የዋናው አጫጭር ልቦለዶች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby sleepless girl » Wed Dec 17, 2008 9:58 pm

ዋንቾ....................እኔም ምችችችችችችችችችችት ብሎኛል::........ :wink:
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Postby early_bird ! » Thu Dec 18, 2008 12:04 am

ወይ ዋናው ..........በ ብረሀን ፍጥነት ነው አንብቤ የጨረስኩት'ኮ.. :) እጅህን አይቆርጥመው እንጂ ሌላ ምን ይባላል............... :D :D
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby ኤልሳ* » Thu Dec 18, 2008 1:25 am

ውይ ሂሩት እንዴት እንዳሳዘነቺኝ. :cry: ......ዋናው በጣም በጣም ቆንጆ ነው.....
ኤልሳ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jul 27, 2006 10:30 pm

Postby Tጂ » Thu Dec 18, 2008 1:26 am

''ምን እስከመቼ አለው እሱ ቢሄድም ሌላው ጉልበተኛ ይተካል ... አየህ ምግብ ቤት 'ሚሠሩ ሠዎች ቤታቸው እየሄዱ አይበሉም ከሚሠሩበት ምግብ ቤት ውስጥ ያለዉን ምግብ ይበላሉ ... ልክ እንደዛ ነው :''

ስታሳዝን :(

ዋንቾ እኔም አጀብ አጀብ ለማለት ነው: እንዲህ ቅምም እያደርግህ ስለምታስነብበን ምስግን እያደረግኩህ::
“Love is like the wind, you can't see it but you can feel it."
Tጂ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 301
Joined: Sat Aug 11, 2007 3:59 am

Postby ዋናው » Thu Dec 18, 2008 2:09 pm

ለ ዋኖስ
ትርንጎ
ውቅሽ
ስሊፕ
የማለዳዋ ወፍ
ኤልሣና
ቲጂ.... ለአስተያየቶቻችሁ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby harar_beer » Thu Dec 18, 2008 2:20 pm

anet lololol
hi eve one bro and sisr
harar_beer
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Thu Oct 02, 2008 1:10 pm

Postby harar_beer » Thu Dec 18, 2008 2:31 pm

anet lol bro
hi eve one bro and sisr
harar_beer
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Thu Oct 02, 2008 1:10 pm

Postby herma » Fri Dec 19, 2008 1:51 am

እኔምልህ? ከየት ነው የምታመጣው? የሰማኸው ወይም የምታወቀው ታሪክ ነው'ኮ የሚመስለው::

አምላኬ ሆይ! ተአማኒነቱና ውህደቱ እንዸት ይደንቃል::

ባጭሩ ከመቀመጫየ ተነስቼ እጅ ነስቻለሁ::

ያበርታህ
herma
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Tue Jul 13, 2004 6:39 pm
Location: usa

Postby harar_beer » Fri Dec 19, 2008 2:05 am

herma ሎል
hi eve one bro and sisr
harar_beer
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Thu Oct 02, 2008 1:10 pm

Postby ዉቃው » Sun Dec 21, 2008 4:22 pm

ሕልሜ እስኪ እንደሰው ....የት ሂጄ ልሰሰው
እያመላለስ ሲያሳየኝ አንድሰው .....

ዓለም ከበደ ለዛ ያለውን ሙዚቃ ታንቆረቁረዋለች :: ግሮሰሪውን ሞልቶ የነበረው ቀስ በቀስ እያለ ወደየማደሪያው ሄዷል :: ሁሌም እንዲህ መሆናቸው ንድድ ያደርገኛል :: በጊዜ ይመጣሉ : ቶሎ ቶሎ ይጠጣሉ : ቶሎቶሎ ያወራሉ : ፈጥነው ይሄዳሉ :: የርጋታ ጊዜ የላቸውም :: እነዚህንስ ማን ይነካቸዋል የተባሉትን ዛፎች እንዴት እያድረኩ በርጋታ ገንዳድሸ እንደምጥላቸው በማስረዳት : አትቸኩሉ እያልኩ ስንቱን አስረድቻለሁ :: ኤዲያ...... ! ቢራዬን አነሳሁና ባንድ ትንፋሽ ጨለጥኩት :: ዞር አልኩና አባፈርዳን አየሁት :: ንግግር ካቆምን ደቂቃዎች ተቆጥረዋል : እሱም በተቀመጠበት በሀሳብ ነጉዷል :: :: የግል ቢራውቹን አመጣችና ከፍታልን ከዓይናችን ጠፋች ::

"ስማ እንጂ ...ጌታው ? ምን እያስብክ ነው ? " አባፈርዳን ከገባበት ሃሳብ ለማንቃት እየሞከርኩ
"ምን እባክህ ...ሰከርኩ መሰል " ቅድም ያጠፋትን ግስላ ለድጋሚ ዙር ትንፈሳ ወደ ከንፍሮቹ እየላከ በረጅሙ ሳቀ
"ባክህ እኔም እንዳንተው ሞቅ ሳይለኝ አልቀረም " አፌ ተሳሰሮብኝ እየተንተባተብኩ ለመመለስ ሞከርኩ ::

"እሺ ..እናንት ጭቁን ወዛደሮች !" አጠገባችን መጥቶ ተቀመጠ ጌታቸው
"ኖር ኖር " አልን ሁለታችንም
"ኧረ ! በልጆቻችን ! "
"እንዴት ነው ባክህ ...ዛሬ ደግሞ አምሮብሃል !" አልኩ አዲስ ያደረጋትን ጫማ እየተመለከትኩ
"እእእእእእ ....ለመሆኑ እንዴት ነበር የዛሬው ምክክር ?" አለ ያልኩትን እንደዋዛ ወደጎን በመተው
ከጌታቸው ስንተዋወቅ ይሄው ብዙ ዓመት አልፏል :: ከመድን ድርጅት የጥበቃ ስራ ጡረታ ከወጣ ጀምሮ ኑሮው ተደላድሏል :: ይህን ያዩ አንዳንዶች ጆሮ ጠቢ ነው እያሉ ያሙታል :: ለነገሩ እሱም ከሰከረው ጋር ስክሮ : ከራበው ርቦት ከጠገበው ጋርም እየቦረቀ መመሳሰሉን ተክኖበታል ::

"ጥሩ ነበር አንተ እንዴት አየኸው ? " መለስኩ እኔ
"እእእ አዎ ጥሩ ነበር " ብሎ ነገሩን ቁርጥ አረገው ::
" በሉ እኔ ልሂድ ...ነገ በጠዋት የምወጣበት ስራ አለኝ ...እናንተ ተጫወቱ " አለ አባፈርዳ ከንፈሩን ልታቃጥል ደርሳ የነበረችውን ግስላ በቦቲው እየደፈጠጠ
"ቆይ ቆይ አብረን እንወታለን ...ይቺን ልጨርስ ...." አልኩ እየተንተባተብኩ ::

የመጨረሻውን ጭላጭ ከተጎነጨሁ በኋላ ለመነሳት ሞከረኩ :: በደንብ ሞቅ ብሏኛል :: አባፈርዳና ጌታቸው ደግፉኝና ከግሮሰሪው ወጣን :: በጠባቧ የስፈራችን መግቢያ ላይ ስንደርስ : ቡዝዝ ባሉት ዓይኖቼ ሾተልን ያየሁት መሰለኝ ::
"እንዴ ..ይሄ ሾተል አይደለም እንዴ ?" አምቧረቅኩ
"ኤዲያ ...አንተ ደግሞ ...እስኪ ዝም በል ሰክረሃል እኮ " አለኝ ጌታቸው በንዴት
"ስንቴ ልንገርህ ? ...እናንተ ገሮሰሪው ውስጥ ስትገቡ እኮ ካራክተሮች ናችሁ እኮ " አለ ካራክተር የምትለዋን ቃል ረገጥ አድረጎ :: የካራክተር ትርጉሟን ደጋግሞ አስረድቷናል ::
"አንተ ራስህ ካራክተር ነህ " አልኩ ጮክ ብዬ ሰፈሩ እንዲሰማ
"አንተ ዝም በል ....ብቻ ....ለማናኛውም.....እዛ ግሮሰሪ የምትሰበሰቡ ሰዎች ካራክተሮች ናችሁ :: ዛሬ ሰካራም : ነገ ቁም ነገረኛ ከነገ ወዲያ ደግሞ ትዳሩን አክባሪ ወይም ዝሙተኛ እየሆናችሁ : ገጸባህርያቱን ትተውናላችሁ :: ተዚያ የግሮሰሪውን ከዕድሩ : የዕቁቡን ከግሮሰሪው ትደበላልቁትና ....እዬዬ ስትሉ ትውላላችሁ "

"አሁን ማን እየየ አለ ....እንከባበር " :evil: አባፈርዳ ቆጣ አለ
"እውነትም ጆሮ ጠቢ " አልኩ ለራሰ በሚሰማ ድምጽ

"በል አሁን ወደ ቤትህ ግባ... ደግሞ ሰፈሩን በዚህ ወድቅት እየዘፈነክ ረብሽ አሉ " አለኝ ጌታቸው የቤቱን መዝጊያ እያስጨበጠኝ ::

"በሉ ደህና እድሩ ..የነገ ሰው ደግሞ ይበለን " አልኩ የቆርቆርዋን በር ለመግፋት እየታገልኩ ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ShyBoy » Sun Dec 21, 2008 7:19 pm

ዉቅሽ: በጣም ጣፋጭ ወግ ናት!!! እስቲ በል ቀጥልባት...
ሰንበት እንዴት ይዞሀል ለመሆኑ? ዛሬ እንኳን ዛፍ ቆረጣ ስለሌለብህ ቀኑን ሙሉ ግሮሰሪ ተዘርፍጠህ እንደምትውል እንኳን ሰው መጥረቢያህ ታውቀዋለች :lol:

ደህና ነህ ግን?
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ትርንጎ* » Sun Dec 21, 2008 8:20 pm

:D ካራክተር...ህምምምም :D እራሴን መረመርኩት እኮ:: ውስጠ ወይራ ጨዋታ ናት::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 709
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ሀሪከን2 » Mon Dec 22, 2008 6:05 am

ውቃው
ሀሪከን አፍንጫውን በሌባ ጣቱ እየጎረጎረ የንፍጥ እንክብሎችን ሲያፈናጥቅ


ነፍሱ እኔ መጠጥ ቤት ስገባ የምጫወተው በብላክ ቤሪየ ነው እንደ አንተ እና ጉዱ ካሳ በመጥረቢያ እና በቢላዋ አይደለም Laughing

አንተ አመዳም እኔ እንኴን በንፍጤ ልጫወት ቀርቶ ባልቻና መዶሻው ግሮሸሪያችሁ ለመምጣት አንድም ቀን አስቤ አላቅም በበሩ ከማለፍ ውጭ ምንም እንኴን ባለቤቱ ሰው አክባሪ ትሁት ሰው ነው ሲባል ብሰማም ግሮሸሪው ጥሩ ስም የለውም አብዛኞቹ የሰውየው ደምበኞች ላብ አደሮች ናቸው እናም አብዛኞቹ ከሽቅል መልስ ወደ ግሮሸሪው በዛው ዘው ስለሚሉ የጫማቸው ሽታም አብሮ ዘው ብሎ ይገባል ይባላል Laughing

አንዳንዴ እንዳውም መጠጥ ቤቱ መጠጥ መሽተቱ ቀርቶ አሮጌ የጫማ ማደሻ ማደሻ ይሽታል ሁሉ አሉ በዚህ ጉዳይ የተማረሩት ጫማ ሰፊው አክየ እና የባህል መድሀኒት አዋቂው ሻይ ቦይ በተደጋጋሚ ለባለቤቱ አቶ ዋናው አመልክተው ውቃው ሊታገድላቸው ስላልቻለ አክየ መጠጥ ቤት ሲቀይር የልምድ አዋላጁ ሻይ ቦይ ግን አልፎ አልፎ ጎራ ማለቱን አልተወም አሉ

ወዳጀ ሙዝም አንድ ቀን እግር ጥሎት ባልቻና መዶሻው ግሮሸሪ ሄዶ የውቃው የጫማ ትዝታ ለብዙ ጊዜ አልረሳው ብሎ እንደነበር አጫውቶኛል

በርግጥ የግሮሰረው ባለቤት የግሮሸሪውን ንጽህና ማስጠበቅ ቢችል ለእኔ እና ለሙዝ ከተራው የህብረተሰብ ክፍል ጋር አብሮ ለመዝናናት እና ተራው የህብረተሰብ ክፍል እንዴት እንደሚያስብ እንዲያም ሲል ሂወትን እንዴት እንደሚኖራት ትልቅ ትምህርት እናገኝበት ነበር ብየ አስባለሁ
_
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ባለሱቅ » Tue Dec 23, 2008 6:43 pm

ወይ ጨረቃ
በጨረቃ ስንትና ስንት ታሪክ ተሰራ
....
ውብ ታሪክ ነው ውድ ወንድሜ ዋናው
ከውብ አፃፃፍ ጋር
መጨረሻው ግን ተጣደፈብኝ.... ቸኮለብኝ.....
ምናልባት አጭር ልቦለድ አፃፃፉ እንደዚህ ይሆን ይሆን
ምናባቴ አውቃልሀለሁ..
የራስህ ጉዳይ
ግን እውነት እውነት ነው የመሰለኝ.. ሳነብህ
...
እንደው አንድ ቀን እኔም የራሴን ታሪክ ብነግርህ.... እንዲህ አሳምረህ እውነት አስመስለህ ትፅፍልኝ ይሆን?... ብዬ... ግዋጓሁ
ደሞም አፈርኩ
ከነስሜ ብትፅፈውና... የፍቅር አምላክ ቢያየኝስ ምን ብዬ ምክንያት ሰጣለሁ ብዬ ... ፈራሁ

ሆ ሆ ጎመን በጤና
የክ/.መንግስት ልጆች ደሞ
ምናባክ ልትሰራ እዛ ቤት ሄድክ እዚሁ አታሳብቅም.. ቢሉኝ,... ምን እላለሁ

ጎመን በጤና
ይሄ ነገር ግን ለምን እንደተባለ ሁሌ የጤና አምድ የከፈተውን ጌታን እጠይቀዋለሁ እያልኩ....
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እስኪ የራስህ ጉዳይ
ሰላም ሁንልኝ

እንዲህ እንደዛሬ አይነት የ"ፍቅር" ስሜት ሲሰማኝ ብቅ ብዬ የማይነገሩ... የማይታዩ... የማይዳሰሱ ነገሮችን... ጫጭራለሁ

ቸር እንሰንብት
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby ሀሪከን2 » Tue Dec 23, 2008 7:39 pm

ዉቃው wrote:ይጽፏል እንደዋንየ : ይዋቧል እንደቆንጅየ::


ትክክል ውቅሽ ከጨረቃ ስር ውብ ታሪክ ነው

ዋንቾ ለመጀመሪያ የዋርካን ልቦለድ በሚገባ አንበብኩ ብቻ ሳይሆን ደግሜ ደጋግሜ አንበብኩ ምናልባትም በመጠኑ ተመሳሳይ ታሪክ ስለማውቅ ይሆናል

ባለህበት ምስጋናየ ይድረስክ ዋንሽ የዋርካ እረፍትን ጨርሰክ በቶሎ እንደምትመጣ ተስፋ አደርጋለሁ
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests