የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Re: ያቺን ቀን በጸፍጸፍ

Postby እንሰት » Sat Feb 02, 2008 4:37 am

እንሰት wrote:ያቺን ቀን በጸፍጸፍ

ርእስ = ያቺን ቀን በጸፍጸፍ
ገጣሚ = አብርሃም ሰሎሞን
ታተመ = ሐምሌ 3/ 1995
ገጽ ብዛት =200
ዋጋው 10 USD
ቦታ/መቼት= ሱዳን - ግብጽ - ሚኒሶታ
ርዕስ የተሰጣቸው ግጥሞች ብዛት = 52
መቅድም ፀሐፊው ሊቁ ደራሲ እና የቤተ ክርስቲያን አባት ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ ሲሆኑ
የደራሲው አድራሻ ስልክ (612) 874 8087 ሲሆን email SLAT6@yahoo.com ነው:: እኔ መፅሐፉን ውድድ ነው ያደረኩት። ከእንጀራ ማብሰል የሚሰረቅ ጊዜ ሲኖረኝ አለፍ አለፍ እያልኩ ከግጥሞቹ አቋድሳችኋለሁ። ለዛሬ ከልባሱ ያገኘሁትን እነሆ!


...«ስቀለው» ነው እንጂ «ፍታው» የሚል ጠፋ፣
ያቺን ቀን በጸፍጸፍ ተከዳሁ በይፋ።

...ለንጹሕ ደምማ ዓለም ለቀደሰው፣
አይበቃም ወይ አባት ከአንተ የፈሰሰው።

...መልካም ዜና ሰማሽ እልል! በይ ገሊላ፣
በአንቺ ተፈጽምዋል የተባለው ሁላ።...

...ስምዖን ባርኳቸው ታቅፎት ሕጻኑን፣
ጦር ያልፋል በነፍስሽ አላት ድንግሊቱን።...

ቃል ወዶሽ ተጠጋ ገባ ከከተማው፣
መለኮት መዋሀድ ካንቺ ጋር ተስማማው።...

...«እፍ!» ብሎ ማብረድ ሲሆን ማጥፋት ሲቻል፣
ዛሬም «እፍ!» ብሎ የሰው ልጅ ያነዳል።...ሁለተኛ መጽሃፍም ደርሷል ይባላል። ያላችሁ ርእሱን ንገሩን። አስነብቡን።
ሰናይ ሰንበት


«ደንቆሮ አይደለሁም እሰማለሁ» አትበል

እንሰሳም ይሰማል አሳብ ባይቀበል
ሲረዳ ነው እንጂ ልብህ ልብ ሲለው
የአንተ መስማት ፍሬ የሚያንጠለጥለው
መንፈሳዊ ዓይንህን በዓለም ኑሮ ጋርደህ
የዓይናማ ዕውር ሆነህ እንዴት ትኖራለህ።
ስለ ፈራህ አትድን ጌታን ስላወቅሀው
ሰይጣንም ይፈራል እስኪያንቀጠቅጠው
ከድጥ ወደ ማጥ ነው ከእሳት ወደ ረመጥ
እምነትና ሥራህ እኩል ያልመጡ ዕለት።
መልካም ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby እንሰት » Sat Feb 02, 2008 4:43 am

መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
በ 1857 በአለቃ ዘነብ ተጻፈ።
በ 1924 በጎህ ጽባሕ ማተሚያ ታተመ ዓ .ም አዲስ አበባ


ካለፈው የቀጠለ


መጽሐፈ ጨዋታ ወንጌላዊ
ክፍል 2

እግዚአብሔር በደብረ ሲና በጁ አሥር ነገር ዘራ የሚያጭደውም በታጣ ጊዜ አንድ ልጁን ቢልከው እንግዳ ነውና በዳዊት ቤት አደረ ይህንም አዝመራ 33 ዓመት ሙሉ ብቻውን አጭዶ በጨረሰ ጊዜ አባቴ አባቴ አመስግነኝ አለ ምነው ከረኛ ቤት ተወለደ ብለን አምተነው ነበር አሁንስ እርሱ ራሱ እረኝነቱን ገለጠው ለካ የበጎች እረኛ እኔ ነኝ እያለ ከሰማይ ተሰዶ የመጣ በጎችን ሊጠብቅ ነውን።
ከሰማይ ድረስ መጥቶ በግ መጠበቅ ካልቀረለት ይህችን ታናሽ መንጋ መጠበቁ ለምንድር ነው ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ ያለውን መንጋ አንድ አድርጎ ጠብቆ ደመወዙን በምስጋና አውጥተን አንሰጠውምን።
የተሰበረውን ጠግኖ የደከመውን አሳርፎ ተኩላ እንዳይነጥቃቸው ጠብቆ ከበጎቹስ መልካካሙን እየመረጠ አይወስድምን።ቀበሮውንስ ያውቀው የለምን አንድ በግ ባገኘ ጊዜ ይዞ ወደ ጉድጓድ እንደሚገባ።
ያችም በግ ከረኛዋ ፈቃድ ወጥታ ከተገኘች መዳን የላትም፤ ምነው እርሱ ባዘዛት ብትገባ ደጁ እርሱ አይደለምን፤ አዳምንና ሔዋንን የኃጢአት ብርድ ቢያንቀጠቅጣቸው ክርስቶስ ሥጋን ለበሰ።
በበረትም ወድቆ ወገኖቹ የላም እረኞች አዩት፤ለላም እረኞችም የምስራች ነገራቸው ለካ እረኛ እረኛ ነው።

ክፍል 3
በ5ሺ አምስት መቶ ዘመን እግዚአብሔር እጅግ ተዋረደ፤አንድ ልጁን ለሰው ባሪያ ሆነህ ሥጋ ተሸከም ብሎ ሰደደው።ወዮ ወዮ ወዮ ዋ ዋ ዋ መላእክትስ ጌታ የሰው ሥጋ ሲሸከም እያዩ ቆመው ዝም ብለው ማየታቸው ለምንድር ነው፤ የስጋ መብል ስላለባት ሁሉም የምድሪቱን ኑሮ ወደዱ በሰማይስ ሥጋም ጠጅም የለም አሉ፤ እንደዚህ ያለ ባዶ አገር መላእክትን እከክ አይቆራርጣቸውምን፤
የእግዚአብሔርስ ልጅ ከአባቱ ጉያ ተለይቶ የመጣ ለሥጋ ጋዋጉቶ አይደለምን።ከሰማይ ድረስ ተሰዶ መምጣቱ ሀብት ሆኖት መቸም አንድ ጊዜ ብላ ብሎታል፤ ዕለቱን እንደመጣ ከዳዊት ቤት በሥጋ አደረ፤
ምነው አብና መንፈስ ቅዱስ ቀሩ፤ ለሥጋ ስሱ ስለሆነ ተቅለብልቦ መጣ እንጂ ሁለቱስ እሳት ናቸው፤ ጥበባቸውም አይታወቅ፤ ይልቁንስ ልጅየው ዘመዳችን ነው፤ ሁሉንም አጫውቶናል፤ የርሱስ ዝምድና ምንድር ነው የዚያው ልጅ ከዚያው ነው ዞረው ዞረው አንድ ናቸው፤ ብሎም የዘመድ ዘመድ ወንዝ ያሻግራል እንዲሉ ሁሉንም እናምናቸዋለንና አይተውንም።

ሰናይ ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ፈጣሪና አበሾች

Postby እንሰት » Wed Feb 06, 2008 4:52 pm

ፈጣሪና አበሾች


አበሾች ተጣልተው አበሾች ሊያስማሙ
በይቅር ለግዚያብሄር ጉንጭ ሊያሳስሙ
ዋሽቶ ማስታረቅን መልካም ነው ይላሉ።
መዋሸት ሃጢያት ሲል የመጽሃፍ ቃሉ
ፈጣሪና አበሾች እዚህ ጋ ተጣሉ


በስንታየሁ አባተ
ጣይቱ ማእከል

ዲሲ ጥር 2000 ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ እንደጻፈው
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ocean12 » Sun Feb 10, 2008 2:22 am

እውነት ብሏል ብርሀኑ...
አስቤውም አላውቅ ነበር...
አይ የኔ ነገር...
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sun Feb 10, 2008 4:31 am

:arrow: :arrow: የሞት.....ጂኒ.....የሞት....መለክተኛ.....
ወጌሻ....የሌለህ.....ክፉ...ሰሎ....መልቲ....ምላስ....መጋኛ.....
ፍቅር...የማይመልስህ.....ቌንቌው.....የማይገባህ......
መርዘኛ...እባብ....የህይወት.....ደመኛ..::
አቢ....ፍሬ.....የማትል....ኬሊን.....ሳሚን....የማታውቅ......
እግር- ከ-ወርች...የምታስር....የምትጠፍር....በእግረ-ሙቅ... :!:
ጆቢራ....የበረሀ...ቁስል...የበረሀ....ንዳድ....አንበጣ....!
ሞት...ያረገዝክ....የሲኦል...ደመና...ጭንጋፍ....እሾክ...ጨባጣ. :!:

እየጠጣህ...የማትጠግብ....እየበላህ...የማትወዛ....የሲኦል...ዘንዶ...
ልጅ...ህጻን....የማትለይ....ወጣት...አዋቂ...የማትል.......
*******ሰደድ....እሳት.....ማገዶ.....*******
እንደ...መዥገር...መጋን....የምትግጥ.....
እንደ...ትኌን....ደም.....የምትመጥ... :evil:
ሰኒ....ጄሪን....በፌን.....የማታቅ.......
ቁልምጫ...የማይገባህ....ፍቅር...የማይመልስህ....
የሲኦል.....አጥር.....የሞት....ሰንደቅ.... :!:
ነብር....አየኝ....በል....አንተ....አርዮስ....መጋኛ.......
ሞትህ...ላይ....ሳልጨፍር...ሬሳህ...ላይ....ሳልደንስ......
ዲስኮ....ሳልረግጥ....ባቲኛ... :arrow:
ከገባህበት...ገብቼ...ቌትህን.....ሳልዘረግፍ....ላልተኛ.....
አልበላም...እምቢ.....ብዬአለሁ.....ሆኜ.....እኖራለሁ....ግዞተኛ:::

************ኤይድስ....ይውደም.... :!: :!: ***********
ለበ/ፍ.....ማስታወሻ....................
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ocean12 » Tue Feb 12, 2008 9:15 pm

ጋሸ መልከጻዲቅ ይቺን ግጥምህን ወድጃታለሁ...
ሳይታክተኝ አንብቤ በመጨረሻው ዋ...ው! ብያለሁ
እረ በርታልኝ...
እንሰት ወደ መጀመሪያዎቹ ገጾች ተመልሼ ሄጄ
አንዷን ደስ ያለችኝን ግጥም ተውሼ እዛች የምናውቃት
ቦታ ወስጄ ለጥፊያታለሁ...
ፈቅድህ እንደሚሆን ተስፋ በማድረግ.. :D :D
ምላሹ የሚገርም ነበር
መልካም ጊዜ...
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby መልከጻዲቅ » Tue Feb 12, 2008 10:11 pm

Ocean 12....እንዲህ ሲል......አስተያየቱን..... ቸረኝ..... 8)

Code: Select all
ጋሸ መልከጻዲቅ ይቺን ግጥምህን ወድጃታለሁ ...
ሳይታክተኝ አንብቤ በመጨረሻው ዋ ...ው ! ብያለሁ
እረ በርታልኝ ...


Thank U , እግዚአብሄር ይስጥልኝ.....ኦሽናችን..... 8) አንዳንዴ.... ብሶትህን.....ሀዘንህን.....የውስጥ ስሜትህን.....መከፋትህን.....የሚሰማህ ሲጠፋ....ራስህ...ለራስህ....ትጮሀለህ... :wink: እኔም...ሳላውቀው ጮክ...አልኩ...መስለኝ...... :!:
አመሰግናለሁ.....ስለአስተያየትህ....... 8)
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby እንሰት » Wed Feb 13, 2008 2:01 pm

ብርሃኑ እንዲህ ከተበ።

ፈጣሪና አበሾች


አበሾች ተጣልተው አበሾች ሊያስማሙ
በይቅር ለግዚያብሄር ጉንጭ ሊያሳስሙ
ዋሽቶ ማስታረቅን መልካም ነው ይላሉ።
መዋሸት ሃጢያት ሲል የመጽሃፍ ቃሉ
ፈጣሪና አበሾች እዚህ ጋ ተጣሉ


በስንታየሁ አባተ
ጣይቱ ማእከል

ዲሲ ጥር 2000 ዶ /ር ብርሀኑ ነጋ እንደጻፈው


ocean12 ም ተድምሞ አሰላሰለ።
እውነት ብሏል ብርሀኑ ... አስቤውም አላውቅ ነበር ... አይ የኔ ነገር ...


እውነት አይደል? የሚገርም እይታ ነው ።

ocean12 በትህትና ....
እንሰት ወደ መጀመሪያዎቹ ገጾች ተመልሼ ሄጄ አንዷን ደስ ያለችኝን ግጥም ተውሼ እዛች የምናውቃት
ቦታ ወስጄ ለጥፊያታለሁ ... ፈቅድህ እንደሚሆን ተስፋ በማድረግ .. ምላሹ የሚገርም ነበር
መልካም ጊዜ ...


የኔ ጌታ ፈቃድም አያስፈልግህም:: ቤቱ ያንተም አይደል...የድረ ገጹ አምድ አላማ እሱው ነው። ደስ ስላለህ እና ስለተዋስክ ደስ ብሎኛል።

መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
በ 1857 በአለቃ ዘነብ ተጻፈ።
በ 1924 በጎህ ጽባሕ ማተሚያ ታተመ ዓ .ም አዲስ አበባመጽሐፈ ጨዋታ ወንጌላዊ
ክፍል 2


ክፍል 4
ማርያም ሰማይን መሰለች ከቶ እሳቱ አጥቁራት ይሆን።አይሁድ ቀን ሆኖ ሳለ በምድር ሲሄዱ የተናቀው ደንጊያ እንቅፋት ሆነባቸው ምነው አስተውለው ቢሄዱ፤ ኒቆዲሞስ ግን በሌሊት ሲሄድ በውሃ ውስጥ መንገድ አገኘ፤ ወሃም ከ5ሺ ከ500 ዘመን መክና የነበረች አሁን ከእግዚአብሔር ልጆች ወለደች።
ከቶ ልጅነት አይቀርም ኢየሱስ ከዮሐንስ ጋራ እጫወት ብሎ ከዮርዳኖስ ባሕር ላይ ወደቀ በርሱም ድንጋጤ ሰማይ ተከፈተ።አባቱም ከላይ ሆኖ ልጄ ወዳጄ ሲል ዋለ፤ ዮሐንስ እነሆ የእግዚአብሔር በግ እያለ ለምን ያሳየዋል ያለጊዜው ይታረድ ብሎ ነውን፤ ቢታረድስ የታደሉና የተመረጡ ጀግኖች ይበሉታል እንጂ ፈሪ አይበላውም።እርሱም ምስጢር አይችል ብናበላውና ብናጠጣው ካባቱ ዘንድ ያየውን ሁሉ ነገረን፡፤
ለቀበሮች ጉድጋዋድ አላቸው ለሰማይ ወፎችም ማረፊያ ዛፍ አላቸው ለሰው ልጅ ግን እራሱን የሚያስጠጋበት የለውም ይላል፤ ለካ ሰማይና ምድር ቢጠበው ነው ከሰው ውስጥ ምውጥቶ ያደር እንደባሪያም የመሰለ።
ኢየሱስ ሠርግ ቢጠሩት በቃና ዘገሊላ ወሀውን ጠጅ አድርጎ አጠጣ በሰው ሠርግ እንደዚህ የሆነ በራሱ ሠርግ እንዴት ይሆን የእግዚአብሔርን ልጅ ሠርግ አይቼ ከድግሱም በልቼ ጠጥቼ ከዚያ ወዲያ ምነው በሞትሁ።
እየሱስ ክርስቶስ ኑ ያባቴ ቡሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን ውረሱ ይላ ዓለም ሳይፈጠር ምን ኖሮታል ጥበቡ አይታወቅ።ክፍል 5
እናንት የዓለም ብርሃን ናችሁ አለ መብራት አብርቶ በእንቅብ ውስጥ የሚኖር የለም ይላል፤ ዓለምን ያህል እንቅብ ደፍቶብን የለምን እኛ በወዴት እናብራ ጳውሎስስ እንክዋ እስከ እድሜው ልክ አበራ።
አንተ ነጋዴ እያላችሁ ለምን ትሳደባላችሁ ገበያ ተደመቀ ምን ደኅና አለ ከእግዚአብሔር የበለጠስ ምን ንጉሥ አለ ገበያ ቢያመቸው 1ልጁን ለዓለም አለወጠውምን ዮሴፍንስ ወንድሞቹ ለ50 ብር አልሸጡትምን ከተሸጠ በኃላ ግን ለምድር ግብጽና ለከነዓን አገር የራብ መድኃኒት ሆነ።
አንበሳ ከርስቶስ በዚህ ዓለም ዱር ገባ ምን አንስሳ ይስብር ይሆን ከዲያቢሎስ በቀር፤ እነዚያ አራቱ መላእክት እንስሶች ናቸው ከጀርባቸው ላይ አንድ ፍም መጥቶ ተሰው ላይ ሲወድቅ አለመናገራቸው ከነዚህስ ገብሬኤል ይሻላል ተሽቀዳድሞ መጥቶ ለቆንጆይቱ የነገረልነ።
የሰማይ እሳት ከሰው ላይ ወድቆ አለማቃጠሉ ምንድር ነው፤ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ልጅስ ገንዘባችሁን እየሰበሰባችሁ ወደ ሰማይ ላኩ፤ ከዚያ ይቆያችኋልና ይለናል፤ ለካ የርሱ ገንዘብ አልበቃው ቢል ወደኛ ልጁን የላከ ቀስ ብሎ ገንዘባችንን በብልሀት እንዲያከማች ኖሯል፤ እንግዴህ አውቀንበት ገንዘባችንንም አናባክን፤ከሰማይስ እኛ ምን አለን፤ገንዘባችንን ወደዚያ አሸክመን ከምንልክ አንካሶችን እውሮችን ችጋረኞችን ወንድሞቻችንን ይዘን እንክት እያደረግነ እንበላዋለን፤እንጠጣዋለን፤እንለብሰዋለን፤በገዛ ገንዘባችን ምን ይመጣብናል፤ አላመጣችሁም ብሎ የሚያደርገውን እስቲ እናያለን።
አባቶቻችንን ከዚህ ቀደም አታሎ ያወጣው ገንዘብ ይበቃዋል ባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ገመል በመርፌ ቀዳዳ መሄድ ይሻላል ይላል፤ ከርሱ የበለጠ ባለጠጋ አለን፤እርሱ በመንግስተ ሰማያት ይኖር የለምን፤ይህንን እያመካኘ የሰው ገነዘብ አሻግሮ ማየቱ ምንድነው ከዚህ ቀደም አሥሩን ተናግሮ ተናግሮ ከወንጌል አደረሰን፤አታስቡ እያለ ገንዘባችንን ሊያስበላብን ወዲያው ተርቤ አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም፤ታርዤ፤አላለበሳችሁኝም።ታምሜ አላያችሁኝም፡፤እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝም።ታሥሬ፤አልጠየቃችሁኝም ይላል፤ ይህን ያህል ስድስት ቃል ምን ያናግረዋል፤ ወዲህ ለነገ አታስቡ ይላል፤ወዲህ አላበላችሁኝም ይላል፡፤ከኛ ወገን የተራበ፤የተጠማ የታረዘ የለም መስሎት ይሆን ተሰማይ ተሰዶ መጥቶ ተርቤአለሁ ተጠምቻለሁ ታርዣለሁ ምንድር ነው፤ሰማይን ያህል ሰፊ አገር ይዞ አባቱ ከዚያ አያበላውም፤አያጠጣውም፤አያለብሰውም፤ልጁስ ሲቀላውጥ ነውር አይፈራምን፤ እኛስ ለሰማይ ንጉሥ ልጅ አናበላም፤አናጠጣም፤አናለብስም፤ከዚሁ ካሉት ከድሆች ወንድሞቻችን ጋራ ገንዘባችንን ተካፍለን እንበላለን፤እንጠጣለን፤እንለብሳለን።
እንደዚህ ያለ ዘወትር ንዝንዝ ምንድር ነው፡ በወንጌል ገንዘባችንን ሊወርስ የጦም አዳር እያለ ሊከፈለን አስቧል መሰል።

መልካም የስራ ሳምንት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ድረ ገጽ - ጋዜጣ ? ሐዋርያ

Postby እንሰት » Sat Feb 16, 2008 11:21 am

ሰላም ወገኖች
ቶሮንቶ - ካናዳ የሚዘጋጅ ጋዜጣ ድረገፅ? አድራሻ አገኘሁና ልጠቁማችሁ በቀዳም ሰንበት ብቅ አልኩ::
ሐዋርያ
http://www.hawarya.net/Hawarya-Amharic.htm
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ባቲ » Sat Feb 16, 2008 8:16 pm

እንሰት ሰላምታዬ ካለሁበት ከች ይበልልህ
ውለታ እየበዛህብን ነው::
ሐዋርያ ጋዜጣን እየገዛሁ እዚህ አነበው ነበር ከጥቂት አመታት በፊት:: ቆየሁ ግን አሁን ካነበብኩ:: ሐዋርያውን እያሳደድኩ የማነበው ዋነኛ ምክንያቴ የገሞራው ምርጥ ምርጥ ግጥሞችና መጣጥፍ ጋዜጣው መሀከል ስለማገኛቸው::
ይመችህ አባ
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Postby ocean12 » Sun Feb 17, 2008 7:01 pm

ይህችን ግጥም ከአዲስጊፍትሾፕ ድረ-ገጽ ላይ አገኘሁዋትና ብንካፈልስ ብዬ እዚህ አመጣሁዋት...

ክልክል ነው

ማጨስ ክልክል ነው!
ማፉዋጨት ክልክል ነው!
መሽናት ክልክል ነው!
ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል
የቱ ነው ትክክል?
ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ሀይል ባደለኝ
"መከልከል ክልክል ነው!" የሚል ትዛዝ አለኝ::

በእውቀቱ ስዩም
የሳት ዳር ሀሳቦች 2000

ምስጋና ድረ ገጹን ለጠቆመን ነቢያት.
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby ocean12 » Fri Feb 29, 2008 5:22 am

ከሎሬት ጸጋዬ እሳት ወይ አበባ ዛሬም አንዱዋን ደስ ያለችኝን
ግጥም መርጨ ላካፍላችሁ ነው አመጣጤ:
ተወኝ
http://www.freewebs.com/ethiopians/Microsoft%20Word%20%2D%20tewegn2.pdf
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby እንሰት » Sat Mar 01, 2008 1:14 pm

ocean12 wrote:ይህችን ግጥም ከአዲስጊፍትሾፕ ድረ-ገጽ ላይ አገኘሁዋትና ብንካፈልስ ብዬ እዚህ አመጣሁዋት...

ክልክል ነው

ማጨስ ክልክል ነው!
ማፉዋጨት ክልክል ነው!
መሽናት ክልክል ነው!
ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል
የቱ ነው ትክክል?
ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ሀይል ባደለኝ
"መከልከል ክልክል ነው!" የሚል ትዛዝ አለኝ::

በእውቀቱ ስዩም
የሳት ዳር ሀሳቦች 2000

ምስጋና ድረ ገጹን ለጠቆመን ነቢያት.

ምስጋና ለማያልቅበት ውቅያኖሳችን:: በእውቀቱ በውነት የሚገርም ልጅ የሚገርም ገጣሚ ነው::
አንዲት ውብ ጅምር ድረ ገጽ ባገኝ ከጠፋሁበት ጉዋዳ ብቅ አልኩ።
http://www.freewebs.com/ethiopians
እኔ ከነ ዘፈኑ ወድጄዋለሁ:: ምናልባት የጌቱ ኦማሂሬ ሀገሬ ዘፈን intro ቢሆን የበለጠ ያምራል ልበል? ጎብኙና አስተያየት ስጡበት::
ሰናይ ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ወጋየሁ ንጋቱ

Postby እንሰት » Sun Mar 02, 2008 9:12 pm

በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2004 የወጋየሁ ንጋቱን ድረ ገጽ አገኘሁና አንድ ሁለት መጣጥፎችን አተመኩ:: ሳስታውስ wegayehu nigatu art center የሚባል ድርጅት ይመስለኛል ድረገፁን የጀመረው::
አሁን አድራሻውን ፈላለኩና እዚህ አመጣሁትhttp://www.wegayehunegatu.org

ምን ገጠመኝ መሰላችሁ::ጽሁፎቹ እንዳሉ ለማረጋገጥ ፍተሻ አድርጌ ምንም ነገር የለም:: ፒሲዬ የስህተት ምልክት አሳየችኝ::

እስኪ ዋርካውያን እና ዋርካውያት መላ አያጡም ብዬ እዚህ ከተብኩት:: መላ በሉ::

መቼም ወጋየሁ ንጋቱ ማን ነው ተብዬ እንደማልጠየቅ ነው::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

የቆሎ ተማሪ ?

Postby እንሰት » Sat Mar 08, 2008 7:41 pm

ደህና ከረማችሁ
የዋርካው የቆሎ ተማሪ ይሁን ሌላ አላውቅም ግን ይህንን የዩቱብ ወይኖን አየሁና ላካፍላችሁ ብዬ ለጠፍኩት
http://www.youtube.com/watch?v=s73Peg9W9Zw
ሰናይ ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests