የዋናው አጫጭር ልቦለዶች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ስርርር » Mon Apr 26, 2010 7:02 pm

ሰዎች...እንዴት ነው አላስፈቀድክም...ዘው ብለህ ገባህ ምናምን...ማለት? ገና እዚህ ቤት ስገባ እኮ እንዲህ ብዬ ነው የገባሁት

ስርርር wrote:ድንቅ ድርሰት ነው! እኛም ከተፈቀደልን ለመፃፍ ቃል እንገባለን::


ዋርካ ደግሞ የሁሉም ናት:: ስለዚህ ባትሰስቱ ጥሩ ነው:: ይበቃናል::

ደራሲ ስርርር
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

ዋጋዬና አክንባሎ ሰባሪዬ

Postby ስርርር » Mon Apr 26, 2010 11:23 pm

አክንባሎ ሰባሪዬ

የመስሪያ ቤቴ ዋና ማናጀር ሆኘ ከተሾምኩኝ እነሆ ሶስት ዓመት ሆነኝ:: በብቃት በቅቼ አልነበረም:: ግን ህይወት ራሷ እየመራች ያደረሰችኝ ቦታ ነው::

የዛሬ 5 አመት አካባቢ እዚሁ መስርያ ቤት በዋና ፀሀፊነት ሳገለግል ሳለ አሁን የያዝኩትን ቦታ ይዞ የነበረው ኦኬሎ የሚባል የጋምቤላ አካባቢ ምሁር ነበር:: በስራው ህፀፅ የሌለበት ሊቅ ነበር:: አንድ ፋይል የሱ ጠረጴዛ ላይ አታድርም:: አምሽቶም ቢሆን ፈርሞበት, አፅድቆ, የውሳኔ ሀሳብ ሰጥቶ, ወስኖ, የመስሪያቤቱን መሪ እቅድ ብቻውን አውጥቶ.....ብቻ ምን አለፋችሁ ድንቅና ውጤታማ አስተዳዳሪ ነበር:: በፀሀፊነቴ (የሱ ፀሀፊ ሆኘ) ከሱ ብዙ ነገሮችን ተምሬያልሁ:: እንዲያው በደፈናው ብዙ ነገሮችን:: ያን ግዜ እልልታ (ልጄ) ተወልዳ የ 8 ወር አካባቢ ነበረች:: ባለቤቴ ብዙ ግዜ በስራ ምክንያት ወደተለያዩ ክፍላተሀገራት ስለሚሄድ የብቸኝነት ኑሮ ያነጫንጨኝ ነበር:: አንድም ቀን ታድያ የኦኬሎን ትዛዛት ከመፈፀም ወደህዋላ ብዬ አላውቅም:: ምሁር ነዋ:: እሱም ያዝንልኛል:: ፍቃድ ብጠይቀውም እምቢ አይለኝም::

ቀኑ አርብ ነበር:: ከቀኑ 10 ስዓት:: ሚያዝያ 18 ቀን:: ኦኬሎ በውስጥ ስልክ ደውሎ ብዙ ስራ ስላለ ማምሸት እንዳለብኝ እና ከኔ ሌላ ማንም ሊያግዘው የሚችል እንደሌለ ነገረኝ::

ወይኔ ልጅት! እልልታ አሳዘነችኝ:: አባቷ እንድተለመደው ክ/ሀገር ነው:: አለቃየን ደሞ እምቢ ማለት አልችልም:: ለማንኛውም ለሰራተኛዬ ደውዬ ነገሬያት ስራዬን ቀጠልኩ:: ያለወትሮየ ልቤ ፈራ ፈራ ይል ነበር:: ከባለቤቴ ውጭ ለማንም ወንድ ወጥቼ አላውቅም::

ኦኬሎ ብዙ ፋይሎችን ከምሮ ወደኮምፒተር ያስገባል:: ከእኩል በላይ የሚሆነውን ወስጀ እኔም ወደኮምፒተር እያስገባሁ ነበር:: ከምሽቱ 2:17 ሲል ሁሉን ነገር ጨርሼ በ MS Office Outlook ኢሜል አረኩለት:: ከጥቂት ደቂቃዎች በህዋላ በስልክ ጠራኝ:: እየተነጫነጭኩና የልጅ እናት መሆኔን....ወደቤት መሄድ እንዳለብኝ እንደምነግረው እያሰብኩኝ ወደቢሮው ገባሁ::

"ስራችንን ጨርሰናል!" አለኝ ፈገግ እያለ:: ከጥቁር ፊቱ ውስጥ ብልጭ የሚሉት ነጭ ጥርሶቹ ልብ ያማልላሉ::
ብድግ ብሎ መጥቶ ግምባሬን ሳመኝ:: እኔም ተሳምኩኝ:: ዝቅ ብሎ ጉንጨን, ከንፈሬን....መጠመጠኝ::
ህሊናየ አልፎ አልፎ "ተይ" ቢለኝም አካሌ ሙሉ በሙሉ ፈቃደኛ ነበር:: It has been a long time. ምን ማለታችሁ ነው:: እልልታ ከተወለደች ግዜ ጀምሮ ባለቤቴ አድርጎኝ አያውቅም:: አክንባሎውም አልተሰበረም::

ልብሴና አንድ ባንድ ከላየ አወላልቆ የሱን ማውለቅ ሲጀምር ስሜቴ ጣርያ ነካ:: ሳላስበው ትርጉሙን በማላውቀው ንግግር እለፈልፍ ነበር:: የተለበለበ ግንድ የሚመስለው አካሉ, ወንዳወንድ ግርማው, ቁመቱ, የደረቱ ስፋት.....ኡኡኡኡ! ከዚያማ...የፖሊስ ቆመጥ በሚያህለውን እንትኑ ልቤ እስኪጠፋ አደረገኝ:: አክንባሎዬንም ሰበረው!!! ሲጨርስ ያለኝን እስካሁን አልረሳውም
"ጭገርሽን በጣም ነው የወደድኩት!"

በማግስቱ ድንግልናዋ እንደተወሰደባት ልጃገረድ መራመድ ሲያቅተኝ, ደውዬለት አልመጣም አልኩት:: በሶስተኛው ቀን ቢሮዬ ስገባ..... በቦታዬ ሌላ ፀሀፊ ተቀምጣለች::

ከወደግራዬ በኩል አይኔን ወርወር ሳደርግ....የመስሪያ ቤቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆኘ መሾሜን የሚገልጥ ፅሁፍ አየሁ:: ዋጋዬ!!!

ኦኬሎ መ/ቤቱን እስኪለቅ ድረስ ሳላናግረው ወደሌላ መ/ቤት ተዛወረ:: እኔም አክንባሎዬ የተሰበረበትን ቢሮ ይዥ ይህው አለሁ:: ዛሬ ታድያ ዝክር ነው:: ሚያዝያ 18:: ለሱ መታሰቢያ ሁልግዜ ለአንድ ወር ያህል ጭገሬን አሳድግና ሚያዝያ 18 እላጨዋለሁ::

አክንባሎ ሰባሪዬ የት እንዳለ አላውቅም!
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ኤስመር » Tue Apr 27, 2010 1:44 pm

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ስለ ጭ** የመተረክ ፍቅርህ ማለቅያ የለውም :!:
.........................................................................
Opinions are like assholes... everybody's got one, and they're often full of shit. :D (from some forum)
.......................................................................
ኤስመር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 95
Joined: Sat Jan 23, 2010 10:17 pm
Location: ኤድሪያን ሲቲ (somewhere in estern Europe!)

Postby ስርርር » Tue Apr 27, 2010 5:30 pm

:D :D :D Thanks Asemer. It seems like you are my only reader. So, am takin it to my own place, so everyone reads my writings. በውነት በጣም ነው የማመሰግንክ!~
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ኤስመር » Wed Apr 28, 2010 12:16 am

ዋናው እዚህ ቤትህ ላይ ዝባዝንኬ አስተያየቶች አበዛነው መሰለኝ... ይቅርታ እንጠይቅና ... አስፈላጊ ከሆነም... ለመደለት(delete ለማረግ) ..ዝግጁ ነን እንላለን::
.........................................................................
Opinions are like assholes... everybody's got one, and they're often full of shit. :D (from some forum)
.......................................................................
ኤስመር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 95
Joined: Sat Jan 23, 2010 10:17 pm
Location: ኤድሪያን ሲቲ (somewhere in estern Europe!)

Postby ዋናው » Wed Apr 28, 2010 11:47 am

ኤስመር wrote:ዋናው እዚህ ቤትህ ላይ ዝባዝንኬ አስተያየቶች አበዛነው መሰለኝ... ይቅርታ እንጠይቅና ... አስፈላጊ ከሆነም... ለመደለት(delete ለማረግ) ..ዝግጁ ነን እንላለን::

ኤስመር ምንም ችግር የለዉም ዳሩ ድረ-ገፅ ላይ መፃፉ ከጋዜጣና ከመፅሔት ልዩነቱ ታዲያ ምንድነው? ሃሳብ አስተያየት እያሰናዘሩ የፅሁፉን ይዘት መቦርቀቅ አይደል... ቢያንስ እቺ ቤት አንድ ሠው አነሳስታ አይተናታል... ይሄ'ኮ ነው የዋርካ ጥቅም:
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

የአማርኛ አስተማሪያችን

Postby ዋናው » Thu Jul 14, 2011 1:12 amየአማርኛ አስተማሪያችን


አማርኛ አስተማሪያችን እግራቸው አንካሳ ነው በዚህ ላይ ቁመታቸው በጣም አጭር ነበር:: አንድ አገጫቸውም በአጭሩና ቆልማማ እግራቸው በኩል የተጣመመ ነው ከመአል ግምባራቸው ተነስቶ በሰያፍ ወደተጣመመው አገጫቸው የተጋደመ ትልቅ ጠባሳቸው አንዳች የማስፈራት መልክ አላብሷቸዋል:: ልጅ ሆኜ ሳስበው እግዚያብሔር ስናስቸግረው እኛን ለመቅጣት ብሎ እሳቸዉን ከሰማይ ባንድ ጎናቸው በንዴት የወረወራቸው ይመስለኛል:: ሲራመዱ ተወላድግዶና አጥሮ ወደጎን እንደመታጠፍ ያለው እግራቸውን እንደምርኩዝ ሰውነታቸዉን ስለሚጥሉበት ከሩቅ ሲመጡ ስናያቸው እንደመኪና መስታወት ዝናብ መጥረጊያ ግራና ቀኝ እየተማቱ ነው::
እሳቸው ገብተው በአጭር ቁመታቸው ተንጠራርተው "የደብተር ፍተሻ" ብለው የጻፉ ቀን ክፍላቸን ይንቀጠቀጣል እኛን መግረፍ እንዳማራቸው ስለምናውቅ መግቢያ መውጪያ እናጣለን:: መጀመሪያ የፊተኛ ዴስክ ላይ ያሉትን ተማሪ ያስነሱና ዴስኩ ላይ ቁጢጥ ብለው ጤነኛና ቆልማማ እግራቸዉን ወምበሩ ላይ አድርገው ቀበቶዋቸዉን ከጎናቸው ከቾኩ ካርቶን ጋር አድርገው ከወየበ የቆዳ ጃኬታቸው የውስጥ ኪስ ቀይ እስኪብርቶ አውጥተው ክዳኑን አውልቀው ከላይ ያጠልቁና በትናንሽ ዓይኖቻቸው "ቀጥሉ" በሚል ደብተር ለመፈተሽ ይቅበጠበጣሉ::
ሲጨርሱ ክፍሉን ቢያንስ ለግማሽ ከፍለዉት እኛን ካንድ ወገን ቆመን ቀበቶዋችንን እንድንጠብቅ ይነግሩናል... ብዙ ጊዜ የሚገርመኝ ስለ አማርኛ ሲያስተምሩን ለየብቻችን በደምብ ለማስረዳት ጊዜው አይበቃቸዉም ግን በየተራ ገላችን ሰመር እስኪያወጣ ሲገርፉን ሳይቻኮሉ ቀስ ብለው ነው:: ይሄን ጊዜ ክፍሉ በሱሬዎቻችን አዋራ ጉም ይለብሳል
"ቆሻሻ የቀሻሻ ዘር ሁላ... እናንተ አትጠሩ ደብተራችሁ አይጠራ... እናንተ አድጋችሁ ነው አሁን እቺ ሃገር 'ምትጠራው...በክት ሁላ" ብለው ቀበቶዋቸዉን መልሰው ያስሩና ግራና ቀኝ እየተወላገዱ ክፍሉን ለቀው ይወጣሉ : ይሄን ጊዜ ሁላችን ቂጣችንን እያሸን እንነጫነጫለን ግን ምንም የማድረግ አቅም አልነበረንም::
ልጅ ሆኜ ሠው ሞት ወሰደው ሲባል ስሰማ ያማርኛ ቲቸራችንን እንዲወስዳቸው ሞትን አግኝቼ በጠየኩት እላለሁ: አንዳንዴም ማንለ እግዝያብሔር እንዲ ሽምድምድ አድርገህ አጣመህ ከምታስቀራቸው ከዛ ከሰማይ ባንድ ጎናቸው ስታፈርጣቸው በዛው በገላገልካቸው ብዬ ፈጣሪዬንም እጠይቅ ነበረ::
አንድ ቀን ክፍል ውስጥ አዛጋህ ብለው ከግማሽ ሰዓት በላይ ሁለት እጆቼን በሁለት እግሮቼ ጀርባ አሾልኬ ጆሮዎቼን ቆንጥጬ እንድቆይ አዘዙኝ በጣም መረረኝ:: ተነሳዉና የጎበጠ ወገቤን ለማቃናት ስንጠራራ ድንገት ያ ወፍራም የቆዳ ቀበቶዋቸው በጀርባዬ ተጠምጥሞ አንገቴን ቢጠብሰኝ የልጅነት እልዬ አናቴ ላይ ደረሰ::
"የእርስዎ ሃሳብ ሁላችንም እንደርስዎ እንድንጣመም ነው አይደል....?"
አልኳቸው ለመሮጥ ወደበሩ እየተጠጋው ቀበቶዋቸዉን በኪፊል መዳፋቸው ላይ እየጠመጠሙ ሲጠጉኝ ክፍሉን ለቀቄ ሮጥኩ ይሄን ጊዜ ክፍሉ በሳቅ ተሞልቶ ነበር ወዲያው ደግሞ መለስ ብለው ወደተማሪዎቹ ሲያፈጡ ረጭ! አለ::
በማግስቱ የመጀመሪያው ክ/ጊዜ የርሳቸው ነበር ምን ሊመጣብኝ እንደሚችል ሳስብ እንቅልፍም በቅጡ አልተኛዉም ነበር:: በዚህ ላይ የአንገቴን የቀበቶዋቸዉን ጠባሳ እናቴ እንዳታይ ባንድ ጎኔ ብቻ ነበር ቤቱስጥ ውር ውር ስል ያመሸዉት::

በወልጋዳ እርምጃጅቸው መጥተው ክፍላችን ደርሰው ከሰሌዳው ፊት ሲቆሙ ተነስተን እጅ ነሳን ማንም ዓይኖቻቸዉን በሙሉ ዓይን የሚያይ የለም ሁላችንም ተንከርፍፈን አንገታችንን ወደመሬት እንደፋለን::
"ተዘፍዘፉ!"
አሉን በተለመደ ቋንቋቸው እኛም ተዘፈዘፍን:: በነዛ የልብስ ቁልፍ በሚመሳስሉ ዓይኖቻቸው ከዛ ሁሉ ተማሪ ፈልገው አገኙኝና ሰሌዳ ማጥፊያዉን (ደስተር) ወርውረው ግምባሬን ቀውረዉት
"ተነስ አጥፋ... ሚያጠፋ ነገር ያጥፋህ ይሄ የድሃ ዘር!"
አሉኝ:: ሚመጣዉን ሁሉ ለመቋቋም ትንሽ ትከሻዬን እየነፋው ወጣዉና ሰሌዳዉን ወምበር ላይ ሳልወጣ በርሳቸዉም በኔም ቁመት ልክ ያለዉን ብቻ አጠፋውትና ማጥፊያዉን ውጪ ወጥቼ ከግድግዳው ጋር ጠብጥቤ ካራገፍኩ በኋላ ከቾክ ክምር ከያዘች ካርቶንስጥ አኖርኩላቸው::
"ወዴት ነው...?"
አሉኝ ግማሹ ያልጠፋ ሰሌዳዉን አይተው
"ልቀመጥ..."
አልኳቸው::
"ያዘዝኩህን መች ጨረስክ አንተ መናጢ..."
"አጠፋው'ኮ ቲቸር..."
"ግማሹስ..."
"ስለማይጠቀሙበት ብዬ ነው..."
አልኳቸው መሬት መሬቱን እያየው::ይሄኔ ክፍሉ በተማሪው ሳቅ ተሞላ
የያዙትን መፅሓፍ ወርውረው ቀበቶዋቸዉን ሲፈቱ ተንደርድሬ ውደበሩ ስሮጥ ባንድ እጃቸው የሹራቤን ጫፍ ይዘው አስቀሩኝ ገና ሳይነኩኝ
"ኡ! ኡ! ኡ!"
ብዬ አቀለጥኩት :: ወደ ግድግዳው ዞሬ እንድቆም አዘዙኝና የክፍሉን በር ዘጉት እምባዬ በጉንጮቼ ፈሰሰ::
"ለመሆኑ አባት አለህ...?"
አሉኝ እየገረፉኝ
"የለኝም... ሞቷል"
"እናትስ?"
"አዎ አለኝ"
ለቅሶዬም መልሴም ባንድ ዜማ ነበር
"ስንት ዓመትህ ነው?"
"11"
"በል ይሄኛው ግርፊያ ደግሞ ለሞተው አባትህ ነው "
አሉኝና በሃይል ገረፉኝ
"አባቴ ምናደረገ.....?"
"አልኳቸው..."
"ከ11 ዓመት በፊት ሞቶ ቢሆን ኖሮ እንዳንተ ዓይነቱ ባለጌ ልጅ ወደዚች ምድር አይመጣም ነበር"
ከብዙ ግርፊያቸው መሃል ላባትህ ብለው የገረፉኝ አንጀቴ ውስጥ ስለተሰማኝ ቆልማማ እግራቸዉን ይዤ ጥምጥም አልኩባቸው: ሁሌም ወደዝኛ ክፍል ብቻ ሲመጡ የሚገጥሙት ስለሚመስለኝ ላወልቀው ታገልኩት ክምር የጎማ ተረከዝ ያላው ጫማቸው እስኪወልቅ ይዤ ተፈራገጥኩኝ በቀበቶዋቸው ዘለበት ሳይቀር አወረዱብኝ:: ሚዛናቸዉን ስተው በጀርባቸው ሲወድቁ ከፊት ለፊ ያሉት ተማሪውች ዴስክ ላይ ተገነደሱ ዴስኩ ተሰባብረ: ክፍሉ በጩእት በጫጫታ ተናጋ:: ይሄን ጊዜ የማምለጡን ዕድል ስላገኘው ያለማቋረጥ እስከቤቴ ድረስ ልቤ ወጥታ ዱብ ልትል እስክትደርስ ድረስ ሮጥኩኝ:: እናቴ የሰውነቴን ሰመር አይታ ኡ! ኡ! አለች ስለአባቴ ያሉኝን ጨምሬ ነገርኳትና ለቅሶዋ በረከተ ነጠላዋ ላይዋ ላይ ጣል አድርጋ ወደት/ቤቱ ሮጠች::
ለእኔ የሚሆን ቁጣ ይዛ ከመምጣት ውጪ የፈጠረችው ነገር አልነበረም ከዛ በኋላ ወደዛ ት/ቤት አልተመለስኩም 6ኛ ክፍልን ባመቱ ደግሜ ሌላ ት/ቤት ተማርኩኝ::
ያአማርኛ አስተማሪያችን ከዕድሜዬ ላይ አንድ ዓመት ወሰዱብኝ: የክፍል ጓደኞቼ ሚኒስትሪ ተፈትነው አልፈው ሌላ ትምሕርት ቤት ቀየሩ ያማርኛ መምሕራችን ግን እዛው ትምሕርት ቤት የሌላ ልጆችን ደብተር እየፈተሹ ነው::
ለሚኒስትሪ እየተዘጋጀው ስለሆነ ከት/ቤት መልስ ቤት ውስጥ አጠናለሁ::
አንድ ቀን እናቴ ያባቴን ፎቶ እያየች ታለቅሳለች አባቴ ከሞተ ገና ዓመቱ ነበር የሰፈር ሠው ሁሉ ስላባቴ ደግነት አውርቶ አይጨርሰዉም::
አባዬ ሊሞት ሁለት ቀን ሲቀረው ጠራኝና ከጎኑ እንድቀመጥ ነገረኝ:: የእጁ ቆዳ ቆርፍዶ የደም ስሮቹ ክርር ብለዋል::
"እኔ ስሞት ስሜ ግን ባንተ ስም ላይ ሲጠራ ይኖራል እራስህን አክብር ልጄ!"
ጠያቂ ያመጣዉን ሁለት ሙዝ ከወረቀት አወጣና ሰጠኝ አንዱ ልጬ ላጎርሰው ስል እንደማይፈልግ ነግሮኝ ዓይኖቹ በእንባ ተሞሉ::
ለምን እንደሆነ አላውቅም ባማርኛ መምሕራችን ቀበቶ ሲገረፍ የሞተ የሞተ መሰለኝ እንባው የኔን እንባ መሰለኝ ከሃሳቤ ስነቃ ድንገት ብድግ አልኩና ከናቴ ፎቶዉን ቀምቼ ደበቅኩባት::
ከቤት ወጣው አስቤው ይሁን ሳላስበው የድሮ ት/ቤታችን ደረስኩኝ:: ተማሪዎች ተለቀው ወደየቤታቸው እየተጯጯሁ ሄደዋል: አሁን አስተማሪዎች መውጣት ጀምረዋል ድብልብል ያለች ድንጋይ አነሳውና ጃኬት ኪሴ ከተትኩኝ ግን ቀጥ ብሎ እንጂ ግራና ቀኝ እየተላተመ የሚወጣ አንድም መምሕር አልነበረም:: ተስፋ ቆርጬ ወደቤቴ ስመለስ ወደሰፈራችን መታጠፊያ ላይ ያማርኛ አስተማሪያችንን አየዋቸው ቀድመው አይተውኝ ነበር::
"እህ አንተ መናጢ...አለህ እንዳባትህ እዛው በተደፋህ?"
አሉኝ በጠማማ አፋቸው ላይ የሰኩትን ጥርስ መጎርጎሪያ እየነካኩ: ድንጋዬን ከጃኬት ኪሴዬ አላወጣዉትም እዛው እንዳለ ጨበጥኩትና ተጠጋዋቸው
"ምናባ እንደ ፊጋ በሬ ታፈጥብኛለህ አንተ መናጢ የመናጢ ልጅ..."
ያባቴን ቃል የበላው መሰለኝ አሁን ራሴን እያዋረድኩኝ መሰለኝ ራሴን ለማስከበር የአማርኛ መምሕሬን መፈንከት አለብኝ በመዳፌ ላብ የወዛችዉን ድብልብል ድንጋይ አወጣዉና ግምባራቸው ላይ አነጣጥሬ ወረወርኩት ከጥቂት ሩጭዬ በኋላ ከርቀት የኡኡታ ድምጽ ተሰማኝ... የሞቱ መስሎኝ ደስ አለኝ::
ቤት ስገባ ሩጫዬን ያየች እናቴ
"ወይ ዕድሌ ደግሞ ምን ሆንክ?"
አለችኝ የትንፋሼን ፍጥነት እያስተዋለች
"አማርኛ አስተማሪያችን...."
አልኳት ድምትጼ እየተቆራረጠ
"ምን.... ዛሬም መቱህ...?"
ብላኝ ሰውነቴን መፈተሽ ስትጀምር
"ፈነክትኳቸው"
አልኳትና ፈገግ አልኩኝ
"ምን"
"አዎ አባዬ ራስህን አክብር ብሎኛል እሳቸው ግን እኔንም አንቺንም አባዬንም ይሳደባሉ...."

ፊለፊት በባለ ጥቁርና ነጭ ፎቶ አባዬ አፍሮዉን አበጥሮ ቆፍጠን ብሎ ሳየው '... ደግ አደረግክ ያለኝ መሰለኝ::


___________________ዋናው
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ቅቅቅቅ

Postby ዋኖስ » Thu Jul 14, 2011 2:34 pm

ዋዉ! ድንቅ ችሎታ! አይዋ!
ሰዉ ሊሞት ሲል በልጁ በወገኑ የሚተዋቸዉ የመጨረሻ መልዕክቶች ግን ለምን ከሆድ ዉስጥ እንደማይወጡ አይገባኝም:: ያዉቁ ይሆን?

ለፈገግታ ደግሞ:

ያኔ ከአማርኛ አስተማሪያችሁ ጋ ባትጣላ ኖሮ..... "ተብታባዉ-ደራሲ" ባላሉሕም ነበር ዋርካዉያን/ያት!! ቅቅቅቅ

ከብዙ ብዙ ማክበር ና ሰላምታ ጋር!

ዳሞት

ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby Tጂ » Thu Jul 14, 2011 9:38 pm

አቦ ተባረክ ዋንቾ በስሜት ድንጋይ አንስቼ ለመወረወር ምንም አለቀረኝም ነበር:: ያቺ ድንጋይ የወረረባት ቅጽበት ምን ያህል ደስታ እንደምትሰጥ አውቃታለሁ::
“Love is like the wind, you can't see it but you can feel it."
Tጂ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 301
Joined: Sat Aug 11, 2007 3:59 am

Re: ቅቅቅቅ

Postby ዋናው » Wed Jul 20, 2011 1:19 am

ዋኖስ wrote:ዋዉ! ድንቅ ችሎታ! አይዋ!
ሰዉ ሊሞት ሲል በልጁ በወገኑ የሚተዋቸዉ የመጨረሻ መልዕክቶች ግን ለምን ከሆድ ዉስጥ እንደማይወጡ አይገባኝም:: ያዉቁ ይሆን?

ለፈገግታ ደግሞ:

ያኔ ከአማርኛ አስተማሪያችሁ ጋ ባትጣላ ኖሮ..... "ተብታባዉ-ደራሲ" ባላሉሕም ነበር ዋርካዉያን/ያት!! ቅቅቅቅ

ከብዙ ብዙ ማክበር ና ሰላምታ ጋር!

ዳሞት


አመሰግናለሁ መሪ ጌታ
እንዴት ንዎት?
ለጥያቄዎ ምናልባትኛ መልስ => ሟች የተሰናበተበት የመጨረሻ የቃሉ ማስታወሻ ስለሆነ ይሆን...?

በተረፈ የኔን መንተባተብ ብሶበታል በተለይማ ከዋርካ ጠፋ ጠፋ ማለት ከጀመርኩኝ በኋላ የፓወር ግዕዝ እና ቪዥዋል ግዕዝ እየተምታታብኝ ሸን ለመጻፍ ደጋግሜ Xን እየነካው በየቦታው ፖስቶቼ የx መዓት በዛባቸው'ኮ... ለምን ግን ተማክረው አንድ ዓይነት ብቻ መጻፊያ እንደማይሰሩ...
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed Jul 20, 2011 1:43 am

Tጂ wrote:አቦ ተባረክ ዋንቾ በስሜት ድንጋይ አንስቼ ለመወረወር ምንም አለቀረኝም ነበር:: ያቺ ድንጋይ የወረረባት ቅጽበት ምን ያህል ደስታ እንደምትሰጥ አውቃታለሁ::


ቲጂዬ እጅ ነስቺያለሁ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby እንሰት » Wed Jul 20, 2011 6:25 am

ያባቱ ልጅ! ሆ ሆ ብለህ ብለህ ባማርኛ አስተማሪ መጣህ? ጉድ እኮ ነው:: የተወሰኑ ጥሩ አማርኛ አስተማሪዎች ስለነበሩኝ ለነሱ ስል አብዛኛውን ከመናገር ተቆጥቤያለሁ::

ግን ቁዋንቁዋ አስተማሪዎች ምን እንዲህ አደረጋቸው? እርግጥ ባማርኛው ቢብስም እንግሊዘኛ አስተማሪዎቹም እዚህ ውስጥ እኮ አታጣቸውም::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ዋናው » Fri Aug 23, 2013 12:47 am

ተመስገን ....
ዛሬ ዋርካ ሎግ ኢን ማድረግ ቻልኩኝ ያልሞከርኩትን ብራውዘር ጠይቁኝ ... ሳፋሪ , ኦፐራ , ክሮም ዛሬ ግን ማሽኔ ብዙ ሪስክ እንዳለው አስምሎ አስገዝቶ እሺ አለኝ ... እኔና ዋርካ አንድ የሆነ ቦታ ተላልፈናል ከምር ... የዋርካ phpbb ኮድ ፕሪሚቲቭ የመሆኑ ጉዳይ አይመስለኝም ...

የሆነው ሆነና ይሄ ሠፈር እንዴት እንደናፈቀኝ ይሄ ሰፈር ስል እነኚህን ሎቦለዶች ማለቴ አይደለም ጠቅላላ ዋርካ ማለቴ ነው .... የማውቃችሁም የማላውቃችሁም ሰላም ብያለው :[/code]

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ሙዝ1 » Fri Aug 23, 2013 8:59 am

ዋናው wrote:ተመስገን ....
ዛሬ ዋርካ ሎግ ኢን ማድረግ ቻልኩኝ ያልሞከርኩትን ብራውዘር ጠይቁኝ ... ሳፋሪ , ኦፐራ , ክሮም ዛሬ ግን ማሽኔ ብዙ ሪስክ እንዳለው አስምሎ አስገዝቶ እሺ አለኝ ... እኔና ዋርካ አንድ የሆነ ቦታ ተላልፈናል ከምር ... የዋርካ phpbb ኮድ ፕሪሚቲቭ የመሆኑ ጉዳይ አይመስለኝም ...

የሆነው ሆነና ይሄ ሠፈር እንዴት እንደናፈቀኝ ይሄ ሰፈር ስል እነኚህን ሎቦለዶች ማለቴ አይደለም ጠቅላላ ዋርካ ማለቴ ነው .... የማውቃችሁም የማላውቃችሁም ሰላም ብያለው :[/code]

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች


ሰላም ዋንቾ የጥንቱ .... እንዴት ነህ ወዳጄ?

ስማኝማ ዋንቾ .... ለምን ይመስልሀል (ይመስልካል አላልኩም እንደነ ጌታ ሸፎ) ...... ለምን ይመስልሀል ብራዉዘሮቹ ሁሉ በማስጠንቀቂያ ያስገቡህ? .... ቀላል ነዉ ... ብራዉዘሮቹ ሞር ሴኪዩርድ ናቸዉ ከሳይበር ኢትዮጵያ:: በጣም ብዙ ክፍት ነገሮች አሉት ሳይቱ ... ዌብ አፕሊኬሽኑ ያለበት ሰርቨር .... ከነ አፕሊኬሽን ሴኪዩሪቲ .... ያዉ የነ አፓቼና አይአይኤስ አጫጫን ጀምሮ ማለቴ ነዉ ... ... የሰርቨር ሶፍትወሩ ሴኪዩሪቲ ፓች ... በየጊዜ አለመደፈን እና እንዲሁም አላስፈላጊ የተከፈቱ ዩዲፒም ሆነ ቲሲፒ ፖርቶች ያሉ ይመስለኛል ... ያ ብቻም አይደለም ... ከሰርቪስ ፕሮቫይደርህ በተጨማሪ አንተም እንደ ባለ ዌብ ሳይት የኔትዎርክ ሴኪዩሪቲን መጠቀም የግድ ይላል ... .... አስፈላጊዉ የፋየርዎል ኮንፊገሬሽን (ሀርድዌርም ሆነ ሶፍትወር .... እስከነ IPS ድረስ ) መስራት ይጠበቅብሀል::

ዋርካችን ይሄ ሁሉ አላት የላትም .... በጣም ሲምፕል የሆኑ የሀኪንግ ቱሎችን ተጠቅመህ መሞከር ትችላለህ:: ትልቁ ነገር ግን ሀላፊነት በሚሰማን መንገድ የምንጽፍ ከሆነ ተወዳጅ ትሆናለችና ... እኛም እርስ በርስ እንዋደዳለንና ያን ያክል ለክፉ የሚሰጥ ነገር አይኖርባትም:: ሌላዉ ከላይ ያልኳቸዉ የሴኪዩሪቲ ሆል መድፈኛዎች ቀላል የማይባል ወጭዎች አሏቸዉና እነ አቶ ቅጣው ብቻ የመሸፈን ግዴታም የለባቸዉም::

ኤኒዌይ, ስላየሁህ ደስ ብሎኛል:: አትጥፋ
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ዋናው » Thu Nov 07, 2013 2:38 am

ሰላም ሙዘይድ የሚገርምህ የጻፍከዉን ምላሽ አንብቤ የራሴን ለማለት ስመጣ ድጋሚ ማሽኔ አሻፈረኝ ብሎኝ ጃቫን ደጋግሜ እየጠረግኩኝ አውርጄ ጫንኩት እንደኔ እንደኔ አሁን በመረጃው መረብ ላይ በአሁኑ ጊዜ 'ምንጠቀምባቸው አዛዥ ዝርዝር ቋንቋዎች (Scripting language) በየጊዜው እየተሻሻሉ ሲመጡ ብራውዘሮች የለመዱትንና 'ሚጠብቁትን ቋንቋ ብቻ ነው ሊረዱ 'ሚችሉት ወደ ውኃላ ሄዳችሁ የተረሳዉን ቋንቋ አስታውሱ ስንላቸው የደሕንነት ጥያቄ አምጥተው ያስጠነቅቁናል ከ PHP database site ውስጥ PHPBB በተለይ በዕድገት ላይ አጅግ ኣዝጋሚ አንደሆነ ይታማል ለብዙ Plugin አንኳን ኣመቺ ኣይደለም::

አሁንማ በተለይ ማሽኔ ላይ ማቭሪክን ከጫንኩኝ በዋላ ብሶበታል ትንሽ በማውንቴን ላየን ጊዜ ይሻለኝ ነበር አንተ እንዳልከው እዚጋ አቅም ትልቅ አስተዋጽዎ አለው ግን'ኮ ባለቤቶቹ ለመረዳዳትም 'ሚያመቹ አልሆኑም እንጂ ዋርካ ከአፈር ቤት ወጥታ ኮንደሚኒየም እንድትገባ ሚያግዛት የራሷ ልጆች አሏት::
የሆነው ሆኖ ግን ዋርካን ለመጠቀም ባልቸገር እኔ 'ምወዳት በድሮ በዚሁ ደብዛዛ ቀለምዋ ነው በዚህ ላይ ደስ የሚለው ከሊንክ ውጪ አልባሌ ቪዲዮና ምስሎች ሚለጣጠፍባት ግድግዳ የላትም::

ለማንኛዉም ግን አሁንም በናፍቆታት ስሜት ሆኜ ሰላምታዬን እያቀረብኩኝ ነው::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest