ተጋላቢ(አስራ ሰባት)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ተጋላቢ(አስራ ሰባት)

Postby የቆሎ ተማሪው » Tue Feb 05, 2008 3:21 am

[/b]

ብርቱ ጋላቢ
ቼ..ባይ ሲያሻው ልጉዋም ሳቢ
ሁሉን ልጋልብ ባይ ጉልበተኛ
አስጎንባሽ አስጎብዳጅ
ያልተገራ አስለማጅ
ውድ ማይሻ ጌታ ጋላቢ
ሁሉን ተፈኛጣጭ ደርሶ አሳቢ
አቅል ነጥቆ ጨርቅ አስጥሎ
ቀልብ ገፎ ቀትራቅልሎ
ፈቃድ ሰልቦ አስገድዶ
ልብ ነስቶ አቅም አርዶ
ካሻው ስፍራ ባሻው መንደር
ባሻው ሠአት ሚያሳድር
በጠኔ እየቀጣ በጥም እየፈታ
ህልም እያበላ ራብ የሚገታ
እየስቀላወጠ እያቁለጨለጨ
በቀቅዠት አውደማ ጨሌ እያስነጨ
ጀርባዬ ላይ ሆኖ አለሙን የቀጨ
እንዲህ እንደኔ አይነቱ ተፈናጣጭ
ከዚያ ጎራ ወዲህ አማጭ
በአመድ አርኪ በአተላ አቅባጭ
እያሳሳቀ ወሳጅ
ከሞት ሰፈር ጥልቅ ሰርጉዋጅ
አለህ(ሽ) ወይ ወዳጅ..?

ይቀጥላል ( 4/ 2/ 8 )
Last edited by የቆሎ ተማሪው on Sat May 24, 2008 2:25 am, edited 6 times in total.
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Postby ዋናው » Tue Feb 05, 2008 3:59 amአቆማዳህን ዓይተን
-ቁራሹን ስንጎመጅ
አንተም ስስት አታውቅ
-ተገኘህ ከኛ ደጅ
እስቲ በል አቋድሠን
-አጉርሠን ባንተ እጅ
::

ዋርካ አስተምራናለች
-መብላቱን ተካፍሎ
ንፍሮን አስዘግኖ
-ተቀብሎ ቆሎ
አበባን ጎንጉነን
-ቀይረን ደበሎ


እንኳን ደሕና መጣህ ወንድማችን የቆሎ ተማሪ

Last edited by ዋናው on Tue Feb 05, 2008 4:22 am, edited 1 time in total.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ትርንጎ 123 » Tue Feb 05, 2008 4:06 am

አቤት አቤት... እረ ስንቱ የቆሎው:: ስምህን ሳየው ድንግጥ አልኩኝ:: አገሬ ጥየው የመጣሁት የከንፈር ወዳጄ ትዝ ብሎኝ ይሆን? :wink:
ትርንጎ 123
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 253
Joined: Sun Feb 03, 2008 6:14 am

Postby የቆሎ ተማሪው » Thu Feb 07, 2008 4:50 am

ተጋላቢ (ሁለት )

ሌጣ ፈረስ ጌታ የለሽ
ጋጣ አልባ ፈቃድ መራሽ
ጥንትም ቢሆን በእኛም ዘመን
ጨሌ እየነጨ ሚጀነን
ሲወራለት እኛ አልሰማን
አንድም ለሩሁ አሊያም ለከርሱ
ለየምናምንቴው ለየግብስብሱ
ራሱን ያልሸጠ
እጁን ያልሠጠ
እንዳሻው የባጠጠ
ጅንን ፋነና
ደርሶ ዘብናና
ጋማው ያልታበተ
በጌታው ያልዛተ
ማይጋለብ ጌኛ
የለም መለኛ


ይቀጥላል
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

ተጋላቢ (ሶሰት)

Postby የቆሎ ተማሪው » Thu Feb 07, 2008 4:55 am

ደልደል ብሎ - ከላይህ ሲቀመጥ
ኮልኮል ሲያረግህ - አርካቡን ሲረግጥ
ደርሶ ሲመቻች - ቀኑን ሲጀምር
በዋል ሊፈስ - አንተን ሲሰግር
ሌላ ሌላ ሲል - በሃሳብ ሲዋጥ
ከጀርባህ ላይ ሆኖ ሲቀብጥ
ቀትሩ ሲርቅ - ከአንተጋ ሲታጣ
በሃሳብ ሲመርሽ ሲያወርድ ሲያወጣ
መለመላውን ሲሆን በሃሳብ ሲዋዥቅ
ሌላ አምባ ደርሶ በልቡ ሲሸምቅ
ሸብረክ በልና - ከአለቱ ፈጥፍጠው
የሆንከውን ይሁን - ፍዳውን አሳየው
ደሞ ደሞ
ድፈረት ካለህ - ከሆንክ እንሰሳ
የሑዋሊት አቅምሰው - ለጌታህ አትሳሳ
አሳሩን አብላው - አሳየው አበሳ
አሊያ ደግሞ
እንቅልፍ የለሽ ህልም ሰሪ
ተስፋ ተቀላቢ ብስራት አውሪ
ቅርብ ኑዋሪ እሩቅ ቡዋጣጭ
ቀውጢ ሳለ ሰላም አማጭ
አደብ የለሽ ጮቤ ረጋጭ
ያልባነነ በሞት ቀባጭ
ሁንበት ተስፋ አስቆራጭ ...
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

ታዛ

Postby ወልዲያ » Thu Feb 07, 2008 8:20 am

ሠላም የቆሎ ተማሪው!


Image

እንዲህ ነው - ጨዋታ እና ለዛ:
በዚያም በዚህም ለሰው ልጅ ታዛ::


መልካም ሓሙስ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby የቆሎ ተማሪው » Thu Feb 07, 2008 11:49 pm

ተጋላቢ (አራት)

ያዋቂ ያለህ ተርጉዋሚ
ሀሳብ ገላጭ አስታማሚ
የወጠረኝን አስተንፋሽ
የገደበኝን አፍርሽ
እንደ አላዛኝ ሙዋርተኛ ውሻ
ሰሚ አድማጭ እህ ባይ ስለምሻ
ታፍኜ ከምፈነዳ
ልተንፍስና ልረዳ
በኔ ላይ ያደላብኝ
ድህነትን ሰፍሮ የሰጠኝ
ጎባጭ አቀርቃሪ ያደረገኝ
ደሞ ደሞ ጠላቴን ከኔ ያጣበቀ
ውድቀቴን የናፈቀ
ሆድ ብሎ ገደል ያሸከመኝ
ሳልበደር እዳ የሸለመኝ
እጄ ካሻው እንዳይዘረጋ ኪሴን የቀደደ
ይህን በኔ የዘየደ
ወኔዬን ያመከነ ልቤን ያራደ
ማጣትን ርስቴ
ድንቁርናን ቤቴ
ጠኔን በሌማቴ
አርጎ የሸለመኝን
ምነው ባውቀው
ብሙዋገት ብዋቀሰው
ስጋዬን ሸልቅቆ
ወዜን ከደሜ ነጥቆ
ተስፋን ከመዳፌ ፈልቅቆ
አቅሜን ሰልቦ ጉልበቴን
ምኞቴን አክስቶ ነገየን
ኃይሌን የወሰደ አቅሜን የሰለበ
ቁጭቴን ያደለበ
እውቂያ ሳይኖረን ጥፋቴን ናፋቂ
አምርሮ ያጠቃኝን የኔኑ ሸማቂ
አውቆ ሚያሳውቀኝ አለ ወይ አዋቂ


ይቀጥላል...
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Postby የቆሎ ተማሪው » Thu Feb 07, 2008 11:50 pm

ተጋላቢ (አራት)

ያዋቂ ያለህ ተርጉዋሚ
ሀሳብ ገላጭ አስታማሚ
የወጠረኝን አስተንፋሽ
የገደበኝን አፍርሽ
እንደ አላዛኝ ሙዋርተኛ ውሻ
ሰሚ አድማጭ እህ ባይ ስለምሻ
ታፍኜ ከምፈነዳ
ልተንፍስና ልረዳ
በኔ ላይ ያደላብኝ
ድህነትን ሰፍሮ የሰጠኝ
ጎባጭ አቀርቃሪ ያደረገኝ
ደሞ ደሞ ጠላቴን ከኔ ያጣበቀ
ውድቀቴን የናፈቀ
ሆድ ብሎ ገደል ያሸከመኝ
ሳልበደር እዳ የሸለመኝ
እጄ ካሻው እንዳይዘረጋ ኪሴን የቀደደ
ይህን በኔ የዘየደ
ወኔዬን ያመከነ ልቤን ያራደ
ማጣትን ርስቴ
ድንቁርናን ቤቴ
ጠኔን በሌማቴ
አርጎ የሸለመኝን
ምነው ባውቀው
ብሙዋገት ብዋቀሰው
ስጋዬን ሸልቅቆ
ወዜን ከደሜ ነጥቆ
ተስፋን ከመዳፌ ፈልቅቆ
አቅሜን ሰልቦ ጉልበቴን
ምኞቴን አክስቶ ነገየን
ኃይሌን የወሰደ አቅሜን የሰለበ
ቁጭቴን ያደለበ
እውቂያ ሳይኖረን ጥፋቴን ናፋቂ
አምርሮ ያጠቃኝን የኔኑ ሸማቂ
አውቆ ሚያሳውቀኝ አለ ወይ አዋቂ


ይቀጥላል...
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Postby ቤቲ_13 » Fri Feb 08, 2008 12:02 am

አጀብ ብያለሁ ምርጥ ,ቅጽል ስም ምርጥ ስራ....ስምን ቄስ ያወጣዋል ይላሉ እንዲህ ነዉ::
Image
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

ተጋላቢ አምስት

Postby የቆሎ ተማሪው » Fri Feb 08, 2008 10:38 pm

ሸክም ተለምዶ
ከእኛነት ተዛምዶ
ሸምጣጩን አሶምሱዋሚ
ጋላቢን አዝጋሚ
አርጎ
ሰንጎ
ሲያጎብጠው ላየው
ሚመስለው
ፈረስ ሳይሆን አህያ ነው
ሸክም ሲለመድ
ሲያስጎበድድ
ልብን ሲያርድ
ቁልቁል ቢያስቀረቅር
አብሮን ውሎ ቢያድር
እንኩዋንስ ለፈረስ
ለአህያም ቀን አለ
---- ለተባለ...
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Postby ክርስትያን06 » Fri Feb 08, 2008 10:48 pm

ኃያል መልዕክት ያለው ቅዋጠሮ.....

ዕጹብ ድንቅ ከማለት ሌላ ምን ይባላል ::

በርታልን ወንድማችን::
ክርስትያን06
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 601
Joined: Fri Sep 08, 2006 5:15 pm

Postby የቆሎ ተማሪው » Sat Feb 09, 2008 3:49 pm

ተጋላቢ (ስድስት)
ከርስ -አደር ከሆንክ መፍቀረ-ገፈራ
ከሞቀበት ሰንባች አዘንባይ ሸራራ
'ኤድያ' ከሆነማ የኑሮህ ቅኝቱ
ከርስህ ካራቀ የአምሮህ ትኩረቱ
ህልምህም መዝሙርህም ገፈራ ከሆነ
አምሮህ ነጥፎ ከሆድህ ከወገነ
እሱኑው ለመሙላት ለሱው ከማሰነ
ግልቢያውም ሸክሙም ከሆነማ መኖ
ሆድ ዘውድ ደፍቶ ያላመሉ ገኖ
አነፍናፊ ከሆንክ ቃርሚያ ፈላጊ
አጮልቆ ተመልካች ደሞም አሰጋጊ
ምስህ ገፈራ - ምግባርህ ማሻመድ -ብቻ ከሀነማ
ለራስ ስም አውጣ እንኚ እኛስ አንተንም አናማ
አንተንም አናማ

ይቀጥላል..
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Re: ተጋላቢ አምስት

Postby ትርንጎ 123 » Sun Feb 10, 2008 3:15 am

የቆሎ ተማሪው wrote:እንኩዋንስ ለፈረስ
ለአህያም ቀን አለ
---- ለተባለ...

የምትገርም ሰው ነህ መቼም...ልብ የምትወጋ ስንኝ ነች::
ትርንጎ 123
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 253
Joined: Sun Feb 03, 2008 6:14 am

Postby የቆሎ ተማሪው » Sun Feb 10, 2008 4:35 pm

ተጋላቢ (ሰባት)
ዐያደርስ ነው አጉል ጥንውት
በዘራ-ፈረስ ሚሆነው ክስተት
የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ ሚለው የአበው ብሂሉ
በኛ ዘንዳ በተጋላቢዎቹ አልሰምር ብሎ ቃሉ
እናቴ ባዝራ እንስቲቱ ፈረስ
ያላመሉዋ ሆና በዋል ፈሰስ
ያለስፍራዋ ያለቦታዋ ውላ
ብቻዋን ተነጥላ
ተነዋላ
ከአለሌ አህያ ተጋልጣ
በፍቶት ፋንና ናጣ
ከእሱው ጋራ ተራግጣ
የሱዋን ነዲድ አስታግሳ
ያለውዴታዬ እኔን ፀንሳ
መካን አረገችኝ
መርገም ሸለመችኝ
በቅሎ አሰኘችኝ

ይቀጥላል...
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Postby የቆሎ ተማሪው » Wed Feb 13, 2008 1:52 am

ተጋላቢ (ስምንት)


ውስጤ ባዶ
እሱው ከብዶ
ከያኔ ተዛምዶ
ከካቻምና ተዋዶ
ከአምና ተዋልዶ
ከትላንት ተጣልቶ
ከዛሬ ተሙዋግቶ
በነገ ተረቶ
ድሮን ሚኖር
ሀሳብ ሚሰግር
መሰል ፍጡር
አፍርታ ይሆን ምድር?
ከዛሬ በስተሁዋላ
በአይደገሜ ንውለላ
ከአፈጀው ሲታገል
በሸሸው ሲቃጠል
ይህን አይቶ
ጉዋዳዬ ገብቶ
እኔን ሚረዳ
ቁጭቴን ሚቀጭ
በሆነብኝ ሚቆጭ
ማነው ረዳቴ
ደራሽ ከቤቴ
ላረጀ ላፈጀው
ይግባኝ ለማይባለው
ውሎ አድሮ ለሚሸሸው
ሰበብ ፈልጎ ሚቀርበኝን
እያኘከ ሚልሰኝን
የበላሁትን ሚበላውን
ተሻሚዬን
በጥሜ ሚረካ
በኃዘኔ ሚያሽካካ
አክ እንትፍ ይሄማ ምንትስ ነው ያልኩትን
ከሆድ ከአንጀቴ ያወጣሁትን
ጨቁኖ ሚግተኝ ባላንጣዬን
ድሜ-አስጋጭ ጋላቢዬን
'አቤት ድሮ" ከተሰኘ ፈሊጥ
የሑዋሊት ከሚዘብጥ
ጅንን ቼ ቼ ባይ
አለወይ አስጣይ...?
ይቀጥላል ....
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest

cron