የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ብራንጎናትርን » Wed Sep 24, 2008 6:54 pm

የገጣሚ ለምን ሲሳይ ድረገጽ:

http://www.lemnsissay.com/poems/index.htm :wink:

ድረገጹ በእንግሊዝኛ ቢሆንም እንደ አማርኛ ድረገጽ እንቁጠረው:: ድንቅ ጸሐፊ ነው:: :)
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
ብራንጎናትርን
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 736
Joined: Fri Dec 29, 2006 6:31 pm

Wordlist and spell checking for Amharic

Postby እንሰት » Mon Sep 29, 2008 5:19 am

http://www.cs.ru.nl/~biniam/geez/crawl.php

http://www.cs.ru.nl/~biniam/geez/install.php
Wordlist and Spell checking for Amharic and Tigrigna
Biniam Gebremichael biniamg@gmail.com

Spell check installation guide
Requirment
1. Open office
2. Amharic and or Tigrigna Dictionary
3. Geez Writer (to write geez documents)
Installation Guide
1. Install Open office. Open office is more or less the same as Microsoft Office, except that it supports more languages that MS office does. Open office can open Microsoft documents without any problem, and you can save your files as Microsoft documents incase you want to open it later with Microsoft office.
For example, get open office 2.0 from here.
2. If you don't have geez fonts already, get one or two from Geez writer.
3. The next step is to download and install Amharic and/or Tigrigna dictionaries into your open office installation. You need to unzip them first and copy ti_ER.dic, ti_ER.aff, am_ET.dic and am_ET.aff files to the dictionary directory of Open office. Usually this directory is located in "C:\program files\openoffice.org 2.0\share\dict\ooo\".
4. Tell Open office that you have installed the dictionary. Add the following two lines at the end of dictionary.lst (located in the same directory as above)
5. DICT am ET am_ET
6. DICT ti ER ti_ER

7. You need to restart your PC at this stage. Or stop soffice program from task manager.
8. Start open office writer and open your Amharic or Tigrigna document (or you can start typing a document if you have geez writer)
9. The default language setting in open office is english. you need to change that. Go to tools -> option -> Languages and change the default language for documents to Amharic or Tigrigna. For open office 2.0 this is available under the Western row.
Corpus building
To help Geez Natural Language Processing (NLP) developers, I have created a web crawler that collects Amharic and Tigrigna texts from the Internet. I wordlist is generated for both languages sorted by the number of occurances, as shown below.
This Geez Crawler software is similar to Kevin Scannell's Crubadan Corpus builder, except that the former is specific to Geez languages. If you want to know more about web crawling, read Kevin's site.

The word-lists is updated periodically, and it is free to download and use for research purpose. You will need a software to unzip the files and unicode font to properly display it.
• Tigrigna word list 227,984 words [.5M zipped]
• Amharic word list 397,352 words [1.5M zipped]
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ዋናው » Thu Oct 02, 2008 9:47 pm

እንሰት እንደሁሌው ምስጋናዬ ይድረስህ ደጅህ ሁሌም እርጥብ ው::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ብራንጎናትርን » Fri Oct 03, 2008 9:16 am

ላስት በት ኖት ሊስት .... :lol:

www.ezraart.net

ይጎብኙት ... ግሩም የሆነ ጀማሪ አርቲስት ነው:: የኒዮርክ ነዋሪ ... :wink:

(ዛሬ መቼስ ዋርካን ተሞላቀኩባት ወይንስ ተመላለስኩባት ነው የሚባለው??)
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
ብራንጎናትርን
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 736
Joined: Fri Dec 29, 2006 6:31 pm

Postby እንሰት » Fri Oct 03, 2008 6:26 pm

ብራንጎ! ብራንጎ! ብራንጎ!

አንዳንዴ በሀሳቦች በፍጭቶች መካከል የሚነበቡ የሚደመጡ ጥልቅ ምልከታዎች እውነታዎች ያስደምሙኛል።

ብራንጎናትርን� wrote:ኤኒዌ ... በአንድ ነገር ልስማማ .... አዎን እኛም አንዳንዴ የዞረብን ነን :: ምን እንደምንፈልግ ላናውቅ እንችላለን :: የናንተ ግን ገደቡን ይጥሳል እኮ ... ልባችሁ ልክ እናቶች እንደሚቋጥሩት ቋጠሮ ነው :: በጣም ጥቂቶች ናቸው ሊፈቱት የሚችሉት ::
Awesome! Thank you እስኪ ማብራሪያ አክልባት

መልካም ቀን
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ብራንጎናትርን » Fri Oct 03, 2008 9:08 pm

^ ወንድም እንሰት ምስጋናህን ተቀብያለሁ:: እኔም ስለመልካም ቃላቶችህ አመሰግናለሁ:: :)

ብዙም ሳላንዛዛ ምን ለማለት እንደ ፈለግሁ ለማብራራት ልሞክር ... :D

ሴቶች ብዙ ጊዜ ልባቸው አይገኝም ይባላል:: ግን ላመኑትና ላፈቀሩት ልባቸውን ብቻ ሳይሆን ነብሳቸውንም አሳልፈው ይሰጣሉ ለማለት ፈልጌ ነው:: ለማያምኑት ወንድ ግን ልባቸውን ክፍት ስለማያደርጉ እስኪያምኑህ ድረስ እንግዲህ ልክ ቋጠሮን እንደመፍታት መታገል ይኖርብሀል:: :lol:

አካበድኩት ነው የሚባለው .... ? :lol:

ሳስበው ግን እኛ በጣም እናካብዳቸዋለን እንጂ ሴቶች ምስኪኖች ናቸው ... ግልጽና እውነትን የሚፈልጉ -- ሁሉም ባይሆኑም:: :P

አረ ጉዴ ... ከመቼ ጀምሮ ነው ስለሴቶች ኤክስፐርት የሆንኩትኝ?? :lol: ትርንጎ ይሄን እንዳታነብና ጉድ እንዳትል .... :oops:
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
ብራንጎናትርን
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 736
Joined: Fri Dec 29, 2006 6:31 pm

Postby ብራንጎናትርን » Sat Nov 08, 2008 1:53 am

www.etiopiainitalia.com

ከዚህ በፊት የዚህ ድረገጽ መስራች ዋርካ ላይ አስተዋውቆት ነበር:: ደግሞ መለጠፉ አይከፋም ... :) ለለውጥ ያህል ... ምነው ዋርካ ትርምስምሷ ወጣሳ? :lol: በሌላ ዐለም ፍጡራኖች የተወረረች እስክትመስል ድረስ ተተራምሳለች::

...

ለኦባማ አድናቂዎች እንኳን ደስ ያለን:: ይህ ሳምንት በህይወቴ አዲስ ምዕራፍን ከፍቶ አልፏል::

አንድ ቀን ኢትዮጵያም ...

1) ለሆዳቸው ሳይሆን ለህዝባቸው የተሰለፉ
2) ለአንድ ቡድን ሳይሆን ለሁሉም የቆሙ
3) እንደ አንዳንድ ያረጁ ያፈጁ አሜሪካውያን ነጮች ለውጥን የማይፈሩ
4) ባለፉት ዘመናት የተናቁ የተረገጡና ከሰው በታች ሲቆጠሩ የኖሩ ወገኖቻችንን ከአሁኖቹ መሪዎች በይበልጥ ከፍከፍ የሚያደርጉና በእኩልነትና በፍትሀዊነት የሚያምኑ
5) ጎጠኝነት ያልበከላቸውና "የሰለጠነ የተማረው ገደል ገብቶ ያልተመረው ያክስቴ ልጅ ወይም ባል ወይም የጓደኛዬ ሚስት ስልጣን ይያዝ ወይም ትያዝ" የሚሉ ኮተታኮተቶችን ያላነገቡ
6) ራሳቸው ተከብረው ሀገራቸውን የሚያስከብሩ
7) ከተመጽዋችነት ነጻ የሚያወጡን
8) ዝናብን ከመለማመጥ ዘላቂና ተፈጥሮን በማይጎዳ መልኩ የመስኖ ግንባታን የሚያስፋፉ
9) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ባጠቃላይ (ካልተቻለም አብዛኞቹ) ኢትዮጵያን እንደ እናታችው እንጂ እንደ እንጀራ እናታቸው እንዳያይዋት የሚያደርጉ
10) ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላምን የሚፈጥሩ
11) የረሀብተኝነትና የድህነት አርማችንን ከምድረ ገጽ የሚያጠፉ
12) በሀገር ውስጥም ውጭም የሚኖርቱን ኢትዮጵያውያንን በፍቅር የሚያቆራኙ
13) ጊዜ የገደለውን ጽንፈኛ ብሔራዊነትን እንዲሁም የተገንጣይነት አመለካከትን የሚያከሽፉ
14) ከድሮው ታሪካችን ለወደፊት ይጠቅማል የሚለውን ወስደው ከመጥፎው ተምረው አላስፈላጊውን ቅርጫት ውስጥ ጥለው ዛሬ ላይ አዲስ (ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም ሊለውጥ የሚችል) ታሪክ እየሰሩ ወደ ፊት የሚራመዱ
15) ባጠቃላይ ዐለምን ጉድ ያሰኘውን የኦባማን እግር የሚከተሉ መሪዎች ያድላት:: አሜን ...
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
ብራንጎናትርን
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 736
Joined: Fri Dec 29, 2006 6:31 pm

Postby እንሰት » Sat Nov 08, 2008 8:41 am

ብራንጎናትርን� wrote:www.etiopiainitalia.com

ከዚህ በፊት የዚህ ድረገጽ መስራች ዋርካ ላይ አስተዋውቆት ነበር:: ደግሞ መለጠፉ አይከፋም ... :)

...


Thank you. ለውጥ አይቼባታለሁ እስኪ በደንብ አያታለሁ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ግእዝ-ዐማርኛ፡ክለሳ፡1.0

Postby እንሰት » Mon Dec 01, 2008 9:11 am

ዛሬ አንድ ድረ ገጽ ባይ ላካፍላችሁ ዋርካ ተመላለስኩ::

http://www.gzamargna.net/index.html
ነጻው፡ኢትዮጵያዊ፡የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐት፥
ዋዜማ፡2001፥ክለሳ፡2.1፡ለዊንዶውዝ፡ኤንቲ፥2000/ኤክስፒ/ቪስታና፡ጠቅላላው፡የግእዝ-ዐማርኛ፡የመረብ፡መገኛ፡
ግእዝ-ዐማርኛ፡ክለሳ፡1.0፡
ወጥተዋል፤ቀድተው፡ይሞክሯቸው።
Source of information deje-selam blog <FRIDAY, NOVEMBER 28, 2008>
<http://deje-selam.blogspot.com/2008/11/interesting-website-wazma-systemwazma.html>
Today I came across an interesting website, ዋዜማ፡ሥርዐት•Wazéma System•Wazéma Système. Very interestingly the editors managed to upload the not-anywhere-you-find Geez Amharic dictionary of Aleka Kidane Weld kifle. Wow!!!! I am really excited to see that. There are other surprises too.

On top of that you will find out of print books books of Geez-Amharic grammar and theology. Take a look at it. http://www.gzamargna.net/index.html

መልካም ቅኝት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች 'በአሉ ግርማ

Postby እንሰት » Sun Feb 15, 2009 3:01 pm

ማየት ስንናፍቀው የነበረ የበአሉ ግርማ ድረ ገጽ ከልጁ ከመስከረም በአሉ እነሆ! አሳታፊም ይሆናል ብለዋል ለዋርካ ገጣሚያን መልካም እድል ብለናል::

[/url]http://www.baalugirmafoundation.org/contact.html
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Apr 01, 2009 2:45 am

ውድ የዋርካ አስተዳዳሪዎች :-

ይህቺን ዓምድ ከፊት አምጥታችሁ በኃይለኛ ካሥማ ብትቸክሉልን ብዬ ለማሣሠብ ነው ::

አመሠግናለሁ ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby እንሰት » Mon Apr 06, 2009 4:26 am

ተድላ ሀይሉ wrote:ውድ የዋርካ አስተዳዳሪዎች :-

ይህቺን ዓምድ ከፊት አምጥታችሁ በኃይለኛ ካሥማ ብትቸክሉልን ብዬ ለማሣሠብ ነው ::

አመሠግናለሁ ::

ተድላ


ለራስ ዝና ባይባልብኝ የተነሳው ሀሳብ ከአምዱ ጠቃሚነት አንጻር ታይቶ የወንድም ተድላን ሀሳብ አግባብነት አለው::
ዋርካውያን ምን ትላላችሁ?
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ፍሬ ሰንበት አምዴ (ጄ/ል)

Postby እንሰት » Sun Apr 12, 2009 2:21 am

ሰላም ዋርካውያን
ይቺን የጋዜጣ ድረ ገጽ አያያዥ ተጠቀሙና አንዳንድ ነገር እዩባት
[url]zethiopianewspaper.blogspot.com[/url]

የኔ ቅንጭብጭብ ይህን ይመስላል
ስለ ጄኔራሉ
ብርጋዲየር ጄነራል ፍሬሰንበት አምዴ
ቅንጭብጭብ
...
አንድ ቀን ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋር በመኪና ሆነው ወደደብረ ዘይት መንገድ ያቀናሉ። ሁሌም እንደሚደረገው አንድ የአካባቢው ተወላጅ ባላገር የጃንሆይን መኪና አስቆሞ እጅ ከነሳ በኋላ አቤቱታ ሊያሰማ ይጠጋቸዋል።ንጉሠ ነገሥቱ መስኮታቸውን ወረድ አድርገው ከውጭ የሚያናግራቸውን ለመስማት ተዘጋጁ። ሰውዬ በኦሮምኛ ቋንቋ አቤቱታውን ማሰማት ጀመረ።

በዚህ ጊዜ እኔ አብሬያቸው መኪና ውስጥ ነበርኩ። እኔ ቋንቋውን ሰላማላውቅ ዝም አልኩ። ጃንሆይ ወደኔ ዞር አሉና “ያናግርሃልኮ እኮ ለምን አትመልስለትም?” አሉኝ። “ጃንሆይ ኦሮምኛ አላውቅም!” አልኳቸው። በያዙት ዱላ ሆዴን ነካ ነካ እያደረጉ ፈገግ አሉና “ የውጭ አገር ቋንቋ ከማጥናትህ በፊት የአገርህን ቋንቋ ብታውቅ አይሻልም ነበር?” አሉኝ። እሳቸው ግን በኦሮምኛ አነጋገሩት። ሰውየውም ቀጠሮ ተያዘለት።

...
የንጉሡ መገልገያ የነበሩትን “ሮልስ ሮይስ” አውቶሞቢሎች በእንግሊዝና በፈረንሳይ ለኢትዮጵያ አምባሳደሮች እንዲሰጥ የሚያዝ ነው። አምባሳደሮቹ በእነዚህ መኪኖቹ ሆነው ቢታዩ የኢትዮጵያን ገጽታ ከፍ ያደርገዋል የሚል ነበር ምንክንያቱ። ጄነራል ፍሬሰንበት ትእዛዙን እቀበላለሁም አልቀበልምም ሳይሉ ጄኔራል ተፈሪ ባንቲን ሲያገኙ በቀጥታ ያነሱባቸዋል።
ለካ ህዝቡ ወታደሮች ምንም አታውቁም የሚለን እውነቱን ነው…
ምን ማለትህ ነው? ይላሉ ጀኔራል ተፈሪ
እንዴ! የአገር ቅርስ እንዴት አድርገን ነው ወደ ውጭ አገር የምንልክው። ይህ መኪና የተሰጠን ከእንግሊዝ ህዝብና መንግሥት ነው። ንብረትነቱም የህዝብ ነው። አሁን ተመልሶ እንግሊዝ ተወስዶ ቢታይ ለስጦታው ዝቅተኛ ግምት መስጠት አይመስልም? ደግሞስ ለአምባሳደር መርቸዲስ መች አነሰውና ነው ከኢትዮጵያ ሮልስ ሮይስ የሚሄደው?

ጄኔራል ተፈሪ በሀሳቡ ተስማሙና መኪኖቹ በባእድ እጅ ከመግባት እጅ ዳኑ። የተባሉትም አምባሳደር መንግሥታቸውን የከዱት ወዲያ እንደነበር ተጽፏል። መኪኖቹ ግን ዛሬ በቤተመንግሥቱ በሙዚየምነት ተቀምጠዋል።

...
ደግሞ ሌላ ጊዜ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም ጄነራል ፍሬሰንበት አንድ ቀን ይጠሯቸውና በቤተመንግሥቱ አጥርና በየግድግዳው ያለውን የዘውድ ሥዕልና ምክልት ሁሉ እንዲያጠፉ ያዟቸዋል። ፍሬሰንበት ትእዛዙን ተቀብለው ይወጣሉ። ምንም ሳያደርጉ ዝም ብለው ይጠባበቃሉ። ሌላ ጊዜ ቆይቶ መንግሥቱ ትዝ ሲላቸው እንደገና ተቆጥተው “ያልኩት ለምን አልተፈጸመም ይሏቸዋል።?” “ቤተመንግሥቱ የተሠራው በልዩ ባለሙያዎች ነው። ስለዚህ ሲፈርስም ባለሙያ መሐንዲስ ያስፈልጋል። እንደገና ለመጠገንም ሆነ ሲፈርስ ገንዘብ ስለሚያስፈልግ የገንዘብ ሚኒስቴር ሰው ያስፈልጋል። የትኛው መፍረስ የትኛው ለታሪክ መቀመጥ እንደሚያስፈልግ መሆኑን የሚያውቅ የታሪክ ሰው ያስፈልጋል። እነዚህ በሌሉበት ሁኔታ ብቻዬን ማስፈረስ ከብዶኝ ነው።” እያሉ ምክንያት ደረደሩ መንግሥቱ ምንም አላሉም። ዝም ብለዋቸው ሄዱ። ከዚያ በኋላ ሁሉም ነገር ታሪክ ሆኖ ቀረ።

http://zethiopianewspaper.blogspot.com/ ... el/Profile
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ስለ አማርኛ ፊደል ማስታወሻ ጽሁፍ

Postby እንሰት » Thu Apr 16, 2009 6:18 am

ሰላም ዋርካውያን እና ዋርካውያት
የአማርኛ ፊደልን አስመልክቶ አንድ ጽሁፍ ስላየሁ አንብቡት ለማለት ብቅ አልኩ::

[url]http://www.quatero.net/pdf/amharic_fidelat2.pdf[/url
መልካም ንባብ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby በይሉል » Thu Apr 16, 2009 9:31 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ውድ የዋርካ አስተዳዳሪዎች :-

ይህቺን ዓምድ ከፊት አምጥታችሁ በኃይለኛ ካሥማ ብትቸክሉልን ብዬ ለማሣሠብ ነው ::

አመሠግናለሁ ::

ተድላ


ሰላም የዋርካ አስተዳዳሪዎች!!!

ይቺ መድረክ ቅመም የሆነች ጣፋጭ መድረክ ናት.
እንዲያዉም እሱዋን ራስዋን ዋርካ ማለት አይበዛባትም.

ምናል አንድ ቦታ ተሰይማ ጠዋት ማታ ብናገኛት.

ከአክብሮት ጋር.
በይሉል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Thu Sep 16, 2004 9:30 pm
Location: Beylul-60km North of Assab.

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests