ እስከ አዋሳ እንሂድ... እሱም ከቃሊቲ ነው የሚያዘው:: እስከ ቃሊቲ ደግሞ በላዳ እንሂድ"

ድሮ ለገሐር የነበረው መነኽሪያ ተነቅሎ ቃሊቲ ገብቶላችኌል:: በስንት መከራ እዚያ ስንደርስ አንድ አዲስ ባለ ደረጃ 1 ባስ ሊሞላ ትንሽ ቀርቶት ነበርና የአባዱላውን ሀሳብ ቀይረን ባሱ ውስጥ ገብተን ባዶ የነበረውን የመጨረሻዎቹን ወንበሮች ያዝን:: ባሱ ውስጥ አንድ የሚያውቀን ልጅ አይቶን በንጉሴ ግፊት ከመሀል አከባቢ ይዞ የነበረውን ወንበሩን ትቶ መጨረሻ ወንበር ከኛ ጋር ሊቀመጥ ሲመጣ ከዝዋይ በኌላ ላለው መንገድ እየተዘጋጁ መሆናቸውን አልተጠራጠርኩም: ላረንጓዴዋ በለስ:: ንጉሴ ጥግ: ልጁ መሀል ከዚያም እኔ ሆነን እንደተቀመጥን አንዲት ወጣት ቆንጅዬ ልጅ መጥታ አራተኛ ሆና ተቀመጠች:: በመጨረሻም ሁለት አዛውንቶች የጎደለውን ወንበር ሞልተው ባሱ ሊንቀሳቀስ አካባቢ ንጉሴ ቦታ እንድንቀያየር ባይኑ ይለምነኝ ጀመር:: ብዙ ጊዜ በሱ አልጨክንም ነበር:: ያን ቀን ግን እኔም ሌላ ቦታ የሚመቸኝ ስላመሰለኝ ፍላጎቱ እንዳልገባኝ ሆኜ አውቶቡሱ እስኪንቀሳቀስ ባይኔ ሸሸሁት::

ይቀጥላል
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby Gosa » Wed Oct 17, 2012 4:12 am

'ባምስት ሰው ወንበር እኮ ነው ስድስት ጭኖ የሚያሰቃየን:: እንዴት ሆነን ነው ይህን ሁሉ ረዥም መንገድ የምንጓዘው!" ቅሬታዋን የምታሰማው ለኔ ይሆን ወይ በወዲያ በኩል ከጎኗ ለተቀመጡት ሰዎች ይሆን ወይ ደግሞ ለእ/ር ምንም ስላልገባኝ ጸጥ አልኳት ረዳት እና ሾፌሩም መቼም አጠገቧ የሉም::
"ስድስትማ አሁን አሁን እየተለመደ መጥቷል:: ሰባት እንዳያደርግ ተግተሽ ጸልዪ' ካሱ ነበር ወንበሩን ቀይሮ ከመሐል የመጣው ጓደኛችን::
"እኔ ብቻዬን ለምን ልጸልይ: አንተም እኮ ትጨናነቃለህ አንድ ሰው ቢጨመር:: ከንፈርህ ሁሉ ስለደረቀ ጾመኛ ሳትሆን ስለማትቀር አንተው ብትሞክርልን አይሻልም ጸሎቱን?" ሳቅ እና ቁጣ በተቀላቀለበት ግራ በሆነ ስሜት ባይኗ ገልመጥ እያረገችው::
"ትኩሳት ያለበት ሁሉ ጾመኛ ከመሰለሽ ተሳስተሻል:: ይልቅ ቫዝሊን ነገር ከቦርሳሽ ስለማይጠፋ አንዴ አቀብዪኝና ደረቀ የምትያቸውን ከንፈሮቼን ልነካካቸው::'
"ቫዝሊን ሂድና ፈላዎች ኪስ ፈልግ:: ከፈለክ ሊፕስቲክ ልስጥህ: የዘመኑ ወንድ መቼም ሴት ያደረገችው ሁሉ አይቅርብኝ ነው የሚለው'
"ተይ እንዲያውም ይቅርብኝ:: ደርቀው ያን ያህል ከሳቡሽ ትንሽ ሲርሱማ ዘለሽ ሳትነክሺኝ አትቀርም:: ሰዎች ለከንፈርም ጭምብል ነገር ሊያስፈልገን ነው ማለት እኮ ነው!! ወይ ጉድ!! ኑጌ ምን ይመስልሀል?' አለው ወደ ንጉሴ ዞር ብሎ::
"ለምን ሳልስም አመት አልቆይም! እንዳንተ የደረቁትንማ ጫማዬን እራሱ አልጠርግበትም እንኳን ልነክስህ" አሁን ትንሽ ቁጣዋ እንደመብረድ ብሎ አተኩሮ ላያት ሰው የተደበቀ ፈገግታ ከወደጆሮቿ አካባቢ ይነበባል:: ንጉሴ ቀበል አድርጎ
"እኔን የከንፈር ጨወታ ውስጥ አታስገቡኝ እባካችሁን:: ከደሙ ንጹህ ነኝ ሀሀሀሀ"
እንደ ባለትዳርነቴ እራሴን አስጠብቃለሁ ብዬ ተኮፍሼ በጨዋ ደንብ ብቀመጥም ንግግራቸው ስቦኝ መቀላቀል ፈለኩ::
"ካስሽ ምነው በግድ የመሳም መጥፎ እድል አጋጥሞህ ያውቃል እንዴ:: ምነው ስለ መከላከያ ማሰብ ጀመርክ?' ካሱ ሳይመልስልኝ እሷ
"ኧረ እሱ በግድ ይስም እንደሆን እንጂ ማን በግድ ይስመዋል ብለህ ነው! አሉ እኮ በግድ እንድትስማቸው የሚያጓጉ የሚያሳሱ የሚያንሰፈስፉ ከንፈሮች:: እሱ የራሱን ውጭ ነው መሰለኝ የሚያሳድራቸው: ውርጭ አቆርፍዷቸዋል:: አሁን አሁን ደግሞ ሮንድም የለም"ኮ እንደ ድሮ:: ችግር ነው::"
"ጎሳ እንኳኑ መሐላችን ሆንክ:: ዛሬ ነበር ጉዴ የሚፈላው "ሳመኝ" እያለችኝ እየቆነጠጠችኝ:: እኔ ደግሞ ብስማት እንደሚያስመልሰኝ ታውቃለህ እንደሷ አይነቷን"
" ቅቅቅቅ ወይ ካስሽ!!" አልኩኝ:: የምናገረውን አጥቼ:: እሷ ወዲያው
"እውነቱን ነው ያልለመዱት ነገር ይከብዳል:: እርግጠኛ ነኝ ቆንጆ ሴት ስመህ አታውቅም"

ገና ካዲስ አበባ አልወጣንም::

መጣሁ ተመልሼ:: እቀጥላለሁ
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby Gosa » Thu Dec 13, 2012 6:11 pm

ማርና ወተቴ wrote:ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ? ቤታችን ደህና እየተሟሟቀ ነው ደጉ ና ሰኚናማ የተለዋወጣችሁት አስተያየት ገንቢና ደስ የሚያሰኝ ነው:;
ሰኚናማ ና ቺኮኩባኖ ያነሳችሁት የተሻለ ጉዳይ ቀደም ሲል የማውቀው ታሪክ ቢሆንም እንደአዲስ በሳቅ ነው የገደለኝ:በዚሁ ቀጥሉ እላለሁ::
ሞፊቲ= እዉነት የተባለው የተበላሸሁ!ጉዳይ ተዋናዩ ጸግእሸት ነው?እርግጠኛ ነህ ወይ? ምክንያቱም እኔ ሌላ ሰው እንደሆነ ስለሰማሁ ነው;;
የቦሬ= የቆሎው ጉዳይ እንዳቺው የብዙዎችን ትዝታ ነው የቀሰቀሰው: ሌላው ዝማም ድሪባን ስታነሺ ካናዳ የአስማማው ሰይፉ እህትስ አለች አይደለም ወይ?
ዛሬ እስኪ ስለ ቦሬ ያለኝን ትንሽ ላጫውታችሁና እናንተም ምታውቁትን ጨምሩበት::
ስለ ቦሬ ከተማ አመሰራረት ይሄ ነው ሚባል ትክክለኛ መረጃ ባይኖረኝም እንደሚወራው ከጣልያን ወረራ በፊት እንደተቆረቆረችና የመጀመሪያውም ሰፈር አሁን የባላምበራስ ከበደ ወንዝ አካባቢ እንደሆነና ድሮ አሮጌ ከተማ ይባል እንደነበር ነው::
ቦሬ የሚለውም መጠሪያ ትክክለኛ ትርጉም በእርግጠኝነት መናገር ባልችልም እንደሰማሁት ግን: <ቦሬ> ማለት የኦሮምኛ ቃል ሆኖ ድፍርስ ማለት ሲሆን (ቦሮዌ)ወይም (ቦሩ) ከሚለው ቃል ጋር ተዛማጅ ሆኖ ከከተማው አጠገብ ያለው አርባ በላ ወንዝ ሁሌም ድፍርስ ሆኖ ስለሚታይ ስሙን ከዚህ ያገኘ ይሆናል የሚል ሲሆን ሌላው ትርጉም ደግሞ <ቦሬ> ማለት ሀይለኛ የሆኑ ላሞች ወይም በሬዎች ተቆጥተው(ቲራ ከብቶች) ማለት ነው በቀንዳቸው መሬት እየቆፈሩ አረፋ ከአፋቸው ሲወጣ <ቦሬ > እንደሚባልና መጠሪያው ከዚህም የመጣ ነው የሚሉ ወገኖችም አሉ:እስኪ ሌሎቻችሁም ምታውቁትን ጀባ በሉን::
የቦሬ ት/ቤት ደግሞ በ1940 ዎቹ አጋማሽ ላይ ከ 1-እስከ 4ኛ ክፍል የተጀመረ ሲሆን ሲከፈት ከነበረው ዳይሬክተር ቀጥሎ የነበረው መስፍን አበበ የተባለ ሲሆን:ይሄው ዳይርክተር በ1952 አ/ም አለሙ ቦቴ የተባለ የስፖርት አስተማሪን በመግደል ወንጀል ተከሶ ይርጋአለም ወህኒ ቤት በመግባቱ በምትኩ ሀይለልኡል የሚባል ከዚያም ደግሞ ክፍለጽዮን የተባለ ዳይርክተር በተከታታይ እንደነበሩ ና ቀጥሎም ብዙዎቻችን የደረስንበት ሀይለ ጊዮርጊስ ደሜ ብዙ አመታት አገልግሎ ወደ አዋሳ ታቦር ት/ቤት እስከ ተዛወረበት ና ከዚያም አለማየሁ ቦጋለ ወዘተ----
የቦሬ ት/ቤት ወዲያው እስከ 6ኛ ከዚያም ቆይቶ መለስተኛ በመጨረሻም እስከ 12 ኛ ክፍል ድረስ ተከፍቶ ሁሉም ወጣት እንደኛ ሳይሆን ከቤተሰቡ ሳይለይ ትምህርቱን የማጠናቀቅ እድል እያገኘ ነው::
የድሮ መምህራንን ትንሽ ለማስታወስ
-መምህር አስፋው
- >> ገ/እግዚያብሄር ገ/መስቀል
- >> ቶሌራ ጎንፋ (የግብረገብ አስተማሪ)
- >> አበበ ቤዛ (ሀይለኛ ተጋራፊ,እንደጦር ሚፈራ)
- >> ገበየሁ እልምነህ(ዘመን የማይሽረው ሁለገብ)
- >> ተስፋዬ ሀ/ጊዮርጊስ
- >> ተክሌ አስፈሀ
_ >> ነጋሽ አብዬ (ተንኮለኛ,ስፖርታኛ,ልበሙሉ ጀግና) - >> ብዙሰው ታመነ
ከጊዜ ብዛት የተነሳ ብዙዎችን ረሳህዋቸው መቼም ግርማ ሞገሳቸው,እንዴት እንደምንፈራቸው እና አሁን ካለው የተማሪ ና የአስተማሪ ግንኙነት ጋር እያነጻጸርኩ በጣም ይገርመኛል::
በሌላ ርእስ እመለሳለሁ ሰላም ሁኑ!!!!

ሰላም ቦሬዎች !
ስለ ቦሬ ት /ቤት መምህራን እና ት /ቤቱ እኔንስ ምን ትዝ ይለኝ ይሆን .....ስለምንወዳቸው አንቱታውን ለዛሬ ላስቀር :: አንጋፋ መምህራንን እነ መ /ር ተስፋዬ ኃይለጊዮርግስ ብርሀኑ ላቀው ነገራ ሙለታ እና ላቀው በጋሻውን ማንም ስለማይረሳቸው እዘላቸዋለሁ ::
አንደኛ እና ሁለተኛ ክፍል ስማር ምንም የማስታውሰው ነገር ያለ አይመስለኝም :: ወደ ሶስተኛ ክፍል አካባቢ ነው ትንሽ ጭላንጭሉ የሚመጣልኝ
መ /ርት አበበች ሔራንጎ A B C D ያስቆጠረችኝን አልረሳትም :: በዚያ ወቅት ደግሞ ደምሴ አንገሎ የሚባል መምህር ከሱታ እየተመላለሰ እንግሊዘኛ ያስተምረን ነበር :: ለሁለት ተራ በተራ ያስተምሩን ወይም እኔ ተቀባዥሮብኝ ይሆን እርግጠኛ አይደለሁም :: ሌላም ደምሴ አለ ....መ /ር ደምሴ ብዙነህ :: ቀላል አይጋረፍም :: ታዲያ አንድ ቀን ይገዙ ጉሚ ዱካሌ የሚባለውን ልጅ ቢገርፈው ቢገርፈው ልጁ አንድ አላለቅስ ይላል :: ኮቱን አውልቆ አስተኝቶት በልምጭ ጀርባውን ቢለጠልጠውም ልጁ ወይ ፍንክች :: ከዚያም መ /ር ደምሴም በመገረም በኦሮምኛ "Firri keeti maan?" ብሎ ሲጠይቀው ልጁ "maaf sitti himadha?" ብሎ ጥያቄን በጥያቄ መለሰለት :: ከዚያ መምህሩም በመገረም "ወንድ ነህ አልገርፍህም በቃ ተነስ " ብሎት ተወው :: በሆነ ወቅት በክላሰር (ዶሲ ) ላይ ስማችንን በትልቁ በፓርከር ጽፈን ማንገቻ ገመድ አበጅተንለት ገና የህብረተሰብ ክፍለ ጊዜ ሲደወል አንጠልጥለን እንጠብቀዋለን :: የልጆችስ ይሆን ባለትዳር እና የልጆች እናት የነበሩት ሴቶችንም ማሰቃየቱ ..እንደዚያው ትልቅ ክላሰር አንጠልጥለው ሲታዩ ፍርድ የሚጠብቁ እስረኞች ነበር የሚመስሉት :: የሳይንስ አስተማሪያችን የነበረች ደግሞ መስታወት ስትሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ሱሪ ለብሳ ያየኌት ሴት እሷን ነው :: ያኔ ግርም ይለኝ ነበር እንዴት እንደማታፍር :: ጅል እና ልጅም ስለነበርኩ ይሆናል :: ዛሬ ዛሬ ደግሞ ረጃጅም ሱሪዎቹም ፋሽኑ አልፎባቸው በጣም በረቀቀ እና በማይክሮስኮፒ ብቻ በሚታዩት ጥቃቅን አልባሳት ተተክተው ሳይ ተመስገን ስልጣኔ እና ቴክኖሎጂ እላለሁ ቅቅቅ :: ማይክሮስኮፒ የምለውን ስጽፍ ማን ትዝ አለኝ መሰላችሁ ...መምህር ጋሻው :: መነጸር የሚያደርጉ አፍሮ የሚያበጥሩ የሳይንስ አስተማሪያችን ... ግራጫ አይዶል ሱሪ ነበረው ::ድምጹ አሁን ይሰማኛል ...ሪፍራክሽን ..ኮንኬቭ ሌንስ ...ይሉ ነበር አብዝተው :: መምህር ግርማ መገንታንስ ታስታውሱት ይሆን ? ሁሌ ንጹህ እና ዘናጭ አስተማሪ ነበር ከእጅ ጽሁፉ በስተቀር :: ግብዴ ባለአራት ማዕዘን የጃፓን ሴኮ ሰአቱ ዛሬም ትዝ ይለኛል :: በምን አወቅክ እንዳትሉኝ የጃፓን መሆኑን ቅቅቅ :: ሳይጠይቁ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው :: ታዲያ እሱን ሳስታውስ አንተነህ ለበኑ ትዝ ይለኛል :: በጣም ተንኮለኛ ልጅ ነበር :: ክፍል ውስጥ አማርኛን ሲያስነብበው "መልመጃ " የሚለውን ቃል እራሱ ሆን ብሎ "ሞልሞጃ " እያለ እያነበበ ጋሽ ግርማን ያናድደው ነበር :: ዬት ይሆን አሁን ያ ልጅ ? በተቃራኒው የእጅ ጽሁፉ ከታይፕ የሚያስነቀው ደግሞ የመ /ር ግርማ ቦጋለ ነው :: አቤት ጽሁፍ ! ይህ ጽሁፉ ሳይሆን አይቀርም ማዕከል ውስጥ አስገብቶት ያስቀረው :: ሌላው ግርማ ደግሞ ጋሽ ግርማ ጉዳ :: ሁሌ እንደሳቀ :በህይወቴ አንድ ቀን ተማሪን ሲቆጣ አይቼ አላውቅም :: ግርማዎችን እዚሁ ትተን ወደ ላይ ከፍ እንበል :: መ /ር አሰፋን (ስከለተን ) የማያውቅ ያለ አይመስለኝም :: በህይወቴ ፊቱ ተፈቶ ሲስቅ አይቼው አላውቅም ካለ አንድ ቀን በስተቀር :: አንድ ልጅ ይረብሽና አስነስቶት ከተማሪዎቹ ፊት ያስቆመዋል ::
"ስምህ ማነው ?"
"ተስፋዬ "
"ተፋዬ ማ ?"
"ተስፋዬ ዲንቃ "
መምህሩ በሳቅ ወደቀ :: ደጋግሞ ስሙን እየጠያየቀው ብቻውን ይስቃል :: በመጨረሻም "ማን ይሆን አንተን ተስፋዬ ዲንቃ ያለህ ? ጅል ! ተስፋዬ ዲንቃ እንዳንተ ጅል ነው ? ና ውጣ !" ብሎት በካልቾ አንዴ ደህና አድርጎ አስገብቶለት ከክፍሉ አስወጣው :: ኌላ ነገሩን ሳስበው ተስፋዬ ዲንቃ የሚባል በወቅቱ ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣን (ጠቅላይ ምንስትር ) ነበር :: ከሱ ጋር አገናኝቶት ነበር ይስቅ የነበረው :: ወይ ጤንነት !
ሞት ይርሳኝና ማንን እንደረሳሁ ታውቃላችሁ ? ጋሽ መንግስቱ ታደሰን :: አቤት ...ሶቭዬት ኅብረት : ሌኒን : ኢምፔሪያሊዝም እና የሰርቶ አደሩ ፓርቲ ድሮ ቀረ :: ግርም የምለኝ ..."ዛሬ ሶቭዬት ኅብረት ውስጥ አንድ መኪና ቢገለበጥ መኪናው "ሾፌሩ እንዲህ ማድረግ ሲገባው እንዲህ ሳያደርጎ ቀርቶ ነው የገለበጠኝ " ብሎ ለሚመለከተው ክፍል መልዕክት ይልካል " ብለው የዛሬ ስንት አመት የነገሩንን :: በዚያ አይነት ያ መኪና አሁን ዬት ደርሶ ይሆን ? ወይ ፖለቲካ ! ከልቡ ፖለቲካ ነበር :: ሌላ ማን ነበር ፖለቲካ ያስተማረን .... አስታወስኩ ... ጋሽ ደመረው :: ጋሽ ደመረው እንኳ ሂሳብ ነው በጣም የሚያምርባቸው :: ያኔ ከኢሰፓው ካኪ ልብስ ጋር የሚያደርጉት ሀይለኛ ጥቁር ቡሽ ጫማ ነበራቸው :: ከጀርመን ነው የገዙት እየተባለ ይወራላቸው ስለነበር አንዳንዴ ትምህርቱን ሳይሆን የጫማውን አካሄድ ነበር እንከታተል የነበረው :: ይኼኔ እኮ እሱም አልቆ ተጥሎ ይሆናል :: ሲያሳዝን ! የአማርኛውን አስተማሪ አያለውን ማን ያስታውሳል :: "ሽልንጌን ሽልንጌ ...ፋጤ ወጂን ዴማ " የስንተኛ ክፍል አማርኛ ይሆን ? አቦ አሁን አግኝቼው ያንን ሽልንጌን ባነበብኩ :: አንድ ቀን ተክኤ ጉልበት ተመስጠው ሂሳብ ካስረዱን በኌላ ጥያቄ እንዳለን ሲጠይቀን ደረሰ ከበደ የሚባል ተማሪ እጁን ያወጣል :: የመጠየቅ ዕድል ሲሰጠውም "ጋሼ ነገ ትምህርት አለ እንዴ ?" ብሎ በመጠየቁ መምህሩ ተበሳጭተው "እንደው አንተ የምትጠይቀውንም አታውቅም ::"ከካም ! ብሎ ልጁን አስደነገጠው :: ልጁ በዕድሜ ከሁላችንም ይበልጣል :: ሀይለኛ ነጋዴም ስለነበር ቀኗን ለሽቀላ ነገር አስቦ ሳይሆን አልቀረም ::
ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ጸጉረ ሉጫ ወንድ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ ? የሂሳብ አስተማሪውን ዘውዱ :: ሴት ኢዝ ዘ ኮሌክሽን ኦፍ ቲንግስ ኦር ግሩፕ ኦፍ ኦብጀክትስ " ሀይ ሽምደዳ :: ሸመደድን ድሮ :: በኛ ጊዜ ሽምደዳ ነበር አሁን ችከላ ሆኖ ቀረ እንጂ ቅቅቅ :: ካሜራማን እና የሳይንስ መምህሩ ጋሽ ጥሩነህ ደግሞ በጣም ከምወዳቸው ጥቂት መምህራን አንዱ ነው :: ከልቡ ያስተምር ነበር :: ሀቢታት .. ኢንቫይሮመንት ...ኮሚዩኒቲ ...ምን ያላስተማሩት ነገር አለ :: እጅግ በጣም የምወደውን መምህሬን መቋጫዬ ላደርገው ነው እስካሁን ያላነሳሁት ... መምህር ጸጋዬ ፍሰሐን :: ማነው ዛሬ በ TTI ሰርቲፊኬቱ ሀይስኩል ገብቶ እንግሊዘኛን ለማስተማር የሚደፍር ! ባንድ ወቅት በስመ ሴርቲፍኬት ከሀይስኩል ወደ ጁነር ሲመልሱት ተማሪው አምጾ ነው እንደገና ወደ ሀይስኩል የተወሰደው :: በጣም ትልቅ ቦታ መድረስ የሚችል ሰው ስንቱ መንገድ ላይ ቀርቷል መሰላችሁ :: ለዛሬ እዚሁ ላይ ላቁምና በሚቀጥለው ትዝ ስለምሉኝ ተማሪዎች ትንሽ እጽፋለሁ ::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests

cron