ትዝታዬ : ናፍቆቴና ግርምቴ ! እናቴ !

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዞብል2 » Sun Oct 16, 2011 8:48 pm

ሙዝ1(ጀጋው ቦጋለ) :P የጻፍከው እሮሮ ነው :wink:አሁንስ አሳዘንከኝ :P

ዞብል ከአራዳ
ዞብል2
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1987
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ደጉ » Mon Oct 17, 2011 8:12 pm

ዉቃው wrote:...መልካቸው ትዝ ይለኛል :: ቆንጆዎች ነበሩ :: እነሱን ስመኝ ..ሳሰላስል : ጸሀይነሽ ቤታችን ተቀጠረች ::

የጠዋት ፈረቃ ተማሪ ነበርኩና ...ከሰዓት እኔና እሷ ብቻንን ነበርን :: ከብዙ መግባባት በኋላ ...አንድ ቀን ምንነቱ ያልታወቀ ልፊያ ተጀመረ :: ልፊያው ረጅም ነበርና ..ሳነነካካ ቀኑ መሸ :: ቀናትም አለፉ ::...

...አህ! ውቃው አንተ ልፊያ አስተምርህ ነው ከናንተ ቤት ወተው እኛ ቤት ሲቀጠሩ ስራ ትተው ካልተላፋን እሚሉት....? ;)
....የት/ቤት ትዝታህ ግን ብዙ ብዙ ነገር አጠገቤ ይቀመጡ የነበሩትን...ከፊቴም ሆነ ከሁዋላዬ ይቀመጡ የነበሩትን ሁሉ አስታውስከኝ....የፍቅር ደብዳቤ ነገር ሳይቸግራቸው ጽፈውልኝ ዳይሪክተራችን አቶ እሸቱ ጋ አስወስጄ ያስገረፍኩዋቸው ...ዙፋን እና ዝናሽ እሚባሉ ልጆች....:( ይሄ ጽሁፍ ካያችሁ ...እባካችሁ እንደገና የፍቅር ደብዳቤ ጻፉልኝ አሁን ማስገረፍ ትቻለሁ::
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4412
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ዛዙ » Fri Jan 20, 2012 2:45 pm

ውቅሹ እንዴት ነሽ ጽሁፍሽ ሁሉ ይመቸኛል:: የኔ ትውልድ ታሪክ ነው: ያብዮት ልጆች ታሪክ:: በቅርቡ አንድ 'ማህሙድ ጋር ጠብቂኝ' የሚል መጽሀፍ አዲስ አበባ ታትሟል:: በውስጡ ያለው አተራረክ ያንተ ስታይል ሲሆን በተለይ የቴሌቪዥናችሁን ታሪክ (አንቴናውን አስተካክዬ ስመለስ ከጣራ ላይ እንደዩሪ ጋጋሪን ደማቅ አቀባበበል ተደረገልኝ' የሚለው ያንተ አጻጻፍ ፊርማ ይታይበታል) እዚህ ገጽ ላይ ያነበብኩት መስሎኝ ነበር:: አሁን ስፈልገው ጠፋብኝ:: እንዳለ ኮርጆህ ነው? ስታይልህን ኮርጆ ነው? አነተ ነህ ጸሀፊው? ወይስ ተሳስቻለሁ?
ዛዙ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 199
Joined: Sat Oct 09, 2004 12:46 pm
Location: ethiopia

Postby ዉቃው » Sun Jan 22, 2012 1:21 am

ዛዙ ፍሬንድ ....

ሰለ ሞራል ሰፖርቱ እጅግ አመሰግናለሁ :: "ማህሙድ ጋር ጠብቂኝን" አንብቤዋለሁ :: በጣም ግሩም ወግ ነው :: ከጠሃፊው ጋር በግል አንተዋወቅም / ወይም ጠሃፊው እኔ አይደለሁም :: ምናልባች ተመሳስሎብህ ከሆነ ... አጋጣሚ እንጂ ሌላ አይደለም ::

በሌላ በኩል እኛ ያብዮት ልጆች ያልፍንበትን ሂደት በጫወታ በሳቅ ብንቀደው በሚል ነበር የጀመርኩት :: ብዙ ኮምፐሌይን አላረኩም እንጂ ለዋርካ ጽፌላት የበላችው ..ስፍር ቁጥር የለውም :: ቢሆንም ቀደዳውን እንዳመቸን እንቀጥላለን :: አንተም አትጥፋ ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ዉቃው » Mon Feb 06, 2012 12:22 am

የኮሜዲያኖቹ ትራጄዲ

ዳላስ እንገናኝ.......ከገጸ ሶስት የዞረ....

ያብዮት ልጆች ቀደዳ ቀጥሏላ !

ለሚወዱን እና ለምንወዳቸው : ለነሃሪክ : ሙዝነት : የፋዘሩ ልጅ: ጉዱ: ኩሩዋ ኮንጂት : ደጉሰው : ፓን : ልብ ሰራቂዋ ያሚታ : ጦምን : ሴክሲዋ ሪጭ : ቂጣሟ የግል :...ሰንቱን ጠርቼ ልዝለቀው ...ሁሉንስ ብወድ ...አሜሪካ በሱፐር ቦውል ጸጥ እንዳለች ..

መጣሁ ...አይ ቤች ፎር ኢላይ ማንኒግ
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ዉቃው » Tue Feb 07, 2012 3:02 am

ዕድል እንደዚህ ነው ጃይንቶች አሸነፉ : እኛም ውርርዱን በላን :: ተመስገን ነው ::
------------------------------------------------------------------------

ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባዎቹ መጨረሻ እና ሰማኒያዎቹ መጀመሪያ በኢትዮጵያ ሬዲዮ አንዳንድ ስርጭቶች አሪፍ ዘመን ነበር ቢባል አይበዛበትም ...በኔ ዕድሜ :: ይንበርበሩ ምትኬ : ጎርፍነህ ይመር : ደምሴ ዳምጤ በስፖርት .....ዳርዮስ ሙዲ : ዓለምነህ ዋሴ : አማረ ማሞ : ነጋሽ መሀመድ : ነግስት ሰልፉ : ብርቱካን ሃረገወይን - በዜና ፋይል ልቤን ቀጥ አርገውት ነበር :: በተለይ ዜና ፋይል ወዝ ዚ ቤስት :: አቀራረባቸው ደምጻቸው እና የዜናቸው ልብ ሰቃይነት ወደር አልነበረውም :: ከሁሉም የንግስት ሰልፉ እና የ ዳርዮስ ሙዲ ድምጽ ፏ ያረገኛል :: በልብ ሰቃይነቱ ደግሞ ዓለምነህ ዋሴንና ሳዳም ሁሴንን (በዴዘርት ስቶርም) እስከመቸውም አልረሳቸውም :: ጄንራል ኖርማን ሽዋርንኮቭን ከራሳቸው ይበልጥ እስከማወቅ አድርሶን ነበር :: ያ ዘመን አሪፍ ነበር ::

አሁን የት ናቸው ቢባል ...ጎርፍነህ ሞቷል : ዳርዮስ ሞቷል : ዓለምነህ እስራኤል ተሰዶ ኍላም መመልሱን ሰምቻለሁ : ዜና ላይ ግን የለም :: ንግስት ሲያትል ናት : የብርቱካንን ሁኔታ አላውቅም :: ደምሴ ታሟል : ነጋሽ ጀርመን : እንዲሁም ይንበርበሩ ጡረታ እንደነበር ..ኋላ ይሙት ይኑር አላውቅም ::

የኢኢሀደግ መንግስት ወይም አባላት ...ለደርግ ባለስልጣናት ምህረት እንዳደረጉ ....በዘመናችን ለነበሩ አብዮታዊ የፕሮፓጋንዳ ዘፍኖች...ዜናዎች እና የፊልም ክምችቶችን ምህረት ሊያደርጉላቸው ይገባል :: እኛ እንዝናናበት ::

ቁርፂ ቁሁርጺ
ቁርጺ ቁሁርጺ
ያወያነ መደንገጢ
መፈርጠጢ
በወሎና በትግራሃ .. ይህን ስንዘፍን ኢሀደግ ወሎን ትግራይን ይዞ አምቦ ደርሷል ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ዛዙ » Wed Feb 08, 2012 10:03 am

ውቅሽ ስለመልስህ አመሰግናለሁ:: መጨረሻ ላይ ስለሁሉም ጋዜጠኞች የሰጠኸው መረጃ በጣም አሪፍ ነው:: አለምነህ ዋሴ ግን አሁንም ፋና ራዲዮ ላይ ይሰራል መሰለኝ:: ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ ያብዮትና የፕሮፓጋንዳ ዘፈኖች ያደግንባቸው ሰለሆኑ ልዩ ትዝታ አላቸውና ያኔ አሰልችተውን ቢሆንም እንኳን አሁን የት ነው የምናገኛቸው ብዬ የተድላ አስፋው ገጽ ላይ ጠይቄ ነበር:: እንደመሰለኝ ግን ማንም ምህረት ሊያረግላቸው አልፈለገም:: እንዴት አንድ ሰው እንኳን ዩትዩብ ላይ እንኳን የሆነ ነገር አልለጠፈም እያልኩ እገረማለሁ:: ለማንኛውም ስለትዝታህ እግዜር ይስጥልን ጓድ ውቃው: :lol:
ዛዙ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 199
Joined: Sat Oct 09, 2004 12:46 pm
Location: ethiopia

Postby ሙዝ1 » Sat Feb 11, 2012 12:58 pm

ዉቅሽ ....
በዛን ዘመንም አካባቢያዊ ለዉጥ ማህበራዊ ክፍተቱ ላይ ያለዉ ተጽዕኖ አናሳ ነዉ ማለት ነዉ? አዲስ አበባም .... ጎጃምም ... ሀረርም ልክ እንዳንተዉ ነበርን .... እኔ ያኔም ዘንድሮም ለሚዲያ ፍቅር የለኝም .... ያኔም የሚወሩት ... ዛሬም የሚወሩት ብዙም አይመቸኝም .... ያንንም ያጠፋሁ መስሎኝ ፔፐር ሚዲያ ላይ ዘዉ ብዬ ገብቼ .... ሹክክክ ብዬ ወጥቻቸለሁ ....

ወደ ትዝታዎችህ ....
ሁሉንም ማለት በሚያስችል ደረጃ ስማቸዉን የማዉቃቸዉ ጋዜጠኖች ናቸዉ .... አንተዉ እንዳልከዉ ዜና ፋይልን .... "ዜ"ን ጎተት አድርጎ ከሚነበበዉ ዜማዉ ዉጭ ብዙም ትዝ የሚለኝ ቁርኝት የለኝም ... ምናልባትም ቡና ቡና የገቢ ምንጫችን ቡና ቡና ከሚለዉ ዘፈንም ለይቼ አላዳምጠዉም ...

አለምነህ ዋሴ ....
ቅዳሜ ከሰዐት ይመስለኛል .... በጎርናና ድምጹ ያነበንባል ... ስለ ማይክ ታይሰን ... ሁሉም የእድሜ እኩዮቼ ተመስጠዉ ያዳምጣሉ .... እኔ እንኳን ከባለ ሬዲዮ ጓደኛዬ (ስሙን አልጠራም) ... የአባቱን ሬዲዮ .... የአባቱን ጫማ .... የአባቱን አሮጌ ጃኬት መልበስ የሚወደዉ ጓደኛዬ ሁኔታን ከላይ እስከ ታች የመቃኘት ያክል የአለምነህ ወግ አይመስጠኝም .... ዛሬም ድረስ እምቢ ብሎ አለምነህ ሲነሳ ያ የቀድሞ ወዳጄ (አሁን ትንሽዬ ባለ ስልጣን ሁኗል) ... አለባበስና ሁኔታ ዉል ይልብኛል ... :: ግን ያሁን ልጆች እንደኛዉ ዘመን የዋህ ይሆኑ ይሆን? ከላይ ወደታች አሮጌ ልብስና ጫማ እንደወረስን ሁሉ .... ... ለነገሩ የቻይና ልብስ መጀመሪያ እኛ ላይ መች በርክቶ ነዉ ለዉርስ የሚበቃዉ ... የያኔዉ ግን ለጉድ ነበር .... በተለይ ወላጆቻቸዉ ወታደር አልያም የአዉራ ጎዳና ሰራተኛ ልጆች ህምምምም

ኤኒዌይ አለምነህ አለ ....
ብርቱካንም አለች አሁንም በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴለቪዥኝ ባለ ስልጣን ነገር ነች መሰለኝ (እህቷ ህብረት ሀረገወይን ጓደኛ ነበረች)
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Sat Feb 11, 2012 5:59 pm

'ዙፋን እና ዝናሽ' ...ይገርማል በእኛ ዘመን የነበሩ ስሞች እንዲህ አይነት ነገር ይበዛቸው ነበር ...ገነት ፋናየ ሂሩት ሰላማዊት ...አፎሚያ የምትባል ክላስ ሜት ነበረችን ...ከጨረቃ የመጣ ስም ይመስለኝ ነበር ...መቼስ ስለ ዘመኑ የሚለው ነገር ይኖረዋል::

በነገራችን ላይ ስም ከተነሳ አይቀር የሰማሁትን ቀልድ እንካችሁ ... ልጁ ስሙን ከአበረ ወደ ናቲ ለማስቀየር ፈለገ አሉ :D ፍርድ ቤት ሄዶ ተቃዋሚ ካለ ምናምን ሲባል አሉ ዳኛው ራሳቸው ተቃወሙና ባንድ ጊዜማ ከአበረ ወደ ናቲ አትቀይርም... ትንሽ በ 'ተስፋይ' መቆየት አለብህ ብለው ...ጠረጴዛውን በመዶሻ ድው :lol:

ደጉ wrote:
ዉቃው wrote:...መልካቸው ትዝ ይለኛል :: ቆንጆዎች ነበሩ :: እነሱን ስመኝ ..ሳሰላስል : ጸሀይነሽ ቤታችን ተቀጠረች ::

የጠዋት ፈረቃ ተማሪ ነበርኩና ...ከሰዓት እኔና እሷ ብቻንን ነበርን :: ከብዙ መግባባት በኋላ ...አንድ ቀን ምንነቱ ያልታወቀ ልፊያ ተጀመረ :: ልፊያው ረጅም ነበርና ..ሳነነካካ ቀኑ መሸ :: ቀናትም አለፉ ::...

...አህ! ውቃው አንተ ልፊያ አስተምርህ ነው ከናንተ ቤት ወተው እኛ ቤት ሲቀጠሩ ስራ ትተው ካልተላፋን እሚሉት....? ;)
....የት/ቤት ትዝታህ ግን ብዙ ብዙ ነገር አጠገቤ ይቀመጡ የነበሩትን...ከፊቴም ሆነ ከሁዋላዬ ይቀመጡ የነበሩትን ሁሉ አስታውስከኝ....የፍቅር ደብዳቤ ነገር ሳይቸግራቸው ጽፈውልኝ ዳይሪክተራችን አቶ እሸቱ ጋ አስወስጄ ያስገረፍኩዋቸው ...ዙፋን እና ዝናሽ እሚባሉ ልጆች....:( ይሄ ጽሁፍ ካያችሁ ...እባካችሁ እንደገና የፍቅር ደብዳቤ ጻፉልኝ አሁን ማስገረፍ ትቻለሁ::
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

Postby ክቡራን » Sat Feb 11, 2012 6:24 pm

ነፍሴ እረ የስም ነገር ከተነሳ ናፒና ናቲ የኛ ዘመን ስሞች አለነበሩም:: ""ምረቱና ምህረቱም ስብሀቱና ሙላቱም እኮ የኛ ዘመን ስሞች ነበሩ :: :lol:ምረቱን ጻፍካትና ኮፒ እስከማድረገው ደርስ አጠፋሀት:: :D :D ወይኔ ወይኔ ....ወይኔ .... :lol: .ለካ በዋልድባም ይጭፈራል እኔ ይሄንን መቼ አውቅልህ..... :D ይቅርታ ውቃው ቤትህ ውስጥ ያብቶብስ ሌባ ገብቶ አይቼ ነው:: 8)

ናፖሊዮን ዳኘ wrote:'ዙፋን እና ዝናሽ' ...ይገርማል በእኛ ዘመን የነበሩ ስሞች እንዲህ አይነት ነገር ይበዛቸው ነበር ...ገነት ፋናየ ሂሩት ሰላማዊት ...አፎሚያ የምትባል ክላስ ሜት ነበረችን ...ከጨረቃ የመጣ ስም ይመስለኝ ነበር ...መቼስ ስለ ዘመኑ የሚለው ነገር ይኖረዋል::

በነገራችን ላይ ስም ከተነሳ አይቀር የሰማሁትን ቀልድ እንካችሁ ... ልጁ ስሙን ከአበረ ወደ ናቲ ለማስቀየር ፈለገ አሉ :D ፍርድ ቤት ሄዶ ተቃዋሚ ካለ ምናምን ሲባል አሉ ዳኛው ራሳቸው ተቃወሙና ባንድ ጊዜማ ከአበረ ወደ ናቲ አትቀይርም... ትንሽ በ 'ተስፋይ' መቆየት አለብህ ብለው ...ጠረጴዛውን በመዶሻ ድው :lol:

ደጉ wrote:
ዉቃው wrote:...መልካቸው ትዝ ይለኛል :: ቆንጆዎች ነበሩ :: እነሱን ስመኝ ..ሳሰላስል : ጸሀይነሽ ቤታችን ተቀጠረች ::

የጠዋት ፈረቃ ተማሪ ነበርኩና ...ከሰዓት እኔና እሷ ብቻንን ነበርን :: ከብዙ መግባባት በኋላ ...አንድ ቀን ምንነቱ ያልታወቀ ልፊያ ተጀመረ :: ልፊያው ረጅም ነበርና ..ሳነነካካ ቀኑ መሸ :: ቀናትም አለፉ ::...

...አህ! ውቃው አንተ ልፊያ አስተምርህ ነው ከናንተ ቤት ወተው እኛ ቤት ሲቀጠሩ ስራ ትተው ካልተላፋን እሚሉት....? ;)
....የት/ቤት ትዝታህ ግን ብዙ ብዙ ነገር አጠገቤ ይቀመጡ የነበሩትን...ከፊቴም ሆነ ከሁዋላዬ ይቀመጡ የነበሩትን ሁሉ አስታውስከኝ....የፍቅር ደብዳቤ ነገር ሳይቸግራቸው ጽፈውልኝ ዳይሪክተራችን አቶ እሸቱ ጋ አስወስጄ ያስገረፍኩዋቸው ...ዙፋን እና ዝናሽ እሚባሉ ልጆች....:( ይሄ ጽሁፍ ካያችሁ ...እባካችሁ እንደገና የፍቅር ደብዳቤ ጻፉልኝ አሁን ማስገረፍ ትቻለሁ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7940
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Sat Feb 11, 2012 7:45 pm

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :D ክብሮም :!: ወጥመድ አትችልም . :idea: እንደምትከታተለኝ አውቄ እጢህን ቁርጥ ለማድረግ አውቄ ያደረኩት ነው :idea: ያኛውንም ክብሮም ጠብቄ ነበር ለጉዳይ ባንክ ደረስ ብሎ ሊመጣ ሄዶ ነው መሰል :lol:

ናፖሊዮን እና ምረቱ እኮ ያንድ እናት ልጆች ናቸው ይሔው በድጋሚhttp://www.youtube.com/watch?v=7bC7mAKYF3o&feature=share
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

Postby ዉቃው » Sun Feb 12, 2012 12:38 am

ቆልሜው ..ያው መቸም ወዲያና ወዲህ ሆነን እንቀደደው በማለት እንጂ ..የአንድ ዘመን ልጆች ሆነንም ላንዳችን ስሜት የሚሰጡን ለሌላችን ላይሰጡን የሚችሉ መሆኑን አላጣሁም :: ሲጀመር እኔ ..ለመጠጥ : ለሴቶች እና ለወሬ ከፍተኛ ፍቅር ያለኝ ነኝ :: አንተ ደግሞ ባንጻሩ ..ይመሰለኛል ..ምሁር .....ለንባብ ...እና ለልማታዊ ባለሀብትነት የተፈጠርክ ነክ :: ስለሆነም የኔ ያለፈ ግማሽ ያለፈ ዉሎ ...ያንተ ያለፈ የድሮ ግማሽ ዉሎ ....የሌላውም ያለፈ የቀድሞ ግማሽ ዉሎ ሲቀደድ ..በስተመጨረሻው ምሉዕ ቀደዳ ይሆናል እልሻለሁ :: ለኡዜም ለዛዙም ለናፒም ለክቡም ለደጉም ለሁሉም ወዳጆቼ የከበረው ምስጋናዬ ይድረስ ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ዉቃው » Sun Feb 12, 2012 1:14 am

የዓለምነህ ድምጽ ከነአቀራርቡ የመሰጠኝ ...በዴዘርት ስቶርሙ ዘገባ ነበረ :: አጋነነክ ባልባል ...በዘመኑ በጣም የተዋጣለት ነበር :: አሜሪካ ኢራቅን ባየር ስተደበድብ ..ኢራቅ ደግሞ ስከድ ሚሳኢል ወደ እስራኤል ትተኩስ ነበር :: እስራኤል ጦርነቱ ውስጥ እንድትገባ ለማድረግ የነበረው ሙከራ በእስራኤል ፔትርየት ሚሳኤሎች መክሸፉን ያወቅኩት ..አሁንም የማስታወሰው ከዓለምነህ እና ከዜና ፋይል የዘመኑ ዘጋቢዎች ነበር ::

በዚያው ዘመን ደጀኔ ጥላሁን የሚያዘጋጀው የእሁድ ምሽት ሶስት ሰዓቱ "ከመጻህፍት ዓለም"ም አላመለጠኝም :: ፍቅር እሰከመቃብር ሲተረክ አልደረስኩም :: ጣምራ ጦር ሲተረክ በጣም ጥቂት ትዝ ቢለኝም አብዛኛውን ታሪክ እሰማ የነበረው ባዲስ አበባው ጦር ሰራዊት መኮንኖች ክበብ ..ክኛ ተለቅ ተለቅ ያሉት ..በየሰኞው ጠዋት ሪቪው ሲያደርጉ ነበር :: መጽሀፉን ፈልጌ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት ባይሳካም .. ገጸ-ባህርይ- አስግድ - ጭንቅላቴ ውስጥ ከቀሩ ስሞች አንዱ ነው :: በከመጻህፍት ዓለም ....የከአድማስ ባሻገሯ ሉሊት እና የሰመመኑ አቤል ሙሉዬ ..በእውን የማውቃቸው ሰዎች ይመስሉኛል :: ስሙን ከረሳሁት መጽሀፍ ደግሞ..... የሞገደኛው ነውጤ ትርካ ያለበት .....ከዚያ ...የመጨረሻዋ ቅጠል በተባለው ትርካም ሽማግሌው በርማን አንዲት ቅጠል ስሎ ዛፉ ላይ በመስቀል እሱ ሞቶ ታማሚዋ ማትረፉን የሰማሁበት ሀዘን አሁንም እንዳለ ነው ::

በኢትዮጵያ ሬድዮ የእሁድ ጠዋቱ የነታደሰ ሙሉነህ እና ታምራት ወግ ...ለማብራሪያው አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ - ተብሎ እንኳን የኔ ቢጤው ጡጦ ራስ ይቅርና ...ለተመራመሩትም ቢሆን ግራ የሚያጋባ የግማሽ ሰዓት ሀተታ : የቅዳሜ ከሰዓቱ መዝናኛ በነ ጌታቸው ማንጉዳይ እና የዘፈነን ምርጫን ክፍለ ጊዜ አስታውሳለሁ :: ነፍስ ሳውቅ የእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ያመለጠኝ ....በወር አንዴ ዕድር ልከፍል በሄድኩ ወቅት ነው :: ለሱም ዋነኛ ምክንያት ...ዕድር ቤቱ የሚክፈተው ከበጽኪያን መልስ ሶስት ሰዓት ሰለነበርና ..በስም ጥሪው ተዋረድ ወቅት ያባቴ ስም አንድ ሶስተኛ አባል ከፍሎ ከሄደ በኋላ ይገኝ ሰለነበር ነው :: እንዲህ እንዲ እያልኩ የአፈሳ ወጌ ጋር ድረሻለሁ :: እቀጥለዋልሁ ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ፀዋር » Sun Feb 12, 2012 1:39 am

አንተ ደግሞ ሽማግሌ ይመስል በትዝታ ትኖራለህ :lol: :lol: ስለ ድሮ እንጂ ስለ ነገ ስታወራ ሰምቼህ አላቅም:: እርጅና ነው? :lol:ዉቃው wrote:የዓለምነህ ድምጽ ከነአቀራርቡ የመሰጠኝ ...በዴዘርት ስቶርሙ ዘገባ ነበረ :: አጋነነክ ባልባል ...በዘመኑ በጣም የተዋጣለት ነበር :: አሜሪካ ኢራቅን ባየር ስተደበድብ ..ኢራቅ ደግሞ ስከድ ሚሳኢል ወደ እስራኤል ትተኩስ ነበር :: እስራኤል ጦርነቱ ውስጥ እንድትገባ ለማድረግ የነበረው ሙከራ በእስራኤል ፔትርየት ሚሳኤሎች መክሸፉን ያወቅኩት ..አሁንም የማስታወሰው ከዓለምነህ እና ከዜና ፋይል የዘመኑ ዘጋቢዎች ነበር ::

በዚያው ዘመን ደጀኔ ጥላሁን የሚያዘጋጀው የእሁድ ምሽት ሶስት ሰዓቱ "ከመጻህፍት ዓለም"ም አላመለጠኝም :: ፍቅር እሰከመቃብር ሲተረክ አልደረስኩም :: ጣምራ ጦር ሲተረክ በጣም ጥቂት ትዝ ቢለኝም አብዛኛውን ታሪክ እሰማ የነበረው ባዲስ አበባው ጦር ሰራዊት መኮንኖች ክበብ ..ክኛ ተለቅ ተለቅ ያሉት ..በየሰኞው ጠዋት ሪቪው ሲያደርጉ ነበር :: መጽሀፉን ፈልጌ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት ባይሳካም .. ገጸ-ባህርይ- አስግድ - ጭንቅላቴ ውስጥ ከቀሩ ስሞች አንዱ ነው :: በከመጻህፍት ዓለም ....የከአድማስ ባሻገሯ ሉሊት እና የሰመመኑ አቤል ሙሉዬ ..በእውን የማውቃቸው ሰዎች ይመስሉኛል :: ስሙን ከረሳሁት መጽሀፍ ደግሞ..... የሞገደኛው ነውጤ ትርካ ያለበት .....ከዚያ ...የመጨረሻዋ ቅጠል በተባለው ትርካም ሽማግሌው በርማን አንዲት ቅጠል ስሎ ዛፉ ላይ በመስቀል እሱ ሞቶ ታማሚዋ ማትረፉን የሰማሁበት ሀዘን አሁንም እንዳለ ነው ::

በኢትዮጵያ ሬድዮ የእሁድ ጠዋቱ የነታደሰ ሙሉነህ እና ታምራት ወግ ...ለማብራሪያው አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ - ተብሎ እንኳን የኔ ቢጤው ጡጦ ራስ ይቅርና ...ለተመራመሩትም ቢሆን ግራ የሚያጋባ የግማሽ ሰዓት ሀተታ : የቅዳሜ ከሰዓቱ መዝናኛ በነ ጌታቸው ማንጉዳይ እና የዘፈነን ምርጫን ክፍለ ጊዜ አስታውሳለሁ :: ነፍስ ሳውቅ የእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ያመለጠኝ ....በወር አንዴ ዕድር ልከፍል በሄድኩ ወቅት ነው :: ለሱም ዋነኛ ምክንያት ...ዕድር ቤቱ የሚክፈተው ከበጽኪያን መልስ ሶስት ሰዓት ሰለነበርና ..በስም ጥሪው ተዋረድ ወቅት ያባቴ ስም አንድ ሶስተኛ አባል ከፍሎ ከሄደ በኋላ ይገኝ ሰለነበር ነው :: እንዲህ እንዲ እያልኩ የአፈሳ ወጌ ጋር ድረሻለሁ :: እቀጥለዋልሁ ::
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Sun Feb 12, 2012 2:49 am

ወደድንም ጠላንም እኔ እና አንተ ያንድ ዘመን ልጆች ነን :D

""እንደምን አደራችሁ ጦርነቱ ተጀምሯል"" ን [ዓለምነህ ዋሴ] በጣም አስታውሳለሁ...

አቤል ሙሉየ (ኦር ጥላዬ ?) እሱን ማን ይረሳል...መጽሀፉ ራሱ መጀመሪያ ያነበብኩት ልብ ወለድ እና ምናልባትም ዮኒቨርሲቲ የመግባት ጉጉት [ያኔ ብርቅ በነበረበት ዘመን] ሳይፈጥርብኝ አልቀረም:: ገጸ-ባህሪውን በተመለከተ ግን በህይወቱ ቢያንስ አንዴ አቤል ጥላየን ሆኖ የማውቅ ያለ አይመስለኝም....

በስንት ጊዜ ቀደዳህን ታደምኩ ...እንደጉድ ነው የምትቀጂው ...የዘመንህ ሰው እንደመሆኔ የቀደዳህን ጣዕም በውል አውቀዋለሁ...ይቀደድ ...
ዉቃው wrote:የዓለምነህ ድምጽ ከነአቀራርቡ የመሰጠኝ ...በዴዘርት ስቶርሙ ዘገባ ነበረ :: አጋነነክ ባልባል ...በዘመኑ በጣም የተዋጣለት ነበር :: አሜሪካ ኢራቅን ባየር ስተደበድብ ..ኢራቅ ደግሞ ስከድ ሚሳኢል ወደ እስራኤል ትተኩስ ነበር :: እስራኤል ጦርነቱ ውስጥ እንድትገባ ለማድረግ የነበረው ሙከራ በእስራኤል ፔትርየት ሚሳኤሎች መክሸፉን ያወቅኩት ..አሁንም የማስታወሰው ከዓለምነህ እና ከዜና ፋይል የዘመኑ ዘጋቢዎች ነበር ::

በዚያው ዘመን ደጀኔ ጥላሁን የሚያዘጋጀው የእሁድ ምሽት ሶስት ሰዓቱ "ከመጻህፍት ዓለም"ም አላመለጠኝም :: ፍቅር እሰከመቃብር ሲተረክ አልደረስኩም :: ጣምራ ጦር ሲተረክ በጣም ጥቂት ትዝ ቢለኝም አብዛኛውን ታሪክ እሰማ የነበረው ባዲስ አበባው ጦር ሰራዊት መኮንኖች ክበብ ..ክኛ ተለቅ ተለቅ ያሉት ..በየሰኞው ጠዋት ሪቪው ሲያደርጉ ነበር :: መጽሀፉን ፈልጌ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት ባይሳካም .. ገጸ-ባህርይ- አስግድ - ጭንቅላቴ ውስጥ ከቀሩ ስሞች አንዱ ነው :: በከመጻህፍት ዓለም ....የከአድማስ ባሻገሯ ሉሊት እና የሰመመኑ አቤል ሙሉዬ ..በእውን የማውቃቸው ሰዎች ይመስሉኛል :: ስሙን ከረሳሁት መጽሀፍ ደግሞ..... የሞገደኛው ነውጤ ትርካ ያለበት .....ከዚያ ...የመጨረሻዋ ቅጠል በተባለው ትርካም ሽማግሌው በርማን አንዲት ቅጠል ስሎ ዛፉ ላይ በመስቀል እሱ ሞቶ ታማሚዋ ማትረፉን የሰማሁበት ሀዘን አሁንም እንዳለ ነው ::

በኢትዮጵያ ሬድዮ የእሁድ ጠዋቱ የነታደሰ ሙሉነህ እና ታምራት ወግ ...ለማብራሪያው አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ - ተብሎ እንኳን የኔ ቢጤው ጡጦ ራስ ይቅርና ...ለተመራመሩትም ቢሆን ግራ የሚያጋባ የግማሽ ሰዓት ሀተታ : የቅዳሜ ከሰዓቱ መዝናኛ በነ ጌታቸው ማንጉዳይ እና የዘፈነን ምርጫን ክፍለ ጊዜ አስታውሳለሁ :: ነፍስ ሳውቅ የእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ያመለጠኝ ....በወር አንዴ ዕድር ልከፍል በሄድኩ ወቅት ነው :: ለሱም ዋነኛ ምክንያት ...ዕድር ቤቱ የሚክፈተው ከበጽኪያን መልስ ሶስት ሰዓት ሰለነበርና ..በስም ጥሪው ተዋረድ ወቅት ያባቴ ስም አንድ ሶስተኛ አባል ከፍሎ ከሄደ በኋላ ይገኝ ሰለነበር ነው :: እንዲህ እንዲ እያልኩ የአፈሳ ወጌ ጋር ድረሻለሁ :: እቀጥለዋልሁ ::
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests