የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ocean12 » Sun Nov 11, 2007 10:07 pm

ለጸጋዬ ወዳጆች
እና ለመልከጸዲቅ
የጸጋዬን እጆች እና ጭንቅላት የባረከ አምላክ ምስጋና ይግባው እያልን....
ይሄው በቃሌ መሰረት...ከእሳት ወይ አበባ መጽሀፉ
ዶጋሌን
http://www.freewebs.com/zelalemethiopia/Dogali.pdf
እረ ምናባቱ ሌላ አንድ ብመርቅህስ?..
ይህኛው ደግሞ መሄዴ ነውይላል
http://www.freewebs.com/zelalemethiopia/mehide%20new.pdf
በነዚህ እናዝግም እስኪ ነገ የሚያመጣውን ማን ያውቃል?... :)
Image
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sun Nov 11, 2007 11:01 pm

እንዲህ...ነው...እንጂ...ደግነት....ወዳጅ...ውቅያኖስ......
"በዶጋሊ:..ጀምረህ....በመሄድ....መኩነስነስ.......!!
ቤትህ...አማን:ይሁን.....በረካው:.....ይብዛልህ.....
ጎዳህ:ወርዱ:ይስፋ.....ማጀትህ.....ይሙላልህ....

እረ...አማን...በል....የቀልዴን...አይደለም! :lol: :lol: :lol:
የውነት:ምስጋናዬ:ይድረስ...... 8) 8)
ከማክበር:ጋር!!
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby እንሰት » Tue Nov 13, 2007 9:59 am

ocean12 እንዲህ አለ
“ ለጸጋዬ ወዳጆች
እና ለመልከጸዲቅ የጸጋዬን እጆች እና ጭንቅላት የባረከ አምላክ ምስጋና ይግባው እያልን ....
ይሄው በቃሌ መሰረት ...ከ “እሳት ወይ አበባ መጽሀፉ”
ዶጋሌን http://www.freewebs.com/zelalemethiopia/Dogali.pdf
እረ ምናባቱ ሌላ አንድ ብመርቅህስ ?.. ይህኛው ደግሞ መሄዴ ነው ይላል
http://www.freewebs.com/zelalemethiopia ... %20new.pdf
በነዚህ እናዝግም እስኪ ነገ የሚያመጣውን ማን ያውቃል ?... “

ማን ያውቃል?
የልቡ የደረሰው መልከጻዲቅ ምርቃቱን አፈሰሰው
መልከጻዲቅ wrote:እንዲህ...ነው...እንጂ...ደግነት....ወዳጅ...ውቅያኖስ......
"በዶጋሊ:..ጀምረህ....በመሄድ....መኩነስነስ.......!!
ቤትህ...አማን:ይሁን.....በረካው:.....ይብዛልህ.....
ጎዳህ:ወርዱ:ይስፋ.....ማጀትህ.....ይሙላልህ....
እረ...አማን...በል....የቀልዴን...አይደለም!
የውነት:ምስጋናዬ:ይድረስ......
ከማክበር:ጋር!!


የዋርካው ወዳጃችን ዋኖስ "ሽንት ይውጣልህ' ነበር ያለው::
በምዕራቡ አለም ልጅ መውለድ እና ማሳደግ እርግማን ቢሆንም የሚታዘዝ የልብ የሚያደርስ ልጅ ይውጣልህ ብያለሁ::
ዛሬ ለታዳሚዎች እና ለተሳታፊዎች የዲሲዋ አቦነሽ አድነው ከ”ኢትዮጵያ ኦርኬስትራ”(?) ጋር በመሆን ለስደተኞች ቀን መታሰቢያ ዝግጅት በኬኔዲ ማእከል ያቀረበችውን ይሆናል የምጋብዛችሁ 2004።ዝግጅቱ አንድ ሰአት ከአምስት ያህል ነው። ሰው ተጋበዙልኝ ብሎ የራሱን ግብዣ ባያናንቅም፣ በተለይ ዋናው የግብዣው ምክንያቴ ግን ከ13፡20 ደቂቃ ጀምሮ ያለውን እንድታዩት ነው።ለኔ የመሳሪያው ሙዚቃ (instrumental music they played) is quite impressive. አጃ ኢብ ያሰኛል። The band did a superb job. ለዚያውም እኛ በምናጣጥለው ማሲንቆ እና ክራር!!
እየበሉ እየጠጡ ዝም እየተጋበዙ ዝም የለም? እስቲ እናንተም አስተያየት ስጡበት።
ዋናው ማያያዣ አድራሻ ይህ ሲሆን
http://www.kennedy-center.org/programs/ ... d=ABONESH#
ድካማችሁን ለመቀነስ ሙሉ አድራሻው ይህ ነው።
http://www.kennedycenter.org/calendar/k ... _video.gif
መልካም መዝናናት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ለአሰተያየቶች መልስ

Postby እንሰት » Tue Nov 13, 2007 10:43 am

ocean12 wrote:እንደገና አሁንም በጣም አመሰግናለሁ.....
ግጥሞቹም ብቻ አይደሉም የድረ ገጽ አድራሻዎቹ በጣም ደስ የሚያሰኙ ናቸው....በተለይ brango ን ወድጀዋለሁ.
ስለሁሉም ጎንበስ ብያለሁ ለምስጋና.
ውቅያኖስ

ኧረረረረ አይገባም አይገባም
እጅ ነስቻለሁ

ዋኖስ እንዲህ ታዘበ
Post subject: ሕምምምም ..
ዕንሰት ልፋትሕን አደንቃለሁ ! ነገር ግን ልፋትሕንና የተጠቃሚዉን ቁጥር ስመለከት ግን ከንቱ ድካም ነዉ ! የማንበብ ባሕላችን እዚሕ ግባ ሊባል የማይችል ሥለኆነ ተሥፋ አስቆራጪ ሁናቴ ላይ ዕንዳትደርሥ እሰጋለሁ ! በርታ ! እጅግ ቆንጆ ሥራ ና ጥቆማ ነው !
ከመልካም አድናቆት ጋ

ልጅ ዋኖስ
ከሁሉ በፊት ምስጋናዬ ይድረስህ። እዚህ ዋርካ ላይ ስሣተፍ እንደምታየኝ እኔ የፈጠራ ሰው አይደለሁም በስሜ የተዘገበች አንዲትም ግጥም ወይም ስድ ንባብ የለችም ስለዚህ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ውስጥ አልገባም። አይዞን
ሌላው አንተ እንዳልከው እዚህም ውጭ ያለነው ሃገር ቤትም ፊደል የቆጠርነው ንባብ ላይ ሲመጣ ወገቤን እንላለን። ብዙ ደራሲዎች ከፍ ካለ 5000 ቅጂ ነው አሳተምን ሲሉ የምሰማው። በአንጻሩ ግን አንዳንድ እድለኞች እንደ ‘ፍቅር እስከ መቃብር’፣ ከ ‘ቡስካ በስተጀርባ’፤ ‘የቃየን መስዋእት’ ‘ቃል ኪዳን’ ‘ሰመመን’ ከሁለት እስከ ሰባት ስምንት ጊዜ የመታተም እድል ደርሷቸዋል። ምናልባት masterpiece ስለሆኑ ይሆናል።
ሌላው ነገር እኔን በተመለከተ ለሰው መልስ የሰጠሁት ካልሆነ እዚህ የማቀርባቸው ጉዳዮች መጀመሪያ ለራሴ ስል አደርጋቸውና፤ ልፋቴን ድካሜን ሳየው ምናልባት እንደኔ በዚህ ጉዳይ የሚታትሩ ካሉ ምናለ ብካፈለው በዚያውም የወገኖቼን ድካም ልቀንስ ብዬ እክትባቸዋለሁ። ሰው ቢጠቀም ቢያነበው አንተ እንዳልከው ደስ ይለኛል። ካልሆነም መቸስ ማል ጎደኒ ፈርሶ መስከረሚ.. እያልን በፊናችን መንጎድ ነው

መሰማማት
ዋኖስ እንደጻፈ(ች)ው:
ዕንሰት ልፋትሕን አደንቃለሁ ! ነገር ግን ልፋትሕንና የተጠቃሚዉን ቁጥር ስመለከት ግን ከንቱ ድካም ነዉ ! ከመልካም አድናቆት ጋበፍጹም በፍጹም ከንቱ ድካም አይደለም ::አንድ ሰው እንኳን ቢያየው በጣም ጥሩ አስተዋጽኦ ነው ::እኔ እንደአዋጅ ነጋሪ ነኝ :ደስ የሚል ነገር ካየሁ በኢሜል ላማውቀው ሁሉ ነው የማዳርሰው :: እንሰት ተባረክ /ኪ (ኸረ ጾታ ይገለጽልን ):: ቆንጆ ስራ ነው ::መለስ ዙፋን ሲለቅ እንሰት ለፕርይምሚንስተርነት !!

አሜን አሜን በረከቱ ላንተም ይድረስ።
ጾታ - ለጊዜው እንደ ”ወንድ” የሚከጅለው ተብሎ ይመዝገብልኝ።
ጽድቁ ቀርቶ በውሉ በኮነነኝ ይባል የለ:: ጠ/ሚነት? ሆ ሆ ምን እሰራበታለሁ ብለህ ነው? ባይሆን ወደ ባህሉ ወደ ትምህርቱ ገፋ ገፋ አድርገኝ::
መልከጻዲቅ
ሰላም :እንሰት
በጸጋዬ :ገ /መድህን :መጽሀፍ :አንጻር :የተጀመረው :ጉዞ :ቀጥሏል .... ስለአትላሱ :የሰጠሀው :ግልጽና :ዝርዝር :ማብራሪያ :በራሱ :ጠቃሚ :
ትምህርት :አለው :: እኔ :አንድ :ነገር :አውቄአለሁ .....
ምስጋናዬ :ይድረስ .....
ከማክበር :ጋር !!!

ምስጋናዬም አክብሮቴም አብዝቶ ይድረስህ። በተሳታፊነት እንስንብት።
[color]ምናለ የጸጋዬ ፍቅር ካለህ እዚህ ዋርካና ስነጽሁፍ አንድ የውይይት መድረክ ክፈትና ብታሳትፈን። ከጸጋዬ ስራዎችን እና ህይወት ብዙ እንማማራለን።

ocean12
መልከጻዲቅ ምናልባት ትወደው ይሆናል በማለት ይህንን ከጸጋዬ ገብረ መድህን እሳት ወይ አበባ መሸ ደግሞ አምባ ልውጣን ጀባ ብያለሁ
http://www.freewebs.com/zelalemethiopia/Pdf%20files.pdf
ያለውን የወረወረ አይነት ነገር ነው ....እስኪ ያቆየንና ሌላም የምወረውረው አላጣም ::
እንሰት ለግጥሞቹ ዝጌር አብዝቶ ይስጥልኝ
ሰላም ሰንበት
[/b]
አሜን አብሮ ይስጥልኝ!!!
ቸር እንሰብት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ድረ ገጽ ላይ ይህም ይገኛል

Postby እንሰት » Thu Nov 15, 2007 12:09 am

አሁን እንቅስቃሴው ይቀጥል አይቀጥል በትክክል አይታወቅም እንጂ ድረ ገጽ ላይ ይህም ይገኛል
"የሚሸጡ ልጆች
"
ልጆች ወልደዋል? ደሃ ነዎት? ታዲያ ለምን አይሸጧቸውም? እውነቴን’ኮ ነው። በተለይ ቀላ ብለው ድንቡሽቡሽ ያሉ ከሆኑ የደራ ገበያ አለ። የኔ ነገር ወሬውን አጋጨሁት መሰለኝ። ልጅ የሚያሸጥ ድህነት ላይ ከተደረሰ ልጁ ድንቡሼ ሊሆን እንደማይቻል ዘነጋሁት። ሰው ኑሮውን ነዋ የሚመስለው። ክፋቱ ደግሞ ዝንብ የወረረውና የሽሮ ቅል የመሰለ ልጅ ለገበያ አይመችም። ቆንጆም ቢሆን ጥቁር ከሆነ አይድከሙ። እርሶስ ቢሆን በግ እንኳን ሲገዙ ምን ቢሰባ ጥቁር ከሆነ ገሸሽ ያደርጉት የለ። እውነቴን’ኮ ነው የጥቁር በግ ዋጋ’ኮ ይቀንሳል። ስለዚህ ጥቁር ከወለዱ ተስፋ ይቁረጡ። ጥቁር ልጅ ፈጽሞ አይፈለግም። ጥቁር ዋጋ አያወጣም። ጥቁር ልጅ ተፈለገ ከተባለ መጠርጠር ነው። ከጀርባው መከራ አለ። የጦርነት፣ የረሃብ፣ የበሽታ (የፖሊዮ)፣ የልመና፣ … ማሳያ ከመሆን አያልፍም። በዚህ ረገድ ‘ዋጋ’ ያወጣል። ቢፈልጉ “ኒውስዊክ”፣ ቢያሻዎ “ዋሽንግተን ፖስት” ካሰኞትም “ታይም” መጽሔት ‘ይገዛዎታል’። በዚህ አይጠራጠሩ። በተለይ እግሩ የተቆረጠ፣ ዓይኑ የተገለበጠ፣ ሆዱ ያበጠና ፀጉሩ የተላላጠ ከሆነ ጥሩ ማሳያ ስለሚሆን “ይፈለጋል!!!”። ነጭ ድንቡሼ ሕፃን ከነዚህ ክፉ ነገሮች ጀርባ ተቀርጾ ማየት መጥፎ ሟርት አይመስሎትም?ቀጠሮ በሥነ-ቃል ሲገለጽ
ለቀጠሮ ደንታ ቢስ መሆን የኢትዮጵያዊነት መለያ!?
በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር
************************************
ስለቀጠሮ አንድ ሺ አንድ ጊዜ ብዙ ቢባልም፣ እኔም ለአንድ ሺ ሁለተኛ ጊዜ ትንሽ ልበል። ስለምን? አሁን ያለነው በአዲሱ ዓመት አናት ላይ ነውና “ካምናው ዘንድሮ ባሰበት” አይነት ትችት እንዳይገጥመን፣ “ከርሞ ጥጃ” በሚል እንዳንወቀስና “የሰው ቀጠሮ ቀርጥፎ የሚበላ” ተብለን በሰው አፍ እንዳንገባ ትምህርት ይሆነን ዘንድ ማንሳቱ አስፈላጊ ስለሆነ ነው።
በአዲሱ ዓመት አናት ላይ ቂብ ተብሎ ወይም አሮጌ ዓመት ዳርቻ ላይ ተሆኖ ወደፊት ይተገበራሉ የምንላቸውን ቁምነሮች እቅድ መልክ መንደፍ የተለመደ ነገር ነው። እቅድ በራሱ ወደፊት ሊፈፀም ይችል ዘንድ በቀጠሮዎች የተያዘ ነገር (ቀጠሮ) ነውና። ስለዚህ ስለቀጠሮ ትንሽ ቢባል የሚያስከፋ አይሆንም።
አስር ደቂቃ ምንም አይደለም። ሃያ ደቂቃም እንዲሁ። ኧረ! ሰላሳ ደቂቃም ቢሆን ለሚወዱት ሰው ተገትረው ቢውሉ ከቁም ነገር የሚጣፍ አይሆንም። ኤዲያ ሰላሳ ደቂቃስ ምን አላት? አንድና ሁለት ሰዓትስ ቢሆን ቀጠሮ ቦታ መገተር ከባሰብን መጐለት ለእኛ አዲሳችን ነው እንዴ?! ድንቄም እቴ! “ይሉትን በሰማሽ፣ ገበያም ባሎጣሽ” አለች ስንዴነሽ። እኛ እኮ ምርጥ አበሻ፣ ጥሩ ኢትዮጵያዊያን እኮ ነን። ማንም ሳይሾመን እራሳችንን ጊዜን አንቀው ከሚገድሉ ጐራ የመደብን አይደለንም እንዴ!? ቀጠሮ ያላከበረ፣ በቀጠሮ ሰዓት ያልተገኘ ሰው ሲገጥመን ምንድን ነው የምንለው? “ድሮስ አበሻ” አይደል? ግን … ግን … ግን “ጊዜ ወርቅ ነው” ተብሎ እንደጥቅስ በሚነበነብበት፣ “… ጊዜ ታክሲ አይደለም፣ አይጠብቅም ቆሞ” … እና መሰል ግጥሞች ስለጊዜ ክቡርነት በሚነገሩበት አገር፣ የሰው በቀጠሮ አለመገኘትና ሰዓት አለማክበር ማርፈድ የኢትዮጵያዊነት ምልክት ተደርጐ መወሰዱ ለምን ይሆን?
ይህ ደግሞ የኛ መገለጫ የኢትዮጵያዊነት መለያ ስላለመሆኑ ዋቢነት ፍለጋ እሩቅ መማሰኑ፣ ጉልበት ማባከኑ አስፈላጊ አይሆንም። ከዚሁ ከቅርቡ ጽሕፈት ትናንትና ከመምጣቱ በፊት በቃል ሲነገሩና እየተነገሩ ያሉትን ሥነ-ቃሎች መመልከቱ ይበቃል። ጊዜና ቦታ የሚገድበን ስለሆነና ነገሩን ሳናሰፋ፣ ጥላሁን ገሠሠ በአንድ የሙዚቃ ካሴቱ ላይ ቀጠሮን ያለማክበር ምች ያጠናገራቸውን ሰዎች፣
“… አርቆ ማሰቢያ እያለው አዕምሮ፣
ሰው እንዴት ይሳነው ለማክበር ቀጠሮ …”
በማለት የነቀፈበትን ባለሁለት ስንኝ ግጥም መንደርደሪያ አድርገን በዚሁ ጉዳይ ላይ ስለተነገሩ በጣም ጥቂት ሥነ-ቃሎች ትንሽ እንበል።
“ጊዜ አለው ለሰው፣ ዕድሜ ካላነሰው” የሚለውን ብሂል መሰረት ያደረጉ አባቶቻችን “ከቶ አይቀርም ሞቱ፣ ምንም ቢዋትቱ” ከሚለው የሞትን አይቀሬነት ከሚያስረዳ መንታ ግጥማቸው ባሻገር፣
“አያሳስትም ሰዓት፣
ቀጠሮ ያከብራል ሞት።”
በማለት ጊዜውን ጠብቆ የሚመጣ፣ ቀጠሮ አክባሪው ሞት ነው ሲሉ የሞትን አይቀሬነት ገልፀዋል። እዚህ ላይ ስለቀጠሮ ምንነት ልብ ይሏል።
ስለሞት በዚህ እናቁምና ከቀጠሮ አከባበር ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አንድ አራት መንታ የፍቅር ሥነ-ቃል ግጥሞችን እንመልከት።
“በኋላ ከሰዓት፣ ነገ፣ ከነገ በስቲያ ነይና ፍቅራችንን እንገላለጽ፣ እናጣጥም” እያለ ቢመክራት፣ ቢዘክራት የከንፈር ወዳጁ፣ “እንቢኝ አሻፈረኝ” ያለችው ወጣት አፍቃሪ ቀጠሮው አለመከበሩ ቢቆጨውና ቢያሳዝነው፣
“ነይ ስልሽ ጊዜ አትመጪም ወይ፣
ሎሚ ለሽታ አይደለም ወይ?”
በማለት ለምን እንደፈለጋትና ፍቅረኛሞች ተቃጥረው ምን እንደሚያደርጉ ለመግለጽ ሞክሯል።
“ቀጣፊን ያመነ፣ ጉምን የዘገነ” እንዲሉ አበው፣ ዘወትር እየቀጠረችው በቀጠሮው ቦታና ሰዓት ከዓይኑ የገባችው ልጃገረድ አለመገኘቷ ያበሸቀውና የነደደው አንድ ወጣት ብስጭት በተሞላበት መንታ ግጥም፣
“አንቺም ሰው ሆንሽና ሰው ቀጥሮ መጥፋት፣
ደባደቦ ምንጭር አክንባሎ ፊት”
ሲል ንቀት በታከለበት ውረፋ ወርፏታል።
የሚገናኙበትን ሰዓትና ቦታ ልቅም አድርጐ ነግሯት፣ እመጣለሁ ብላ በምላስ ደልላ የቀረችበት ወጣት፣
“ከቤትሽ በስቲያ ተኮረብታው ላይ
እመጣለሁ ብለሽ መቅረትሽ ነወይ?”
ወደ እንስቲቱ መለስ እንበልና ደግሞ፣ የሚወደውን ታቦት አስጠርታ፣ “እዛ እምንገናኝበት ቦታ በይህን ያህል ሰዓት አደራ እንዳትቀር” ብላ አጥብቃ ነግራው፣ ወዳጇ ግን ቀጠሮውን ነገሬ ሳይል ዘንግቶ ቢቀርባት፣
“በአቦ በሚኻኤል ምሎ ተገዝቶ፣
ሰው እንዴት ይቀራል ቀጠሮ ዘንግቶ”
በማለት የባልንጀራዋን ልበቢስነት አስረግጣ ተናግራለች።
ሌላው ደግሞ “ውዴ፣ ፍቅሬ፣ …” የሚላትን “የእኔ የዓለም ቆንጆ …” እያለ እየቀጠረ በረባ ባልረባው ምክንያት አልገኝ ብትለውና በቀጠሮው ስፍራ እያመላለሰች መከራውን ብታሳየው፣
“በሽታየ አንቺው ነሽ በሽታም የለብኝ
እመጣለሁ እያልሽ እየቀረሽብኝ”
ሲል በማንጐራጐር የፍቅር ሕመሙ እንደጠናበት ለማሳየት ሞክሯል።
ከላይ በተለያዩ ጥቂት ሥነ-ቃሎች አባቶቻችን ለጊዜ ክቡርነት ምን ያህል እንደሚጨነቁ፣ ለቀጠሮ ክቡርነት ምን ያህል እንደሚጠበቡ ከብዙ በትንሹ ለማሳየት ተሞክሯል። እናም አሁን የያዝነውን አጉል እምነት አሽቀንጥረን ጥለን፣ “የጊዜን ክቡርነት የተረዳው ፈረንጅ ብቻ ነው” የሚለውን ተራ ዲስኩር እንደአሮጌው ዓመት ወደኋላ ትተን “ለጊዜ ዋጋ እንስጥ!”፣ “ለቀጠሮ ዋጋ እንስጥ!” የአዲሱ ዓመት መፈክራችንም ይሁን።
ጠብቄሽ ነበረ
መንፈሴን አንጽቼ
ገላዬን አጥርቼ
አበባ አሳብቤ
አዱኛ ሰብስቤ
ጠብቄሽ ነበረ
ብትቀሪ ጊዜ
መንፈሴን አሳደፍኩ
ገላዬን አጐደፍኩ
አበባው ደረቀ
አዱኛው አለቀ
ብትቀሪ ጊዜ
የጣልኩብሽ ተስፋ
እኔን ይዞ ጠፋ
------------------------------------------------
{‘ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ’ - ደበበ ሰይፉ}
የተወሰደ

ንጋት በያሬድ ክንፈ የሚዘጋጅ የድረ ገጽ ጋዜጣ ይመስለኛል
ለማንኛውም እነዚህን ማያያዣዎች ተመልከቱ
http://www.geocities.com/nigatyka/page_main.htm
http://www.geocities.com/nigatyka/social_006.htm
http://www.geocities.com/nigatyka/art_005.htm
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Fri Nov 16, 2007 4:36 am

እንሰት:እንዲህ:አሰበና:ጻፈ....ች......
[b][code]ምስጋናዬም አክብሮቴም አብዝቶ ይድረስህ። በተሳታፊነት እንስንብት።
[color]ምናለ የጸጋዬ ፍቅር ካለህ እዚህ ዋርካና ስነጽሁፍ አንድ የውይይት መድረክ ክፈትና ብታሳትፈን። ከጸጋዬ ስራዎችን እና ህይወት ብዙ እንማማራለን


ሰላም:ሰላም:የዋርካ:ወዳጆቼ.... :D :D
እንደምን:አላችሁልኝ:በአያሌው.. :?: መቸም:ይሄ:ቤት
:ይናፍቃል...ትናፍቃላችሁ... :wink: :wink: ያልምድልህ:
አትሉኝም :?: እንሰት:ምስጋናዬ:ከፍተኛ:ነው:ስለቀረበው:
ሀሳብ :idea: :idea: እንግዲህ:ያንተ(ቺ)ና:የወዳጄ:
ውቅያኖሱም:አስተዋጽኦ:ተጨምሮበት:በጸጋዬ:ግጥሞች:ዙሪያ:
አንድ:ትንሽ:ጎጆ:መቀለስ:ይቻላል...ማን:ይፈራል:ሞት :?: ቀስ:እያልን:ደግሞ:እናሰፋውና:Town-house:አድርገነው:
ጎዛችንን:አንቀርቅብን:መግባት:ነው 8) 8)
ታዲያ:መቸም:ቤተኞች:መሆናችን:እየታየ:ነውና:ለዚህ:
ይጠቅማል:ያልኩትን:ጥያቄ:ላነሳ:ነው;....እንሰት:
መስማማት:ለጠየቀው:ጥያቄ:የተሰጠው:መልስ: ቡሬ:ነው..
ሽፍንፍን.......... :wink: :wink: "......ለጊዜው:እንደወንድ:የሚከጅለው:
ተብሎ:ይነበብልኝ........." የሚለው:ማብራሪያ:ይፈልጋል 8)
ግድየለም:ይተንተን!!!
በተረፈ:እንግዲህ:የጸጋዬን:ጉዳይ: እኔም:ችላ:አልልም :!: እናንተም:እንግዲህ:አሰሳችሁን:ቀጥሉ :!:
የቤተ-ዘመዱ:ይታያል...ጉዱ...አደለ...የሚባለው...!
በሉ:በደረቁ:ከመጨቅጭቅ:ሙዚቃ:ልበላ.... :!:
ኩኩዬ:ትዝታዋን:እንግዲህ:ገለጸች.... :arrow:
http://www.youtube.com/watch?v=ayHlSNUYRPg
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby እንሰት » Fri Nov 16, 2007 9:43 am

መልከጻዲቅ wrote:...ምናለ የጸጋዬ ፍቅር ካለህ እዚህ ዋርካና ስነጽሁፍ አንድ የውይይት መድረክ ክፈትና ብታሳትፈን። ከጸጋዬ ስራዎችን እና ህይወት ብዙ እንማማራለን
...:ምስጋናዬ:ከፍተኛ:ነው:ስለቀረበው:
ሀሳብ :idea: :idea: እንግዲህ:ያንተ(ቺ)ና:የወዳጄ:
ውቅያኖሱም:አስተዋጽኦ:ተጨምሮበት:በጸጋዬ:ግጥሞች:ዙሪያ:
አንድ:ትንሽ:ጎጆ:መቀለስ:ይቻላል...ማን:ይፈራል:ሞት :?: ቀስ:እያልን:ደግሞ:እናሰፋውና:Town-house:አድርገነው:
ጎዛችንን:አንቀርቅብን:መግባት:ነው


ሰላምህ ይብዛ! ጀምረውና ቤት ለእምቦሳ እንላለን::

የቤተ-ዘመዱ:ይታያል...ጉዱ...አደለ...የሚባለው...!
በሉ:በደረቁ:ከመጨቅጭቅ:ሙዚቃ:ልበላ.... :!:
ኩኩዬ:ትዝታዋን:እንግዲህ:ገለጸች.... :arrow:
http://www.youtube.com/watch?v=ayHlSNUYRPg


እኔም እንዲህ ሰማሁዋት
“በጉንጮቼ ወለል ሲፈስ የሚታየው
እባክህ አስረዳኝ
ዝናብ ነው? እንባ ነው ?” ስትል
እኔ ደግሞ ይቺን እወድላታለሁ “የኔስ ለብቻው ነው”
ስትል
http://www.youtube.com/watch?v=svUZlHXr ... re=related

አብዬ መልከ ጻዲቅ ቤት ለእንግዳ ብለናል። ምነው በጠራራው ጸሃይ መጣህ? እስኪ አረፍ በል። አንተ መቸም የምትወደው ጸጋዬን ነውና። እስኪ ትንሽ አነባ..በ..ው
ስለ ጸጋዬ ከድረ- ገጽ ያነበብኩትን ከ ‘እናት አለም ጠኑ’ እንዲህ ይላል

ቲያትሩ ሲጀመር ጀግናው በላይ ዘለቀ ተገርፎ ይሰቀላል። በላይም ተራግሞ እንደሞተ...አውቆ አበዷ አዴ ውቃው (አስናቀች ወርቁ (ነበረች የተጫወተችው) ክራሯን እየገረፈች እንዲህ ብላ ትዘፍናለች...
የጣሊያን ባንዲራ ይላል ዱቼ ዱቼ
ይላል ዱቼ ዱቸ
አርኩ አንዳሬ ቪያ ኢዮ ማሬቶ ቼ።
ኢዮ ማሬቶ ቼ... (ክራሯን ትገርፋለች።)
አሞራ በረረ ጣሌ ድል ተመታ
ባንዳ ተደራጀ አርበኛ ተፈታ


ጸጋዬ ይናገረዋል ነው የሚባለው። አይደል? የአርበኛ መበደል በዛ አይደል እንደዚያ ለአገሩ ተርቦ ተጎሳቁሎ ሞቶ ኧረ ስንቱ? ምን ያልተሰራው አለ
አርበኛው ሴቲቱ ብትበድለው

“አርኩም ይሄድና ሶልዲውም ያልቅና
ያስተዛዝበናል ይሄ ቀን ያልፍና”


ቢያስተዛዝንም
አዪዪ ጉድ ሆንክ ብላ
እንደ ልቧ አዴ ውቃው ተወው አርኩም ሄዶ አኪርህ አልቆመም ብላ አርበኛው የሆነውን አንጎራጎረቻ

“አሞራ በረረ ጣሌ ድል ተመታ
ባንዳ ተደራጀ አርበኛ ተፈታ”


ሲያዝን! ምስኪን::
ከነጻነት መመለስም በኋላ ባንዳው ተደራጅቶ ማጁም አቅፈውት ባንዳው ስልጣን መያዝ ሲጀምር እና እነ “በላይ” ሲስቀሉ
ነገሩ ሁሉ የፈናጅራ ሲሆን ዝነኛው ባለቅኔ, አስተማሪ የኔታ ዮፍታሔ ንጉሴ እንዲህ ተቀኘ አሉ::

ኢትዮጵያ ሃገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ”


አሁን ትንሽ አረፍክ መልኬ ህ......ም......ም ምንድን ነበር ያልከኝ

ጥያቄ:ላነሳ:ነው;....እንሰት:
መስማማት:ለጠየቀው:ጥያቄ:የተሰጠው:መልስ: ቡሬ:ነው..
ሽፍንፍን..........


እውን ሽፍንፍን ነው:: በኔ እምነትና ፍላጎት ስልጣን የምትፈልገውን የምትመኘውን ጥሩ ነገር ማድረጊያ ነው። የፖለቲካው ስልጣን ቀርቶ; ሌላውን ወደ ገንዘቡ ወደ ሚዲያው ጠጋ ብል የኢትዮጵያን ከፊል ህዝብ አንባቢ የማድረግ
የ”ልም እዛቶች” አሉኝ ለማለት ነው”
የምተገብራቸው::

......ለጊዜው:እንደወንድ:የሚከጅለው:
ተብሎ:ይነበብልኝ........." የሚለው:ማብራሪያ:ይፈልጋል
ግድየለም:ይተንተን!!!


ምንም የሰራሁት ስራ ስለሌለ በጾታ ወንድ፣ በምግባር በጀግንነት (በተሰልፍኩበት የሙያ መስክ ያደረጉሁት ስለሌለ) ክጃሎቱ አለኝ ለማለት ያህል ነው።
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ባሻ አሸብር በአሜሪካ

Postby እንሰት » Fri Nov 16, 2007 4:58 pm

(posted October 15,2005)
ከመንግስቱ ለማ

ባሻ አሸብር በአሜሪካ
የዛሬ አሥር ዓመት በታላቅ ሹመት
አሜሪካ ልኮኝ ነበረ መንግስት።

ዋሽንግተን ገብቼም ዋልሁ አደርሁኝና
ሽር ሽር ሳለ ባንድ አውራ ጎዳና
አላፊ አግዳሚውን ጥቁሩን ነጩን
ሳይ ስመለከተው በኢትዮጵያዊ ዓይን
የውሃ ጥም ደርሶ ስላረገኝ ቅጥል
ከመንገድ ዳር ካለች ካንድ ትንሽ ውቴል
ጎራ አልኩና ገና ከወምበር ላርፍ ስል
ተንደርድሮ መጣ የውቴሉ ጌታ
አማረው ቋመጠ ከጀለው ሊማታ።

«አብዷል ሰክሯል እንዴ? ምንድን መሆኑ ነው?
በል ንካኝ በዱላ ግንባርህን ላቡነው!»
ብዬ ስነጋገር ሰምቶ ባማርኛ
አሳላፊው ሆነ አስታራቂ ዳኛ
ለጥ ብሎ እጅ ነሣና እንዳገራችን ሕግ
አክብሮ ጠየቀኝ ምን እንደምፈልግ።

እኔም ጎራ ያልሁት የሚጠጣ ነገር
ለመሻት መሆኑን ነግሬ - ከወንበር።
«ይቅርታዎን ጌታ አዝናለሁ በጣሙ
ምናምኒት የለም በከንቱ አይድከሙ»
አለና እጅ ነሳኝ ሳቁን እየቻለ።
«ውኃም የለ?» ብለው በሳቅ ገነፈለ።

ቤቱን የሞላው ሰው ሁሉም አጨብጭቦ
«ብራቮ! ተባለ ብራቮ! ብራቮ!»

በጣም ተገርሜ ደንቆኝ ያየሁት
ከዘራዬን ይዤ ሄድሁኝ ወጣሁት።

ሐሳብ ገብቶኝ እደጅ ሳሰላስል ቆሜ
ያን ቂዛዛ መስኮት ባስተውለው አግድሜ
አራዳ ግሪኮች እንደሚሸጡት
ያለ በያይነቱ አየሁኝ ብስኩት
ትዝ አለኝ «አራዳ አዲሳባ ሆይ
አገርም እንደ ሰው ይናፍቃል ሆይ?»...
አጎመዠኝ በሉ ሳይርበኝ ጠግቤ
አስተውለው ጀመረ መስኮቱን ቀርቤ።

የምገዛውንም በልቤ ቆጥሬ
ዳግም ልገባ ስል በስተበሩ ዞሬ
ዘወር ብዬ አያለሁ የውቴሉ ጌታ
ተኩሮ ያየኛል። ወደኔም ተጠጋ።
«ስንት ነው ሰውዬ ያንዱ ብስኩት ዋጋ?»

የያዘው አባዜ ብሎት አላናግር
ዓይኑ ደም ለበሰ ይጉረጠረጥ ጀመር።
«ዓለም ሁሉ ያውቃል መሆኔን ታጋሽ...
ትግሥቴ አሁን አልቋል።
ጥፋ ብረር ሽሽ!...
አገጭህን በቦክስ ሳላፈራርሰው
ይህ ፈጠጤ ዓይንህን እዚህ ሳላፈሰው
እሱቄ መግባትህ አንሶህ አሁንስ
መስኮቴ ፊር ደሞ ልትልከሰከስ?!
ገበያ አላገኝም!
ደንበኞቼም
እዚህ አንተን ካዩ ደግመኛ አይመጡም።
ሥራ ሥራ እኮ ነው አይገባህም እንዴ?
ወግድ! አትገተር ይቋረጣል ንግዴ!»

ይህንን እንዳለ ቁጣው ጠና ጋለ።
አገጬና ጉንጬም በቡጢ ነገለ።

በቦክስም አይለኝም መልሶ መልሶ..!
እስኪሸረፍ ድረስ ጥርሴ በደም ርሶ..

ዠለጥ አደረግሁት በያዝኩት ከዘራ።
ገና አልጠቀመውም ዘበኛ ተጣራ።
ፖሊስ ቢሮ ሄድን።
እሱ ተለቀቀ።
አሸብር ከልካይ ግን እወህኒ ማቀቀ።

ማን ሊሰማኝ እዚያ ዘሬን ብቆጥር
ብሸልል ባቅራራ ወይስ ብፈክር?
ደረቴ ላይ ያለው ያገሬ ባንዲራ
ያምራል ተባለ እንጂ ከብሮም አልተፈራ።

የሞጃው ተወላጅ የጠራሁት መንዜ
ሸጎሌ ሻንቅላ ተብዬ መያዜ
በግፍ እንደሆነ ባሰት በውሸት
አቃተኝ ማነንም ከቶ ማስረዳት።

ሲቸግረኝ ጊዜ አንዱን ተጠግቼ
«ሻንቆን» እንዲህ አልሁት ነገሬን አስልቼ፦
«ሰማኸኝ ወንድሜ አላሳዝንህም
በሰው ጠብ ገብቼ በከንቱ ስደክም?

አውቃለሁ ከጥንትም ነጭና ሻንቅላ
በቁም እንደኖረ ሲዋጋ ሲጣላ።
እኔ ግን ሐበሻው ምን ወገን ልለይ?
በማይነካኝ ነገር ለምን ልሰቃይ?
እንካ...ጠጉሬን እየው...ሸጎሌ አይደለሁም።
ፊቴን ተመልከተው..እንዳንተ አልጠቆርኩም።
ቀይ ዳማ ነኝ..እየኝ..ይሁን ጠይም ልባል፡..
እኔን መቁጠሪያ ራስ የሚለኝ ሰው አብዷል!
ዘራችንም ቢሆን ከነገደ ሴም
ሲወርድ የመጣ ነው ከዳዊት ካዳም።
የንግስተ ሳባን ታሪክ ሰምተህ የለ?
ልጇ ቀዳማዊ ምኒልክ ተባለ...
ዛጓማ ከገረድ ነው የተወለደ...
አያወጣው ወጥቶ ከዙፋን ወረደ።

የካም ልጆች ናችሁ እናንተ ጥቁሮች
ፈረንጆችም ናቸው የያፌት ልጆች...»
ብዬ እንደጀመርኩኝ ታሪክ ላስጠናው
ባጭሩ አቋረጠኝ ትእግስት አጣ ሰሚው።

«እንዲህ ያል ንግግር ያሰኛል አላቲ!
ባሻ አሸብር ከልካይ ልጠይቅህ እስቲ
ገና አንተ ነህና ኢትዮጵያዊ
አይደለሁም ልትል ጥቁር አፍሪካዊ?!

ምን ይሆናል እንጂ አንተን ላይዘልቅህ
ነበረኝ ባያሌው ብዙ እምነግርህ...

ቁጥርህ ከማን እንደሁ ከነጭ ወይ ጥቁር
ማወቅ ቢፈልግህ ወዳጄ አሸብር
እነጮች ቡና ቤት ገብተህ ቡና ጠጣ
ወይ በባቡር ስትሄድ አብረህ ተቀመጣ
ይህም ባይቻልህ ሞክር ባልደረባ
ነጮች እገቡበት ሆቴል ልትገባ።

ባንተ አልተጀመረም ያዳሜ ምኞት
ከተጠቃው «መራቅ» አጥቂን «መጠጋት»
ኃይለኛውን «መውደድ» ደካሙን «መጥላት»...
ሰው ባያቱ ይምላል አባቱ ሳይከብር።
ማነው የድኃ ልጅ ዘሩን የማይቆጥር?»

እስከ ዛሬ ድረስ ይህ አነጋገር
ሲታወሰኝ አለ ባሰብሁት ቁጥር።

ይመስገነው ገባኝ ከጊዜ በኋላ
አማራ፣ ...ራ፣ ...ና፣ ሻንቅላ
ሱማሌ፣ ኪኩዩ፣ ሡዋሂሊ፣ ባንቱ
ኩኑኑሉሉ፣ ማሣይ፣ ...ሮ፣ ባማንጓቱ
ማለት እንደሆነ ስልቻ ቀልቀሎ
ቀልቀሎ ስልቻ ስልቻ ቀልቀሎ
ስልቻ ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ።


መንግስቱም የጸጋዬም እናት አለም ጠኑ የተገኙት ከ አቁማዳ http://yekolotemari.blog.com/ ድረ ገጽ ነው:: ጎብኙት
መልካም ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Fri Nov 16, 2007 7:52 pm

እግዚአብሄር:ይስጥልን:እንሰት... :wink: :wink:
አመት-አመት:ያድርስልን.......
የከርሞ:ሰው:ይበልልን 8) 8) 8)
እኔም:እስኪ:.....ትንሽ:ጥላው:በረድ:ሲል...
ጨረቃ.....መውጣት:ስትጀምር:.....
ከጸጋዬ:ጋር.....ልወያይ.....ልማከር :!:
እያልኩ:ነው:ከራሴ:ጋር...
በምናብ:መንጽር :!:
ይዤ:እመጣለሁ....ያለኝን
....የነገረኝን :!: :!:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby መልከጻዲቅ » Fri Nov 16, 2007 7:59 pm

እግዚአብሄር:ይስጥልን:እንሰት... :wink: :wink:
አመት-አመት:ያድርስልን.......
የከርሞ:ሰው:ይበልልን 8) 8) 8)
እኔም:እስኪ:.....ትንሽ:ጥላው:በረድ:ሲል...
ጨረቃ.....መውጣት:ስትጀምር:.....
ከጸጋዬ:ጋር.....ልወያይ.....ልማከር :!:
እያልኩ:ነው:ከራሴ:ጋር...
በምናብ:መንጽር :!:
ይዤ:እመጣለሁ....ያለኝን
....የነገረኝን :!: :!:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ocean12 » Fri Nov 16, 2007 10:24 pm

ወዳጆቼ ሁሉ እንዴት ናችሁልኝ?
ዛሬ ነገ ስል አልሞላ ቢለኝ ነው ድርግም ብዬ የጠፋሁት::
ማን ሲሞላለት አይተሀል እንዳትሉኝ ታዲያ :D
ይሄው አሁንም በሱው ችሮታ ጭል ጭል እላለሁ
ይመስገን!!
መልከጻዲቅ...እጅህ ከምን እያልክ ነው?
እረ የት አባቱ
ዛሬም እንደወትሮው ከጸጋዬ ግጥሞች አንዱን ጥማችሁን እንዲያቆርጥላችሁ በማሰብ ተጋብዛችሁዋል:: :D :D
ጸጋዬ ምስጋና ይድረሰው!
http://www.freewebs.com/zelalemethiopia/Microsoft%20Word%20%2D%20dehnaway%20emama1.pdf
ደህና ዋይ እማማ


አዬ፣ እማምዬ፣ ደህና ዋይ
ያሳወረሽ አሳወረኝ ፣ ቀን የተጣባብን ሥራይ፤
ዓይኔ ዓይንሽንም አያይ…
ያለ ጠር መጣረር ዕዳ ፣ወይ ያለባላንጣ ግዳይ፤
አቆላልፎን ፣ አቆራርጦን፣ በእንባ በትካዜ ብካይ
ዘመን የተፋው ሾተላይ
አዬ፣ በቃሽኝ፤ በቃሁሽ፣ ዓይኔስ ዓይንሽንም አያይ…
በቃ እማማ እናት አለም፣እማትነፍጊ እማታቅማሚ
እማታሳጪ እማታሚ
እኔን በራበኝ፣ በጠማኝ፣ እንዲያ አብረሽኝ ስትጠሚ
ምነው ወተቴን ከጡትሽ፣ በጊዜ--ገፊ ታስቀሚ?

አንጀቴ ያንጀትሽ ቁራጭ
አጥንቴ ያጥንትሽ ፍላጭ
ሕይወትሽ የሕይወቴ ምንጭ፤ ወዜ የፍቅርሽ ወዝ ምጣጭ
ማህጸንሽ የፍጥረቴ አማጭ…
ከንግዲህ በቃሁሽ በቃኝ እማማ የነፍሴ ቁራጭ
ይበጠስ ውልሽ ከውሌ፣ ቃሌ ከቃልሽ ይፈለጥ
ዓይንሽ ባይኔ ትል ዘነበ፣ በቃኝ የኔው ብሌን ይፍረጥ
ብቻ በምን አንጀቴ ነው፣ አንጀቴን ባንጀቴ እምቆርጥ?
ይቆረጥ እንበል፣ ይገርሰስ?
ይረሳ፣ ይሙት፣ ይደምሰስ?
እርም አፈር እንበል ይበጠስ?
ማህጸንሽ ጽዋው መረዘኝ፣ ዘጠኝ ወር ያጠባኝ ገንቦ
ጡትሽ የደም ወተት ዘንቦ
ሆድሽ የቁስል ምጥ ታልቦ
ባዳ ቅሪት ተመትሮበሽ፣ የአንብርቴ እልባት ተሰብሮ
ደሜ በፋፋበት እትብት፣ ገፊ ዲቃላ ተቋጥሮ

በቃ እማማ፣ እማምዬ
መቀነቴ፣ ገበናዬ
በቃሁሽ አድባሬ፣ መቅኔ
ከንግዲህስ ላንቺ መጥኔ
አዬ ላንቺ አዬ ለኔ…
ጫቅላዬን ባዘለ እቅፍሽ
ገፊ ጉግ ማንጉግ መፅነስሽ
ጎምቱ ሾተላይ ማብቀልሽ…
አይሆንም እንጂ ከሆነልሽ፣ ካለልሽ ካዘለቀልሽ
እግዚአብሄር ያሳድግልሽ፣
አዎን፣ ቃል ለምድር ለሰማይ
ደህና ዋይ፣ በቃ፣ ደህና ዋይ
ዓይኔ ዓይንሽንም አያይ፤
ከፉም በጎም አናሰማ
እንዲያው ደህና ዋይ እማማ
እናተ አለም የስሜ አርማ
የህይወቴ ወዝ የአይኔ ማማ
እትነፍጊ እማታቅማሚ
እማታሰጭ እማታሚ
እኔን በራበኝ በጠማኝ አብረሽኝ እምትጠሚ
ጥቃቴን እምትጠቂ፣ ቁስሌን እምትታመሚ
ፍስሃዬን፣ ፈገግታዬን፣ ሳቄን ብቻ እምታልሚ
አንቺ እማማ
አንቺ የነፍሴ ዓልማ
የዓይኔ ማማ….
ምነው ጡትሽ ተጣረረኝ?
በጊዜ- ገፊ ለወጠኝ?
እንዴት ይንጠቀኝ ሾተላይ?
ቀን የተጣባብን ሥራይ
ያለኝታ ህብስተ-መና፣ የወገን ያጥንቴን ሲሳይ
የደሜን ምንጭ የሕይወቴን ማይ
የማህፀን የእትብቴን አዋይ?...
አዎን፤ ይብቃን እናት አለም፣ አንጀቴ ባንጀቴ ይቁረጥ
አጥንቴም በአጥንቴ ይድፈጥፈጥ
ቃሌም ከቃልሽ ይፈለጥ
የዓይኔም ውሃ በዓይንሽ ይፍረጥ
ይረሳ፣ ይጥፋ፤ ይደምሰስ
እርም አፈር እንበል ይበጠስ…
በቃ እማምዬ ደህና ዋይ
የደሜ ምንጭ የህይወቴ ማይ
የማህፀን የእትብቴ አዋይ
አሜን ቃል ለምድር ለስማይ
ዓይኔ ዓይንሽንም አያይ።1953 ሎንዶን
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby መልከጻዲቅ » Wed Nov 21, 2007 6:28 am

:arrow:
Last edited by መልከጻዲቅ on Thu Jul 29, 2010 7:57 pm, edited 1 time in total.
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby እንሰት » Wed Nov 21, 2007 9:30 am

ጸጋዬ መልኩን ቀይሮ መጣ አይደል? ዘይገርም ሻሸመኔ ...አለች አሉ ሴትየዋ። መልከ ጻዴቅ እስኪ ይሁን አጀማመርህ ይበል በርታ እደግ ተመንደግ የሚያሰኝ ነው። ታዲያ እጅህ ከምን ከተባልኩ እሳት አመድ ወለደ ነዋ

እሳት አመድ ወለደ

ለተማሩ ለማይማሩ አፈ ሊቃውንት ( ፪፩፻፰፡ አዲሳባ ) ከእሣት ወይ አበባ
በሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን

አባቴስ ወንድ ወለድኩ ይበል !
ወለድኩ ይበል ይልቅ፤ በቃ፤
በምላሱ የሚያመርቃ !
ወኔው በአረቄ እሚነቃ
ልቡን በቧልት እሚደቃ
በሤራ በነገራ አሽሙር
' በታክት በእንትሪንግ' አዙር
ሳሮጥ ሳሽከረክር ሳዞር
በብልጠት በአንደበት ንቃት፤ በመስሎ አስመስሎ መኖር
ሴቷን በነገር መብለጥለጥ ጋለሞታን በምላስ ጦር
ሁሏን ረትቼ አሸንፌ፤ በምጸት ወግ፤ በጌጥ፤ በ ' አሞር'
ሲነጋ እንደ አመድ አፋሽ ገል
ሲመሽ እንደ ሽንቁር በርሜል
የአግቦ ጢስ በማንቃረሩ
ወሬ በማንሸራሸሩ
ተሞልቶ በመተርተሩ፤
ነፋስ ጠብቶ አየር ታልቦ
የነገር ረሃብ ተርቦ
ጉድ በማናፈስ ተስቦ
ከዚህ ቀዶ እዝያ ዘንቦ _ _ _ _
ውሃ እንደ ማይቋጥር ገንቦ
ላባቴ ተወልጄለት ቅምትል የልቡ ኩራት
ግስላው የወኔው እሳት
ይመካ እንጂ ይንቀባረር
ይሞካሽ እንጂ ይገደር
የዘር ወጉ እንዳይደፈር
ደርሼለት እሱን መሰል
በተከለው የሚከተል
አባቴስ ወንድ ወለድኩ ይበል።
መድሰል ወራሽ ወለድኩ ይበል፤ የዘር ቅርሱን የሚያስፋፋ
ድል የሚመታ ሰተቴ፤ በነገር በአሽሙር ልፈፋ
በአግቦ እንደ ቅኔ ዘረፋ
በሽሙጥ ባፍ ዘለፋ፤
ይበል እንጂ ' እኔም ወንድ ወለድኩ
ባፍ እሚበልጠኝ አደረስኩ
ያባት ልጅ ያዘው ቅምጥል'
የደሙ ትክል የወኔው ሽል፤
ፈጠርኩ ይበል ቀበዝባዛ እንደአዙርት እሚፈትል
በምላስ ቀስት አነጣጥሮ፤ ቂም በልቦና እሚተክል
ደም በደም እሚያስተጣጥብ፤ ወገን ከወገን እሚያክል
እንደ ሠራ ሠር ደብተራ፤ ላንቃው መርዝ እሚያቀላቅል
ውጋቱ ዘር እሚያጣጥል
እንደጦስ እሚደበልል
እንደዛር ውላጅ አሽሮ
ያጥንት ስባሪ አቅሮ
ደም መራዥ ልጅ ያፋፍ ላይ ድጥ
መስክ መሳይ ያሽሙር ደለል፤
የወሬ ማንፈሻ ጋሻ ፤ ደርሼለት እሱን መሰል
በተከለው እሚተከል _ _ _
አባቴስ ወንድ ወለድኩ ይበል" !


የተቀዳበት ምንጩ http://www.quatero.net/gitem/esatamed1.php

መልካም የስራ ሳምንት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ባገር መመሰጥ

Postby መሪ ወንዝ » Wed Nov 21, 2007 11:17 am

ሠላም እንሰት!


ጥሩ አምድ ከፍተሓል ትምህርት የሚስጥ:
በውጭ ከመመካት ባገር መመሰጥ::

Image

ትምህርት ለማገኘት ብሎም ለመቃኘት:
አጥብቆ መታገል ለኢትዮጵያ አንድነት::
ፍቅር እና ሠላም ለሁላችን
መሪ ወንዝ ከተከዜ (ጎርፉ)
Image
ፍቅር እና ሠላም ለኢትዮጵያ
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=21238
መሪ ወንዝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 470
Joined: Sat May 06, 2006 5:13 am
Location: ኢትዮጵያ

Re: ባገር መመሰጥ

Postby እንሰት » Thu Nov 22, 2007 11:16 am

ውድ መሪያችን እግዜር ሰላሙን ላንተም ያብዛልህ
መሪ ወንዝ wrote:ሠላም እንሰት!

ጥሩ አምድ ከፍተሓል ትምህርት የሚስጥ:
በውጭ ከመመካት ባገር መመሰጥ::
Image
ትምህርት ለማገኘት ብሎም ለመቃኘት:
አጥብቆ መታገል ለኢትዮጵያ አንድነት::


ፍቅር እና ሠላም ለሁላችን
መሪ ወንዝ ከተከዜ (ጎርፉ)


ለጸጋዬ ወዳጆች
በእነዚህ የድምጽ ክሊፖች ተዝናኑ
በሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን
አብረን ዝም እንበል!

Audio form
http://www.quatero.net/gitem/newgitmaw2.php
ይድረስ ለቅንጅትና ለህብረቱ

Audio
http://www.quatero.net/gitem/newgitmaw2.php
http://www.abugidainfo.com/?page_id=73
Poems
Poet Laureate Tsegaye Gabre-Medhin
audio
Introduction - 3:10
Abren Zim Inebel - 3:58
Ilma Geda Aba Geda - 10:17
Petros - 11:53
Esop - 13:55
Awash - 12:51
Merkato - 6:34


እነዚህ ሌሎች ናቸው
An English Poem about Gondar submitted by Getachew Selassie
An Amharic poem about Gondar submitted by Getachew Selassie
An Amharic poem for kids about a cow submitted by Getachew Selassie
An Amharic poem by Sahlu Bekele(Toronto)

እያዳመጣችሁና እያነበባችሁ ተዝናኑ
መልካም የምስጋና በአል እረፍት ለአሜሪካ ተሳታፊዎች
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests