መፀሔተ-ዋርካ___________________________::

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የወይዘሮ አዜብ ሕልም

Postby ዋኖስ » Mon Aug 13, 2007 10:25 pm

የወይዘሮ አዜብ ሕልም! ተፃፈ በኩማ


ኩማ wrote:የመንግስተ ሰማያት ስዓቶች
የመሪያችን ባለቤት ወይዘሮ አዜብ አያድርግባቸውና በህልማቸው ሞተው መንግስተ ሰማያት ሲገቡ ያያሉ ። እንደገቡም ቅዱስ ጴጥሮስ በክብር ይቀበላቸውና መንግስተሰማያትን እያዟዟረ ያስጎበኛቸዋል። ታዲያ በጉብኝታቸውም ወቅት እጅግ በጣም በርካታ የግድግዳ ሰአት በየቦታውና በየግድግዳው ተሰቅሎ በማየታቸው ይገረሙና ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲህ ሲሉ ይጠይቁታል።

"ለመሆኑ ይሄ ሁሉ ሰአት ምን ያደርጋል ብላችሁ ነው? "

ቅዱስ ጴጥሮስም "ይሄ እያንዳንዱ ሰአት በምድር የሚገኘውን እያንዳንዱን ሰው የሚወክል ነው ። ጥቅሙም ውሸትን ለመቆጣጠር ነው። " ብሎ ይመልሳል

ወይዘሮ አዜብም ደንገጥ ብለው "እንዴት ነው ውሸትን በሰአት የምትቆጣጠሩት? " ብለው ይጠይቃሉ።

ቅዱስ ጴጥሮስም ሲመልስ "በምድር የሚገኝው እያንዳንዱ ሰው አንዴ በዋሸ ቁጥር ሰአቱ አንድ ዙር ይዞራል ደግሞም ሲዋሽ እንደዛው ይቀጥላል "። በማለት ከገለጸላቸው በኋላ፤ ለምሳሌ ይልና ግርግዳው ላይ ካሉት አንዱን የማይነቃነቅ ሰአት እያመለከተ "ይህ ሰአት የማዘር ትሬዛ ሰአት ነው። ማዘር ትሬዛ በህይወት ዘመኗ ዋሽታ ስለማታውቅ ሰአቱ አንዴም ዞሮ አያቅም። " በማለት ሲገልጽላት

ወይዘሮ አዜብ በአንደኛው ግድግዳ ላይ ያሉትን ሳይቆሙ የሚሽከረከሩ ሰአቶች አይታ "እነኝህስ የውሸታም ሰዎች መሆናቸው ነው? " ብላ ትጠይቃለች

ቅ _ጴጥሮስም "አዎ በዚህ መደዳ ያሉት በሙሉ የፖለቲካ ሰዎች ሰአት ናቸው። ለምሳሌ ይሄ የክሊንተን ፥ ይሄ የጎርቫቾቭ፥ ይሄ የብሌር፥ " እያለ ያሳያት ጀመር።

ወይዘሮ አዜብ የባለቤቷም ሰአት እዚሁ አካባቢ እንደሆነ በመገመት ለማየት ጓጉታ "የኔስ ባለቤት ሰአት የቱ ነው "ብላ ትጠይቃለች።

ቅዱስ ጴጥሮስም ሲመልስ "ያንቺ ባለቤት ሰአት አፕስቴር ጌታ ቢሮ ውስጥ እንደ አየር ማቀዝቀዣ (fan ) እየተጠቀመበት ነው" ብሏት እርፍ። የባለቤትዋ ሰአት እንደ ፋን ሲሽከረከር ታይትዋት ነው መሰለኝ ወይዘሮ አዜብም በድንገት ጉብኝትዋን አቋርጣ ከእንቅልፏምኘ ባና ከኤዶም ገነት የከነፈች አራት ኪሎው ገነት ቤተመንግስት ከች አለች እላችኋለሁ።

ክፉ እልም በሉ

ምንጭ: http://www.quatero.net/keld/yeazebhilm1.htm

አንድነት ኃይል ነው!
ኩማ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

ቅቅቅ

Postby ዋኖስ » Mon Aug 13, 2007 10:46 pm

ቅቅቅቅ ሳሚኃብ ዕንደፃፈዉ! ቅቅ

እኒደው ማን ነው ዬጣፈው ብሌሽ እንዳትጥይ እኔ ተጎረቤት ነው ማሪያምን ነው እምልሽ
በቄዴም ሌታ ከታስኪ ሲቲወሪጂ አይቼሽ አይኔ ኢንዴ ሰፈሩ አቦራ ኔው ቡን ያሌው
ቤቃ ዲሮ እኛ ቤት ቴስቂላ የነቤሬቺውን ማሪያሚን ነው ያስታወስኩኝ ሊክ ቁሪጥ ኢስዋን
ሊክ ሳይሽ እንደ መቢራቱ ሌቲሪክ ጌቢቶ ሰውነቴን አንቀጠቀጠኝ እንዴ እች ልጅ
አስማተኛ ኔች ወይ እስኪል ዲረስ ነው የሆኒኩት መብራት ተቃጢሎ እቤት ሲቀጥል
የቄመስኩት ሌትሪክ ኢንኮን እንዲህ አላንቀጠቄጤኝ ግን ሚገሪሚሽ እኔን ያንቀጤቀጤኝ
አንቺኝ ደጊሞ እንደ ሲጋቤት መቢራት ነው ያቤራሽ ከታሲኪ ወሪደሽ ባጠገቤ
እስክታሊፊ ዲረስ ቤቃ እዛ ፒያሳ ኢንዳለው ሀዊልት ነው የቆሚኩት አይኔ አንቺን አዪቶ
እንዴዛ ሲንቀጤቀጥ ባጠገቤ ስታሊፊ ሽቶሽ ኢንደ ማሲቲካ አጣቢቆኝ ሄደ
ኢንደ ታቦት ማሪያም ሊሳለምሽ ቃጣኝ ሊቤ ደግሞ ኬቦታው ሼርቴት ብሎ አልደፊር አለኝ

ወዩ ኢች አገር ብዬ ገርሞኝ በቆሙኩበት ስዞር ሌካስ ካጠገቤ ቢዙ ሪቄሻል
ኢንዴው እግርዋ ኢንደ ጊመል ያኪል ተመቼው ኢዛ ደረሰች ብዬ ሊሮጥ ሲሞክር
ኢግሬ እንደ ዲንጋይ ከቤደኝ አልራሜድ አልሮጥ አሌኝ ደጊሜ ኢንደጌና እቺ ልጅ አሲማተኛ ነች
ብዬ ጮክ ብዬ ሲናገር አንድ ሴቲቱ ሴሚቶኝ ማን ነቺ አስማቴኛ አንቴ ብሎ ጤየቁኝ
ጤፋች ቴሰወረች አልኩዋቼው ኢስዋ ናቲ አፊህን እንዲህ ኬፊታው የሄዴቺው ሲሉኝ
ሚን ድነው ሚሉት ኢማማ ሲላቸው አፊህ እኮ ሀኪም የኬፈተው ይመስል ነቤር አሉኝ
ኢንጃ ኢማማ ሀኪሜ ነሺ መድሀኒቴ ያሌው ዘፋኙ ለሶ ይሆናል ሲላቸው ኢንጃሊህ
የዜንድሮ ዘፈኝ በሊቶ ስቂ ሲለው ሲቅ አለኝ ቢሎ ይዘፊናል የድሮ ሴው ግን
ውሀ ይጤጣበታል ልጄ ቢለው ጢለውኝ ሄዱ ተጪንቂላቴ ወጥቶ የነቤረው ደሜ ተመሊሶ
ሴውነቴ መንቀሣቄስ ሲጄሚር ሚንድነው ያሌሚኩት ብዬ ኢራሴን ሳትኩኝ ደጊሞ ፊጥነቱ
ተታስኪ ወሪደሽ ባጤጌቤ አሊፊሽ ታይኔ እስተምትሠወሪ ዴኪካም አሊሞላሺም መሲ
ቢታይሽ ኖሮ ነይ ተኔጋ ሩጪ ኔቤር የሚቲሊሽ እኔ ጊን አንቺን ታየሁሽ ጀሚሮ
ጢዋት ወጣች ማታ ጌባች ማሌት ነው ሲራዬ ሲሚሽ አላቄውም በሲም እንዳልጠራሽ
ኢንዳላናጊሪሽ ሚላሴ ኢንቢ አሌ ሚን ብዬ ኢንደሚናገር ከሚን ኢንደሚጄሚር ጤፋቢኝ
እዚህ ሲናገሩ ስምቼ ወረቀት መጣፍ ሲሉ ሰምቼ ነው ሚጺፈው ያለሁት እና
ኢባክሽ ኢባኪሽ የኔ መቤት ሲታነቢው አሊጌባ ካሌሽ ደቢዳቤውን ይዜሺው ጋብርኤል ነይ
ማታ እዚ ሊሳለም ሲሌሚሄድ ቁጭ ቢለን አቢሬን ኢናነበዋለን መልስ ከጻፍሽ ሜሊሼ ኢጽፊልሻለሁ

ማርያም ቲጠብቂሽ

ቶሎሳ ነው ጎረቤት

ከፍቅር መወዳደሪያ አምድ የተገኘ በሳሚሀብ!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Tue Aug 14, 2007 11:05 pm

ከባሕልና ስነፅሑፍ የተገኘ

አንዱ ወደ መጠጥ ቤት ይገባና አንድ አይነት መጠጥ በሶስት የተለያዩ ብርጭቆዎች እያዘዘ ይኮመኩማል - ሁሌ ::

አስተናጋጁ የሰውየው ሁኔታ ግራ ቢገባው 'ወንድም አንዱን ብርጭቆ ገልብጠህ ስትጨርስ በላዩ ላይ ብጨምርልህ አይሻልም ..ሶስት ብርጭቆ ምን ይሰራልሀል ?'

ሰውየው 'አየህ :- አንዱ ብርጭቆ የኔ ድርሻ ሲሆን ሁለቱ ብርጭቆዎች ግን አሁን አጠገቤ የሌሉ የሁለት ጉዋደኞቼ ድርሻ ነው :: ለነሱ ማስታወሻ ነው የምጠጣው ' ይለዋል ::

አንድ ቀን ያልተለምደ ነገር ሰውየው ፈጸመ - ሁለት ብርጭቆ ብቻ አዘዘ :: አስተናጋጁ በሀዘን 'ምነው አንዱ ጉዋደኛህ ሞተ እንዴ ?' ቢለው ... ሰውየው 'የለም :- የሞተ የለም :: እኔ መጠጥ ስላቆምኩ የራሴን ድርሻ መቀነሴ ነው '

ተፃፈ በ ዩፎ
ደሴምበር 22 2005


____________________________________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby በጎሲያ » Wed Aug 15, 2007 3:53 pm

ዋርካፍቀር ውስጥ እንዚ አይንት ምርጥ ጽዉፍ አይቼ አላውቅም ...ለዚ ነው እዚ መጸሄት ውስጥ መስፈር አለባት ብዬ ያመጣዋት
ከዋናው ድንቅና ምርጥ ጽሁፎች መካከል
********************************************************************************
ደግሞ ለመቀበጣጠር ማን ብሎኝ ቅቅቅቅ

በቀደም የልጅ አለማየሁ ቴውድሮስን መቃብር ልጎበኝ ካሜራዬን አንግቼ ስሄድ ነው ::

መቃብሩ ውስጥ ገብቼ ባይተዋር ሆኖ ኖሮ ባይተዋር ሆኖ የሞተዉን የልጅ አሌክስ መቃብርጋ በትዝታ የሠጠምኩኝ ይመስለኛል ....ከመቃብሩ ድንጋይ ስር አንዲት የእድሜ ባለፀጋ ጉንዳን እድሜ የሸረሸረው ግንባሯን እያሻሸች መጥታ አበሻ ነህ ? አለችኝ ...''ምነው አልመስልም ?'' አልኳት ፈገግ ብላ ሲጋራ ጠየቀችኝ እንዳቆምኩኝ ስነግራት በስጨት ብላ የአሌክስ መቃር ላይ ብነፃነት ፈልሰስ ብላ ቁጭ አለች
''...ከአለማየሁ ጋር የተሰደድኩኝ ነኝ ብዙ ነበርን ጓደኞቼ ሁሉ አልቀዋሉ አሁን አንድ የአየሪሽ ልጅ አግብቼ ከርሱ ጋር ነው ምኖረው ...'' አለችኝ በሀዘን እያየች
ከአለማየሁ መቃብር የርሷ ታሪክ እንደሳበኝ ሁሉ
''ልጆች አሉሽ ?'' አልኳት

''አምስት ወልጄ ሶስቱ ሞቱብኝ በተለይ አንዱ እንዴት ያለ ቆንጣጭ መሰለህ ''ብላኝ እምባዋ በመንታ ሆኖ ደረቷ ላይ ሲረግፍ በስድስት እግሮቿ ይሁን እጆቿ ብቻ እየቧጠጠች አደራረቀችና

''...እስቲ ተወው ...ይልቅ አክሱም ሲመለስ እኛም ከአለማየሁ ቀብር ጋር እንመለሳለን ብለን አስበን ነበር ...ከአክሱም ጋር የተሰደዱት የትግራይ ነቀዞች ላገራቸው ሲያበቃቸው እንዴት ቀናው መሠለህ ...''

''መመለስ ትፈልጊያለሽ ?'' አልኳት አንድ ፊቱን እንደኮሶ ግምዝዝ ያደረገ ሸረሪት ለስለላ በሚመስል እይታ መጥቶ ገልመጥ አደረገን

''ተወው ባክህ ይሄ ባንዳ ነው የካረቢያን ባሮች ተገዝተው ሲመጡ አብሮ የመጣ የጃማይካ ሸረሪት ነው አንዷን ልጄን ወዶ መከራዉን እያየ ነው '' አልችና ወደጥያቂየ ተመለሰች
''ለሚለኒየም ብገባ ደስ ይለኝ ነበር ግን ባይተዋሩን ትቼ አጥንቱ እሾህ ሆኖ ይወጋኛል ምንም ቢሆንኮ የመይሣው ልጅ ነው ''
አልችና ቀለሙ ደብዛዝ የከንፈር ቀለም የተቀባ ከናፍርቷን ወደ አለማየሁ መቃብር ጠቆመችኝ

''...ባለፈው ብሪቲሽ ሙዚየም ሄጄ ገዳማቸዉን ታጭቀው የመጡበት የኢቲዮጲያ ብራናዎች ውስጥ ያደረጉትን ባሕታዊያን ምስጦች አግኝቼ ነበር ከፊሎቹ አርጅተዋሉ ከፊሎቹ ግን አሁንም ወጣት ናቸው አንደኛው ምን እንዳለኝ ታውቃለህ ....? ያገሬ ህዝብ ሁሉ ሲሰደድ ምነው አግሩም እግር አብቅሎ ወድዚ ቢመጣና ጦቢያዬን ባየዋት አለኝ ቅቅቅ '' ሳቀች ለካ የጉንዳን ሳቅ እንደልብስ ዚፕ ጥዝዝዝዝዝ ነው ሚለው

የ ሾካክ ጃማይካዊው ሸረሪት ከአንድ የቬንዙዋላዊ ቀንዳውጣና ከአንዲት የታይላንዳዊ ሽርሙጥሙጥ ያለች ፌንጣ ጋር ሆነው መጡ ልብ ብዬ ሳይ ማውቃቸው ይመስለኛል ምናልባት ሳልወለድ በፊት ተዋውቄያቸዉም ይሆናል 'ኮ የኔ ነገር እረሳለው ..አረጀው መሠለኝ (አባባ ተስፋዬን ሆኜ የለ ቅቅቅ )
.
.
.
ይቀጥላል

ውናዋ <== ______________________________
_________________

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ በጣም ትገርማላቹ እንዴት አድርጎ ነው መቀበጣጠር ሚቀጥለው

ሌላ ቅብጥርጥሮሽ ሲኖረኝ ደግሞ በሌላ ቅብጥርና ብቅ ልበልንጂ ...ምናልባት በእኛ ==> ጷጕሜ 13 ቅቅቅ
ይመቻችሁ ::

ከክቡር ደራሲ ባለቅኔ ገጣሚ ሰሀሊ ፎቶግራፈር ጸሀፊተውኔት ዋናው

****************************************************************
ጎሲያ ነኝ
በጎሲያ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 93
Joined: Mon Dec 29, 2003 8:48 pm

Postby ዋናው » Wed Aug 15, 2007 11:09 pm

በጎሲያ wrote:

ከክቡር ደራሲ ባለቅኔ ገጣሚ ሰሀሊ ፎቶግራፈር ጸሀፊተውኔት ዋናውጎሲያችን ቅቅቅቅቅ ይሄን ሁሉ ሹመት እንደ መንጌ አሸክመህኝ አይከብደኝም?

ምስጋናዬ በርክቶ እንዳለ ሆኖ


____________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed Aug 15, 2007 11:35 pm

እቺ ፖስት የቻት ሩም አብሮ-አቃዳጆችን(ጓደኞቻችንን) ስለምታስታውስ ነው እዚች መፅሔታችን ውስጥ የዶልኳት::

በኤሊው ቤት የዱድን ቡና ከገንዬ ጋር ቁጭ ብለን ስንጠብቅ ከጭንቅላቴ ላወጣውና እንዳልተሰማው ልረሳው የወሰንኩበት ናፍቆት 'ናላዬን ' ያዞረው ጀመር

ቅቅቅ ወይ ጉድ ! 'ያላዩት አገር አይናፍቅም ' የሚሉት አባባል ምን ያህል እውነት ነው ?
አገርን በሰው ብመስለውና ያላዩት ሰውም አይናፍቅም ብዬ ከራሴ ብታገል - ይህ ሀሳቤ በአሸናፊነት የሚወጣ አይመስለኝም :;
ምንም እንኳን ለሁላችሁም ያለኝን ያገር ልጅ ፍቅር ለማሳየት ብዙም ያልጣርኩ ቢሆንም በጣም የምወዳችሁ ያገሬ ልጆች የዋርካ ቻት 'ፍሬንዶቼ ' በሚረባውም በማይረባው ያስቀየምኳችሁና የተዘጋጋን ወገኖቼ ፍጹም ከልብ የሆነው የናፍቆት ሰላምታዬ ይድረሳችሁ ::

ኤሊው እንዳልኩህ ስቅታው መቼም አይለቅህም - ሁሌም የምትታሰብ ነህና :: ለሚጻፍልህም አጸፋዊ መልስህ ፍጥነቱ ልክ ለፍቅር እንደተደረገው ቢሆን ደስታውን አንችለውም :
(ለሞኒክም መልስህ እንደዛው ፈጣን መሆኑን አስተውያለሁ )
የየትኛው እንደሚበልጥ ግን አሁን ትንሽ ግራ እየገባኝ መጣ :: ፍቅር ወይስ ሞኒክ ---አቦ ግራ አታጋቡና :

ሄለንዬ የኔ ጭምት -- ብዙም አልል ዋው ነው ስላንቺ :
ገንዬ ስዊት --- ሳሚሀብ በዚህ ስምህ ብቅ በላ --ሆፕ ካለሽበት ሰላምታዬ ይድረስሽ
ጣዕሙ የቅርቡ ሩቅ -ዋኖስ ፈላስፋው ከነቱቱህ -- ንዴቭ የአባዲሩ -- ቢዲ የመጀመርያዋ ፍቅሬ (ቅቅቅቅ የዛሬን አያድርገውና ) ዱድም ከጀለብኝ አንቺን -- ጉዱ ካሳም ---ዘውዲቱ ባለብዙ ሚስጥር --ዘመድኩን አረ ስም ይለወጥ -----አስራርርርር ረዥሙ ----ሌዲ 1 የጥንቷ ---እቴኑ ብሩክ ሌላ ዱድ ሌላ --- መልካሟ አትታዪም ---ምርቄው አጎቴ ---"ጎርጀስ " ሞኒክዬ --- ሬች እህታችን ---ደግነት ወንድማችን --- ሊዲሻ በረሮ --- ጫልቱ --- ሜሪ ሜሪ ሜሪ ---አረሩ ዋኖስ ያቆላምጥህ ----ጅንኑ (ቀብራራው )---እንድርያስ ጫካው --- ጎርጎራ ---ኩኩሻ 007 የተሰወርሽብን --- እንጎችዬ , መንዝነት እናንተማ -- የድሮዋ ጉብል --- ፌጦ ? --- ወርቅዬ ሞልቶ አፌቶ , ሚዲስፒያቼ --ዲመንቲካቶ ሊንጓ ኢታሊያና --- ፓንሪዝኮ የቼካችን አድባር - ሳምሶን 13 --የብርዱ አለቃ እንደልቡ የራሺያው --- ሌሎቻችሁም
ወንዶቹ --ትከሻ ለትከሻ
ሴቶች እህቶቼም ባብዛኛው ጉንጫችሁን አንዳንዶቻችሁንም ካልሰሰታችሁ ከንፈራችሁን ---እምምምምምምምምምምምጷ
ያለኝ ፍቅር በቅደም ተከተሉ አይወሰንም --ለሁላችሁም እኩል ነው ::
አንድ ቀን እንገናኝ ይሆናል በቻት አድባራችን

ተፃፈ በbrookk
ዲሴምበር 13 2005


________________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu Aug 16, 2007 9:00 pm

ትህትና 2 ባንድ ወቅት የነበሯትን ፅሑፎች ሠብስባ ስትወስዳቸው ....አምልጣት የቀረቻት ፅሁፍ ነች እቺ ::
ይሄ የትህትና ነገር , "እድሜ በኢቨንት ሲለካ " ያለችው ኮንሴፕት ደግሞ ሶስተኛውን አስጀምሮኛል ::
ህይወት እንዴት ግሩም ነው ! አንዳንድ ሰዎች ያሉት እውነትም ለሌላው ነው !


አልኩ እንዴ እንደዛ ? ግን እውነት 'እድሜ ' የሚባለው እንዴት ነው ? አንዱ ኤክሰንትሪክ ፈላስፋ "ግዜ /Time ወደኍላ እንደማይሄድ ምን ማረጋገጫ አለ ? ጊዜ ወደፊት ሄዶ ሳይሆን past ያለፈው ራሱን ወደ ፕሬዘንት ቀይሮስ ከሆነ ???ለምን የተሰበረ ብርጭቆ መልሶ ራሱን አይሰበስብም ??" ብሎ ጠየቀ . እኔኮ እንደው እነዚህ eccentric beings ነብሴን ሲያለመልሙት . አቤት ያ የማያቁት " Innocent ጉራቸው " ሲያማልል ሆድ ሲያሳምም . Ach, It hurts .እውነቱን እኮ ነው . አመጸኛ አይምሮው ካልገባው ምን ያርግ !
ግን እኔ "እድሜን " እንዴት ተርጉሜው ነው በኢቬንት ሲለካ ያልኩት ......ህምምምምም . ምሁሩም አልገባው እኮ . ዴም . ለካ ደሞ ስለማላቀው ነገር ሳወራ 'የመጀመሪያ ' ግዜ አይደለም .
ከሰማይ በታች ከምድር በላይ ከህጻናት እና ከ eccentric ምሁሮች የበለጠ የሚወደድ ምን አለ ?
..................................................................................................
አንዲት ብሎንድ ነጭ ወጣት ልጅ 'ይቅርታ ...እንትና ." እያለች ወደኔ በሩጫ እርምጃ ትመጣለች .
"ይቅርታ ስልኬ ክሬዲቱ ትንሽ ስለሆነ ለደይቃ ባንቺ ስልክ ልጠቀም ?"
"ስልክ አልያዝኩም . ግን እዛ ጋር በገንዘብ መደወያ ቤት አለለሽ "
"አይ ሳንቲም የለኝም "
እኔ ጋር ያለውን ሳንቲም ሰጠኍት . ሳንቲሙን እያቀበልኩ በሆዴ ያስብኩት ነገር ቢኖር ...."ስለኔ ደግ የሚናገር ወንድ መቼም አይኖርም .እስቲ አንቺ "ናይስ " ሆነችልኝ " በይ
....................................................................................................
.....አንዱ የእሲያ ባሪያ በመኪና እኔ በግሬ በጎኔ እያለፈ ለተናገረው አረፍተነገር (ሴክሹዋል ኮሜንት ) ስድብ ለመመለስ አቅሙ አጠረኝ . ደከምኩ . ያዳም ዘሮች አደከሙኝ . ከወንድ ለሚመጣ ጥቃት ሁሉ ያረጀሁ መስሎኝ ነበር . ጸጥ ብዬ 'ተሰድቤ (በኔ አስተሳሰብ ስድብ ነው )" መጣሁ . ኮምፕሊመንት አያረኩላት ነው ይል ይሆናል እኮ . የወንድ አይምሮ .....
"ከጥቁር (እሲያዎችን ጨምሮ ) ወንድና እና ከሞሮኮ ሴት በላይ ማን ደፋር አለ እዚህ ምድር ላይ ?"
ተፃፈ በትህትና 2
ሜይ 09 2006


_______________________________________________________::
_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

እዚሕ ጋ ባዳብለዉስ

Postby ዋኖስ » Fri Aug 17, 2007 12:33 am

ይችንም ብታነቧት ሳትጠቅም አትቀርም!

http://mahder.com/doc/ethiopian_writers.pdf
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Fri Aug 17, 2007 10:37 pm

እስቲ አዲሳባዎቹ ስለባሕር ማዶዎቹ አበሾች ምን እንደሚሉ በናፍቆት ብሕር እንቃኝ


እሺ .......... ባለውጭ አገሮች ! እንዴት ከረማችሁ ? ፎቆቹ ደህና ናቸው ?

የሰሞኑን ደሞ እስቲ ልቀባጥርላችሁ ... አንዷ ባለፈው ከናንተ ወደዚህ የመጣች አለች (move አደረገች ነው መሰለኝ የምትሉት እናንተ ) - እና አሁን በቅርቡ መኪናዋ ገባችላት ... እና የመኪናዋን መምጣት ምክንያት በማድረግ መሰለኝ barbeque አዘጋጅታ ጠራችን : (አሪፍ ጋርደን አላቸው ) እና ስንጋበዝ መጠጥ ራሳችሁ እየያዛችሁ ኑ ተባልን እና ይዘን ሄድን እንዳቅማችን : (የራሳችንን መጠጥ ይዘን ሄደን መጋበዝ እንግዲህ ከፈረንጅ አገር የመጣልን ስልጣኔ መሆኑ ነው መሰለኝ እና ከተለያዩ አገሮች የመጡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ባጋጣሚ ነበሩ :: ወንዶቹ .. ይሄ ባለሎቲውም ባለሹሩባውም ባለጨበሬውም ምናምኑም ... አንዳንዶቹ ከዛ የመጡት ዝብርቅርቃቸው ወጥቷል :: ለሴት ምን እንደሚወራ ሁሉ የጠፋበት አለ :: አንዱ impress ሊያደርግ ይመጣና ባልሆነ ወሬ ቁዝር አርጎ ከመሄዱ ... ሌላኛው ደሞ ይመጣና more impress ለማድረግ more ቁ ..ዝ ..ር የሚያደርግ ወሬውን ይለቃል ::..... ሌላው ....... ወሬያቸው በብዛት የነበረው ባሁኑ ሰአት አዲሳባ ቆንጆ ቺኮች እንደበዙ (as if በፊት ቆንጆ እንዳልነበረ )... ሴቱ ከበፊት የበለጠ 'inviting' እንደሆነ .... ሰለ ናይት ክለቦች ..... ምናምን .... ያንዱ cellphone ካንዱ ምን ያህል የበለጠ facility እንዳለው .. ምናምን ..... ጋባዥዋ ደሞ መኪናዋን ለማሳየት ሰሞኑን ከተማ እየዞረች outdoor service የሚሰጥባቸው ቦታዎች ስትሰጣ እንደጠቆረች ምንምን ..... (by the way ላላወቃችሁ ባሁኑ ሰአት አዲሳባ outdoor service የሚሰጥባቸው ቦታዎች ያዳዲስ መኪና display ማድረጊያ እና ለዛ ለሀብታሙ ሰውዬ ሴቶች ተመርጠው ፒክ የሚደረጉበት ቦታዎች እየሆኑ መጥተዋል ) .... ስለመኪናዋ ሌተስትነት ምናምን አወራችልን .... እና ፑፒ (የውሻዋ ስም ነው ) 700 ዶላር ከፍላ እንዳስጫነቻትና ሰሞኑን እንደምትገባ ነግራን ነበር ::

ትናንት ልጅትዋ ደወለች .... guess what! በጉጉት ስትጠበቅ የነበረችው ፒፒ ገባች :: ደስ አይለም ?... እና የሱአን መምጣት ምክንያት በማድረግ ያንን barbeque እንደግማለን ተባለ :: This time ግን ይዘን የምንሄደው መጠጥ ሳይሆን ወሻዎቻችንንና ለነሱ አጥንት ነው ተብለናል :: አይጥምም ? .... እኔም ትንሽዬ ውሻ አለችኝ - እና የውሻን ፍቅር I understand. ግን .... እ ..... ካለአቅሙ የስጋ አምሮት ልቡን ው ..ል ..ቅ ሲያደርገው ስጋ ቤት በር ላይ ቆሞ ጮማውን እያሰበ በቆሎ የሚነጭ ስንት ህዝብ ባለበት አገር ቁጭ ብሎ ውሻዬ መጣች ተብሎ ካጥንት ጋር ኑ ብሎ ሰው መጋበዝ ... እሱን እናንተ ታውቃላችሁ :: አሁን እዛ ብሄድ የሚወራውን ከወዲሁ እገምታለሁ .... እ ... like .... ፑፒ ስንት ቀን ሶፋ ስር ሸንታ እንደተገረፈች ... ወይ ደሞ ፑፒ አልጋ ስር ስንት ቀን ከቦይፍሬንዷ ጋር እንደተያዘች .... ምናምን አይነት ትርኪ ምርኪ .... ግን እንደዛም ሆኖ እሄዳለሁ ብያለሁ .... ከዚህ ካድካሚ ህይወት ከሚባለው ጊዜ ውስጥ አንዳንዴ ለትርኪ ምርኪም ሰአት መመደብ ጥሩ ነው :: ካለበለዚያ ሁሌ ቁም ነገር ከሆነ ህይወት አሰልቺ ይሆናል :: በኔ ስልቹነት ....

ግን ፑፒዬን ገና ሳላውቃት ወደድኳት ... u know why? እንኳን ደህና መጣችልን እንጂ ብትሞት ደሞ ለቅሶ ድረሱ ቢሉን አስቡ ... ለፈረንጅ ውሻ ለቅሶ ስንቀመጥ አልታያችሁም ? ..... እኔ ለራሴ እዚህ አገር ድ ....ክ ....ም ከሚለኝ ስርአት አንዱ የለቅሶ ስርአት ነው ::

ው ......ይ ......... አማርኛ ታይፕ ማድረግ የበለጠ ያደክማል ልበል ? ብዙ ነገሮቻችን ለምን አሰልቺና አድካሚ እንደሆኑ እኔ ምንም አይገባኝም ::

ተፃፈ በናፍቆት
ኤፕሪል 23 2004


ዋናው_______________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Aug 19, 2007 8:43 pm

ከባሕልና ስነፅሑፍ የተገኘ

ሄይ ኮኒ

የሰው ልጅ እሚወለደውም እሚሞተውም ወዶ ፈልጎት አይደለም :: የተፈጥሮ ወይም የፈጣሪ ፍቃድ ነው :: ወይም የወሲብ ውጤት ነው :: ፍጡር ደግሞም የሚሊሰከንዶች አጋጣሚ ውጤት ነው :: ለኔ የሚያሳዝነኝ ሳይፈለጉ መወለድና መሞት ሳይሆን ከተወለዱ በኌላ የሰው ልጅ በሰው ልጅ የሚያገኘው ስቃይ ና መከራ ነው :: አንደኛው የአስቃይነት ሌላኛው ደግሞም የተሰቃይነት ቦታ ይዞ ህይወት የምትኖር ትራጀዲ ስትሆን ነው :: ዛሬ ጨካኝ የሆነው ሰው ትላንት ምንም እማያቅ ምስኪን ህፃን ነበር :: እሚፈጥርን መውቀስ ደግሞ ህይወትን ሁሌም መራራ አድርጎ መውሰድ ይሆናል :: ወይም የህይወትን መራራ ጎን ብቻ ማየት ነው :: ለኔ ሄዋን አሳስታው አዳም የእውቀትን ፍሬ በልቶ ከገነት ባይባረር ኖሮ ህይወት የምትደብር በሆነች ነበር :: ለፍቶ ሰርቶ አለመብላት ?????????? very boring???? ህይወት ከነ ምሬቷም ጣፋጭ ነች :: ስለዚህ አዲስ የሚወለድ ህፃንን ወደዚች ምድር ለምን መጣህ ብዬ ሳይሆን የማዝንለት ; እንኳን ደህና መጣህ ነው የምለው :: በእያንዳንድዋ የሰከንድ ስንጣቂ የሚወለድ ህፃን ; ወይ ሂትለር አለበለዚያ አንስታይን የመሆን እጣ አለው :: ሂትለርን ደግሞም አንስታይን ያጠፋዋል :: የህይወት ውበቷ ከነ ቆሻሻዋ እስከሆነ ድረስ እያንዳንዱን ፊደል ስተይብ የሚወለደው ህፃን ለአለም መጣፈጥ ነው የሚል እምነት አለኝ ::
_________________

ተፃፈ በ jossy 1
ማርች 02 2006


ዋናው_____________________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Aug 20, 2007 8:06 pm

ጉዱሽካ የሞኒካ ቡና ቤት ተከፍቶ ለምረቃ ይዞ የሄደው ቀልድ ነው

እረ ጉድ !... ለካ በከተማውና በየዋርካው ሥር የሚወራው ስለዚህ ቡና ቤት ነው !! አቤት ! ኮርኒሱ ! የወለሉ ምንጣፍ ! አሁን በዚህ አቧራ በቃመው በረባሶዬ ይህን ምንጣፍ ብረግጠው ይገላምጡኝ ይሆን ? መቸም አሁን ገና ስራ ሰራሁ ትበል ! እንደው የሰው ልጅ ለፍቶ ከሰራ ካሰበበት ቦታ ይደርሳል ! ይህው በሞኒት አየሁት ! መጀመሪያ የቦኖ ውሐ መሽጥ ጀመረች ከዚያም ቅቅል በቆሎ በበርሜል ንግድ ገባች እንዲህ እንዲህ ስትል ይህው እላይ ወጣች ! አሁንም አንድዬ ሀብቷን በላይ በላይ ይጨምርላት !

እስቲ ልግባና አንድ እንደወረደ ቡና አፌ ላይ ለትሜ ልውጣ ! እዚህ ቤቶች ....እንኳን ደስ አላችሁ ! (አቤት አሁን ካልጠፋ ቦታ አይናቸው ከበረባሶዬንና ከተጣፈውን ቁምጣዬ ምን ጉዳይ አላቸው ?) እስቲ ያለችኝን ጀባ ልበልና ልውጣ ! መቸም ንግድ ቤት ምረቃ ሲመጣ አንድ ነገር ወርውራችሁ ሒዱ ተብሏልና !

ነገሩ በቅርብ ነው :: የአንድ ጓደኛዬ እህት ሁለተኛዋን ሴት ልጅ ሰለወለደች እሷን ለመጠየቅ ወደ ቤትዋ ሄድኩኝ :: እዛው ቁጭ ብዬ እየተጨዋወትን እያለ የመጀመሪያዋ የአራት አመት ወንድ ልጇም አጠገባችን ነበር :: እናቲቱም ህጻኗን ገላዋን አጥባ ልብሷን ለማልበስ እያደራረቀቻት እያለች ወንድሟም ትኩር ብሎ የትንሽ እህቱን ገላ እያየ በመገረም ፊቱ ኮስተር ፈታ እያለ በዚያ በሚጥም ኮልታፋ አፉ ይህንን ጥያቄ ለናቱ ጠየቀ ! " አንቺ ማሚ .....እ ....እ ...የቤቲ ሽንት መሽኛዋን እ ....እ .... ማን ነው የነቀለባት ? "

በሉ እስቲ እኔም ከሰሞኑ አንድ ቢዝነስ ለሞመከር እያሰብኩ ነው ! ምን አትሉኝም ? የተነቀለባትን የሚጠግን ሐላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ !

እስቲ ልጓዘው ! አቤት የበረባሶዬ ዱካ ምንጣፉ ላይ !

ጉዱ ካሳ
ከፒያሳ

ተፃፈ በጉዱ ካሳ
ዲሴምበር 28 2005


ዋናው___________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

የግል

Postby ወልዲያ » Tue Aug 21, 2007 12:38 am

ሠላም ዋናው!ምርጫህ ብትንትኑ የወጣ ነው ወይንስ የግል ነው?


ዋናውም አማርኛ አዋቂ ሁኖ ዋኖስ ሳይቃኘው ቀረ:: ስለ ቀራው ባናውቅም ስለ አቀራሩ ከመማር አንዘልም::

Image


ለማንኛውም ብርታቱን ይስጥህ እና ይስጠን
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby ዋናው » Thu Aug 23, 2007 12:56 am

አንዳንዴም ከራሳችን አቆማዳ ...

አይ እቺህ ሦስት (3)_______________

''አንተ ምን ሆነህ ነው ትላንትና ስልክህን ብሞክር ብሞክር ቮይስ መሴጅ ይሄዳል ''

''እኔንጃ ይሰራ ነበር ስንቴ ሞከርሽው ?''

''ሦስቴ ''
______________________________________
''ምን ባክህ የሰጠህኝ ዕቃ አይሰራም 'ኮ ደጋግሜ ሞከርኩት ምንም ...''
''እምቢ አለህ ...ስንቴ ሞከርከው ?''
''ሦስቴ ሞክሬው ቢሰለቸኝ ተውኩት ''
_________________________________________
''ምንድነው የሰጠህኝ ካርድ ወደአገቤት አልደውል አለኮ ብሞክር ብሞክር ምንም አይቀበልም ''
''እንዴት እምቢ አለሽ እስቲ ድገሚና ሞክሪው ....''
''እምቢ አለኝ እያልኩህ ሦስቴ ሞከርኩትኮ ....''
_________________________________________
''ይሄንን ፊልም ሦስቴ ነው ያየውት በጣም ነው የምወደው ''
__________________________________________

ለምንድነው ብዙ ብዙ ነገሮች በሦስት ቁጥር የተጠመዱት ከላይ ለምሳሌ ጠቃቀስኩኝንጂ በጣም ብዙ ነገሮች በሶስት ይመሰላሉ ...
ለምንድነው ? የምታውቁት ነገር አለ እስቲ ጥቁሙኝ አደራ ?

ሦስቱ ስላሤዎች
ሦስት ጉልቻ
ጌታን ወደ ጎለጎታ ወስደው በመስቀል ሲሰቅሉት እሱ ሦስተኛው ተሰቃይ ነበር
ጴጥሮስ የሱስን ሲክደው የሱስ ዶሮ ሳይጮው ሦስቴ ነበር ትክደኛለ ያለው (ካልተሳሳትኩኝ )
በስፖርት ዓለም ውስጥ ተወዳድረው የሚሸለሙት እስከሦስት የወጡት አሸናፊዎች ናቸው
ሁለት ጊዜ አስነጥሶንን በሦስተኛው ጉንፋን ነው ይባላል
ላንድ ነገር መንደርደሪያ ቁጥር የሚቆጠረው እስከሦስት ነው ....
ብቻ ብዙ ብዙ ነገሮች ውስጥ ሦስት ትልቅ ቦታ አላት ምክኚያቱን የሚያውቅ ይኖር ይሆን እሲ ካለ ጠቁሙኝ

ቸር እንሰንብት

ዋናው ________________________________::

እራሴው እንደፃፍኩት:
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Aug 26, 2007 2:37 am

ባንድ ወቅት ቢኖ ስለፍቅር እንዲህ ብሎ ፅፎ ነበር


ብዙ አይነት ፍቅር እናዳለ ባውቅም አሁን የማወራው ስለጾታዊ ፍቅር ነው ብዙ ሰዎ ስለፍቅር ድርሳናቸው ሲያወሩ እንደምሰንማው ሲጽፉ እንደማነበው ከሆነ ብዙወን ጊዜ የፍቅር አጀማመራቸውን ሲተርኩ ወይንም ሲጽፉ በድንገት በአጋጣሚ ሳላስበው የሚል ሀይለ ቃል ነው የሚጠቀሙት ከዚህም የምረዳው ነገር አብዛኛዎቹ በፍቅር የሚያዙት እንደመብረቅ ዱብዳ ነው ::
ይህ ነገር ደግሞ እኔን አይዋጥልኝም ምንም እንኳን ለፍቅር ቀመርና ስሌት ሰጠን አባዝተን ደምረን ቀንሰን አካፍለን የተለያዩ ፎርሙላዎች ሰጠን ፍቅረን እንዲህ ነው ብለን አንድምታውን መናገር ባንችልም ሁላችንም እንደየራሳችን አስተያየትና ግምት የምናምንበትና የምንረዳው ነገር አለ በዚህ መሰረት እኔን እስከሚገባኝ ድረስ እውነተኛ ፍቅር ሊጸነስ የሚችለው ድንገተኛ በወረደ ዱብዳ ሳይሆን በመቀራረብና በመለማመድ ነው እንጅ ምንነቷን የማላውቃት ልጅ ድንገት በተፈጠረ ክስተት በኔ ወስጥ የፍቅር ቦታ ሊኖራት አይችልም ፍቅር የሚጽነሰው መቀራረብና መለማመድ ወደመዋደድ መዋደድ ወደፍቅር ፍቅርም ብዙውን ጊዜ በሚገባ ከኮተኮቱትና ከጠበቁት ወደ ተቀደሰ ጋብቻ ያድጋል :: ይህ እንግዲህ የኔ አመለካከት ነው ምናልባት እንደዚህ ልል የቻልኩት ለጾታዊ ፍቅር ካለኝ አናሳ እውቀት ሊሆን ይችላል እስቲ የፍቅር ፕሮፌሽናል ኤክስፐርቶች ምን ትላላችሁ ::
መቸም ሚሚ love በዚህ አምድ አይነተኛ ተዋናኝ እንደምትሆን ጥርጥር የለውም

ተፃፈ በቢኖ
ማርች 4 2006


_________________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ከወደ ቶሮንቶ

Postby ዋኖስ » Mon Aug 27, 2007 4:53 pm

ከወደ ቶሮንቶ የተገኘ ምክር ቢጤ ፅኁፍ! በሳኅሉ በቀለ:: ያንብቡት!

ያሰብከው ዓላማ
(ከሣህሉ በቀለ ቶሮንቶ)
ያሰብከው ዓላማ፤ ግቡን ካልመታልህ
ችግሩ ከበዛ፤ ጠላት ካየለብህ
ጠላትህን ቀንስ፤ ወዳጅህን Aብዛ
ታላቅ Eቅድ Aውጣ፤ ለEምነትህ ተገዛ
ጥበብን ፈልጋት፤ Eውነትን ደግፋት
Eብደትን ንቀፋት፤ ውሸትን ሰርዛት
ሰፋ Aርገህ Aስብ፤ Eይታህ Aይጥበብ
በዛፍ Aትጣላ፤ ጫካ Eንዳለ Aስብ
Aርቀህ ተመልከት፤ ራEይ ይኑርህ
ሁልጊዜም ለዛሬ፤ ነገ Aለ ብለህ
ትናንትን በማንሳት፤ Aትሂድ ወደኋላ
ለAዲሱ ክረምት፤ Eንዲሆን ከለላ
ቀይስ ጥሩ ዘዴ፤ ፍጠር Aዲስ መላ
ወጤቱን Eንድታይ፤ የኋላ የኋላ፡፡
ሥራና ሃሳብህ፤ ከጊዜው ጋር ይሁን
ፀፀትና ቁጭት፤ Aሳሪህ Eንዳይሆን
ትርጉም ያለው ሥራ፤ ትርጉም ያለው ህይወት
መሆኑን Aትዘንጋ፤ የEድገት መሠረት
ደግሞም ለብቻህን፤ Aትሩጥ Eንዳበደ
ወገን Eንዳጣ ሰው፤ Eንዳልተወደደ
ሥራህ ጥራት ካለው፤ ቃልህን ካከበርክ
ለህሊናህ Eንጂ፤ ለሆድህ ካላደርክ
Eንኳን ወዳጆችህ፤ Aንተን የሚመስሉ
የሚፈሩህና፤ የሚጠሉህ ሁሉ
የሸነፉልሀል፤ Aማራጭ ሲጠፋ
መኖር ሲሳናቸው፤ በጉራ በፉፋ
ከንቱ ሆኖ ሲቀር፤ Eውነት ያሉት ተስፋ፡፡
ስሜትህ ይሟሟቅ፤ ጉልበትህ ይበርታ
AEምሮህ ያስተውል፤ ነገር በዝግታ
ለመፍረድ Aትቸኩል፤ ሌላውን Aትኮንን
በውሸት ጀብደኛ፤ ዝነኛ Aትሁን
መቻቻልን ልመድ፤ ጥፋትህን ተቀበል
ለመቆ’ጠብ ሞክር፤ ከAጉል ቂም በቀል
ተመከር ተዘከር፤ ልቦናህን Aፅዳ
ካለብህ ለወገን፤ ያልከፈልከው Eዳ
Aይኖችህን ፈጠጥ፤ ጆሮችህን ከፈት
Eጆችህን ዘርጋ፤ Aፍህንም ዝግት
Aድርገህ ሞክረው፤ Eስኪ ለEውነት ብለህ
የያዘህ Aባዜ፤ ድንገት ቢሄድ ብለህ
ሐቁ ከውሸቱ፤ ተከፍሎ Eንዲታይህ
የEውነት መክፈቻው፤ ቁልፉ Eንዳይጠፋብህ፡፡
በዛም ሆነ በዚህ፤ የሰው ልጅ ነህና
ምንግዜም፤ ከኃጥያት Aትፀዳምና
ትናንትና ዛሬ፤ ዘንድሮም Aቻምና
ላይገርምህ ይችላል፤ የራስህ ስንፍና
የገዛ ጆሮህ፤ ጠላትህ ነውና፡፡
ለወገን ለAገር፤ ማሰብከን Aታቁም
ለመብት ለነፃነት፤ መጮህክን Aታቁም
ለሠላም ለፍትህ፤ መጮህክን Aታቁም
ለዴሞክረሲያዊ ሥርዓት፤ መጮህክን Aታቁም
ያብዛኛው ሕዝብ ምርጫ፤ ማሸነፉ Aይቀርም
ትግልህና ድልህ፤ ብዙ Aይራራቁም፡፡
ያች ውድ Eናትህ፤ Iትዮጵያ የሚሏት
በታሪክ በባህል፤ ጥንታዊነት ያላት
ከውስጥም ከውጭም፤ ብዙ ጠላት ያላት
የጀግኖች ያርበኞች፤ ያማኞች ወላጅ ናት፡፡
ይህን ተገንዝበህ፤ በታሪክህ ኮርተህ
ጊዜና ጉልበትህን፤ ባንድ ላይ Aድርገህ
የጋራ ጠላትህን፤ በጋራ መክተህ
በተባበረ ኃይል፤ መብትህን Aስከብረህ
የምትኖርበት ቀን፤ Eጅጉን ተቃርቧል
የEናትህ መከራ፤ ማብቂያው ቀን ተዳርሷል
Eውነትና ንጋት፤ Eያደር ይጠራል
ዓላማህ ይሳካል፤ ድል ያንተ ይሆናል!


(የግጥሙ ፎርማት ማስኩሊን ቢሆንም ከወንድ ትምክህት ነፃ ነው፡፡ ሣ.በ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests