ተጋላቢ(አስራ ሰባት)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ስርርር » Tue May 04, 2010 11:41 pm

ስንት ነን....

ስንት ነን ጥያቄው.....ደርሷል ከብዙዎች
መነጋገርያቸው .... ለአነካኪዎች
መዓት ለሚያወሩ.....ለምድር ሁሉ ጉዶች

እስቲ አውሪን አንዴ....እማማ ስንት ነን ?
ስሌታችን ስንት ነው.... ቁጥሩን አሳውቂን

እኛ እንደሰማነው.....አበው እንዳስረዱን
እልፍ አእላፍ ስንሆን በቁጥር አንድ ነን

በልዩነታችን ......... አጊጣ እማማ
አንድ ነው ደማችን ....የኛ የልጆችዋማ

ከአንድ ሌላ መልስ ...... ያለህ ሰው ንገረን
እስኪ ባንተ ስሌት ...... በእውነት ስንት ሆንን?
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

ተጋላቢ ሀያ አራት

Postby የቆሎተማሪው » Mon Aug 16, 2010 6:29 pm

ተጋላቢ ሀያ አራት


ይድረስ ለፈጣሪ
ለፍጡር አፍቃሪ
እኔና ፣ፍቅረዬን
ህልምና፣ ምኞቴን
ካላፍ ዓለማትህ አንዱን ምራንና
ከምድር ንጠቀን ፣ ከሰው ሰውርና
እልፍ አመት እንኑር እንሰንብት ለብቻ
የመላእክት መና ሆኖልን እንጎቻ፤
ብዬ ስለጻፍኩኝ ይድረስ ለፈጣሪ
ፖስታውን ሳላሽግ ፊርማሽን አኑሪ።
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

አጀብ!

Postby ዋኖስ » Tue Aug 17, 2010 4:01 pm

አጀብ!

ቆንጆ ናት!!

ግና የዘመኑ አፍቃሪያት በቀላሉ የሚፈርሙ አይደሉም:: ፊርማዋን ካላኖረችስ?? ቅቅቅ ፖስታዉ ሳይላክ ይቀር ይሆን? :lol:

ከአክብሮት ጋ!!

ዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

ተጋላቢ

Postby የቆሎተማሪው » Wed Aug 03, 2011 1:56 am

[b][/b]በድንነትለእግር ስንደነግጥ
በሱ ስንቀልጥ
እንዳልነበር ሁሉ
አድረው እየዋሉ
ጨርቆች እያጠሩ
ስፍራ እየቀየሩ
መሄድ ሲጀምሩ
ጭራሽ እየበደን
መደንገጥ አቃተን
እስቲ ሸፍኑልን ።
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

Postby የቆሎተማሪው » Fri Sep 23, 2011 9:10 pm

ተጋላቢ ሀያ አምስት


ለተከበሩ ናቂታ
የ ጀርባዬ ግጥበት
የ ክንዶቼ ዝለት ፤
ለከርሶ ሙላት
ለነፍሶ ግሳት
መንስኤ እንደሆነ ቢያውቁ
እኔን ፣ እንትኖን… ባልናቁ
ይልቁንስ ለኔ ለእንትኖ ቢያጋፈሩ
ቀለቤን ቢሰፍሩ
ኣባቷን ክደው በስሜ በማሉ
አህዮ ይሙት ..… እያሉ ።

ግና ፣ ይሄ አይደለምና የርሶ ምርጫ
አለሎት ….. እርግጫ !!
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

ተጋላቢ ሀያ ስድስት

Postby የቆሎተማሪው » Fri Mar 02, 2012 4:26 pm

መንደረተኛ

ይሄ መንደርተኛ ድካም የወደደ፣
ላይሰምርለት ነገር አጉል የዘየደ
ጢስ አልባ ጎጆዬን አያንጎዳጎደ ፤
ቁና ሙሉ እጦት ይዞብኝ ነጎደ ።
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

ተጋላቢ ሃያ ስድስት

Postby የቆሎተማሪው » Sun Mar 25, 2012 12:40 am

ማነው …..?
ነፍስ ሲቃዋ ሲሰብቃት ስለት በውስጧ ሲሻጥ
ወዝ ላበቷ ሲሆን ደሟ እንደ ስብ ሲቀልጥ
መቅኒዋ እንደ እንባ ፈሶ ፣አካሏ እያደር ሲሰልል
የምጥ ለቅሶዋን የሚያደምጥ፣ ሕመሟን ነቅሎ የሚጥል
የብሶቷን ምንጭ የችግሯን ሽንቁር ፈጥኖ የሚደፍነው
ጥቃቷን የማይወድ አጋር፣ አጽናኟ ማነው…?
የቆሎ ተማሪ…
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

ተጋላቢ

Postby የቆሎተማሪው » Tue Jun 12, 2012 1:12 pm

ክንፍ ሸልሙልን

ራዕይ ስንከላ ጉርጓድ ለሚምሱ
አሻፈረኝ ላሉ ፣ ቆርጠው ለተነሱ ፤
በመንገዳችን ላይ እንቅፋት ላኖሩ
መርገጫ ላሳጡን ፣ ወጥመድ ለሰወሩ
መውጫውን ላጠሩ
እጅጉን ለተጉ
ሳይተኙ ላነጉ
ከቶ ለማያርፉ ፣ ደባ ለሚያምጡ
ተንኮል ለሚንጡ
ለነ አይረሴ ጽናት ላላበሱን
በሾህ እያጠሩ ዝላይ ላስተማሩን
ሴራቸው አንቅቶ ለውጦናልና
በዛ ምታልፉ ስጡልን ምስጋና ።

ልክ አንደትናንቱ ፣ ዛሬም እንዲግሩ
በቀልን ተጠምተው ፣ ለኛ እንዲሰሩ
ነጋችን አንዲዋብ ፣ በረው እንዲያሰፉን
እናንት ንስሮች ክንፍ ሸልሙልን ።
http://www.ethiotube.net/video/20281/Ye ... hePart-Two
http://www.ethiotube.net/video/20316/Ye ... Part-three
http://www.ethiotube.net/video/20340/Ye ... ----------
http://www.ethiotube.net/video/20250/La ... yeMiyalqes
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

Postby ዋኖስ » Sat Jun 16, 2012 10:48 pm

ሰላም የቆሎ እንዴት ነህ?

ክሊፖቹ ተመችተዉኛል:: በርታ:: ለማየት ግን በጣም ዘገየሁ:: እሄን ያክል ከዋርካ መጥፋቴን አወቅሁበት! ቅቅ

እናመሰግናለን::

ዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby የቆሎተማሪው » Wed Jun 20, 2012 8:44 pm

ሰላም ሰላም… ዋኖስ ወንድሜ ፣ እንደምን ከረመኻል ? … ይመስገነው ደህና ነኝ !!


http://www.ethiotube.net/video/20495/Me ... omon-Taye-

http://www.ethiotube.net/video/20475/Ye ... part-eight
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

ተጋላቢ ሀያዘጠኝ

Postby የቆሎተማሪው » Fri Jun 22, 2012 12:58 pm

ዕጣ ፈንታከአንድ ኩሬ ተቀድቶ
ከአንድ አፈር ተቦክቶ
በአንድ እጅ ለስልሶ
በአንድ እሳት ተጠብሶ ፤
ቅርፁና መጠኑ ስለተቀየረ
ጢስ እየጠገበ ኩሽና እየኖረ
ማብስያ እንዲሆን ለእሳት ተፈጠረ ።
እደጅ እየዋለ እቤት እያደረ
ዞሮ እየገባ በጀርባ እየኖረ
እንስራው ወንድሙ ለውሀ ተዳረ ።http://www.ethiotube.net/video/20533/Ye ... part-ten--
http://www.ethiotube.net/video/20531/Ye ... -part-nine
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

Re: ተጋላቢ ሀያ አራት

Postby ስርርር » Tue Jun 26, 2012 9:49 pm

Yዚህ ግጥም ርእስ 'ፊርማሽን አኑሪ" ቢሆን እንዴት ያዋጣ ነበር

ሥርርር ሰራሪው
የቆሎተማሪው wrote:ተጋላቢ ሀያ አራት


ይድረስ ለፈጣሪ
ለፍጡር አፍቃሪ
እኔና ፣ፍቅረዬን
ህልምና፣ ምኞቴን
ካላፍ ዓለማትህ አንዱን ምራንና
ከምድር ንጠቀን ፣ ከሰው ሰውርና
እልፍ አመት እንኑር እንሰንብት ለብቻ
የመላእክት መና ሆኖልን እንጎቻ፤
ብዬ ስለጻፍኩኝ ይድረስ ለፈጣሪ
ፖስታውን ሳላሽግ ፊርማሽን አኑሪ።
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby የቆሎተማሪው » Wed Jun 27, 2012 10:41 pm

ሰላም ሰላም …..ወንድሜ ስርርር እንደምን ከርመሀል..በነገራችን ላይ መልካም አስተያየትህን ተቀብያለው።
ዳሩ ግን አስተያየትህን የሰጠህበት ግጥም ፀሎተ - ቀናኢ በሚል ርዕስ ታትሞ ስለወጣ እንደ አማራጭ እንኩዋ ለመያዝ አልቻልኩም ፤ ምስጋናዬ ግን ይድረስህ።

http://www.ethiotube.net/video/20574/Ye ... art-Eleven

http://www.ethiotube.net/video/20586/Ye ... art-Twelve
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

ተጋላቢ ሰላሣ

Postby የቆሎተማሪው » Mon Sep 10, 2012 11:02 pm

ጥንውተ ግጥም

በጥቅሻ ሳይለከፍ
በፈገግታ ሳይቀሰፍ
በጭን ልፊያ ሳይነደፍ
በሥነ-ግጥም ተሰድሮ
በሥርወ - ቃል ተጠፍሮ
በድምፀቷ ተመስጦ
በለዛዋ ተሽቆጥቁጦ
ሰርክ እየማቀቀ
አካሉ ባለቀ
ግስ እየገሰሰ ቃላትን ባረባ
ቅኔ እየቋጠረ ፣ በሰው ልብ በገባ ፤
ባለ መድሃኒቶች ፣ እጀ-ሰብ ሚያውቁ
ከንባብ የነጹ ከቅኔ የፀደቁ
ከግጥም አባዜው አዝነው ሊታደጉት
አጎዛ አልብሰው በርበሬ አጠኑት።

ከማዕዶት የግጥም መድብል የተቀነጨበ
(የቆሎተማሪ)
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests