የኮምፒውተር የሶፍትዌር እና ተዛማጅ ጥያቄዎች እና መረዳጃ..

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ocean12 » Sun Aug 31, 2008 6:26 pm

ሰላም ወገኖቼ...
ndave የጠፋ ሰው: እረ ደግ አይደለም ወዳጄ..
ቶሎ ቶሎ ብቅ ብትል ደስታውን አንችለውም... :D ታዲያ በደረቁ አይደለም :D
ዋናው...በጣም ደስ የሚል አኒሜሽን ግሩም ፈጠራ...ምስጋናዬ
ይድረስ::
አዋሽ98... እረ እንኩዋን በደህና ተመለስክ ወዳጄ :D
እረ እኔስ ይቺን ቤት ጣል ጣል ማድረጌ አልነበረም
...እዚህ የሚመጣው ሰው ሁሉ በመጠየቁም በመመለሱም
አስተያየት በመስጠቱም እንዲሳተፍ በመፈለግ ነው
ለአሁኑ ጥያቄህም የማውቀውን ለመመለስም ዘግየት
ያልኩት::
እንደኔ እንደኔ ስንፍናውን የት አባህ ብለህ እንደ
flicker ወይም photobucket ላይ መጀመርያ upload
ለማድረግ ብትነሳ ነው የሚያዋጣህ.. :D አንተ ባልከው
መንገድ በቀጥታ በ USB ፖስት ለማድረግ የሚቻል ነገር
አይመስለኝም ለሁሉም እስኪ ሌላ መንገድ አለው የሚል
ሰው ካለ ደግሞ እናያለን :D
መቼም ያለህን ሁሉ ባይሆንም እስኪ ስትችል ስትችል
አንድ አንድ እያልክ አቁዋድሰን..እኔ አንድ ሃምሳ ፎቶ
እጠብቃለሁ.. :)
በሉ መልካም እሁድ ለሁላችሁም...ሰሞኑን ያመለጡኝን
ነገሮች ላይ ልድረስባቸው.. :D
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby ቡናማ » Tue Sep 02, 2008 10:11 pm

ሰላም ወዳጆች

የዚህን ቤት አነሳስ አላማና እድገቱንም ከሚደግፉት ውስጥ ነኝ::
እኔ እንደዕድል ሁኖ አንዳንድ የድህረ ገጽ (websites) አሰራርና ጉዳዮቹን ያጣቀሰ ኮርስ በቅርቡ መውሰድ ችያለሁ::በሰአቱም በግሌ እያዘጋጀሁዋቸው ያሉ የትዕዛዝና የግሌም መሰል ስራዎች አሉ::በዚሁም አጋጣሚ ጠቃሚና በብርቱው አጋዥ ሆነው ያገኘኋቸውን ነጥቦች ወጥ የሆነን በራስ ፍላጎትና ጥረት የድህረ ገፅ መስራትን የምትሹ ብትኖሩ ብየ አንዳንድ ጉዳዮችን ለመጠቆም ፈለግሁ::
በመሰረቱ ለአንድ ድህረ ገፅ ቅድሚያ ልናካብተው የሚገባን እውቀት html (or xhtml) and css ስለተባሉት ወሳኝ የመገንቢያ ጥበቦች ነው::እነኚህ ነገሮች ብቻ ያለተጨማማሪ መስህብ ፈጣሪና ማዛኚያ ወጣኝ ፕሮግራሞች (dynamic approaches and interactive elements) ለምሳሌም እንደ Flash, JavaScript, php etc.. ያሉትን ባለማከል ማለፊያ የሆነ ድህረ ገጽ ማዘጋጀት ይቻላል::
ይሁንናም ዘመኑ በየእለቱ እንደ አሸን በሚፈሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የቱን አብልጦ በመያዝ መጠቀም እንደሚቻልና ከጊዜው ጋር ሳይራራቁ ተራማጅ የመሆንን ነገር ምን ያህል አስፈላጊ አድርጎ ስለሚከስትብን የማውቀው ብቻ ይበቃኛል ብሎ መቆም እንዳንችል እንሆናለን::
ስለዚህ እስቲ ለሁሉም ቀላል ባልላቸውም ወሳኝ በሆኑት ሁለቱ የመጀመሪያ ፕሮግራሞች ዙሪያ ካወቅሁት ጥቂት ጀባ ልበል::
Html(or Xhtml) የሚባለው የድህረ ገጽ ወሳኝ አካል አንድ ዌብሳይት አካቶ የያዛቸውን የፅሁፍና ብሎም የስዕል አካላት በሙሉ የምናቀርብበት ጠቅልላውን በገጹ ላይ ሊሰፍሩ የሚገባቸውን ነገሮች የምንወስንበት ነው::
CSS (or Cascading style sheetስ) በሚባለው ደግሞ የትኛው ፅሁፍ በምን አይነት ቀለም በምን አይነት የጀርባ ስዕል ላይና ስፍራ ሊቀርብ እንደሚገባና የመሳሰሉትን የምናረቅቅበትና ውሳኔ የምናስተላልፍበት ፕሮግራም ነው::
ቀርቦና ደፍሮ ላልሞከራቸው ሁለቱም በመጀመሪያ ላይ በጣም አስቸጋሪና ውስብስብ ይመስላሉ::ይሁን እንጂ በበርካታ ጀማሪያንና በዚሁ ሞያ ላይ በተሰማሩት ሁሉ ተወዳጅነትና ተመራጭነትን ያገኙት www.selfhtml.org(በጀርመንኛ ቋንቋ ብቻ ይሆንን?) or www.w3schools.com የተባሉት ዌብ ሳይቶች ምንም ነገር አስፈሪ እንዳልሆነ ያስተምራሉ::አስፈላጊ የሆኑት መረጃዎች ሁሉ በእውነተኛ መነሳሳትና ፍላጎት ሊሞክር ለተነሳ ሁሉ በነኚህ ገጾች ላይ ሰፍረው ሊያገኝ ይችላል::
በዚህ ጉዳይ ላይ ከራሴ ተመኩሮዎች ተነስቼ እንዳብራራ የምትፈልጉብኝ ካላችሁ አሳውቁኝ::የማውቀውን ሁሉ ለማካፈል ደስተኛ ነኝ::
ለመነሻ ያህል ይህንን ካልኩ ለምሳሌ እንበልና አንዳንዶቻችን ከዚህም ያለፈ እውቀቱ ኖሮን የየራሳችንን ሆምፔጆች አዘጋጅተን ይሆናል::በተለይ ለእንደዚህ መሰሎቹ አድቫንስድ ዋርካዊያን ባለሙያዎች ጠቃሚ ይሆናል ብዬ ያገኘሁዋቸው lightbox, floatbox, lytebox, etc. የሚባሉ የፍላሽና ጃቫ ስክሪፕት የጥበብ ውጤቶች ናቸው::
እኒህ የፕሮግራም ጥንስሶች አገልግሎታቸው በድህረ ገጻችን ላይ ለዕይታ ያቀረብናቸውን የፎቶና የስዕል ነገሮች መስህብ ባለውና አርኪ በሆነ መንገድ የምናሳይባቸው በነፃ ዳውንሎድ ተደርገው በቀላሉ ከሆምፔጆቻችን ጋር አሰባጥረን ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ናቸው::
ለምሳሌም ቢሆን እኒህን ገጻት በመጎብኘት ስለሁኔታው የተሻለ መረዳት ይቻላል::
http://www.dolem.com/lytebox/
http://www.huddletogether.com/projects/lightbox2/
http://en.wikipedia.org/wiki/Lightbox_(JavaScript)

በወዳጅነት እንቀጥል
ቡናማ
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Postby ሾተል » Tue Sep 02, 2008 11:04 pm

እንዴ አንተ አጁዛም ቡናማ የሚሉህ እያጎ አለህ እንዴ...ተመስጌን አልሞትክም......ክፋት አልመላለጠኽም?

በነገራችን ላይ ሰሞኑን ዝፈን ዝፈን ብሎኝ በራሴ የንድምጽ መቅጃ የሰዎችን ዘፈን...እንግሊዘኛውንም አማርኛውንም ዘፍኜ ዘፍኜ ዱቅ ብያለሁ....እና እነዚህን ዘፈኖች ዩ ትዩብ ላይ ልለጥፋቸው ብዬ ስሞክር የግድ የሆነ ፎቶ ወይም ተንቀሳቃሽ ምስል እንዲኖረው ይፈልጋሉና እንዴት ብዬ ለምሳሌ ያለቪድዮ ሰል የውሻዬም ይሁን የእኔ ፎቶ ወይም በቃ የሆነ የብርጭቆም ማይንቀሳቀስ ፎቶ አድርጌ የቀረጽኩትን ድምጽ እንዴት መለጠፍ እችላለሁ?ነው ጥያቄዬና ጩቤ በደረትህ ከዚህ ከቪየና ወርውሬ ጀርመን ድረስ አድርሼ ሳልሰነቅርብህ መልስልኝ.....ደግሞ መልስ የማግኘት መብት አለኝ.....ስግብግብ ካልሆንክ የተማርከው ላንተ ብቻ አይደለም...አለማችንን ለመቀየር ጭምር ነው......አውቀኽ የማሳወቅ ግዴታ አለብህ.....ካላደረክ ቆለቴን ይዤ ከረገምኩህ እዛው ኮምፒውተርህ ላይ እንደተቀመጥክ ሽንት በሽንት ትሆናለህ....እንደ እያጎ ጫማም አስወረውርብሀለሁ....ፈስህ እንዲያመልጥህ አንደርቢ አደርግብሀለሁ......ደግሞ ሳይህ እራስህን ሆነህ የመጣኽ ትመስላለህ.....ምክሬ እውን ሊሆን ነው....ያወቅከውን ለማሳወቅ ስለጀመርክ አድናቆቴ ትልቅ ነው....ስለእኔም ጎርጉረኽ የደረስክበት ነገር ካለ እባክህ ዋርካዊያን እየጠበቁ ነውና አዲስ ነገር ስለ ሾተል ወይም አምባቸው አባተ ደጀኔ....ደጀኔ አምባቸው አባተ....አባተ ደጀኔ አምባቸው እንድታቀርብላቸው....እኔም ስለ ራሴ የማላውቀው ነገር ካለ አሳውቀኝ ባክህ......ስለ ሰው አይደል የምትኖረው?ካልሆነ ሰው ጋር አምላክ ጥሎህ ነው ኑሮኽን የምታማርረው....ቀድመህ ሾተልን አለማወቅህ ነው እንደዚህ ቆሞ ያስቀረኽ.......እግዜር ይስጥኽ አሳወቅከኝ...አስከበርከኝ....ለዛውም በተባራሪ ተበድቶ የሚሄድ ---- ልታስበዳኝ ነው........ካድናቆዎቼ አንዱዋ ከች ብላ ትማስ ወርቁዋን አሽራኝ ልትጭር ነው...ወይኔ ከአበሻ ጋር ተጀናጅኜ ፍቅር መስራቱን እችል ይሆን?እስቲ ከተማርከው የምታውቀው ዌብ ሳይት ካለ እንዴት እንደሚጀነጀን የሚያስተምር ዌብ ሳይት ካለ ላክልኝ....

በል ለአሁኑ ቻው.....የጀመርካቸውን ሩሞች አትዝጋቸው....ይንቀሳቀሱ....ምንም አንገትህ በእፍረት ቢደፋም ይህእ የሳይበር ህይወት ነውና የቤት ኪራይህን የሚከፍልልህ ከሌለና ኑሮህን የሚከፍልልህ ከሌለ አትፈር....የታባቱ መርዘኛው የክፋት ልብህን ይዘህ ከች በልና የምትችለውን አስተምረን...

በል ጥያቄዬን እንደምትመልስልኝ ነው....ዘፈኖቼን በነጻ በነጠላ በጥንድ በመንታ በዩትዩብ ልለቃቸው አስቤያለሁ....መልስህን በቶሎ እጠብቃለሁ...

ሾተል.......ዘመናዊው ዘፋኝ....ወይ ቦብ ማርሌይ በሰማኝ.....በወልይኛ ዘፈኑን ስዘፍንለት....
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ቡናማ » Wed Sep 03, 2008 3:51 pm

ሰላም ዋርካውያን

ይህንን ሾተል የሚባል እንደጢንዚዛ በየተገኘበት እየደረሰ ሰላም የሚያደፈርስ ሰው ማን ነው የሚገላግለን?ንቀው ሲተዉህ አትተው: አርመውህና ስህተትህን ነግረውህ እንደጨዋ ስነምግባራም ሰው ሆነህ ለመገኘት ከመጣር ይልቅ ከንቱና ግብዝነትህን በሜዳው ስታስተዋውቅ ምጽዓት መድረሱኮ ነው!ኧረ ተው ልብ ግዛ!
መቸም አንዴ ያንተ እያጎ አድርገኸኛል-ስለዚህም በመጀመሪያ ደረጃ 'አእምሮዬን ጨምቄ' የምመክርህ ራስህን እንድታጠፋ በነበረ! እንዲህ ያለውን ምክር ግን ላንድ ክቡር የሰው ልጅና ደግሞም ለኢትዮጵያዊ ወገኔ የምመክር ሰው ስላይደለሁ: ብሎም እኔ አንተ በውስጥህ እንደቀረጽከኝ ጥላህን የምወጋና የማሸብጥብህ ኢያጎያዊነት የተጠናወተኝ ሰው እንዳይደለሁ ደግመህ ከመወለድህ በፊት ማወቅህ አይቀርም ብየ አምናለሁ!
ወደ ጥያቄህ ተመልሼ ሙያዊ እገዛዬን ለመስማት ከፈለግህ ግን የምመክርህ በYoutube ላይ ልታቀርበው የፈለግኸውን ሙዚቃ በምስል ደጋፊነት የምታሳያቸውን ፎቶዎች በሙሉ በመጀመሪያ ደረጃ power point በተባለው የ ማይክሮ ሶፍት ኦፊስ ፕሮግራሞች አንዱ እንደሙዚቃው መጠን ልክ በመገጣጠም ልትሞክረው ትችላለህ::ወይም window movie maker የተባለውም ሊያግዝህ ይችላል::
በመሰረቱ እኔ የምጠቀምበት ፕሮግራም የፒናክል Studio 9 or 10 ይባላል::ይህን ፕሮግራም የምታገኝ ከሆነ ሙዚቃዊውን ስራ ህይወት ሊዘሩበት የሚችሉ ተጨማማሪ dynamic interactive Elements and Effects ስላሉት ችግርህን ያቀሉልሃል ብዬ አምናለሁ::ከዚያም ስራህን ወደ ዩቱብ ከማምጣትህ በፊት በዌብ ላይ መጠኑ አመርቂ ሆኖ እንዲቀርብ ስለ ፋይሉ መጠን ፕሮግራሙን ልትጠቁመው ትችላለህ::መልካም ሙከራ!

ቸር ወሬ ያሰማማን::
ቡናማ
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Postby የሚሚ:ባል » Thu Sep 04, 2008 9:05 am

.

ሰላም ሰላም::

የአለም ታላላቅ ሰዎችን በ1 ላይ ያቀፈ ለባክግራውንድ የሚሆን ምስል እንካችሁ:-

click here for image

.
Image
የሚሚ:ባል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1276
Joined: Mon Oct 22, 2007 8:41 am
Location: dictation:donation: duration:information: foundation: gas station:relation: rotation:vacation

ኔትወርክ ራውቲንግ

Postby ትብብር » Sat Sep 06, 2008 6:07 pm

የኔትወርክ ፕሮጄክት በግሌ እየሰራሁ ነው:: ይህም ፕሮጀችት የአይፕ አወቃቀርን(IP address breakdown) በሚመለክት የተመደቡትን የክፍል አወቃቀር አይከተልም:: ማለትም በተለምዶ ተጠቃሚነት ያላቸውን የአይፒ አወቃቀር አይከተልም:: ይህም CIDR (Classless Inter Domain Routing) የሚባለውን ይጠቀማል:: ጥቅሙ በተመሳሳይ ሁኔታ ለመጥቀስ, (draw a line on the sand and claim it) የሚሰኘውን ለማድረግ, ወይም የፈለግነውን የአይፒ ብሎክስ መጠቀም እንድንችል ይረዳናል:: ወደጥያቄው ለመመለስ, ብዙ ጊዜ ብሮድካስት በኔትወርክ መጠቀም አይመከርም, ምክንያቱም ኔትወርኩንም ሆነ ኢንተርኔትን ሳያጥለቀልቅ (without flooding the network) የሚሰራባቸው ሁኔታዎች ያንያህልም አይደሉም:: ከሚጠቀምባቸው ቦታዎች ውስጥ ደሞ ኦ.ኤስ.ፒ.ኤፍ ራውቲንግ (OSPF routing) ስንጠቀም ጎረቤቶችን ለመለየት ስፓኒግ ትሪ አልጎሪትም (Spanning tree algorithm) እንጠቀማለን:: ይህንን አሰራር ከብሮድካስት ለይቼ አላየውም:: ነገር ግን የጎረቤቶቹ ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ አንዱ ራውተር ለሌላው ያለውን የራውቲንግ ሰንጠረዥ ለማሳወቅ ብሮድካት ይጠቀማሉ ማለት ይቻላል:: ከናንተ ጋር ለመወያያ ማቅብ የፈለኩት አሁን የጀመርኩት በአራት ኔትውርኮች ነው, በአነስተኛ ቁጥር ኮምፒዩተሮች:: እንደነገርኳችሁ ለአራቱ ኔትወርክ የሚሆን አይፒ አዘጋጅቼያለሁ:: ጥያቄው - አሁን ባለበት ደርጃ ኦ.ኤስ.ፒ.ኤፍ ራውቲንግ ችግር አይኖርበትም በፍትነት የራውቲንግ ሰንጠርዡን አፕዴት ለማድረግ:: ነገር ግን የኔትወርኩ ቁጥር እየጨመርን ሲመጣ, ምንም እንኳን በየሰከንዱ አፕዴኤት ባያደርግም, ከተወሰነ የኔትወርክ ቁጥር በኍላ ሰንጠርዥ በሚያስተካክልበት ጊዜ መጠነኛ የፍትነት ልዩነቶች እንያለን:: በምን ያህል ፍጥነት ኔትወርኩ ስፒድን እንደሚቀንስ, ቢያንስ ከንድፈ-ሀሳብ አንትጻር, ፕሩቭ የምናደርግበት ሂሳብ እንድሚኖር የሚያው ካል እስቲ ለውይይት ብታቀርቡት በትህትና እጠይቃለሁ::

ሌላው ያቄ, አይፒ ብሬክዳውን በሚመለከት CIDR ስንጠቀም በተለምዶ ተጠቃሚነት ያለው የአይፒ ስኪም (N, G, U, B) ሲሆን, non-default የሆነው ደሞ (N, U, G, B) ናቸው:: ብሬክዳውን አድርገን ለጥቅም ስናውል አሰራራችን ዩኒፎርም እስከሆነ ድረስ ብዙም ችግር አይኖረውም ሎካል ኔትወርኩን በሚመለክት:: በዚህ አጋጣሚ የኔ ጥያቄ ምርጫችንን በምን መልክ እንወስናለን, ብሎም ጥቅሙ ምንድነው? ይህንን ጥያቄ በተመሳሳይ አናሎጂ ለማቅረብ ልክ እንደ ነትዎርክ ዋየሪንግ ስትራክቸር በ 568A and 568B መካከል ባሉ አጠቃቀሞች ያለ ልዩነት ይመስላል::

በቅድሚያ አመሰግናልሁ ለተሳትፎዋችሁ
ትብብር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 119
Joined: Mon Oct 04, 2004 6:34 am
Location: united states

ኔትወርክ ራውቲንግ

Postby ትብብር » Sat Sep 06, 2008 6:09 pm

Postby የሚሚ:ባል » Tue Sep 09, 2008 2:53 pm

.

በመሳርያ የተቀነባበረ የአማርኛ ሙዚቃ ነጻ ዳውንሎድ
(እራሴ ነኝ አፕሎድ ያረኩት : ኖ ቫይረስ! )

amharic instrum..mp3

.
Image
የሚሚ:ባል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1276
Joined: Mon Oct 22, 2007 8:41 am
Location: dictation:donation: duration:information: foundation: gas station:relation: rotation:vacation

Postby መብረቁ » Wed Sep 10, 2008 11:53 am

ስላም ትብብር

ጥያቂህ በርግጥ በደንብ ገብቶኛል ለማለት ባልደፍርም ግን ካያሁት ነገሮች, 1. have you tried considering IPV6 ? Or is that out of question ?
2. አራት ኒት ወርክ ነው ያለህ ለዛ don't you think OSPF is a bit too much ? although EIGRP can be an option i guess you don't want to be limited to a single vendor (CISCO), how about RIP ?
3. Just incase if i have got the wrong end of the stick pls clarify the Q for me.

መልካም ቀን
They Never Test Who Always Drink, They Always Talk Who Never Think.
መብረቁ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Thu Oct 02, 2003 3:00 pm
Location: ethiopia

Postby ትብብር » Thu Sep 11, 2008 11:30 am

መብረቁ wrote:ስላም ትብብር

ጥያቂህ በርግጥ በደንብ ገብቶኛል ለማለት ባልደፍርም ግን ካያሁት ነገሮች, 1. have you tried considering IPV6 ? Or is that out of question ?

ሰላም መብረቁ, አመሰግናለሁ ለመልስህ::
On this project I don't have IP shortage.
For each private network I used 172. IP which gives me several thousands of nodes but my interest on this private IP breakdown as each private network branchout to department level the need to breakdown into managable group of IP may be desirable to answer any scalable issues that may arise in the future. In addition to this the determination of IP breakdown most commonly used scheme are either [N, U,G,B = Network, Usables, Gateway, Broadcast] or [N,G,U,B = Network, Gateway, Usables, Broadcast], which is best advised, by default the second one is most commonly used?

As far the public side, I have leased 5 usable public IP segment and the scheme setup from the ISP is [N, U, G, B], which means I have a total of 8 IP addresses. Since all the four network are located in the same building currently I will setup only one single IP for the WAN gateway. Could the private IP breakdown will have any comparability to the NUGB of the public?

2. አራት ኒት ወርክ ነው ያለህ ለዛ don't you think OSPF is a bit too much ? although EIGRP can be an option i guess you don't want to be limited to a single vendor (CISCO), how about RIP ?
3. Just incase if i have got the wrong end of the stick pls clarify the Q for me.

The reason I have chosen OSPF over RIP is because the max hop for RIP is only 15 and the need to have unlimited hop count is important as the network grow, particularly when remote sites exist. The routing issue which I was talking about is not problem for the 4 network and you will not notice any routing table update issue on these number of network. But as we grow, particularly spread around remote loations the problem might be noticeable and RIP is not really a good choice for this and might even compound the problem. Now my question on this is to findout, as the network spread across areas, how we can be able to calculate the time delay? I will like to stay with OSPF because distribute routing info among routers in a single autonomous system, the best part of it is that chooses the least-cost path as the best route, unlike RIP. So I am thinking more of the future on this.

መልካም ቀን

አመሰግናለሁ በቅድሚ[/quote]
ትብብር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 119
Joined: Mon Oct 04, 2004 6:34 am
Location: united states

እባካችሁ ይህን ዕንቆቅልሽ ፍቱልኝ

Postby ኦሚሊተ » Sun Sep 21, 2008 3:30 pm

ዋርካዎች እባካችሁ ይህን ዕንቆቅልሽ ፍቱልኝ

ሠላም ለዚህ ቤት ታዳሚዎች:: በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ:: በመቀጠልም በኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ/ ከአንድ ሳምንት/ ጀምሮ የገጠመኝን ችግር እገልጻለሁ::

1. በመጀመሪያ ከዋርካ ድረ-ገጽ ብጀምር, አንድ ሀሳብ ወይም መልዕክት ፖስት ካደረግን በሁዋላ በገጹ ከቀኝ ጫፍ ላይ ሶስት ምልክቶች ይታያሉ /quote, edite, delite(X)/ እነዚህን ምልክቶች በመጠቀም ፖስት የተደረገዉ መልዕክት ስህተት ካለዉ እነዚህን ምልክቶች በመጠቀም edite/delite(X) ማስተካከል ይቻላል:: እኔን የገጠመኝ ችግር ታዲያ ከአንድ ሳምንት ጀምሮ ፖስት ካደረኩ በሁዋላ በገጹ ቀኝ ጫፍ ላይ quote ከሚለዉ ምልክት በስተቀር edite እና delite(X) አይታዩም:: የመስሪያ ቤታችንን IT Administrator ስለሁኔታዉ ስጠይቀዉ " የድረ-ገጹ አስተዳዳሪዎች/ባለቤቶች አንተ መልዕክት ፖስት እንዲታደርግ ብቻ ነዉ የፈቀዱልህ: edite /delite(X) ማድረግ እንዳትችል የአንተን account disabled አድርገውት ሊሆን ይችላል" የሚል መልስ ሰጠኝ:: እኔ አሁን መጠየቅ የፈለኩት: ዋርካዎች እንደዚህ ያደርጋሉ ወይ? ይህ ያጋጠመዉ አለ? ይህን የሚያደርጉት ለምንዲን ነዉ?

2. ከዚሁ ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ ከአንድ ሳምንት ጀምሮ ሌላዉ የገጠምኝ ችግር ደግሞ, ለዋርካ ፖስት የማደርጋቸዉን ፎቶዎች Photobucket upload አድርጌ copy በማድረግ ነበር:: ነገር ግን ከአንድ ሳምንት ጀምሮ ፎቶዎችን በ Photobucket upload ማድረግ ብቻ ነዉ እንጅ የምችለዉ copy, edite, delite ማድረግ አልችልም:: ይህንንም ችግር የመስሪያ ቤታችንን IT Administrator ስጠይቀው "ይህ ሊሆን የሚችለዉ Internet Service Provider ወይም ሌላ የዉጭ አካል የአንተን IP Address እና Photobucket Album በመጠቀም copy, edite, delite እንዳታደርግ disabled አድርገዉት ይሆናል" አለኝ:: ወገኖቼ ዕንቆቅልሹ እዚህ ላይ ነዉ እንግዲህ:: IT Administrator ያለዉ ሊሆን ይህችላል? ለምን?
መልሳችሁን እጠብቃለሁ::

መልካም ሰንበት
ኦሚሊተ
ኦሚሊተ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 110
Joined: Sun Jul 01, 2007 3:34 pm

እርዳታ!!!

Postby የሚሚ:ባል » Tue Sep 23, 2008 9:52 pm

.

PLS HELP!
Does ANY1 know where I can get Geez font for MAC??? All available online is for PC, and i cant view warka in amharic from mac. plssssssssss
ወረታውን እከፍላለሁ!
Image
የሚሚ:ባል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1276
Joined: Mon Oct 22, 2007 8:41 am
Location: dictation:donation: duration:information: foundation: gas station:relation: rotation:vacation

Postby ocean12 » Wed Sep 24, 2008 7:05 am

ሰላም ወገኖቼ...
ቡናማ ያወከውን ነገር ለሁላችንም
ለማካፈል የጀመርከውን ሀሳብ ወደ ሁዋላ እንዳትልብን
በጣም ጠቃሚ ነው::
ወደፊትም በምታውቃቸው እና በተማርካቸው ነገሮች ላይ
በሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ መልስ እና አስተያየት በመስጠት
እንደምትሳተፍ ሙሉ እምነቴ ነው::
ለሾተል ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ በመስጠትህም የዩቲዩብ
ቪዲዎዎቹን ለመኮምኮም ችለናል::
ሾተል :D መቼም ስለ አንተ ጸባይ
እስካሁን ከራስህም ጨምሮ በሌሎቹም ከተባለው ሁሉ
አንድ የወደድኩት ነገር ቢኖር የማታውቀውን ነገር ምንም
ያህል ከማትግባባው ወይም በሌላ ጊዜ በነገር
ከምትጎሻሸመውም ሰው ቢሆን ለመማር ፍላጎትህን
ማሳየትህን እና ' ወንድሜ አስተምረኝ ! አላውቅም
አሳውቀኝ!" ማለትህ ምን አይነት ሰው እንደሆንክ ሌላ
ተጫማሪ ማሳያ ነው: በዚህ በዚህ ምናለ ሁላችንም እንዳንተ በሆንን ብያለሁ::( እኔም ሌላው ሁሉ እንዳለ
ሆኖ እናትህ እንዲህ ሆና እንዲህ ትሁን ሲባል ስሰማ
ከማይወዱት አንዱ ነኝ) በል በሌላ ጥያቄህ ብቅ በል
ደግሞ... :D
ትብብር እና መብረቁ...
መቼም እኔ ብቻ አይመስለኝም ስለምን እየተወራ መሆኑ ግራ የተጋባብኝ.. :D ትብብር ባነሳው ጥያቄ ላይ መልስ
ለመስጠት ብነሳ ወገቤን እንደምሰብር አውቀዋለሁ ደግነቱ መብረቁን ጣለልን.. :) በሉ ሁለታችሁም ሌላ ጊዜ
ከበድ ከበድ ያለ ነገር ሲመጣ ወደ እናንተ አንገታችንን ማቅናታችን አይቀርም.. :)
ኦሚሊተአሁን አንተ ያጋጠመህ
ነገር ያጋጠማቸው ሰዎች ካሉ የሚሉትን ለመስማት እኔም
እጠብቃለሁ..አንድ ጥያቄ አለኝ...ዋርካ ላይ ፖስት ያደረከውን እና delete ለማድረግ የሞከርከው የመጨረሻ
ፖስትህን ነው?...ዋርካ ላይ እንዳስተዋልኩት delete የሚለው ምልክት ከመጨረሻው ፖስትህ በቀር ሌሎቹ ላይ
አይገኝም::
በመጨረሻውየሚሚ ባል ዳውንሎድ እንድናደርግ እና እንድንደሰትበት ፖስት ካደረከው
በሙዚቃ መሳሪያ የተቀነባበረ ሙዚቃ ጨምሮ ዋልፔፐሩን
አንድ ቀን ምሽት 'ኦ... ያ እንትና ነው አይሽው እንትናን እዛጋ' እያልን አመሸንበት ...ትልቅ ምስጋና!
ወደጥያቄህ ሳልሄድ.. :) የአብርሃም የሳራ ያድርገው! እንትፍ እንትፍ ብያለሁ.. :) (ወይኔ ሲያምሩ እኛስ መቼ ነው ባታስብልብኝ ኖሮ እኔም ወድጄው ነበር)
ባለፈው ይህንን አንተ ያነሳህውን ጥያቄ ብራንጎናትርን አንስቶት አንዳንድ ማጣቀሻዎች ለጣጥፈን ነበር ምናልባት
ሊረዱህ ይችላሉ በማለት እዚህ አምጥቻቸዋለሁ::
http://www.linguistsoftware.com/lamu.htm#Macintosh
ይህኛው ዋጋው ውድ ሆነብኝ ብሎ ነበር እናም
እኔ ይህንኛውን ገጽ አገኘሁ
http://tlt.its.psu.edu/suggestions/international/bylanguage/ethiopic.html

እኔ ማክ የሚባል ነገር ኖሮኝ ስለማያውቅ አልሞከርኩትም
እስኪ ሞካክር እና ውጤቱን አሳውቀን.. :)
አንድ ቀን እኔም ወደማክ ማቅናቴ አይቀርም ቢሳካልኝ... :)
ቪስታ አንጀቴን አሳረረኝ :)

የሰላም ሳምንት ይሁንላችሁ...መልካም ጊዜ::
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Re: እርዳታ!!!

Postby ብራንጎናትርን » Wed Sep 24, 2008 3:10 pm

የሚሚ:ባል wrote:.

PLS HELP!
Does ANY1 know where I can get Geez font for MAC??? All available online is for PC, and i cant view warka in amharic from mac. plssssssssss
ወረታውን እከፍላለሁ!

Hey buddy,

just click on the following link:

ftp://ftp.ethiopic.org/pub/fonts/TrueType/gfzemenu.ttf

:)

እድሜ ለኩዛ ... ይሄን ሊንክ ካገኘሁት ቆየሁ:: :wink:

ኦሽናችን ... የኔ ጥያቄ ዛሬም አልተመለሰም ... :cry: :) ምንም እንኳ ከላይ ያስቀመጥኩትን ሊንክ ተጠቅሜ ድረገጽ ላይ የተጻፉ ነገሮችን ያለምንም ችግር ማንበብ ብችልም ... ማይክሮሶፍት ዎርድና ኤክሴል እንዲሁም ሌሎች ኮምፒውተር ውስጥ የሚገኙ ፕሮግራሞች ላይ በግዕዝ መጻፍ የሚያስችለኝን ፕሮግራም እስከዛሬ አላገኘሁም:: ብዙዎቹ ገበያ ላይ ያሉት ለዊንዶውስ ተብለው የተሰሩ ብቻ ናቸው:: :( ለማክ ተብሎ የቀረበው ያ አንተ ባለፈው የሰጠኸኝ ሊንክ ነበር:: እሱ ግን አይቀመሴ ሆነብኝ:: :lol:

ኩዝሽ .... አዲስ ግኝት ካል እስኪ ሹክ በለኝ ባክህ ... :lol:
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
ብራንጎናትርን
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 736
Joined: Fri Dec 29, 2006 6:31 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests