ይፈታልኝ ቅኔው...

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Thu Apr 24, 2008 10:37 pm

ከሰው ተቀላቅለህ -ከሰው ሽል መሆንህ
በፍጡር ዋሻ ውስጥ - ከሰው በማደርህ
በረቂቁ ስራው-ከፈጣሪ ፍጥረትህ
መፈጠር ሲገባህ -አለመፈጠርህ
ማን ስልጣን ነበረው- ለሞት ሚወስንህ
ከደም ነበርክና -በደም አፈሰሱህ
አለም ሳያሳዩህ -ወንጀል ፈጸሙብህ
ኑሮን እንዳትቀምሳት -ከውሀው አስቀሩህ
እራብ እንዳትማር -ባጭሩ ወሰኑህ
ጥም እንዳያነድህ ገለው ተበቀሉህ
ፍርግጥግጥ እንዳትል -በጃቸው ታጠቡህ
የልጅ ወግ እንዳታይ -በጨርቁ ጨመቁህ
አድገህ እንዳትስቅ -በጉዋንት ጎረጎሩህ
ጎልምሰህ እንዳትረብሽ -ከሆድ ውስጥ አሟሙህ
አግብተህ እንዳትወልድ- መወለድን ገቱህ
ሰርተህ እንዳታልብ -ከጭንጋፍ መደቡህ
ሸብተህ እንዳትመልጥ -መግደል ተማሩብህ
ይብላኝ ለገደሉህ -አንተስ ትጸድቃለህ
ለነሱ ሲኦል ነው -ገነት ትወርሳለህ
ጋነም ሲቃጠሉ -በጥርስ ትስቃለህ
ዘላለምን ሲሞቱ- ሁሌም ትኖራለህ.....

ሾተል...................አጨናገፈነ...በደም ታጠበነ.....ሲኦል ጠበቀነ....ከሳት ሊያኖረነ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Apr 24, 2008 10:50 pm

እረ ጉልበተኛዋ ፓስፖርቴ
የት ተደበቅሽብኝ በሞቴ
ኩኩሉ ነው ጨዋታሽ ?
አልነጋም ገና ማለትሽ ?
ወይስ የምን ድብብቆሽ
ሰላሜን አጥቼ ስፈልግሽ
ካንዱ ስርቻ ተደብቀሽ
በነፍሴ አንዳች ተጫወትሽ
ምን ልታገኚ ብስተጓጎል
ስራ እንጀራዬ ቢሰናከል
ልጅነቱ ይቅር በይ ውጪ
እኔን በማዳን ሳትቆጪ
እኔም ኑሮዬን ልግፋበት
አገር ላገር ዞሬ ልደሰት
በቃሽ ተከሰች ፓስፖርትዬ
አንቺ የኔ ፈቃድ አለኝታዬ
ሰላሙን አግኝቼም ልደር
ከፍለጋዬ መርበትበት ስካር
በይ አብረን እንሄዳለን
ብርር ብለን ከሰማዩ ሆነን
ምድርን ወደታች እያየን
ወደክሮሺያ እያቀናን
በይ ውጪ ተገኚ
በደስታዬ ሳታዝኚ.......

ሾተል...ዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑ...
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat May 24, 2008 1:50 am

ህሊናችሁ ቆስሎ?
ወይስ አርጅቶ ዝሎ
ምን ሆነባችሁ
እንዲህ እስኪያስገምታችሁ
በማዳላት ርብራብ ሸክም
ባንድ ጎናችሁ አዘንብላችሁ ማዝገም
ፋሽን አድርጋችሁታል
ላለመነካት ተማምላችሗል
በስህተታችሁ ልትገዙ
በመድረኩ ሁሉ ስታዙ
አይሆንም የሚል መጣና
ለእውነት ኑሩ ከማለቱ ገና
ተብረክርካችሁ ጠፋችሁ
ላለተስፋ ተካተታችሁ
አንድያውም ጎን መጥቶ ይወቅሳል
አልገባው ብሎም ሚጠይቅም ታይቷል
አቤት ማፈር መታፈር
ከእውነት ርቆ ለማደር
መማሰን እንደዚህ ለውሎ?
ለውዳሴ ከንቱ ታጅሎ

ሾተል.....ምጽ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed Jul 09, 2008 8:17 am

--------------------------------------------------------------------------------

ችሎትን ጎስሜ
አግስቼ ታድሜ
ለበቅኩት ውሎዬን
ናፍቆት ትዝታዬን
ያገሬ ርቀቱን
የሀሳብ መስመሬን
በባዳው ውሎዬን
ተስፋ ያሳጣኝን
መተርኩ እያንዳንዱዋን ....

ሾተል .......ከኖዬዶርፍል
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed Jul 09, 2008 8:17 am

ውስጥዋ በክፍለት ተቡዋቅሶ -
አይኑዋ በእምባዋ ሲርስ
ሀዘኑዋ ሰፍቶ በዝቶ -
እንባዋ ደም ሆኖ ሲለቀስ
አለሁልሽ ሚላት ጠፋ -
ፍላጎቱ ለሆዱ ቀድሞ
ስቃዩዋን ወዲያ ከልቶ -
ጥጋቡን በቁንጣን አስታሞ
በሌላው ላይ ሲረማመድ -
ዘላለም ሚኖር መስሎት
ሲያካብት ግብስብሱን -
አቆልሎ አብሮት ላይሞት
እሱዋን በስቃይ አመሳት -
ፍሬዋን አደራርቆ
ግፍና እርዛት ዘርቶ -
እየኖረ አየነው ስቆ ....

ሾተል ---ከከኖዬ ዶርፍልሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሌባ » Thu Jul 10, 2008 12:06 am

ምነው ሾተል? አሁን ይህን ሁሉ ዝባዝንኬ ግጥም ብለህ እየጠራህ ነው ሌሎችን ማረምና መፎተት የገባኸው?ይህንን ሁሉ ገጽ የለቀለቅኸውን ሁላ ከአንታራም ግጥምነት ምን እንደሚለየው ታውቃለህ? -ሳድሳዊ የቤት መድፊያ ዜማው ብቻ ነው::እስቲ ለመሆኑ ግጥም ማለት ምንድነው ነው የምትለው?
ግን አንተ እንዲህ አደረገህ ተሳሳትህ መባልን ስለማትወድ ይህንንም አርሞ ለመገኘት ፈጽሞ አትሞክረውም::ስለዚህ እንደመሰለህ ተረዳው::
የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንን ኦቴሎ የአማርኛ ትርጉም አንብበኸው ታውቃለህ ለመሆኑ? ከፈለግኸው በግል ጻፍልኝ::እንድታገኘው አደርጋለሁ::

ከዚያ ውጭ ግን በጣም ያስገረመኝ ነገር ይህ ነው::ቆይ ቆይ ይህ ሰው ሰልማ 1 የሚሉት አልነበረም እንዴ!?
ሰልማ1 wrote:ሾትል
ከእርካታሽ ምኞትሽ ተገናኘሽ -
በዑኡታ ሲቃ እያነባሽ
ተከቶብሽ በነጻነት -
ላማሰለሽ አመስግነሽ

ገጣሚ, ደራሲ, ሀያሲ ሾትል እኔ መቸም ያንተን ያህል ባላቅም እንዲህ እንዳንተ በሳድስ ማለትም በሽ, ስ, ር, ት, የሚገጥሙ ገጣሚወች በጣም ቀሽሞች ናቸው ይባላል እንዴት ትላለህ ?

ለምሳሌ እኔ እንኴን ቀሽሙ እንዲህ ብየ ልገጥምብህ እችላለሁ በሳድስ :lol: :lol:

አይ ሾትል
የሆንክ ግመል
የኦስትሪያ ወደል

አክየን የምትመስል
አንተንስ ነበር መግደል :lol: :lol:

ቀን ቆጥሮ "የኋለኛው እንዳይሸሽ የቀድሞ ወዳጁን በሻሽ መቅበሩ" ኖሯል!!!???

ኣድነን የሚያስብል ነው!
ሌባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Thu Mar 16, 2006 5:12 pm
Location: midre beda

Postby ሾተል » Thu Jul 10, 2008 8:45 am

ሌባ wrote:ምነው ሾተል? አሁን ይህን ሁሉ ዝባዝንኬ ግጥም ብለህ እየጠራህ ነው ሌሎችን ማረምና መፎተት የገባኸው?ይህንን ሁሉ ገጽ የለቀለቅኸውን ሁላ ከአንታራም ግጥምነት ምን እንደሚለየው ታውቃለህ? -ሳድሳዊ የቤት መድፊያ ዜማው ብቻ ነው::እስቲ ለመሆኑ ግጥም ማለት ምንድነው ነው የምትለው?
ግን አንተ እንዲህ አደረገህ ተሳሳትህ መባልን ስለማትወድ ይህንንም አርሞ ለመገኘት ፈጽሞ አትሞክረውም::ስለዚህ እንደመሰለህ ተረዳው::
የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንን ኦቴሎ የአማርኛ ትርጉም አንብበኸው ታውቃለህ ለመሆኑ? ከፈለግኸው በግል ጻፍልኝ::እንድታገኘው አደርጋለሁ::

ከዚያ ውጭ ግን በጣም ያስገረመኝ ነገር ይህ ነው::ቆይ ቆይ ይህ ሰው ሰልማ 1 የሚሉት አልነበረም እንዴ!?
ሰልማ1 wrote:ሾትል

ኣድነን የሚያስብል ነው!

ጥሩ ገመገምከኝ እንድልና እርማቴን እንዳስተካክል የሰውን ስራ አጣቅሰኽ ሳይሆን የራስህን ስራዎች ከጭንቅላትህ አውጥተኽ አጣቅሰህ ጻፍና ጥሩ ገምጋሚ ነህ ወይም ጸሀፊ ነህ ብዬ ካንተ እማራለሁ::ስለ ጸጋዬማ ጸጋዬ እራሱ ነው የጻፈው::ጸጋዬ ኦቴሎን ተረጎመው ያልከው የጸጋዬ ስራ ሳይሆን ኦቴሎ የሼክሲፒር ነውና ያንን እንደማጣቀሻ አልቀበለውም::ጸጋዬ እራሱ ከጭንቅላቱ የጻፈው ስንት ነገር እያለ የሰውን ስራ ተረጎመ ብለኽ እንደምሳሌ ታቀርብልኛለህ?የተነሳኸው ለግምገማ ሳይሆን እንዴው ነገር መፈለግ ስለፈለክ ስለሆነና የምትናገረው ስለተምታታብህ ደደብነትህን ልቀበለው ችያለሁ::ደደብነትህን እንዳወቀ አድርጌ እንድቀበለው በዚሁ ኒክህ አንድ የራስህን ስራ አቅርብልኝ....

ካለዛ እኔም ቅኔዬን እጽፋለሁ....አንተም አይገባህም...ከዛ እንደዚህ እያልን እንኖራለን::መጻፍ እችላለሁ....እጽፋለሁ....ውስጥህ ተቀብሎኛል...ውጭኽም ይቀበለኛልና አይዞን እንደዛ እያልን እንኖራለን::
ለመሆኑ እስቲ ለግምገማ ከመጣህ የጻፍኩትን እየተነተንክ እዚህ ጋ አንታራም ነው...እዛጋ ተጨመላልቆዋል...እዚህ ጋ ተዳክሞዋል ብለኽ ጎልጉለኽ አሳየኝ...በደፈናው ጥላቻህን ለማሳየት ብለኽ እራስህን አታስገምት::

ከደደቦች ጋ አሁንም ክብርነቴ ለካስ እየኖረ ነው ጃል..

በል ስራ አለብኝና ወደስራዬ ልሂድ::

ሾተል...........ጸሀፊው....ገምጋሚው.....ተልታዩ----ከኒውዶርፍል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu Jul 10, 2008 8:46 am

ሌባ
እንዳልገመገመኝ

ምነው ሾተል? አሁን ይህን ሁሉ ዝባዝንኬ ግጥም ብለህ እየጠራህ ነው ሌሎችን ማረምና መፎተት የገባኸው?ይህንን ሁሉ ገጽ የለቀለቅኸውን ሁላ ከአንታራም ግጥምነት ምን እንደሚለየው ታውቃለህ? -ሳድሳዊ የቤት መድፊያ ዜማው ብቻ ነው::እስቲ ለመሆኑ ግጥም ማለት ምንድነው ነው የምትለው?
ግን አንተ እንዲህ አደረገህ ተሳሳትህ መባልን ስለማትወድ ይህንንም አርሞ ለመገኘት ፈጽሞ አትሞክረውም::ስለዚህ እንደመሰለህ ተረዳው::
የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንን ኦቴሎ የአማርኛ ትርጉም አንብበኸው ታውቃለህ ለመሆኑ? ከፈለግኸው በግል ጻፍልኝ::እንድታገኘው አደርጋለሁ::

ከዚያ ውጭ ግን በጣም ያስገረመኝ ነገር ይህ ነው::ቆይ ቆይ ይህ ሰው ሰልማ 1 የሚሉት አልነበረም እንዴ!?

ኣድነን የሚያስብል ነው![/quote]
ሌባ

ጥሩ ገመገምከኝ እንድልና እርማቴን እንዳስተካክል የሰውን ስራ አጣቅሰኽ ሳይሆን የራስህን ስራዎች ከጭንቅላትህ አውጥተኽ አጣቅሰህ ጻፍና ጥሩ ገምጋሚ ነህ ወይም ጸሀፊ ነህ ብዬ ካንተ እማራለሁ::ስለ ጸጋዬማ ጸጋዬ እራሱ ነው የጻፈው::ጸጋዬ ኦቴሎን ተረጎመው ያልከው የጸጋዬ ስራ ሳይሆን ኦቴሎ የሼክሲፒር ነውና ያንን እንደማጣቀሻ አልቀበለውም::ጸጋዬ እራሱ ከጭንቅላቱ የጻፈው ስንት ነገር እያለ የሰውን ስራ ተረጎመ ብለኽ እንደምሳሌ ታቀርብልኛለህ?የተነሳኸው ለግምገማ ሳይሆን እንዴው ነገር መፈለግ ስለፈለክ ስለሆነና የምትናገረው ስለተምታታብህ ደደብነትህን ልቀበለው ችያለሁ::ደደብነትህን እንዳወቀ አድርጌ እንድቀበለው በዚሁ ኒክህ አንድ የራስህን ስራ አቅርብልኝ....

ካለዛ እኔም ቅኔዬን እጽፋለሁ....አንተም አይገባህም...ከዛ እንደዚህ እያልን እንኖራለን::መጻፍ እችላለሁ....እጽፋለሁ....ውስጥህ ተቀብሎኛል...ውጭኽም ይቀበለኛልና አይዞን እንደዛ እያልን እንኖራለን::
ለመሆኑ እስቲ ለግምገማ ከመጣህ የጻፍኩትን እየተነተንክ እዚህ ጋ አንታራም ነው...እዛጋ ተጨመላልቆዋል...እዚህ ጋ ተዳክሞዋል ብለኽ ጎልጉለኽ አሳየኝ...በደፈናው ጥላቻህን ለማሳየት ብለኽ እራስህን አታስገምት::

ከደደቦች ጋ አሁንም ክብርነቴ ለካስ እየኖረ ነው ጃል..

በል ስራ አለብኝና ወደስራዬ ልሂድ::

ሾተል...........ጸሀፊው....ገምጋሚው.....ተልታዩ----ከኒውዶርፍል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሌባ » Thu Jul 10, 2008 10:53 am

እንዲህ እንኳን ይሻላል::-መቸም ያለማነወር መልስ ያንተ ተፈጥሮ ባይመስልም-atleast እንድንተራረም ተስማምተሀል::
እንግዲህ ልገምግምህ ማለት ነው....

ሾተል wrote:--------------------------------------------------------------------------------

ችሎትን ጎስሜ
አግስቼ ታድሜ
ለበቅኩት ውሎዬን
ናፍቆት ትዝታዬን
ያገሬ ርቀቱን
የሀሳብ መስመሬን
በባዳው ውሎዬን
ተስፋ ያሳጣኝን
መተርኩ እያንዳንዱዋን ....

ሾተል

_________________

ችሎትን ጎስሜ....(?)
ጎሰመ:- መታ: ደበደበ: ደለቀ:: ወይም ጀርባውን ውጋት ሰፍቶ የያዘውን ሰው ጀርባ በሀይል ተጫነ: አንቋቋ::...
-እንግዲህ ይህ ባንተ አባባል ምን ትርጉም እንዲሰጥ ፈልገህ ነው ማለት ነው?

አግስቼ ታድሜ....(?)
ደልቶኝ ሞልቶልኝ ፎክሬ ታደምኩ እንደማለት ነው?
ከሆነ የመጀመሪያው ስንኝና ይህ የቀጠለው የትርጉም ተንሰላሳይነትን ተጣማጅነትን አያሳዩም::ያን የመሰለ ስነግጥማዊ ህብር መፍጠር ከተፈለገ እንደኔ አስተሳሰብ የቃላት ምጣኔውና አቀራረቡ መሻሻልን ይፈልጋሉ::

...ለበቅሁት ውሎዬን...(?)
-ለበቀ(መለበቅ): መታ: ሾጥ አደረገ: ሸነቆጠ:: ወይም ጎበሰ: ጎሸ: ታወከ ልቡን ጓገጠው: ቋቅ አለው: ልቡን ለበቀው: ጎሰመው::....
-እና እዚህ ጋር የተጠራው ውሎ- የተገረፈው? ልቡን የለበቀው?...?...?
ምን ስሜት እንዲሰጥ ተፈልጓል?

ያገሬ ርቀቱን
...የሀሳብ መስመሬን
በባዳው ውሎዬን
ተስፋ ያሳጣኝን
መተርኩ እያንዳንዱዋን...
እኒህ ተከታይ ሀረጎች(ወይም ግማሽ ስንኞች) የሚያትቱት ላንባቢ የተሻለ አስደማሚ ስሜት ቢያቀብሉም ሆኖም በውስጣቸው ታጭቋል የሚባል ስነ ግጥማዊ ክረትና ሀይል የላቸውም::
ግጥም ሀይሉ ውስን ቃላትን ተላብሶ ተአማኒና ስሜትን ኮርኳሪነቱ ነው::
ስለዚህ በድጋሚ በእኔ አስተያየትና ግምገማ የመስጠት ከሆነ ቦታ በተደነገገልኝ ባለመብትነት መሰረት እነኚን እንደወረዱ የተደረደሩ የግጥም አካላት አንታራማዊና መደበኛ በሆነ የግጥም አቀራረብ እንደሚከተለው ተመራምሬባቸዋለሁ::
--------------------------------
በችሎቱ ጎስሜ
በታደምኩበት አግስቼ
ባደራሁት-በውሎዬ
ተፋለምኩት ትዝታዬን::
ትዝታዬን ተፋጠምኩት-
...ያንን ጠላት አሸማቂ
ልቤን ባዘን
አይኔን በእንባ አጣማቂ...(ላልቶ ይነበብ!)
በሀሳቤ መስመሩን ሰርቶ
መትሮና ዘረጋግቶ....
እንደውሀው ቦዩን ቀድዶ
-በባዳው ቀን ውሎ አዳሬ-
የሰላም መጋኛየን
የተስፋዬን ቀበኛ
አሽቆልቁሎ እያሳየኝ..
የሁዋሊዮሽ
የጥንትዮሽ.....
ግን እጄን አልሰጠሁትም!
እንቢዮ!!

---------------
ወደድከው?
እንዳላበለሻሸሁብህ ተስፋ አደርጋለሁ::
ጋሼ ፀግሽን በማንሳቴ የራሴን ስራ ለምሳሌ ለማቅረብ አቅም እንደሌለኝ አይነት አድርገህ ስለወሰድክብኝ ደብሮኛል::ሆኖም ግን አንድ ቀን የሞካከርኩዋትን ግጥም ብትወድልኝም ባትወድልኝም ጽፌያታለሁ::....

/ርዕስ የለሽ/
------------

የማይገባኝ ነገር ቀኖቼን የሞላ
ለጠላም አንቡላ? ለጠጅም አተላ!?
ብርጭቆው ተቀዶ እንጨት ከተሰፋ
ሸማም ተሰባብሮ ቂጣም ከተደፋ...
እግዚዮ አይሻልም ወይ ቢለማም ቢከፋ!?

በሰላም ዋል::
ሌባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Thu Mar 16, 2006 5:12 pm
Location: midre beda

Postby ሾተል » Thu Jul 10, 2008 11:42 am

ሌባ...
ምነው መጀመርያ እንደዚህ በጀንትል ብትመጣ ኖሮ....በለፈለፉ በዘለፉ ክብርን አጡ ሆነ እኮ..

እና እስቲ እኔ ልል የፈለግኩትን አንዱን ትርጉም ልንገርህ...
መጀመርያ ባንተ አባባል እስማማለሁ....ባንተ አይን ስላየኸው ልክ ነህ...

የእኔን ሀሳብ ደግሞ እይልኝና እንማማር...

ችሎት...ችሎታ በእኔ ውስጥ ተደለቀ....መቻል...ተግስት በእኔ ውስጥ ጮቤ ረገጠ

አግስቶ ታደመ ስል...የሚያገሳ ነገር ሲስማማ ነው::ወደህም ተመገብከው በግድ ተጋትከው ሰውነትህ ከተስማማው ያገሳሀል....ታድያ ተግስቴ ወይም መቻሌ በእኔ ውስጥ ተመችቶት ተስማምቶት አገሳ...

ታደመ ስል ተኮፈሰ...ቦታውን ያዘ...

ካገሳኝ በሁዋላ ውሎዬ ለበቀ...አስታወከ...ወይም ቀርሽቶ ወጣ...ያ ደግሞ ናፍቆት ነው ያቀረሸኝ...የሚያቀረሽ ወይም የሚስታወክ ነገር ሳይስማማ ሲቀር ነው...ናፍቆት በእኔ ውስጥ አልተስማማኝም ነበርና ውስጤን ሳይስማማው ቀርቶ ወጥቶ ታየ...ታወቀ...ውስጤ ሊደብቀው አብላልቶ ሰውነት ሊሆነኝ አልተቻለውምና....ስለዚህ የጉዋጎጤኝም ትዝታ ጭምር ነው...

ያገሬ እርቀት በሀሳብ መስመሬ ሰመርኩት...

በባዳ ውስጥ ያለሁት...የዋልኩት ከአገሬ የሀሳብ እርቀት መስመር ጋር ሳስበው ተስፋ የሚያሳጣ ነው....ታድያ ያንን ሁሉ መተርኩት....ለካሁት....ያ ደግሞ ተስፋ አስቆረጠኝ....እንደማይሆን ስላወቅኩ ማለት ነው....

ያልገባህን ጠይቀኝ...

በነገራችን ላይ የመለስኩልህ መልስ እንዳመጣጥህ እንጂ ከራሴ ፈልስሜ አይደለምና ምን እንደጻፍክ ቀድመህ እየው::

ሾተል....ለመማማር ዝግጁ...
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሌባ » Mon Jul 14, 2008 10:51 pm

ሾተል ገጥሞት እንደነበረው...

መንገዳገዴን አይተህ ላታቆመኝ
ልጋፈጥህ ስዘጋጅ ላትቁዋቁዋመኝ
ከቶ ትግሌን ካልቻልክ አትሞክረኝ
ፊሽካ ነፍተህ ስጀምር ቆመህ ላታስጨርሰኝ
አርፌ ልተንፍስ ትግልን አታስጀምረኝ
ካፌ እስከገደፌ በደንብ ስለታጠቅኩኝ
የታጠኩት ትጥቀት ስለሚከላከልልኝ ....

ይህ ደግሞ ወደመጀመሪያዎቹ ገፃት አካባቢ ያገኘሁት ሲሆን እንደስነ ግጥም ወይስ እንደስድ ጽሁፍ ቢነበብ እንደሚሻል ብዙ ደቂቃዎች አሳሰበኝ::አንተ አንድ ሀሳቡን እንደመጣለት ዘርግፎ እንደምጥ መገላገልን የሚወድ አይነት ሰው ነህ ብዬ አምኛለሁ::ወይም መፀዳጃ ቤት ያማጣውን ቁርጠት ፍልጠት ምንም ዳግሚያ እንዳያሳስበው ጥያፌውን ተጎፍንኖ ያደረገውን አድርጎ የራሱን ውጤት ትንፍጋት እንዳያለብቀው እግሬ አውጪኝ ብሎ እንደሚጠፋ አይነት::
አሁን የተሻለ ስነ ግጥማዊ ማሰብ ና መተለም ትችል ይሆናል-ይህን ከጻፍክበት ጊዜ ይልቅ::ምክንያቱም አንተ ራስሁ እኒያን ከላይ ተንዘላዝለውና ተዘለው በዘፈቀደ የተደረደሩ ሀረገ ሀረጋትና ስንኛት ብትፈትሻቸው ልታስተላልፍ የፈለግኸውን ሀሳብ በሳድስኛ ቤት አስደፋሀቸው እንጂ ምንም አይነት አንኩዋራዊነትና ብስለት አላከልክባቸውም::ይህን የምልህ መገማገምን እንደምትወድና አንተም ለመገምገም እንደምትስምማ ባሳወቅኸኝ መሰረት ነው::
በፊተኛው ግምገማዬ በቃላትና በሀረጋት ከፋፍዬና ነጣጥዬ ፍተሻ እንዳደረግሁት ይህኛውን ስራህን ለማበጠር በብላሽ ጊዜን ከማባከን በቀር ጥቅሙ ስላልታየኝ በጥቅሉ የሚከተለውን ላሳስብህ ፈቀድሁ::
ለማንኛውም አይነት የፈጠራ ውጤት ተመስጦና አርምሞ የተላበሰ አዲስ ምልከታን ፈላጊና ጠቁዋሚነት እጅግ እጅግ ወሳኝ ነገር ነው::አንዳንዶችን ከታሪክ አንባ ተመልሰን ብንጎበኝ ስንትና ስንት አይነት የጊዜ የፍላጎት የትእግስትና በፀናኢነት የጥበብ ግዴታን ውዴታናን በታማኝነት የመወጣት ነገር ማስተዋል እንችላለን::
ይህ ሁሉ የምታውቀው ነገር ስለመሆኑ ጥርጥር አላበዛም::ስለዚህ እባክህ ነገሮቹን ሁሉ በማስተዋል. በማብሰልሰል በሚዛናዊነትና በብስለት መጀመሪያ ለራስህ ቀጥሎም ለተደራሲዎችህ ለማሳየት ሞክር::

ቀጣይዋን አጭር ግጥም የምጽፍልህ አንተም እንዲሁ የኔ የምለውን ያጻጻፍ ዘይቤ እስከመገምገምና አስተያትህን እስከመስጠት እንዲቻልህ በሚል ነው::
-------------------------------------------------

ኑሮህ ንግድ ሳለ ትርፍን ካላመጣ
ፍቅርህን አትክሰረው እምነትም አትጣ
የተስፋን ወይን ጠጅ ድፈርና ጠጣ
ሁሉም ሀላፊ ነው ከራስህ ከወጣ!
--------------------------------------
ቀጥለን እስከምንገናኝ!
ሌባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Thu Mar 16, 2006 5:12 pm
Location: midre beda

Postby ሾተል » Mon Jul 14, 2008 11:54 pm

ሌባ የተጀመረን ነገር ሳይጨርስ ወደሌላ ቦታ የሚሄድ ሰው ያናድደኛልና የጀመርነውን በጠለቀ ሁኔታ ተማምረን እንጨርስና ወደሁለተኛ ምርመራ እንሄዳለን:.ግምገማ ጀመርከኝ መለስኩልህ ከዛ ለዛ መልስ እፈልጋለሁ....ከዛ ወደሌላው እንሄዳለን....

ምለው ገብቶሀል አይደል...ቻሌንጅ መደራረግ ደስ ይለኛል....ለመለስኩት ግምገማ እፈልጋለሁ...ከዛ መልስ ካለኝ እመልስልሀለሁ...ከዛ መልስልኝ...ያንን ስንጨርስ ወደሌላ እንሄዳለንና የጀመርነውን እንጨርስ....

ደግሞ መልስ የሚያዘገይ ያናድደኛል...ገምጋሚ እስከሆንክ ድረስ መልስ ማማጥ አያስፈልግህም....የሚገመግምና የሚጽፍ ጭንቅላት ለምንም ጊዜ ዝግጁ መሆን አለበት....ካልኩለስ ወይም ስለሪላቲቪቲ ፕሮብሌም ሶልቭ ማድረግ አይደለም የያዝነው...ጥበብ ነው...ጥበብ ደግሞ በማንኛውም ጊዜ ችሎታ አለኝ የሚል ያቅሙን ይጠበባል...

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሌባ » Tue Jul 15, 2008 1:57 pm

Yeah man shottel!

ላቀረብኩልህ የመጀመሪያው ግምገማዬ በመለስክልኝ ክፍል መነሻ አካባቢ ላይ ነገሩን እኔ ባየሁት መልኩ "ትክክል መሆኔን" አስምረህበት ነበር::ከዚያ አንተ የመሰለህን ትንታኔ አስከትለሀል::ነገሩኮ መማማርና መተራምረም እንጂ እራስን ማዳኛ ምክንያት ሲያስሱ መዋል አይደለም::የትንታኔህ መሰረቱ የቃላት ትርጉማቸውን መሰደሩ ሲሆን የግምገማዬ ኢላማው ደግሞ እንዲህ በትርጉማቸው የምትረዳቸውን ቃላት ያላግባቡና ያለውበት ደርድረሀቸዋል የሚል ነበር::
ስለዚህ በዚያ የግጥም ስራህ ላይ ያደረግነው ውይይት ብዙም አልፎ ሊያስኬደን እንዳይችል ተሰምቶኝ ነው ወደሌላው ስራህ ያነጣጠርኩት::
ላንተ ተስማሚ መልስ ለመስጠት ተጨንቄና ተጠብቤ አልነበረም ለውስን አፍታ ድምጼን ያጠፋሁት::ጊዜ አጥሮኝ ሁኖ እንጂ::ደግሞስ ማን ጊዜ ያላጠረው አለ!?አንተም ብትሆን ኮ እንደበፊቱ በፎረሙ መግቢያ ላይ በተደረደሩ ርዕሶች ፊት ስምህን አዥጎድጉዶ ማሳየት ተወት አድርገሀል::ይገባኛል ብዙ ነገሮች ባንዴ ለማድረግ የምትጥር ባተሌ ሰው እንደሆንህ::ፅናቱን ይስጥህ!
በዚህ መሰረት ለምን ስለመጀመሪያው ግምገማዬ ይህን አይነት መደምደሚያ ላይ እንደደረስኩ ከተረዳኸኝ ቀጥዬ ስላቀረብኩት ደግሞ የምትለኝን ለማንበብ ጠብቃለሁ::
ሌባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Thu Mar 16, 2006 5:12 pm
Location: midre beda

Postby ሾተል » Tue Jul 15, 2008 3:12 pm

ሌባ እንደጻፈ

ሰላም ሌባው..
በትንሹ ተረድቼሀለሁ:.ግን አሁንም የመጀመርያው ግምገማ ላይ ብዙ የሚያስኬዱ ነገሮች አሉ:.የግድ ቆረቆረኝ ከተባለ አካላዊ ቁሩቁዋሮ ብቻ መሆን የለበትም...ቲንከር ከሆንን ውስጣዊ አስተሳሰባዊ ዉሩቁዋሬ ወይም ጉርባጦ ሊሆን ይችላል:.ቃላቶችን ያላግባብ ነው የተጠቀምካቸው ብለኸኛል...እኔ ደግሞ ባግባብ ነው ብየ ለዛ መልስ ሰጥቻለሁ....እና ባንተ አይን ያየኸውን ባንተ አይን ትክክል ነኽ ብዬሀለሁ አይካድም....ታድያ እነ አንተን ስለማልሆንና ያንተና የእኔ አይን የላይ ሆነ ጠልቆ የማየት እይታችን አንድ ስላልሆነ የእነን እይታና ቃላቶቹ አግባብ ባላቸው ቦታ ላይ መቀመጣቸውን ወይም መጠቀሜን ጠቅሼ አብራርቼ ጽፌልሀለሁ:.እና ያ ባንተ አይን እኔ ያየሁት እይታ ያስኬዳል ወይስ አያስኬድም ነው...አያስኬድም ካልከኝ በምን መንገድ ንገረኝና ከዛ እነ ደግሞ ወይ ያስኬዳል እልሀለሁ ወይም አያስኬድም ልክ ነህ ተሳስቻለሁ እልሀለሁ::አሁን የተግባባን መሰለኝ:.ስለዚህ ያላለቀ ቢዝነስ ስለጀመርን ያንን አብጠርጥረን አይተን እንጨርሰውና ወደሁለተኛው ጨዋታችን እንሂድ::ያለዛ አንልፋ::ጠንቆል አድርጎ ወደሌላ መሄድ ጥሩ አይደለም::አፈር ከድሜ አብልቶ ማሸት ነው ወይም እንደቆዳ ማልፋት ተገቢ ነው::ከእኛ መማር የሚችሉ ወይም የሚሳተፉ ሰዎች አይጠፉምና እኔ ላላለቀም ብያለሁ አንተ አልቆዋል ስትል አመልክተኝ::ወይም የእነን ያይን ያስተሳሰብ እይታ ተረዳልኝ::አንተ እስክታሳምነኝ ድረስ የጻፍኩት ግጥምና የተጠቀምኩባቸው ቃላቶች አግባብ ባለው ቦታ ላይ ነው እያልኩ እራሴን ኮፍሼ እከራከራለሁ::ስህተቴን ካልነገርከኝና ባንተ አይን ብቻ ካየኸው ነገሮች እንዴት ሊፈቱ ይችላሉ?እንማማር...

ሾተል........መልስ እጠብቃለሁ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሌባ » Tue Jul 15, 2008 11:14 pm

ጀምሮ የማይቀጥል ሰው ጥሎብህ አትወድ ይሆናል እንጂ የጀመረከውን ሁሉ አንተው ራስህ እንደማትጨርስ ብዙዎች እንደሚመሰክሩ እርግጠኛ ነኝ::አብጠርጥሮ መገማገም እሰየው የሚባል የትህትና ጥበብ ነው::ስለዚህ በደስታ እንቀጥላለን::
በተለይ ስህተትህን አምነህ መቀበል ከቻልክ! አንተ ግን ያመጣህብኝ ፈሊጥ "ስትገመግመኝ በራስህ አስተያይ ሁኔታና በተረዳኸው መልኩ ነው" ምናምን የሚል ነው::እኔ በምንም ልረዳው በምንም ትኩረት ሰጥቼ የሞገትኩህ ወይ የገመገምኩህ ቃላቶችን ያላግባባቸው ቅደም ተከተላቸውና
ትርጉም አሰጣጣቸው አዛብተህ እንዳቀረብክ ነው::ያንን ደግሞ ልትቀበል የፈለግህ አትመስልም::
ለምሳሌ
ችሎት...ችሎታ...በእኔ ውስጥ ተደለቀ...መቻል...ትግስት በእኔ ውስጥ ጮቤ ረገጠ...
የሚል የማብራሪያ ነገር አስፍረሀል::ማለትህ ችሎት የችሎታ ተዋራሽ ዝርው ቃል ነው?ሁለቱ በትርጉም አንድ አቅጣጫ ያላቸው ናቸው ነው የምትለው?የምንነጋገረው ስለአማርኛ ከሆነ ማንም ተነስቶ ምስክርነቱን መስጠት ይችላል-ችሎትና ችሎታ የሚተካኩ ቃላት እንዳልሆኑ::
ችሎታ በውስጥህ ተደለቀ:- ተነረተ?ተመታ?ተደበደበ? ልትል ያሰብከው ችሎታ በውስጤ አደላ ተበራታ ተንሰራራ ከሆነ ተደለቀን በግድ መለወጥ ያስፈልጋል::....
እያልን እያልን ብዙ ብዙ ልናወጋ ይቻለናል ወንድም ሾተል::ግምገማችን ምሁራዊም ይሁን ዘልማዳዊ የምንግባባበት ቋንቋ አማርኛ እስከሆነ ድረስ ስሩን የለቀቀና መስመር የሌለው አጠቃቀም በጣም አሳፋሪና አስገማች እንደሆነ ግልፅ ሊሆን ይገባል::

አይደለም ነው!?
ሌባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Thu Mar 16, 2006 5:12 pm
Location: midre beda

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests