ተጋላቢ(አስራ ሰባት)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Re: ተጋላቢ አስራ ስምንት

Postby መልከጻዲቅ » Wed Aug 05, 2009 4:27 am

ሰላም የቆሎተማሪው ባጭር ቃላትና አገላለጽ ጥልቅ ክዋኔዎችን መግለጽ ትልቅ ስጦታ ነው:: አድናቆቴን ልገልጽልህ ነው:: በርታ:: 8)


የቆሎተማሪው wrote:አባትየው

የልጁን ስም ለራሱ አውጥቶ
ልጁን ያለ መጠርያ ባዶውን ትቶ
እሱ ዘመኑን የራሱን ጨርሶ
በልጁ ውስጥ ይኖራል አሁንም ጎልምሶ
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ትርንጎ* » Sun Aug 09, 2009 12:21 pm

የቆሎዬ አንኩዋን ደህና መጣህ...በል ፃፈው:: አንተ ሰው ግጥምህ ይፈናከታል ልበል? :D ታዲያ ችሎታ እኮ ነው:: በል አትጥፋ::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 709
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

እንክዋን ደህና መጣህ

Postby እፎይታ » Sun Aug 09, 2009 4:54 pm

እንክዋን ደህና መጣህ ወንድሜ ከብዙ ቆይታ በኈላ በርታ ግሩም ግጥም ነው;ግን እንደዚህ ይጠፍል እንዴ? መለስ ቀለስ እኮ ብል ድምጽህ ጠፋ, ደስ ብሎኛል በመምጣትህ
እፎይታ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 10
Joined: Wed Mar 09, 2005 5:08 pm
Location: united states

ተጋላቢ (እስራ ዘጠኝ)

Postby የቆሎተማሪው » Sun Aug 09, 2009 6:37 pm

ተጋላቢ (አስራዘጠኝ)

መልከፀዲቅ ትርንጎ እፎይታ [/b]ሰላምታዬ ይድረሳችሁ ስልምትስጡኝ አስተያየት እጅግ አመሰግናለው
እግዚያብሄር ይስጥልኝ
እመ-ቤት..

እኔ አምስት አስርታትን ኖሬ
ግማሽ ምእተ-አመት አስቆጥሬ
አንቺም አርባ ሻማዎችሽን አዳፍነሽ
ከኔጋራ የመንግስታችንን ዘመን ያህል ኖረሸ
አያሌ ምጣድ ተሙዋሽቶ ብዙ አክንባሎ ተሰብሮ
ያን ሁሉ ዘመን ተኑሮ
የጉልቻችንን እድሜ ቆይታ በአሃዝ ስጠይቅሽ
ስሌት ስለሚይዝልሽ
የደስታውም የመከራውም ቀናት ሲያበቃ ተቆጥሮ
ጨለማው ቀን ሁሉ ተደማምሮ
በእንዴት አይነት ስሌት አመጣሽው ዜሮ
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

Postby ራያራዩማ » Mon Aug 10, 2009 4:38 pm

የቆሎ ተማሪው እና የቆሎተማሪው......አንድ መሆናቸው ነው!? ወይ የዋርካ ነገር...........!?
ራያራዩማ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 16
Joined: Fri Jul 18, 2008 9:52 pm

Postby ቤቲ_13 » Sun Aug 16, 2009 4:52 pm

:roll: የቆሎዉም........ተመለሰ.........እረ እልልልል ቅልጥ ማድረግ ነዉ..... እንኩዋን ደህና መጡ አለቃ
Image
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby የቆሎተማሪው » Thu Apr 01, 2010 9:39 pm

ብርሃን ስንሻ፣ ጨለማወ ካየለ
ብርታትን ስንፈልግ፣ ክንዳችን ከዛለ
መሄጃ ከጠፋ፣ ደጁ ከተዘጋ፤
ምርኩዝ እንደገፍ በተስፋ እናንጋ።
ሽንፈት ከውስጥ ነው፣ መነሻ ዥረቱ
ከራስ መራኮቻ፣ መሽሎኪያው ካፎቱ
ቅዠት ቢመስልኳ የጨለማ ውበት
እሱ አይደለም ወይ፣ ጨረቃን እንደዛ፣ ፍንትው ሚያረጋት
ስለዚ እንዳሁን ጽልመት ሲጎንቦ
ብርሃን ሊወጣ ነው ሰፋ ይበል ልቦ…
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

Postby ስርርር » Fri Apr 02, 2010 6:44 pm

አቁማዳህ ሞልቶ ......... በቀይ ወጥ ባልጫው
ብሩህ ሆኖ አዕምሮህ ......... ቀለም የጠገበው
የልብስህ መአዛ ..................የእጣን ጧፉ ሽታው
የአምላክ ቃል ሆኖ ሳል ....... ልብህን የሞላው
ታድያ ምነው ሐገሬ ...... ስም ማውጣት ተሳነው
የቆሎ ተማሪ .................ብሎህ የሰየመው???

እድሉ ቢሰጠኝ ...... ተዘጋጅቻለሁ
አንተን ለመሰየም ......ብዙ መክሬያለሁ
የቀለም ቀንድ ብዬ.........ለአለም አውጃለሁ
___________________
እንደዚህ ያለ ንፁህ ብዕር ሳይ ደስ ስለሚለኝ ነው:: ሒስ ከተቀበልክ ደግሞ! (ማለቴ ለግጥሞችህ) ....ብዙ አለኝ
ሰላም!
ስርርር ትግራዋይ
Last edited by ስርርር on Tue Apr 06, 2010 7:50 pm, edited 1 time in total.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby የቆሎተማሪው » Sat Apr 03, 2010 3:27 am

ሰላም ሰላም ወንድሜ ስርርር ----
ስለመልካም አስተያየትህ ከልብ አመስግናለው፤ እግዝያብሄር ይስጥልኝ።
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

Postby ስርርር » Tue Apr 06, 2010 5:08 pm

ሰላም የቀለም ቀንድ!

በላ ቀለሙን አፍስልን! ምነዋ!
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

ተጋላቢ ሀያ እንድ

Postby የቆሎተማሪው » Sun Apr 25, 2010 2:02 am

ተጋላቢ ሀያ እንድ


መፈለግ ጎራዴ

ናፍቆትን ሰንቀው ፣ ከዋሉ በተስፋ
ቆንጆዋን ለማፍቀር ፣ እቅፎ ከሰፋ
ውዶን እስኪያገኙ ፤መጠበቅ ባልከፋ።
አንገት ሚያስደፋው ፣ ልብን ሚሰብረው
እሷም በተራዋ ሌላ ብትጠብቅ ነው
ስለዚህ ደጆንም ፣ እግሯንም ይቃኙ
በንውለላ አጥናፍ ፣በባዶ እንዳይናኙ
ከዚህ ሁሉ በላይ የተሻለው ዘዴ
ቋንጃ ለመስበርያ ቢጠፋ እንኳ ጓንዼ
ራስ ለመጠበቅ መፈለግ ጎራዴ ...
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

Postby ዋናው » Tue Apr 27, 2010 11:04 pm

ሠላም የቆሎ ተማሪ
ዋርካ ውስጥ ትመልሰህ ስላየሁ ደስ ብሎኛል::

እንደሁሌም ማለፊያ ስንኞች ናቸው.... ቃላት ይርቡልህ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby የቆሎተማሪው » Wed Apr 28, 2010 6:38 pm

ሰላም ሰላም ፡--- ወንድሜ ዋናው እንደምን ከረምክ ...
አበረታች ስለሆነው ግሩም አስተያየትህ እጅግ በጣም አመሰግናለው...
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

ተጋላቢ ሀያ ሶስት

Postby የቆሎተማሪው » Tue May 04, 2010 12:53 am

ስንት ነን
( ላንቺ ነው )


የኛ ሳይፈታ፣ ቋጠሮው ሳይረግብ፣ ሳይላላ ውጥረቱ
ተንፈስ ሳያሰኘን ፣ እፎይታ ርቆን ፣ ሳይረግብ ጡዘቱ
ሰብስቦ- ሰብስቦ ሽምቅቆ- ቆጣጥሮ
በድምፅሽ ምትሃት፣ ባንድ ልጥ ጠፍሮ
ፈገግታሽ፣ እንደ ፀበል በልባችን ተረጭቶ
ቃልሽ፣ ሚስጢረ ሙዳያችንን ከፍቶ
ጸዳልሽ፣ መታጠቂያ ጥብጣባችንን ፈትቶ፤
ለዛሽ፣ እንደ ፀደይ አደይ ፈክቶ
ውበትሽ ፣ወንዱን ሁላ ኣዘናግቶ
ብስለትሽ፣ ሰጋር ስሜታችንን ገርቶ
ባንድ አክርሞ፣ ባንድ አውሎ
እንደ እዝን ገበታ፣ ባንድ መሶብ ቀላቅሎ
በልባችን እልፍንጅ ያለከልካይ ስትኩነሰነሺ
እንደታሪክ እመቤት፣ ገነሽ ስትምነሰነሺ
እኛም- በኣዚምሽ አቅበጥብጥ ስንናጥ
በጫርሽብን አሳት ግመን ስንቀልጥ
ቀልሶ ኑዋሪ ልባችን ዘልኖ
ቆራቢ ገላችን በምኞት ሴስኖ
በየፊናችን ስናጎላጅ፤ ገዳችንን እንድትመርቂ
ምናልባት አንቺም በተራሽ፣ እንደኛው ብትማቅቂ
ያለ እጣ ክፍላችን ቅኔ እየዘረፍን
በኳሽሚያ ልሳን፣ ገድልሽን እየተረክን
ስምሽን እንደድርሳ ናት ባደባባይ እየደገምን
ባገደምሽበት እየተገኘን
በዋልሽበት እየከረምን
ነጋሪት ባስጎሰምን፤
ቀልባችን ሸፍቶ ባንቺ ዘንድ በታደመ
ፅኑ ሕመም ታመመ እንጂ ምን ተጠቀመ
የኛ ሳይፈታ፣ ቋጠሮው ሳይረግብ፣ ሳይላላ ውጥረቱ
ተንፈስ ሳያሰኘን ፣ እፎይታ ርቆን ሳንተነፍስ ፣ ሳይረግብ ጡዘቱ
በነጋ በጠባ ግድ የሚለን
ከመማችን አብልጦ ሚያመን
ሰርክ ሚያብሰለስለን
በቁጥር ፣ስንት ነን
የሚለው ስሌት ነው ያማቀቀን
እሱነው ድቅቅቅቅ.... ያረገን
የቆሎተማሪው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun Jun 08, 2008 7:15 pm

Re: ተጋላቢ ሀያ እንድ

Postby እተስፍ » Tue May 04, 2010 10:50 pm

የቆሎተማሪው wrote:ተጋላቢ ሀያ እንድ


መፈለግ ጎራዴ

ናፍቆትን ሰንቀው ፣ ከዋሉ በተስፋ
ቆንጆዋን ለማፍቀር ፣ እቅፎ ከሰፋ
ውዶን እስኪያገኙ ፤መጠበቅ ባልከፋ።
አንገት ሚያስደፋው ፣ ልብን ሚሰብረው
እሷም በተራዋ ሌላ ብትጠብቅ ነው
ስለዚህ ደጆንም ፣ እግሯንም ይቃኙ
በንውለላ አጥናፍ ፣በባዶ እንዳይናኙ
ከዚህ ሁሉ በላይ የተሻለው ዘዴ
ቋንጃ ለመስበርያ ቢጠፋ እንኳ ጓንዼ
ራስ ለመጠበቅ መፈለግ ጎራዴ ...


ጓንዴ ምንድ ነው??? የምታውቁ ካላችሁ ብትጠቁሙኝ. አመሰግናለሁ
እተስፍ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 92
Joined: Thu May 07, 2009 10:56 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests