ከኔም ከነሱም...(አጤ ቴዎድሮስና እሳቸውነታቸው..)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ከኔም ከነሱም...(አጤ ቴዎድሮስና እሳቸውነታቸው..)

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 12:58 pm

የሆነ ረጅም ስራ ለመስራት ስለፈለኩኝ ለስራዬም ዋናው ነገር ከአይምሮዬ ተወልደው ተቀርጸው ታስበው የሚወጡትን ውልደቶች ወይም ስራዎች በታይፕ ተምትሞ ፍ'ጡር ለማድረግ የግድ ልክ እንዳሰብኩ በዛ ፍጥነት በታይፕ የመተምተም ችሎታ ስለሚያስፈልገኝና ሁል ጊዜ እራሴን በራሴ ስለማስተምር እራሴን በራሴ ያለማንም ገፋፊነትና ትእዛዝ በፍጥነት በፍጥነት የታይፕ መተምተም ችሎታ ለማግኘት ሰሞኑን ከራሴም ሆነ ከለሎች ሰዎች ስራዎች እየጻፍኩ ታይፕ በፍጥነት መተምተም ለራሴ አስተምራለሁ::

እራሴ ለራሴ ነኝና ሰው አነበበው ወይም አላነበበው የኔ ጉዳይ አይደለም::ጉዳዩ ሾተል በምን ያህል ፍጥነት በሀሳቡ የተወለዱትን ዝባዝንኬዎች ቶሎ ቶሎ ታይፕ ያደርጋቸዋል ነው::

በራስ ለራስ ልምምዴን በሚቀጥለው ገጽ እጀምራለሁ::


ሾተል....የራሱ አስተማሪ
Last edited by ሾተል on Tue Aug 14, 2007 1:15 pm, edited 1 time in total.
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:00 pm

ወሲብን የሚቃወሙት ደስታ እንዲርቅህ ጸጸተኛ እንድትሆን ፍርሀት እንዲያድርብህ ሊያደርጉ የሚችሉበት መንገድ ስለሆነ ነው::አንዴ በፍርሀት መራድ ከጀመርኽ እንደፈለጉ ሊበዘብዙህ ይችላሉ::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:02 pm

ገንዘብ ለነገሮች ያላችሁ ፍቅር ነው::ገንዘብ ከሰዎች ራሳችሁን የጠላችሁበት ነው::ገንዘብ ሞትን ለመራቅ የምትሞክሩበት መከላከያችሁ ነው::ህይወትን ለመቆጣጠር የምትሞክሩበት በገንዘብ ነው::ገንዘብ አንድ ሺህ አንድ ነገር ነው::ገንዘብ የመገበያያ ወረቀት ብቻ አይደለም::እንዲያ ቢሆን ኖሮ ሁናቴዎች ሁሉ እጅግ ቀላል በሆኑ ነበር::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:05 pm

ነፍስ የምትገኘው ከስጋ ውስት ነው::ፍቅር የሚገኘው ከወሲብ ውስጥ ነው::ወሲብ ስጋዊ ነገር ነው::ፍቅር ግን መንፈሳዊ ነው::ወሲብ እንደመሬት ያለ ነው::ፍቅር ደግሞ እንደጽጌሬዳ ነው::ነገር ግን መሬቱ ከለለ ጽጌሬዳን ለማግኜት አይቻልም::ስለዚህ መሬቱን አትጥሉት::


OSHO
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:10 pm

አእምሯዊ ምስል ፈጠራ በብዙ የህይወት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ዋጋ ቢኖረውም ከሁሉም ምስሎች የሚበልጥ አንድ ምስል አለ-የራስ ምስል::"ሰው በልቡ ያሰበውን ነው" የሚል አንድ አባባል አለ::ራስን እንደ ስከታማ ሰው ከሳሉት ይሳካለታል::እንደማይሳካ ካመኑ በሄዱበት ሁሉ ውድቀት ይገጥሞዎታል::ሙሉነት ካሰቡ የእርስዎ ይሆናል::ጎዶሎነትን ካሰቡም እንደዚሁ::አለም እንደግዙፍ የገደል ማሚቶ ናት::ወደላይ የወረወሩት ውሎ አድሮም ቢሆን መመለሱ አይቀርም::ሰዎችን የሚወዱ ከሆነ ያ ፍቅር ወደ ራስ ተመልሶ ይመጣል::ንዴትና ጥላቻን ከዘሩ ንዴትንና ጥላቻን ያጭዳሉ::ስለራስና ስለፍላጎቶች ብቻ የሚያስቡ ከሆነ ለሎች ወደርሶ አይሳቡም::ራስዎን ከሁዋላ አድርገው ለሎችን የሚያስቀድሙ ከሆነ ሁሉም ሰው ጉዋደኛዎ ይሆናል::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:16 pm

በራሶ የማይተማመኑ ከሆነ የህይወት መሰረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ አይችሉም::እኔ ማነኝ?ከየት ነው የመጣሁት?መድረሻዬ የት ነው?እዚህ ምን እየሰራሁ ነው?ጥርጣሬ ካለዎት ንቁ ያልሆነው አይምሮ ግራ ይጋባል::ተስፋ ይቆርጣል::"ይህ ሰው ምን እየሰራ እንደሆነ የማያውቅ ከሆነ"ይለዋል ለራሱ:"በዚህ ወይም በዚያ መንገድ ተጉዋዝ ብዬ ለምን አስቸግረዋለሁ?ምንም ለውጥ ስለማያመጣ እነም መጨነቅ አይኖርብኝም::"ስለዚህ እምነት ማጣት ከፍተኛ አለመረጋጋትን ሊፈጥር ይችላል::ጠንካራ ስበና ያለው ሰው በከፍተኛ ጥረት ይታገላል::እንዲህ አይነቱ ሰው ቢሳካለት የተሳካለት በራሱ ነው::ምክንያቱም የራሱ ምስል የማያናውጥ ነበርና::


NORMAN VINCENT
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:20 pm

አለምን የቸገራት ምንድነው?ምግብ?ልብስ?ቤት?አዎን በሙሉም ባይሆን በከፊል የነዚህ ነገሮች ችግር አለባት::ግን የሰውን ልጆች ይበልጥ ያስጨነቀው ይህ ችግር ብቻ አይደለም::አለም ለሚኖሩባት ፍጡሮች የምትበቃ ሰፊ ናት::ምንም እንኩዋን የህዝብ ብዛት የሰዎችን ኑሮ ያጣብባል እየተባለ ማስጋቱ ኤርግጠኛ ነገር ቢሆን በዚያው መጠን ደግሞ ሰዎች በአለም አካባቢ የሚገኙ ነገሮች ሁሉ መጠቀምያ እያደረጉዋቸው ስለተገኙ ችግሩ ላያሰጋም ይችል ይሆናል::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:23 pm

ለምሳሌ ውሀ ነፋስ መሬት እሳት በድሮ አገልግሎታቸው ብቻ የተወሰኑ አልሆኑም::ሁሉም ለሰው እለታዊ ፍላጎት በብዙ መንገድ ማገልገል ችለዋል::ይሁን እንጂ ችግር ሁሉንም ነገር አልፎ ወደሰዎች እየተጋፋ ከመጣ የመወለድን ብዛት በመቆጣጠር የሰዎችን የኑሮ ችግር ማቃለል እንደሚቻል ያመኑ ብዙዎች ናቸው::ነገር ግን እስካሁን ድረስ መድሀኒት ያልተገኘለት ችግር የመልካም ሰዎች ማነስ ነው::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:27 pm

ሰው ብዙ ነገሮችን ተረድቷል::ራሱን ግን ገና አላወቀም::ሊያስመካ የሚችለውን ነገር ሁሉ ዘንግቶ በማያስመካው ነገር ይመካል::በዚህም ምክንያት ጥሩ ሰው አነሰ::ሰው!ሰው!ሰው!የሰው ያለህ!የሚያሰኝ ዘመን ነው::ሰው ደስታን ሰላምን ነጻነትን ለማግኘት የሚጣጣር ይመስላል::ጥረቱ ብርቱ ይመስላል::ነገር ግን ጥረቱ ከግዙፍ ነገሮች ጋር ብቻ ስለሆነ ተፈላጊውን እውነተኛ ነገር ለማግኘት አልቻለም::ሰው እንዴት አድርጎ እራሱን ብቻ እንደሚጠቅም ከማሰብ ይልቅ እንዴት አድርጎ ከወንድሞቹ ጋር በሰላም መኖር እንደሚችል ጨምሮ ቢያውቅ ይበልጥ በተደሰተ ነበር::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:29 pm

በአለም ውስጥ ከተራ ሰዎችም ሆነ ከመሪዎች አልፎ አልፎ አንዳንድ ቅን አሳቢዎችና ሰሪዎች ይገኛሉ::ይሁን እንጂ እነሱም ብዙዎች ባለመሆናቸው ሀሳባቸው አጭበርባሪዎች በብዛት በሚገኑበት አለም ብዙ ጊዜ ስለሚዋጥ እየጠፋ ከመቅረት አላመለጠም::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:31 pm

የአለም ችግር በመሰረቱ ከምንም ሳይሆን ከሰው የመነጨ ነው::ሰው በቅን መንፈስ ከተመራ የተፈጥሮ ችግሮችን ሁሉ አስወግዶ የተመጠነና ደስታ ያለው ኑሮ ለማግኘት የማይችልበት ምክንያት የለም::አንዳንድ ሰዎች ይህን በመረዳት ቅን መንገድን ሲከተሉ ብዙ ችግሮችና መሰናክል አልፎ አልፎም ህይወትን የሚያሳጣ አደጋ ያጋጥማቸዋል::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:39 pm

ህንዳዊያኑ ጋንዲና ኔህሩ,አሜሪካዊው አብርሀም ሊንከን መስኮባዊው ሌኒን አረባዊው ኡመር አልሀጣባ ቱርካዊው ሙስጠፋ ከማልና እነሱን የመሰሉ ጥቂት መሪዎች ከራሳቸው ይልቅ ለሌሎች ሰዎች ጥቅም መፈጠራቸውን መካድ ራሱ ታላቅ ወንጀል ነው::ለሰው የተፈጠሩ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ::ነገር ግን የውንብድናዋ አለም ከምታፈራቸው ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ምሳሌ አድርገው ሊከተሉዋቸው የሚሹት ከነዚህ ታላላቅ ሰዎች ይልቅ በራስ ብቻ ፍቅር የሰከሩትን ወንበዴዎች ነው::በአለም ያሉ ጄኔራሎች ሁሉ ናፖሊዎንን ለመሆን ትችላላችሁ ቢሏቸው አለምን ሊያጠፋ ይችላል በሚባለው የኑክልየር የጦር መሳርያ ጦርነት ለማንሳት ባልተመለሱሱም::ሀሳባቸውን የሚገታው የዘመኑ ጦርነት ሬሳው የትም ወድቆ የሚቀር ተሸናፊንና በመዳሊያና በዝና የሚንቀባረር ድል አድራጊን መፍጠር ሳይሆን የጋራ መውደምን ማስከተሉን ማወቅ ብቻ ነው::እነጋንዲን ለመከተል የሚፈልጉ መሪዎች ግን መኖራቸው ያጠራጥራል::ታላቁ ህንዳዊው መሪ ጃዋህራል ኔህሩ ሲሞት በህንድ ውስጥ እንኩዋን የጋንዲ አላማ እየጠፋ ይሄዳል ብለው የሚያምኑ እጅግ ብዙ ናቸው::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:43 pm

በመስኮብ አገር ታላቁ ሌኒነንደሞተ የቅርብ ተከታዩ የነበረው ጆሴፍ እስታሊን እንኩዋ የርህራህእውን አላማ ወደጭካኔ በመለወጥ የሌኒንን መንፈስ እንዳልተከተለ ይነገራል::ትላንትና ጆን ኤፍ ኬኔዲ ለሰው ልጆች የሚገባውን ትክክለኛ አላማ ይዘው በሚደክሙበት ጊዜ አለምን ባሳዘነ ሁነታ ተገድለዋል::መልካም ሰዎች በንፋስ ጥግ ባለች መቅረዝ ላይ እንደሚበራ መብራት ብልጭ ብለው ወድያው እልም ስለሚሉ የሰዎች ችግር እንደነበረ ነው::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 1:52 pm

ከተራ ህዝቦችም ውስጥ ብዙ ጥሩ ሰዎች ይገኙም ይሆናል::ነገር ግን እነሱም በቂ አልሆኑም::የደህና ሰዎች ቁጥር መብዛት አለበት::ሰው ያለሰው አለመኖሩን ተገንዝበው ፍቅርን ሰላምን መረዳዳትን መተማመንን የሚወዱ ሰዎች መብዛት ያስፈልጋቸዋል::ራሳችንን ስናየው ባንድ በኩል የሰዎች ጥገኛ ባንድ በኩል ደግሞ የሰዎች መጠጊያ የሆነ ነው::እኛ ማነን?ከዘጠኝ ወር በላይ በሰው ሆድ ውስጥ የቆየን ከሶስት አመት በላይ በሰው ክንድና ጀርባ ላይ የኖርን ከዚያም በሁዋላ ለብዙ አመታት በሰው ሀሳብ የኖርን ስንሞት ወዳጆቻችንና ዘመዶቻችን በእንባ በሀዘን እየተሰቃዩ ከመጨረሻ ቦታችን የሚያሳርፉን የሰው ባለእዳዎች እይደለንም?ምንም እንኩዋ የጥቅም ልውውጥ ቢሆን በየቀኑ የምንፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ አብዛኛዎቹ በለሎች እጅ የተሰሩና በለውጥ የምናገኛቸው አይደሉምን?ታድያ ለምን ነው ሰው ለራሱ እንጂ ለለላው አይኖርም የሚባለው ትምህርት የሚያደነዝዘን?ለምን እራሳችንን ብቻውን ሳይሆን ከለሎች ጋ ደርበን አንወደውም?ራስን ለመጥቀምም ቢሆንኮ ፍቅር ፍቅር የበለጠ ጠቃሚ ነው::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Aug 13, 2007 2:00 pm

እነዚህ ከባድ ጥያቄዎች በቂ መልስ ባለማግኘታቸው ሰዎች አሁንም ባውሬነት ባህሪያችን ስር እንገኛለን::"ሳይንስ! ቴክኖሎጂ!ሳይንስ!ቴክኖሎጂ!"የአዋቂውም የመሀይሙም የሀይማኖታዊውም የሀይማኖት የለሹም ያፍ ማሙዋሻዎች ሆነዋል::ጥሩ ነው::ሰው ጥቅሙን የሚያስገኙለትን ነገሮች በስምምነት አውቆዋል ማለት ነው::ነገር ግን አንድ ጊዜ"ፍቅር!ሰላም!ነጻነት!እውነት!"የሚሉ ነገሮች ደግሞ በህዝብ በንፈስ ላይ ገንነው ካልታዩ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የተባሉት የዘመኑ ጣኦቶች ብቻቸውን የሰውን ልጆች ደህንነት አያመጡትም::በአለም ላይ ሁሉም ነገር ሊከበር የሚገባው ለሰው በሚሰጠው ጥቅም መጠን ነው::አውሮፕላን ስለጮኸና ስለበረረ ብቻ አንፈልገውም::ሰዎች ወደምንፈልገው ቦታ ፈጥኖ ስለሚያደርሰን እንጂ::ኤሌክትሪክ,ብርሀን ጉልበት ስላለው ብቻ አንሻውም::ብርሀኑና ጉልበቱ ለሰው ልጆች ጥቅም በመዋሉ እንጂ:ሁሉም ነገር እንዲሁ ነው::ሰዎችን ካልጠቀመ በራሱ መፈጠር ብቻ ታላቅ የሚባል የስልጣኔ ፍሬ ቢኖር ደደቦች የሰጡት ስም ነው እንጂ እውነተኛ ስሙ አይደለም::
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests

cron