ትዝታዬ : ናፍቆቴና ግርምቴ ! እናቴ !

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ትዝታዬ : ናፍቆቴና ግርምቴ ! እናቴ !

Postby ዉቃው » Sun Mar 25, 2007 4:02 pm

ሰላም ዋርከኞች

ነገሩ እያነሳህ ጣለው ነውና የባጥ የቆጡን አብረን እያነሳን እንጥላለን :: በቅድሚያ ወንድማችን ሀሪከን <ልጅ እያለሁ> በሚለው ርዕሱ ወደኋላ ሄደን ትዝታችንን እንድናወጋና : ለዚህች ርዕስም መነሻ እንዲሆነኝ ስላሳሰበኝ አመሰግነዋለሁ ::

ይጀመራ ቀደዳው !

እንግዲህ ጊዜ በጣሙን እያለፈ በመጣ ቁጥር አንዳንዶቹን ሳሰባቸው ምናለ ተመልሰው አሁን ቢሆኑ : ያስብሉኛል :: አንዳንዶቹ ግርም ሲሉኝ ቀሪዎቹ ደግሞ እንደጉድ ይናፍቁኛል ::

ከግርምቴ ልጀምር ::
በልጅነቴ እጅግ በጣም ሲበዛ ቅማላም ነበርኩ :: ቅማሎቹ እንዴት ከምን ለምን በማን አናቴ ላይ ተፈጠረው ሲርመሰመሱ እንደሚውሉ አሁንም አይገባኝም :: በቃ የቅማል ሰራዊት ደሜን ሲመጥ ይውላል ያድራል :: በወላጆቼ ቅማሎቹን ለማጥፋት : ያልተደረገ ጥረት : ያልተቀባሁት እምነት : ያልጠጣሁት የጸበል ዓይነት አልነበረም :: ወደ ኋላ ላይም ጸጉሩ ሉጫ ቢጤ ሰለሆነ የሰው ዓይን ነው ተብሎ የተቆጣጠሩ ነገሮች ለዓመታት አንገቴ ላይ አንጠልጥያለሁ ::

እነ ቅማል ግን : ወይ ፍንክች !

የናቴ ተጨማሪ ስራ ቀን በእናት ቅማሎች ሲዘሩ የዋሉትን ቅጫሞች ማታ ሲያላቀቁ ማምሸት ነው :: ቅጫሞቹ ብዙውን ጊዜ ከጸጉሬ ጋር በጣም ሰለሚጣብቁ : እናቴ ቅጫሞቹን በጥፍሮቿ ለማላቀቅ በምታደረገው ጥረት : በአሰቃቂ ሁኔታ መነጨቴ አይቀሬ ነው :: በቅማል ሲፈተፈት የዋለ ቆሮቆራም ጭንቅላት በናቴ ጥፍር ደግሞ ሌላ ተጨማሪና ሰልታዊ ጥቃት ይደርሰበታል ::

በቃ ቅማሎች ቢራገፉ : ምደረ ቅጫም ሲመዘዝ ቢያድር : ጭንቅላቴ በማላውቀው ኬሚካል ሲታጠብ ቢያመሽ : አንድም ለውጥ የለውም :: በበነጋው ማታ የዉቃው አናት ቀድሞ ከነበሩት ቅማሎች በእጥፍ ይሞላል :: ባጠቋቸው ቁጥር ራሳቸውን የሚያባዙበት አንዳች ዓይነት ምትሃት ሳይኖራቸው አልቀረም :: አሁን አሁን ለድድብናዬ ዋነኛ ተጠያቂዎች ለዘመናት ሲመጠመጡኝ የኖሩት ቅማሎች መሆናቸውን ተገንዝቤያለሁ ::

መጣሁማ ! የውጭ በር ተንኳኳ መሰለኝ
Last edited by ዉቃው on Tue Aug 14, 2012 2:17 am, edited 5 times in total.
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ዉቃው » Sun Mar 25, 2007 11:36 pm

ተመለስኩኝ :;

አንድ ቀለብላባ ነጭ በር አንኳኩቶ ፔፐሮኒ ፒትዛ ኦርደር አርገሃል ወይ ይለኛል :: ትናንት የገዛኋትን በበርበሬና በዘይት የታሸች አነባበሮ አላየ !

ወደ ግርምቴ ሰመለስ : ያው እንግዲህ የሆነ ዕድሜ ላይ ሰደርስ ቅማል የሚባል አናቴ ላይ የለም :: እንዴት በምን ለምን በማን እንደጠፉ የማውቀውም የሰማሁትም ነገር የለም :: በቃ ብን ብለው ጠፉ !

ሌላው የሚገርመኝ ደግሞ የሾዳ ጉዳይ ነው :: አይ ሸራ ጫማ ! ለምንድን ነው ግን ሸራ ጫማ ትናንት ተገዝታ ከአንድ ሁለት ሞቅ ያለ እግር ኳስ ጨዋታ በኋላ ቡን የምትለው ? በፍጠነት ከመቀዳደዷ ይልቅ ይገርመኝ የነበረው ግን ለየት ያለው ቁናሷ ! አቤት ቁናስ ! አሁን ላይ ሆኘ ወደኋላ ሳሰበው ያኔ በልጅነቴ : እግሮቼ ሞተው ነበር እንዴ ? እያልኩ ራሴን እጠይቃለሁ :: ሞተው ቢሆን እንጂማ ነፍስ ያለው እግር እንዴት እንደዚያ ይሸታል ! በኔ ሰሌት በዓመት ሀያ ጊዜ ጉንፋን ይይዘኝ እንደሆን : ለአስራ ዘጠኙ ተጠያቂ ሸራ ጫማዎቼ ናቸው :: እርግጥ ነው ሸራ ጫማውም ሆነ እኔ ውሃ የሚያገኘን በሳምንት አንዴ ነበር :: ያውም በዕለተ ቅዳሜ ! ሸራዋ እሁድ ታጥባማ ለሰኞ ት/ቤት አትደርቅማ ! ሰለዚህም ሸራዬ በቅዳሜ መታጠቧ ግድ ነው :: አቤት ያቺ ብረት ግን ምጣድ ምን ያላየችው አለ ! እኔ እታጠብባታለሁ : እነቦጌም ይታጠቡባታል : ቁናሳሟ ሸራዬ : የቤቱ : የሴቱ : የከብቱ ጣጣ ይታጠብባታል :: ከዚያ ከተረፈች ደግሞ በርበሬ ይሰጣባታል :: በዚህ ቢበቃት እሺ :: ደሞ የቶታአው እናት ይመጡና : "የዉቃው እናት ብረትምጣዶን ያውሱኛል " ተብሎላት : የነሱን ቤት ደግሞ ስታገለገል ትውላለች :: ብረት ምጣዶች እኮ ባለውለታዎቻችን ናቸው :: ከነ ጆግና ማስታጠቢያ ተደምረው ጋር ሆነው በገጣሚያኑ ሊገጠምባቸው ይገባል ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ማይ ኔም » Mon Mar 26, 2007 2:19 pm

[quote][/quote]ዉቃዉ በሳቅ ገደልከኝ
:lol: :lol: :lol:
ማይ ኔም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 164
Joined: Thu Mar 17, 2005 6:16 pm
Location: united states

Postby ቅራሪ » Tue Mar 27, 2007 5:10 pm

ወይ ውቃው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ በጣም ነው በሳቅ የገደልከኝ
ቅራሪ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 247
Joined: Wed May 10, 2006 4:42 am
Location: adiss abeba

Postby ጌታ » Tue Mar 27, 2007 5:29 pm

ዋርካ አንድ ጥሩ አጫዋች አግኝታለች:: ይመችህ አቦ!!!!

ነገረ ሥራህ ሁሉ ግን ያን የምወደውን ጓደኛዬን ጉዱን ትመስላለህ:: ትንሽ ልዩነታችሁ እሱ ሸራ ጫማ ሳይሆን በረባሶ ነበር የሚገዛለት::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ቅራሪ » Tue Mar 27, 2007 5:33 pm

ጌታ ምነው እኛ አንወደድም እንዴ???? ምነው ለጉዱ አደላህ? ጉዱ ቢሰማህ ደስ አይለውም...
ቅራሪ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 247
Joined: Wed May 10, 2006 4:42 am
Location: adiss abeba

Postby ጉዱ ካሳ » Tue Mar 27, 2007 5:58 pm

አይይይይ ጌታ! አሁን አንተም ከኔ የተሻልክ አትመስልም? የምትበልጠኝ በባለሰደርያው ካልሲ በረባሶህን ስለምታደርግ ብቻ ነው:: ግን የቶታው ነገር ሳስበው ግርም አለኝ! ለካ እንደዚያ አመዳም የሚመስለው ከነ ውቃው በተዋሰው ብረት ምጣድ የአሻሮ-ሻወር እየወሰደ ነው! ታጥቦ ማይጠራ ሽንፍላ ብቻ ይመስለኝ ነበር! ቱፍ! ቱፍ! አበስኩ ገብርኩ! በጾሙ ምድር ስለሽንፍላ አወራሁ::
ቅራሪነት አይዞሽ አንቺንም እንደሚወድሽ ያ ሸውራራ አይኑ ያሳብቅበታል:: በል ውቃው ወንድማችን እስቲ ለጥቅልን! ወግ መጠረቁን ተክነህበታል አቦ! በርታልን!

ጉዱ ካሳ
ከፒያሳ
ጉዱ ካሳ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 356
Joined: Wed Oct 22, 2003 6:22 pm

Postby ጌታ » Tue Mar 27, 2007 6:31 pm

ቅራሪ wrote:ጌታ ምነው እኛ አንወደድም እንዴ???? ምነው ለጉዱ አደላህ? ጉዱ ቢሰማህ ደስ አይለውም...


መጀመሪያ እስቲ እኛ የሚለውን አብራሪው:: አንቺን ግን በጣም ትወደጃለሽ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby የመንደራው » Tue Mar 27, 2007 6:56 pm

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ውቃው ፍንድት ልልህ ነው በሳቅ በተለይ በበርበሬና በዘይት የታሸች አነባበሮ ፒትዛ መሆኗ ነው አየ አንተ ሰው እዴት መጣልህ አቦ ይመችህ ቀጥልበት


የመንደራው
የመንደራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 190
Joined: Thu Oct 05, 2006 1:01 pm

Postby ቅራሪ » Tue Mar 27, 2007 7:29 pm

ጌታ ጌታጠንበለል ሰላም ነህ በምጀመሪያ ሰላምታ ላስቀድም ብዬ ነው "'እኛስ"" ብዬ የጠቀስኩት እኔ አንተን ጉዱን እና እምናውቃትን ለማለት ያህል ነው ግን ዋናው ቁምነገር ለጥያቄዬ መልስ ስለሰጠህኝ አመሰግናለሁ በኛም በኩል እንደዛው ነው

ጉዱ ቅቅቅ ሸውራራ ለሸውራራ ተያይዞ ገደል ነው በለኝ ቅቅቅ አትጥፋ
ቅራሪ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 247
Joined: Wed May 10, 2006 4:42 am
Location: adiss abeba

Postby ጌታ » Tue Mar 27, 2007 7:32 pm

ቅራሪ wrote:ጌታ ጌታጠንበለል ሰላም ነህ በምጀመሪያ ሰላምታ ላስቀድም ብዬ ነው "'እኛስ"" ብዬ የጠቀስኩት እኔ አንተን ጉዱን እና እምናውቃትን ለማለት ያህል ነው ግን ዋናው ቁምነገር ለጥያቄዬ መልስ ስለሰጠህኝ አመሰግናለሁ በኛም በኩል እንደዛው ነው

ጉዱ ቅቅቅ ሸውራራ ለሸውራራ ተያይዞ ገደል ነው በለኝ ቅቅቅ አትጥፋ


ኧረ ተይ አንቺ ልጅ እምናውቃትን እያልሽ እየሸፋፈንሽ ሌላ ነገር አታስመስያት!!! ስም ካላት ተናገሪና እንደምትወደድና እንደማትወደድ እነግርሻለሁ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby በቃል » Tue Mar 27, 2007 8:40 pm

ሰላም ለቤቱ እና ለባለቤቱ

አቶ ጌታ ሰላም ኖት ወንድማችን ውቃው የኛኑ ታሪክ ከሽኖ ያወጋናል:: መቼስ ማንነትን በቃል በዚች መስኮት መግለጽ ባይቻልም እንደውቃው አሳምሮ ማቅረቡ ትልቅ ችሎታ ነው::
ውቅነት እስቲ ለጥቅበት.....

ቸር እንሰንብት
በቃል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Fri Feb 11, 2005 10:38 pm

Postby ShyBoy » Tue Mar 27, 2007 10:14 pm

እኔም እንደውቃው ጽሁፍ የሚያዝናናኝ የለም!!! ዋርካ ውስጥ ብዙ Stars አሉ.........ማዝናናትን በተመለከተ ደግሞ ውቃው Super-Star ነው!!!!!!!!!

እስቲ እባክህ ቀጥልበት!!!!!!!!!!!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ቅራሪ » Mon Apr 02, 2007 9:36 pm

ውድ ውቃው ምነው የት ነው እልም ብለህ የጠፋህው? አረ ብቅ በልልን ናፍቆት ሲበዛ እኮ ሆስፒታል ያስተኛል ብለዋል ስለዚህ አትጥፋብን
ቅራሪ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 247
Joined: Wed May 10, 2006 4:42 am
Location: adiss abeba

Postby ማያዬ » Mon Apr 02, 2007 11:20 pm

ዉቃው wrote:አሁን ላይ ሆኘ ወደኋላ ሳሰበው ያኔ በልጅነቴ : እግሮቼ ሞተው ነበር እንዴ ? እያልኩ ራሴን እጠይቃለሁ :: ሞተው ቢሆን እንጂማ ነፍስ ያለው እግር እንዴት እንደዚያ ይሸታል ! በኔ ሰሌት በዓመት ሀያ ጊዜ ጉንፋን ይይዘኝ እንደሆን : ለአስራ ዘጠኙ ተጠያቂ ሸራ ጫማዎቼ ናቸው :: እርግጥ ነው ሸራ ጫማውም ሆነ እኔ ውሃ የሚያገኘን በሳምንት አንዴ ነበር :: ያውም በዕለተ ቅዳሜ ! ሸራዋ እሁድ ታጥባማ ለሰኞ ት/ቤት አትደርቅማ ! ሰለዚህም ሸራዬ በቅዳሜ
መታጠቧ ግድ ነው :: አቤት ያቺ ብረት ግን ምጣድ ምን ያላየችው አለ ! እኔ እታጠብባታለሁ : እነቦጌም ይታጠቡባታል : ቁናሳሟ ሸራዬ : የቤቱ : የሴቱ : የከብቱ ጣጣ ይታጠብባታል :: ከዚያ ከተረፈች ደግሞ በርበሬ ይሰጣባታል :: በዚህ ቢበቃት እሺ :: ደሞ የቶታአው እናት ይመጡና : "የዉቃው እናት ብረትምጣዶን ያውሱኛል " ተብሎላት : የነሱን ቤት ደግሞ ስታገለገል ትውላለች :: ብረት ምጣዶች እኮ ባለውለታዎቻችን ናቸው :: ከነ ጆግና ማስታጠቢያ ተደምረው ጋር ሆነው በገጣሚያኑ ሊገጠምባቸው ይገባል ::ውቃው..... በናትህ ሆዴን ነው ያሳመምከኝ በሳቅ ሂሂሂሂሂሂ
ነፍስህ አይማርም የብረት ምጣዱ ነገር ምን እንዳስታወሰኝ ታውቃለህ ...አንዲት ልጅ እዚህ ምንም አልመች ይላትና ወደ ሀገርቤት በጣም መመለስ እንደምትፈልግ እያማረረች ስትናገር የሰማት ልጅ...ተዋት ትሂድ በብረት ምጣድ መታጠብ ናፍቓት ነው አለ....ሂሂሂ ሂሂሂሂ እስኪያመኝ ድረስ .......አንተ ድግሞ የባስክ ነህ አትጥፋ እባክህ ትንሽ አስነብበን
አክባሪህ
''''ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ''''
ማያዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Mon Jan 29, 2007 2:48 pm

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests