ይፈታልኝ ቅኔው...

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ይፈታልኝ ቅኔው...

Postby ሾተል » Tue May 15, 2007 12:06 pm

አማክሎ ችግሬ ውስጤን ከዘጎነው
አልዘናከት ብሎ መቆሜን ካዛባው
መቻሌን ዘንቆ ትንፋሼን ከበላው
ውጭምድምዱ አጥንቴ እከክ ከፎከተው
የወየበው ደሜ አካሌን ካነባው
ስጋዬም አስታኮ ውስጤን ካበለዘው
ተጠናውቶ ደዌ ቁስሌን ካወበራው

ይጎልማ ኮስሞ መናኛው እኔነቴ
ጎባባው ተስፋዬ ይራቅ ከራቁቴ
ድክሙ ሰላሜ ይሳለቅ በትብቴ

ውስኗ እድሜዬ ቀድማኝ ካረጀችኝ
ህሊናዬ ሰልቶ አልሞ ከሾተለኝ
ጠናናው ልቦናዬ አቁስሎ ካደማኝ
የተጠናበሰው አይኔ አላይልህ ካለኝ
ያቀነነው ልቤ ሌት ተቀን ከወጋኝ
የቀተረው ስጋዬ ግሞ ካስቸገረኝ
አቅለ ገመናዬ ዘጉኖ ከፎከተኝ

እንግዲህ ምን ሰው ነኝ መናወዙ ይቅርብኝ
ንዑሱ አካላቴ ይናጠብ ይረፈኝ
ምንም አይደል ሞቴ ህይወትም ይገልማኝ
የቀብር ውርስ ስርዐት ባጀብ ይከተለኝ
ይሞሽሞሽልኝ ሙሾው ዋይታው ያደንቁረኝ
በዋይዋይ ዳንኪራ ቅኔ ይውረድልኝ
ባልዋልኩበት ሜዳ ገድሌን ያንቡልኝ
በሰጥሥጥ ጽናጽል ዜማ ይጩኽብኝ
የሀጥያቴ ቅርሻ ጋዲው ይፈታልኝ
ቀባሪ በወረብ አልቅሶ ይቅበረኝ
ስሜ ከትውልድ ቀኔ ከላዬ ይጫነኝ
ይጎበብ ድንጋዩ ክታብ ይወቀረኝ
አቅመቢስ ነኝና አፈሩም ይቅለለኝ
ጉድፍ ክርፋቴንም በሂጾብ አጥቦልኝ
ክርስቶስ ሲመጣ ከጎኑ ያቁመኝ....


ሾተል.........ጥልፈተ አማርኛ
Last edited by ሾተል on Tue May 15, 2007 3:02 pm, edited 5 times in total.
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 15, 2007 12:16 pm

...........................................

ድሮ እዚህ ጋ ግጥም ነበር


ሾተል....ሰረዘው
Last edited by ሾተል on Tue Jun 05, 2007 2:49 pm, edited 1 time in total.
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 15, 2007 12:27 pm

...

$$$$$$$$$$$$$$


ዶላር


ሾተል
Last edited by ሾተል on Tue Jun 05, 2007 2:52 pm, edited 1 time in total.
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 15, 2007 12:34 pm

ሁ .....


ሾተል ..........አድማስ ወድያና ወዲህ
Last edited by ሾተል on Tue Jun 05, 2007 2:56 pm, edited 1 time in total.
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ጢኒቲ » Tue May 15, 2007 1:39 pm

ሰላም ሾተል
ግጥምህ እጅግ በጣም መሳጭ ሆኖ እግኝቼዋለሁ::በርታልን
በመሀል ይህችን አስተያየት ስለሰነቀርኩ ይቅርታ ስለተመቸኝ ነውና :idea: :) :)
ጢኒቲ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Wed Apr 18, 2007 10:42 am
Location: Hamus

Postby ሾተል » Tue May 15, 2007 3:09 pm

ጢኒቲ wrote:ሰላም ሾተል
ግጥምህ እጅግ በጣም መሳጭ ሆኖ እግኝቼዋለሁ::በርታልን
በመሀል ይህችን አስተያየት ስለሰነቀርኩ ይቅርታ ስለተመቸኝ ነውና :idea: :) :)ውዱ ጢኒቲ...

እበረታለሁ....ምንቅዋው አስካለኝ ድረስ እውልኛውን ተመስጬ እየተመለከትኩ የስነጽሁፍ ወዠብ እንደገፈተረኝ ተውስጤ እያስዘርበረብኩት እያዳፋሁት እስኪጠንነኝ ድረስ ጠንቡዋ ጠንቡዋ እያደረኩ ኪቦርዴን በጣቶቼ እየተመተምኩ ላስነብብህ እሞክራለሁ::ምንቅዋ እንዳይሸሸኝ ጠልይልኝ__


ሾተል........ድግነ ቃል አጣጪ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 15, 2007 6:01 pm

አመሰግናለሁ ልል አሳንቴ ብልሽ
ማንም አልቻለበት ስምሽን ሊጠራሽ
በህንዲቷ አክተር አሻንቲ አሉሽ

የስምሽ መብዛት ድንግርግር እያለሽ
እዛም ትሄጃለሽ በሥተቱ ስምሽ
አንድ አይደል እንግዲህ መታወቅያ ቁዋንቁዋሽ
ብክን ንድድ አርጊኝ ሂጂላቸው ባሻሽ...


ሾተል........የውሻዬ ስም አሳንቲ እንጂ አሻንቲ አይደለም...እከሳለሁ በዛ ብትጠሩዋት...ዋ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

ሕምምም...

Postby ዋኖስ » Tue May 15, 2007 11:01 pm
ሾተል wrote:
የተሰረሰረው አካሌ ከቶ ቢረብሸኝ
ውስጤ ሰላም አጥቶ ሁሌም ቢያስቸግረኝ
ፍቅር ከኔ ጠፍቶ ጥላቻ ቢወረኝ
ጥንካሬ ደርቆ ድክመት ቢዘንብብኝ
ህልሜ ቅዠት ሆኖ በቁም ቢያባንነኝ
ቀኔ ሌት ሆኖብኝ አልተኛ ቢለኝ
ተስፋዬ ጉም ሆኖ ጠቁሮ ባይታየኝ
እንባ ካይኔ ጥላ እንደፏፏቴ ቢፈሰኝ
ድምጼ ሳይወጣ ከውስጥ ቢጮኽብኝ
ከንግዲህ ምን ሰው ነኝ- ምንስ ተስፋ አለኝ
እፍረት ሰውነቴ ከመቃብር ይገኝ
መሬትዋን ከምከብዳት እሱዋም ከምትጠላኝ
ልሸንቆር ካፈሯ ምስጥም እኔን ይብላኝ .......


ሕምምምም....አንዳንዴ ሰው ከሚፅፈዉና ከሚናገዉ የሰዉዬዉን ምንነትና ማንነት መገመት ይቻላል ሲባል እሰማ ነበር ግና በየትኛው ደረጃ ና በምን ሁናቴ ትገኛለሕ ብሎ በድፍረት መናገር ባይቻልም ከአንዳንድ ሥራዎችሕ ላይ ቀቢፀ-ተሥፋ ይነበባቸዋል! በእንደዚሕ ሁናቴ የሚፃፉ አብዛኞቹ ፅሁፎች ዉስጥን መሳለመሳ የመግለፅ ኃይል አላቸዉ!! ዕውነት ይኆን?


ሾተል....የተስፋ ብርሀን ሲጨልም በቀኑ....
ሁሉን አድርገህልኛልና አመሰግንሀለሁ አምላኬ...
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Re: ሕምምም...

Postby ሾተል » Wed May 16, 2007 4:26 pm

ዋኖስ wrote:ሾተል wrote:
የተሰረሰረው አካሌ ከቶ ቢረብሸኝ
ውስጤ ሰላም አጥቶ ሁሌም ቢያስቸግረኝ
ፍቅር ከኔ ጠፍቶ ጥላቻ ቢወረኝ
ጥንካሬ ደርቆ ድክመት ቢዘንብብኝ
ህልሜ ቅዠት ሆኖ በቁም ቢያባንነኝ
ቀኔ ሌት ሆኖብኝ አልተኛ ቢለኝ
ተስፋዬ ጉም ሆኖ ጠቁሮ ባይታየኝ
እንባ ካይኔ ጥላ እንደፏፏቴ ቢፈሰኝ
ድምጼ ሳይወጣ ከውስጥ ቢጮኽብኝ
ከንግዲህ ምን ሰው ነኝ- ምንስ ተስፋ አለኝ
እፍረት ሰውነቴ ከመቃብር ይገኝ
መሬትዋን ከምከብዳት እሱዋም ከምትጠላኝ
ልሸንቆር ካፈሯ ምስጥም እኔን ይብላኝ .......


ሕምምምም....አንዳንዴ ሰው ከሚፅፈዉና ከሚናገዉ የሰዉዬዉን ምንነትና ማንነት መገመት ይቻላል ሲባል እሰማ ነበር ግና በየትኛው ደረጃ ና በምን ሁናቴ ትገኛለሕ ብሎ በድፍረት መናገር ባይቻልም ከአንዳንድ ሥራዎችሕ ላይ ቀቢፀ-ተሥፋ ይነበባቸዋል! በእንደዚሕ ሁናቴ የሚፃፉ አብዛኞቹ ፅሁፎች ዉስጥን መሳለመሳ የመግለፅ ኃይል አላቸዉ!! ዕውነት ይኆን?


ሾተል....የተስፋ ብርሀን ሲጨልም በቀኑ....
ሁሉን አድርገህልኛልና አመሰግንሀለሁ አምላኬ...
ውዱ ዋኖሳችን....
[color=blue]ሕምምምም....አንዳንዴ ሰው ከሚፅፈዉና ከሚናገዉ የሰዉዬዉን ምንነትና ማንነት መገመት ይቻላል ሲባል እሰማ ነበር.....)
ይህን አባባል እኩሉን አልቀበለውም::ለምን ብትለኝ ሰው ያየውን የሰማውን,በህልሙ የተመለከተውን,የሰውን የታየን ህልም,ያነበበውን ጨማምሮ,የተነበየውን ወዘተም ሊጽፍ ይችላል::ዘንድሮ ምን የማይታይ ነገር አለ ጃል?አንተ ችግር ላይ ሳትሆን እንደዲታ እየኖርክ የተቸገረ ታሪኩን ተርኮልህ ጽሁፍ የመጫር ጅማሬው ኖሮህ እንደሰውየው ስሜት ስሜቱን ተካፍለህ ልትጽፍም ትችላለህ::ዘንድሮ ምን ያልመረረው ዜጋ አለ ብለህ ነው?አንተ ህይወትን እንደአመጣጥዋ ተቀብለሀት ሳለና እየተደሰትክ እየኖርክ ሳለ አንዱ አዲሱ ኑሮን እንደአመጣጥዋ ያልተቀበለ ስለኑሮ ሲማረር ትሰማለህ ከዛ ምሬቱን ትጽፋለህ::ጸሀፊ ማለት እኮ ስለራሱ ብቻ የሚጽፍ ስግብግብ መሆን የለበትም...ስለሌላውም መጻፍ አለበት....እኔ በዛ ነው የማምነው::ባለፈው አንድ ጽሁፍ ስለመንገድ ተዳዳሪዎች ለመጻፍ ብሞክር ያንተን ኑሮ ነው የምትጽፈው ብሎ አንዱ ተረበኝ::ስለወሲብ ስጽፍ እንደዚሁ.....እንግዲህ ስለሴት ልጅም ስጽፍ አንተ ሴት ስለሆንክ ነው ብሎ አንዱ እንዳይከራከረኝ ፈራሁ::

በጽሁፎቼ ሙካሬዎች ውስጥ እኔነቴን የሚገልጹ ነገሮች በጣም ጥቂት ናቸው ወይም ከቶም የሉም::ልክ ኮምፑተር ላይ ቁጭ ስል የሰማሁትን ያየሁትን እጽፋለሁ::እኔን በምናገራቸውና በምጽፋቸው ማግኘት ከቶም አይቻልም::

ዋርካ ላይ ስድብ አስተምረውኝ ስለተሳደብኩ ተሳዳቢ ነህ ብባል መጃጃል ነው::በእውን ሾተል ሰድቦኝ ያውቃል ወይም ሲሳደብ ሰምቻለው የሚል አብሮኝ አንድ ከተማ ውስጥ የሚኖር ሰው ካለ እራሴን ለፍርድ ቅጣት አቀርባለሁ::ስናደድ ወይም ሰው ሲያበሳጨኝ መናገር አልችልበትም...ወድያው ወደድብድብ እቃና ይሆን ይሆን እንጂ.....ክፉ ቃል ከጣቴ የኪቦርድ ትምተማ ይወጣ ይሆናል እንጂ(እሱም ዋርካ ባልጎ ካባለገኝ ጀምሮ ነው)በአፌ ወጥቶም የሚያቅ አይመስለኝም...ድብድብ ያው የአበሻ ደንቡ ስለሆነ በዛ አልታማም::

እስቲ ዋኖስ ቅርቤ ያሉ ሰዎች የምታውቃቸው ካሉ በፕራይቬት ጠይቅና ግምትህን አስተካክል::በቃ ስለራሴ አልናገር::

ለማንኛውም ቸር እያዋለ ያሳድረን::ሠሞኑን ጠላቶቼ ምቀኞቼ ቢጠፉኝ ወደ እየሞከርኩት ወዳለሁበት የግጥም ትምተማዬ ገባሁ....ይመቸን::

ሾተል...........ደስታን አታርቅብኝ/ን..
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed May 16, 2007 4:48 pm

ከልጅነቴ ጀምሮ የፈረንጁን ቁዋንቁዋ ባልቻልኩበት የእክድክ ዘመኔ ማለት ነው ያገራችን ጸሀፊዎች የጻፉትን ከባእድ ቁዋንቁዋ የተረጎሙትን,ጋዜቶችን,መጽሄቶችን እየተከታተልኩ አነብ ነበር.ትምህርቴ እስኪዘነጋኝ ድረስ::..እንዲሁም ስለመጽሀፎች የተሰጡ ክሪቲክሶችንም አነብ ነበር::ለአሁኑ ሙከራዬና በሙከራዬ ሳልገረፍ,ሳልሰደብ,ስትረስ ሳይሰጠኝ ተከብሬ እንድሰራና የላቤን ያለብዙ ድካም እንዳገኝ ለረዳኝና ለዚህ ላበቃኝ ለሀይስኩል አስተማሪያችን ለክቡር አቶ አሳምሬ ሳህሉ ምስጋና ይግባና እንዲሁም ለአገራችን ጸሀፊዎች ክብር ምስጋና ይግባቸውና በነሱም በዝያም በዚህም ስለ ስነጽሁፍ ቁንስል እውቀቴ አንድ መጽሀፍ ክሪቲክ ሲሰጠው ስለመጽሀፉ እንጂ ስለጸሀፊው ባህሪ ሂስ ተሰጥቶ አይቼም ሰምቼም አላውቅም
...)
::የትያትርና የፊልም ዳይሬክተርም ቢሆን ስለዳይሬክተርነቱ እንጂ ስለሰውየው የግል ነገር አልነበረም::ታድያ ዘንድሮ ግራ የገባኝ አንድ ጽሁፍ ተጽፎ ሲገኝ ይበልጥ ዋርካ ውስጥ ጽሁፉን ሳይሆን ሰውየው ላይ ግምገማው ሲጡዋጡዋፍ ይታያል::ምን አልባት ይሄ ዘመን ከዱሮው ቀድሞ ወይም ከገሀዱ አለም ተስፈንጥሮ ቀድሞ ከሆነ አላውቅምና የምታውቁ አስረዱኝና አፌን ከማሞጠሙጥ እርፍ ብዬ ልሰተር ያለዛማ ስነጽሁፋችን ያድጋል የሚለው ትንበያዬ ፍሬ ከርስኪ ሆኖ እንዳላገኘው ፈራሁ::

ምናለ ጸሀፊውን ከፈራነው ወይም ከጠላነው ከሱ ስራ ባንሳተፍ ወይም መገምገም ካለብን ስለገሀዱ ስራው ብንገመግም መማርና መማማር እንፈጥርና ለአገራችን ጥሩ ጸሀፊ ልናፈራና የድሮዎቹን እነዶክተር ሀዲስን,,,እነበአሉ ግርማን...እነ ብርሀኑ ዘሪሁንን ወዘተ ልንተካቸው እንችላለንና የግል ግለሰብ ወቀሳችንን አቁመን ስለሚጻፉ ጽሁፎች የምንችለውን ያወቅነውን ግምገማ እያደረግን እንደኔ ያሉ አዲስ ሞካሪዎችን ስህተታቸውን እያሳየን እያስተማርን ለጸሀፊነት እናብቃቸው እላለሁ::ይህ የዜግነት ግዴታችንም ነው ብዬ አምናለሁ::

የረሳሁት......የመረረ ጥላቻና ፍርሀት ሲኖረን እኛ አበሾች ስለሰው እንዴት ክርቲክ እንደምናረግ የታወቀ ነው::ምንም ያ ሰውዬ የአለም ሁሉ ጥሩ ነገር ቢሰራም ስለማንወደው ወይም ስለምንመቀኘው ስንወርድበትና ወስደን ከአመድ ውስጥ ስናንደባልለው እንገኛለን ነገር ግን የሰው ኮሾ ነገር ግን በባዶነቱ ቀድሞ እራሱን አስከብሮ ባዶነቱን በሀብቱ ሆነ በሆነ ነገር ሸፍኖ ተኮፍሶ እየተገኘ ሳለ የሆነ ነገር ከሱ ስለምንፈልግ ምንገድ ላይ አራም ቀዘነም የሱ አርና ቅዘን አይገማን...የማያስቀው ጨዋታው ሲያስፈነድቀን ይውላል:.ባልዋለበት ግዳይ እንጥልለትና ገድሉን ስንተርክለት እንውላለን::አይ አበሻነት...መርዞች ለሆድ አደሮች እኮ ነን...መጥኔ ለኛ...መጥኔ ለወለደችን...

በነገሬ ላይ ማንም ሰው ጽሁፌን የመገምገም ስልጣን አለው::ጽሁፌን እንደፈለጋችሁ አብጠልጥሉት ጉድፍ ካገኛችሁበት....አድናቆት ምኔም አይደል ለምን ቢባል የምጽፈው ያየሁትን የስሜቴን እንጂ ሜዳል ላገኝበት ወይም ቺክ ልጠብስበት ወይም ገንዘብ ላፍስበት አይደለም::ያለዛ ደግሞ ጊዜ ባገኘው ቁጥር ያለኝን የማካፍላችሁን ጽሁፌን የምትወዱ ካላችሁ በዝምታ ያለክፍያ ኮምኩሙ.........ኑሮዬ ስለሚበቃኝ ሌላ የምስጋና ኑሮ አልፈልግም::በገሀዱ አለም ያለኝ የስራ ሀላፊነት በገሀዱ አለም ካሉ ሰዎች የሚቸረኝ አድናቆትና እድል አያንስብኝም::ስለዚህ እኔን ለቀቅ ነገር ግን ጽሁፌን ገምገም እላለሁ::

ፍቅርና ማስተዋልን በመሀላችን ያምጣ::

ሾተል.....ውዳሴ ከንቱን የሚጠላ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri May 18, 2007 9:40 am

አደፌም አይምጣ በኼደብኝ ይቅር
እውነት ከወለደው አርግዤ እንድቀር
በድባብ የምሄድ ዘረ ወላድ ነኝ
ወተቴም ማይነጥፍ አምላክ ያደለኝ

እክሉን በቤቴ ስደትም ላኩኝ
ምርር ብሎ አልቅሶ ሁሉም ረገመኝ
ምን አጠፋሁ እኔ ምጬ በወለድኩኝ
የራሱ ወንድም ነው ሚያሰቃይብኝ
የሱህመም ተሰምቶኝ ሳነባ አለሁኝ....

ሾተል......በዚህ ግጥም ነገር ደግሞ ሴት ተብዬ እንዳልፈረጅ ፈራሁ.....ድንቄም....አሽሙዋጠትኩ....
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed May 23, 2007 3:57 pm

ቭላድሚር ፑቲን እዚህ ቪየና ናቸው
እኔም ባይኔ በብረቱ ዛሬ አየሁዋቸው
አቤት ኑሮ ነው የሚባለው የሳቸው?
እንዲህ በሰው አንዳች መታጀባቸው
በአገር ፖሊሶች መጠበቃቸው
መቼም አያኩም ቂጣቸውን-
በሰው ፊት ድንገት ቢያሳክካቸው
የጋዜጤኛ ካሜራ ስለሚቀጭማቸው
ሚስታቸው አርጀት ቢሉም እንዲህ ተመኘሁላቸው
ከባላቸው ይበልጥ ብዬ ባረካቸው
ኬጂቢ እየላኩ ሰው ማስገደላቸው
ለምን ፑቲን ስራ በጣም ስለሚበዛባቸው
ለሚስታቸው ጊዜ ስለሌላቸው
ቸው ቸው ቸውውውውውውው..ሾተል... ፑቲንን ለማየት ጥዋት ወጥቶ ምህረት በሌለው ጸሀይ ሲወቃ ውሎ መልኩን ያጠቆረው ወረኛ የራሱ ጋዜጠኛ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue Jun 19, 2007 6:26 pm

ውስነ ጉዞዬን ጸሀይ መርቶት
ከዳመና አርቆ አቀጣጥሎት
እፎይ ላልል ትንፋሽ ነስቶኝ
ሙቀት በውስጠ-እላዬ አላልቦኝ
ልቦናዬን አሰልሎት ወበቁ
ከውርጅብኝ ንፋስ እኔነቴን ማዳረቁ
ያም አልበቃ ብሎ እርቆኝ መንገዴ
ጨርቅ አልሆን ብሎ ሲያስኬደኝ በዳዴ
ዝም ብየ አየሁት የሆነው ይሁን ብዬ
ህልመ ድራሽዬን ከቃጠሎው ከልዬ
ጉዞዬ ተገባዶ ቀን ያልፋል ብዬ....ሾተል........ቀለበት መንገድ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue Jun 19, 2007 6:36 pm

ላይ ተገትሬ በመስታወት ህልሜን
ተሳስቼ ይሆን እንጃ አየሁት አራሴን
የምኮራበት ወንዳወንድ ጠይምነቴን
በፍቅር መርዝ ነድፌ ስንቱዋን የምጥልበትን
ፍቅር አንጠልጥዬ እያሳየሁ ማርኬ ምቀምሳትን
ልሆናት ቃል ገብቼ እንደገፍ የማፍሳትን
ከመብላቴ በሁዋላ በቃሌ የማልገኝበትን
ህልሜን ከልቶ አሳየኝ ይሄን መልኬን......


ሾተል.....ቃል ቅድም ነበር ግን ስግብግብነት አሸነፈው
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue Jun 19, 2007 6:42 pm

መንገዳገዴን አይተህ ላታቆመኝ
ልጋፈጥህ ስዘጋጅ ላትቁዋቁዋመኝ
ከቶ ትግሌን ካልቻልክ አትሞክረኝ
ፊሽካ ነፍተህ ስጀምር ቆመህ ላታስጨርሰኝ
አርፌ ልተንፍስ ትግልን አታስጀምረኝ
ካፌ እስከገደፌ በደንብ ስለታጠቅኩኝ
የታጠኩት ትጥቀት ስለሚከላከልልኝ....


ሾተል......አትድረስ ካልቻልክ መቆየቱን
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests