የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ocean12 » Wed Dec 05, 2007 5:59 am

እነዚህን ግጥሞች ያገኘሁዋቸው ካሁን ቀደምም
አድራሻው እዚህ የተጠቀሰ ቢሆንም ከብራንጎ
ገጽ ላይ የሚሄላ ግጥሞች በሚለው ርእስ ስር ነው::
በሚገርም ሁኔታ የተጻፉ ናቸው ....
አጭር ግን ግዙፍ መልክት እና ስዕል...
መልካም ንባብ
http://metatef.org/wpmu/brango/category/mihelas/
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby እንሰት » Thu Dec 06, 2007 12:33 pm

ocean12 wrote:እነዚህን ግጥሞች ያገኘሁዋቸው ካሁን ቀደምም
አድራሻው እዚህ የተጠቀሰ ቢሆንም ከብራንጎ
ገጽ ላይ የሚሄላ ግጥሞች በሚለው ርእስ ስር ነው::
በሚገርም ሁኔታ የተጻፉ ናቸው ....
አጭር ግን ግዙፍ መልክት እና ስዕል...
መልካም ንባብ
http://metatef.org/wpmu/brango/category/mihelas/

የወንድማችንን ocean12 ጊዜ እጅ አይንና ጉልበት ይባርክልን እንጂ ምን የማናነበው አለ::
ለማንኛውም እኔን ካስደመሙኝ አንዱን ነቀስኩና አመጣሁት እዚህ::
የኔ በሽተኞች

ጭራሮ እጆቻቸው፡

የደረቀ ቆዳ…..

ስጋ አልባ አጥንታቸው፡

ማልቀስ ተስኗቸው…..

ማላዘን….ማላዘን

ማላዘን…ስራቸው

የኔም ልብ ያለቅሳል

‘ባካችሁ ንገሩኝ…

ለድህነት መረፌ..

ክኒን የት ይገኛል?

--------------------
(1995 ዓ.ም ሀረር
ህይወት ፋና ሆ/ል ህፃናት ክፍል ተፃፈ)

© March 5th, 2007


ጥያቄው የኔም ነው:: መልሱን ወዲህ በሉኝ::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Thu Dec 06, 2007 3:46 pm

:arrow:
Last edited by መልከጻዲቅ on Thu Jul 29, 2010 8:01 pm, edited 1 time in total.
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ዋናው » Fri Dec 07, 2007 2:38 am

ሠላም እንሰት
ለእንጀራ ከመራወጡ መዐል ሽራፊ ጊዜ ስታገኝ ድረ-ገጾችን እያሠስክ ሚዛና ሚደፋዉን እየጠቆምክና እየጨለፍክ ለማስነበብህ ልትመሠገን ይገባል (ምስጋናዬ ቢረፍድም)

በጎ አሣቢ አድርጎ የፈጠረህ አምላክ ዕድሜ ይስጥህ

ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby እንሰት » Sat Dec 08, 2007 9:35 am

ዋናው wrote:ሠላም እንሰት
ለእንጀራ ከመራወጡ መዐል ሽራፊ ጊዜ ስታገኝ ድረ-ገጾችን እያሠስክ ሚዛና ሚደፋዉን እየጠቆምክና እየጨለፍክ ለማስነበብህ ልትመሠገን ይገባል (ምስጋናዬ ቢረፍድም)
በጎ አሣቢ አድርጎ የፈጠረህ አምላክ ዕድሜ ይስጥህ
ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር


ጋሼ ዋናው
አቤት ኡ ኡ ኡ የሰሩም እንዲህ አልተመሰገኑ እንኩዋን እኔ የዘረፍኩት:: በጸሀፊዎቹ ስም ምስጋናውን እጅ ነስቼ ተቀብያለሁ:: ሎንዶኖች አልያዝ እያላችሁ አስቸግራችሁዋል:: ወይስ ስራችሁ ራሱ እንግሊዝ ነው:: አንድ ጊዜ ጃርሶ ሞት ባይኖር ኪሩቤል ኢንተርቪው ሲደረግለት ሰምቼ ሎንዶንን ገነት ነው ያደረጋት:: ስለ ሀይድ ፓርክም ስለ ራስህ ስራዎችም ስለ ስነጽሁፍም አውጋን እስኪ

ለዛሬ ደብለቅለቅ ያሉ የድረ ገጽ አመላካቾች ይሆናል የምጠቁማችሁ::
http://www.ethio-calgary.ab.ca/hibret.html
የኮምኒቲ ድረ ገጽ ነው አማርኛ ስለሆነ ወደድኩላቸው

http://www.amhara.com/HTMLFiles/AmhricLtr.htm
እምምምምም
አንዱ ግጥም እንዲህ ይላል


መድፉም አቧረቀ እንደሰማይ መብረቅ፤

እንደ እግዚኣብሔር ቁጣ፤

ውሃው በመዘውር እሰገነት ወጣ።

ስልኩም ተናገረ፡ ባቡሩም ሰገረ።

ያለ የሌለውን እያግበሰበሰ፡ አዋሽ ላይ ደረሰ።

ምነው አስፈራራኝ ይሄ ጥበባቸው፤

እርሶም፤ ልጆችዎም እኛም አንችላቸው።

እንግሊዝ፡ ፈረንሳይ፡ መስኮብ፡ አሜሪካን ከገቡ አገራችን፤

ቋንቋቸው አይገባን፡ አይገባው ቋንቋችን፤

እኛስ እናልፋለን ዋ ለልጆቻችን።

አነጋገራችው እንደ ጓጉንቸር፤

አመጣጣቸውም ከባህሩ ዳር።

አነጣጣቸውም እንደ ቀይ ስንቡል፤

እኛም አንደርስበት እንዳንገላግል።

እነርሱን አንጥቶ እኛን አጥቁሮን፤

የተኩላ መሎክሴ ሁነው መጡብን፤

እንቧዩን ትርንጎ ብለው ቢሰጡን፤

እኛም ተመገብነው መራራው ጣፍጦን።

ጓዛቸውን ጭነው ከገቡ አገራችን፤

እንዳናስወጣቸው የቱ ጥበባችን፤

ይብላኝ ለሚመጡት ለልጅ ልጆቻችን።

ይብቃ ተዉ ይብቃ፤

የኚህ ተንኮለኞች የመርዘኞች እቃ።

በመርዘኛ አርቄ ድንበር አስከባሪው ነፍጠኛው ተወቃ፤

ልቡን አደከመው ተኝቶ እንዳይነቃ።

ይመናሹ የምትባል አሚና ለአጼ ምኒልክ የገጠመችው።
Copyrights 1999, HRI Corpይህ ግጥምም የተነቀሰበት ከዚህ ታች ያለውም
የፖለቲካ ድረ ገጽ ቢሆንም የአማርኛ ጽሁፎች ስላሉት እዚህ አካትቼዋለሁ። ስንዴውን ከእንክርዳድ መለየት የናንተ ድርሻ ነው።
http://www.eprp.com/party/man_yawra.asp

መልካም ሰንበት ወዳጆቼ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ዛሬም ፀጋዬ ሲዘከር

Postby እንሰት » Mon Dec 10, 2007 7:20 am

http://www.addisadmass.com/Tibeb/news_i ... NewsID=829
የጸጋዬ ስራዎች በሃገር ፍቅር ትንሿ ቲያትር ቤት ለሚቀጥሉት አራት ሳምንታት እንደሚዘከሩ ተዘገበ።

ከአዲስ አድማስ የተተየበ የጸጋዬ ግጥም
ጸጋዬ ገብረ መድህን 1956 - ማስታወሻነቱ ለኢተፋ ዋላጋ

በቃኝ

በቃኝ የኑሮ አጉራህ ጠናኝ
እፎይ እድሜ-አዚሜ ጠራኝ።
አስለመለመ መብራቱ
በሕይወት የመዋተቱ
ከከነግ-ነግ መንከራተቱ
መንከላወስ ልፋቱ...
መከሬ ሻማው ጠፋ
መሸ ቀኔ ሳንቀላፋ።
የዕድሜ-ጀምበሬ ጠለቀች
ቅድመ-ፍጥረቴ አሸለመች
ልደቴ ተረመረመች
ተጭለመለመች በበርኖስ
እንደጭጋግ ዶፍ ጥቀርሻ ተዳፍና የዕድሜዬ ፋኖስ
ጠራኝ የዕድሜ አዚሜ ጠራኝ
እኔም በቃኝ እፎይ በቃኝ
መሸች ጠለቀች ጸሓዬ
የሕይወት ክረምቴ ወጣች ጉም ተላበሰች ጥላዬ
እረፍቷን ተከናነበች ተስለመለመች ዕጣዬ
በቃኝ ትግሌን ተገላገልኩ
ውጣ ውረዴን አከተምኩ
እፎይ ደከምኩ አስለመለምኩ...
ተሸነፍኩ አዎን ተሸነፍኩ
የከበደኝ ጣር ቀለለኝ
ያታከተኝ ያደከመኝ
ያሰለቸኝ እድሜ ተወኝ
እፎይ ቀለለኝ ቀለለኝ...
ባለወር ተራ ተተካ
ተቀበለኝ ትግሌን እንኳ
ማነህ አንተ ባለሳምንት
ያስጠምድህ ባስራ ስድስት
በዕድሜህ ያስጠምድህ...ወይኔ
በልደትህ ያስፈርድህ..መጥኔ
ለኔስ መሽቶልኛል ቀኔ።
በቃኝ የኑሮ አጉራህ ጠናኝ
እፎይ የዕድሜ-አዚሜ ጠራኝ።
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ባቲ » Mon Dec 10, 2007 3:52 pm

ሰላም እንሰትና
ለዚህ ቤቱ ታዳሚዎች ሁሉ

እንሰት ከላይ የአስቀመጥክልን የፀጋዬና በሚኒልክ ዘመነ መንግስት የተገጠመው እንዴት እንዳስደስተኝ ልነግርህ አልችልም:: ከመልከጻዲቅ ጋር እየተቀባበላችሁ ስላሳያችሁን የጥበብ ስራዎች ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ::

የዋርካው ጥቁር እንግዳ ልጅ ባቲ

ኖር ብለናል ! ያችን የአንተና የፓን የታሪክ ጥም ቀሰቀስኩ እንዴ ?
አሁን እኔን ሞኝ አድርገህ ሜሪ ታደሰ በውጭ ሃገር በ BBC Amharic program ምናልባትም በሃገር ውስጥ የመጀመሪያ የአማርኛ ዜና እና ሪፖርት አንባቢ ነበረች እንድልህ ነው አይደል ? እኔ እንደው አልነግርህ


ምን 'እንድልህ' ነው አለው እንሰት ወዳጄ? አሳምረህ አልካት እንጂ:: የልጅቷን ፎቶዋን ለማየት ጉግልን እንደ ጉድ ነበር የጎለጎልኩት:: አለሆነም:: ለምን አትለኝ? ደራሲዎች የሚከየፉባቸው ሰዎች በሁሉ ነገራቸው ለየት ያሉ ናቸው:: ደራሲው በምናቡ የሚያውቃቸውን የሰላምና ፍቅር መላክ መሳይ ሰዎች በአካል ሲራመዱ እንደማየት ነው:: ፊያሜታ የበአሉን ቆንጆ ሳስባት የማውቃት የማውቃት ይመስለኛል:: አቤት ስወዳት:: አንዴ እንግሊዝኛ ስማር የበአሉ የኢትዮጵያ ሴቶችን የሚያቆላምጥበትን አንጋገሮች ፅፌ አስተማሪው ከቢሮው ጠርቶኝ የዚህ ሰው መፅሀፍ ይተርርጎም ነበር ያለኝ::

ስለዘገየሁ ይቅርታ ይደረግልኝ::
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Postby እንሰት » Wed Dec 12, 2007 9:57 am

ባቲ wrote:ሰላም እንሰትና
ለዚህ ቤቱ ታዳሚዎች ሁሉ

እንሰት ከላይ የአስቀመጥክልን የፀጋዬና በሚኒልክ ዘመነ መንግስት የተገጠመው እንዴት እንዳስደስተኝ ልነግርህ አልችልም:: ከመልከጻዲቅ ጋር እየተቀባበላችሁ ስላሳያችሁን የጥበብ ስራዎች ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ::

የዋርካው ጥቁር እንግዳ ልጅ ባቲ

ኖር ብለናል ! ያችን የአንተና የፓን የታሪክ ጥም ቀሰቀስኩ እንዴ ?
አሁን እኔን ሞኝ አድርገህ ሜሪ ታደሰ በውጭ ሃገር በ BBC Amharic program ምናልባትም በሃገር ውስጥ የመጀመሪያ የአማርኛ ዜና እና ሪፖርት አንባቢ ነበረች እንድልህ ነው አይደል ? እኔ እንደው አልነግርህ


ምን 'እንድልህ' ነው አለው እንሰት ወዳጄ? አሳምረህ አልካት እንጂ:: የልጅቷን ፎቶዋን ለማየት ጉግልን እንደ ጉድ ነበር የጎለጎልኩት:: አለሆነም:: ለምን አትለኝ? ደራሲዎች የሚከየፉባቸው ሰዎች በሁሉ ነገራቸው ለየት ያሉ ናቸው:: ደራሲው በምናቡ የሚያውቃቸውን የሰላምና ፍቅር መላክ መሳይ ሰዎች በአካል ሲራመዱ እንደማየት ነው:: ፊያሜታ የበአሉን ቆንጆ ሳስባት የማውቃት የማውቃት ይመስለኛል:: አቤት ስወዳት:: አንዴ እንግሊዝኛ ስማር የበአሉ የኢትዮጵያ ሴቶችን የሚያቆላምጥበትን አንጋገሮች ፅፌ አስተማሪው ከቢሮው ጠርቶኝ የዚህ ሰው መፅሀፍ ይተርርጎም ነበር ያለኝ::

ስለዘገየሁ ይቅርታ ይደረግልኝ::


ኧረ ዘገየሁ የሚያሰኝ ምንም ነገር የለም:: ኮምፕዩተር savvy የሆኑ ወዳጆቻችን ሜሪ ታደሰን from Ethiopian Observer አምጥተው እስኪለጥፉልን ድረስ በምናብህ ሳላት::
አክባሪህ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: ዛሬም ፀጋዬ ሲዘከር

Postby እንሰት » Sun Dec 16, 2007 2:43 am

እንሰት wrote:http://www.addisadmass.com/Tibeb/news_item.asp?NewsID=829
የጸጋዬ ስራዎች በሃገር ፍቅር ትንሿ ቲያትር ቤት ለሚቀጥሉት አራት ሳምንታት እንደሚዘከሩ ተዘገበ።

ከአዲስ አድማስ የተተየበ የጸጋዬ ግጥም
ጸጋዬ ገብረ መድህን 1956 - ማስታወሻነቱ ለኢተፋ ዋላጋ

በቃኝ

በቃኝ የኑሮ አጉራህ ጠናኝ
እፎይ እድሜ-አዚሜ ጠራኝ።
አስለመለመ መብራቱ
በሕይወት የመዋተቱ
ከከነግ-ነግ መንከራተቱ
መንከላወስ ልፋቱ...
መከሬ ሻማው ጠፋ
መሸ ቀኔ ሳንቀላፋ።
የዕድሜ-ጀምበሬ ጠለቀች
ቅድመ-ፍጥረቴ አሸለመች
ልደቴ ተረመረመች
ተጭለመለመች በበርኖስ
እንደጭጋግ ዶፍ ጥቀርሻ ተዳፍና የዕድሜዬ ፋኖስ
ጠራኝ የዕድሜ አዚሜ ጠራኝ
እኔም በቃኝ እፎይ በቃኝ
መሸች ጠለቀች ጸሓዬ
የሕይወት ክረምቴ ወጣች ጉም ተላበሰች ጥላዬ
እረፍቷን ተከናነበች ተስለመለመች ዕጣዬ
በቃኝ ትግሌን ተገላገልኩ
ውጣ ውረዴን አከተምኩ
እፎይ ደከምኩ አስለመለምኩ...
ተሸነፍኩ አዎን ተሸነፍኩ
የከበደኝ ጣር ቀለለኝ
ያታከተኝ ያደከመኝ
ያሰለቸኝ እድሜ ተወኝ
እፎይ ቀለለኝ ቀለለኝ...
ባለወር ተራ ተተካ
ተቀበለኝ ትግሌን እንኳ
ማነህ አንተ ባለሳምንት
ያስጠምድህ ባስራ ስድስት
በዕድሜህ ያስጠምድህ...ወይኔ
በልደትህ ያስፈርድህ..መጥኔ
ለኔስ መሽቶልኛል ቀኔ።
በቃኝ የኑሮ አጉራህ ጠናኝ
እፎይ የዕድሜ-አዚሜ ጠራኝ።


ባለፈው እንዳልኩዋችሁ ጸጋዬ ተዘክሯል:: http://www.addisadmass.com/Tibeb/news_i ... NewsID=833
የባለቅኔው የጸጋዬ ገብረመድህን ምሽት December 15, 2007 በሃገር ፍቅር ተካሄደ ከላይ ባለው ድረ ገጽ አመላካች ይጠቁሙና ይዝናኑ።
ይድረስ ለወንድሜ ለማላውቅህ ከሚለው ግጥሙ ጋዜጣው የቀነጨበው
...አገው ነህ ወይስ ሺናሻ
ቅማንቴ ነህ ወይ ፈላሻ
ስምህ የሆነብን ግርሻ
ግራ ጎንደር ነህ መተከል
ባላዋቂ የምላስ ቅርስ የዘር ንፍገት ስትቀበል
ያለእዳህ ስምህ ሲበከል
እምትችል እምትቀበል እማትሞት
እማትነቀል
ማነህ
ቆለኛ ሸክላ ሰሪ ነህ
ያገር እድር ያገለለህ...


መልካም ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ዋናው » Sun Dec 16, 2007 4:57 am

እንሰት wrote:

ጋሼ ዋናው
ሎንዶኖች አልያዝ እያላችሁ አስቸግራችሁዋል:: ወይስ ስራችሁ ራሱ እንግሊዝ ነው:: አንድ ጊዜ ጃርሶ ሞት ባይኖር ኪሩቤል ኢንተርቪው ሲደረግለት ሰምቼ ሎንዶንን ገነት ነው ያደረጋት:: ስለ ሀይድ ፓርክም ስለ ራስህ ስራዎችም ስለ ስነጽሁፍም አውጋን እስኪ


ሠላም እንሠት
እንደተለምደው ምልከታህን ከማድነቄ ግርጌ እቺን ጥያቄህን መዘለሌ ዛሬ ትዝ ቢለኝ ነው....
ስለለንደን የጋሽ ጃርሶን ያህል ባይሆንም ያቅሚቲን አውቃታለው.... እዞርባታለው በጣም ነው ምወዳት... ከነሠካራም ሕዝቦቿ ጋር.... ከዓይናውጣ እንስቶቿ ጋር ከሠፋፊ ፓርኮቿ ጋር... ዕድሉን አግኚቼ ካውሮጳም የተወሠኑ ከመካከለኛው ምስራቅም የተወሠኑትን.... ከኤዢያም በከፊል አይቺያለው .... በመልካም ሕዝብነታቸው ሩቅ ምስራቆችን ብወዳቸዉም ብሪታኒያን በስነምግባሯ በሕዝቦቿ ስልጣኔ.... በብዙ ብዙ ጎኗ አስበልጣታለው::
ካለማችን ብዙ ቋንቋ ሚወራባት ተብሎ ካሜሪካንም በልጦ ባላፈው እዛው አገረ-አሜሪካን ላይ በዜና መነገሩን ውቃው ሹክ ብሎን ነበር... ለንደንን ብዙዎቹ ያገራችን ስደተኞች ያማርሯታል እኔ ግን በጣም ነው ምትመቸኝ የጥበብ የዕውቀት አገር ናት:: ስታዝን ባያዝኑልህም ሀዘንህን ያዩልካል ስትስቅ ሳቅክን ይጋሩካል ስትሠክር ስካርህን ያዳምቁልሀላ....
ለንደን ጨለማ ብትሆንም እኔ ቀለም በጥብጬ ብረሀን እፈጥራላታለው ደግሞ ሞኝ ናት ቶሎ ፈገግ ትልልኛለች....
ብሩንም ለፈለገ ከሁሉም አውሮጳ የተሻለች ናት በኑሮ ውድነት ከነቶኪዮ ጎን ብትፈረጅና ያገኘኸውን ብትነጥቅህም...ቅሉ......:: በተረፈ ስለለንደን ... ያንተ የማወቅ ፍላጎትን ገደብ ባላውቀዉም በመጠኑ ጥላ-ዓልባ ልቦለዴ ላይ ገልጪያታለሁ ሽርፍራፊ ጊዜ ሢኖርህ አንብባት::

መልካም ሠንበት
ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby እንሰት » Mon Dec 17, 2007 3:42 pm

ዋናው wrote:
እንሰት wrote:

ጋሼ ዋናው
ሎንዶኖች አልያዝ እያላችሁ አስቸግራችሁዋል:: ወይስ ስራችሁ ራሱ እንግሊዝ ነው:: አንድ ጊዜ ጃርሶ ሞት ባይኖር ኪሩቤል ኢንተርቪው ሲደረግለት ሰምቼ ሎንዶንን ገነት ነው ያደረጋት:: ስለ ሀይድ ፓርክም ስለ ራስህ ስራዎችም ስለ ስነጽሁፍም አውጋን እስኪ


ሠላም እንሠት
እንደተለምደው ምልከታህን ከማድነቄ ግርጌ እቺን ጥያቄህን መዘለሌ ዛሬ ትዝ ቢለኝ ነው....
ስለለንደን የጋሽ ጃርሶን ያህል ባይሆንም ያቅሚቲን አውቃታለው.... እዞርባታለው በጣም ነው ምወዳት... ከነሠካራም ሕዝቦቿ ጋር.... ከዓይናውጣ እንስቶቿ ጋር ከሠፋፊ ፓርኮቿ ጋር.. ብሪታኒያን በስነምግባሯ በሕዝቦቿ ስልጣኔ.... በብዙ ብዙ ጎኗ አስበልጣታለው::
... ለንደንን ብዙዎቹ ያገራችን ስደተኞች ያማርሯታል እኔ ግን በጣም ነው ምትመቸኝ የጥበብ የዕውቀት አገር ናት:: ስታዝን ባያዝኑልህም ሀዘንህን ያዩልካል ስትስቅ ሳቅክን ይጋሩካል ስትሠክር ስካርህን ያዳምቁልሀላ....
ለንደን ጨለማ ብትሆንም እኔ ቀለም በጥብጬ ብረሀን እፈጥራላታለው ደግሞ ሞኝ ናት ቶሎ ፈገግ ትልልኛለች....
ብሩንም ለፈለገ ከሁሉም አውሮጳ የተሻለች ናት በኑሮ ውድነት ከነቶኪዮ ጎን ብትፈረጅና ያገኘኸውን ብትነጥቅህም...ቅሉ......:: በተረፈ ስለለንደን ... ያንተ የማወቅ ፍላጎትን ገደብ ባላውቀዉም በመጠኑ ጥላ-ዓልባ ልቦለዴ ላይ ገልጪያታለሁ ሽርፍራፊ ጊዜ ሢኖርህ አንብባት::

መልካም ሠንበት
ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር


ልጅ ዋናው እኔ በግሌ አንድን መጽሀፍ/ጽሁፍ ከ ለ April 2006 - December 2007 ጠብቆ ለማንበብ ትግስቱ የለኝም:: ያው "ጥላ አልባ" ሲያልቅ አነባለሁ ብዬ እጆቼን አጣጥፌ ተቀምጬ ነበር:: በጥቆማህ መሰረት በወፍ በረር እይታ ቃኝቼ ውልቅ ብያለሁ::
ያንተም የሎንዶን አስተያየት ዋዛ ነው እንዴ? እንዴት እንደተደሰትኩ አትጠይቀኝ:: ጥሩ ተመልክተሀታል::
እስኪ ከላይ ያልከውን እንደ እንግዳ እየው:: ሰውኛ ነው ሎንዶንን ያናገርካት::
ለምስጋናው ከወገቤ እጥፍ ከጉልበቴ ሸብረክ ብያለሁ::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

የድረ ገጽ ጅማሮ

Postby እንሰት » Mon Dec 17, 2007 3:45 pm

ይቺን ድረ ገጽ እስኪ ለዛሬ ይዝናኑባት
http://www.hyperscheme.ch/homeless/inde ... &Itemid=86
ኢትዮጵያውያን በስዊዘርላንድ
- የድረ ገጹ ስም

ቅንጣቢ ከድረ ገጹ
የሚጥሙ ልዩ ልዩ ሙዚቃዎችን ይስሙ!
እቤት ካሉኝ አንዳንድ ሙዚቃዎች ቀላቅዬ ለኢትዮጵያ ተነሺ አንባቢዎች ለማዝናናትና ለማስተዋወቅ ነው፡፡
ሙዚቃዎቹን ለማጫወት እንደሌሎቹ ሪይል ፕላየር፣ ዊንዶውስ ሜዲያ ፕላየር፣ ዊን አምፕ አያስፈልገዎትም!!! የፈለጉትን የሙዚቃ አይነት ብቻ ጠቅ ያድርጉ፤ እርስዎንም ላለማስቸገር ሙዚቃው በራሱ ይጫወታል!! ያለምንም ኮተት፡፡ በቀላሉ!!
ሙዚቃዎቹን ከወደዷቸው ባሉበት የአለም ክፍል አካባቢ ፈላልገው መግዛት ነው፡፡ በተረፈ ግን እነዚህን የሚጥሙ ሙዚቃዎች "ኢትዩጵያ ተነሺ" ላይ በመስማትዎ እንደሚዎዱት ተስፋ አለኝ፡፡ ይከስክሱ አ ታዲያ!


ማሳሰቢያ፤ የተሻለ፤ የሚያረካና ጆሮ የማይቆረቁር ሙዚቃ መስማት ከፈለጉ ቢያንስ ጥሩ የድምፅ መጉያ ያስፈልግዎታል፡፡ ውድ አይደለም፡፡ ያስቡበት!
ሙዚቃ ከኢትዮጵያ፣ ከማሊ፣ ከጃማይካና ካሜሪካ፡፡ ይከስክሱ!

ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች፡፡

የሚጥሙ ልዩ ልዩ መሳሪያ ቅንብር ሙዚቃዎች ከኢትዮጵያ፡፡

የሚጥሙ የማሲንቆ፣ የከበሮና ዋሽንት ሙዚቃዎች ከኢትዮጵያ!

የሚጥሙ ሙዚቃወች ከኢትዮጵያ፣ ማሊና ኩባ


መልካም የስራ ሳምንት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

እንሰት

Postby ዋኖስ » Mon Dec 17, 2007 5:31 pm

እንሰት በቅድሚያ ምሥጋናዬ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ላቅ ያለነው!! ይህ ዌብ ሳይት ሙዚቃዎቹ እንዴት እንደተመቹኝ! ጥንታዊ ነገሮች/ምርጥ የእኛው ሥራዎቻችንን/ በጣም እወዳለሁ! አመሰግናለሁ! በርታ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ocean12 » Tue Dec 18, 2007 2:33 am

ሁልጊዜ እዚህ በመጣሁ ቁጥር አንድ ደስ የሚል ነገር
ነው ይዤ የምሄደው...
አይዞን እንሰት...እንዲህ ፍልፍል እይደረክ የምታመጣቸው
አድራሻዎች ሁሉ የሚመቹ ናቸው....
እንዲህ ድምጼን ባላሰማም የማልመጣ እንዳይመስልህ
...ብቅ ሳልል አላድርም...ቅቅቅቅ
ሰላም ጊዜ...
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby እንሰት » Wed Dec 19, 2007 3:50 pm

ልጅ ዋኖስ እንዲህ ቡራኬ ናኘ
እንሰት በቅድሚያ ምሥጋናዬ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ላቅ ያለነው !! ይህ ዌብ ሳይት ሙዚቃዎቹ እንዴት እንደተመቹኝ ! ጥንታዊ ነገሮች /ምርጥ የእኛው ሥራዎቻችንን / በጣም እወዳለሁ ! አመሰግናለሁ ! በርታ

እኛም አሜን አሜን አልን - ሁላችንንም ይመቸን

ocean12 አለሁ አልጠፋሁም ሊለን የሰላምታ እጁን በትየባ ቁልፎቹ ላይ ቢያሳርፈው እንዲህ ተነበበ::
ሁልጊዜ እዚህ በመጣሁ ቁጥር አንድ ደስ የሚል ነገር
ነው ይዤ የምሄደው ...
አይዞን እንሰት ...እንዲህ ፍልፍል እይደረክ የምታመጣቸው
አድራሻዎች ሁሉ የሚመቹ ናቸው ....
እንዲህ ድምጼን ባላሰማም የማልመጣ እንዳይመስልህ
...ብቅ ሳልል አላድርም ...ቅቅቅቅ
ሰላም ጊዜ ...

ሰላም ጊዜ ለሁላችን። ተፍልፍሎ የተበላ ይመቻል። ሳል የለውም። በመደሰትህ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ::

በዋናው ጋባዥነት
ስለለንደን ... ያንተ የማወቅ ፍላጎትን ገደብ ባላውቀዉም በመጠኑ ጥላ -ዓልባ ልቦለዴ ላይ ገልጪያታለሁ ሽርፍራፊ ጊዜ ሢኖርህ አንብባት ::

መልካም ሠንበት
ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር


ለንደንን በጓዳ በር ዘው አልንባት። ማንን ይዘን ወጣን? መንግስቱ ለማን በድጋሚ። የለንደን ቅኝታችን ወደ School of Oriental and African Studies ወሰደንና የዛሬ 39 አመት ትምህርት ቤቱ በመጽሄቱ የዘገበውን እንዲህ አየን።

‘Under the clear moon’-
An Amharic poem


በጠራ ጨረቃ
በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
ዓይኖቿ እያበሩ እንደ ከዋክብት
«ሳማት! ሳማት!» አሉት «ዕቀፍ! ዕቀፋት።»
አላወላወለም ወጣቱ ታዘዘ
ወገቧን አንገቷን በእጅና እጁ ያዘ
ከንፈሩ በረአድ ወደ አፏ ተጠጋ
ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ የጉማሬ አለንጋ
ጆሮ ግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ።
በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
ዋ ጀማሪ መሆን! ዋ ተማሪነት
ዋ ትእዛዝ መፈጸም ዋ ምክር መስማት!


ይህ ግጥም እኛ ባለፈው ካነበብነው ትንሽ ለየት ቢልም ገጣሚም ተርጓሚም የሞቱበትን ይህን ግጥም ደግመን ቃኘነው። የ Michael Coke በጠራ ጨረቃ እንዲህ ይነበባል።

Under the clear moon deep in the night,
While like the stars her eyes shone bright
‘Kiss her! Kiss her! Embrace her!’ they said;
His purpose was this, and the youth was compelled-
Her waist and her neck in his arms he held,
And his lips drew up to her mouth in dread.
Although her pointed thorn-like breasts were firm,
He felt her slap across his temples burn.
As her whip-like hand began to fight-
Under the clear moon, deep in the night:
Woe to the biginner, and to the learner woe,
Oh, to carry out orders, and to advice to know!


ሰላም ሁኑ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests