ሰላም ወገኖቼ !!
ሰሞኑን አንድዬ ኮምፕውተሬ በቫይረስ ተለክፋ መቀዠብ ጀምራለች:: እንኳን ቫይረስ ሌላ ሰው እንዳይነካት እጨነቅላት የነበረችው ለአመታት ከኔ ጋር የዘለቀችው የስደት ጓደኛዬና መቆዘሚያዬ የሆነችው ቢል ጌት ሰራሽ ኮምፕውተሬ እንዲህ መሆን በጣም አሳዝኖኛል:: ምንም እንኳን አስቀድሜ እንኳን ከቫይረስ ከቡዳና መጋኛ ይከላከላል ብዬ እገምት የነበረውን ""ኒሮቲን አንቲ ቫይረስ"" ገዝቼ በክታብ መልክ አንጠልጥዬላት የነበር ቢሆንም በቅርቡ ስከፍተው ግን ጊዜው እንዳለፈበት ተረድቻለሁ::
በቅርቤ ወደሚገኘው ""ፋሚሊ ዶክተርዋ"" ጋር ወስጄ ሳስመረምራትም ያዘዘላት መድሀኒት ዋጋ ከተገዛችበት ዋጋ የማይተናነስ ሆኖ ወገቤን ሰበረኝ:: የማደርገው ባጣ ተአምረኛዋ የአዲስ አበባዋ እንጦጦ ማርያም ጠበል በቀሳፊው ኤች አይ ቪ/ኤድስ ቫይረስ መያዛቸው በሀኪም ከተረጋገጠ በኍላ የተፈወሱ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁና; መቼም ቫይረስ ዘሩ አንድ ነው በማለት ወደዚያ ልኬ ሁለት ሰባት ላዝላት እያሰብኩ ነው:: ከዚያ በፊት ግን መቼም ዋንቾ ብልሀት አያጣም በማለት ወደ ዋርካ ጎራ አልኩ:: ምን ትመክሩኛላችሁ ጎበዝ?? ""የኒሮቲን"" ፓስ ወርድ ያላችሁ ብትተባበሩኝ ደስ ይለኛል...