ትዝታዬ : ናፍቆቴና ግርምቴ ! እናቴ !

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Feb 12, 2012 4:32 am

ፀዋር wrote:አንተ ደግሞ ሽማግሌ ይመስል በትዝታ ትኖራለህ :lol: :lol: ስለ ድሮ እንጂ ስለ ነገ ስታወራ ሰምቼህ አላቅም:: እርጅና ነው? :lol:

የእርጎ ዝንብ :: ውቃው እንደተመቸው ይጫወት :: አንተን እዚህ የሚጣፍጥ ጨዋታ መካከል ምን ጥልቅ አደረገህ :evil:

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby እንሰት » Sun Feb 12, 2012 4:41 am

ናፖሊዮን ዳኘ wrote:ወደድንም ጠላንም እኔ እና አንተ ያንድ ዘመን ልጆች ነን :D

""እንደምን አደራችሁ ጦርነቱ ተጀምሯል"" ን [ዓለምነህ ዋሴ] በጣም አስታውሳለሁ...
::
[/quote]

እኔ ደግሞ የአጋነው ዋሴን አረፍተ ነገር ዜና እንዴት እንዳደረገው ነው ትዝ የሚለኝ

ጦርነቱ ተጀምሯል "እንደምን ዋላችሁ ነው

ዋርካ ይገርማል አይደል ውቃው ትዝታ ይጫወታል ያው የሚያውቀውን ግን የወደፊት ተንባዮችም አሉ እስኪ ኖስትራዳመሶችንም እንስማ መቸም ህዳሴ... አባይ ... እንደማይሆኑ ነው
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Sun Feb 12, 2012 5:28 am

ኖስትራዳመስ ...ታምራት ገለታ ማለትህ ነው :lol: በዚህኛው ዓለም ዋንጫ ያየነው የጀርመኑ አሳ ይሻል ነበር ...ችግሩ አሳ ጃርት አይወድም አሉ :D
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Feb 12, 2012 6:37 am

ሰላም ውቃው :-

መቼም እንደ አንተ ጨዋታዎች የሚጥሙኝ የሉም ::

በኢትዮጵያ ሬድዮ ድምፃቸውን እሠማቸው የነበሩትን አዘጋጆች ልጅ ሆኜ በዕዝነ-ልቡናዬ ሥሥላቸው ልክ እንደ ድምፃቸው ጥንካሬ ነበር :: በጣም ጎርናና ድምፅ ያላቸው በጣም ግዙፍ ሰዎች ይመስሉኝ ነበር :: በጣም ለስላሣ ድምፅ ያላቸው ደግሞ ኮሣሦች ይመስሉኝ ነበር :: በኋላ አንዳንዶችን በአካል ሣውቃቸው በልጅነቴ ያሠብኳቸውን ሣይሆን ... አዬ ልጅነት ...

ዳሪዮስ ሞዲን (ሞተ ነው ያልከኝ :cry: :cry: :cry: አፈሩን ያቅልልለት) ለመጀመሪያ ጊዜ በሰማኒያዎቹ መጀመሪያ አራት ኪሎ ለምለም ቤት ዊስኪ ሲጠጣ ነበር ያየሁት :: እርሱ ባለጌ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ከሬስቶራንቱ ባለቤት (ለምለም) ጋር እያወጋ በቀን ዊስኪውን ይለጋል :: ድምፁ የማውቀው ሰው ድምፅ ሆነብኝና ጓደኛዬን ብጠይቀው እርሱ መሆኑን ነገረኝ : አንድ ከሲታ ቀይ ሰው : አፍንጫው ከፊቱ የረዘመ :: በተቃራኒው የቤቱ ባለቤት ለምለም እጅግ ለጆሮ የሚሠቀጥጥ አሰቀያሚ ድምፅ ነበራት :: እርሱ ቀስ ብሎ ሲያወራ እርሷ በየመካከሉ ያንን አስጠሊታ ድምጿን ከፍ አድርጋ ታሽካካለች :: እኔ ያኔ ጆሮዬን አልይዝ ነገር ...ብቻ ....

በድምፅ ጉዳይ የተሸወድኩበት ሁለተኛው ሰው ደግሞ የደርግን የርሸና አዋጅ ያነብቡ የነበሩት ማቹን አቶ አሰፋ ይርጉን ያየሁ ዕለት ነው :: አዲሱ ገበያ አካባቢ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ለአንድ ለማውቀው ሰው ቀብር ሄጄ የቀብሩ ሰዓት እስኪደርስ ድረስ ከወዳጆቼ ጋር እዚያ ቤተክርስቲያኑ አፀድ ውስጥ እንንጎራደዳለን :: በአጠገባችን አቶ አሰፋ ሲያልፉ ከወዳጆቼ አንደኛው ቀስ ብሎ በለሆሣሥ 'አቶ አሰፋ ይርጉ ማለት እኒህ ናቸው :" አለን :: ዐይኔን ማመን አልቻልኩም : ''እንዴት ከእኒህ አጭርና ኮሣሣ ሰው ያን ያህል አገር የሚያንቀጠቅጥ ድምፅ ይወጣል ብዬ::" እንደገና ዞሬ ተመልሼ ማዬትና ማረጋገጥ አለብኝ አልኩና ተከትዬ ሄጄ አየኋቸው :: ወይ ጉድ ...

የአንዳንዶቹ ሥም የወንድማማቾች ሥም ይመሥላል :- አማረ እና ጥሩነህ ማሞ (የዘፈን ምርጫ ክፍለ-ጊዜ) ... በጣም እወደው የነበረ ፕሮግራም ::

ስፖርት ፕሮግራም ከሰለሞን ተሠማ እና ይነበርበሩ ምትኬ ጀምሮ እስከ ጎርፍነህ ይመርና ደምሴ ዳምጤ ያሉትን አስታውሣለሁ :: እነርሱ የሚናገሩት በሙሉ በጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርፆ ቀርቷል : በተለይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲጫወት :: አሁን በሕይወት ያለው ደምሴ ብቻ መሠለኝ ::

ከዜና ይበልጥ የሚስቡኝ የእሑድ ፕሮግራም : ከመጻሕፍት ዓለም : ልጅ ሆኜ ደግሞ ጋሸ ሰለሞን ቅዳሜ ቅዳሜ ጠዋት ያዘጋጅ የነበረው የሕፃናት ፕሮግራም ::

አሁን እኒያ ሁሉ ፕሮግራሞች እንዴት እንደሚተላለፉ ማዳመጥ ቀርቶ ....

መልካም ሠንበት ይሁንልህ : ይሁንላችሁ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ፀዋር » Sun Feb 12, 2012 10:57 am

አቶ ተድላ ክብርህን ራስህ ካልጠበቅከው ማንም አይጠብቅልህም:: በማያገባህ ገብተህ ስትሳደብ ይህ ለሁለተኛ ጊዜህ መሆኑ ነው:: ክብርህን ጠብቅ ብዬሀለሁ:: ቀትረ ቀላል::

ተድላ ሀይሉ wrote:የእርጎ ዝንብ ::
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby ክቡራን » Sun Feb 12, 2012 2:34 pm

ውቃው እኔም እስኪ እቺን ለዚህ ቤት ላዋጣልህ...የጋዜጠኞች ትዝታ ሲነሳ ሁላችንም የማንረሳው የእሁድ ፕሮግራም ነበር:: በዛ ፕሮግራም ውስጥ አንከር ከሚባሉ ጋዜጠኞች ውስጥ አንዱ ንጉሴ አክሊሉ ነው:: ንጉሴ አሁን አይኑ ላይ በደረሰበት ችግር በህክምና እየተረዳ ቢሆንም ያይኑ ብርሀን እየደከመ በመምጣቱ እቤት መዋል ጀምሯል....ህክምናውን አልጨረሰም....ታዲያ የኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት ድህረ ገጽ አንተም የምታወቀውና የምታደንቀው ድህረ ገጽ ( (ቆይ አድሬሱን እዚህ ጋ ልጻፈው... ) http://www.CyberEthiopia.com ዋና አዘጋጅ የሆኑት ንጉሴን እንግዳ አድረው አቅርበዋችው ነበር:: ከቤቱ ርእስ ጋር ስለሚሄድ እቺን ላዋጣ ብዬ ሊንኩን እዚህ አምጥቼዋለሁ::
http://www.archive.org/download/Intervi ... dited1.mp3
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7938
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Sun Feb 12, 2012 5:35 pm

የጨርቆሱ ክብሮም :D ውቃው በርድና ቢጠልጥህ እንጂ ካንተ የሚያስን እንዳይመስልህ :idea:

ሰማኒያ ምናምን ሺ አንባቢ የተተራመሰበት ቦታ ለጥፈህ ጎብኚ ለሌለው ሳይተህ ትራፊክ ጃም እያፈላልክ...ኮንትሪቢዮት እያደረኩ ነው ትላለህ?? አራዳዎች እኮ በጣም ሼም ያውቃሉ ነብሴ ...ሊንክህን ዱቅ ካረክ በኍላ እንኳን ታንኪዮ አትልም? :twisted:

ንጉሴ አክሊሉንስ ቢሆን ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ሲዘግቡ ወያኔ በአጋዚ አላደገደባቸውም... አይናቸውን ጨምሮ?! ሼም የሚባል ነገር (እንታዩ ሽሙ አላልኩም) ኤግዚስት ያደርጋል ....

ናፖሊዮን ዳኘ::

ክቡራን wrote:ውቃው እኔም እስኪ እቺን ለዚህ ቤት ላዋጣልህ...የጋዜጠኞች ትዝታ ሲነሳ ሁላችንም የማንረሳው የእሁድ ፕሮግራም ነበር:: በዛ ፕሮግራም ውስጥ አንከር ከሚባሉ ጋዜጠኞች ውስጥ አንዱ ንጉሴ አክሊሉ ነው:: ንጉሴ አሁን አይኑ ላይ በደረሰበት ችግር በህክምና እየተረዳ ቢሆንም ያይኑ ብርሀን እየደከመ በመምጣቱ እቤት መዋል ጀምሯል....ህክምናውን አልጨረሰም....ታዲያ የኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት ድህረ ገጽ አንተም የምታወቀውና የምታደንቀው ድህረ ገጽ ( (ቆይ አድሬሱን እዚህ ጋ ልጻፈው... ) http://www.CyberEthiopia.com ዋና አዘጋጅ የሆኑት ንጉሴን እንግዳ አድረው አቅርበዋችው ነበር:: ከቤቱ ርእስ ጋር ስለሚሄድ እቺን ላዋጣ ብዬ ሊንኩን እዚህ አምጥቼዋለሁ::
http://www.archive.org/download/Intervi ... dited1.mp3
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

Postby ሓየት11 » Sun Feb 12, 2012 5:50 pm

ናፖሊዮን ዳኘ wrote: ጎብኚ ለሌለው ሳይተህ ትራፊክ ጃም እያፈላልክ...


:lol: :lol: :lol: :lol:

ይሄ ---- ከሱ ብሶ ደግሞ አፍ የፈታና ያልፈታ ሲል አይገርምም:: ጃም ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንኳን አያውቅም ግማታም :lol: እናንተዬ አፉስ መጠንባቱ :lol: :lol:
Last edited by ሓየት11 on Sun Feb 12, 2012 6:57 pm, edited 1 time in total.
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ክቡራን » Sun Feb 12, 2012 6:12 pm

ምረቱ oops ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈው(ች) ው:

Code: Select all
በርድና ቢጠልጥህ እንጂ ካንተ የሚያስን


ተብታባ!! :o
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7938
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Sun Feb 12, 2012 6:55 pm

ወይ አነ ወይ አነ
በጣም ተሸወድነ
በአማሀርኛ መስሎነ
ብትግርኛ ፃፍነ

""ቢበልጥህ እንጂ"" ተብሎ ይነበብ:: ለሰጡት ሙያዊ ማብራሪያ ያቀንኧለይ ሳልል አላልፍም .... አባጨጓሬ በጢምህ ላይ ይለፍና

ብአማህርኛም በእንግሊዝኛ ቋምቋ ችሎታኦ የሚመካብዎ

ናፖሊዮን oops ምረቱ

ውቃው ፎር ዘ ሜስ አፕ... ቤትህን ያለ እውቀትህ ኮሜርሺያል ሲሰራበት አይቼ ነው:: ክብሮም እና እኔ ጦርነታችንን እዛው ዋርካ ፍቅር እንድንወስድ እጠይቃለሁክቡራን wrote:ምረቱ oops ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈው(ች) ው:

Code: Select all
በርድና ቢጠልጥህ እንጂ ካንተ የሚያስን


ተብታባ!! :o
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

Postby ክቡራን » Sun Feb 12, 2012 7:10 pm

Code: Select all
ክብሮም እና እኔ ጦርነታችንን እዛው ዋርካ ፍቅር እንድንወስድ እጠይቃለሁ


አረ ሰውየው አበደ....ነርቭህን ነካሁት እንዴ..?? :D መቼነው እኔና አንተ ዋርካ ፍቅር ላይ ተወያይተን የምናውቀው ..? ወይ መልቀቅ!! እዛም ሌላ ስም ይኖርህ ይሆናል እንደ ቃልቻ :lol: ማን ያውቃል...እንድ ባንድ አንለቅመዋልን...:: አይዞኝ:: 8)


ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7938
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Sun Feb 12, 2012 8:03 pm

:lol: :lol: :lol: አንተ ሰው ግዴለህም ትልቅ ከሆንክ በኍላ ነው ጨርቆስ የመጣኸው

እሺ በቃ ዋርካ ጄኔራል እንወስደዋለን:: ለኮሜርሻልም ይመችሀል---ኢትዮጵያ ዚስ ዊክ ...

ክብሮምነትሽንም ስለተቀበልሽ ...ሳላመሰግን አላልፍም! በፂምሕ ላይ አይለፍና ዚስ ታይም ...as a credit

ክቡራን wrote:
Code: Select all
ክብሮም እና እኔ ጦርነታችንን እዛው ዋርካ ፍቅር እንድንወስድ እጠይቃለሁ


አረ ሰውየው አበደ....ነርቭህን ነካሁት እንዴ..?? :D መቼነው እኔና አንተ ዋርካ ፍቅር ላይ ተወያይተን የምናውቀው ..? ወይ መልቀቅ!! እዛም ሌላ ስም ይኖርህ ይሆናል እንደ ቃልቻ :lol: ማን ያውቃል...እንድ ባንድ አንለቅመዋልን...:: አይዞኝ:: 8)


ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

Postby ዉቃው » Fri Feb 24, 2012 3:31 am

:oops:
Last edited by ዉቃው on Fri Feb 24, 2012 9:33 am, edited 2 times in total.
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby -...- » Fri Feb 24, 2012 4:34 am

ስማ ውቅቾ ምነው ነገር ጀምረህ ትተዋለህ

ጸሀይነሽን ስጪኝ ብለህ ጠይቀሀት ራሷን ላይ ታች እየነቀነቀች እሺ ብላህ ነበር :: እምሱን አገኘኸውና አስገባህ ወይስ ውጪ ሸናህ ወይስ እስከናአካቴው ሊል ዊሊ ፍርሀት ጨፍድዶት ቀና አልልም አለ ? ጨርሰውማ!
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

Postby ዉቃው » Thu Sep 06, 2012 3:22 am

ጥርግ ጥርግ ....የሸረሪት ድሩን......


ዕድሌ ሆነና ..የሌበር ዴይ ዊኬንዴን ያሳለፍኩት ከማሚ ጋር ነበር :: ሽንቅጥ እንዳለች ናት :: ጤናዋ አሁንም አሪፍ ነው :: ክትፎዋን አዘጋጅታ ይዤ የሚሄደውን ዳቦ ጋግራም ነበር የጠበቀችኝ :: ምስኪን !!! ስታየኝ ደስ አላት ..እኔም ውስጤ ደስ ብሎታል :: ቤቷ ከገባሁ ሰዓት ጀምሮ ትንደፋደፋለች :: ድግሷን አብልታኝ ..ጠግቤ ..እንደገና ብላ ትለኛለች :: አሁን ዕድሜዬም ቋ ስላለ ...መብሰል ብቻም ሳይሆን እርር ብያለሁና ...ብላ ስትለኝ "አሁን በልቼ" እያልኩ አልከራከርም :: ልጇ ነኝና በልቼ የምጠግብ አይመስላትም ..እናም የቻልኩትን ያክል ብበላላት ደስ ይላታልና ..የቻልኩትን አጭቃለሁ :: እናም ጠግቤ ...ሶፋው አልመች ይለኛል ...."ትራስ ላምጣልህ ..ልጄ ?" የተመቸኝ አይመስላትም :: አዎ እላታለሁ ደስ ቢላት :: ትራሱን አምጥታልኝ ...ጋቢ እግርህ ላይ ደርብ ትለኛለች .......እናቴ ..መቶ ዲግሪ ሙቀት አገሩን እያነፈረው ባለ ወቅት ::

አያልቅም ::

ከብዙው መስተንግዶዋ በኋላ ወሬ ተጀመረ :: ጳጳሱና ጠቅላይ ሚ/ሩ ዋና ርዕሷ ነበሩ ::

እንግዲያው ታሪኩን ከኋላ ልጀምረው መሰል ::

እናም ...አባቴ ከሞተ በኋላ ቤታችን ችግር ገባ :: የናቴ ደሞዝ ብቻውን ካባቴ የተቆራረጠ ጡረታ ጋር ልጆች ማሳደጉ ..ተራራ ሆነባት :: [እዚህ መድረክ ላይ ልገልጸው የማልችለው የወዳጅ ዘመድ ተጸእኖ ሳይጨመር] :: የመከራዋን መብዛት ያየ አንድ ሰው.. በዘመኑ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ብርሃኑ ባይህ ጋር ቀጠሮ ይይዝላታል :: እናቴ እኔን ይዛኝ ቢሯቸው ትሄዳለች :: ሚ/ሩ ለኛ ቀና ነበሩ :: ያባቴ መሞትን አለማወቃቸውን ለናቴ ነገሯት ..ነገሩ በአጽንዖት ነበር :: የተበሳጩም ይመስላሉ :: እንዴት አልተነገረኝም ነገር [አሁን በዛ ዘመን ማን እሳቸውን አስቦ ለመንገር ይደፍር ነበር ] ያም ሆነ ይህ ...ሁሉን አዳመጧትና ..የሚችሉት እንደሚያድረጉ ነግረውን ወጣን :: [እኔ የማየው ግን ቀዩን ምንጣፍ ነበር ...እስካሁን አይረሳኝም]

ጓድ ብርሃኑ ያሉት አልቀረም :: ማሚ በ275 ደሞዟ ላይ 75 ተጨምሮ ያንዲት ትንሽ ክፍል ረዳት ተብላ ተሾመች :: ይሁንና ሹመቷ ብዙም
ሳይቆይ ..ብሶት የወለደው ሰራዊት ከተማውን ተቆጻጸረ ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 5 guests