የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Re: ለ ocean12 እና ለ Kiyora

Postby መልከጻዲቅ » Wed Nov 07, 2007 3:10 am

እንሰት:እንዲህ:ሲል:ጻፈ(ች) "......... ይህንን ግጥም ካሁን በፊት ያነበብኩት ቢሆንም አሁን ግን እንደገና ለማግኘት በማልችልበት ሰዓት እዚህ ፖስት ስላደረግሽልን ከፍ ያለ ምስጋና !
አንቺን ጨምሮ ሌሎቻችሁም የግጥሞችንና ጽሁፎችን ማያያዣዎች (ሊንክስ ) እዚህ ፖስታ ያደረጋችሁ ሁሉ
በርቱ ...እጃችሁን አያሳጥርብን .........
ሰላም ሰንበት
ሰላም ለሁላችን
ocean12 ገብረ ክርስቶስን ከወደድከው/ሽው አንድ ሁለት መጣያ ከመጽሃፉ ነቅሻለሁ እነሆ........."
ውድ;እንሰት:ሰላምና:ጤናን:እመኛለሁ.... በስነጽሁፍ:መድረክ;ይህ:የመጀመሪያዬ:ነው! የስነ-ጽሁፍ;አፍቃሪ:ስለሆንኩኝ;ብቅ;ማለቴ;አይቀርም......
እንግዳ:ተቀባይ:ከሆናችሁ.... :wink: :wink:
አስቸጋሪ;እንግዳ;እንዳልባል;እንጂ;የደራሲ;ጸጋዬ;ገ/መድህንን:
ስራዎች;ከየትኛው:web-site or link እንደማገኝ:ብትጠቁመኝ:
ደስ:ይለኛል....!!ከታላቅ:አክብሮት:ጋር!!


__________________________
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

መልስ

Postby እንሰት » Wed Nov 07, 2007 10:25 am

መልከጻዲቅ wrote:..."
ውድ;እንሰት:ሰላምና:ጤናን:እመኛለሁ.... በስነጽሁፍ:መድረክ;ይህ:የመጀመሪያዬ:ነው! የስነ-ጽሁፍ;አፍቃሪ:ስለሆንኩኝ;ብቅ;ማለቴ;አይቀርም......
እንግዳ:ተቀባይ:ከሆናችሁ....
አስቸጋሪ;እንግዳ;እንዳልባል;እንጂ;የደራሲ;ጸጋዬ;ገ/መድህንን:
ስራዎች;ከየትኛው:web-site or link እንደማገኝ:ብትጠቁመኝ:
ደስ:ይለኛል....!!ከታላቅ:አክብሮት:ጋር!!
__________________________

ሰላም መልከ ጻዴቅ
እሳት ወይ አበባ እኔም የለኝም። ብዙ ልረዳህ አልቻልኩም። አንዳንድ እዚህ የተዘረዘሩትን ድረ ገጾችን ብትጎበኝ ግን ስለ ብላቴን ጌታ ፍንጭ ይሰጡሃል። የተወሰኑ ግጥሞቹም አሉበት።
Our father FROM HIS daughters Mahlet and yodit
http://www.seleda.com/jan01/tsegaye.shtml
Tsegaye’s interview with lines from his theatre ‘ የከርሞ ሰው’
http://yekolotemari.blog.com/591565/
ናጋቲካ ያ ጋሼኮ!....
http://www.ethioforum.org/images/Gashe_Tsegaye.pdf
http://www.blengrafix.com/blenmagazine/amharic_poem.htm
ለሰአሊው እስክንድር ቦጎስያን መታሰቢያ የተጻፈ ግጥም
http://www.youtube.com/watch?v=YhYzrTqkEV8
የጸጋዬ መታሰቢያ
ገና ጅምር ይሁን እንጂ የጸጋዬ መታሰቢያ ተብሎ የተዘጋጀ ድረ ገጽም አለ
http://www.tsegaye.se/#
http://www.ethiopians.com/tsegaye/ የህይወት ታሪኩ
http://www.quatero.net/meta/Laureate%20Tsegaye.pdf የህይወት ታሪኩ
http://www.ethiopians.com/abay/ አባይ
የት አባቱ ሞትም ይሙት
http://folk.uio.no/abie/Mott_Tsegaye.pdf
መልካም ቅኝት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Wed Nov 07, 2007 2:47 pm

እግዚአብሄር;ይስጥልኝ! እንሰት;ስለመልሱ...በጣም:አመሰግናለሁ!! ያልከኝን:ማጣቀሻዎች:አያቸዋለሁ....ወደሆላ..ጥላ..በረድ:ሲል.......
ጨረቃ...መውጣት....ስትጀምር....!!!
ለመቀለድ:ብዬ:ነው......... መጽህፉ;የሚገኝበትን:አድራሻ;ስትስማ...አትርሳኝ!!
ከማክበር:ጋር! 8) 8)
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

መልከጻዲቅ

Postby እንሰት » Fri Nov 09, 2007 5:44 pm

መልከጻዲቅ wrote:እግዚአብሄር;ይስጥልኝ! ....ወደሆላ..ጥላ..በረድ:ሲል.......
ጨረቃ...መውጣት....ስትጀምር....!!!
....... መጽህፉ;የሚገኝበትን:አድራሻ;ስትስማ...አትርሳኝ!!
ከማክበር:ጋር! 8) 8)

ሰላም የመጽሀፉን አድራሻ ለመፈለግ የኢትዮጵያ ካርታ አስፈልጎኝ ኖሮ ወዲህ አንዱ ግድም ካርታው ተገኘ::
ለዛሬ ስለኢትዮጵያ ካርታ አድራሻ ልጠቁም:: ተማሪዎች ካላችሁ ይጠቅማል ብዬ ነው::

2006 Atlas of the Ethiopian Rural Economy
http://dx.doi.org/10.2499/0896291545


መግቢያውን ላስነብባችሁ
ይህ የኢትዮጵያ የገጠር ኢኮኖሚ አትላስ በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ስለሚገኙ ግለሰቦችና ቤተሰቦች የኑሮ ሁኔታና የአኗኗር ዘይቤ፣ በተለይ በግብርናው ዘርፍ ስለተሰማሩባቸው ቀያዊ የኢኮኖሚ ዘርፎች ዝርዝር አካባቢያዊ መረጃ የሚሰጥ ጠቃሚና በቀላሉ የሚገኝ አዲስ የመረጃ ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡ በአትላሱ ውስጥ የተካተቱት ካርታዎች ከእርሻ በተጓዳኝ ከብት እርባታ ዋነኛ መተዳደሪያ በሆነባቸው የሀገሪቷ ገጠራማ ሥፍራዎች በወረዳ ደረጃ ስላለው ስለአጠቃላዩ ሕይወታዊና ጉዛካላዊ አካባቢ፣ ስለማህበራዊ አገልግሎቶች ሁኔታ፣ ስለህብረተሰቡ ስነህዝባዊ ጠባያት፣ እንዲሁም ስለሰብልና እንስሳት ምርት አሃዛዊ መረጃ ያቀርባሉ፡፡ በዚህ አትላስ ውስጥ የሚገኙት ካርታዎች በመላ ሀገሪቷ በተጨባጭ ስላለውም ሆነ እንዲሁም በታሳቢው የኑሮ ደረጃና የመሬት አጠቃቀም ዘዴ ላይ አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩ ሁኔታዎች፣ እንዲያውቅ ያስችሉታል፡፡ ይህን አትላስ በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ በወረዳና በዞን ደረጃ ያለው መረጃ የተወሰደው በዋነኛነት በማእከላዊ የስታቲስቲክስ ኤጀንሲ (ማስኤ) ተሰብስቦ ከተሰናዳው የመረጃ ቋት ሲሆን ከሌሎች የመንግስት ተቋማት የአጠቃላይ መረጃ ምንጮች የተገኘ ውሂብም ተጨምሮበታል፡፡ ከሁሉም በላይ ለዚህ አትላስ ዝግጅት ዓቢይ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለገለው እ.አ.አ. በ2002 (1994 ዓ.ም.) በማስኤ አማካይነት የተካሄደው የኢትዮጵያ የግብርና ናሙና ቆጠራ ውጤት ነው፡፡ ከሌሎች ምንጮች የተገኘው መረጃ የሚከተሉትን ጉዳዮች የሚያካትት ነው፤ እነሱም ስለመሬት አቀማመጥና ስለምድር ሽፋን ከሳተላይት የተቀረጸ መረጃ፣ ከፍተኛ የቀለም ጥራት ደረጃ ያላቸው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መረጃዎች፣ እ.አ.አ. በ1994 ዓ.ም. በተካሄደው የኢትዮጵያ የህዝብና የቤቶች ቆጠራ ላይ የተመሰረቱ የህዝብ እድገት ትንበያዎች፣ በመንግስታዊ ተቋማት ስለሚሰጡ የአገልግሎት አውታሮች የተዘጋጁ አስተዳደራዊ ሰነዶች ናቸው፡፡ የዚህ አትላስ ዋነኛ ታሳቢ ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያን የዘላቂ ልማት እና የድህነት ቅነሳ መርሀግብር፣ በተለይ ደግሞ በሀገር አቀፍ፣ በክልልና በወረዳ ደረጃ ያሉትን የግብርናና የገጠር ልማት ፖሊሲዎች እንዲሁም ስትራቴጂዎች በመንደፍና በማስፈጸም እንቅስቃሴ ተሳታፊ የሚሆኑ ፖሊሲ አውጪዎችና ተንታኞች ናቸው፡፡ በአትላሱ ሊካተቱ የሚገባቸውን ጉዳዮች በመምረጥ ረገድ ዋናው መመዘኛ ‘የሚካተተው መረጃ በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ስለሚገኘው ድህነት አካባቢያዊ ገጽታ እና ስለኢኮኖሚ እድገት አማራጮች ያለንን እውቀት ሊያዳብር ይችላል ወይ?’ የሚለው ቁልፍ ጥያቄ ነበር፡፡ ስለዚህ አትላሱ በመላ ሀገሪቷ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፍጠር ታስበው የሚወሰዱ እርምጃዎችን በየአካባቢው ለማቀድ ጠቃሚ ሰነድ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በጣም ሰፋ አድርገን ስናየው ደግሞ አትላሱ ከዚህ ከፍ ያለ ትርጉም አለው፡፡ ያልተማከለ የውሳኔ አሰጣጥ እየጨመረ በመምጣቱ በማደግ ላይ ባለው የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ውስጥ የፖሊሲ ውሳኔዎች የሚተላለፉት በቀድሞ ጊዜያት እንደሚደረገው በጥቂት ግለሰቦች ሳይሆን ከጊዜ ወደጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ በሚሄድ የህብረተሰቡ አባላትና ወኪሎች ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ አትላስ የሚሰራጨው ለዋና የመንግስት ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆን ለምክር ቤት አባላት፣ለአካባቢ መሪዎች/ታዋቂ ግለሰቦች ፣ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች፣ ለኢኮኖሚና ለማህበራዊ ጉዳይ ተመራማሪዎች፣ ለትምህርት ተቋማትና ለለጋሽ ድርጅቶቸ ጭምር ነው፡፡ በፖሊሲ ቀረፃ ሂደት ውስጥ ተሳትፎ የሚኖራቸው እንደእነዚህ ዓይነት ተቋማት ሁሉ ለኢትዮጵያውያን፣ በተለይ ደግሞ ለገጠሩ ክፍል ነዋሪዎች የተሻለ ልማት ስለሚገኝበት መንገድ ለመመካከርና ለመከራከር በተቻለ መጠን ጠቀም ያለ መረጃ ማግኘት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ አትላስ የተዘጋጀው ለእንዲህ ዓይነቱ የፖሊሲ ቀረፃ ተግባር መመሪያ የሚሆን መረጃ ለማቅረብ ነው፡፡ በሀገሪቷ ውስጥ ስላለው ተጨባጭ ሁኔታ ሰፊ መረጃና እውቀት ያላቸው ፖሊሲ ቀራጮችን በማፍራቱ ረገድ የዚህ አትላስ መዳረስ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ስለዚህም የዚህ አትላስ ለትምህርት ተቋማት (ለዩኒቨርሲቲዎችም ሆነ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች) መሰራጨት ይገባዋል፡፡ የዛሬዎቹ ተማሪዎች ነገ የሀገሪቷ ፖሊሲ አውጪዎችና መሪዎች ይሆናሉ፡፡ አትላሱ እነዚህ ተማሪዎች በገጠር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መተዳደሪያቸውን ስለሚያገኙበት ጉዛካላዊ የግብርና አካባቢ ልዩ ልዩ ጠባያት መሰረታዊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ocean12 » Sat Nov 10, 2007 3:40 am

እንደገና አሁንም በጣም አመሰግናለሁ.....
ግጥሞቹም ብቻ አይደሉም የድረ ገጽ አድራሻዎቹ በጣም ደስ የሚያሰኙ ናቸው....
በተለይ brango ን ወድጀዋለሁ.
ስለሁሉም ጎንበስ ብያለሁ ለምስጋና.
ውቅያኖስ
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

ሕምምምም..

Postby ዋኖስ » Sat Nov 10, 2007 7:02 am

ዕንሰት ልፋትሕን አደንቃለሁ! ነገር ግን ልፋትሕንና የተጠቃሚዉን ቁጥር ስመለከት ግን ከንቱ ድካም ነዉ! የማንበብ ባሕላችን እዚሕ ግባ ሊባል የማይችል ሥለኆነ ተሥፋ አስቆራጪ ሁናቴ ላይ ዕንዳትደርሥ እሰጋለሁ! በርታ! እጅግ ቆንጆ ሥራ ና ጥቆማ ነው!

ከመልካም አድናቆት ጋ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Re: ሕምምምም..

Postby መሰማማት » Sat Nov 10, 2007 7:26 am

ዋኖስ wrote:ዕንሰት ልፋትሕን አደንቃለሁ! ነገር ግን ልፋትሕንና የተጠቃሚዉን ቁጥር ስመለከት ግን ከንቱ ድካም ነዉ!

ከመልካም አድናቆት ጋ


በፍጹም በፍጹም ከንቱ ድካም አይደለም::አንድ ሰው እንኳን ቢያየው በጣም ጥሩ አስተዋጽኦ ነው::እኔ እንደአዋጅ ነጋሪ ነኝ:ደስ የሚል ነገር ካየሁ በኢሜል ላማውቀው ሁሉ ነው የማዳርሰው:: እንሰት ተባረክ/ኪ(ኸረ ጾታ ይገለጽልን):: ቆንጆ ስራ ነው::መለስ ዙፋን ሲለቅ እንሰት ለፕርይምሚንስተርነት!!
መሰማማት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 290
Joined: Mon Aug 20, 2007 6:37 am

Postby መልከጻዲቅ » Sat Nov 10, 2007 3:58 pm

ሰላም:እንሰት :idea: :idea:
በጸጋዬ:ገ/መድህን:መጽሀፍ:አንጻር:የተጀመረው:ጉዞ:ቀጥሏል.... :!: ስለአትላሱ:የሰጠሀው:ግልጽና:ዝርዝር:ማብራሪያ:በራሱ:ጠቃሚ:
ትምህርት:አለው:: :idea: :idea: እኔ:አንድ:ነገር:አውቄአለሁ.....
ምስጋናዬ:ይድረስ..... 8) 8)
ከማክበር:ጋር!!!
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ocean12 » Sat Nov 10, 2007 7:09 pm

ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby ocean12 » Sat Nov 10, 2007 7:10 pm

ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ

Postby ocean12 » Sat Nov 10, 2007 7:38 pm

መልከጻዲቅ ምናልባት ትወደው ይሆናል በማለት ይህንን ከጸጋዬ ገብረ መድህን እሳት ወይ አበባመሸ ደግሞ አምባ ልውጣንጀባ ብያለሁ

http://www.freewebs.com/zelalemethiopia/Pdf%20files.pdf
ያለውን የወረወረ አይነት ነገር ነው....እስኪ ያቆየንና ሌላም የምወረውረው አላጣም::
እንሰት ለግጥሞቹ ዝጌር አብዝቶ ይስጥልኝ
ሰላም ሰንበት
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sat Nov 10, 2007 8:46 pm

ሰላም:ውቅያኖስ:አንተ;ወይም:አንቺ;ለማለት;ስለተቸገርኩ:
እንዲያው:በደብዛዛው:ምስጋናዬ:ይድረስ....Yes I loved It 8) 8) ይህንን:ግጥም:ካነበብኩት:በጣም:ቆይቷል....ተባረክ(ኪ)
ምናልባት;ሁኔታው:ሲመች:ቡዙ:ጊዜ:የምሳተፈውPolotical forum ላይ:ስለሆነ:የደራሲያን:ጉዳይ:ሲነሳ:ይህንን:ግጥም:
እለጥፈዋለሁ....ፍቃድህ(ሽ):ካልሆነ:ግን:ይቀራል..... 8) 8)
ሌላም:ሲኖር:እንግዲህ:አትርሳኝ! :wink: አትርሺኝ..... :wink:
ከማክበር:ጋር!!
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ocean12 » Sat Nov 10, 2007 9:13 pm

መልከጻዲቅ wrote:ሰላም:ውቅያኖስ:አንተ;ወይም:አንቺ;ለማለት;ስለተቸገርኩ:
እንዲያው:በደብዛዛው:ምስጋናዬ:ይድረስ....Yes I loved It 8) 8) ይህንን:ግጥም:ካነበብኩት:በጣም:ቆይቷል....ተባረክ(ኪ)
ምናልባት;ሁኔታው:ሲመች:ቡዙ:ጊዜ:የምሳተፈውPolotical forum ላይ:ስለሆነ:የደራሲያን:ጉዳይ:ሲነሳ:ይህንን:ግጥም:
እለጥፈዋለሁ....ፍቃድህ(ሽ):ካልሆነ:ግን:ይቀራል..... 8) 8)
ሌላም:ሲኖር:እንግዲህ:አትርሳኝ! :wink: አትርሺኝ..... :wink:
ከማክበር:ጋር!!

እረ አይገባም አይገባም... :) :) ሌላ ጊዜ አንተ በሚለው ልጠቀስ እችላለሁ...ባለፈው የጸጋዬን ግጥሞች እንደምትፈልግ ስላየሁ ይቺን ግጥም በpdf ለማዘጋጀት አሳሬን ነው ያየሁት... :) :) ስቀልድ ነው
ግን አንድ ነገር እንድማር ምክንያት ሆነልኝ....
ሌላውን ደግሞ እንግዲህ እሱ ያለ ለት ....
ምናልባት ነገ.. :)
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

ምስጋና

Postby እንሰት » Sat Nov 10, 2007 10:40 pm

ለ ocean12፣ ዋኖስ፣ መሰማማት፣ መልከጻዲቅ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ። ቤቱ የሁላችን ለሁላችን በሁላችን ነው እንዲህ አሰማምሩት እንጂ ። ለእያንዳንዳችሁ አስተያየት ተገቢ አክብሮታዊ ወገናዊ እና ወንድማዊ መልስ ለመስጠት ፈልጌ ሁሉንም አንዴ በአንድ post, quote ለማድረግ እውቀቱ አነሰኝ ። ለማንኛውም በተለይ ዋኖስ ላነሳኸው አስተያየት ከአጠቃላይ የንባብ ባህላችን ጋራ አዛምጄ አንድ ነገር እላለሁ።
እስቲ አረፍ በሉ።
በደረቁ አደርቅሁዋችሁ አይደል?
ምን ላምጣ? ምን ልጋብዝ?
በዚህ አዝግሙ፤
“...ፍቅሬም ትውስ ትለኛለች:: ከወይራው ስር:: ሳላስበው ፊቴ ላይ ድቅን ብላ ፈገግታዋን ትቸረኛለች:: እኔ ጋ ሁና እኔ ጋ ግን የለችም:: ከወይራው ስር እናቴም ብቅ ብላ የናትነት ፍቅርዋን ሳትሰስት ታንበሸብሸኛለች:: እናቴ ለኔ ብርቄ:: ሃብቴና ወርቄ:: ብርሃኔ:: የሌሊትም ኩራዜ:: ከወይራው ስር አባቴ የኔ ክብር የኔ ኩራት የኔ መመኪያም ትውስ ይሉኛል:: ያባትነት ፍቅራቸው እንደ ክረምት ዝናም ከላዬ ላይ ይዘንባል:: የሳቸው ሳያካፋ የህቴ ይከተላል:: የወንድሜም መብረቅና ነጎድጉዋድ ሆኖ የህቴን ያጅበዋል:: ሁሉም ተሰልፈው ፍቅራቸውን ተራ በተራ “እንካ” ይሉኛል:: እኔም እቀበላቸዋለሁ:: ቢርቁም ቅርቤ ናቸው:: ከወይራው ስር:: ጉዋደኞቼም የድሮ ዘፈናችንን እየዘፈኑ ዳንሳችንን እየደነሱ ፍቅር የተራበችውን ልቤን ደስታን ይመግቡዋታል:: በናፍቆት እንባ ያስታጥቡዋታል:: ከወይራው ስር:: ታዲያ ግን ምን ያደርጋል? ከወይራው ስር ሆኜ ከትቤ የማልጨርሰው አለኝ ብዙ ነገር ውስጥ ውስጤን የሚበላኝ:: አንዳንዱ አስደሳች አንዳንዱ አሳዛኝ:: ያንኑ የከተብኩትን መልሼ ሳነበው ለነፍሴ ሐሴት ነው:: ለነገሩ ስለ ህይወት ሁሉም ነገር መጻፍ የለበትም:: አንዳንድ ነገሮች ዝም ብለው መደነቅ የሚገባቸው ናቸው:: በቃላት ህይወት ልንሰጣቸው ስንሞክር ወይ እንገላቸዋለን ወይ አካለ ስንኩል አድርገን ውበታቸውን እንቀንሳለን:: ስለዚህም ውብ ሆነው በአዕምሮ የትዝታ ካዝና ውስጥ ተከርችመው መቅረት ይኖርባቸዋል:: አዕዋፋትና ሌሎች የዱር እንስሳት የምጽፈውንና የማነበውን እያዩና እየሰሙ እንደጉዋጉ እንዳይቀሩ እነሆ ለነሱ ስል ይህን መድረክ ከፈትኩ:: ከጻፍኩዋቸው ነገሮች ጥቂቶቹን ልጋራቸው:: ከወደዱ ወደዱ ከጠሉም ጠሉ:: እኔ ምንተዳዬ! ማካፈል ያማረኝን ብቻ አካፍላለሁ:: ከወይራው ስር::...”

ይህ ጥቅስ የተቀነጨበው ከዋርካ ቤተሰባችን አንድ ከሆነው ብራንጎ ነው። ለዛሬ ደግሞ የብራንጎን የስነ ጽሁፍ ድረ ገጽ ይሆናል እነሆ የምለው።
http://metatef.org/wpmu/brango
ጎብኝታችሁ፣ አንብባችሁ፣ እንደምትደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ።
መልካም ንባብ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Sun Nov 11, 2007 12:20 am

Ocean 12 እንዲህ:አለ......
Code: Select all
እረ አይገባም አይገባም ...   ሌላ ጊዜ አንተ በሚለው ልጠቀስ እችላለሁ ...ባለፈው የጸጋዬን ግጥሞች እንደምትፈልግ ስላየሁ ይቺን ግጥም በ pdf ለማዘጋጀት አሳሬን ነው ያየሁት ...   ስቀልድ ነው
ግን አንድ ነገር እንድማር ምክንያት ሆነልኝ ....
ሌላውን ደግሞ እንግዲህ እሱ ያለ ለት ....
ምናልባት ነገ ..


ውቅያኖስ....ተስማምተናል....ተግባብተናል.... :D :D
ከእንግዲህ:ሁሌም:በአንተና:እኔ:እንዘልቃለን.... 8)
"....መሽ:ደግሞ...አምባ:ልውጣን....." የጸጋዬን:ግጥም:ፋይሌ:
ውስጥ:የክብር:ቦታ:ሰጥቼ:አስቀምጫታለሁ... :idea: :idea:
እንግዲህ:የጸጋዬን:ስራዎች:ስታገኝ:አትለፈኝ!! እናም:ስትጠራኝ:ከች:እላለሁ.....ቡዙ:ጊዜ:የፖሎቲካውን:መድረክ:
ባዘወትርም:.....አሁን:አሁን:ግን:ወደዚህ:ቤት:ቶሎ:ቶሎ:መለስ:
ማለቴ:አይቀርም!!አንድ:ቀን:እስከናካቴው:ገብቼ:ዝጉብኝ:ሳልል:
እቀራለሁ:ብለህ:ነው :?: 8)
እንግዳ:አቀባበላችሁና:ፈጣን:መልሳችሁ....ልቤ:ገብቷል :D :D
ውቅያኖስ:ወንድሜ:ሰላምና:ጤናን:ላንተም:ለቤቱም:እመኛለሁ....!!
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests