የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ocean12 » Sat Nov 24, 2007 12:30 pm

እንሰት በየጊዜው እዚህ በመጣሁ ቁጥር እንደተደመምኩ ነው...
አሁንም እነዚህን ሁሉ አድራሻዎች ጊዜን ሰውቶ ማሰባሰብ ትልቅ ስራ እንደሆነ ስለማውቅ....አሁንም እንደገና
ምስጋናችን ይድረስ....
የድምጽ ከሊፖችን ወድጃቸዋለሁ...
ሰላም ቀን..
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sat Nov 24, 2007 8:59 pm

:arrow:
Last edited by መልከጻዲቅ on Thu Jul 29, 2010 7:59 pm, edited 1 time in total.
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ዋኖስ » Sun Nov 25, 2007 4:55 am

መልከፃዲቅ ይችን ክፍል ሁለት በደምብ ደጋግሜ አነበብኋት ጣመችኝ ደገምኋት ታዲያ በዚህ አያያዝሕ ሌላም እጂግ መሳጪ ና አስደሳች ፅሁፍ ካለሕ ደጃችሁን ለማዘዉተር ቃል እገባለሁ!! በዚሕ አጋጣሚ ዉቅያኖስ ና እንሰት በርቱ

መልከጻዲቅ wrote:ክፍል-2 ካለፈው:የቀጠለ......................... :arrow:
:arrow: :arrow: :arrow: :arrow: :arrow: :arrow:
....ተኮማትረው:የነበሩት:የግንባሩ:መስመሮች:ሲፈታቱ:ታየኝና:
ፍርህቴ:ለቀቀኝ::የበለጠ:መቀራረቡን:ስለፈለኩ:እጄን:ለሰላምታ:
ዘረጋሁኝ...........ግን:አይቶት:እንዳላየ:ስለሆነብኝ:አፍሬ:ቶሎ:
መለስኩት:: "ሰላም:ነህ:ጋሽ:ጸጋዬ?"አልኩት.....ድሮ:ከማውቀው:
ቁመቱ:የረዘመ:መሰለኝ...አዎ:አልተሳሳትኩም:ሁለት:ጊዜ:
በአካል:አይቸዋለሁ::ዘለግ:ያለ:ቁመና:ቢኖረውም:አንደ:
አሁኑ:ግን:ረጅም:አልነበረም::ሰላም:መሆኑን:በአዎንታ:
ገለጸልኝና:ያለበት:ቦታ:ግን:ትንሽ:ቅዝቃዜና:ብርድ:እንዳለው:
አስረዳኝ::"የት;አካባቢ:ነው:የምትኖረው?አልኩት......"ለማወቅም:
ከፍተኛ:ጉጉት:አደረብኝ.................!!!
"በሰሜን:የምድር:ጫፍ:ትይዩ:ባሉ:ተራሮች:አናት:ላይ:ዋና:
መኖሪያዬን: አድርጌአለሁ:ለምድር:የሚቀርበን:ቦታ:በበረዶ:
ግግር:የወዛውና:ከላይ:ሆነህ:ስታየው:የሚያብልጨልጨው:
የአንታርክቲክ:ክፍል:ነው:.......ለዚህም:ይመስለኛል...በሰሜን:
አንጻር:የሚነፍሰው:ንፋስ:አካባቢያችንን:እያቀዘቀዘ:ያልፋል.." አለኝ::
ይህን:ሲያወራኝ:በማማረር:ወይንም:በመከፋት:ሳይሆን:........
የማወቅ:ጉጉቴን:በመገንዘብ:ነበር::"እንዴ:ለምን:ታዲያ:ወደ:
ምድር-ሰቅ:አክባቢ:አትመጣም...ለምሳሌ:ወደ-መካከለኛው:
ምስራቅ:ወይንም:ወደ:ሰሀራ:በረሀ:ማቁረጫ:መስመሮች.....
አይሻልህም:ነበር?.........ለምን:ብለህ:ነው:ሰሜን:ዋልታ:ጫፍ:
ላይ:የከተምከው: ?አልኩት:: ትንሽ:ሳቅ:እንደማለት:አለና:
"ያ:አይሆንም:" አለ::"የኔ:ምርጫ:ነው...እኔ:ነኝ:እዚህ:መኖር:
የመረጥኩት!"አለኝ::ሁኔታው:ግራ:እንደገባኝ:ስላወቀ:ማስ
ረዳቱን:ቀጠለ::"አየህ...እዚህ:አካባቢ:የምፈልጋቸውና:የማው
ቃቸው:ሰዎች:ይኖራሉ:ሽክስፒር:ጎረቤቴ:ነው:ከሱ:ቤት:ፊት:
ለፊት:ከሚታየው:በሰማያዊ:ደመና:ውስጥ:በተሸፈነው:ጫካ:
ውስጥ:ዳቭንቺን:አገኝዋለሁ:ተፈጥሮን:ያደንቃል:የሰማይ:
ውበትን:ይስላል:....በስተቀኝ:በኩል:ያለውን:ቀጭን:መንገድ:
ተከትለህ:ስትሄድ:የምሽት:ኮከቦች:የሚወጡበትን:ተራራ:
ታገኛለህ:....ከተራራው:ስር:ከበደና:አዲስ:በጉርብትና:ይኖራሉ::
ይህን:ሁሉ;ሲነግረኝ:ቡዙ:ነገር:በአእምሮዬ:መጣ!!የሰማይን:
ሚስጥር:ማወቅ:ናፈቀኝ.........!!ታወራላችሁ?ስለድሮ:.............
ህይወታችሁ:ትነጋገራላችሁ?"አልኩት:: "አናወራም!" አለኝ!
ፊቱን:ኮምጨጭ:አድርጎ.."ስላለፈው:ነገር:ማንም:ምንም:
አያወራም...ሁሉም:እዚህ:በስራ:ተጠምዷል...እረፍት:የለም..."
አለኝ............................
በዚህ:መሀል:አልፎ;አልፎ:ብቻ:አለን:ለማለት:ድምጻቸውን:
የሚያሰሙት:እንቁራሪቶች:አንዳች:ነገር:እንዳዩ:ባንድ:ላይ:
ተንጫጩ!!!!ወዲያው;የእነሱን:ድምጽ:ተከትሎ:ከቆምንበት:
በስተግራ:በኩል:ካለው:የጥድ:ዛፍ:መሀል:የታነቀ:የቁራ:
ጩሀት:የመሰለ:ድምጽ:ተሰማ.............
"ሰአቴ:ደርሷል:መሄድ:አለብኝ...."አለ:በድንገት......ለሰላምታ:
የዘረጋሁትን:እጄን:ሳይጨብጥ:በመጣበት:ፍጥነት:ተመለሰ.......
.........ይቀጥላል........ :arrow: :arrow: :arrow: :arrow:
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby መልከጻዲቅ » Sun Nov 25, 2007 1:36 pm

እግዚአብሄር:ይስጥልን:ወንድማችን:ዋኖስ 8) 8)
ስለሰጠሀን:አስተያየት:አመሰግናለሁ :!:
ጽሁፉም:የበለጠ:ህይወት:እንዲኖረው:በጸጋዬ:ስራዎች:ውስጥ:
መጠቀስ:አለበት:የምትለውን:የግጥም:ስራዎቹን:ብቻ:ሳይሆን:
የእለት:ተእለት:ገጠመኞቹንም:ብትልክልን:አብረን:
እናሳድገዋለን..... :!: በድጋሚ:ምስጋናዬ:ይድረስህ 8)
አረ:እንሰት:የት:ነው:ያለሀው;እንግዳ:ውጭ:ቆሟል :!: :wink:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

ቤቶ.....ች ኳ... ኳ... ኳ....

Postby እንሰት » Sun Nov 25, 2007 10:23 pm

ኳ... ኳ.... ቤቶ…….ች ደህና ስነበታችሁ። ይቺ የእንጀራ ጉዳይ እንክርት ይዛኝ ጠፋሁ። ዴ….ዴ…. ቤቱ ሞቋልሳ አዬ በጉዴ ወጣሁ። ቤቱን ክፍት ትቸው ሔጄ እንግዳ ቀድሞኛልሳ። ኧረ በእግዜር አይገባም አይገባም አትነሱ።

Ocean 12
እንሰት በየጊዜው እዚህ በመጣሁ ቁጥር

እንደተደመምኩ ነው ...

አሁንም እነዚህን ሁሉ አድራሻዎች ጊዜን ሰውቶ ማሰባሰብ
ትልቅ ስራ እንደሆነ ስለማውቅ ....አሁንም እንደገና

ምስጋናችን ይድረስ ....

የድምጽ ከሊፖችን ወድጃቸዋለሁ ...
ሰላም ቀን ..


ያልምድህ በተሳትፎውም በርታ

ዋኖስ
መልከፃዲቅ ይችን ክፍል ሁለት በደምብ ደጋግሜ

አነበብኋት ጣመችኝ ደገምኋት ታዲያ በዚህ አያያዝሕ

ሌላም እጂግ መሳጪ ና አስደሳች ፅሁፍ ካለሕ ደጃችሁን

ለማዘዉተር ቃል እገባለሁ !! በዚሕ አጋጣሚ ዉቅያኖስ ና እንሰት በርቱ


የኛ አያልቅበት ዋኖሳችን እዚህም ከጸበሉ አዳርሰን እንጂ!

የኛው ባቲ አልፎ አልፎ ሲገጥም እንዲህ ብሎ ነበር እኛም ተዋስንና አበጃጀነው።

ለመልከ ጻዴቅ፣ ለ Ocean 12 እንዲሁም ለዋኖስ እንዲህ ብንልስA ን ሲያቆላምጧት , ጎጆናት አሉኝ

አሻርኩህ ቆንጆ A, ብቻ 'ዳያንስብኝ

ከወደድከውማ , ተመቸኝ ተመቸኝታሽቶ ሲዳበሱ , በዚያ ሀገር በቀል

አሁንም አሁንም , ያስደግማል ልበል ?መልከ ጻዴቅ የእጅና የአእምሮህ ምናብ ፍጭት ምን ያስነብበን ይሆን?
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ጸጋዬ ከግጥም ውጭ

Postby እንሰት » Mon Nov 26, 2007 8:14 am

መልከጻዲቅ እንዲህ ፎከረ
መልከጻዲቅ wrote:እግዚአብሄር:ይስጥልን:ወንድማችን:ዋኖስ
ስለሰጠሀን:አስተያየት:አመሰግናለሁ :!:
ጽሁፉም:የበለጠ:ህይወት:እንዲኖረው:በጸጋዬ:ስራዎች:ውስጥ:
መጠቀስ:አለበት:የምትለውን:የግጥም:ስራዎቹን:ብቻ:ሳይሆን:
የእለት:ተእለት:ገጠመኞቹንም:ብትልክልን:አብረን:
እናሳድገዋለን..... :!: ...


እኔ አላውቅም ምን እንደምታደርገው ነገሩ ቢያሳዝንም ቃልህ መከበር ስላለበት ብቻ ዋኖስን የጠየከውን እኔም ልገዝህ ብዬ
እነሆ


ዋ ጋሽ ጸጋዬ! «እባክህ አንድ ነገር ፍጠርና ጥሩኝ። ለአገሬ አፈር አብቁኝ! »
Saturday, March 04, 2006 at 04:16


የነቢይ መኮንን ጸጸት ነው::ጸጋዬ በምድረ አሜሪካ አረፈ
ኣ የልቡ ሳይሞላ

ምንጩ http://www.addisadmass.com/Tibeb/news_i ... ?NewsID=32

አዲስ አድማስ የመሄዴ ጉዳይ ሌላ ነበር:: ሰለሱ አጫውታች ሁአለሁ::

ጥያቄም አለኝ:: ለመጀመሪያው ትክክለኛ መላሽ ግን ምን እንዴት እንደምሰጥ አላውቅም ሀሳቡ ቢኖረኝም - መልሱ ከመንግስቱ ለማ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ነው:: አረፍ ብዬ ልመለሳ ለጥያቄው
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Mon Nov 26, 2007 3:37 pm

እንሰት: " A " ን: አያት.......
ልብ:ብሎም:አስተዋላት..... :!:
ከዛም...አወደሳት.... :!:
ቅኔም:ወረደላት......
:arrow: "A" እንዲህና:እንዲህ....ተባለላት........

Code: Select all
A ን ሲያቆላምጧት , ጎጆናት አሉኝ 

አሻርኩህ ቆንጆ A, ብቻ 'ዳያንስብኝ 

ከወደድከውማ , ተመቸኝ ተመቸኝታሽቶ ሲዳበሱ , በዚያ ሀገር በቀል

አሁንም አሁንም , ያስደግማል ልበል


ሰላም:እንሰት 8) 8)
ከላይ:ያበጃጃሀትን:ግጥም:ወደድኮአት.... :!:
ልጅ:ሆኜ:ጃንሜዳ:ለጥምቀት:ከሰፈሬ:ልጆች:ጋራ:እሄድ:ነበር...
ታዲያ:የቀበና...የፈረንሳይ....የጃንሜዳና:አካባቢው:ልጆች......
በአርቦኒካ:የሚጫወቱት:ግጥም:ትዝ:አለኝ....... :!: :!:
አረ...ንኪው..ንኪው.....ባንገትሽ..... :wink:
ግጥሙ....ባይገጥም.....አንቺ...ምን:ቸገርሽ... :wink:
ቡዙ.....ነበር.....ተረሳ..... :arrow: :arrow:
መቼም:እንሰት:የማትገባበት:የለምና: አንድ:ቀን:ሲመችህ.....
የአርቦኒካን:ዘፈን:ግጥሞች:ታስነብበናለህ:ብዬ:ተስፋ:
አደርጋለሁ..... 8)
የላክልኝ:"...የነቢዩ:መኮንን....ጸጸት....." በጣም:ግሩም:ነው....
እጅህ:ብሩክ....ይሁን......
አንድዬ:ውለታህን.......ክትፎ...ባይቤ.....ጠጅ....በብርሌ.......
አድርጋ:ትመልስልህ...... :lol:
በቃ:አታስብ:አይዞህ.....ይሄንን:ይዞ....መፈትለክ:ነው.....
ወደ:አለም:መጨረሻ..........
ወደ:ምድር:ዋልታ: ጫፍ........
በውድቅት;ሌሊት:የሚጀምረው;የሰማይ:ጉዞ:ይቀጥላል :arrow: :arrow: :arrow: :arrow: :arrow:
ማን:ይፈራል...ሞት........ :?:
ዘ..ራ...ፍ.. :!:

ሰላም:ያገናኘን....እንሰት.... :idea:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

ተሳትፎ እናድርግ

Postby ወለላዬ » Tue Nov 27, 2007 5:19 pm

ስለ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ሲገለጽ ጅምር ይሁን እንጂ የመታሰብያ ድረ ገጽ በመሰራት ላይ መሆኑን ልንረዳ ችለናል:: ይህን ገጽ ቀደም ብዬ በተመለከትኩበት ወቅት ለአዘጋጁ የበኩሌን ሀሳብ ሰንዝሬ ነበር በዚህ ቦታ ከተነሳ አይቀር ለገጹ የኛ ተሳትፎ የሚረዳ ከሆነ አዘጋጁ ሀሳብህን ብትሰነዝርልን መልካም ነው::
ወለላዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 403
Joined: Wed Jan 26, 2005 11:20 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Wed Nov 28, 2007 8:07 am

:arrow:
Last edited by መልከጻዲቅ on Thu Jul 29, 2010 8:00 pm, edited 1 time in total.
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby መልከጻዲቅ » Wed Nov 28, 2007 8:08 am

:arrow:
Last edited by መልከጻዲቅ on Thu Jul 29, 2010 8:01 pm, edited 1 time in total.
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby መልከጻዲቅ » Wed Nov 28, 2007 2:55 pm

ወለላዬ:እንዲህ:ብላ:ሀሳብ:አቀረበች.........
Code: Select all
ስለ ሎሬት ፀጋዬ ገ /መድህን ሲገለጽ ጅምር ይሁን እንጂ የመታሰብያ ድረ ገጽ በመሰራት ላይ መሆኑን ልንረዳ ችለናል :: ይህን ገጽ ቀደም ብዬ በተመለከትኩበት ወቅት ለአዘጋጁ የበኩሌን ሀሳብ ሰንዝሬ ነበር በዚህ ቦታ ከተነሳ አይቀር ለገጹ የኛ ተሳትፎ የሚረዳ ከሆነ አዘጋጁ ሀሳብህን ብትሰነዝርልን መልካም ነው 

ሰላም:ወለላዬ:እንደምን:አለሽ... :?: ዘግይቼ:መልስ:በመስጠቴ:ይቅርታ....በግል:መለክት;
ማስቀመጫ;ላይ:መለክት:ትቼ;ነበር....በሎሬት:ጸጋዬ:
ገ/መድህን:ስራዎችና:ህይወት:ላይ:የሚያጠነጥን:ድህረ-ገጽ:
እየተሰራ:መሆኑን:ገልጸሻል::በጣም:ደስ:የሚል:ነው::የጸጋዬ:
አፍቃሪዎች:የሆንን:ሁሉ:የምንችለውን:እናደርጋለን :!: :!: እኔ:በበኩሌ:በወዳጃችን:በእንሰት:አነሳሽነት:የአምሮዬ:
ምናብ:እያፋጨ:የሚሰጠኝን:ለመጻፍ:ዳር:ዳር:እያልኩ:ነው::
ሀሳቡን:የጀመሩክት:ጸጋዬ:የመሪውን:እጄታ:እየመራ:
እንዲሄድልኝ:በማሰብ:ነው.....አሁን:ግን:ጽሁፉ:ራሱ:ወዴት:እያመራ:
እንደሆነ;እኔም:አልገባኝም....በተቻለኝ:መጠን:ጋሽ:ጸጋዬን:
ዋና:ተዋናይ:ማድረግ:እፈልጋለሁ::ጽሁፉ:ሚዛን:ደፍቶ:ላልሽው:
web-site የሚበቃ:ከሆነ:አንቺም:ሆንሽ:አዘጋጁ:
ልትጠቀሙበት:ስገልጽ:በከፍተኛ:ደስታ:ነው::በዚህ:አጋጣሚ:
ውድ:ወገኖቻችን:አስተያየታችሁን:አቶ:እንሰት:በከፈቱት:
ቀስቶ:ጠጅ:ቤት:ድረስ:እየመጣችሁ:ብትሰጡን:ትባረካላችሁ!!
ከጠጁም:ትቀምሳላችሁ :wink: :wink:
መልካም:የስራ:ሳምንት:እመኛለሁ :!:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Re: ጸጋዬ ከግጥም ውጭ

Postby እንሰት » Sat Dec 01, 2007 12:13 am

እንሰት wrote:አዲስ አድማስ የመሄዴ ጉዳይ ሌላ ነበር:: ሰለሱ አጫውታች

ሁአለሁ::

ጥያቄም አለኝ:: ለመጀመሪያው ትክክለኛ መላሽ ግን ምን

እንዴት እንደምሰጥ አላውቅም ሀሳቡ ቢኖረኝም - መልሱ

ከመንግስቱ ለማ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ነው:: አረፍ ብዬ

ልመለሳ ለጥያቄው


ደህና ሰነበታችሁ ወገኖቼ ሰሞኑን አንድ ጥያቄ አለኝ ብዬ ነበር። የጥያቄዬ ምህዋር የሚሾረው በመንግስቱ ለማ ግጥም ይዘት ነው። ወጣት መንግስቱ ገጠመ በሎንዶን (በዚያው ዘመን አጠራር )

«በጠራ ጨረቃ»

በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
አይኖቿ እያበሩ እንደ ከዋክብት
«ሳማት! ሳማት!» አሉት
«እቀፍ! እቀፋት።»
አላወላወለም ወጣቱ ታዘዘ
ወገቧን አንገቷን እጇን በእጁ ያዘ
ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ የጉማሬ አለንጋ
ጆሮ ግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ።
ዋ ጀማሪ መሆን! ዋ ተማሪነት
ዋ ትእዛዝ መፈጸም ዋ ምክር መስማት!
በጠራ ጨረቃ በኩለ ሌሊት


ግጥሙ አሁን በምታዩት መልኩ በመስፍን ሀ/ማርያም አርታኢነት ደማሙ ብእረኛ ብሎ ከታተመው የ መንግስቱ ለማ የግል ታሪክ የተነቀሰ ነው።
ይህ ግጥም እውነተኛ ታሪክ ነው። መጽሃፉን ያነበባችሁ ወጣቷ ማን እንደሆነች አብዬ መንግስቱ አስታውቀዋል። ጥፊውንም ቀምሰዋል።

ጉዞ ወደ ጥያቄዎቹ

ጥያቄ አንድ
1. በሎንዶን ትኖር / ትማር /ትሰራ የነበረችው ውቧ ወጣት ማን ትሰኛለች?
ጥያቄ ሁለት
2. ውቧ ወጣት በተለይ የምትታወቅበት ጉዳይ ምንድን ነው?


ሁለቱን ጥያቄዎች የመለሰ በተለይ ሁለተኛውን ሽልማቱን ማስታወቅ ይችላል።
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: ጸጋዬ ከግጥም ውጭ

Postby እንሰት » Tue Dec 04, 2007 5:05 am

እንሰት wrote:«በጠራ ጨረቃ»

በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
አይኖቿ እያበሩ እንደ ከዋክብት
«ሳማት! ሳማት!» አሉት
«እቀፍ! እቀፋት።»
አላወላወለም ወጣቱ ታዘዘ
ወገቧን አንገቷን እጇን በእጁ ያዘ
ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ የጉማሬ አለንጋ
ጆሮ ግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ።
ዋ ጀማሪ መሆን! ዋ ተማሪነት
ዋ ትእዛዝ መፈጸም ዋ ምክር መስማት!
በጠራ ጨረቃ በኩለ ሌሊት


ግጥሙ አሁን በምታዩት መልኩ በመስፍን ሀ/ማርያም አርታኢነት ደማሙ ብእረኛ ብሎ ከታተመው የ መንግስቱ ለማ የግል ታሪክ የተነቀሰ ነው።
ይህ ግጥም እውነተኛ ታሪክ ነው። መጽሃፉን ያነበባችሁ ወጣቷ ማን እንደሆነች አብዬ መንግስቱ አስታውቀዋል። ጥፊውንም ቀምሰዋል።

ጉዞ ወደ ጥያቄዎቹ

ጥያቄ አንድ
1.በሎንዶን ትኖር / ትማር /ትሰራ የነበረችው ውቧ ወጣት ማን ትሰኛለች?
ጥያቄ ሁለት
2.ውቧ ወጣት በተለይ የምትታወቅበት ጉዳይ ምንድን ነው?


ሁለቱን ጥያቄዎች የመለሰ በተለይ ሁለተኛውን ሽልማቱን ማስታወቅ ይችላል።


ዝምታው ሲበዛ ዋርካ ጭንቅ አትወድም ብዬ ወጣቷን እኔው ዱብ አደረኳታ!!!

ሜሪ ታደሰ ትባላለች

መልኬ እባክህ የጸጋዬን ወግ አውጋና አድባሩ አውጋሩ እየጠበቀህ ነው""
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ባቲ » Tue Dec 04, 2007 6:00 am

እንሰት እንደምን አለህ ወዳጄ?
ጥፊም ይደገማል ተብሎ የለ በነካ እጅህ የሁለተኛዋንም መልስ ጀባ በልን:: ብታብራራት ደግሞ ፅድቅ አልካት!
2.ውቧ ወጣት በተለይ የምትታወቅበት ጉዳይ ምንድን ነው ?


ይመችህ::
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

ባቲ ጠየቀ? ሜሪ ታደሰ ማናት

Postby እንሰት » Wed Dec 05, 2007 5:22 am

መነሻው ይህ ነበር::

ደህና ሰነበታችሁ ወገኖቼ ሰሞኑን አንድ ጥያቄ

አለኝ ብዬ ነበር። የጥያቄዬ ምህዋር የሚሾረው በመንግስቱ

ለማ ግጥም ይዘት ነው። ወጣት መንግስቱ ገጠመ

በሎንዶን (በዚያው ዘመን አጠራር )

«በጠራ ጨረቃ»

በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
አይኖቿ እያበሩ እንደ ከዋክብት
«ሳማት ! ሳማት !» አሉት
«እቀፍ ! እቀፋት።»
አላወላወለም ወጣቱ ታዘዘ
ወገቧን አንገቷን እጇን በእጁ ያዘ
ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ የጉማሬ አለንጋ
ጆሮ ግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ።
ዋ ጀማሪ መሆን ! ዋ ተማሪነት
ዋ ትእዛዝ መፈጸም ዋ ምክር መስማት !
በጠራ ጨረቃ በኩለ ሌሊት


ግጥሙ አሁን በምታዩት መልኩ በመስፍን ሀ /ማርያም አርታኢነት ደማሙ ብእረኛ ብሎ ከታተመው የ መንግስቱ ለማ የግል ታሪክ የተነቀሰ ነው።
ይህ ግጥም እውነተኛ ታሪክ ነው። መጽሃፉን ያነበባችሁ ወጣቷ ማን እንደሆነች አብዬ መንግስቱ አስታውቀዋል። ጥፊውንም ቀምሰዋል።

ጉዞ ወደ ጥያቄዎቹ

ጥያቄ አንድ

1. በሎንዶን ትኖር / ትማር /ትሰራ የነበረችው ውቧ ወጣት ማን ትሰኛለች ?

ጥያቄ ሁለት

2. ውቧ ወጣት በተለይ የምትታወቅበት ጉዳይ ምንድን ነው ?


እንሰት ትእግስት አጣና በአራተኛው ቀን እንዲህ ብሎ መለሰ::
ዝምታው ሲበዛ ዋርካ ጭንቅ አትወድም ብዬ

ወጣቷን እኔው ዱብ አደረኳታ !!!

ሜሪ ታደሰ ትባላለች


የዋርካው ባቲ; ጸሃፊው፤ ባቲ ገጣሚው ባቲ የታሪክ አፍቃሪው
የሜሪ ነገር ክንክን አደረገውና ማን ነች? በዚያን ዘመን እንግሊዝ ተማሪ የነበረች የመንግስቱ ለማን ጆሮ ግንድ በጥፊ አቃጥላ ካህን በመሆኑ በመቋሚያ ባይማታ በብእሩ ሃይል የተበቀላት እያለ ቢያብሰለስል፤ የታሪክ ዛር ከናላው ውስጥ ቢጮህበት፤ በስጨት ብሎ በጥፊ ከተማታህም ምንድነው ለኮፍ አድርጎ መተው ባይሆን የምትለንን በለን እና እንረፍ አለው ግልገል ወዳጁን። በወዳጅነት ይሰንብቱና

እንሰት እንደምን አለህ ወዳጄ ?

ጥፊም ይደገማል ተብሎ የለ በነካ እጅህ የሁለተኛዋንም መልስ ጀባ በልን :: ብታብራራት ደግሞ ፅድቅ አልካት !
Quote:
2.ውቧ ወጣት በተለይ የምትታወቅበት ጉዳይ ምንድን ነው ?


ይመችህ ::


እንሰትም አሰበ

እኔ እንኩዋን ያ ግጥም የዘመኑ የኢትዮጵያ አምባሳደር

አበበ ረታ ፊት ምናልባትም ሜሪ ባለችበት ሲነበብ ምን

ተሰምቷት ይሆን ብዬ አሰብኩ። አቤት ጥፍሯ ውስጥ

ተደብቃ ይሆን?


አስቦም አልቀረ ለባቲ መልሱን እንድነግርህ ነው? አለና
መልክት ሰደደ ዋርካም መልክቱን ተቀብሎ እንዲህ አደረሰን
የዋርካው ጥቁር እንግዳ ልጅ ባቲ

ኖር ብለናል! ያችን የአንተና የፓን የታሪክ ጥም ቀሰቀስኩ እንዴ?
አሁን እኔን ሞኝ አድርገህ ሜሪ ታደሰ በውጭ ሃገር በ BBC Amharic program ምናልባትም በሃገር ውስጥ የመጀመሪያ የአማርኛ ዜና እና ሪፖርት አንባቢ ነበረች እንድልህ ነው አይደል? እኔ እንደው አልነግርህ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests