ከኔም ከነሱም...(አጤ ቴዎድሮስና እሳቸውነታቸው..)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Wed May 14, 2008 11:22 am

በሌላ ቀን ስለሆነው ነገር ደግሞ ይሄው ዎልድሜየር ሲጽፍ "......አንድ ቀን ከንጉሱ ጋር በጋማ ከብት ተቀምጠን በአገር ውስጥ እንዘዋወር ነበር::አንድ ሰው ከመንገዳችን ላይ ቆመና ጃንሆይ ጃንሆይ እያለ ሾኸ::ንጉሱም "ምን ሆነሀል ተናገር"አሉት::ሰውየውም "ከመንገድ ላይ ሀያ ብር አገኘሁ::ይህ ገንዘብ የማን እንደሆነ ዕነ አላውቅም::ብዚህ ምክንያት ገንዘቡን ወደ ጃንሆይ አመጣሁት"አላቸው::ንጉሱም "ይሄ ያንተ የዋህነት ነው::አሁንም ገንዘብ የጠፋው ሰው እስኪገን ድረስ ገንዘቡን አንተ ጋ አስቀምጠው::ስላንተ ታማኝነት ግን እኔ ሌላ ሀያ ብር እሰጥሀለሁ::"ብለው ሰጡት::ሰውየውም እየተደሰተ ሄደ::ይሄን ወሬ አንድ ሌላ ሰው ሰምቶ እንዲህ በቀላሉ ገንዘብ የሚገኝ ከሆነ የቀበርኩትን አርባ ብር አውጥቼ ለንጉሱ ላቅርብ ብሎ ይዞ መጣና "ጃንሆይ ይሄንን ገንዘብ ከመሬት አገኘሁ::የማን ገንዘብ እንደሆነ ስለማላውቅ ወደ እርስዎ አመጣሁት"አላቸው::ንጉሱም የሰውየውን አታላይነት ገብቷቸው "ገንዘቡን ወስደህ ለኔ ገንዘብ ያዥ ስጥ"አሉት::ሰውዬውም እያዘነ ገንዘቡን ለንጉሱ ገንዘብ ያዥ አስረክቦ ወደቤቱ ሄደ ..."በማለት ጽፏል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed May 14, 2008 11:45 am

ዱፍተን ስለ ቴዎድሮስ አዛኝነት ሲጽፍ ".....ድሆችን እራሳቸው እየተቆጣጠሩ ይጠብቃሉ::ድንኳናቸው በተተከለበት ቦታ ሁሉ የድሆችን አቤቱታ መስማት ይወዳሉ::ሁልጊዜ ስራ ከመጀመራቸው በፊት የድሆችን ጉዳይ ይሰማሉ::በጉዞም ላይ በሳምንት በሺዎች የሚቆጠር ብር ለድሆች ይሰጣሉ::ይህንንም ስጦታ በሚሰጡበት ጊዜ "ድሆችን ባልረዳ ለእግዚአብሄር ያሳጡኛል::እኔም እራሴ ድሀ ነበርኩ ይላሉ ....."ብሏል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed May 14, 2008 11:54 am

ፕላውዲን እንደጻፈው ደግሞ ".....አንድ ቀን ለጉዞ ልንነሳ ስንል ስጦታ ሰጡኝና አልቀበልም ብላቸው "አንተ ልጀ ነህ::ከኔ የምትፈልገውን ነገር ስሰጥህ ለምን አትቀበልም?" አሉኝ::እነም የታዘዝኩት ምን እንደሆነ ብነግራቸው "ግድ የለም::መልክተኞች ሁሉ ከመንግስታቸው እንደሚከፈላቸው አውቃለሁ::አገሬ ግን እንግዶችን እንድንቀበል ትጠይቀናለች::የእንግዶችን እግር ማጠብ ይገባናል::....ክፍያ የምከፍልህ አይደለም::የምሰጥህ ለእህልና ለውሀ ነው::መቀበል አለብህ::ከኔ የበለጠ ሀብታም መሆንህን አውቃለሁ::ይሄ ግን አሁን ብድር ነው::አንተ ደግሞ በተግባር ትከፍለኝ ይሆናል::ባንተም ረዳትነት ብዙ ቤቶችን እገነባለሁ::"አሉኝ::እኔም "ምንም አይደለም::ለርሶ የሚጠቅሙ የኔ ንግስት ናቸው::"አልኳቸው::እሳቸውም "ስማኝማ::ያለእግዚአብሄር ፈቃድ የምድር ነገስታት ሁሉ በነ ላይ ተቃውመው ለመነሳት አይችሉም::ስለዚህ አልፈራቸውም::ግን ያንተ ንግስት አንተን ወደኔ ልከውልኛልና ክርስትያን ናቸው::እምነታችንም ያስተሳስረናል::ክርስቶስ ወዳጅነታችንን ፈቅዷል::እግዚአብሄር በዚህ መልካም መንገድ ይምራኝ" አሉኝና ለብቻየ ወስደው አንድ ሺህ ብር ሰጡኝ::ከዚያም እጄን ይዘው ሰው ሁሉ ሟች ነው::አንድ ነገር በኔ ላይ ቢደርስ ልጄ ወዳጄ ሁነኝ::ወደአገርህም ሁላችሁንም የሚወድ ሰው ነው ብለህ ጻፍ::....እወድሀለሁ::አምንሀለሁ::በል ሂድ::ደህና ዋል አሉኝ..." ብሏል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed May 14, 2008 1:20 pm

ፕላውዲን ጁን 25 ቀን 1855 ወዳገሩ ባስተላለፈው ሪፖርት ".....ንጉስ ቴዎድርስ በእድሜ ወጣት ናቸው::....ትሁትና ደስተኛ ናቸው::የባሪያ ንግድን አጥብቀው የሚቃወሙ ናቸው::የተሸጡትን ባሪያዎች እሳቸው እንደገና የተገዙበትን ዋጋ እየከፈሉ በማስለቀቅ ነጻ ያወጧቸዋል::....ወታደሩም ከሚከፈለውና እየሰራ ከሚያገኘው ገቢ በስተቀር ከገበሬው ዘንድ እንዳይደርስ ጥብቅ ትእዛዝ ሰጥተዋል::....በማለት ለህዝቡ ያላቸውን ርህራሄ ገልጿል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed May 14, 2008 1:24 pm

ዎልድ ሜየር ስለ ባርያዎች ጉዳይ በጻፈው በጎንደር አካባቢ ባሪያ ነጋዴዎች የሚወስዷቸውን አስጥለው በብዙ መቶ የሚቆጠሩትን በነጻ ከለቀቁ በሁዋላ ጥቂቶቹን ለዎልድሜየር ሲልኳቸው በጻፉት ደብዳቤ "...እነኝህን ወጣት ልጆች ትበብና ሀይማኖቶች እንድታስተምራቸው ይሁን::እንደ እነኝህ ያሉትንም ያልታደሉ ፍጥረቶች ባገኘሁ ጊዜ ሁሉ እልክልሀለሁ::ደስ እንዲላቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ የምችለው እኔ ነኝ..."ብለውታል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ET-Princess » Mon May 19, 2008 9:43 pm

ሾተል
ጽሁፍህን ወድጄዋለሁ በጣም ጥሩ ነው
ET-Princess
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 58
Joined: Thu Dec 30, 2004 9:40 am
Location: ethiopia

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 12:28 pm

የቲዎድሮስን እንደምናውቀው የደጃዝማች ክንፉ ልጆች መኮንንና ይልማ የጎጃሙን ገዢ ብሩ ጎሹን ቸንቲ በር ከተባለው ስፍራ በተዋጉ ጊዜ ያን ጊዜ ካሳ ይባሉ የነበሩት ቴዎድሮስ ድል ሆነው ጦራቸው በተበታተነ ጊዜ የያኔው ካሳም አምልጠው አለፋ ላይ ካንድ ሰው ቤት ተደብቀው ወር ወር ሙሉ መቀመጣቸውን እናውቃለን::ብዙ ቆይቶ የያኔው ካሳ ከቴጌ መነን ጋ ተዋግተው ድል ካደረጉ በሁዋላ ሰራዊታቸውን በየባላገሩ ቤት ምሪት ሰደዱት::ምሪት ከገባባቸው ባላገሮች መሀል ያ ድሮ ወር ሙሉ ሰውሮ ወር ሙሉ ከደበቃቸው ሰው ቤት 12 ወታደሮች ገብተው ሰፈሩበት::ይህ ሰው ሊቀለቡ የገቡበት ሰዎች ስለበዙበት በለሊት ተነስቶ ወደያኔው ካሳ ዘንድ ሄዶ ጮኸ::ደጃች ካሳም ሰውየውን በድምጡ አውቀው ወታደር ልከው አስይዘው አስመጡት::እንደመጣም አንተ እገሌ የምትባለው ሰው አይደለህምን?ብለው ቢጠይቁት አዎን ነኝ አለ::ከዚያም የሰራላቸውን ውለታ ሁሉ ነግረው ከእልፍኝ አስገብተው ከባለቤታቸው ከወይዘሮ ተዋበች ጋር አስተዋውቀው ጋበዙት::በመጨረሻም አንድም ወታደር እንዳይገባበት አድርገው ሀያ ብር ስምንት በሬ ስምንት ላም ሴትና ወንድ ባሪያዎች ሰጥተው አገሩን የሱ ግዛት ጉልት አድርገው ሰጥተው ሰደዱት::ይህም ቴዎድሮስ አስታዋሽ አእምሮና ብድር መላሽ መሆናቸውን ያሳያል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 12:51 pm

በሽፍትነት ዘመናቸው ስማቸውም ካሳ በነበረበት ጊዜ ከወዳጃቸው ከሌላው ሽፍታ ከእንድሪስ ጋር ሆነው አምበለይ ከሚባል ሻንቅላ አገር ዘመቱ::ከዚያም ብዙ ዘረፋ አግኝተው 600 የሚሆን ሻንቅላም ተማረከ::የተዘረፈው ፍየልና በግም ለቁጥር አስቸግሮ ነበር::ይህ ሁሉ ሲሆን ከካሳ በኩል ሁለት ወታደሮች ሻንቅላ ሲያባርሩ በጦር ተወግተው ወድቀው መቅረታቸውን ካሳ ሰሙ::እንደሰሙ ሰባት ያህል አሽከሮቻቸውን አስከትለው ሁለት ወታደሮቻቸው ወደወደቁበት ቦታ ሄዱ::ከቦታውም ሲደርሱ ወታደሮቹ ክፉኛ ተወግተው ወድቀው አገኟቸው::አንዱን የቆሰለ ወታደር አሽከሮቻቸው ሲሸከሙ አንዱን ግን እሳቸው ተሸክመው ይጓዙ ጀመር::በጉዞው ጊዜ ካሳ የተሸከሙት ወታደር ከሚፈሰው ደም ብዛት የተነሳ ደሙ በካሳ ጀርባ እየተንቆረቆረ በእግራቸው እያለፈ ይወርድ ጀመር::አለቃ ዘነበ እንደጻፉት በደም የተበከለው የልጅ ካሳ እግር "....በክረምት እንደሚሄድ ሰው ብዙ ጭቃ አነሳ" ::ካሳ እንዲህ ለፍተው ከሰፈር ያደረሷቸው ሁለቱ ወታደሮች ከሰፈሩ ሲገቡ ሞቱ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 1:05 pm

ወሎ ውስጥ ለጋምቦ ላይ ጮቄ ጮሜ በተባለው ቦታ ሰፍረው ሳለ በአውሮፓ እንደሚዘንበው በረዶ አይነት ወይም እንደአመድ የሚበን በረዶ ዘነበ::ይህም በሰውም በከብቱም ላይ ሁሉ እየወረደ እንደጭቃ እየተመረገ ተቀመጠ::አቅመ ቢሶችና ህመምተኞች በበረዶው ምክንያት ብዙዎቹ ሞቱ::በዚህ ጊዜ ቴዎድሮስ ድንኩዋናቸው ውስጥ ነበሩ::መጠግያ ወይም መከለያ የሌለው ህዝብ በበረዶው መመታቱን ያዩት ቴዎድሮስ ቴዎድሮስ ህዝቡ በእንደዚህ ያለ ስቃይ ላይ ሆኖ እኔ ከድንኮአን ውስጥ ተጠልዬ አልቀመጥም ብለው ከደጅ ወጥተው በረዶው ከሚወርድበት ውስጥ ቆሙ::ሰራዊቱንም እግዚኦ በል ብለው አዘው እግዚኦታው ሲጀመር በረዶው ቆሞ ጸሀይ ወጣ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 8:23 pm

ሳስተውል ዛሬ የጻፍኩትን የመይሳው ካሳን ታሪክ ብዙ ሰዎች እንዳነበቡት አየሁና በጣም ደስ አለኝ::ምንም ቢደክመንም ይበልጥ የሳቸውን ወዳጆች ለማስደሰት ስል የተወሰነ እጽፍላችሁና ወደ ሌላ ሩም የጀመርኩትን ጨዋታ እቀጥላለሁ::

መልካም ንባብ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 8:32 pm

ጭካኔ


አጼ ቴዎድሮስ የበፊት ሚስታቸው እቴጌ ተዋበች ከሞቱ በሁዋላ ጠባያቸው ተለዋዋጭ ጨካኝ ሆኑ የሚሉ አሉ::ፈረንጅ ጸሀፊዎችም መካሪያቸው ጆን ቤል ከሞተ በሁዋላ መካሪ በማጣት የጭካነ ስራ ጀመሩ እያሉ ጽፈዋል::እንደተባለውው የተዋበችና የቤል መሞት ቴዎድሮስን ከብስጭት ላይ ቢጥልም አጠቃሎ የቴዎድሮስን ጸባይ ለወጠ ለማለት አይቻልም::ገና በሽፍትነት ሳሉ በህብረት እየዘረፉኢ አብረው ሊበሉ የተስማሟቸው ሽፍቶች ለየራሳችን ያገኘነውን እንብላ ቢሏቸው ተቆጥተው የተያዙትን ሰባት ሽፍቶች ጉልበት ጉልበታቸውን ቆርጠው ጣሏቸው::ከእንዲህ አይነት ቅጣት መግደል የተሻለ ነው::ከዚያም ሌላ የሱዳን ወዳጃቸውን የእንድሪስን ጠላቶች ድል አድርገው ከማረኩ በሁዋላ የእሳቸው መጨረስ አንሶ 210 ኢትዮዽያዊያኖችን በፈለገህ መንገድ ግደላቸው ብለው ለእንድሪስ ሰጡት::እንድሪስም ሁሉንም በሰይፍ ፈጃቸው::ራሳቸው ከሳም በዚሁ ጊዜ ከተማረኩት ሰዎች መሀከል 50ዎቹን ሁለት ሁለት ጆሯቸውን እያስቆረጡ ግፍ ከሰሩ በሁዋላ ለቀቋቸው::ይህን የመሳሰለውን ቅጣታቸውን ስናይ ቴዎድሮስ ጨካኝነታቸው ከመጀመርያው ጀምሮ እንጂ ከተዋበችና ከቤል መሞት በሁዋላ አይደለም::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 8:47 pm

ወይዘሮ ተዋበችን ካገቡም በሁዋላ ቢሆን ብዙ የጭካኔ ተግባሮችን ፈጽመዋል::ቀኛዝማች ወንድይራድን ራትና ምሳህ ኮሶ ይሁን ብለው በእንስራ ሙሉ የተበጠበጠ ኮሶ ሰጥተው እያጠጡ በጭካኔ የገደሏቸው ወይዘሮ ተዋበች ሳይሞቱ በፊት ነው::ጊምባ ላይ የተማረኩ 47 ኦሮሞዎችን ሁለት ሁለት እጃቸውን እየቆረጡና ቁራጩን አንገታቸው ላይ በገመድ እያሰሩ አገርህ ግባ ብለው የሰደዱት እቴጌ ተዋበችም ቤልም እያሉ ነበር::ይህንን የመሳሰለውን ብዙውን ቅጣት ስናይ ቴዎድሮስ ከተዋበችና ከጆን ቤል ሞት በሁዋላ ጠባያቸው ተለዋወጠ የቢባለው አባባል ትክክል አይመስልም::ምናልባትም ከሁለቱ ሰዎች ሞት በሁዋላ የበለጠ ጨካኝ ሆኑ ቢባል ይሻላል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 8:48 pm

አለቃ ገብረ ስላሴ እንደጻፉት ደግሞ ቴዎድሮስ ጭካኔ ያበዙት የሸዋው ሚኒሊክ ካመለጡ በሁዋላ ነው ይላሉ::ይህንን ሲያብራሩ "....ከእስክንድርያው ሊቀ ዻዻስ አቡነ ቄርሎስ ጋር.....ከእለታት ባንድ ቀን ሲነጋገሩ "አባቴ በሀገርዎ ሳሉ የኔን ወሬ ይሰሙ ኖረዋልን?" ብለው ጠየቋቸው::እሳቸውም "ቸር ነህ,ጀግና ነህ ይሉሀል::ነገር ግን የሸለመውን የሾመውን ያስራል,ይገድላል,ይቆርጣል ይሉሀል::"አሏቸው::አጼ ቴዎድሮስም መለሱ 2በሽፍትነቴ በረሀ ለበረሀ ስሄድ መነኩሴ አገኘሁ::ያም መነኩሴ ትነግሳለህ,ነገር ግን ያሳደከው ሰው ከቤትህ የወጣ ለት መንግስትህ ያጥራል ብሎ ነገረኝ::ይህን የማደርገው ስለዚህ ነው::" አሏቸው::አቡነ ቄርሎስም "እግዚአብሄር የሚያነግሰውን ሸፍኖ ይጠብቀዋል እንጂ አንተ መቼ ታገኘዋለህ"....አሏቸው..." ይላሉ::ይህም እውነት ቢሆን እንኮአ ቴዎድሮስ ጭካኔ የጀመሩት ሚኒሊክ ከመማረካቸው በፊት ገና በሽፍትነት ሳሉ ነው::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 8:55 pm

አንዳንድ ሰዎች ቴዎድሮስ ጨካኝ የሆኑት የአገሪቱን አንድነት ለማስከበር ሲሉ ነው ይላሉ::ይህም እውነት ቢመስልም ህዝብ የሚያብረው በሰላም መንገድ እንጂ በሀይልና በጭካኔ አይደለም::የሀይል ስራ ለጊዜው ላይ ላዩ መልካም ውጤት የሰጠ ቢመስልም ውስጡ ግን የሚያመረቅዝ ነው::ለቴዎድሮስም በሰላም የገቡላቸው ሁሉ የሀይል ስራቸውን በመመልከትና በመስማት ነገ በኔ እያለ ከዳቸው እንጂ ለጥ ሰጥ ብሎ አልተገዛላቸውም::ኢትዮዽያን አንድ አድርጌ እገዛለሁ ያሉት ቴዎድሮስ በመጨረሻው ሰአት የእንግሊዝ ጦር በመጣ ጊዜ ሰላምገ ላይ ሆነው "....ወደአምባው አመልክተው "ግዛቴ ያ ብቻ ነው::ስለዚህ ከዚህ እቆያቸዋለሁ::ከዚያም በሁዋላ እግዚአብሄር ያለው ይሆናል::...."ብለው መናገራቸውን ዶክተር ብላንክ ጽፏል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 9:17 pm

የየቴዎድሮስን አስተዳደር ሁኔታ እያየ ሰራዊቱና መኩዋንቱ ባይከዳቸው ኖሮ የኢትዮዽያ ወሰን ለእንግሊዝ ጦር ክፍት ሊሆን ባልቻለ ነበር::እንግሊዞቹም ቢሆኑ እስረኞቻቸውን ለማስፈታት ለመግባት የደፈሩት የመኩዋንንቱን መለያየት በማየትና ምቹ ክፍት ጎዳና በማግኘታቸው ነው እንጂ በጉልበታቸው ብቻ ተመክተው ቢመጡ ኖሮ ምን አልባትም በኢትዮዽያ ውስጥ የደም መፋሰስ ይደርስ ነበር::ግን የሁሉም በቲዎድሮስ ላይ ማደምና የሁሉም መከፋፈል የቴዎድሮስን መንግስት አዳከመ::ዶክተር ብላንክ ሲጽፍ "...አጤ ቴዎድሮስ ከጥቂት ወራት በፊት ይገዙት የነበረው ግዛት ሁሉ ቀረና በጣም ትንሽ እርሱዋንም ሊከላከሏት የማይችሏት መሬት ቀረቻቸው::በሰነ ወር 1859 አ.ም ያለ ግዛት ንጉስ,ያለ ጦር ሰራዊት ጀነራል ሆኑ::መቅደላና ዙር አምባ በርሳቸው ወታደሮች እንደተጠበቁ ነበሩ::ከነዚህም ቦታዎች በስተቀር ግን የኔ ነው የሚሉት አንድም ቦታ አልቀረ..."ብሏል::ያኔ በቴዎድሮስ ጎን ጥሩ አማካሪዎች ቢኖሩና ቴዎድሮስም ተቀባይ ቢሆኑ ኖሮ የቴዎድሮስ መንግስት ቶሎ ለመውደቅና በየጊዜው ከመዋጋት ባልደረሱ ነበር::ነገር ግን ዙሪያቸውን የከበቡዋቸው ወዳጆቼ የሚሉዋቸው ሁሉ የእለት ጥቅማቸውን ፈላጊዎችና መስሎ አዳሪዎች በመሆናቸው ለቴዎድሮስ አወዳደቅ መሰላል ዘርጣጮች ሆኑ::ቴዎድሮስም ቢሆኑ "የሚጠሉህን ሰዎች ከማጥፋት ይልቅ የሚጠሉብህን ነገር አጥፋ"የሚለውን የምስራቂያዊያንን ምክር አልተከተሉም::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests