የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby መልከጻዲቅ » Thu Dec 20, 2007 7:25 pm

:arrow:
Last edited by መልከጻዲቅ on Thu Jul 29, 2010 8:03 pm, edited 1 time in total.
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

የኢትዮጵያ ሳምንት

Postby እንሰት » Fri Dec 21, 2007 3:54 pm

ሰሞኑን ፍተሻዬ ወደ አውሮፓ ወስዶኝ: ጣሊያን ጣለኝ::
አንድ ለየት ያለ ድረ ገጽ አድራሻ አገኘሁና እዚህ ዶልኩት:

http://www.etiopiamagica.it/

እንደምትደሰቱበት በጣም እርግጠኛ በመሆን ነው::
መልካም ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

መልካም ገና

Postby መሪ ወንዝ » Sat Dec 22, 2007 10:55 am

ሠላም እንሰት!የኢትዮጵያን ስነ ጽሁፍ ይዘት እና አካሄድ ለሁሉም ጠቁሞ እና ምንጩን አስፍሮ ማለፉ የሚያስመሰግን ነው::

Image

መጪው የአውሮፓውያን ዘመን የፍቅር እና የሰላም ይሁንልህ:: አንባቢያንም ጭምር::

Image


መልካም ገና
መሪ ወንዝ ከተከዜ (ጎርፉ)
Image
ፍቅር እና ሠላም ለኢትዮጵያ
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=21238
መሪ ወንዝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 470
Joined: Sat May 06, 2006 5:13 am
Location: ኢትዮጵያ

Re: መልካም ገና

Postby እንሰት » Mon Dec 24, 2007 9:11 am

መሪ ወንዝ wrote:ሠላም እንሰት!

የኢትዮጵያን ስነ ጽሁፍ ይዘት እና አካሄድ ለሁሉም ጠቁሞ እና ምንጩን አስፍሮ ማለፉ የሚያስመሰግን ነው::

Image

መጪው የአውሮፓውያን ዘመን የፍቅር እና የሰላም ይሁንልህ:: አንባቢያንም ጭምር::

Image


መልካም ገና
መሪ ወንዝ ከተከዜ (ጎርፉ)

መልካም ገና ለሁላችን::
ምስጋናዬ ይድረስህ::

ለዛሬ ደግሞ ጅምር የሆነ ግን ሲያድግ ቁዋሚ ማመሳከሪያችን ይሆናል ብዬ የማስበውን ድረ ገጽ ልጠቁማችሁ
http://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ትግሬብሆንስ? » Mon Dec 24, 2007 11:06 am

ይች thread በጣም ሰፊ ከመሆንዋም በላይ ብዙ ጥልቀት ያላትና ተዝቆ እምያልቅ እውቀት የተከማቸባት ቀፎ ናት :: በቂ ጊዜ ቢኖረኝ እንዴት ግሩም ነበር !
ለመሆኑ Love unto crypt ፍቅር እስከመቃብር በእንግሊዘኛ ተተርጉማ ቀርባለች ሲባልላት የሰማሁዋት መጽሓፍ ትሆን ? እስዋ ከሆነች በጣም አሪፍ ስምን ነው የሰጡዋት :: ከደራሲው ቤተሰቦች ፈቃድ አግኝቶና: አስፈላጊውን ሮያልቲ ከፍሎ ከሆነ: በርግጥ ተርጓሚው ይመሰገናል :: መግዛት ትፈልጋለህ ወይ: ብሎ አንዱ ዘመድ ነገር በስልክ ጠይቆኝ እንደነበረ ትዝ ስላሰኝች ነው: በመጽሓፍዋ ላይ ብዙ ያተኮርኩት:: ኣሁን ተሎ ገዝተህ ላክልኝ ልለው መስኛለሁ ::
Two are better than one ;
therefore ,
00 > 0 .
ትግሬብሆንስ?
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 406
Joined: Fri Dec 21, 2007 5:27 pm

ግራ ያጋባል

Postby እንሰት » Tue Dec 25, 2007 12:21 am

ትግሬብሆንስ? wrote:...
ለመሆኑ Love unto crypt ፍቅር እስከመቃብር በእንግሊዘኛ ተተርጉማ ቀርባለች ሲባልላት የሰማሁዋት መጽሓፍ ትሆን ? እስዋ ከሆነች በጣም አሪፍ ስምን ነው የሰጡዋት :: ከደራሲው ቤተሰቦች ፈቃድ አግኝቶና: አስፈላጊውን ሮያልቲ ከፍሎ ከሆነ: በርግጥ ተርጓሚው ይመሰገናል :: መግዛት ትፈልጋለህ ወይ: ብሎ አንዱ ዘመድ ነገር በስልክ ጠይቆኝ እንደነበረ ትዝ ስላሰኝች ነው: በመጽሓፍዋ ላይ ብዙ ያተኮርኩት:: ኣሁን ተሎ ገዝተህ ላክልኝ ልለው መስኛለሁ ::


እኔ በወሬ ስሰማ Prof. David Appleyard (የሚባል በ SOAS አማርኛ እና ግእዝ አስተማሪ - የዱክትርና መመሪቂያ ጽሁፉን አማርኛ ላይ በ1975 የሰራና ከዚያም በሁዋላ አገው ቁዋንቁዋዎች ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረገ )መተርጎም ጀምሮ የተወሰኑ ምእራፎችን አዲስ አበባ አምጥቶ ያሳያቸው ወዳጆቹ ነግረውኛል:: ለማንኛውም መጽሀፉ ሲታተም በሲሳይ አየነው ስም ነው:: እንግዲህ አንድ ነገር አለ ማለት ነው::
ስለ ኮፒ መብት እና ሮያሊቲ ባለመብቶቹን አላስፈቀደም ተብሎ አንድ ድረ ገጽ ላይ ከማንበቤ ውጭ ለጊዜው የማውቀው ነገር የለም::
አማርኛውን አንብበኸው ከሆነ ጥሩ ነው እንግሊዘኛውን ማንበቡ ጥሩ ይመስለኛል::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ትግሬብሆንስ? » Wed Dec 26, 2007 1:12 am

እንሰት,
ለሰጠኸኝ መልስ አመሰግናለው:: ፍቅር እስከመቃብርን ከብዙ ዓመታት በፊት እንዳነበብኩዋት ትዝ ይለኛል :: What a shame ...ታሪኩን ምሉ ለምሉ ረስቸዋለው :shock: :: ነገር ግን : ስታነባት ልብህን የምታንሳፍፍ መጽሓፍ እንደሆነች: እስካሁን በደምብ አስታውሳለው::
ዛሬ የጊዜ ጥበት ቢኖረኝም : ፋታ ሲገኝ በንግሊዘኛው ቅጅ ላነባት እሞክራለው :: በድጋሚ ታንክስ !
መልካም የፈረንጅ አዲስ ዓመት ይሁንልህ !
የወንዝህ ልጅ ትግሬብሆንስ?ነኝ ::
Two are better than one ;
therefore ,
00 > 0 .
ትግሬብሆንስ?
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 406
Joined: Fri Dec 21, 2007 5:27 pm

ወደ አማርኛው መልስ

Postby እንሰት » Wed Dec 26, 2007 10:47 am

(1) ንጋት የስነጽስሁፍ መድረክ

ከአደረጃጀታቸው ብዙ ልንማር እንችላለን እና ጎብኙት
[url] http://www.haddisnigat.org/
[/url]

(2) ክለሳ (ፍራሽ እደሳ) - ከዚህ በፊት ላላያችሁት
ነፍሰ ጡር ስንኞች
ከተሰኘው አይነ ስውሩ ገጣሚ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ገ /ዮሐንስ
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22482&start=0&sid=9dd22c54bb89c4ecb85dc393b4c9de9e
የተወሰኑ ግጥሞቹ

22. ወዮላት
ይህች የምታምር
የምሥራቅ ኮረዳ
ተንቆጥቁጣ ደምቃ
በአልቦ በጉትቻ
በድሪ በማርዳ
በትላንት ውብ ሸማ
ዓይኗ ገጿን ጋርዳ
አንድ እግሩዋን በክምር
በረዶ ላይ ሰቅላ
አንዱን በሳት ማግዳ
እንኳን ክዳን ልትፈትል
የጨርቋን አዝራር ቁልፍ
ለመቆለፍ ታክታ
መለመላዋን ብትቀር
ገላዋን አጋልጣ
ለጣይ ለቁር ስጥታ
ኃፍረቷ እንቅልፏ
በኣላፊ በአግዳሚው እየተጎበኘ
"ኧረ ልብሷስ ?" ቢባል
ቁልቁል ተንሸራቶ
ግብፅ ወድቆ ተገኘ ::

65. ለተራች
"እጁን ታጥቦ ሠራት !"
ብለህ ለአድናቆትህ
የጨመርከው እርሾ
ሰሪው የሚታጠብ
መች እጁ ቆሽሾ ?

62. ገዳይ እንግዳ
የአማረ ለምድ ተጎናጽፋ
የውበት ጥርሶቿን ስላ
ወኔዬን ልትቀረጣጥፍ
ቀልቤን አኝካ ልትበላ
ከደሜ ሠርጻ ልትዋኝ
ከኔ ዘንድ መጣች "ተኩላ "::

3) ለጸጋዬ ወዳጆች የአንድ ደቂቃ ቪዲዮ
ለባለቅኔ ጸጋዬ ገ /መድህን (Video)


[url]http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22870&sid=9dd22c54bb89c4ecb85dc393b4c9de9e
[/url]
http://www.youtube.com/watch?v=YhYzrTqkEV8
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

አንድምታ ቁጥር 9

Postby እንሰት » Fri Dec 28, 2007 12:32 pm

ሰላም ለሁላችን
አዲስ እትም ለሰንበት ይዤላችሁ ቀርቤአለሁ:: መነበብ የሚገባው ጽሁፍ ነው::
ምስጋና ለአዘጋጆቹ
ብሩክ እና ኅሩይ አብዱ
ለቅምሻ ያህል እስኪ ከመግቢያው
አንድምታ

አንድምታ በየሶስት ወሩ በኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ክበብ የሚዘጋጅ የስነ ጽሑፍ ልሳን

አንድምታ 9 መስከረም-ኅዳር 2000 ዓ.ም.


ታዲያ ዛሬስ እጃችሁ ከምን ስንላቸው:: ብሩክ እና ኅሩይ እንዲህ ይላሉ
በዚህ እትም ውስጥ ሁለት አንጋፋ ደራሲያን ከአቻዎቻቸው ሥራዎች ጋር ያስተዋውቁናል። አዳም ረታ (የማህሌትና ግራጫ ቃጭሎች ደራሲ) ከጃርሶ ሞት ባይኖር ኪሩቤል “አስኮ ጌታሁን መድበል” አንዱን አጭር ልብወለድ መዞ ይተነትነዋል። ነቢይ መኮንንም (የነጭ ጥቁር ግራጫና ስውር ስፌት ደራሲ) በተራው ከጋሽ ጸጋዬ ገብረመድህን “እሳት ወይ አበባ” የግጥም መድበል ውስጥ ስንኞች እየጠቃቀሰ ያጎርሰናል። የነሱን የመሰለ የውስጥ አዋቂ ሂስ እንደሚለመድ ተስፋ እናደርጋለን።


የአሁኑ እትም ሁለት ጉዳዮች ላይ ብቻ ማተኮሩን የአንድምታ ማውጫ እንዲህ ይጠቁመናል

አስኮ ጌታሁንና ዝምታ (ግምገማ) አዳም ረታ
እሳት ወይ አበባ (ግምገማ) ነቢይ መኮንን


ውድ ዋርካውያን እነሱ እንደተመኙላችሁ

መልካም ንባብ
ብዬ ላሳርጋ
ለድረ ገጹ መጠቆሚያ ይቺን ማያያዣ ይጠቀሙ
http://web.missouri.edu/~asfawa/andemta9.pdf
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: አንድምታ ቁጥር 9

Postby እንሰት » Sat Dec 29, 2007 8:30 am

እንሰት wrote:ሰላም ለሁላችን
አዲስ እትም ለሰንበት ይዤላችሁ ቀርቤአለሁ:: መነበብ የሚገባው ጽሁፍ ነው::
ምስጋና ለአዘጋጆቹ
ብሩክ እና ኅሩይ አብዱ
ለቅምሻ ያህል እስኪ ከመግቢያው
አንድምታ

አንድምታ በየሶስት ወሩ በኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ክበብ የሚዘጋጅ የስነ ጽሑፍ ልሳን

አንድምታ 9 መስከረም-ኅዳር 2000 ዓ.ም.


ታዲያ ዛሬስ እጃችሁ ከምን ስንላቸው:: ብሩክ እና ኅሩይ እንዲህ ይላሉ
በዚህ እትም ውስጥ ሁለት አንጋፋ ደራሲያን ከአቻዎቻቸው ሥራዎች ጋር ያስተዋውቁናል። አዳም ረታ (የማህሌትና ግራጫ ቃጭሎች ደራሲ) ከጃርሶ ሞት ባይኖር ኪሩቤል “አስኮ ጌታሁን መድበል” አንዱን አጭር ልብወለድ መዞ ይተነትነዋል። ነቢይ መኮንንም (የነጭ ጥቁር ግራጫና ስውር ስፌት ደራሲ) በተራው ከጋሽ ጸጋዬ ገብረመድህን “እሳት ወይ አበባ” የግጥም መድበል ውስጥ ስንኞች እየጠቃቀሰ ያጎርሰናል። የነሱን የመሰለ የውስጥ አዋቂ ሂስ እንደሚለመድ ተስፋ እናደርጋለን።


የአሁኑ እትም ሁለት ጉዳዮች ላይ ብቻ ማተኮሩን የአንድምታ ማውጫ እንዲህ ይጠቁመናል

አስኮ ጌታሁንና ዝምታ (ግምገማ) አዳም ረታ
እሳት ወይ አበባ (ግምገማ) ነቢይ መኮንን


ውድ ዋርካውያን እነሱ እንደተመኙላችሁ

መልካም ንባብ
ብዬ ላሳርጋ
ለድረ ገጹ መጠቆሚያ ይቺን ማያያዣ ይጠቀሙ
http://web.missouri.edu/~asfawa/andemta9.pdf


ያው እናንተን እንደጋበዝኳችሁ እኔም የነቢይ መኮንንን ጸጋዬን አነበብኩት። የአንድምታ አዘጋጆች እንዲህ ነበር ያሉን “ነቢይ መኮንንም (የነጭ ጥቁር ግራጫና ስውር ስፌት ደራሲ) በተራው ከጋሽ ጸጋዬ ገብረመድህን “እሳት ወይ አበባ” የግጥም መድበል ውስጥ ስንኞች እየጠቃቀሰ ያጎርሰናል። የነሱን የመሰለ የውስጥ አዋቂ ሂስ እንደሚለመድ ተስፋ እናደርጋለን።”

ነቢይም የጸጋዬ የሥነ ግጥም ጭብጦች ብሎ ወደ ስምንት የሚሆኑ ርእሶችን ደርድሮ ስለ ጸጋዬ አውርቶናል። እንዲህ በማለት
1.ስለ ማህበረሰባዊ/ ስለ ግለሰባዊ ችግሮች
2.ጥበብን በተመለከተ ቁርቋሬውን ስለማሳየት
3.ፖለቲካዊ መልዕክቶች/ይዘት ያላቸው ሸንቋጮች
4.የፍቅር ጉዳይ
5.የታሪክና ጀግንነት ጉዳይ
6.በህይወት ፍልስፍና
7.ባህላዊ እሴት
8.መልክዓምድራዊ ይዘት
ህምምም ግን ግጥም የጸጋዬም ሆነ የማንም ሰው ግጥም ከነዚህ ጉዳዮች ውጪ ምን ሊያወራ ኖሯል?
ምናልባት ነቢይ እንደ ቅርበቱ ለጸጋዬ ማለት ነው።መመለስ የነበረበት ጸጋዬን ገንኖ ያወጣው፤ ከሌሎቹ የለው ምንድን ነው የሚለውን ቢመልስ ነበር። እነዚህን ስምንት ነጥቦች ለመዘርዘር ነቢይን መሆን አያስፈልገንም።ማንኛችንም ተራ አንባቢያን ልናደርገው የምንችለው መስሎ ታይቶኛል። እስኪ ዋርካውያን የምትሉት ካላችሁ አንድ በሉ።
መልካም ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ገሞራው

Postby እንሰት » Sat Dec 29, 2007 7:44 pm

ገሞራው - ሃይሉ ገብረ ዮሃንስ


ስለ ሀይሉ ገብረ ዮሃንስ ብዙ ሊባል ቢችልም በ1950ዎቹ መጨረሻ ብቅ ያለ ገናና ግን ሞገደኛ ጸሃፊ ነው። ዝነኛ ያደረገውም አንደኛ እጅግ አምራች ጸሃፊ መሆኑ በሌላ አባባል የማይነጥፍ ብእሩ ሲሆን፤ ሁለተኛ በዘመኑ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግጥም ውድድር ላይ ያቀርባቸው የነበረ የጊዜውን ፖለቲካውን ትኩሳት የሚለኩ ግጥሞቹ፤ እና ሶስተኛው የታተመው የግጥም መጽሃፉ በረከተ መርገም ናቸው። እድሉ ካጋጠመኝ እና መጽሃፉ (የገሞራው) እጄ ከገባ “ስለ እናትክን በሉልኝ” አባይን ነው አንድ ቀን አጫውታችሁ ይሆናል።

ግጥሞቹ ብሶት ራሮት ቢበዛባቸውም ከ1980 ጀምሮ ደግሞ በተለያዩ መጽሄቶች አጫጭር መጣጥፎች ያወጣል። ብዙዎች እዚህ ዋርካም ሲሚሰክሩለት ከወዳጆቹ የሚሰነብት ነው ይሉታል።በግል ሳስበው ገሞራውን ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገው ልክ እንደ ዋርካው ወንድማችን ዋኖስ - ዳሞት ቃላት ይበረክቱለታል።

በቋንቋው ህግ ጥላ ስር አዳዲስ ቃላትም ያመርታል፤ ህምምም ይፈበርካል ማለት ይሻል ይመስለኛል። ይህም ደግሞ ለቋንቋው ማደግ አይነተኛ ሚና ይጫወታል። ስለ ነጭ ዘረኛነት፤ ነጭ አንዴ ከመረዘ እንደ ኮሶ ተጣብቶ አለመልቀቁን ለማስረዳት የተጠቀመበት ቃል አሁንም ድረስ ጆሮዬ ላይ ያቃጭላል። “ነጩሌው ለከፈኝ ነው” ያለው። ነጭ -- ነጩሌ - አቆላምጦ ሲጠራው ግርም አያሰኝ.....ም?እስኪ ወደ ሌላው ጉዳይ ከመሄዳችን በፊት ከገሞራው ድረ ገጽ ያገኘኋቸውን አንዳንድ አንኳሮቹን በዘመን ቅደም ተከተላቸው እነሆ ልበላችሁ።

(1)ነቅናቂው ነቅንቆ ቢያነቃንቀው
የሚያነቃንቀው ነቅንቆ ጣለው (1956አ.ም.)

(2)ያሰብከው አላማ አልሆን ብሎህ ሲከሽፍ ሁኔታው ሲጠጥር
ጠጣሩ እንዲላላ በረገበው በኩል የላላውን ወጥር (1959 አ.ም.)

(3)በመንቃት ላይ ባሉ ፍጡራን መካከል
ህይወት የምንለው እንደ ጥሬ እህል
በኑሮ ምጣድ ላይ ቢቆላ ቢማሰል
የበሰለው ያራል ጥሬው እስኪበስል (1961 አ.ም.)

(4)መርዝን በመርዝነት ስለመርዝ መመረዝ
የመርዙን ለመርዙ በመርዙ ማስመረዝ (1961አ.ም.)

የ ገሞራው - ሃይሉ ገብረ ዮሃንስ ድረ ገጽ
http://www.angelfire.com/hi4/Gemoraw/
ሊታይ የሚገባው ይመስለኛል
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Sun Dec 30, 2007 5:51 am

ሰላም እንሰት 8)
መቼም የተረሱትንና ያልታወቁትን ጸሀፍት ስራቸውን እየፈለክ የብእራቸውን ትሩፋት ስለምታቆአድሰን ምስጋናዬ ይድረስህ... :idea: በጎመራው ጽሁፍ ውስጥ አንተ እንደጠቀስከው "ነጩሌው...ለከፈኝ...." ያለው አራዳዊ አባባል....ቦታውን አግኝቶ ስነ-ጽሁፍ ውስጥ ሲገባ ድንጋይ የሚሰብር አገላለጽ ሆኖ አግኝቼዋለሁ:: ሌላው እኔን ፈገግ ያደረገኝ በ11ኛ ተራ ላይ የተቀመጠው ምስለኔ ነው.....እንዲህ ይላል......
አለቅጥ ቢጠማኝ....መጠጥ.....አስፈልጎኝ........
ከፍቼ ልጠጣ ጠርሙስ ጠጅ አጋጥሞኝ....
በሀይል....ተቀርቅሮ....ያ "ቡሽ"...አስቸገረኝ.....
ለጆርጅ...ቡሽ...ይሄ ቢተረጎምላቸው...ጥሩ...ነበር. :lol:
መልካም ምሽት/ቀን እመኛለሁ.. 8)
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Re: ገሞራው

Postby እንሰት » Tue Jan 01, 2008 6:08 pm

እንሰት wrote:ገሞራው - ሃይሉ ገብረ ዮሃንስ


ስለ ሀይሉ ገብረ ዮሃንስ ብዙ ሊባል ቢችልም በ1950ዎቹ መጨረሻ ብቅ ያለ ገናና ግን ሞገደኛ ጸሃፊ ነው። ዝነኛ ያደረገውም አንደኛ እጅግ አምራች ጸሃፊ መሆኑ በሌላ አባባል የማይነጥፍ ብእሩ ሲሆን፤ ሁለተኛ በዘመኑ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግጥም ውድድር ላይ ያቀርባቸው የነበረ የጊዜውን ፖለቲካውን ትኩሳት የሚለኩ ግጥሞቹ፤ እና ሶስተኛው የታተመው የግጥም መጽሃፉ በረከተ መርገም ናቸው። እድሉ ካጋጠመኝ እና መጽሃፉ (የገሞራው) እጄ ከገባ “ስለ እናትክን በሉልኝ” አባይን ነው አንድ ቀን አጫውታችሁ ይሆናል።

ግጥሞቹ ብሶት ራሮት ቢበዛባቸውም ከ1980 ጀምሮ ደግሞ በተለያዩ መጽሄቶች አጫጭር መጣጥፎች ያወጣል። ብዙዎች እዚህ ዋርካም ሲሚሰክሩለት ከወዳጆቹ የሚሰነብት ነው ይሉታል።በግል ሳስበው ገሞራውን ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገው ልክ እንደ ዋርካው ወንድማችን ዋኖስ - ዳሞት ቃላት ይበረክቱለታል።

በቋንቋው ህግ ጥላ ስር አዳዲስ ቃላትም ያመርታል፤ ህምምም ይፈበርካል ማለት ይሻል ይመስለኛል። ይህም ደግሞ ለቋንቋው ማደግ አይነተኛ ሚና ይጫወታል። ስለ ነጭ ዘረኛነት፤ ነጭ አንዴ ከመረዘ እንደ ኮሶ ተጣብቶ አለመልቀቁን ለማስረዳት የተጠቀመበት ቃል አሁንም ድረስ ጆሮዬ ላይ ያቃጭላል። “ነጩሌው ለከፈኝ ነው” ያለው። ነጭ -- ነጩሌ - አቆላምጦ ሲጠራው ግርም አያሰኝ.....ም?

እስኪ ወደ ሌላው ጉዳይ ከመሄዳችን በፊት ከገሞራው ድረ ገጽ ያገኘኋቸውን አንዳንድ አንኳሮቹን በዘመን ቅደም ተከተላቸው እነሆ ልበላችሁ።

(1)ነቅናቂው ነቅንቆ ቢያነቃንቀው
የሚያነቃንቀው ነቅንቆ ጣለው (1956አ.ም.)

(2)ያሰብከው አላማ አልሆን ብሎህ ሲከሽፍ ሁኔታው ሲጠጥር
ጠጣሩ እንዲላላ በረገበው በኩል የላላውን ወጥር (1959 አ.ም.)

(3)በመንቃት ላይ ባሉ ፍጡራን መካከል
ህይወት የምንለው እንደ ጥሬ እህል
በኑሮ ምጣድ ላይ ቢቆላ ቢማሰል
የበሰለው ያራል ጥሬው እስኪበስል (1961 አ.ም.)

(4)መርዝን በመርዝነት ስለመርዝ መመረዝ
የመርዙን ለመርዙ በመርዙ ማስመረዝ (1961አ.ም.)

የ ገሞራው - ሃይሉ ገብረ ዮሃንስ ድረ ገጽ
http://www.angelfire.com/hi4/Gemoraw/
ሊታይ የሚገባው ይመስለኛል


መልከ ጻድቅ ምስጋናዬ ይድረስህ::
እንዚህን ማያያዝዎች ተጠቅማችሁ የገሞራውን የቅርብ ጊዜ ግጥሞች ተመልከቱዋቸው::
መልካም ንባብ
1. አንደበት
http://www.angelfire.com/hi4/Gemoraw/ANDEBET.jpg
2. የህይወት ታሪኩ
http://www.angelfire.com/hi4/Gemoraw/hailobioc.htm
3. የሙታኑ ህያዋን ጦማራት (ደብዳቤዎች)
http://debteraw.files.wordpress.com/200 ... etters.pdf
4. ለማላከብርዎ ቀማተኛ
http://debteraw.files.wordpress.com/200 ... moraw1.pdf
5. ቅኔ ዘኮፊ ቡና
http://debteraw.files.wordpress.com/200 ... e-kofe.pdf
6. ቅኔ በየዘርፉ
http://debteraw.files.wordpress.com/200 ... rtukan.pdf
7. ቅኔ ዘጌሾ
http://debteraw.files.wordpress.com/200 ... _gesho.pdf
8. ቅኔ ዘጥሻ
http://www.debteraw.com/Gemorawu-Qene-Zetisha.pdf
(ይህ የምታዩት የድረ ገጽ ማያያዣ አልሰራልኝም) እስኪ ይህንን የታችኛውን ማያያዣ ሞክሩት
http://debteraw.files.wordpress.com/200 ... etisha.pdf
9. ዝንብም እንደ ንቦ
http://debteraw.files.wordpress.com/200 ... edited.pdf
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

አዲስ ድረ ገጽ

Postby እንሰት » Fri Jan 04, 2008 4:33 pm

ባለፈው የድረ ገጽ እይታችን ገሞራውን ነበር ያየነው። አብዛኞቹ የግለሰብ ድረ ገጾች ቶሎ ቶሎ አይታደሱም። አመትም ሁለት አመትም እንዲዚያው ሆነው ነው የምናገኛቸው። የዛሬው ግን ትንሽ ለየት ያለ ነው።
አንደኛ የዋርካ ተሳታፊ ነው።
ሁለተኛ በትርፍ ጊዜ ስራዎቹ ሁለገብ ነው። ከስነጽሁፍ ጀምሮ ሙዚቃው ባህሉ የኢትዮጵያ ታሪክም አይቀረው። እነዚህን ሁሉ በደንብ አካትቶ የያዘ ድረ ገጽ ነው። ከጓደኞቹም ጋር የሚወያይበት መድረክም (blog) አለው። ተሳተፉ ይለናል።
ሶስተኛ በየጊዜው ይታደሳል እናም አዳዲስ ነገሮችን እናይበታለን።
አይታችሁ ፍረዱዋ። አስተያየታችሁን እዚህም እዚያም እንድታሰፍሩ ታድማችሁዋል።
ማነው? እንቆቅልሽ

[url]www.myspace.com/ethiopiawi
[/url]


መልካም ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: አዲስ ድረ ገጽ

Postby እንሰት » Fri Jan 04, 2008 5:16 pm

ቱ ሳናድድ አለ ባለሱቅ
እንሰት wrote:ባለፈው የድረ ገጽ እይታችን ገሞራውን ነበር ያየነው። አብዛኞቹ የግለሰብ ድረ ገጾች ቶሎ ቶሎ አይታደሱም። አመትም ሁለት አመትም እንዲዚያው ሆነው ነው የምናገኛቸው። የዛሬው ግን ትንሽ ለየት ያለ ነው።
አንደኛ የዋርካ ተሳታፊ ነው።
ሁለተኛ በትርፍ ጊዜ ስራዎቹ ሁለገብ ነው። ከስነጽሁፍ ጀምሮ ሙዚቃው ባህሉ የኢትዮጵያ ታሪክም አይቀረው። እነዚህን ሁሉ በደንብ አካትቶ የያዘ ድረ ገጽ ነው። ከጓደኞቹም ጋር የሚወያይበት መድረክም (blog) አለው። ተሳተፉ ይለናል።
ሶስተኛ በየጊዜው ይታደሳል እናም አዳዲስ ነገሮችን እናይበታለን።
አይታችሁ ፍረዱዋ። አስተያየታችሁን እዚህም እዚያም እንድታሰፍሩ ታድማችሁዋል።
ማነው? እንቆቅልሽ
[url]www.myspace.com/ethiopiawi
[/url]

መልካም ሰንበት


ይህንን ፖስት አድርጌ እንደጨረስኩ ለዋርካ ወዳጆቼ የሚገረብ አግኝቼ ተመለስኩ። ገራባውን አድቁታ ዋናው እስኪገኝ::
ከዚህ በፊት ስለ ጸጋዬ ይህንን ድረ ገጽ እንድጎበኘን ታስታውሳላችሁ
Posted: Mon Dec 10, 2007 7:20 am Post subject: ዛሬም ፀጋዬ ሲዘከር
http://www.addisadmass.com/Tibeb/news_i ... NewsID=829
የጸጋዬ ስራዎች በሃገር ፍቅር ትንሿ ቲያትር ቤት ለሚቀጥሉት አራት ሳምንታት እንደሚዘከሩ ተዘገበ።

ከአዲስ አድማስ የተተየበ የጸጋዬ ግጥም
ጸጋዬ ገብረ መድህን 1956 - ማስታወሻነቱ ለኢተፋ ዋላጋ

በቃኝ

በቃኝ የኑሮ አጉራህ ጠናኝ
እፎይ እድሜ -አዚሜ ጠራኝ።
አስለመለመ መብራቱ
በሕይወት የመዋተቱ
ከከነግ -ነግ መንከራተቱ
መንከላወስ ልፋቱ ...
መከሬ ሻማው ጠፋ
መሸ ቀኔ ሳንቀላፋ።
የዕድሜ -ጀምበሬ ጠለቀች
ቅድመ -ፍጥረቴ አሸለመች
ልደቴ ተረመረመች
ተጭለመለመች በበርኖስ
እንደጭጋግ ዶፍ ጥቀርሻ ተዳፍና የዕድሜዬ ፋኖስ
ጠራኝ የዕድሜ አዚሜ ጠራኝ
እኔም በቃኝ እፎይ በቃኝ
መሸች ጠለቀች ጸሓዬ
የሕይወት ክረምቴ ወጣች ጉም ተላበሰች ጥላዬ
እረፍቷን ተከናነበች ተስለመለመች ዕጣዬ
በቃኝ ትግሌን ተገላገልኩ
ውጣ ውረዴን አከተምኩ
እፎይ ደከምኩ አስለመለምኩ ...
ተሸነፍኩ አዎን ተሸነፍኩ
የከበደኝ ጣር ቀለለኝ
ያታከተኝ ያደከመኝ
ያሰለቸኝ እድሜ ተወኝ
እፎይ ቀለለኝ ቀለለኝ ...
ባለወር ተራ ተተካ
ተቀበለኝ ትግሌን እንኳ
ማነህ አንተ ባለሳምንት
ያስጠምድህ ባስራ ስድስት
በዕድሜህ ያስጠምድህ ...ወይኔ
በልደትህ ያስፈርድህ ..መጥኔ
ለኔስ መሽቶልኛል ቀኔ።
በቃኝ የኑሮ አጉራህ ጠናኝ
እፎይ የዕድሜ -አዚሜ ጠራኝ።


የዋርካዋ ዋርካ (=አድባር) ናፍቆት እንዲህ ታሳርገዋለች ከግል እይታዋ አንጻር። ናፍቆት Posted: Wed Jan 02, 2008 9:55 am Post subject: ስለ ሰንበት ውሎዋ እንዲህ አለች።
ትናንት ማታ ቆንጆ ምሽት አሳለፍኩ :: በሀገር ፍቅር ትንሽዋ አዳራሽ 'የጸጋዬ ገ /መድህን መዘከሪያ ምሽት ' የመጨረሻው ክፍል ነበር :: ያለፉትን ሶስት ሳምንቶች የመግቢያ ትኬት ለማግኘት ባለመቻል ችግር ማየት አልቻልኩም ነበር :: በብር አይደለም የሚገባው - በ ግብዣ ብቻ ነው :: ከሱ በፊት የመንግስቱ ለማ መዘከሪያ ለ 4 ሳምንት ተላልፎ አምልጦኛል - ያኔ እንኳን ስለፕሮግራሙም መኖር አልሰማሁም ነበር :: ዋና አዘጋጅና አቅራቢዎቹ አበበ ባልቻ - ፍቃዱ ተ /ማርያም - ነቢዩ መኮንን ነበሩ - አንድ በሀይሉ የሚባልም ኮሚክ ነገር በየመሀሉ ሲያስፈግገን አመሸ ::

በምሽቱ የጸጋዬ ምርጥ ስራዎች ቀርበዋል ... ስለሱ ግጥም አጻጻፍም አስተያየት በነቢዩ ቆንጆ ተደርጎ ተተንትኗል - ደስ ያለኝ ደሞ ከዚህ በፊት የትም ሚዲያ ላይ ያልቀረበ ፊልም ቀርቦ ነበር ... ጸጋዬ አሜሪካን አገር ሆኖ የተቀረጸው ..... probably in his last days ...

እና እዛ ላይ በየነጫጭባ አገር ህይወታቸው ካለፈው ብርቅ ኢትዮጵያውያን መካከል ለ እስኩንድር በጎሲያና ለገ /ክርስቶስ ደስታ የገጠማቸውን ግጥሞች እንዲሁም እንዴት መጀመሪያ የትና እንዴት እንደተዋወቃቸው ያወራል :: .... ምናምን .....

በጣም አሪፍ ነበር :: ሁለቱም በነጭ አገር 'ወድቀው ተገኙ ' ነው የሚባለው ..... ብሎ ነበር ..... ሰዎቹ በህይወት እያሉ ምን አይነት ሰዎች እንደነበሩም ይናገራል ::

ደስ የሚልም የሚያሳዝንም ምሽት ነበር :: እኔማ በጭራቃ ነገር አይደለሁ ..... አንዳንዴ ለማልቀስ ሁሉ እፈልግ ነበር :: ግን ደሞ የሆነ ውስጥህ .... በቃ የሆነ satisfaction ሲያገኝ ደሞ ይሰማሀል :: እነዛን መሰል ሰዎች 'ከዚህ ' መሆናቸው በራሱ የሚሰጥህ እንትን ነገር አለ .....

ከብዙ በጥቂቱ
ጸጋዬ ካላቸው ...
እስኩንድርን መጀመሪያ ሳገኘው 'እስክንድር ነው እንጂ ለምን እስኩንድር ተባልክ አልኩት ' ..... እሱም 'እስክንድር ልሁል አለ ብለዋል .... ደስ አላላቸውም ብለዋል .... ሲባል ሰማሁና እኔም Je m'en fou! I don't give a shit! አልኩና ስሜን እስኩንድር ብዬ ቀየርኩት " አለኝ ....... እስኩንድር ብዙ ጊዜ I don't give a shit! ብሎ ንግግር መጨረስ ይወድ ነበር ..... እኔም ታድያ ያው 'ሀጠራው ' እለው ነበር ......


****
......

ዝግጅቱ ላይ ..... አበበ ባልቻ ከኦቴሎ .... ፍቃዱ ት /ማርያም ደሞ ከቴዎድሮስ ትያትር ቀንጭበው አቅርበው ነበር ..... ፍቃዱ የቴዎድሮስን የመጨረሻ ንግግር ሲል ለራሴ እስኪገርመኝ ድረስ አፌ አብሮት ያነበንብ ነበር .... እንዲህ እንደተቀረጸብኝ አላውቅም ነበር ..... መጨረሻ ላይ መነባንቡን ሲጨርስ ሰዉ ብድግ ብሎ ጭብጨባውን ማቆም አልተቻለም ነበር :: ያኔስ እንባዬንም ለማቆም አልታገልኩም ::

It was really a memorable night.

******
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... 387b140ae9

አዲስ አድማስም በDecember 29 የድረ ገጽ እትሙ እንዲህ አሳርጎታል
http://www.addisadmass.com/Tibeb/news_i ... NewsID=841

የዚህ ሳምንት እይታችንም እንደገና ሲዘከር www.myspace.com/ethiopiawi
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests

cron