ከኔም ከነሱም...(አጤ ቴዎድሮስና እሳቸውነታቸው..)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 9:17 pm

ግራዝማች አለሜ የሸፈቱ ጊዜ አንዱ አሽከራቸው ተይዞ መጣ::ከንጉሱ ችሎት በቀረበ ጊዜም ቴዎድሮስ የሞት ፍርድ ካስፈረዱበት በሁዋላ "...መቅደላ,ወረሂመኑ,ደላንቴ,ዳወንቴ,ዋደሌ ጦርህን ከዚህ ሰው ደም ያላስነካህ ጠላቴ ነህ...."ብለው በመናገራቸው ያ ሁሉ ህዝብ በንጉሱ ትእዛዝ መሰረት ሁሉም በጦር ሲወጋው ብትንትኑ ወጥቶ ለምልክት እንኳን የሚታይ ስጋው ከመሬት ላይ ጠፋ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Tue May 20, 2008 9:17 pm

አለቃ ወልደማርያም እንደጻፉት ደግሞ ቲዝባ ከሚባለው አገር ህዝብ መሀል ጥቂቶቹ ከቴዎድሮስ ዘንድ ቀርበው "ጃንሆይ ሁሉንም እንደአባትህ እደር ብለውታል::እኛም ያባታችን ም,አደርያ ሌሊት ገስግሰን በረት ከፍተን ላም ነድተን ሰው ሲተኛ ግድግዳ ምሰን ያገኘነውን ወስደን እንኖራለንና ይሄው ይፈቀድልን ብለው አመለከቱ::ቴዎድሮስም "አሁን ያላችሁት ጥቂቶቹ ናችሁና ሁላችሁም አንድ ሆናችሁ ነገሩኝ" ብለው በቀጠሮ መለሷቸው::በቀጠሮው ቀን ሽማግሌና ህጻኑ ሁሉ ሳይቀር ህዝቡ በሙሉ መጣ::ቴዎድሮስም በለው ብለው ሲያዙ ወታደሩ ያንን ሁሉ ህዝብ በጦርና በጎራዴ ፈጀው::በፊት የቀረቡት ተንኮለኞች ወይም አላጋጮች ብቻ መቀጣት ሲገባቸው ምንም የማያውቀውን ባላገር ሁሉ በማስጎምጀት አሰብስበው ማስፈጀቱ መልካም ድርጊት አልነበረም::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu May 22, 2008 9:34 pm

ሰላም ለዚህ ሩም ታዳሚዎችና ለመይሳው ካሳ ለጀግኖቹ ጀግና የኢምዬ ኢትዮዽያ አንድነት መሰረት ወዳጆች ለሆናችሁ ይሁን::
ሰላም በፕራይቬት መልክት የተለዋወጥነው እህቴ ይሁንልሽ እንዲሁም ለጉዋደኖችች በሙሉ::የስሜትሽን ነግረሽኛል...መክረሽኛል...እቀበላለሁ...አመሰግናለሁም::ስለ ሉሲና ስለ አባ ታጠቅ በጉደኛው እንደምትከታተይና ጓደኞችሽም በጉጉት እንደሚከታተሉ አንታካራውን አቁሜ ወደጽሁፎቹ እንዳተኩር መክረሽኛል ...ነግረሽኛል...ሰው በፍጹምነቱ አልተፈጠረምና እንዲሁም ስለማይኖር ላደርገው በተፈጥሮ ብሸነፍም እንደሚቻል እያመዛዘንኩ ሁሉንም ከእግዚአብሄር ጋ አደርገዋለውና ማለቴ የወባ ትንኞችን የሰውን አካል እንዳይመጠምጡ ዲዲቲ እየነፋሁባቸው ለጨዋዎቹ ደግሞ ያነበብኩትን ያለኝን የራሴንም ጭምር እያካፈልኩ ለመሄድ እሞክራለሁ::ለዛሬው በገባሁልሽ የስጦታ ቃል መሰረት ስለ መይሳው ካሳ ከቆምኩበት ልጀምር::ጓደኞችሽንም ሰላም በይልኝ::ስለ ኢትዮዽያ ካንቺ ጋር አብረው እንዲጸልዩ ንገሪልኝ::ኢትዮዽያ ጸሎት ያስፈልጋታል::ድንበርዋን የሚያስከብርላት,አንድ አድርጎ የሚገዛት,ስለህዝቦችዋ የሚጨነቅ ለሆዱ የማያስብ መሪና አስተዳዳሪ ያስፈልጋታል::

በይ ወደ አባ ታጠቅ ጭካኔ ከቆምኩበት ልቀጥል::

መልካም የንባብ ጊዜ...

ሾተል...የአባ ታጠቅ የዘር ግንድ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu May 22, 2008 9:57 pm

ደጃጅ ተድላ ጓሉን ለመያዝ አጤ ቴዎድሮስ ገስግሰው በድንገት ደርሰው በተዋጉ ጊዜ ስምንት ሺህ ሰዎችን ማረኩ::ይህንን ሁሉ ምርኮኛ እንጅባራ ላይ ሰብስበው ራሱን ሲያስቆርጡ ውለው ጊዜው ሲመሽ የተረፈው ሰው ተቆጥሮ አደረ::ሲነጋጋ ንጉሱ ተነስተው ያደሩትን ሰዎች አምጣ ብለው አስቀርበው ሁሉንም አስደብድበው ፈጁት::ያንን ሁሉ ክምር ሬሳ እየተዘዋወሩ ሲያዩ ከሬሳዎቹ መሀል አንዱ አልሞተ ኖሮ ሲንፈራገጥ አዩት::ቴዎድሮስም ሳትገሉት ነው የጣላችሁዋቸው ብለው ያ የሚንፈራገጠውን እራሳቸው ገድለውሌላው ሁሉ እየታየ ያልሞተው ሁሉ እንዲገደል አዘዙ::ሁሉም ካለቀ በሁዋላ "ይህን ሁሉ ጠላቴን በጄ ጥሎ እንዲህ አስተኝቶ ያሳየኝ እግዚአብሄር ይመስገን " ብለው መሬት ስመው ከድንኳናቸው ገቡ::አልቃሽም

"አንጥረኛው ብዙ ከንጉሱ ቤት
ባል አልቦ አደረጉት ይህን ሁሉ ሴት "ብላ አለቀሰች::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu May 22, 2008 10:03 pm

በ1859 አ.ም የአማራ ሳይንት ሰዎች ሊከዱ ነው ብለው ስለነገሩዋቸው ቴዎድሮስ ከአማራ ሳይንት መኳንንት 40 ሰዎች አስይዘው ሁሉንም በጎራዴ አስደብድበው ፈጇቸው::አንድ ሰው ከዋድላ ሰዎች ጋ ቢጣላ ከቴዎድሮስ ዘንድ መጥቶ ዋድሎች ሊከዱዎት ነው ብሎ ነገራቸው::ቴዎድሮስም "ለዋድላ ሰዎች ገንዘብ እሰጣለሁና ሁሉም ተሰብስቦ ይምጣ " ብለው አዋጅ አስነገሩ::ይህንንም አዋጅ የሰማው ህዝብ እረኛ እንኩዋን ሳይቀር በሙሉ ተሰብስቦ መጣ::አጤ ቴዎድሮስም በራስ አዲሉ የሚመራውን የየጁን ጦር ዙሪያውን አስከብበው ስድስት መቶ ሰዎችን በጎራዴ አስደብድበው ፈጇቸው::ይህን የግፍ አገዳደል ያዩት ራስ አዲሉ ለሊቱን አምልጠው መሸፈታቸውን አለቃ ተክለ እየሱስ ጽፈዋል::ከአለቃ መጽሀፍ ሌላም እናነባለን::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu May 22, 2008 10:05 pm

የሜጫና የአገው ሰዎች ሊሸፍቱ ነው ብሎ አሳባቂ ነገራቸው::ቴዎድሮስም አራት መቶ የሜጫና የአገው መኳንንት ሰብስበው ዙሪያውን በሾህ አጥር አጥረው ሱሪ ብቻ እያስታጠቁ እራቁታቸውን እንደከብት አጎሯቸው::እህልና ውሀም እንዳይሰጣቸው አዘዙ::በርሀብና ውሀ ጥም የሚሰቃየው ህዝብም ከአስር ቀን በሁዋላ መሞት ጀመሩ::በ 15ተኛው ቀን ግን ሁሉም በረሀብና በውሀ ጥም አለቁ::ወሰን ቢሰውር የሚባሉት የሜጫ መኮንንም "ጃንሆይ አምስት መቶ ብር ልክፈልና አንድ ዋንጫ ውሀ የሰጠኝ "ቢሏቸው ቴዎድሮስም ሰምተው ዝም ብለውት አለፉ::ወሰን ቢሰውር ከሞተም በሁዋላ ሚስትየዋ

"ጌታ የጌታው ልጅ ወሰን ቢሰውር
ውሀ ልግዛ ይላል ባምስት መቶ ብር "ብላ ገጠመች::

ጤዎድሮስ ቃሮዳ ከሚባል አገር ሄዱ::ቃሮዳ በአትክልት አብቃይነቱ በተለይ በወይን ሰብል የታወቀ አገር ነበር::ቴዎድሮስ ቃሮዳ እንደደረሱ ህዝቡን ሰብስቡልኝ ብለው ህጻናት ሳይቀሩ 1700 ሰዎች ተሰበሰቡ::ይህን ሁሉ ሰው ቤት እስከቻለ በየቤቱ እያስገቡ ሁሉንም በእሳት እያቃጠሉ መጨረሳቸውን ወልደ ማርያም ጽፈዋል::ሌላም አለ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu May 22, 2008 10:08 pm

ማህደረ ማርያም በወረዱ ጊዜ ካህናቱ ንጉሱን ለመቀበል ከለቻ ክሚባል ቦታ ላይ ቆመው በጸናጽልና በከበሮ እያመሰገኑ አቀባበል አደረጉላቸው::ይህን ያዩት ቴዎድሮስ በልልኝ ብለው ወታደሩን አዘው 450 ካህናት በጎራዴ ተደብድቦ አለቀ::ከዚያም ተመልሰው ደብረ ታቦር በወጡ ጊዜ ከርብ ጀምሮ እስከ ፍርቃ በር ወታደራቸውን አሰማርተው ሲቆፍርም በመንገድ ሲሄድም የተገኘውን ሁሉ 7700 ሰዎችን አሰበሰቡ::ይህን ሁሉ ሰብስበው በየቤቱ ውስጥ እያጎሩ የታጎሩበትን ቤት በማቃጠል ሲያስፈጁዋቸው ዋሉ::ሰው ተቃጥሎ ሲያልቅ ጊዜው ስለመሸ ተራፊውን ከሜዳ ላይ እየጠበቀ እራቁታቸውን እንዲያድሩ አዘዙ::ለሊቱንም ዝናብ ስለዘነበ ህጻናትና እመጫት ሳይቀሩ በዝናብ ሲደበደቡ አደሩ::በማግስቱ ቴዎድሮስ ያደረውን ህዝብ ለማቃጠል መጥተው ሰው ከሚቃጠልበት ቤት እየተከፈለ ሲገባ አንድ የአምስት አመት ልጅ እናቱን እየጎተተ "ነይ እንደትናንቱ ዝናብ እንዳይመታን ቶሎ ከቤት እንግባ "እያለ ሲያለቅስ እናቱም ስታለቅስ ቴዎድሮስ አይተው "ለምን ያለቅሳሉ ?" ብለው ጠየቁ::ልጁ የተናገረውን ቢነግሯቸው "ፈጣሪዬ ምነው እንዲህ ታደርገኛለህ:.ወይ እኔን ቶሎ ግደልና ፍጥረትህ ይረፍ ብለው አልቅሰው ሊቃጠሉ የቀረቡትን ሁሉ ማሩት::ይህ ከሆነ በሁዋላ ጣና ህይቅ ውስጥ ከምትገኘው ምጽርሀ ወደምትባለው ደሴት ሄደው በደሴቲቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች በሙሉ በቤት ውስጥ እያስገቡ ቤቱን በማቃጠል ጨረሱት::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu May 22, 2008 10:24 pm

ዶክተር ብላንክስለቴዎድሮስ የጭካኔ ተግባር ጽፈው አቶ ዳኜ ከተረጎሙት ብንመለከት "ህዳር 21 ቀን 1859 አ.ም ከሰአት በሗላ አጼ ቴዎድሮስ የተመረጡ ጥቂት ፈረሰኛና እግረኛ ወታደሮች አስከትለው ጎንደርና ከጎንደር ግምብ ውስጥ እየተደበቁ የሚያስቸግሯቸውን ሽፍቶች ለማጥፋት መገስገስ ጀምረው አስራ ስድስት ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሰማንያ ማይልስ ርቀት ያለውን ጎዳና አንድ ጊዜ ስንኳ ሳይቆሙ ሲጉዋዙ አድረው ወገግ ሲል የጎንደር ከተማ ከሚገኝበት ተራራ ስር ደረሱ::ምንም እንኳን በድንገት ለመድረስ አቅደው የመጡ ቢሆንም የጎንደር ነዋሪ ህዝብ ወሬውን ሰምቶ ስለነበረ በመጨነቅና በመሸበር ወጥተው በእልልታና በደስታ ሲቀበሏቸው በፋሲል ግምብ ውስጥ ተሰግስጎ የነበረው ሽፍታ ሸሽቶ ከጎንደር ወጣ::ወድያውም ሽፍቶቹን ለማግኘት ሰራዊቱ ቤቱንና ቤተክርስቲያኑንም ሳይቀር በመበርበር መዝረፍ ያዘ::ዳሩ ግን ሽፍቶቹ ባለመገኘታቸው ከ 10,000 በላይ የሆነውን የከተማውን ነዋሪ ህዝብ እንደከብት ሰብስበው ነዱት::ከዚህም በሗላ የጥፋት ስራቸውን ጀምረው ህዝቡን ቤቱን ቤተክርስቲያኑንና ቤተመንግስቱንም ጭምር በእሳት አቃጠሉት::ከቀሳውስት መካከል አንዳንዶች የደፈሩ አጉረምርመው የንጉሰ ነገስቱን አፈጻጸም በግልጽ ተቃውመው ስላወገዙ ብዙ መቶ ሽማግሌ ቀሳውስት ወደ እሳቱ ተወርውረው ተቃጠሉ::የማቃጠሉ ነገር ከዚህ ላይ ሳይቆም "እልል እያሉ የተቀበሉት ሴቶችስ የታሉ እነርሱ እልል ባይሉ ኖሮ ሽፍቶቹ መምጣታችንን የት ያውቁ ነበር?"በማለት ሴቶቹ ሁሉ ተይዘው እንዲመጡ አጤ ቴዎድሮስ በማዘዛቸው ሁሉም ከነህይወታቸው ወደተቃጠለው ቤት እየተወረወሩ ነደዱ::...."ብለዋል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu May 22, 2008 10:42 pm

ይህን የመሳሰለውን የቴዎድሮስን የጭካኔ አስተዳደር ስንመለከት ቴዎድሮስ ጠላት ሳይኖርባቸው በራሳቸው ላይ ጠላት የሚፈጥሩና የሚያበዙ ሰው ነበሩ::ብዙ ጸሀፊዎች እንደጻፉት ቴዎድሮስ የሚፈጽሙት የጭካነ ተግባር ሁሉ በትክክል የተፈጸመ ትክክለኛ ተግባር ይመስላቸው ነበር::ሲናገሩም "ለአገሬ እድገት ብዬ ነው::" ይሉ ነበር::ወዳጃቸው ፕላውዲን እንደጻፈው "....ባንድ አጋጣሚ ንጉስ ሲያጫውቱኝ "አንተና ቤል ብቻ ትወዱኛላችሁ::አበሾች ግን የሚገዙት በእግዚአብሄር ፈቃድ ነው::ግን ገና ብዙ የምሰራው አለ::ዛሬ ማታ ብሞት ወይም ብመነኩስ እንኩዋን ይህ የሚሆነው በእግዚአብሄር ፈቃድ ነው::በዚህ ቤት ሙሉ ወርቅ ብጸጠኝ ጥቅሙ ምንድነው?እምመኘው ጥበብን ነው::ቅጣት የማበዛውም አገሬ በስራት እንድትተዳደር ለማድረግ ነው::...ለእነ ለአንድ ድሀ ይህን ዙፋን የሰጠኝ እግዚአብሄር ጥበብን ደግሞ ይስጠኝ"አሉ::..." ብሏል::ቴዎድሮስ በንዴት ወይም በሌላ ጊዜ የጭካነ ተግባራቸውን ይፈጽሙ እንጂ በጥሞናው ጊዜ ባለፈው ተግባራቸው ይጸጸቱ እንደነበር ብዙዎች ጽፈዋል::ብዙ ንጹሀን ሰዎች ፈጅተው ከጨረሱ በሗላ "እኔን ግደለኝና ሰራዊትህ ይረፍ"እያሉ ይጸልዩ ነበር::ፕላውዲንም "...ባንድ አጋጣሚ ደግሞ እንደሚወዱኝ ነግረውኝ እግዚአብሄር ጥሩ ልብ እንዲሰጣቸው እንድጸልይላቸው ለመኑኝ..."ይላል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu May 22, 2008 10:58 pm

አጤ ቴዎድሮስ ሁሉን ነገር በሀይል አስፈጽማለሁ ወይም በሀይል ስራ ጸጥታውን አስከብራለሁ እያሉ ነገሩን ሁሉ አበላሹት እንጂ ለአገራቸው ፈጣን እድገት አሳቢና ለስራውም ታታሪ ነበሩ::በተለይም የወይዘሮ የተመኙን ቁባት ካስቀመጡ በሗላ ከወይዘሮ የተመኙ ዘንድ እየቆዩ ብዙ አረቄ መጠጣት ስላበዙ በሞቅታ በሚሰጡት ፍርድና ተፈጻሚነት ጠላታቸው እየበዛ ሄደ::ይህ ባይሆንና ቴዎድሮስ ሁሉንም ነገር በጥሞና ነገር በመቻልና በማሳለፍ አገሪቱን ቢመሩ ኖሮ ለአገሪቱ የፈለጉት እድገትና ስልጠና ሁሉ በሰላም በተከናወነላቸው ነበር::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Thu May 22, 2008 11:14 pm

ፍርድቴዎድሮስ ከነገሱ በሗላ በ 1846 አ.ም ደብረ ወርቅ ላይ ሰፍረው ሳለ ሁለት ሰዎች ተከሰው ለፍርድ ቀረቡላቸው::ከሳች ሹምዬ ጃሎ ሲባል ተከሳሽ ደግሞ ጠቦ ወልደሚካኤል ይባላል::ሹምዬ ጃሎ አንድ ፈረስ ለጠቦ ሰጥቶታል::ሹምዬ ጃሎ የራስ አሊ አሽከር ነበርና ከራስ አሊ ጋር ሆኖ ካሳን የወጋ ሰው ነበር::አሊ ድል ሲሆኑ ሰዋቸው ሲዘረፍ ሹምዬም ልብሱን ሳይቀር ተገፎ ከባድ ድህነት ላይ ወደቀ::ሀብት ባለው ጊዜ ፈረስ ከሰጠው ወዳጁ ከጠቦ ዘንድ ሄዶ እባክህ ልብሴን የምገዛበት አንድ ብር ስጠኝ ብሎ ለመነው::ጠቦም አልሰጥህም አለው::ውለታውን ቆጥሮ ቢለምነው እምቢ አለ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri May 23, 2008 12:37 am

ከዚህ በሗላ አቶ ሹምዬ የደህና ቀን ወዳጁን ጠቦን ከስሶ ከቴዎድሮስ ዘንድ አቀረበው::ከዚያም ቀርበው ሲሟገቱ ሹምየ በደህናው ቀን ፈረስ መስጠቱን አመልክቶ አሁን ተዘርፎ ድህነት ሲጫነው ለልብስ መግዣ አንድ ብር ቢለምነው እምቢ ማለቱን አመለከተ::ጠቦ ወልደሚካኤልም ነገሩን ሸፈጠና ፈረስ አልሰጠኝም ብሎ ካደ::ሹምዬ ጃሎ ሲመልስ "ፈረስ ለመስጠቴ ምስክር አለኝ::ምስክረም እግዚአብሄር ነውና እግዚአብሄርን ምስክር እጠራብሀለሁ"አለው::የዚህ ጊዜ ጠቦ ወልደሚካኤል ደነገጠና "እግዚአብሄርን ምስክር ከጠራኽስ አዎን ሰጥተኸኛል" ብሎ አመነ::ይህን እግዚአብሄርን መፍራቱን የሰሙት ቴዎድሮስ "እግዚአብሄርን ፈርተህ እውነቱን ስለተናገርህ እኔ እከፍልሀለሁ::"ብለው ለሹምዬ ጃሎ አስር ብር አንድ ፈረስ አንድ በቅሎ ሰጥተው ገላገሏቸው::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri May 23, 2008 12:42 am

ቴዎድሮስ ጋይንት ላይ ሰፍረው ሳለ ወታደሮቻቸውን በባላገሩ ላይ ተሰሪ አገቡ::ባላገሩ እንዲቀልብ በየቤቱ ማስገባት ማለት ነው::ተሰሪ ከገቡት ወታደሮች ማህል አንዱ ወታደር አንዱን ባላገር ገደለው::የሟች ወገንም ከቴዎድሮስ ዘንድ መጥቶ አመለከተ::ቴዎድሮስም ወታደራቸውን ሁሉ አፈርሳታ አስቀምጠው ገዳዩን አውጣ ብለው ያዙ::ወታደሩም በመላው አድሞ ገዳዩን አላየንም እያለ በቄስ እየተገዘተ ወጣ::የሟች ገዳይ ወታደር በመጥፋቱ ቴዎድርሶ ተናደው "ወታደር ብላ,ባላገር አብላ ያልሁ እኔ ነኝ::ደመኛህም እኔ ነኝና እኔን ግደል " ብለው ተነስተው ለከሳሹ ነገሩት::ከሳሹም "እነ ንጉስ መግደል አይቻለኝም" አለ::ቴዎድሮስም እንግዲያውስ ደም በከንቱ አይቀርም ብለው ለሟቹ ወገን የደም ገንዘብ ዋጋ ሰጥተው ሸኙት::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri May 23, 2008 6:26 pm

Image

አቶ ገሪማ ታፈረ አንዳንድ የቴዎድሮስን ፍርዶች ጽፈዋል::አንድ ጊዜ ቴዎድሮስ አንድ ታማኝ ወታደራቸውን ጠርተው "በፍርቃ በር በኩል እርጉዝ ሴት እንኳን ብትሆነንዳታልፍ ጠንክረህ ጠብቅ " ብለው አዘዙት::በሌላ ቀን ደግሞ ሌላውን ወታደር ጠርተው "ፈረስ እያለዋወጥህ ይህን ወረቀት የጁ ሰጥተህ ባስቸኳይ በስድስት ቀን ውስጥ ተመልሰህ እንድትመጣ ብለው ላኩት::ይህን የታዘዘ ወታደር በፈረስ እየጋለበ ሄዶ ፍርቃ በር ደረሰ::የፍርቃ በሩ ጠባቂ ዘበኛ አታልፍም ብሎ ከለከለው::የተላከው ወታደር ደግሞ "ከኑጉሱ ተልከ ነው በስድስት ቀንም የጁ ደርሼ እንድመለስ ባስቸኳይ ጉዳይ ልከውኛልና ልለፍ"አለ::ዘበኛውም "ከተላክህ አትከልክሉት የሚል ማህተም እንዳለኽ አሳየኝና ታልፋለኽ እንጂ ያለዚያ አታልፍም"ብሎ ከለከለው::የተላከው ወታደር በግዴታ አልፋለሁ ብሎ መንገድ ሲጀምር ዘበኛው ጥይት ተኩሶ ገደለው::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri May 23, 2008 6:45 pm

የሟች ወገኖች የንጉሱ መልክተኛ ወንድማቸው ንጉሱ ልከውት ሲሄድ በመገደሉ ጉዳዩን ከስሰው ቴዎድሮስ ዘንድ አቀረቡት::ቴዎድሮስም ችሎት አስችለው ፍርድ እንዲፈረድ አደረጉ::በችሎቱ ላይ የተቀመጠው ፈራጅ ሁሉ እየተነሳ ጉዳዩም "በደለኛ ነህ::እምቢ አልፋለሁ ቢልህስ ለንጉስ ታሰማ ነበር እንጂ ራስህ ፈርደህ እንዴት የንጉስ መልክተኛ ትገላለህ? አሁንም ስትሞት ይታየናል" እያሉ ፈረዱ::አንድ ፈራጅ ግን ከተቀመጡበት ተነስተው "....ማየት የሚገባን በመጀመርያ ከንጉሱ የተሰጠውን ትእዛዝ ነው::አንዱን ጠርቶ በዚህ በር ያለኔ ፈቃድ ወንድ ይቅርና የጸነሰች ሴትም ብትሆን እንዳታልፍ ብሎ ማዘዝ;እንደገና ሁለተኛን ወታደር ጠርቶ ቀንና ለሊት ሳታርፍ በስድስት ቀን የጁ ደርሰህ እንድትመለስ ብሎ ማዘዝ አግባብ ስላልሆነ ጥፋቱ የሚመለከተው ንጉስ ነገስቱን ነው::ነገር ግን ብርሀን ናቸውና ምን ይደረግ" ብለው ተቀመጡ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests