ተጋላቢ(አስራ ሰባት)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby የቆሎ ተማሪው » Wed Apr 16, 2008 1:34 am

ሰላም ሰላም ቤቲ 13 እንዲሁም መልከጸዲቅ ስለሰጣችሁኝ አስተያየት ከልብ አመሰግናለው እግዚያብሄር ይስጥልኝ ፡፡
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

ተጋላቢ (አስራ ሶስት)

Postby የቆሎ ተማሪው » Sat Apr 19, 2008 5:17 pm

ተጋላቢ (አስራ ሶስት)

እሱማ አብዶ - አቅሉን ጥሎ
ገመና ገልጦ- እርቃኑን ውሎ
ሩኁን ስቶ - ከራሱ ኮብልሎ፡፡
ተነዋሎ !!
ተጃጅሎ!!
ይሉኛል፡፡
እኒህ ልብሰኞች ፤መደረብ የሚያውቁ
ዘበናይ ጨርቀኞች ፣ በቅጡ የለበሱ ቦላሌ የታጠቁ
እነአፈር ጥይፉ ፣ለግራቸው ደህንነት መጫሚያ ያጠለቁ ፡፡
መጀቦን መደረት፤ ሌላውን ትረካ ፣በጠላሁ ትወና
ንክ ነው ብለው አስወሩ፤ መቅኖ አልባ ፣ ባከና፡፡
ይልቁን እንደኔ ቢያወልቁ፤ ጨርቃቸውን ቢጥሉ
ገመናቸው ቢታይ፣ ስውሩን ቢከሉት ፣ራሳቸውን ቢያክሉ፤
ይህ የኔን ነጣነት እንዴት ባስተዋሉ፡፡
አረ ጎበዝ ከዚህ አምባ ማዶ እንውረድ
ጨርቅ እንጣል፤ ራስ እንምሰል፤ አብረን እንበድ…
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Postby የቆሎ ተማሪው » Sun Apr 27, 2008 3:49 pm

ተጋላቢ አስራ አራት

የዘመነ ቅርሻት ግዜየን ሳሰላ፣
የዳዴዬን ሁላ ፤
ሰዶ ማሳደድ ሆኖብኛልና
ድክ ድክ አሰኘኝ ድክ ድክ በእግሬ
ወፌ ቆመች በለኝ ይፈታ እስሬ፡፡
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Postby የቆሎ ተማሪው » Sat May 03, 2008 5:36 am

ተጋላቢ (አስራ አምስት)

ኩስኩስ ባይ ስንኩል፣
አጥንት የለሽ ሽል፤
ታግሎ ማይጥል፣
ቂመኛ ዳተኛ፣
ከራስ ያልራቀ ግለኛ፤
ያዙኝ ባይ አጉዋጊ፣
የእፍኝ አስጣይ አዘናጊ፤
ማይረገም ማይመረቅ፣
ግልጥ ያልዋለ ሚሸምቅ፤
ለሙግት ማይመች፣
ከአይን ስውር ከልብ ታጋች፤
ሩቅ ሳለ ቅርብ ሚያድር-
ማይነገር …
አለ ወይ ሚስጢር…
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Postby dama978 » Sun May 04, 2008 12:26 am

አይ ኢትይፕያዊነት, አይ ህሊና
እነፕሮፈሰር ኣለማየሁ, ዶ/ር ብርሀኑ ወይም ሊሎች አምላኮች ማንም ላይ የጥላቻ ላይሰንስ ሊሰጡ እንደማይችሉ አለማወቅህ ግድየለሽነትህን የሚገልዸው::
dama978
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 353
Joined: Sun Oct 02, 2005 6:10 pm
Location: ethiopia

Postby ትርንጎ 123 » Sun May 04, 2008 3:56 pm

የቆሎዬ እኔ በጉዋሮ ብቅ እያልኩ አብሬ እየጋለብኩ ነው...በርታልን...መቼም ተዝቀው የማያልቁት ቃላቶችህ እኔንም እያስቀኑኝ ነውና ዋ :twisted:

Dama ድሮ እናቴ 'ተናግሮ አናጋሪን ያዝልኝ" ትል ነበር ከቤትዋ ደጃፍ ስትወጣ...አንተን ታውቅህ ይሆን? አስተያየት መስጠት መብትህ ሆኖ ሳለ...ምነው ሰው ላይ ፊጥ የምትላትን ነገር ብትተው? ችሎታው ካለህ ቅር ያሉህን አባባሎች በጨዋ ደንብ ተንትንልንና አይናችንን ክፈተው...አለዛ ደግሞ ዋርካ መጥቶ መለቅለቅ ግዴታ አይደለም እኮ አባው...አንብቦ ውልቅ ማለት ይቻላል:: በነገራችን ላይ በአማርኛ ፊደላት ታይፕ የማድረግ ችሎታህን አድንቄያለሁ...ሰው በችሎታው መመስገን አለበትና::

እፎይ...እስቲ በሰላም አውለን!
ትርንጎ 123
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 253
Joined: Sun Feb 03, 2008 6:14 am

Postby ቤቲ_13 » Sun May 04, 2008 8:21 pm

ጉድ ፈላ .....!!የቆሎዉ ቅቅቅ እንዴት እንዴት አይነት አንባቢ መጣብህ ቅቅቅቅ....ለነገሩ ምንም አይደል አንዳንዴ << አላንባቢ>> ሲገጥም አንጣሎ አንቀርቅቦ ምናምን ማዉጣት ነዉ,,,,,,,!!
ጽሁፍህ ወደር የለዉም ቃላቶችህ....ዉብ
አያልቅበት ብዬሀለሁ
አክባሪህ!!አድናቂህ.....
ዉይ በሞትኩት...ትርሻ እንዴት ነሽልኝ???
Image
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby ትርንጎ 123 » Mon May 05, 2008 9:44 am

ቤቲዬ :lol: :lol: <አላንባቢ> :lol: :lol: ገደልሽኝ...አለሁልሽ እሙ...ይቅርታ የቆሎሻ...ቤትህን ቦስጣ ቤት አደረኩት...ቤትዬን አይቼ አላስችል ብሎኝ ነው::
ትርንጎ 123
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 253
Joined: Sun Feb 03, 2008 6:14 am

Postby dama978 » Mon May 05, 2008 10:38 pm

የተማረበት ሞያው ነው ባማርኛ ቃላት ሀይል ከልቡ የሚለውን ከኛ መሰወር::አርቲስ ነው ስለሆነም ማስመሰል::
የቆሎ ተማሪ ስራው ነው: እንዳዉም ከሱ out of print የአማርኛ መዽህፍት መግዛት እፈልጋለሁ:: ከድሮም ቢሆን አውቀዋለሁ:: አላንባቢ እያልሽ በኒና እሱ መሀል በማጥላላት በማሳበቅ ልትገቢ መከጀልሽ ይቅር ይበልሽ::
dama978
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 353
Joined: Sun Oct 02, 2005 6:10 pm
Location: ethiopia

Postby የቆሎ ተማሪው » Sat May 10, 2008 4:01 am

ተጋላቢ (አስራ ስድስት)


አንቺ አበባ ፣ የፍሬ ፅንስ ፣የመከር እናት፤
የአራሽ ተስፋ፣ የአይን ማርፈጃ፣ የልብ ኩራት ፡፡
አንቺ አደይ፣ ባለ ኅብር ፣የመፀው ልእልት፤
የአይን ረሃብ ፣ የልብ አምሮት፣ ክፉ ልክፍት፡፡
እነሱም የኛ፤ እኔም የኔ ምልሽ ደርባባ ፤
ዘመኑ ዘምኖ፣ የኔም ዘመን እስኪጠባ፤
እየቀላወጥኩሽ ፣ከደጅሽ ላድፍጥ ፣ከቅጥርሽ ላድባ፡፡
ሰማሺኝ… ካኖሩሽ ስፍራ እጄም ደርሶ ባይዘረጋ፤
እንደመሻታችን ፣ ምንም እንኩዋ ባይሆን አልጋባልጋ
ህልማችን እስኪይዝ ፣ከዚያማዶ ወዲህ እናውጋ፤
ሰበብ አይከልክለን ፣ ጨለማው ይራቅ ሌቱ ይንጋ ፡፡
አንቺ አበባ የፍሬ ፅንስ የመከር እናት
የአራሽ ተስፋ ፣የአይን ማርፈጃ ፣የልብ ኩራት ፤
አንቺ አደይ፣ ባለ ኅብር ፣የመፀው ልእልት፤
የአይን ረሃብ ፣ የልብ አምሮት፣ ክፉ ልክፍት ፤
ባይሆን ቀልቤን ካንቺ ዘንድ አኑሬ፤
የልብሽን አድምጬ ፣ከምክረሽ ተማክሬ፤
ከማህሌትሽ ሳልታጣ ፣ ዝክርሽን ዘክሬ፤
በገናዬን እየደረደርኩ፣ ቁርባንሽን ቆርቤ፤
ፆምሽን እየፆምኩ፣ ርሃብሽን ተርቤ፤
እነሱም የኛ፤ እኔም የኔ ምልሽ አበሱዳ፤
አጣፋጭ ቅመሜን ፣የርዕዬ ተራዳ፤
ከቀልብሽ መንደር፣ ከልብሽ ጉዋዳ፤
አሰልሼ አበክሬ፤
ኣሰረግጬ አስዘርዝሬ፤
እንደ ቀላጤ ነገር ሰሪ፤
እንደ ተመፅዋች ተዘካሪ፤
በሩቁ እየቀላወጥሁ፤
ቃሌ ቃል እያልሁ፤
እነሱም የኛ፤ እኔም የኔ ምልሽ አበሱዳ፤
አጣፋጭ ቅመሜን ፣የርዕዬ ተራዳ፤
እንደ መታች ጠሎት ፣እየደገምኩሽ ላርፍዳ፡፡

ግልቢያ ይሉዋል እንዲህ እንደኛ…
እርካብ ረጋጭ ፤ ማዶ ተጉዋዥ፣ ፈረሰኛ…፡፡
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Postby የቆሎ ተማሪው » Sat May 24, 2008 2:24 am

ጨቅላነት ደርዝ አውጥቶ፣
ቆዳ ለብሶ አፀጉርቶ፤
መቀመጫ ስበንለት መኸለኛ ሆኖ፣
ተኮፍሶ፤ ጋሽ-ማሙዬ ተዘባኖ፤
ግላጭ ውሎ ግላጭ ሲያድር፣
እሱም ላይሰቅቀው ራሱን ላይሰውር ፣
እየተመቻቸ ወንበሩ ላይ ሲያንቡዋችር፣
እኛም ነጠላ እያጣፋን ስናደገድግ
እንደስጋጃ ተነጥፈን ሽቅብ ስናሰግግ
በደረታችን ስንሳብ ጎድለን ከሰው-ማረግ
ጋሼ-ማሙሽ ምንተዳዬ ተዳልቶ
ደርዝ አውጥቶ ቆዳ ለብሶ አጸጉርቶ
ተኮፍሶ ተዘባኖ
ቀላምዶ አመካክኖ
ዘመኑን አዘምኖ
አጉሮን በጉሮኖ
አልሸት አለን ፋኖ…
የቆሎ ተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Feb 05, 2008 12:35 am

Postby ብራንጎናትርን » Sat May 24, 2008 3:25 am

ኡፈይ ... በጣም ይመቻል! ይጨመር ይጭመር ...

በተለይ "አጸጉርቶ" ምትለዋ ቃል ውስጤ ዘልቃለች::

በርታ

ብራንጎ

የቆሎ ተማሪው wrote:ጨቅላነት ደርዝ አውጥቶ፣
ቆዳ ለብሶ አፀጉርቶ፤
መቀመጫ ስበንለት መኸለኛ ሆኖ፣
ተኮፍሶ፤ ጋሽ-ማሙዬ ተዘባኖ፤
ግላጭ ውሎ ግላጭ ሲያድር፣
እሱም ላይሰቅቀው ራሱን ላይሰውር ፣
እየተመቻቸ ወንበሩ ላይ ሲያንቡዋችር፣
እኛም ነጠላ እያጣፋን ስናደገድግ
እንደስጋጃ ተነጥፈን ሽቅብ ስናሰግግ
በደረታችን ስንሳብ ጎድለን ከሰው-ማረግ
ጋሼ-ማሙሽ ምንተዳዬ ተዳልቶ
ደርዝ አውጥቶ ቆዳ ለብሶ አጸጉርቶ
ተኮፍሶ ተዘባኖ
ቀላምዶ አመካክኖ
ዘመኑን አዘምኖ
አጉሮን በጉሮኖ
አልሸት አለን ፋኖ…
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
ብራንጎናትርን
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 736
Joined: Fri Dec 29, 2006 6:31 pm

Postby ብራንጎናትርን » Sun May 25, 2008 6:16 pm

"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
ብራንጎናትርን
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 736
Joined: Fri Dec 29, 2006 6:31 pm

ተጋላቢ አስራ ስምንት

Postby የቆሎተማሪው » Sun Aug 02, 2009 4:15 am

አባትየው

የልጁን ስም ለራሱ አውጥቶ
ልጁን ያለ መጠርያ ባዶውን ትቶ
እሱ ዘመኑን የራሱን ጨርሶ
በልጁ ውስጥ ይኖራል አሁንም ጎልምሶ
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

Postby ዘሚል » Sun Aug 02, 2009 5:51 am

የቆሎተማሪ ጨካኝ አረመኔ ነው:: በራሱ ላይ የማጭክን የሌላውን ጉዳት አይረዳም:: እስቴ ወንድ ከሆነ ላንዴ በአረመኔነቱ የሚቀበለውን ጭብጨባ ይቅርብኝ ብሎ ይህን የአረመኔ ልምዱን ያቁም::
ዘሚል
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 562
Joined: Sun Mar 08, 2009 1:53 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 2 guests