ከባልቻ መዶሻ ድርሰት ውስጥ የተወሰደ ....ምልልስ
ባልቻ ፎዴን አራት ኪሎ የማያውቀው የለም ''...እኔ ባልቻ ያላቀናውት የመኩዋንንት ጫማ የለም ...'' ይላል ባለሙያነቱንና የስራ ልምዱን በኩራት ሲናገር ሽብሽብ የፊቱ ገጽ ስር የጠነገሩና ኑሮ 'ሀክ !' ያላቸው አይኖች አሉት ገብስማ ጢሙቹ ፊቱን እንደጉንዳን ቆንጥጠውታል የግራ ጆሮው ቀዳዳ ነው ተበስቶ ነበር ብቻ ሰፍና ቀዳዳ ሆነ ሁሌም ለሰላምታ እጅ ሲነሳ በቀር ከአናቱ የማትወልቀው ቅዱስ ገብሬልን ለማስፈራራት አትማ እዛው አናቱ ላይ ያረጀቸው የጨርቅ ኮፍያው መለያው ነች ::
ይገበዋል ጠጅ ቤት ገብቶ የመጀመሪያውን ብርሌውን በቁሙ አንቆርቁሮ ጠንጋራ አይኖቹን ሲማትር ባለንጀራው ጎበናን አየው ፈገግታ ሰጠው :: ጎበና መጥቶ አጠገቡ ተቀመጠ ::
...''እህሳ ባልቻ 'እንዴት ነህ ?'' አለው ብልጭልጭ ያለ ጥቁር ፊቱን ሁሉ ፈገግታ ሞልቶ
''አለው ቅዱስ ገብሬል የተመሰገነ ይሁን ...'' አለው ወደ ጣሪያው እጆቹን ዘርግቶ
''ስራስ እንዴት ነው ? ''
''አለው ይሄው የምድረ ሙጃሊያምን ፎዴ በውረንጦዬ እየወሰወስኩኝ ሸፋፋ ካለ ባልቻ ጾሙን አያድርም ....ጎበናዬ ''
ጎበና በመሀልና በሌባ ጣቱ ቆንጥጦ ያመጣትን ብርሌ በዜማዋ ወድጉሮሮው ዶቅ !ዶቅ !ዶቅ !... እያደረጋት ከንፈሮቹን ክብ አደረገና የወረዛ ጠጁን በሁለት ጣቶቹ አልቡ ጉልበቱ ላይ እያበሰ
''እንዴት ማለት ...?'' አለው ድምጹ እንደሰውነቱ ወፈር ያለ ነው ቢጫ ያይኖቹ ብሌኖች ተልቀው ጎበናን የሞኝ ገጽታ አላብሰውታል
'' በቃሀ ምን እንዴት አለ ሸፋፋ እንደሆን ጫማ ይቀዳል ሲቀደድ ደግሞ ውደባልቻ ...''
ጎበና ድጋሚ ሳቀና
''አይ ባልቻዬ ቅዱስ ግብሬልን እየተማጸንክ የሰዉ እግር ሁላ ቢጠማዘዝልህ ደስ ባለህ ....ቅቅቅ ''
''ታዲያሳ አንተስ ብትሆን ጠላ የሚያንቃርር ከሌለህ ስራ አጣህ ማለት አይደለ ? እቺ አለም 'ኮ እንዲህ ናት ያንዱ መከራ ላንዱ ጉራ አይደል ?...''
''አሀይ የኔስ አህያ አተላ ብታጣ የሆዳሞችን ጤፍ ታመላልሳለች ሞኞ ''
አለ ጎበና በኩራት ጠጁን 'የተጎነጨ
''...አይ አሁን በዛች ሸፋፋ አህያ ማን አምኖ እህል ይጭናል አተላውስ ቢደፋም አተላ ነው ...''
''ምነው ሸፋፋ አልካት እሱዋ 'ንድሆን ጫማ የላት ''
.''ቅቅቅ አይ ጎበና አንተ ኤኔትሬ ቢኖርህ ምን ትሆን ነበር በዚች አህያ እንዲህ የኮራህ ደሀ ወርቅ አይግዛ ....ነው የተባለው ''
ተፃፈ በዋናው
ፌብረዋሪ 26 2006
.