by ትብብር » Sun Dec 16, 2007 9:57 pm
በመጀመሪያ ይህንን ፕሮግራም ያዘጋጀህ ወንድማችን ልትመሰገን ይገባሀል::
የኮምፒዩተራችንን ጤንነት እንዴት እንጠብቃለን?
ይህንን ለመመለስ ችግሮቹን ማወቅ ያስፈልጋል:: የሚከተሉት ምናልባት መነሻ ችግሮች ናቸው::
1. ተጠቃሚው ኢንተርኔት ላይ የተቀመጠን የነጻ ሶፍትዌር ሁሉ ዳውንሎድ ማድረግ::
2. የሴኪዩሪቲ ሶፍትዌር ያላቸውን አጠቃቀም በደንብ አለማወቅና የቫይረስና ስፓይዌር አውቶ-ስካንና ላይቭ-አፕዴት ያላቸውን ጥቅም መርሳት::
3. በጊዜው ሲስተም ኦፕቲማይዜሽን አለማድረግ
4.. ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዲፎልት ክንውኖች የሚኖራቸውን ጉዳት ባለመገለጻቸው ምክንያት የተከፈቱት ፖርቶች ቮነረብሊቲን ሲጋብዙ, ቢያንስ መኖራቸውን እንደ አማራጭ ሲስተሙ ሊጠይቀን ይገባ ነበር:: እነሱን መረዳትና ግልጋሎታቸውንና ጉዳታቸውን መመርመር::
5. ከውጭ ያለንን ግንኙነት ሞኒተር ማድረግ::
ሲሆኑ, በርካታ ሌላም ችግሮች ይኖራሉ ነገር ግን እነዚህ አይነተኛ ናቸው::
መፍትሄ:
1. ለማይክሮሶፍት ሲስተምስ የቀረበ ነጻ ሶፍትዌር አብዛኛው በስያሜ ነጻ ቢሆኑም ከሆነ ፋይናሺያል ድጋፍ ሰጪዎች ግንኙነት አላቸው:: ስለዚህም አንዱ አድቨርታይዝመንት ሲሆን ሌላው ያለንን ብራውዚንግ ልማድ ማጥናትና ከአድቨርታዘርስ ጋር መጋራት ሲሆኑ, ሌላም በርካታ ምክንያቶች ይኖራሉ:: በአሰራር ጸባይ በነጻ የሚታወቀው የሊኒክስ ሶፍትዌርና ለሱ ተብለው የተሰሩ ሶፍትዌሮች ብቻ ናቸው:: ዳዎንሎድ ማድረግ ካለብን, እንደፒሲ መጋዚን ያሉ ግምጋሚዎችን ዳውንሎድ ካምድረጋችን በፊት መመልከት ይጠቅማል::
2. በኮምፒዩተራችን ውስጥ ያሉ ሴኪዩሪቲ ሶፍትዌሮች መስራታቸውን በየጊዜው ሞኒተር ማድረግ, በተለይም ላይቭ-አፕዴት መካሄዱን ማወቅ:: ሌላው ከአንድ በላይ አንታይ-ስፓይዌር ሊኖረን ይችላል ነገር ግን ከአንድ በላይ አንታይ-ባይረስና ፋየርወል ሊኖረን አይገባም:: ከሆነም ኮምፒዩተራችን በድንብ ሊሰራ አይችልም:: ከዚህም ሌላ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 7 ካለን ፊሺንግ ፊልተር (phising filter) የሚባል ፋየርወል አብሮት ይመጣል:: ሌላ ፋየርወል ካለን እሱን ማቆም አለብን::
3. ሲስተም ኦፕትማይዜሽን ለማድረግ ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር እንጀምራለን: ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ሜኒዩ ክሊክ Tools/Internet Options, ከዚያም Delete cookies/Ok, Click Delete Files/Delete all offline folders then OK, ሲጨርስ Delete History/Yes ሲጨርስ ክሊክ Security tab/ ከዚያም አራቱም ዞኖች ዲፎልት ሌቭል ሴታፕ መሆናቸውን ማረጋገጥ:: ከዚያም ከሊክ Connection ከዚያም ግንኙነታችን ሃይ ስፕዲ ከሆነ, ክሊክ LAN Settings ዳያላፕ ከሆነ ከሊክ Settings, ምንም ፕሮክሲ ሴታፕ አለመሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል::
ከዚያም ዲፍራግመንቴሽን ያስፈልገው እንደሆነ መመርመር:: ይህንን ለማድረግ ክሊክ Start/All Programs/Accessaries/System Tools/Disc Defragmentor ከዚያም ክሊክ Analyze የሚለውን, ሲስተሙን ከመረመረ በኍላ ፍራግመንትድ ከሆነ ዲፍራግመንቴሽን ማድረግ እንዳለብን ይነግረናል, አለበለዚያም አይስፈልገውም ብሎ ይመክረናል::
4. ሲስተሙ በተለምዶ የከፈታቸው ፖርቶች ሆን ተብለው ተጠቃሚውን ለመጉዳት ሳይሆን የተለያዩ ሰርቪሶችን ማይክሮሶፍት ለመስጠት የከፈታቸው በሮች ናቸው:: ለምሳሌም ዊንዶውስ አፕዴት ሲካሄድ አውቶማቲካሊ ሳናየው ነው የሚመጣው:: ስለዚህም ሲስተማችን ከማይክሮሶፍት ሰርቨሮች ጋር ኢንተራክቲቭሊ ይሰራል ማለት ነው:: ነገር ግን እነዚህ ለመልካም የተከፈቱ በሮች ለቮንረብሊቲ በር ናቸው:: ስለዚህም የሚከተሉትን ወይ ማገድ ወይም በጥንቃቄ መመርመር:
ህ) የሲስተሙን መሴንጀር ከአድምንስትሬቲቭ ቱልስ ውስጥ ዲስኤብል ማድረግ::
ለ) ሪሞት ሄልፕ Remote help)ን ዲስኤብል ማድረግ::
ሐ) የዊንዶስ ስክሪፕት ሆስት ዲስኤብል ማድረግ::
መ) ኮምፒዩተሩ ሁሌም የመጨረሻ ተጠቃሚን ዩዘር አካውንት ይጠብቃል:: ይህንን ስክሪፕት ዲስኤብል ማድረግ::
ሠ) የታይም ሲንከርናይዜሽንን ዲስኤብል ማድረግ
ረ) ሲስተማችን ውስጥ ችግሮች ሲኖሩ, ለማይክሮሶፍት መላክ ትፈልጋለህ ወይ የሚል ጥያቄን ያዘለ ሳጥን ይመጣል:: ይህንን አይነት ሰርቪስ የሚሰጠውን ስክሪፕት ዲስኤብል ማድረግ::
ሸ) የሲስተሙን ዩኒቨርሳል ፕላግ ኤንድ ፕለይ ዲስኤብል ማድረግ::
ቀ) Active-X Control ን ዲስኤብል ማድረግ
በ) ከ NetBIOS ጋር ባለ ግንኙነት የተከፈቱ ፖርቶችን ዲስኤብል ማድረግ, ለምሳሌም: ፖርት 137, 139, 145 እና ሌላም::
ባጠቃላይ ወደ 25 ለቮነረብሊቲ ምክንያት የሆኑ ክንውኖች አሉ:: እነሱን በጥንቃቄ መመርመር ተገቢ ነው::
5) ከውሽ ያለንን ግንኙነት የሚያሳየው ስታተስ አይከን ያለውን አክቲቪቲ ማጤን ይጠቅማል:: ምን ነገር ከኢንተርኔት ሳንጠይቅ የትራፊክ አክቲቪቲ ካየን ችግር አለ ማለት ነው:: በኛ ሲስተም ውስጥ ያለ ሆስት ነው ወይስ ከውሺ ይህንን ዴዲኬትድ ኮምኒኬሽን የሚያካሂደው? ይህንን መለየት::
ይበለጠ ወደፊት እመለስበታለሁ::
አመሰግናለሁ