የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby እንሰት » Fri Apr 17, 2009 5:41 am

ይቺ የስነ ጽሁፍ አድባር የሰፈረባት ቤት እንዳታመልጣችሁ::

የኛው ዋናው ነው::
http://www.zekiwos.webs.com/

ታዲያ ቤቱን ከጎበኛችሁ ዱካች ሁን ተ...ው...::
መልካም በአል
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby እንሰት » Sun Apr 19, 2009 7:11 pm

ቴዲ አፍሮ ከመታሰሩ በፊት ያዘጋጀው የፋሲካ መዝሙር ይህ ነበር
መልካም ፋሲካ
http://www.youtube.com/watch?v=UoDd80lm1EQ&feature=PlayList&p=F4CBA0CB50BB234E&playnext=1&playnext_from=PL&index=2
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: ስለ አማርኛ ፊደል ማስታወሻ ጽሁፍ

Postby እንሰት » Mon Apr 20, 2009 4:01 pm

እንሰት wrote:ሰላም ዋርካውያን እና ዋርካውያት
የአማርኛ ፊደልን አስመልክቶ አንድ ጽሁፍ ስላየሁ አንብቡት ለማለት ብቅ አልኩ::

[url]http://www.quatero.net/pdf/amharic_fidelat2.pdf[/url
መልካም ንባብ

http://www.quatero.net/?p=1433
አሁንም ቁዋጠሮ ድረ ገጽ የፊደል መሻሻልን አስመልክቶ ሌላ ጽሁፍ ስለወጣ ቀድሞ ካስታወስኩዋችሁ የአቶ ክንፈ ጽሁፍ ጋራ አንድ ላይ ብታነቡትስ?
http://www.quatero.net/pdf/Amharic%20fidel%20imprvt_sebsbe.pdf

የአንባቢያን አስተያየት ምልልሶቹ ይህን ይመስላሉ::
http://www.quatero.net/?p=1474#comments

መልካም ንባብ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ዋናው » Mon Apr 20, 2009 5:11 pm

እንሰት wrote:ይቺ የስነ ጽሁፍ አድባር የሰፈረባት ቤት እንዳታመልጣችሁ::

የኛው ዋናው ነው::
http://www.zekiwos.webs.com/

ታዲያ ቤቱን ከጎበኛችሁ ዱካች ሁን ተ...ው...::
መልካም በአል

አመሠግናለሁ!!!

በየጊዜው አዳዲስ ነገር ጣል ስለማደርግባት እነሰት እንዳለው መጎብኘታችሁን አትርሱ... በቅርቡ በቀጥታ አማርኛ ምንፅፍበትን ዘዴ አስተካክለዋለሁ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Re: ስለ አማርኛ ፊደል ማስታወሻ ጽሁፍ

Postby እንሰት » Fri Apr 24, 2009 7:39 pm

እንሰት wrote:
እንሰት wrote:ሰላም ዋርካውያን እና ዋርካውያት
የአማርኛ ፊደልን አስመልክቶ አንድ ጽሁፍ ስላየሁ አንብቡት ለማለት ብቅ አልኩ::

[url]http://www.quatero.net/pdf/amharic_fidelat2.pdf[/url
መልካም ንባብ

http://www.quatero.net/?p=1433
አሁንም ቁዋጠሮ ድረ ገጽ የፊደል መሻሻልን አስመልክቶ ሌላ ጽሁፍ ስለወጣ ቀድሞ ካስታወስኩዋችሁ የአቶ ክንፈ ጽሁፍ ጋራ አንድ ላይ ብታነቡትስ?
http://www.quatero.net/pdf/Amharic%20fidel%20imprvt_sebsbe.pdf

የአንባቢያን አስተያየት ምልልሶቹ ይህን ይመስላሉ::
http://www.quatero.net/?p=1474#comments

መልካም ንባብ

አቶ ክንፈ የመልስ መልስ ጽፈዋል - ምላሻቸው በራሱ ተነባቢ ሆኖ ስላገኘሁት አንብቡት ብዬ እዚህ ከተብኩት
kinfe m Says:

አቶ ሰብስቤ ያዘጋጃቱን መጣጥፍ አንብቤዋለሁ ማለፊያ ነው። ቃልዎን በማክበርዎም ሊመሰገኑ ይገባል። ለጡሁፍዎ አስተያየቴን እነሆን
፩ኛ/ እኔ ታላላቆቹ የሰሩትን እንደኔ ላልሰሙት ለማሰማት ሞከርኩ እንጂ በግሌ ያደረኩት ነገር ማለት ከታላላቆቹ እኩል የሚያስመሰግነኝ ስራ አልሰራሁም። ስሜም ከነሱ እኩል መነሳት የለበትም።
፪ኛ/ የጽሁፉ አርዕስት ራሱ ከዚህ በታች በማቀርበው ምክንያቶች ትክክል አይመስለኝም። ለምን የዘለፋ እንድምታ አለው፡፡ እኔ የጠቀስኳቸውን እንደ ተዘፈነላቸው ቆጥረው ይመስላል። ከዚህ የተሻለ አርዕስት መች ጠፋ? እንዳሉት ቀጣይ ብታሰኙት የተሻለ ነበር። ወይም ከ፲፱፻፺ ወዲህ አለያም ከዚህ ተመሳሳይ መምረጥ ሲቻል እንዲያው አልተዘፈነላቸውም ብለው የጠቀሷቸውን ሊቃውንት እኔ የጠቀስኳቸውን እንደተዘፈነላቸው አድርገው ይመስላል። መዝፈን ብቻ አይደለም ዳንኪራም ቢረገጥላችው ማለፊያ ነበር። ሀዘኑ እዚህ ላይ ነው። እንኳን ዘፈን ዳንኪራ በቅጡ የሚያውቃቸውም ትንሽ ነው። ስርዓቱ አንድ ሰው ላይ ብቻ የሚያጠነጥን ስለነበር የሌሎቹን ስራ ሽፍኖታል። ይህ እንዳናውቃቸው አርጎ ክፉ ነገር ሲደርስ ማንም የቆመላቸው የለም።
ኢትዮጵያ ለጀግኞቿ ዘፍና አታውቅም ባልልም የተዘፈነላቸው በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። እነሱም ቢሆኑ የጦር አበጋዞች/ጀግኖች ብቻ እንጂ ለብርዕ(ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ብዕር ማለት ስህተት ነው ይላሉ)፣ ለኪነት፣ ለሰነ ጥበብ፣ ለኪነ ጥበብ ለዕደ ጥበብ፣ ለፍልስፋናና ለመሳሰሉት ሊቃውንት ተዘፍኖ አያውቅም። በተረፈ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ት/ቤት ቆሞላቸዋል። እርሶ ከጠቀሷቸው ውስጥ ታላቁ መንግስቱ ለማ በዩኒቨርሲቲው በስማቸው የቆመ የት/ዕድል አለ። ከበደ ሚካኤል የክብር ዶ/ት የተጎናጸፉት በቅርብ ነው ሌላ በስማቸው የቆመ ነገር እኔ የማውቀው የለም። ካለ አሹ ነው (የቋንቋውን ጉዳይ ብቻ እንጂ በሌላው ዘርፍ በዚይ ዐይነት የተዘከሩ አልፎ አልፎ ብልጭ ብልጭ የሚሉ አሉ፣ ዶክተሮቹ ጌታቸው ቦሎዲያና ዓለማየሁ ተምሳሌት) እነሱም ቢሆኑ በትምህርትና በቀለም ሰዎች አካባቢ እንጂ ህዝብ ያውቃቸዋል ለማለት አያስደፍርም። ያልተዘፈነላቸውን ቤቱ ነው የሚቆጥራቸው። በተለይ ባለፉት አራት አስርታት ውስጥ ብሔራዊ ሀብቶች ሰውም ሆኔ ቁሳቁስ ደብዛው እየጠፋ ነው። ይህም ሆኖ ተዘፈነላቸው ማለት ትክክል አይደለም። የተቀሩት እንዲያው ዝም ነው። እንዲያው ሁሉም ያልተዘፈነላቸው ስለሆኑ ከመሀል ትንሽ ብቻ ጠቅሶ ያልተዘፈነላቸው ማለት ግን ትክክል ስላልሆነ አርዕስቱ ለሁሉም እንዲሆን ቢታረም እላለሁ። ወደ ዋናው ጽሑፍ ስገባ፦

እመጀመሪያው ገጽ ላይ ስድስተኛው አዲስ መስመር ላይ የመንግስቱ ለማን በ፺ቹ የታተመውን ግለ ታሪክ በ፵ቹ ለተደረገው ሙከራ አንድ አንኳር የታሪክ ነቁጥ ይዟል ይላሉ። መልካም ነው። እኔ ያቀረብኩት የጽ/ሚኒስቴር ያቋቋመውን ኮሚቴ ስራ ነው። የተጠቀሱትም ኪሚቴው ያነሳቸውን ነው። አቶ ሰብስቤም በደፈናው ተናገሩ እንጂ የያዘውን ነቁጥ አላብራሩም ትንሽ እንኳን ምን እንደሆነ ማለቴ ነው። ማለት ስለ ፊደል መሻሻል ይዘት ጠበቅ እንዲሆን ለተደረገው ጥናት አሰተዋጽኦውን። ቀጥለው የሮጀር ካውሊንና ስቲፈን ራይትን መጣጥፎች መዘንጋታችውን አስታውሰዋል። እኒህ ሁሉቱ ባንድ አስተዋጽኦ ስም ኢትዮጵያኒስት ተበለው ከሚጠሩት ሊቃውንት ሲሆኑ መጣጥፉቸውን ባለሁበት ፈልጌ አላገኘሁትም። ስላላየሁት ዋቤ ላይ መጥቀሱ አይገባም ብዬ ነው። ሮጀር ኮውሊን ግን ሌሎችን ስጠቅስ እሱን ስተይብ ነው የዘነጋሁት። አብርሃም ደሞዝ ጠቅሰውታል የኔ ስህተት ነው። ባቶ ደገፌ የተጠቀሰው የጥፈት መኪና ማርሴ ለግራ ማዘጋጀታቸውን አላውቅም አቶ ሰብስቤ በማሳወቃቸው ይመሰገናሉ። ይህም ሆኖ ግን እኔ ካቀረብኩት ከፊደሉ መሻሻል ጋር ወይም ሕግ እንዲጠብቅ ለተደረገው ጥረት ያረገው ወይ የተጫወተው ሚና ካለ አልተገለጸም። ለምን መኪናውን የቋንቋውን እድገት ያፋጥናል እንጂ የፊደሉን ብዛት አልቀነሰም። አንቷን ዲባዲ የመጀመሪያውን ያማርኛን መ/ቃላት ያዘጋጁ ፈረንሳዊ ሊቅ ናቸው ኢትዮጵያ ውስጥም ረጂም ዘመን ኖረዋል።

ወረድ ብለው አቶ ሰብስቤ ላማርኛ ቋንቋ ዕድገትና መስፋፋት አፄ ሚኒልክንና አፄ ቴዌድሮስን ጠቅሰዋል። እኔ አፄ ሚኒልክን የጠቀስኩት ፊደሉን ለማሻሻል ያደረጉትን አስተዋጽኦ አንስቼ እንጂ ከቋንቋው መበልፀግና ማደግ ጋር አይደለም። የአማርኛን ፊደል መሻሻልና ያማርኛን ቋንቋ ዕድገት መለየት አለብዎ። አለያ ከአርዕስትዎ ወጡ።

ሁለተኛው ገጽ ያማርኛ ፊደል ማሻሻያ ላይ በ፸ቹ የተደረጉትን ጥናቶች ብለው ሁለት ተምሳሌት አቅርበዋል። የቋንቋዎች አካዳሚ አሻሽሎ ያቀረበውን የፊደል ገበታና ለ፲፭ ቋንቋዎች ፊደል ተቀርጾ የቀረበውን። አሁንም አቶ ሰብስቤ የተሻሻለውን ምን እንደሆነ አልገለጹም። እኔ የተሻሻለና ሕግ የተጠበቀ የሚለውን ዘርዝሬ አቅርቤአለሁ። አቶ ሰብስቤም ወደፊት ይህን የጀመሩትን እንዲያብራሩ እጠብቃለሁ።

ከ፲፱፻፹ እስከ ፳፻፩ ድረስ ብለው ሶስት ነጥቦችን ጠቅሰዋል። ሶስቱም ያማርኛን ቋንቋ እድገትና ስፋት እንጂ ከፊደል መሻሻል ጋር ወይም ኮሚቴው ካጠናው ጋር የሚገናኝ አይመስለኝም። በቁ ፩ የተገለፀው አክራሪ የኦሮሞ ድርጅትና አቀንቃኞቹ ያቀረቡት ነው። ለዚህም አንድ አሁን የማላስታውሰው ጋዜጠኛ(ዋሽንግተን ኗሪ) አባቷን አታውቅ አያቷን ናፈቀች ብሎ መልስ ሰጥቷል። ባዬ ይማምም እንዲሁ ። በቁ ፪ ለገለፁት ፊደሉ የተሻሻለው ሌሎች ቋንቋዎችን እንዲያስተናግድ እንጂ ራሱ ያማርኛ ፊደል እንዲሻሻል አይደለም። ተራ ቁ ፫ስትም ካንደኛው ጋር አንድ ስለሆነ ሌላ ገለጻ የሚያስፈልገው አይመስለኝም። የሰነ መንግስት ጉዳይ ያስከተለው ችግር እንጂ ለቋንቋው ዕድገትና ብልጽግና የተደረገ እንቅስቃሴ አልነበረም። ለምን ቢሉ እርስዎ እንደገለጹት ያማርኛ ፊደል የቅኝ ገዢ ስለሆነ ከነቋንቋው ነው ማጥፋት ስለሚሉ። የቋንቋ ጉዳይ ብቻ ቢሆን የጎደለው እንዲሞላ በተለይ ኦሮምኛ የሚፈልገውን አንድ ፊደል ማዘጋጀት ቀላል ስራ ነበር ተዘጋጅቷልም።
ሌላው አቶ ሰብስቤ ያቀረቡት ያማርኛን መቀምር ያዘጋጁትን አገር ቤትና ውጭ አገር ያሉትን ሊቃውንት ሲሆን። ከፊደሉ መሻሻል ጋር የደረጉትን እሰተዋጽኦ አልጠቀሱም። በበኩሌ የምጠቀምበትና እስከ አሁን ያጋጠሙኝ መቀምሮች በሙሉ ያማርኛን ፊደል እንዳለ ለቅመው ማለት ፬፻፸፩ዱን ወስደው የሚሰሩ እንጂ ኮሚቴው እንዳቀረበው በ፳፱ ፊደላት ብቻ የተዘጋጁ አይደሉም። ሊቃውንቱ ያደረጉት ያማርኛን ቋንቋ/ፊደል ከዘመኑ ርዕደ ጥበብ ጋር እንዲራመድ እንጂ ጊዜን፣ገንዘብንና ጉልበትን እንዲቀንስ አይመስለኝም። ይህ በመሆኑም ዲባቶ (መስፍን አረጋ ዶ/ር የሚለውን ላማርኛ መልሶት እሱን መጠቀሜ ነው) ዳንኤል ክንዴ ያማርኛን ፊደል ለSMS ጥቅም እንዲውል ለማድረግ ባደረጉት ጥናት አንድ ትንሽ መልዕክት ለመጻፍ የጅ ስልኩን ብዙ መጠቅጠቅ ችግር እንዴት ሊቃለል እንደሚችል የጥናታቸው ትኩረት እንደነበርና እሱን ለማሻሻል ይተጉ እንደነበር ተዘግቧል። አቶ ሰብስቤ ከጠቀሷቸው ውስጥ ያማርኛን ፊደል አሳጥሮ ለመቀምር ያዘጋጀ ካለ ይንገሩን አለያ የፊደልን ሳይሆን የቋንቋን መመንደግ ነው የነገሩን። በተጨማሪም የተወሰኑትን ጠቅሶ ሌሎች ያልተዘፈነላቸውን መተውም አግባብ አይመስለኝም። እኔ ራሴም ሌሎች ብዙ የተጉ እንዳሉ አውቃለሁ።

አንድ ጽሑፍ የተወሰነ ዕውነታ ላይ ያተኩራል፡፤ የኔም የ፳ኛው ክ/ዘመን መባቻ ላይ የተውጠነጠነ ነው። ታላላቹም ስራቸውም የዚያን ዘመን ነው። የርሶም ትኩረቱና ትንታኔው ባስተያየትዎ እንደ ገለጹት ድህረ ፸ ነው። እኔም አርሶም ጨራረፍነው እንጂ ዘመን በዘመን ቅጽ በቅጽ በየጊዜው ሊጣፍ የሚገባው ነው። በመሆኑም ያላነሳኋቸው እንዳሉ የቀዳሁበት ምንጭ ላይ ያሉትን ብቻ መዘከሬን ቀደም ብዬ ገልጫለሁ። ያማርኛ መሻሻል ከተጀመረ ብዬ ብነሳ ብዙ ጊዜና ጥረት ይጠይቃል። ከሺህ አመት በላይ ያስመዘገበ ታሪክ ነው የሚጎለጎለው። ምንጩና ጠቢቡ ከተገኘ ወደፊት የሚሰራው እይጠፋም እላለሁ። እርሶ የዘረዘሯቸውን ያላካተትኩት ሳይዘፈንላቸው እንዲቀሩ ሳይሆን በተጠቀሰው የታሪክ ምዕራፍ ብቻ ያማርኛን ፊደል ለማሻሻል የተሰራውን ሥራ ከነሰሪዎቹ በማቅረቤ ነው። ማለት የጽ/ሚኒስትሩ ኮሚቴ የ፲፱፻፶ቹ። የርሶ ከዚያ የቀጠለ ነው። ማለፊያ ስራ!! ያ በመሆኑ እንጂ ሆነ ብዬ ያረኩት እንዳልሆነ ይታወቅልኝ። በተጨማሪ ሊቃውንቱ ይዘውት የነበረውን ቃለ ጉባኤ እንዳለ አቀረብኩት እንጂ ከመሻሻሉ ጋር ሁሉን ያቀፈና የተያያዘ ጥናት ተኮር የሆነ መጣጥፍ አይደለም ያቀረብኩት። ቢሆን ብዙዎች መጠቀስ ያለባቸው እንደሚኖሩ አውቃለሁ በመግቢያው ላይም ጥቁሜአለሁ። ሙሉዕ ለማድረግ ብዙ ጥናት ይጠይቃል። ካለሁበት አገር ውጪ መዞርና ከምንጮቹ መቅዳት አለብኝ። ይህ አሁን ባለኝ ሁኔታ አይቻልም። እርሶ እንደቀጠሉት ሌሎች ደሞ ይቀጣጥላሉ አንዱ ያላሟላውንና ያጎደሌውን ሌላው እየሞላና እያሟላ የኢትዮጵያ የታሪክ ቅርስ በዚህ ዓይነት ይጠበቃል ወደሚቀጥለው ትውልድ ይተላለፋል። እርሶ እንዳሉት ምሳሌአቸውን መከተል ነው።

አርአያነት ማንኛውም ምክንያት ከሚያስከትልወ አጀብ የበለጠ ወገን የሚስብ ሀይል አላት
በቀለ ተገኝ 1921-1994

ክንፈ ሚካኤል
በቸር ይግጠመን
ሚያዝያ ፲፫
ምንጭ http://www.quatero.net/?p=1474#comments
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ሉሲ ዛሬ

Postby እንሰት » Thu Jun 11, 2009 6:54 pm

ይህ ድረ ገጽ መጣጥፎች ያቀርባል:: ሌሎች ድረ ገጾች እንደሚያደርጉት እነኝህ አርካይቭ ማከማቻ ስላላበጁለት ግን የለት የለቱን አንብባችሁ ዞር ነው::

ማያያዣውን እነሆ

http://www.lucyzare.com/lucyblog.aspx?Col=Tibeb
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ትርንጎ* » Fri Jun 12, 2009 8:24 am

:lol: ለማስጠንቀቂያው እናመሰግናለን እንሰቴ...የምትጥም ድረ ገፅ ነች:: ጋዜጣ ነገርም አላቸው ልበል? በቀደም ስለጥሌ አንድ ቆንጆ እትም ያነበብኩ መሰለኝ:: እጅ ነስቻለሁ...እንቅልፌ አልቆብኝ ነበር...ማፍጠጫ አገኘሁ::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 716
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

የአማርኛ ግጥሞች በ Face book

Postby እንሰት » Thu Jul 02, 2009 7:59 am

እንደምን ከረማችሁ የዋርካ ወዳጆቼ

59 ምልልስ እና 350 ፖስቶች የተካተቱበትን በ Facebook የግጥም ሽንጎ ትጎበኙ ዘንድ ነው አመጣጤ::

http://www.connect.facebook.com/topic.php?uid=29213608820&topic=6268&post=36309#topic_top
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

አዲስ ፎረም

Postby እንሰት » Mon Oct 19, 2009 7:01 am

ሰላም ዋርካውያን
ይቺን የወዳጃችንን ያማርኛና የንግሊዘኛ ዝንቅ ያላትን ድረ ገጽ ጎብኙአት

http://ethio.freeforums.org

መልካም ቅኝት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

አባ ጃሌው ከ አዲስ ፎረም

Postby እንሰት » Tue Oct 20, 2009 10:24 pm

እንሰት wrote:ሰላም ዋርካውያን
ይቺን የወዳጃችንን ያማርኛና የንግሊዘኛ ዝንቅ ያላትን ድረ ገጽ ጎብኙአት

http://ethio.freeforums.org

መልካም ቅኝት

ጊዜ ላላገኛች ሁ ይቺን አባ ጃሌው የተሰኘች ጽሁፍ አምጥቼላችሁዋለሁ አንብቡዋት እስኪ::

አባ ጃሌው!

by selam on 13Oct 2009 < http://ethio.freeforums.org/a-t227.html>
“ክፉውን በክፉ አትቃወሙት፣ ግራው ፊትህን ለሚመታህ የቀኙን ስጠው… ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ የሚረግሟችሁን መርቁ…!”
ማቴ፡ 5፡ 39 ፤ ሉቃ፣ 6፡ 27-28
አባ ጃሌው በሰፈራቸው ከታወቁና አሉ ከሚባሉት ሽማግሌዎች ሲሆኑ በጣም የተከበሩ ሰው ናቸው። የሰፈሩ ሰው ማንኛውም ጉዳይ ሲኖረው ሁሌ የሚጠራውእርሳቸውን ሲሆን፣ ለምሳሌ ለሚስት አማጭ ሰው ሲፈለግእርሳቸውን ለምኖ ከሽማግሌዎቹ መሃል ካስገባ፣ ተጠያቂውእምቢ ብሎ መመለስ በጣም ይከብደዋል። ለዚህም ሁሌ ይቀናቸዋል፣ ጉዳዩም ቶሎ ይፈጸማል። በመሬት ሆነ በገንዘብ የተጣላውን ለመሸምገል ዘወትር ሰዉ ሁሉ የሚጠራው አባ ጃሌን ነው። ባልና ሚስትም ሲጣሉ ዋና አስታራቂ ከአባ ጃሌው የተሻለ ሌላ የለም? ስለዚህ አባ ጃሌው የኅብረ ሰቡ ዋና ማገርና ምሰሶ ናቸው ቢባል ከሓቁ የራቀ አይሆንም።
አባ ጃሌውእድሜያቸው በትክክል ባይታወቅም፣ አሁንእያረጁ ወደ ዘጠና ዓመትእንደ ተጠጉ ይገመታል። ጥልቅ አስተዋይነታቸውና ብልኅነታቸው የታወቀው ገና ድሮ ሲሆን፣ ያኔ የዓርባ ዓመትእድሜ ያህልእንኳን የነበራቸው አይመስሉም ነበር። በሰፈሩ ሰርግ ሆኖ አሳላፊእንዲሆኑ ተመድበው፣ የመጣውንእንግዳእየተቀበሉ ከዳስ ሲያቀምጡና ሲያስተናግዱ፣ አንዱ ጠጥቶ ሞቅ ያለው በሰፈሩ የታወቀ ልክስክስ፣ በሆነ ነግር ተላከፋቸውና ግርግር ፈጠረ። ሴቶች ወደሚሠሩበት ወጥ ቤትም ካላለፍኩእያለ፣ ተው አይሆንም ሲሉት፣ ግልፍ ብሎ ዞር አለና በቃሪያ ጥፊ ጆሮአቸውን አጮላቸው። በዳሱም ሰዉ ሁሉም “O!’ ብሎ ደነገጠ።
አባ ጃሌው ፈጽሞ ያልጠበቁት ነገር ነበር፣ ግን የቁጣ ቃል ሳይናገሩ፣ ፊታቸውን ሳያጠቁሩ፣ ድምፃቸውንም ሰበር ሳያደርጉ፣ ሰውየውን፤ “ና፣ ወንደሜ፣ ግድ የለህም፣ አይዞህ፣ የማጫውትህ አንድ ጉዳይ አለኝ፣ ናእማ!”እያሉእጁን አጥብቀው ይዘው ውጭ አወጡትና አጋፋሪዎቹን፤ “ስካሩእስኪበርድለትእንዳይገባ!” ብለው ከዳስ ተመልሰው ገብተው፣ አንዲትምእንዳልሆነ ሰው የአሰላፊነታቸውን ተግባር በሚገባ ቀጠሉ።
አባ ጃሌ ረጋ ያለው ባሕሪያቸው ከዚያ በፊት በሰፈሩ ቢታወቅምእንኳ በይበልጥ አንጸባርቆ ለሰዉ ሁሉ የታየው በዚያን ጊዜ ነው። ሰው ጠጋእያለ፣ “አባ ጃሌው፣እንዴት አስቻልዎት?እጅግ የሚደንቁ ትEግስተኛ ሰው ነዎት!” ሲላቸው፣ “ይህንን ካልቻልኩማ ለአሰላፊነት የማልበቃ ሰው ነኛ! መቻል አለብኝእንጂ!እርሱ መች መታኝ፣ የመታኝ ጠላው፣ ወይ ጠጁ እንጂእርሱ አልመታኝም።”እያሉ ነው አሳስቀው የመለሱላቸው።
“አባ ጃሌው” ሊባሉ የቻሉት በሰፈሩ ሰው አጠራርእንጂ ትክክለኛው ስማቸውስ አያሌው ነበር። ከሰፈሩ አሮጊቶች አንዷ፣ ፊዴል እንኳን ያልቆጠሩት፣እማሆይ ወለተ-ጽዮን የሚባሉት አንድ ቀን፤ “አባ አያሌው” ለማለት፤ “አባ ጃሌው!” ብለው ሲጠሯቸው፣ ከዚያን ጊዜ ወዲያ ሁሉም ተቀብሎ፣ ስማቸውን ከአባ አያሌው ወደ አባ ጃሌው ለወጠው። በልጅነት የወጣላቸው ትክክለኛው ስማቸው ተረስቷል። ዛሬ ይኸው በሰፈሩ ሁሉ “አባ ጃሌው” በሚል መጠሪያ ስም ብቻ ነው የሚታወቁት።
አባ ጃሌው ያደጉት በባላገር ገበሬ ሆነው ቢሆንም፣ ልጆቼን ላስተምር ብለው ወደ አውራጃው ከተማ ከተዘዋወሩ ብዙ ዓመታት አልፏቸዋል። የእርሻው መሬታቸውንም ለባለ ሢሶ ገበሬ ሰጥተውት፣ በየዓመቱ በአህያ ጥቂት ዳውላ ገብስ፣ በቆሎና፣ ማሽላምእየተጫነ ይመጣላቸዋል። ከዚህ ለቤታቸው የሚበቃቸውን አስቀርተው፣ ‘ገበያ ደህና ውሏል’ ሲባል ከተማ ወርደው ለቸርቻሪ ነጋዴ ሸጠው ይገላገላሉ። ሌሎች ራሳቸው ከገበያ የሚቸረችሩ ሰዎች፤ “ለነጋዴ ከምትሰጥ ራስህ ብትቸረችረው የተሻለ ገቢእኮ ታገኛለህ…” ሲሏቸው፣ “ቸርቻሪውስ ምን ይብላ!” ነው የሚሉት። ዋናው ምክንያት ግን ከገበያ ቆመው ከአላፊ አግዳሚው በዋጋ ውጣ-ውረድ የእንካ ስላንትያ ትንንቅ መያያዙን አልፈለጉትም።
አባ ጃሌው በኑሮአቸውም ሁሉ ረጋ ብሎ መመላለስን የሚወዱ ሰው ናቸው። አንድ-አንድ አስቸጋሪ ሰው ሲያጋጥማቸው ገለል ይሉለታል፣ ወይም ከፊታቸው ገለል የሚያደርጉበትን መንገድ ይፈልጋሉእንጂ፣ መከራከር፣ መጨቃጨቅ፣እልኽ መያያዝ የሚባል ፍጹም አይወዱም። ሊያገኙት የማይፈልጉትን ሰው ከሩቁ ሲያያዩት መንገዱን አሳብረው ይሄዳሉእንጂ፣ ካልሆነ ሰው ጋር መላከፍና አፍ መካፈትን አይወዱም።

አባ ጃሌውን አሰተዋዩ አእምሯቸውና ትእግሥታቸው በሰፈሩ ሰው ሁሉ ዘንድ ታዋቂነትና ተወዳጅነትን አትርፎላቸዋል። ስለዚህም ለሽምግልና፣ ለአማጭነት ሆነ የተጣሉትን ለማስታረቅ ሁሉም ሰው ይለምናቸዋል። ለሆነ ጉዳይ ምክር ፈላጊውም ሁሉ ከበራቸውና ከደጃፋቸው አይጠፋም። አባ ጃሌው በአውራጃው ከተማእንዲህ ቢከበሩምእንኳን ተወልደው ባደጉበት በባላገሩ አካበቢ ግን በወጣቶቹ ዘንድ ትዝታቸው መረሳቱ አልቀረም።እርግጥ ስማቸው አልፎ-አልፎ በአዛውንቱና በአሮጊቶቹ ቢነሳምእንኳን ማንነታቸው ግን ብዙም አይታወቅም። ለዚህም ዋና ምክንያቱ ከተማ ከገቡ ብዙ ዓመታት በማለፉ ነው።

አንድ ቀን በመኸር ወራት ታድያ መሬቱንእንዲያርስ የሰጡት የሢሶው ገበሬ ድንገት በማታ ከተፍ ብሎ ወደ ቤት መጣ። አባ ጃሌም፤ “ምነው ደህናም አይደለህ? አሁን በመኸር ጊዜ፣ ሥራ በበዛበት ወራት ከከተማ ድረስ ምን ጉዳይ ሊያመጣህ ቻለ?” ቢሉት፤ “አረእኔስ ደህና ነኝ!” ብሎ ያመጣውን ጉዳይ ሳይናገር አደረ። በማግስቱ ግን በማለዳ ተነስቶ፣እንደ መርዶ ነጋሪ፤ “አስቻለው የተባለ አንድ ጥጋበኛ ጎረምሳ ከአዙሪት ወንዝ ዳር ያለውን መሬት አጥር አጥሮበት ሄዷል…”እያለ፣እርምዎን ያውጡ በሚል ዓይነት አነጋገር መርዶውን አረዳቸው።
አባ ጃሌው ልጆቻቸውን አሳድገው፣ ሁሉም አዲስ አበባ ሄደው በተለያየ መስክ በሥራ ገበታ ላይ ሲገኙ፣ ከሁሉም ታናሹ ልጃቸው ኮሌጅ ልማር ብሎ፣ ወንድሞቹ ይረዱታል። በክረምት ወራት ግን ከአባቱ ቤትእየመጣ ያሳልፋል፣ ስለዚህ “ነገሩስ ነገር ነው፣ ግን ሰይፍ አያማዝዝም!”እንዲሉ፣ መሬታቸውን ማንም ጥጋበኛ አጥር ተክሎ በመቀማቱ ቅር ቢሰኙምእንኳ ብዙም አልተጨነቁም። ከልጆቻቸው ማንኛውም ቢሆን ከአገር ቤት ሄዶ በግብርና የሚሰማራ አይኖርም፣እርሳቸውም ከከተማው ምቾት ወጥተው ዳግም ወደ ባላገር ኑሮ አይመለሱም። ቢሆንስ ታድያ መሬቱ የአያት፣ የቅድመ-አያት ርስት ነውና ለቅርብ ቤተ ዘመድ ይሰጣል እንጂ ማንም ጥጋበኛ ጐረምሳእንዴት ይነጥቀዋል! ነገሩ የሚከነክን ነው።
“እስቲ ደግ ነው፣ መክሬ የማደርገውን አደርጋለሁ።እስከዚያው ሂድ ሌሎቹንእርሻዎችእያረስክ ቆይ…” ብለው የሢሶውን ገበሬ በማሰናበት፣ ነገሩን ማሰላሰል ያዙ።እንደ ድሮ ጉልበትና ብርታት ቢኖራቸው ኖሮ ነገሩን ቶሎ ያጣድፉት ነበር፣ ዛሬ ግንእርጅና መጣና፣ ወደ ፍርድ ቤት መመላለሱን ጠልተው፣ ጉዳዩን ለደህና ነገረ-ፈጅ ሰጥተውት ተመለሱ።
ይህ በሆነ ወርእንኳን ሳይሞላው፣ የሆነ ሰው ከባላገር ተልኬ የመጣሁ ነኝእያለ ዘው ብሎ ከቤት ገባና መልእክቱን ሲነግር፤ “አባታችን፣ አባ ጃሌ፣ ሰላምታ ይድረስዎት። ፍርድ ቤቱን ይተውት፣እኛእናስታርቅዎታለን። ለጊዮርጊስ እለት ረፋድ ላይ፣እርሶዎንና አጥር ተከለ የተባለውን፣ ልጅ አስቻለውን ጠርተናችኋልና እንዳይቀሩብን አደራ። በቀጠሮ ቀን ከአዙሪት ወንዝ ዳርቻ ባሉት ግራሮች ስርእንጠብቅዎታለን!” የሚል ቃል ነበር።
አባ ጃሌም፣ “የሚያሰታርቅማ ከተገኘ፣ ከፍርድ ቤት ማን ይንከራተታል” ብለው፣ “እሺ፣ ካስታረቃችሁኝስ ደግ፣እመጣለሁእንጂ!” የሚል መልስ ላኩ። በተባለውም ቀን በቅሎ ተዘጋጅታ፣ ከቤት ልጅ አንዱን አስከትለው ተነሱ። በማለዳምእንደ ሰንሰለት ከተያያዙት ተራሮች ጥግ-ጥጉን ይዘው ሲሰግሩ ካረፈዱ በኋላ ከአዙሪት ወንዝ ደረሱ፣ ከተባለው ቦታ አካባቢ መቃረባቸው ነበር። ትንሽእንደ ተጓዙም በሩቁ ሦስት ግራሮች ከወንዙ ዳር ብቅ ብለው ታዩ። የቀጠሮው ቦታም ከዚያው ነበር።
ወራቱ በልግ ስለ ነበረ አዝርእቱና እሸቱ በመንገዱ ግራና ቀኝ ሜዳውን አልብሶታል። የዱር አበባም ሽታው ከሩቁእውድ-Eውድ ይላል፣ ንብ፣ ተርብና ልዮ-ልዮ ወፎችም ውር-ውር ይሉ ነበር። አባም ከበቅሎዋቸው ኋላ ያፈናጠጡትን ልጅ፤ “በል ውረድ ልጄ፣ አሁንስ ደርሰናል፣ ምንም አልቀረንም፣እኒያ ግራሮች ድረስ በእግርህ ተከተለኝ” ብለውት ወርዶ፣ በእግሩ ከኋላ-ኋላቸው መከተል ያዘ። ከግራሮቹ ጠጋ እንዳሉም ሁለት ሰዎች ሲጠብቋቸው አዩ። ሰዎቹም አባ ጃሌን እንዳዩ፣ ከተቀመጡበት ተነስተው፣ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ በአክብሮትእጅ ነስተው ተቀበሏቸው። ሰላምታ ከተለዋወጡም በኋላ፤
“አባታችን፣ አባ ጃሌ፣ ይቅርታ ያርጉልን አደከምንዎት፣ ካሉበት ድረስ መምጣት የሚገባንስ እኛው ነበርን፣ ግን ጉዳዩ ያለው ከዚህ ቦታ ሰለሆነ፣እርሰዎን ማድከም የግድ ሆኖብን ነው?”እያሉ ይቅርታ ጠየቁ።
አባ ጃሌም፤ “የለም ለጆቼ፣ ለኔም ነፋስ መቀበያ፣ ከቤት መውጫ ሆነኝእንጂ፣ ይህ በመሰለ ቀን ትንሽ ሽርሽር፣ ምን ድካም ይባላል?” አሉ።
“እንግዲያው አስቀድመን ጥሪያችንን አክብረው ስለመጡእናመሰግናለን፣ አሁንም አቶ አስቻለው እንደ መጣ ብዙ አንይዝዎትም፣ በቶሎ ቤትዎ እንዲመለሱእናደርጋለን፣ ብዙ የሚያስቆይ ነገር አይኖረንም!” አሉ።
አባ ጃሌም፤ “ለመሆኑ ደህና ናችሁ ወይ? አገሩ ሁሉ ሰላም ነው?” አሉ።
ሰዎቹም ሲመልሱ፤ “አባታችን፣እኛ ደህና ነን፣ አገሩም ሁሉ በእርስዎ ጾምና ጸሎት ሰላም ነው። በልጉም እንደሚያዩት አምሮበታል፣ አሁን በቅርቡ ለዓጨዳና ለዓውድማ ይደርሳል። ዘንድሮ ጥጋብ ነው!” አሉ።
የአገር ሽፍታ የተባሉት ሰዎች ይቅርና የብረት መሣሪያእና ጠመንጃ፣ አንዲት ጩቤም የሌላቸ፣ ከያዙት ቀጭን ከዘራ ብጤ በእጃቸው አንድም ነገር የሌላቸው ሰዎች ነበሩ። እንዲህ እያወሩና እየተጫወቱ ከአንድ ሰዓት በላይ ካለፈ በኋላ፣ ከሁለቱ መሪ መስሎ የሚታየው፤ “አቶ አስቻለው የሚመጣ አይመስልም፣ በቂ ጊዜ ጠበቅነው ግን አልመጣም።እርስዎን አባታችንንም በከንቱ አድክመን አጉላላንዎት፣ ይቅርታ!እንግዲያውስ ይሂዱ፣ የቀረውን ለኛ ይተውልን።እኛውእንጨርሰዋለን!”እያለ ተነሳ።
አባ ጃሌም፤ “ተባረኩ ልጆቼ፣እንደእናንተ የመሰለ አውራ ከየሰፈሩእና ከየቦታው በሃገራችን አይጥፋ። ሰውየው ካልመጣ’ማ ምን ይደረግ? በሉ በሰላም ዋሉ።” ብለው በመሰናበት ልጃቸውን አስከትለው ወደ ቤታቸው መንገድ አቀኑ። ከዚያ ትንሽ ራቅእንዳሉም በቅሎዋን አቁመው ልጁን ከኋላ አፈናጠጡናእየሰገሩ ወደ አውራጃው ከተማ ጉዟቸውን አመሩ።
ይህ በሆነ ሳምንትእንኳን ሳይሞላው፣ በአቶ አስቻለው ላይ የደረሰው ጉድ ወሬው በከተማው ይነፍስ ያዘ። ‘ጠርተነው ሳይመጣ የቀረበትን ትእቢትና ንቀቱ እንዲበርድለት…’ ብለው ሽፍቶቹ በሌሊት ከቤቱ ድረስ ሄደው፣እጅና እግሩን ጠፍረው በማሰር፣ በሽመል ሙልጭ አድርገው ገርፈው፣ ‘ሁለተኛ አይለምደኝም!’ ብሎ እየጮኸ፣ ተማጥኖና ተገዝቶ፣ ፍዳውን ሁሉ ቆጥሮ፣ አፈር መሬት አብልተው ለቀቁት ይባላል። ብዙ ሳይቆይም ዘመድ ወዳጆቹን አለማምኖ ያቺ አጥር ተነቅላ እንድትነሳ አስደረገ። በሰው እንጂ እርሱ’ማ ምንም ሊያደርግ አይችልም ነበር፣ በግርፋት ቆስሎ የተገጣጠበው ጀርባው እስኪድን ለረዥም ጊዜ የአልጋ ቁራኛ ሆነ አሉ።
በጥጋቡ ያመጣው ጦስ ስለሆነ ከቅርብ ቤተሰቡ በቀር ማንም ያዘነለት አልነበረም። የብዙዉ ሰው አስተያየት፤ ‘በሃገሩ መሬትና ቦታ አልጠፋ! ጥሻውን መንጥሮ፣ የሚለበደውን ለብዶ፣ የራሱእርሻ ማልማት ይገባው ነበር። በጥጋቡ የሽማግሌው፣ የአባ ጃሌው ንቀት ነው ያጋለጠው! የሰው መሬት ማን ንካ አለው? ደፋር፣ ዓይነ ደረቅ፣ የእጁን አገኘ፣እሰይ!’ ብቻ የሚል ነበር። አቶ አስቻለው ቀደም ብሎ የቅርብ ቤተ ሰብና ወዳጆቹን ቢያማክር ኖሮ ይህ መች ይመጣበት ነበር? ለሌላው መቀጣጫ ሆኗል።
አባ ጃሌም ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ፣ “እኔ ምን አውቃለሁ? እንደእኔ’ማ ፍርድ ቤት ይወስን ብዬ አመልክቸ ነበር፣ ግን ይህ ጉዳይ በፍርድ ቤት ታይቶ፣ ምስክር ተቆጥሮ፣ ይግባኝ ተብሎ፣ ከላይ በዳኛ ተወስኖ፣ ለፍርድ አሰፈጻሚ ደርሶ በተግባር ላይ እስኪውል ድረስ ብዙ ዓመታት ይፈጃል። ያ ሁሉ እሲኪሆን ታድያ ለጠበቃ፣ ለተላላኪ፣ ለመዝገብ ቤት ፋይል አውጪ፣ ለዳኛ ጉቦ እያሉ ስንት ወጪ አስከትሎ ኪሳራ ላይ ይጥላል። መንግሥት ለሃገሩ ሁሉ የቆመ ስለሆነ ለስንቱ ይዳረሳል? እስኪዳረስ ጊዜ ይፈጃል፣ የተበደለው ሰውም ብዙ ጥቃት ይደርስበታል።እንዲህ የመሰለ አውራ ሲኖር ግን፣ ማንም አለሁ ባይ ባለጌ ጉልበቱን ተማምኖ ወንጀል ሲፈጽም በቶሎ አርሞ ይቀጣዋል፣ ለተበደለውም ይደርስለታል። ስለዚህ በየአገሩ፣ በየቦታው አውራ አይጥፋ!” ይሉ ነበር።
ይህ ከሆነ በኋላም አባ ጃሌው ብዙ ሳይቆዩ በምስጢር በዚያ በሢሶ ገበሬ እጅ መልእክት ልከው፣ መሬታቸውን ላስመለሱላቸው ሽፍቶች ከልብ ከመነጨ ምስጋና ጋር ማለፊያ የሆነ ሙክት እንዲሰጥ አደረጉ። ይኽም ከፍርድ ቤቱ ክፍያ ጋር ሲመዛዘን ቅንጣትም አይሆንም። ምክንያቱም ለማመልከቻ ጸሐፊና ለፋይሉ ማስመዝገቢያ የወጣው ብቻ እንኳን ቢደመር ከሙክቱ ዋጋ እጥፍ ከፍ ብሎ ቢበልጥእንጂ አያንስም።
አባ ጃሌው ዛሬ ብዙውን ጊዜ ጋቢአቸውን ደረብ አድረገው ከአልጋቸው ተጋድመው ነው የሚውሉት። ልጆቻቸው ከአዲስ አበባ ሊጠይቋቸው ሲመጡ፤ “አባባ፣ ምን ይዘንልህ እንምጣ?” ሲሏቸው፣ “ልብስ!” ይላሉ። ልጆቻቸው የሚያመጡላቸውን ልብስ ግን ሲለብሱት ማንም ሰው አይቶት አያውቅም። የሰፈሩ ድሆች ብቅእያሉ፤ “አባ ጃሌው! እንዴት ሰነበቱ…”እያሉ ሊጠይቋቸው ሲመጡ ልብሶቹን ከአጠገባቸው እያነሱ፤ “እንካ ያውልህ፣ ሸፍነህ፣ ደበቅ አድርገኸው ሂድ!” ብለው መለገስ ነው።
የሰፈሩ ድኻ ሁሉእየመረቃቸው ለብሶ ይኖራል።እንዲህ እያሉ በሰላም ሲኖሩ ታድያ አንድ ቀን በአውራጃው ከተማ ከታወቁት የማዘጋጃ ቤት ባለ ስልጣኖች አቶ ስንዱ የተባለ ሰርግ ደግሶ፣ ልጁን ዳረ። አባ ጃሌው ታድያ ከቤት ውለው፣ የሰርግ መሄጃ ዘመኑ አልፏቸው፣ ስለ ድግሱ ሰፊ ዝግጅት በወሬ ይሰሙ ነበር። የዛሬን አይበለውና በዚህች የአውራጃ ከተማ አባ ጃሌ ከአማጭነት ጀምሮ አስከ አሰላፊነት ያልተካፈሉበት ሰርግ እንደ ሰርግ የማይቆጠርበት ጊዜ ነበር። የማያልፍ የለም፣ ያም ሁሉ አልፏል።
ሰርጉ በተደገሰበት ማግስት ታድያ አንድ ጉድ ሰተት ብሎ ወደ ቤታቸው አመራ። የተዳረችው የአቶ ስንዱ ልጅ ድንግል ሆና አልቆየችም። ሙሽራው በዚህ ተናድዶና ተቆጥቶ ሙሺሪቱን ከጫጉላ ቤት አባረራት። ቤተ-ሰብ ሁሉ ጉድእያለ ተሰብስቦ ሲያዝን፣ አባት እና እናት ልጅቱን ለብቻዋ ከመኝታ ቤቷ አስገብተው፣ በጥያቄ እንዲህ ያደረገሽ ማን ነው እያሉ አውጣጧት። “የኔን ድንግል የወሰደው በቀለ ነው።” አለች። አቶ ስንዱም በቀለን እገድላለሁ እያለ መደንፋቱ በከተማው በይፋ ተወራ።
በቀለ የአባ ጃሌው የመጨረሻው ልጃቸው ነው። በእውነትም የኮሌጅ ተማሪ ሆኖ፣ በክረምት-ክረምት ከአዲስ አበባ መጥቶ፣ ከአባቱ ጋር ጊዜ ሲያሳልፍ፣ ከአንዴም ሁለቴ ልጅቱን ይዟት ከቤት መምጣቱ አባ ጃሌው ትዝ አላቸው። ያ ነገር ታድያ ዛሬ ሦስት፣ ወይም ኣራት ዓመት ገደማ ሆኖታል። አሁን በቀለ ኮሌጅ ጨርሶ ከጅማ በቡና ቦርድ ሥራ ይዟል። ታድያ ምን ለማድረግ ይቻላል? አባ ጃሌም በልባቸው፣ “ጐሽ የኔ ልጅ!” ቢሉም፣ ምንእንደሚያደርጉ ማሰብና ማሰላሰል ያዙ። አቶ ስንዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደእርሳቸው አቅጣጫእንደሚገሰግስ ምንም አልሳቱትም።
አባ ጃሌው፤ ‘የልጄን ክብር ገሥሷል… በቀለንእገድለዋለሁ’እያለና እየደነፋ የሚመጣውን አቶ ስንዱን እንዴትና በምን ዓይነትስ ሁኔታ እንደሚቀበሉት ጨነቃቸው። ምን ብለውእንደሚመልሱለትና ምንስ እንደሚሉት ማውጣትና ማውረድ ያዙ። ምን ቢሉት ይሻል ይሆን? አባ ጃሌው አውርደውና አሰላስለው መላ-ምት መቱ፣ አንድ ብልሓትም ፈጠሩ። ከቤት ልጆች አንዱን ጠርተው፤ “ልጄ እስኪ ወረቀትና ብእር ይዘህልኝ ና። አንድ የምትጽፍልኝ ደብዳቤ፣ የለም፣ ሁለት ደብዳቤዎች ናቸው። ቶሎ በል!” ብለው ጠሩት። ሁለቱን ደብዳቤ እንደ ጻፈላቸውም በቶሎ አንዱን ደብዳቤ ወደ ልጃቸው፣ በፖስታ ቤት ወደ ጅማ ላኩለት። ደብዳቤው ይዘቱ፤ “ልጄ፣ በቀለ! ለአንድ አስቸኳይ ጉዳይ ስለምፈልግህ ሳትውል፣ ሳታድር፣ ዛሬውኑ ስልክ ደውልልኝ…” የሚል ነበር።
ሁለተኛውን ደብዳቤ ግን በትራሳቸው ከተደረደሩት የድሮ ደብዳቤዎች አንዱን ፓስታ ከፍተው በውስጡ ከተቱና ጋቢአቸውን ደራርበው ገደም አሉ። ገደም እንዳሉ ብዙም አልቆየ፣ “የፈሩት ይደርሳል… ”እንዲባል፣ አቶ ስንዱ ወድያው ከቤታቸው እየደነፋና እየጮኸ ከተፍ አለ።
አቶ ስንዱ ጤና ይስጥልኝ ብሎ ገብቶ፤ “ተቀመጥ!” ሲሉት፣ ሳይቀመጥ፣ በቁጣ ብው አለና፣ “አባ ጃሌው፣ ዛሬ የመጣሁበት ጉዳይ ልጅዎ በቀለ ልጄን አስካለችን ደፍሮብኝ፣ አዋርዶኛል። የመጣሁበት ምክንያት ካሳ ለመጠየቅ እንዳይመስልዎት።እኔ ሌላ ካሳ አልፈልግም፣ በቀለን በእጄ ልገድለው ነው የመጣሁት። የት ነው ያለው? ይንገሩኝ!” አላቸው።
አባ ጃሌም፤ “ይካሱኝ ብትልስ ምኔን ነው የምክስህ? በል ሂድ ግደለዋ! እኔ ምን ላድርግ? የዛሬ ልጆች ወላጅ የሚመክራቸውን መች ይሰሙና! አንተስ ወልደህ አይተኸው የለ? ምን አድርግ ነው የምትለኝ?” አሉት።
“በቀለ ያለበትን ብቻ ይንገሩኝ፣ የማደርገውንስእኔ አውቃለሁ!” አለ።
አባ ጃሌም ደብዳቤውን ከጻፈው ልጅ ሌላውን የቤት ለጅ ጠርተው፣ ከትራስጌ ቀደም ብለው ያስቀመጡትን ደብዳቤ አወጡና፤ “ባለፈው ሰሞን በፖስታ የመጣልኝ ነው፣እስኪ ልጄ አንብብልኝ…”እያሉ ሰጡት።
ልጁም፤ “አባባ፣ ለጤናዎ እንደምን አሉ…” ወዘተ፣ ብሎ ስላምታውን ካቀረበ በኋላ፣ ስለ ራሱ ጤንነት፣ ቀጥሎም የሥራ እድገት አግኝቶ ወደ ሓረር መዘዋወሩን የሚገልጽ ዝርዝርና በቅርቡም ወደ አውራጃው ከተማ መጥቶ እንደሚሰናበታቸው የሚገልጽ ወሬ አበሰረ። ይኸ ሁሉ አባ ጃሌ አስቀድመው ያውጠነጠኑትና የጠመጠሙት ሲሆን፣ በቀለ አባቱን ሊያይ ይመጣል ብሎ አቶ ስንዱ ከዚሁ ተቀምጦ እንዲጠብቅና፣እሱን ለማደን ወደ ጅማ እንዳይሄድ ያዘጋጁት የተንኮል ደብዳቤ ነበር።
አቶ ስንዱ ይኸንን ሲሰማ፤ “መቸ ነው ደብዳቤው የተጻፈ ብሎ ጠየቀ። አባ ጃሌም አስቀድመው ባውጠነጠኑት የደብዳቤው እለት የዛሬ ሦስት ሳምንት አድርገውታል። አቶ ስንዱ፤ “ነገውኑ ወደ ሓረር እገሰግሳለሁ!”እያለ ደጋግሞ ደነፋ። ቀጥሎም፤ “ካልገደልኹት ይኽን ሱሪየን ግልብጨ ነው የምለብሰው። ልጄን ደፍሯት እንዲሁ በከንቱ አይቀርም!” አለ።
አባ ጃሌም፤ “እኔ ምንም የምልህ የለኝም።እንዳልከው ሂድና ግደለው። እውነትህን ነው፤ እኔም ሴት ልጄን ማንም ሰው ቢደፍርብኝ ያው ነው። አልምርም። ሂድ ግደለው!” አሉት።
አቶ ስንዱ ይህ ፈጽሞ ያልጠበቀው መልስ ሆኖበት ግራ ገባውና ምን እንደሚላቸው ጠፋው። አንደበቱ ሁሉ ተሳሰረ። ነገሩን ሲጀምር ‘ልጄን እንዳትነካ!’ የሚሉት መስሎት ነበር፣ ‘ሂድና ግደለው…’ የሚል መልስ ሲሰማ ግን የቁጣ መንፈሱ በረድ እያለ መምጣቱ ከፊቱ በግልጽ ይታይ ነበር። ያም ቢሆን እንዳመጣጡ እየፎከረና እየደነፋ ወጣ።
ወጣ እንዳለ ግን አባ ጃሌው የቤት ልጆቻቸውን፤ “እስኪ ልጄን መግደል ቀርቶ የፊቱን ዝንብ እሽ ሲል አያለሁ! ወይ ጉድ! የዛሬ ሴቶች ወንድ ሲያዩ የሚሆኑትንእያጡ፣ ሲያቅበጠበጣቸው፣ እራሷ ለምናውስ ቢሆን ማን ያውቃል? አስገድዶኝ ነው ልትል ይሆን? ታድያ’ማ ከቤቱ ድረስ ምን ያመላለሳት ነበር? ደግ አደረገ! የወንድ ልጅ ‘ሰረቀ፣ ዋሸ’ ተብሎ አይወራበት እንጂ፣ ይኽ’ማ የጀግና ሥራ ነው የሠራው፣ ጐሽ!” አሉ።
አቶ ስንዱ እንደፎከረው በማግስቱ ማለዳ ገስግሶ፣ በአውቶቡስ ተሳፍሮ ሓረር መሄዱን ሰሙ። አባ ጃሌ የጻፉት ሁለተኛው ደብዳቤም ከጥቂት ቀናት በኋላ ደርሶ፣ ልጃቸው በቀለ ከጅማ በጎረቤት ስልክ ደወለላቸው። አባ ጃሌውም በከተማው የሆነውን ሁሉ ዘርዝረው በማስረዳት፣ “ልጄ! ተጠንቀቅ፣ ለጥቂት ቀናት ነገሩ እስኪበርድ ድረስ ከወንድሞችህ ዘንድ፣ አዲስ አበባ ሂድና ተደብቀህ ቆይ… ነገሩ ሲበርድ እኛውእንነግርሃለን።” ብለው መክረው አስጠነቀቁት።
አቶ ስንዱ ሓረር ለሳምንት ያህል ተንከራትቶ፣ በቀለን ቢያጠያይቅ ሳያገኘው ቀረ። ምናልባት ገና ከጅማ አልተዘዋወረ ይሆናል በማለት ወደ ጅማ ሄደ። ከዚያም አጠያይቆ በቀለን በሥራ የሚያውቁት ሰዎች አገኘ፣ ግን በጅማ ከተማ ለጥቂት ቀናት አለመታየቱን እንጂ ወዴት እንደ ሄደ ለማወቅ አልቻለም። ተስፋ ቆርጦ በሁለተኛው ሳምንት ከቤቱ ተመለሰ። የከተማው የማዘጋጃ ቤት ቋሚ ሠራተኛ በመሆኑ፣ በልጁ ሰርግ ሰሞን በወሰደው እረፍት ላይ ተጨምሮ የዓመት እረፍቱ ቀናቶች ሊያልቁበት ሆነና፣ ሳይወድ ከሥራው ገበታእንዲመለስ ተገደደ።
“የዋለ፣ ያደረ ነገር አትጥላ!”እንዲባል፣ ውሎ አድሮ ነገሩእየቀዘቀዘ መጣ፣ አባ ጃሌውም አቶ ስንዱን እንታረቅ ሲሉ ሽማግሌዎች ላኩበት።ከአቶ ስንዱ ዘንድ የተላኩት ሽማግሎች ከቤቱ ገብተው፤ “አባ ጃሌው ራሳቸው መጥተው፣ በጉልበታቸው ከመሬት ተንበርክከው ይቅርታ ቢጠይቁህ በወደዱ ነበር። ግን እንዳየኻቸው አርጅተው የአልጋ ቁራኛ ሆነዋል። ‘ሰው ቂም ይዞብኝ እንዳልሞት’እያሉ በጣም ተጨንቀው ነው የላኩን። ታድያ ቂምህን አውርጃለሁ በላቸው!” አሉት።
እርሱም፤ “እኔ ከእርሳቸው መች ተጣላሁ፣ የምን ቂም ኖሮኝ ነው እርቅ የሚያስፈልገን? ያልተጣላ ይታረቃል እንዴ?”እያለ አንገራገረ።
እነርሱም ቀጥለው፤ “እስኪ ከዛሬ ልጆች ማን ነው የአባት፣ የእናት ምክር የሚሰማ? ምን ያድርጉ ብለሃቸው ነው?እሳቸውም እንደሆኑ ከአፋቸው የሰማኸው አይደለም እንዴ? የልጃቸውን ጥፋት ተቀብለው፣ ‘ሂድ ግደል!’ አሉ እንጂ፣ ልጄ ነው ብለው ጥፋቱን ለመሸፈን አልሞከሩ፣ አላንገራገሩ! በል እንግዲያው አሁን እንዳልካት ከአባ ጃሌው ጋር ቂም ከሌለህ፣ አሁኑ ሄደህ፤ ‘አኔ በእርሰዎ ላይ ቂም የለኝምና፣ ‘ይቅር!’ ብያለሁ’ በላቸው እና በሰላም ይሙቱ። ይቅር ለእግዚሄር ነው!”እያሉ ለመኑት፣ ተማጠኑት።
አቶ ስንዱ የተላኩትን ሦስት ሽማግሌዎች፣ የገፋእድሜያቸው፣ የሸበተው ጺማቸው፣ የተመለጡ ራሶቻቸውን፣ ከደረቡት ነጭ ጋቢ ጋር፣ ድንቅና እጹብ ግርማ ሞገስ አልብሷቸው ሲያይ፣ ከቤተክርስትያን ያለውን የሦስቱ ሥላሴን ምስል ያየ ሆኖ ተሰማው፣እንዴት ብሎ እምቢ ይበል? ወዲህ፣ ወድያ አያለ፣ የባጥ የቆጡን እያወጣና እያወረደ ዘላበደ፣ ለጥቂት ጊዜም አቅማማ።እነርሱስ መች ዋዛ፤ “እሺ እስክትለን ከተቀመጥንበት አንነሳም፣ ከቤትህም አንወጣም!” ብለው ወጥረው ያዙት፣ መፈናፈኛም አሳጡት።
ቢጨንቀውና መውጫ ቢያጣ፤ “ካላችሁስ እንግዴህ ምን ላድርግ፣እሺ!” አላቸው። ሦስቱም ተራ በተራእየተነሱ፣ አንቀው እየሳሙ፣ “እመቤታችን እግዚትነ ማርያም ራሷእሺ ትበልህ፣ ተባረክ ልጃችን፣ ረዥም እድሜና ሙሉእንጀራም ጨምሮ፣ አብዝቶ ይስጥህ!”እያሉ መረቁት።
አቶ ስንዱም፤ “አሜን፣ አሜን!”እያለ ምርቃታቸውን ተቀበለ።
“በል እንግዴህ ዛሬ፣ ነገ ሳትል፣ ፈጥነህ ሄደህ ጠይቃቸው፣ የሽማግሌ ነገር አይታወቅም፣ ብዙ ቀን የቀራቸውም አይመስሉም። ንስሓ ገብተው፣ ነፍሳቸውን አዘጋጅተው፣ ስጋ-ወደሙእንዳይቀበሉ፣ አንተ የያዝክባቸው ቂም በልባቸው ገብቶ፣እስካሁን የጋረዳቸው እሱ ብቻ ነው!” አሉት።
“እሺ፣ እሺ! አባቶቼ፣ ያላችሁኝን ሁሉ በቶሎ እፈጽማለሁ!” ብሎ ቃል ገባላቸው። ከዚያም ሽማግሌዎቹ ተነስተው ወደ መጡበት ተመለሱ።
የአባ ጃሌው አሰተዋይ ጥበብና ዘዴ እንዲያ ቦግ ብሎ ሊነድድ እና አገር ሊያቀጣጥል ተነስቶ የነበረውን እሳት አበረደው። አቶ ስንዱም በገባው ቃል መሰረት ከጥቂት ቀናት በኋላ ከአባ ጃሌው ቤት ሄዶ ቂሙን ማውረዱ ሊገልጽ ሲገባ፣ እሳቸውም በቀረችው ጉልበታቸው፤“ልጄ! ልጄ!እሰይ፣እሰይ! እንኳን’ማ መጣህልኝ!”እያሉ ከአልጋ ሊነሱ ሲሞክሩ፣ ያረጀውና የሳሳው አካላታቸውን አይቶ አንጀቱ ክልውስውስ አለበት። የበፊት ንዴቱ ወዴት እንደ ገባ እርግፍ አድርጎ ረሳው።
“የለም! የለም አባቴ! አይነሱ! አይነሱ! አይገባም፣ አረ ፈጽሞ አይገባም!”እያለ እንዳይነሱ ለመከልከል ወደእርሳቸው ጠጋ ሲል፣ አባ ጃሌውም፤ “ይቅር በለኝ ልጄ፣ ይቅር በለኝ!”እያሉ ተንገዳግደው ከላዩ ዝልፈልፍ ብለው ተጠመጠሙበት። እንደምንም ደጋግፎ ከአልጋው መልሷቸው፤
“እኔ እርስዎን መች ተቀየምሁ? አረ ይተውኝ አባቴ፣ ደግሞስ ምን ቂምና ይቅር የሚባል ነገር ኖሮ ነው?” ብሎ ሲላቸው፣ ሁለቱም ተቃቅፈው፣ ተላቅሰው፣ ‘ይቅር! ይቅር ለግዚሄር!’ ተባብለው ተሳሳሙ።
ወድያውም ቡናው ተፈልቶ፣ የማሽላ ቆሎ ፍንድሻ ተፈንድቶ፣ አብረውእያወሩና እየተጫወቱ እኽል ውሃ ብለው ታረቁ። ከዚያ ቀን ጀምሮ፤ ‘አሁኑኑ እገድለዋለሁ! በቀለን ካለበት ውለዱ፣ የታለ?’እያለ ሲፎክር የነበረው አቶ ስንዱም ቂሙና ቁጣውንእርግፍ አድርጎ ረሳው።
በሁለቱም ቤት መካከል ሰላም ወረደ። መታረቃቸውም በሰፈሩ ሁሉ በይፋ ታወቀ። ከዚያማ ወድያ አቶ ስንዱ ዋና ቤተኛና ዘመድ ሆኖ አባ ጃሌውን ዘወትር እየተመላለሰ ይጠይቃቸው ነበር።እንግዴህ አባ ጀሌው በቀለ ሊጠይቃቸው ሲመጣ አንዲት ጊደር ወይ መሲና ብጤ አስይዘው ከአቶ ስንዱ ቤት ሄዶ ይቅርታ እንዲጠይቅ ይልኩታል። ከዚያም ወድያ የቂሙ ጉዳይ አበቃ፣ ተከተተ ማለት ነው። ለጥፋት ታጥቆ የመሚጣውን ጠላት ተቀብሎ ወዳጅ ማድረግ ረቂቅ ጥበብና ዘዴ የሚጠይቅ ነው።
መደምደሚያ፦
በተፈጥሮእጅግ ከሚደንቁ ረቂቅ ነገሮች አንዱ፤ ዘወትር አካላታችንን ለመጉዳትና ለማጥቃት፣ ከሆነላቸውም ለማጥፋት የሚችሉ ብዙ ዓይነት ጠንቀ-ኅዋሳት ወደ ውስጣችን ይገባሉ። ሰውነታችንም ሁሌ ሲዋጋቸው ይኖራል። የሚጎዱትንና የማይጠቅሙትን ጠንቀ-ኅዋሳት በብዙ ዘዴዎች አንጥሮና አበጥሮእየለየ በብጉር፣ በላብ፣ በሽንትና በእዳሪ መልክ ውጭ አውጥቶ ሲጥል፣ አንዳንዶቹን ግን በልዩ ዘዴ አባብሎ በመያዝ በተለያዩ ብልቶች ውስጥ በማስቀመጥ በብዙ አገልግሎት ላይ ያውላቸዋል።
በጨጓራችንና በሌላውም መላው የሰውነታችን ክፍሎች ከሚኖሩት ብዙ ዓይነት ጠንቀ-ኅዋሳት ጋር፣ በሰውነታችንና በኅዋሳቱ መካከል ግሩምና ረቂቅ የሆነ ስምምነትና መግባባት በመፈጠሩ፣ ካለእነርሱ ልንኖር ቀርቶ፣ ለደቂቃም ቆመን ልንሄድና ልንተነፍስም አንችልም። ጠንቀ-ኅዋሳቱ ለእኛ የሚጠቅሙ ልዩ-ልዩ ተግባሮችንእየሠሩ ሲያገለግሉን፣እኛም የምግብ ምንጭ፣ መኖሪያ፣ መጠጊያና ከለላም ሆነናቸው በስምምነትእንኖራለን።
ለመጉዳት የሚመጣውን ጠላት አባብሎና አግባብቶ የልብ ወዳጅ ማድረግ ጥልቅ አስተዋይነትና ዘዴ ሲጠይቅ፣ በዓለም ላይ ከዚያ የበለጠ ጥበብ አለ ብሎ ለማለት ያዳግታል። ይህን ጥበብ የዓለም መሪዎች በሥራ ላይ ቢያውሉት ኖሮ ምድር ገነት በሆነች ነበር።
አባ ጃሌው ፊዴል ያልቆጠሩ መሃይም ናቸው፣ ግን ተፈጥሮ ባደላቸው ብሩህና አስተዋይ አEምሮ ይህንን ጥልቅ የተፈጥሮ ጥብበ ደርሰውበታል። በሕይወታቸው ዘመንም ዘዴውን ደጋግመው በሥራ ላይ አውለውታል።
*የአባ ጃሌው ታሪክ በእውነተኛ ሰው ሕይወት የተመሰረተእንጂ ልብ-ወለድ አይደለም። የታሪኩ ኮከብ የሆኑትም ሰው ከመቶ ዓመት በላይ ኖረው ከጥቂት ዓመታት በፊት ከዚህ ዓለም በሰላም አልፈዋል።
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: አዲስ ፎረም

Postby እንሰት » Wed Nov 04, 2009 11:21 pm

እንሰት wrote:ሰላም ዋርካውያን
ይቺን ያማርኛ ልብ ወለድ ጽሁፍ ያላትን ድረ ገጽ ጎብኙአት

http://www.scribd.com/AmharicWriter

መልካም ቅኝት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ocean12 » Thu Nov 05, 2009 12:05 am

ሰላም ወዳጅ እንሰት እንዴት ከርመሀል? እንደወትሮው ጥሩ ማጣቀሻዎች ለማለት ያክል ነው :)
ቶሎ ቶሎ ምጣ :)

መልካም ጊዜ ይሁንልህ::
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Re: አባ ጃሌው ከ አዲስ ፎረም

Postby ፍቅርኢትዮ » Thu Nov 05, 2009 1:29 am

በጣም ጣፋጭ ታሪክ ነው ወድጂዋለው.. :D :D እናመሰግናለን!!
ፍቅርኢትዮ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Mon Aug 10, 2009 2:00 am
Location: US

Re: ወጋየሁ ንጋቱ

Postby እንሰት » Fri Mar 05, 2010 1:17 pm

እንሰት wrote:በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2004 የወጋየሁ ንጋቱን ድረ ገጽ አገኘሁና አንድ ሁለት መጣጥፎችን አተመኩ:: ሳስታውስ wegayehu nigatu art center የሚባል ድርጅት ይመስለኛል ድረገፁን የጀመረው::
አሁን አድራሻውን ፈላለኩና እዚህ አመጣሁት
http://www.wegayehunegatu.org

ምን ገጠመኝ መሰላችሁ::ጽሁፎቹ እንዳሉ ለማረጋገጥ ፍተሻ አድርጌ ምንም ነገር የለም:: ፒሲዬ የስህተት ምልክት አሳየችኝ::

እስኪ ዋርካውያን እና ዋርካውያት መላ አያጡም ብዬ እዚህ ከተብኩት:: መላ በሉ::

መቼም ወጋየሁ ንጋቱ ማን ነው ተብዬ እንደማልጠየቅ ነው::

ሰላም
ይቺን በአዲስ መልክ የተደራጀቺውን የወጋየሁን ድረገጽ ማጣቀሻ ይዤ ብቅ አልኩ::

http://www.wegayehunegatu.org/index.html

ከድረ ገጹ ቅንጫቢ እነሆ

Wegayehu Negatu, one of the brightest stars to come out of the Ethiopian Theatrical scene, was born on June 1944 in Qebenna, Addis Ababa. Wegayehu attended the Swedish Evangelical Mission School and he went on to complete his secondary education at Teferi Makonnen.
Wegayehu Nigatu Art Center
Attn. Amsale Genet
P.O.Box 3332
Georgia Ave.
Washington DC. 20010
Tel - 240.351.4602
Email support@wegayehunegatu.org

Thank you for your support!!
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ይችንም ተመልከቷት

Postby ወለላዬ » Fri Mar 05, 2010 5:44 pm

ይችንም ድህረ ገጽ ተመልከቷት አዲስ ብትሆንም ወደፊት ጥበብ ምታቆአድስ ነች

http://kitabethiopia.com
ወለላዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 403
Joined: Wed Jan 26, 2005 11:20 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests