የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Re: ይችንም ተመልከቷት

Postby እንሰት » Fri Mar 05, 2010 9:47 pm

ወለላዬ wrote:ይችንም ድህረ ገጽ ተመልከቷት አዲስ ብትሆንም ወደፊት ጥበብ ምታቆአድስ ነች

http://kitabethiopia.com

አዎ ድረ ገጹዋ አዲስ ነች ንጥት ጥድት ያለች:: ጠንካራ የባለሙያዎች ስብስብ የታከለባት:: በርቱ ተበራቱ እንላለን::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ለ ሎሬት ፀጋዬ መታሰቢያ ከወልደ አማኑዔል

Postby እንሰት » Wed Mar 10, 2010 1:59 pm

ለጸጋዬ ወዳጆች

ብዕር ሆይ! (ከወልደ አማኑኤል)

(ለሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን መታሰቢያ)

ብዕር ሆይ!

ማነው ፀጋሽን የገፈፈሽ

የቀለም ብልቃጡን ማነው ያነጠፈብሽ?

ሕመም ይሆን የሰው ልጆች ጠላት

ስደት ይሆን የሀገር ፍቅር ናፍቆት

የመድረክ ንጉሦች ወጋየሁና አውላቸው

ድረስልን ብለውት ይሆን ቴአትር ትወና ናፍቋቸው

ወይንስ መንግሥቱ ለማ፣ የቅኔ ረሃብ ጠንቶበት

“ፀጋዬ” ብሎ ሲጠራው፣ ጥሪውን ሲያከብርለትብዕር ሆይ!

ማነው ፀጋሽን የገፈፈሽ

መልስም የለሽ

ዋይ! ከአሁኑ ዝምታ ዋጠሽ

ዓርማውን የሚያነሳ ተተኪም ልጅ የለሽብዕር ሆይ!

ይብላኝ ላንች እንጅ እኛ ምን ጎድሎብን

የእሾህ አክሊልና በልግ የከርሞ ሰው በእጃችን

እሳት ወይ አበባ፣ ኦቴሎና ሐምሌትን

በንባብ እንጠግባለን ከመደርደሪያችን አውጥተን

ቢሻን በትዝታ - መድረክ ቴአትር እየቃኘን

ሀሁ አቡጊዳ፤ መልዕክተ ፐፑ እንላለንብዕር ሆይ!

ጥናቱን ይስጥሽ

ዳግም የማይገኝ ፀጋሽን ነው የተገፈፍሽ

ከወልደ አማኑኤል

(ፀጋዬ ያረፈ ሰሞን የዛሬ አራት ዓመት ገደማ የተደረሰ)
http://cyberethiopia.com/news/?id=151788
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

የቁም ነገር መጽሄት ድረ ገጽ

Postby እንሰት » Sat Mar 13, 2010 3:35 pm

ሰላም የስነ ጥበብ እና የስነ ጽሁፍ አፍቃሪያን:: አሁን በቅርቡ የቁም ነገር የኪነጥበብ መጽሄትን ድረ ገጽ ማያያዣ በማግኘቴ ላካፍላችሁ ብቅ አልኩ::

እንደምትደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ::
http://www.kumnegermedia.com/index.php

ሰናይ ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ቁም ነገር

Postby ዋኖስ » Sat Mar 13, 2010 4:57 pm

ሰላም እንሰት! በቅድሚያ ታላቅ ምስጋና!

እስካሁን ድረስ ካየኍቸው የአማርኛ መረጃ መረባት ለእኔ በአደረጃጀቱና በአወቃቀሩ የተሟላ "ሳይት" አላገኘሁም ነበር:: ይህን ግን በእጅጉ በጣም ወድጀዋለሁ:: እንደ መረጃ መረብነቱ ማካተት ያለበትን ጥበብና የጥበብ ዉጤቶች ወይንም ዘሮች ይዟል:: እናም በነካ እጂህ እናመሰግናለን! በልልኝ::

አዘጋጆች በጣም ግሩም ስራ ነው በርቱ! ለነገሩ ስብስባችሁም ምርጦች ናችሁ! ለጥበብ ቅርብ ዝምድና ያላችሁ ማለቴ ነው::ከመልካም አክብሮት ና ምስጋና ጋ!

ዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Re: ቁም ነገር

Postby እንሰት » Sat Mar 13, 2010 11:58 pm

ዋኖስ wrote:ሰላም እንሰት! በቅድሚያ ታላቅ ምስጋና!

እስካሁን ድረስ ካየኍቸው የአማርኛ መረጃ መረባት ለእኔ በአደረጃጀቱና በአወቃቀሩ የተሟላ "ሳይት" አላገኘሁም ነበር:: ይህን ግን በእጅጉ በጣም ወድጀዋለሁ:: እንደ መረጃ መረብነቱ ማካተት ያለበትን ጥበብና የጥበብ ዉጤቶች ወይንም ዘሮች ይዟል:: እናም በነካ እጂህ እናመሰግናለን! በልልኝ::

አዘጋጆች በጣም ግሩም ስራ ነው በርቱ! ለነገሩ ስብስባችሁም ምርጦች ናችሁ! ለጥበብ ቅርብ ዝምድና ያላችሁ ማለቴ ነው::ከመልካም አክብሮት ና ምስጋና ጋ!

ዳሞት

ትልቁ ወዳጄ;
አንተ ውደደው እንጂ ለማድረስ ምን ከፍቶኝ:: ምስጋና ይገባቸዋል ልክ ነህ::
አክባሪህ
እንሰት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ማሪቱ ለገሰ - አሪታ ፍራንክሊን

Postby እንሰት » Wed Mar 17, 2010 8:52 am

ወለላዬ wrote:ይችንም ድህረ ገጽ ተመልከቷት አዲስ ብትሆንም ወደፊት ጥበብ ምታቆአድስ ነች

http://kitabethiopia.com

ክታብኢትዮጵያዎች ማሪቱን አወድሰዋታል::

ኢትዮጵያዊቷ አሪታ ፍራንክሊን
http://ethiopiazare.com/art/art-opinion ... a-frnaklin

ዘነበ በቀለ

ርዕሱ ብዙዎችን ያሳስታል ብዬ አልገምትም። የሁለቱንም ዘፋኞች ሙዚቃ አገናዝቦ መረዳት የሚቻል ነውና። አሪታ በልጅነት ዘመኗ ”ሬሰኩዩሚ” እያለች ያቀነቀነችው ሙዚቃ በአንድ በኩል የሙዚቃው ርዕስ ጭንቀቷን ገላጭ ቢመስልም፤

በሌላ በኩል ደግሞ የድምፅዋን ልክ ያሳየችበት ዕፁብ ድንቅ የሆነ ዜማዋ ነው። ኢትዮጵያዊቷ አሪታ ፍራንከሊን ደግሞ በባህላዊ መንገድ ችግርን አምቆ መያዝ እንጂ ለአደባባይ አስጥቶ ማሳየት የተለመደ አይደለምና ሁሉን ቻይ ሆና መከራዋን

የምትገፋው ድምፃዊቷ ማሪቱ ለገሠ ነች። ማሪቱ ከአሪታ ጋር የምትመሳሰልበትና የምትለያይበት ጉዳይ አለ። የምትመሳሰለው በድምፅ ገደቧ ማለትም የሶፕራኖ ድምፅን ገደብ ሙሉ በሙሉ አጠናቃ የምትጫወት መሆኗ ሲሆን፤ የምትለያየው ደግሞ አድኑኝ በማለት እንደ አሪታ አለመጠየቋ ነው። ማሪቱ በሀገራችን ውስጥ የሶፕራኑ ድምፅ ገደብን ጠብቃ የምታቀነቅን ምንም አይነት የፎልሴቶ አዘማመር ጠባይን የማትከተል በይበልጥም የጉሮሮ አዘማመር ባህርይን የያዘች ብቸኛ ዘማሪ ነች። ከሷ ጋር ተመሳሳይ

አዘማመር ባህርይ የምትከተለው ብዙነሽ በቀለ ስትሆን የዜማ ስኬል ገደባቸው አንድ ቢሆንም ባሠራር ቴክኒክ ይለያያሉ። ብዙነሽ የመተላለፊያ ዜማዎችን በትናጋ፤ በራስና በላንቃ አዘማመር ፈሊጥ አስቸጋሪውን ቦታ ስታልፈው፤ ማሪቱ ግን ልክ

እንደ አሪታ ፍራንክሊን ፊት ለፊት ተጋፍጣ ድምፅ የምትፈጥረው ያለምንም ቮይስ ማስክ መሆኑ በ”አምባሰል” ሙዚቃዋ ላይ ይንፀባረቃል። ማሪቱ የባህል መገለጫ ናትና አምባሰልን ስትዘምር በትክክለኛ ቶንና ስሜት ነው። ያም የሆነው አምባሰል ቅኝት የሚቃኘው በብሩህ ተስፋ አመላካችነት ስሜት ላይ በመሆኑ የማሪቱ ድምፅ ከርቀት ሆኖ የሚጣራ የተስፋ ምልክት ድምፅ ነው። ከዚህ ሌላ ቃላቶቿ ግልፅና ተደማጭ መሆናቸው ከአሪታ ጋር ያመሳስላታል።

ያለመታደል ሆኖ በሀገራችን ውስጥ የተፈጠሩ የሙያው ሰዎች ምንም ጊዜ በሙያቸው ተጠቅመውበት አያውቁም። ነፍሱን ይማረውና ታዋቂው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ የልጅነት ዘመኑን በሙሉ ሰውን በማዝናናት ሲያሳልፍ

ለሕይወቱ የሚበጀው ሀብት አልሰበሰበም ነበር። ታምራት ሞላ፤ አለማየሁ እሸቴ፤ መልካሙ ተበጀ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ ... ወዘተ በሕይወታቸው ገንዘብ ለማበጀት አልሮጡም። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ስጦታ ያላቸው አርቲስቶች በትምህርት

ዕውቀታቸውን የገነቡ አርቲስቶች ሁሉም አይነት አሏት። ነገር ግን አንዳቸውም በሙያቸው ተጠቃሚ ሆነው አያውቁም። ለምን እንዲህ ሆነ? ብሎ መጠየቅ ይቻል ይሆናል፤ ገንዘብ ባለመፈለጋቸው? ሁኔታው ስላልተፈጠረላቸው? መልስ ለመስጠት የራሱ ጥናት የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። አንዳቸውም ተጠቃሚ አለመሆናቸው ግን ያለ ሐቅ ነው። ሻለቃ ሳህሌ ደጋጎን ያህል አቀናባሪ የትም ተጥሎ የሽምግልና ዘመኑን በችግር እየገፋ ላለፉት ሰባት ዓመታት ከአልጋ ሳይወርድ መጋቢት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ለአንዴና ለዘለዓለሙ አጥተነዋል። በኃይሉ እሸቴ በሕመም ሲሰቃይ ነበር ሲባል ሰምተናል። ታላቁ ደራሲ ተስፋዬ ለማንስ ከምን ላይ እንደሆን የሚያውቅ አለ? ጌታቸው ካሣስ? አረ

ስንቱ! ...

ይህ የሆነበት ምክንያት ታላላቅ የሙያው ጠበቆች እንደ ፕሮፌሠር አሸናፊ ከበደ አይነቶቹ ባለመታደል ለሀገራቸው መሬት ሳይበቁ ያለፉ ናቸው። ሆኖም ግን በኖሩበት ዘመን ሁሉ የሙዚቃን ደረጃ ከፍ ለማድረግ ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። ያ! ጥረት ሰምሮ ቢሆን ኖሮ ዛሬ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ቢገፉት የማይነቃነቅ ሙያዊ ማኅበር በሆነ ነበር። ያለ ሙያ ማኅበር ደግሞ መብትን ማስከበር የሚታሰብ አይሆንም። ውጤቱ ለአንዳንድ አጭበርባሪዎች ሲሳይ ሆኖ መሰንበት ነው። በመጨረሻም ለሕመሙም ሆነ ለእርጅናው ዘመን የሚደርስለት ለአርቲስቱ ሁሉ የራሱ እንጉርጉሮ ሆኗል።

ሙዚቀኛ የህዝብን ጭንቀት ተጋሪ በመሆኑ፤ ከህዝብ ጭንቀትን ከሀገር ባህልን ይወርሳል። ስለሆነም በበሽታ የመጠመጃው ዕድል ከፍተኛ ነው። ልክ እንደማሪቱ በተፈጥሮ ፀጋቸው ያለምንም ፎርማል የድምፅ ልምምድ ተፈላጊው እርከን ላይ

የደረሱ ጥቂት አይደሉም። አሪታ ፍራንክሊን በቤተክርስቲያን ዘማሪነት ያዘማመር ፈሊጥን አውቃለች። የኛዎቹ ለማ ገብረህይወትና ማሪቱ ለገሰ ከከፍተኛው የድምፅ አወጣጥ ደረጃ ላይ ያሉ ናቸው። ግን አስተማሪያቸው ምናልባትም ለማሪቱ

የጦሳ ተራራ፣ ለለማ ገብረሕይወትም የቡልጋ ተራራ ሊሆን ይችላል። በገደል ማሚቱነት የተባበራቸው (reciprocal በሆነ አቀራረብ የተባበራቸው)።

በሀገራችን ሙዚቃ ላይ የየራሳቸውን ስታይል ትተው ያለፉም ያሉም ሙዚቀኞች በርካታ ናቸው። ለምሳሌም ያህል፦ ማሪቱ ለገሠ፤ ብዙነሽ በቀለ እና ለማ ገብረሕይወት የሶል ሙዚቃ ስታይል፤ ዓለማየሁ እሸቴ - ”ኢትዮ ሮክንሮል”፤

ጌጡ አየለ፣ መልካሙ ተበጀ፣ ትዕግስት ፋንታሁን እና አበባ ደሳለኝ - ”ካባሬት ሙዚቃ”፤ ባህታ ገብረሕይወት፣ ሙሉቀን መለሰ እና አስቴር አወቀ - ”ሪዝም ኤን ብሉስ”፤ እማሆይ ፅጌ ማርያም ገብሩ - ”ኢትዮ ክላሲካል

ፒያኖ” በተለይም የሜንዶልሰንና የሹበርትን አጨዋወት ስልት የተከተለ፤ አሸናፊ ከበደ - ”ሲምፎኒክ ፖየም” ለፍሉትና ለስትሪንግ መሣሪያዎች፤ ነርሲስ ናልባንዲያን - ኳየር፤ ከዚህ ሌላ በየጨዋታዎቹ ላይ የየራሳቸውን ችሎታ ያበረከቱ

በርካታ ናቸው ለመጥቀስ ያህል ጌታ መሳይ አበበ በትዝታ ላይ፤ ጌታቸው ካሣ እና በዛወርቅ በትዝታ ላይ፤ የግጥም አጠቃቀምን ከባህላዊው የወል ግጥም ስሪት ወጣ ባለ መልኩ አዲስ ስታይል በማቅረብ ያበረከቱ ደግሞ ንዋይ ደበበ፣

ቴዲ አፍሮ፣ ጎሣዬ ተስፋዬ፣ ፍቅር አዲስ ነቅዓጥበብ እና ትዕግስት በቀለ ሲሆኑ፤ ተሾመ ምትኩ፣ መልካሙ ተበጀ እና ፍሬው ኃይሉ ትሩባዱር ስታይልን በማስተዋወቅ፤ ... ወዘተ ይገኙበታል። ጥላሁን ገሠሠ፤ ታምራት ሞላ፤ መሐሙድ

አህመድ እና ዓለማየሁ እሸቴ በሶል፤ በጃዝ፤ በሪዝም ኤን-ብሉስ እና በሮክንሮል ውስጥ በርካታ ጨዋታዎች አሏቸው።

ባጠቃላይ ሙያቸው ሌላውን እንጂ እራሳቸውን ያልጠቀመ በሕይወት ያሉና ያለፉ በርካታ የሙያው ሰዎች መኖራቸው የማይታበል ነው። ካሣ ተሰማ ክራሩን በየሄደበት ከተጫወተ በኋላ ይሰብር ነበር። ሲጠየቅም ”እኔ ቧምቧ ሰሪ እንጂ

ሙዚቀኛ አይደለሁም” የሚል መልስ ነበር የሚሰጠው። ብስጭቱ ምን እንደሆን ግን ሳይታወቅለት ነው ያለፈው። አስናቀች ወርቁ በክራር፤ አሰፋ አባተ በመሰንቆ፤ የመጀመሪያውን ያገር ባህል ኦርኬስትራ የመራው እዩኤል ዮሐንስ በድርሰትና

በዝማሬ። መዲናና ዘለሰኛ ይጥና ታደገኝና አለማየሁ ፋንታ፤ ገረርሶ ወሰኑ ዲዶ በመሰንቆ፤ አርጋው በዳሶ በዝማሬ፤ በኦሮሞኛና በአማርኛ አቀላጥፎ የሚጫወተው አበበ ተሰማ በዋሽንት መላኩ ገላውና አፈወርቅ ወደር አይገኝላቸውም። ሁሉም

ለዚህ ሙያ ከፍተኛ አሰተዋጽዖ ያበረከቱ የሙያው ሰዎች ነበሩ። ናቸውም። በሙያቸው ተጠቅመውበታል? አይመስለኝም። የሙዚቃ ጥበባቸውን እንደዘሩ ሳይሰበስቡት ያለፉም በሕይወት ያሉም አሉ። ይህ ችግር በቀጣይነት የሚዘልቅ ለመሆኑ

አሁንም ያለው የሙያው ሰዎች አለመሰባሰብ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደርጋል። ስለዚህም ስቶክሆልም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሙዚቃና ድራማ ግሩፕ ሁሉም በያለበት ተደራጅቶ የጋራ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ማኅበር እንዲመሰረት ጥሪውን

ያቀርባል። ተመሳሳይ ግንዛቤ ካለዎት አስተያየትዎን በሚቀጥለው አድራሻ ያድርሱን።

የኢትዮጵያ ሙዚቃና ድራማ ግሩፕ

www.kitabethiopia.com
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ትውፊት በዳንኤል ክብረት

Postby እንሰት » Wed Mar 24, 2010 10:53 pm

ለረጅም ጊዜ የማሕበረ ቅዱሳን አስተባባሪ የሆነው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለ ኢትዮጵያ ትውፊቶች የራሱን እይታ የሚያወጋበት የድረ ገጽ አምድ ጀምሯል::

ለቅምሻ ይቺን እዩአት::
ለምጣዱ ሲባል

በትግራይ የሚነገር አንድ ብሂል አለ፡፡ አንድ ባል እና ሚስት አንዲት ትንሽ አይጥ አስቸገረቻቸው፡፡ አንድ ቀን ባል እና ሚስቱ ዱላ ዱላቸውን አንስተው የቤቱን ዕቃ ሁሉ ገልብጠው አይጧን ማሳደድ ጀመሩ፡፡ በዚህ ሲሏት በዚያ፣ በዚያ ሲሏት በዚህ ብዙ እያለች በጣም አደከመቻቸው፡፡ በመካከሉ ሚስቲቱ አይጧን ስታባርር አይጧ ዘልላ ምጣዱ ላይ ወጥታ ቁጭ አለች፡፡ ሚስቲቱም የሠነዘረችውን ዱላ ወደ ኋላ መልሳ፣ አይጧን በአግራሞት ማየት ጀመረች፡፡ ባልዋም የሚስቱን ሁኔታ ተመልክቶ «ምነው ትቆሚያለሽ አትያትም ወይ?» አላት፡፡ ብልኋ ሚስትም «መምታቱ አቅቶኝ አልነበረም ነገር ግን «ምእንቲ ዛ ምጎጎ እታ አንጭዋ ትሕልፍ» አለችው ይባላል፡፡ «ስለ ምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ ብዬ ነው» ማለቷ ነው፡፡

ለዚያች እናት ምጣዱ የትዳሯ ትልቁ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ እንዲህ እንደ ዛሬ እንጀራ ተገዝቶ መበላት ሳይ ጀምር በፊት ያልጋገረ ሰው እንጀራን አያገኘውም፡፡ ከዚያውም በላይ ደኅነኛ ምጣድ ከገበያ እንደ ልብ አይገኝም፡፡ ቢገኝም ማሟሸቱ ብዙ ሞያ እና ድካምን ይጠይቃል፡፡ እናቶቻችን ወዝ የለመደ ምጣድ የሚሉት አላቸው፡፡ የጋጋሪዋን ወዝ የለመደ፣ ጋጋሪዋም ጠባዩን የለመደችው ምጣድ ማለት ነው፡፡ እንዲያውም እንዲህ ያለው ምጣድ የትም ስለማይገኝ ለድግስ ሥራ ሲጠሩ የራሳቸውን ምጣድ ይዘው ሄደው የእነርሱን ድርሻ በለመዱት ምጣድ የሚጋግሩ እናቶች ነበሩ፡፡ አሉም፡፡ ለዚህ ነው ያቺ እናት «ምእንቲ ዛ ምጎጎ እታ አንጭዋ ትሕልፍ» ያለችው፡፡

ለሰርክ ንባብ የድረ ገጹን ማያያዣ እነሆ
http://www.danielkibret.com/

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views

ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባሕል፣ እምነት፣ ፖለቲካ እና ትውፊት ምልከታዎች ይቀርቡበታል This blog will reflect my views on Ethiopia's culture, politics, religion and tradition.
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ከ ቻሌንጅ አዲስ መጽሄት - የግጥም ስራዎች

Postby እንሰት » Tue Mar 30, 2010 8:11 am

አዲስ በድረ ገጽ የተናኘ መጽሄት አገኘሁና ላካፍላችሁ ብቅ አልኩ::
ከስለሺ ሐጎስ ስራ የቀነጨብኩትን ሁለት ግጥሞች እዩና ሌላውን እዚያው አንብቡት

http://ecadforum.com/blog1/News/1109

ብቸኝነት
ቀኑ ተሰናብቷል፤
ጨለማው በርትቷል፤
ጨረቃ የት ጠፋች?
ምን ሆኑ ኮከቦች?
ጅቦቹ አይፈነጩ!
ውሾቹ አይንጫጩ!
ጨለማው ፍፁም ነው
ነፋስ ጭራሽ አይነፍስ!
ሳሩ አይወዛወዝ፤
አንድ ወፍ አይላወስ!
ሁሉም ጸጥ!
በያለበት ለጥ!
ሰው ሁሉ ምን ነካው?
ድምፁ እንዲህ የጠፋው?
እኔንስ ምን ነካኝ
እንቅልፍ የማይወስደኝ ?
እኔ ብቻዬን ነኝ
በዚህ ደረቅ ውድቅት ፤
ልቤ እያቃተተ ጠልቶ ብቸኛነት
ሰው አለ ወይ ባገር
ማረፊያ ለፍቅር
ፈላጊና - ተፈላጊ ሁሉ፤
ቀናው ወይ በሙሉ?
የቀረ የለም ወይ ባገሩ አለኔ
በምኞት ኩነኔ!
እኔ እንደዚህ ስዋኝ
ባሳብ በትካዜ
የት ይሆን ያለሽው
አንቺ ይህን ጊዜ
ምን ታደርጊ ይሆን?
እንገናኝ ይሆን?
መች ይሆን ዕለቱ?
ምን ይሆን ሰአቱ?
የትስ ይሆን ቦታው
እንዴት ይሆን እውቂያው?
እጠብቅሻለሁ ልቤን እየታዘዝሁ፤
አትቅሪ! ፈልጊኝ! እፈልግሻለሁ!
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

አድባር
ጉልበትህን አሟጥብኝ
እየጨከንክ ጨክንብኝ
ደሞ አድስ አዲስ አውጣ
አውሬነትክን ጨርስ አምጣ
በስቃዬ ለመደሰት ለነጻነት
ለነገ ስል ዛሬ ልሙት
ለዚህ ታሰብኩ ለዚህ መጣሁ
ሸክሜ አይደለም አምባሬ ነው
እንካ ደረት ለርካሹ ለጥይትህ
እንካ ኑሮ ላውሬነትህ
አፈራርሰው
አሰናክለው
አውተብትበው
ሞክር! ሞክር! ሁሉን አርገው
ሀዘኔ አይደል ሀሴቴ ነው
ግን ልንገርህ ቀና ብዬ
ከሰው መሀል ተነጥዬ
ፍጠን! ፍጠን! ቶሎ ተሎ
ሁሉን ከውን ዛሬን ውሎ
ነገማ ያንተ አይደለም
ከጅህ ወጥቷል አልፏል የለም
የልጄ እንጂ የወለድኳት
በምጥ ስቃይ ያመጣኋት
የኮከቧ የደማቋ የሀሌዋ ፍልቅልቋ
የርሷ አለም ግን ዝቃጭ የለው
እድሜ ላንተ ጨርሰኸው
ያንተ ጥይት የነግ ናፍቆት
ይቺን ቆንጆ ውቧን አለም
ስቦ አመጣት

በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby እንሰት » Fri Dec 10, 2010 8:39 am

ሲመቸኝ ብቅ እያልኩ አንዳንድ ድረ ገጾችን ማስተዋወቄ አልቀረም:: እነሆ ዛሬም በሀይማኖት ጉዳይ የሚያተኩሩ ድረ ገጾች ግብዣ

http://www.dejeberhan.org/
http://betedejene.blogspot.com/
http://www.kesisyaredgebremedhin.com/

http://www.ethiopianmuslims.net/
የመጨረሻው በሁለት ቁዋንቁዋ ነው::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby እንሰት » Thu Dec 16, 2010 4:10 pm

ይቺን ድረ ገጽም ደርባችሁ እዩዋት
http://www.atlantaabo.org/

እንሰት wrote:ሲመቸኝ ብቅ እያልኩ አንዳንድ ድረ ገጾችን ማስተዋወቄ አልቀረም:: እነሆ ዛሬም በሀይማኖት ጉዳይ የሚያተኩሩ ድረ ገጾች ግብዣ

http://www.dejeberhan.org/
http://betedejene.blogspot.com/
http://www.kesisyaredgebremedhin.com/

http://www.ethiopianmuslims.net/
የመጨረሻው በሁለት ቁዋንቁዋ ነው::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby እንሰት » Wed Jun 01, 2011 10:35 pm

ተገላቢጦሽ

በሃገር ቤት ሳለን ….

ኩታ ከደራረበው መሀል - እርቃኑን ሲሄድ ብናየው
አንጀታችን ቢላወስ - አበደ ለየለት አልነው
አይሰማ የለ ዛሬ - ይኽው ደርሰን ከውጭ ሃገር
ለቅፅበት ላፍታ ያህል - ድንገት ብትወጣ ጀንበር
እርቃኑን ከተመመው መሀል - ብንታይ ኩታ ደርበን
ከእብዶች ጎራ ፈረጁን - ዘመኑ ይህን አሳየን

ወይ ጉድ …….!

በትሩዝ የተገጠመ!

ምንጭ http://metatef.org/wpmu/amxambe/
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby እንሰት » Tue Jun 07, 2011 7:30 am

ጅምር ድረ ገጽ
http://abinetababu.wordpress.com/
ሲመቻችሁ ቃኘት አድርጉት
የናይሮቢ የጉዞ ማስታወሻዎች “የስልጣን ውል”
Posted on April 27, 2011 by AbinetAbabu

ለም አቀፋዊቷ የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን በየጊዜው አዳዲስ ካህናትን ትሾማለች። በተለይ በኬንያ ውስጥ የምትገኘው የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ግን በአብዛኘው ኬኒያውያን ዘንድ የታወቀች ነች። በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ያየሁትን እና በቤተክርስቲያን በፖለቲካውም ሊለመድ ይገባዋል የምለውን ነገር ላካፍላችሁ። የሚያስገርመው ነገር በኬኒያዋ የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ቢሾፕ ሲሾም ውል ይፈርማል አሉ። የምን ውል አትሉኝም። እኔ እከሌ እከሌ የተባልኩት በዚህ ቀን ከሌሊቱ ከዚህ ሰዓት ስለጣኔን ለቅቄ ለሚተካኝ ሰው እንደማስረክብ በመሃላ እና በፊርማዬ አረጋግጣለሁ ይላል። ታዲያ ሥልጣን ላይ ወጥተው በአመጽ ካልሆነ አንነሳም ለሚሉ በርካታ መሪዎች አያስፈልግም ትላላችሁ።
ሁለተኛውም ቢሆን የዋዛ አይደለም! ምን መሰላችሁ በዚች ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚመረጡ ቢሾፖች በየጊዜው ከተለያየ ጎሳ ነው የሚመረጡት። አሁን ኩኪዩ ፣ በሚቀጥለው ሉዎ፣ በሚቀጥላው ካልነጂ እያለ ይቀጥላል። ታዲያ በብሄር ተቧድነው ለሚናቆሩ አንዳንድ መሪዎቻችን ጥሩ መድሃኒት አይሆንም ትላላችሁ! እኔ ግን ሁለቱም መልካም ናቸው እላለሁ። ምን ይመስላችሃል?
ስለ ሌጂዮ ማርያ እና ስለጥቁሩ መሲህ ደግሞ እንጫወታለን…
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ሾተል » Tue Jun 07, 2011 9:47 am

ሰላም እንሰት::እንደምን አላችሁልን?እኛ ደህና ነን ስንል ሰሞኑን ገጠር ሄደን ላሞችና ጥጆችን ጎብኝተን ለዛውም ሁለት ደስ የሚሉ ከብቶች በምላሳቸው ፊታችንንና ጭንቅላታችንን ላስ ላስ ሲያደርጉልን ደስ ብሎን የጎረቤታችን የእነ እንትና ላሞችና በሬዎች ትዝ አሉን::

ልጅ እያለን የሰፈር ውሪዎች ተሰብስበን ስንጫወት በጣም ለማዳ የነበሩ ከብቶች ከሁዋላችን እየመጡ ይታገሉን ነበር::ታድያ የእኔን ጸጉር ትላስ የእኔን እያልን እንጣላ ነበር::ታድያ ሳይታሰብ ገጠር ብንሄድ ልጅነታችንን የሚያስታውሰን ድርጊት አጋጥሞን ደስ ብሎን በዛውም ትኩስ ወድያው የታለበ ወተት እንደጉድ ስንቀመቅም ሰንብተን ደረታችን አብጦ ከች በማለት እዚህ ቤት ለመግባት በቃን::

ታድያ እዚህ ቤት ዘው ያልንበት ጉዳይ እንደሚከተለው ነው::

እነሆ ፍሬ ነገሩ ሁል ጊዜ እንሰትን ስናየው ሁለዜ ወይም ኦልወይስ ወይም ኤቭርይ ታይም ወይም ኮንቲኒየስልይ ወዘተ ኢቲሲ እንሰት ሾተል ከሚሉት የዋርካ ባለጌ ተሳዳቢ ጋር ከተመላለሳቸው አንዳንድ አረፍተ ነገሮች ውጪ እንሰት አንድም ቀን ከራሱ ጽፎ ለዋርካ ያስነበበው ነገር የለም ነገር ግን የሰዎችን ጽሁፍና ድረገጽ ኮፒ ፔስት በማድረግ በጣም የታወቀ ስለሆነ ይቀራል ብለን አንጠረጥርም::

ታድያ እንሰትን የምጠይቀው ጥያቄ ሁልጊዜ የራሱን ሳይጨምር የሰውን ስራ ብቻ እየተከታተለ የሚያስተዋውቅ ሰው እውነተኛ የገሀዱ አለም ኑሮውም በኮፒ ፔስት የተሞላ ነው?ከሆነ እንዴት አንድ ሰውን የሚያክል ፍጡር እስከመቼ ድረስ በሰው ጭንቅላትና የሰውን በማድነቅ ብቻ ይኖራል?

እንደዚህ የሚኖር ሰው ባዶ ኮራጂ ቀላዋጭ ቢባል ባዩ ልክ አይደለም ተብሎ ይወቀሳል?

እንሰት በኮፒ ፔስት ዋርካን ስታጥናት አንድም ቀን ሰው በሰው ጭንቅላት ብቻ የሚኖር ብሎ ይታዘበኛል ብለኽ ታውቃለኽ?ካወቅክ መቼ ነበር ያልከው?ከቻልክ አመተ ምህረቱን,ወሩን,ቀኑን,ሰአቱን,ደቂቃውንና ሴኮንዶቹን ብትነግረን.......ቀን ከሆነ አየሩ እንዴት ነበር?ጸሀይዋ በየት በኩል ነበር የዛን ጊዜ የወጣችው?ጸሀይዋ ተንቀልቅላ ነበር ወይስ ጀዝባ?ዊንተር ከነበረም በረዶው የቆሙ መኪናዎችን ሸፍኖ ነበር?ሲሸፍናቸው ባለቤታቸው ምን ተሰማው?አንተስ የዛ ጊዜ የለበስከው ካቦርታ ከየት አለም የተሰራ ነበር?ማርኩ እውቅ ማርክ ነበር?ወቅቱ የቶርኔዶ ወቅት ከነበር ልክ ንፋሱ ምድርን እየጠረጋት ወዳንተ ሲመጣ ሀው ወዝ ዩር ፊሊንግ?

ሌላው ጥያቄዬ አንድም ቀን የራስህን ሳትጽፍ የሰዎችን እንደ ዋርካው ሌላኛው ከብታችን እንደ አለማየሁ ዋርካን በኮፒ ፔስት ስታጥለቀልቃት ጎርጉረኽ ስበህ ያመጣኽላቸው ሰዎች ኮፒ ፔስት ስላደረክላቸው ይከፍሉሀል?ከከፈሉህ ስንት ከፈሉህ?ብሩን ምን አደረክበት?በኤርትራ ገንዘብ በናቅፋ ሲመነዘር ስንት ይመጣል?ለሰራህበት የቀን ስራ ከፋዮችህ ሲከፍሉህ ገንዘቡን ሰው ይሰርቀኛል ብለኽ አልፈራኽም?

ለምሳለ እንደዚህ ያለ ሩምን ከፍተኽ በየድረገጹ እየፈጋህ የምትለጥፍልንን ካንተ ቀድሞ ሰው የሚያውቀውና ያንን ድረገጽ ያላነበበው ይመስልኻል?እንዲሁም ዋቢ ጠቅሰህ ስለመጽሀፎች የምታስተዋውቀን ምን አልባት ሰው ኦሪጅናል መጽሀፎቹን ገዝቶት እቤቱ ሊኖሩ ስለሚችሉ ሰውን ለማሰልቸት ከመቸኮልህ በፊት ይኸንን መጽሀፍ ወይም እዚህ ድረገጽን ታውቃላችሁ ወይ ብለኽ የማትጠይቀው ሳይቀድሙኝ ልቅደም በማለት ከራስኽ ጋር እሽቅድምድም ለመግባት አስበኽ ነው ወይስ የሰው ልጅ የተደጋገመ ነገር ይወዳል ብለው የታመሙ አስተማሪ አስተምረውኽ ነው?ካስተማሩህ እኚህ አስተማሪ ስማቸው ማን ይባላል?የተወለዱት የትና በስንት አመተምህረት ነው?ሰውየው ሲጋራ ያጬሳሉ?በሙቀት ጊዜ አብዝተው ውሀ ይጠጣሉ?ከጠጡስ ሀይላንድ ነው ወይስ አምቦውሀ ነው የሚጠጡት?መጠጥ መግዣ ገንዘብ ከየት አምጥተው ነው የሚገዙት?

ሌላው እራስህን ሆነህ ታይተህ ስለማታውቅ ሌላውን መሆን አይሰለችም?ባዶነት ተሰምቶህ ያውቃል?እራስህን ፈልገህ ታውቃለኽ?

በል ሌላም ጥያቄ ስለሚኖረኝ በክብርነታችን ሆነን እንመለሳለን ስንል ላንተ ኮፒ ፔስት እኔ ደከመኝ ስል ሰው እንዴት ምንም ትሁን ምን ያለ ፈጠራ እንዴት ከዚች አለምና ህብረተሰብ ጋር ተስማምቶ ይኖራል ብዬ ተገረምን እንጂ ይቀራል ብለን አንጠረጥርም::

ሾተል ነን......ስንሆን ዝም ብለን ሳይሆን የእንሰት ኮፒ ፔስት ታለንት እየገረመንም ጭምር ነው እንጂ ለሌላም አይደለም::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby እንሰት » Tue Jun 07, 2011 2:51 pm

ሰሞኑን ደግሞ ተድላ ላይ ተነስተህበታል:: አየህ ዋርካ ላይ ሁሉ ተሰድቦ ዝም አይልም ምናምንህንም ያውቃል:: በገሀዱ አለምም የሚደክመኝ ለአንድ ሰው አንድ ነገር ሰባቴ ስደግም ነው:: እኔ ልክ እንዳንተ አምባቸው ተብዬ ስላልወጣሁ በገሀዱ አለም የምሰራውን እዚህ ማምጣት አልችልም:: ስንቴ ልንገርህ? በዚህ ላይ ደግሞ ለዋርካ ስነጽሁፍ አይሆንም::

ከተናግሮ አናጋሪ ሰውረኝ ይባላል:: ተናግሮ ማናገር የጆሮ ጠቢዎች ስራ ነው:: እዚህ የምታስተዋውቅላቸው ስንት ከፈሉህ? ብለሀል:: በቃ አናትህ ላይ ገንዘብ ነው ያለው ማለት ነው? ወይ ጉ....ድ:: ማነግ ብሮ ለፍቅርም ተብሎ ይሰራል::

አሀ አንተ መለስ ዜናው ይከፍልሀል ማለት ነው? ኢሀዴግ ይከፍልሀል ማለት ነው? እዚህ መጥተህ የምታናፋው? እስኪ እባክህ ወርቅ የተጫነች አህያ የማትከፍተው በር የለምና ለኔም ስራውን ፈልግልኝ::

በቃ ካልከፈሉህ ሙልጭ አድርገህ መሳደብ ነው ግንቦት ሰባቶች ፓልቶኮች እዚህ የሚሰደቡት በክፍያ ሳትስማሙ ቀርታችሁ ነው?

በድጋሚ ለመንገር እኔ ስለሌለኝ አንድ ነገር ሳገኝ እኔ ከተጠቅምሁ በሁዋላ ሌላ ሰው በቀላሉ ቢያገኘው ቢጠቀምበት ብሎ ማስተዋወቅ ምን ክፋት አለው?

እስኪ አንተ የአለም ቁጥር አንድ ንፉግ ካነበብከው ወይም ተውሰህ ካስቀረሀቸው ኢንተርቪው አድርጌያለሁ ካልካቸው ሰዎች እስኪ ዋርካ ላይ አምጥተህ ያስተዋወከው ነገር አለ? የለም::

አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እስኪ ግርም ስላለኝ ነው ነኝ የምትለው ባህሪህና ያደረከው ነገር አልገጣጠም ስላለኝ ነው:: To give you the benefit of doubt ደግሞ ምክንያቱ ምን እንደነበረ ሰለማላውቅ ነው:: ጥያቄውን እንካ

እዚህ ዋርካ ላይ ማራቶን ግማሽ ማራቶን እሮጣለሁ ሮጬም ዋንጫ ሜዳሊያ አግበስብሻለሁ ሪከርዴም የአለም ሬከርድ ውስጥ ነው ብለህ አቅራርተህብን ነበር:: ምነዋ ታዲያ ሀይሌ ኦስትሪያ ሲመጣ ሳትወዳደር ቀረህ? ፈራህ? ሀይሌ ያሩዋሩዋጭ ያለህ ሲል ምነው እኔ ገብቼ ባሩዋሩጠው የተሻለ ሰአት ያስመዘግባል ብለህ ያው ንፉግነትህ ተነስቶ ቀረህ? መቸም የመወዳደሪያ ገንዘብ መክፈል አቃተኝ እንደማትል ነው:: ከራስህ ባትከፍል ስፖንሰር ባታገኝ የሪሳይክል ቆርቆሮ ጠርሙስም ተሰብስቦ ተሸጦ መመዝገብ ይቻል ነበር:: ሙት እልሀለሁ እኛም ዋርካውያን ቢያንስ አስር እና ሀያ ኦይሮ አናጣልህም ነበር? መቸም ሸቅል ነበረኝ ብትል እስቅብሀልሁ ምክንያቱም የለቱ ለት ሀይሌን በሆነ ጥቁር ቆመጥ ልትመታ ስትሮጥ ፖሊስ እንዳነቅህ አይቻለሁ:: እስኪ ምክንያትህን ዱቅ አድርጋት

ሾተል wrote:ሰላም እንሰት::እንደምን አላችሁልን?እኛ ደህና ነን ስንል ሰሞኑን ገጠር ሄደን ላሞችና ጥጆችን ጎብኝተን ለዛውም ሁለት ደስ የሚሉ ከብቶች በምላሳቸው ፊታችንንና ጭንቅላታችንን ላስ ላስ ሲያደርጉልን ደስ ብሎን የጎረቤታችን የእነ እንትና ላሞችና በሬዎች ትዝ አሉን::

ልጅ እያለን የሰፈር ውሪዎች ተሰብስበን ስንጫወት በጣም ለማዳ የነበሩ ከብቶች ከሁዋላችን እየመጡ ይታገሉን ነበር::ታድያ የእኔን ጸጉር ትላስ የእኔን እያልን እንጣላ ነበር::ታድያ ሳይታሰብ ገጠር ብንሄድ ልጅነታችንን የሚያስታውሰን ድርጊት አጋጥሞን ደስ ብሎን በዛውም ትኩስ ወድያው የታለበ ወተት እንደጉድ ስንቀመቅም ሰንብተን ደረታችን አብጦ ከች በማለት እዚህ ቤት ለመግባት በቃን::

ታድያ እዚህ ቤት ዘው ያልንበት ጉዳይ እንደሚከተለው ነው::

እነሆ ፍሬ ነገሩ ሁል ጊዜ እንሰትን ስናየው ሁለዜ ወይም ኦልወይስ ወይም ኤቭርይ ታይም ወይም ኮንቲኒየስልይ ወዘተ ኢቲሲ እንሰት ሾተል ከሚሉት የዋርካ ባለጌ ተሳዳቢ ጋር ከተመላለሳቸው አንዳንድ አረፍተ ነገሮች ውጪ እንሰት አንድም ቀን ከራሱ ጽፎ ለዋርካ ያስነበበው ነገር የለም ነገር ግን የሰዎችን ጽሁፍና ድረገጽ ኮፒ ፔስት በማድረግ በጣም የታወቀ ስለሆነ ይቀራል ብለን አንጠረጥርም::

ታድያ እንሰትን የምጠይቀው ጥያቄ ሁልጊዜ የራሱን ሳይጨምር የሰውን ስራ ብቻ እየተከታተለ የሚያስተዋውቅ ሰው እውነተኛ የገሀዱ አለም ኑሮውም በኮፒ ፔስት የተሞላ ነው?ከሆነ እንዴት አንድ ሰውን የሚያክል ፍጡር እስከመቼ ድረስ በሰው ጭንቅላትና የሰውን በማድነቅ ብቻ ይኖራል?

እንደዚህ የሚኖር ሰው ባዶ ኮራጂ ቀላዋጭ ቢባል ባዩ ልክ አይደለም ተብሎ ይወቀሳል?

እንሰት በኮፒ ፔስት ዋርካን ስታጥናት አንድም ቀን ሰው በሰው ጭንቅላት ብቻ የሚኖር ብሎ ይታዘበኛል ብለኽ ታውቃለኽ?ካወቅክ መቼ ነበር ያልከው?ከቻልክ አመተ ምህረቱን,ወሩን,ቀኑን,ሰአቱን,ደቂቃውንና ሴኮንዶቹን ብትነግረን.......ቀን ከሆነ አየሩ እንዴት ነበር?ጸሀይዋ በየት በኩል ነበር የዛን ጊዜ የወጣችው?ጸሀይዋ ተንቀልቅላ ነበር ወይስ ጀዝባ?ዊንተር ከነበረም በረዶው የቆሙ መኪናዎችን ሸፍኖ ነበር?ሲሸፍናቸው ባለቤታቸው ምን ተሰማው?አንተስ የዛ ጊዜ የለበስከው ካቦርታ ከየት አለም የተሰራ ነበር?ማርኩ እውቅ ማርክ ነበር?ወቅቱ የቶርኔዶ ወቅት ከነበር ልክ ንፋሱ ምድርን እየጠረጋት ወዳንተ ሲመጣ ሀው ወዝ ዩር ፊሊንግ?

ሌላው ጥያቄዬ አንድም ቀን የራስህን ሳትጽፍ የሰዎችን እንደ ዋርካው ሌላኛው ከብታችን እንደ አለማየሁ ዋርካን በኮፒ ፔስት ስታጥለቀልቃት ጎርጉረኽ ስበህ ያመጣኽላቸው ሰዎች ኮፒ ፔስት ስላደረክላቸው ይከፍሉሀል?ከከፈሉህ ስንት ከፈሉህ?ብሩን ምን አደረክበት?በኤርትራ ገንዘብ በናቅፋ ሲመነዘር ስንት ይመጣል?ለሰራህበት የቀን ስራ ከፋዮችህ ሲከፍሉህ ገንዘቡን ሰው ይሰርቀኛል ብለኽ አልፈራኽም?

ለምሳለ እንደዚህ ያለ ሩምን ከፍተኽ በየድረገጹ እየፈጋህ የምትለጥፍልንን ካንተ ቀድሞ ሰው የሚያውቀውና ያንን ድረገጽ ያላነበበው ይመስልኻል?እንዲሁም ዋቢ ጠቅሰህ ስለመጽሀፎች የምታስተዋውቀን ምን አልባት ሰው ኦሪጅናል መጽሀፎቹን ገዝቶት እቤቱ ሊኖሩ ስለሚችሉ ሰውን ለማሰልቸት ከመቸኮልህ በፊት ይኸንን መጽሀፍ ወይም እዚህ ድረገጽን ታውቃላችሁ ወይ ብለኽ የማትጠይቀው ሳይቀድሙኝ ልቅደም በማለት ከራስኽ ጋር እሽቅድምድም ለመግባት አስበኽ ነው ወይስ የሰው ልጅ የተደጋገመ ነገር ይወዳል ብለው የታመሙ አስተማሪ አስተምረውኽ ነው?ካስተማሩህ እኚህ አስተማሪ ስማቸው ማን ይባላል?የተወለዱት የትና በስንት አመተምህረት ነው?ሰውየው ሲጋራ ያጬሳሉ?በሙቀት ጊዜ አብዝተው ውሀ ይጠጣሉ?ከጠጡስ ሀይላንድ ነው ወይስ አምቦውሀ ነው የሚጠጡት?መጠጥ መግዣ ገንዘብ ከየት አምጥተው ነው የሚገዙት?

ሌላው እራስህን ሆነህ ታይተህ ስለማታውቅ ሌላውን መሆን አይሰለችም?ባዶነት ተሰምቶህ ያውቃል?እራስህን ፈልገህ ታውቃለኽ?

በል ሌላም ጥያቄ ስለሚኖረኝ በክብርነታችን ሆነን እንመለሳለን ስንል ላንተ ኮፒ ፔስት እኔ ደከመኝ ስል ሰው እንዴት ምንም ትሁን ምን ያለ ፈጠራ እንዴት ከዚች አለምና ህብረተሰብ ጋር ተስማምቶ ይኖራል ብዬ ተገረምን እንጂ ይቀራል ብለን አንጠረጥርም::

ሾተል ነን......ስንሆን ዝም ብለን ሳይሆን የእንሰት ኮፒ ፔስት ታለንት እየገረመንም ጭምር ነው እንጂ ለሌላም አይደለም::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby የተሞናሞነው » Tue Jun 07, 2011 3:29 pm

አንተ ደነዝ አፈር ብላ...ሰው እኩል ነው ብዬ የማምን ብሆንም አንተ ግን የሰው ትንሽ ወራዳ መሆንህን ከልቤ ልንገርህ ልብ የለህምና ይሄም አይገባህም እንጂ::

በመጀመሪያ ደረጃ እንሰት እንዳንተ የብልግና ዌብሳይት ከፍቶ ኢትዮጵያዊነትን የሚያዋርድ ስብእናን የሚነካን ነገር የሚለጥፍ አይደለም...እሱ የሚጠቅምን ልንማርበት የምንችልን ነገር ነው መርጦ እዚህ ላይ እንካፈል ያለውና እያካፈለን ያለው....ለምሳሌ ብዙ ጊዜ ከራሱ የጥናት መስክ ጋር የማይያያዝን ነገር ፈልጎ አፈላልጎ ለማንበብ ጊዜ የሚያጥረው ብዙ ሰው አለ...ሲፈልጉትም አንዳንዴ አይገኝም...እሱ ግን ሲያነብ ጠቃሚ ነው ያለውን አምጥቶ አካፈለንና ሌሎቹንም እንዲያካፍሉ ይሄንን አደረገ.... እኛም ተጠቃሚ እየሆንንን ነው:: ለምሳሌ እዉነቱን ልንገርህና ከዚህ ውስጥ ተጠቃሚ ከሆኑት ውስጥ እኔ አንዱ ነኝ...ለራሴም አንብቤ ኢትዮጵያ ለሚገኝ የዩኒቨርስቲ አስተማሪ ወጣት ጓደኛየ ብዙ ነገር እየላክሁለት እሱም ተጠቃሚ ሆኖ ለተማሪወቹም እያካፈላቸው ይገኛል....አንተ ግን የዚህ ጥቅሙ አይገባህም....---- ነህና :lol:

ሌላው ጠቃሚ የሆነን ነገር መርጦ ማንበብ የራስ የሆነን ነገር ይጠይቃል....ብዙ ድረ-ገጾች ላይ እንዳንተ አይነት አላዋቂ መሃይማንም ችሎታ ሳይሆን እዩኝ እዩኝ ባይነት ተጠናውቷቸው ብዙ ፍሬ ፈርሲኪ ይጽፋሉና....እሱ ግን የሚጠቅመውን ደም ያለውን ልናገኛቸው አስቸጋሪ የሚሆኑብንን ብዙ ነገሮች ይሄንን ቤት ከፍቶ እንድናገኛቸውና ማንበብ ለምንፈልግ እንድናነብ እያደረገ ነው....የራሱ የሆነ ስነ-ጽሁፋዊ ውጤትም ሊኖረው ይችላል...እዚህ ላይ እያነበብነውም ይሆናል ግን የግድ እንዳንተ እወቁኝ እወቁኝ የሚል መሆን የለበትም:: የራስ መተማመን ያለው ሰው የግድ እንዳንተ አይነቱ መሃይም አወቀው አላወቀው ግድ አይሰጠውምና:: አሁን አንተን እንውሰድ እዚህ ላይ ምን የረባ ነገር ጽፈህልን ታውቃለህ :?: እውን አንድ ሰው የሆነ ጽሁፍ ሲጽፍ ወይም አስተያየት ሲሰጥ ያንን ተከትሎ እናቱን እያራከሱ በቃላት ድረታ የብልግና ስድብ መአት ማዋረድ ፈጠራ ነው እንዴ? ለዚህ ነው አንተን አህያ ---- ነህ የምልህ :lol:
ለእንሰት

እንሰት ወዳጄ ሆይ ይሄንን ቤትህን ከማንም በላይ እኔ ተጠቅሜበታለሁ ተጠቅሜም የስነ ጽሁፍ ጥማት ላለው ባለፈው አመት በአማርኛ ፎክሎር ኤንድ ሊትሬቸር ማስተርሱን በአመርቂ ውጤት ጨርሶ ባሁኑ ሰአት በአንድ ዩኒቨርሲቲ በማስተማር ላይ ለሚገኘው ጓደኛየ ብዙ ነገር ዳዉን ሎድ እያረግሁኝ አካፍዬዋለሁና በዚህ አጋጣሚ ይሄንን ቤት ከፍተህ ሌሎቹም እንዲያካፍሉ እያደረግህ ስላለህው ትልቅ አስተዋጽኦ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረስህ:: የኔን ዌብሳይትም ገና በጅምር ብትሆንም አንድ ቀን አንተ ወይም አንዱ ደርሶባት እዚህ ውስጥ እንደማያትና እንደምትነበብ የሚያሳድግ አስተያየትም እንደማገኝ ተስፋ አደርጋለሁ::

የተሞናሞነውሾተል wrote:ሰላም እንሰት::እንደምን አላችሁልን?እኛ ደህና ነን ስንል ሰሞኑን ገጠር ሄደን ላሞችና ጥጆችን ጎብኝተን ለዛውም ሁለት ደስ የሚሉ ከብቶች በምላሳቸው ፊታችንንና ጭንቅላታችንን ላስ ላስ ሲያደርጉልን ደስ ብሎን የጎረቤታችን የእነ እንትና ላሞችና በሬዎች ትዝ አሉን::

ልጅ እያለን የሰፈር ውሪዎች ተሰብስበን ስንጫወት በጣም ለማዳ የነበሩ ከብቶች ከሁዋላችን እየመጡ ይታገሉን ነበር::ታድያ የእኔን ጸጉር ትላስ የእኔን እያልን እንጣላ ነበር::ታድያ ሳይታሰብ ገጠር ብንሄድ ልጅነታችንን የሚያስታውሰን ድርጊት አጋጥሞን ደስ ብሎን በዛውም ትኩስ ወድያው የታለበ ወተት እንደጉድ ስንቀመቅም ሰንብተን ደረታችን አብጦ ከች በማለት እዚህ ቤት ለመግባት በቃን::

ታድያ እዚህ ቤት ዘው ያልንበት ጉዳይ እንደሚከተለው ነው::

እነሆ ፍሬ ነገሩ ሁል ጊዜ እንሰትን ስናየው ሁለዜ ወይም ኦልወይስ ወይም ኤቭርይ ታይም ወይም ኮንቲኒየስልይ ወዘተ ኢቲሲ እንሰት ሾተል ከሚሉት የዋርካ ባለጌ ተሳዳቢ ጋር ከተመላለሳቸው አንዳንድ አረፍተ ነገሮች ውጪ እንሰት አንድም ቀን ከራሱ ጽፎ ለዋርካ ያስነበበው ነገር የለም ነገር ግን የሰዎችን ጽሁፍና ድረገጽ ኮፒ ፔስት በማድረግ በጣም የታወቀ ስለሆነ ይቀራል ብለን አንጠረጥርም::

ታድያ እንሰትን የምጠይቀው ጥያቄ ሁልጊዜ የራሱን ሳይጨምር የሰውን ስራ ብቻ እየተከታተለ የሚያስተዋውቅ ሰው እውነተኛ የገሀዱ አለም ኑሮውም በኮፒ ፔስት የተሞላ ነው?ከሆነ እንዴት አንድ ሰውን የሚያክል ፍጡር እስከመቼ ድረስ በሰው ጭንቅላትና የሰውን በማድነቅ ብቻ ይኖራል?

እንደዚህ የሚኖር ሰው ባዶ ኮራጂ ቀላዋጭ ቢባል ባዩ ልክ አይደለም ተብሎ ይወቀሳል?

እንሰት በኮፒ ፔስት ዋርካን ስታጥናት አንድም ቀን ሰው በሰው ጭንቅላት ብቻ የሚኖር ብሎ ይታዘበኛል ብለኽ ታውቃለኽ?ካወቅክ መቼ ነበር ያልከው?ከቻልክ አመተ ምህረቱን,ወሩን,ቀኑን,ሰአቱን,ደቂቃውንና ሴኮንዶቹን ብትነግረን.......ቀን ከሆነ አየሩ እንዴት ነበር?ጸሀይዋ በየት በኩል ነበር የዛን ጊዜ የወጣችው?ጸሀይዋ ተንቀልቅላ ነበር ወይስ ጀዝባ?ዊንተር ከነበረም በረዶው የቆሙ መኪናዎችን ሸፍኖ ነበር?ሲሸፍናቸው ባለቤታቸው ምን ተሰማው?አንተስ የዛ ጊዜ የለበስከው ካቦርታ ከየት አለም የተሰራ ነበር?ማርኩ እውቅ ማርክ ነበር?ወቅቱ የቶርኔዶ ወቅት ከነበር ልክ ንፋሱ ምድርን እየጠረጋት ወዳንተ ሲመጣ ሀው ወዝ ዩር ፊሊንግ?

ሌላው ጥያቄዬ አንድም ቀን የራስህን ሳትጽፍ የሰዎችን እንደ ዋርካው ሌላኛው ከብታችን እንደ አለማየሁ ዋርካን በኮፒ ፔስት ስታጥለቀልቃት ጎርጉረኽ ስበህ ያመጣኽላቸው ሰዎች ኮፒ ፔስት ስላደረክላቸው ይከፍሉሀል?ከከፈሉህ ስንት ከፈሉህ?ብሩን ምን አደረክበት?በኤርትራ ገንዘብ በናቅፋ ሲመነዘር ስንት ይመጣል?ለሰራህበት የቀን ስራ ከፋዮችህ ሲከፍሉህ ገንዘቡን ሰው ይሰርቀኛል ብለኽ አልፈራኽም?

ለምሳለ እንደዚህ ያለ ሩምን ከፍተኽ በየድረገጹ እየፈጋህ የምትለጥፍልንን ካንተ ቀድሞ ሰው የሚያውቀውና ያንን ድረገጽ ያላነበበው ይመስልኻል?እንዲሁም ዋቢ ጠቅሰህ ስለመጽሀፎች የምታስተዋውቀን ምን አልባት ሰው ኦሪጅናል መጽሀፎቹን ገዝቶት እቤቱ ሊኖሩ ስለሚችሉ ሰውን ለማሰልቸት ከመቸኮልህ በፊት ይኸንን መጽሀፍ ወይም እዚህ ድረገጽን ታውቃላችሁ ወይ ብለኽ የማትጠይቀው ሳይቀድሙኝ ልቅደም በማለት ከራስኽ ጋር እሽቅድምድም ለመግባት አስበኽ ነው ወይስ የሰው ልጅ የተደጋገመ ነገር ይወዳል ብለው የታመሙ አስተማሪ አስተምረውኽ ነው?ካስተማሩህ እኚህ አስተማሪ ስማቸው ማን ይባላል?የተወለዱት የትና በስንት አመተምህረት ነው?ሰውየው ሲጋራ ያጬሳሉ?በሙቀት ጊዜ አብዝተው ውሀ ይጠጣሉ?ከጠጡስ ሀይላንድ ነው ወይስ አምቦውሀ ነው የሚጠጡት?መጠጥ መግዣ ገንዘብ ከየት አምጥተው ነው የሚገዙት?

ሌላው እራስህን ሆነህ ታይተህ ስለማታውቅ ሌላውን መሆን አይሰለችም?ባዶነት ተሰምቶህ ያውቃል?እራስህን ፈልገህ ታውቃለኽ?

በል ሌላም ጥያቄ ስለሚኖረኝ በክብርነታችን ሆነን እንመለሳለን ስንል ላንተ ኮፒ ፔስት እኔ ደከመኝ ስል ሰው እንዴት ምንም ትሁን ምን ያለ ፈጠራ እንዴት ከዚች አለምና ህብረተሰብ ጋር ተስማምቶ ይኖራል ብዬ ተገረምን እንጂ ይቀራል ብለን አንጠረጥርም::

ሾተል ነን......ስንሆን ዝም ብለን ሳይሆን የእንሰት ኮፒ ፔስት ታለንት እየገረመንም ጭምር ነው እንጂ ለሌላም አይደለም::
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests