ወራሽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Apr 03, 2008 10:47 am

ጨዋታን ጨዋታ እያነሳው የዛሬው ባለ ልደት ከዛሬ ብዙ አመታት በፊት በንጉሰ ነገስቱ ዘመን ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ዩንቨርሲቲ አስተማሪ በነበሩ ጊዜ በበርካታ ሹማምንቶች ቤት የእራት ግብዣዎች ላይ ተገኝተው እንደነበረና ..ከሁሉም በላይ በንጉሰ ነገስቱ ቤተመንግስት የግብር አዳራሽ ስለነበረው ግብዣ አንስተው ብዙ ብዙ ትዝታዎቻቸውን አጫወቱን ....በትዝታ ብዙ አመታት ወደ ኋላ ተመልሰው እነዛን ምርጥ ምርጥ ትዝታዎቻቸውን ካካፈሉንና እንባ ያዘሉ የሽማግሌ አይኖቻቸውን በመሀረባቸው ካባበሱ በኋላ ኪሳቸውን ደባብሰው አንድ አሮጌ ፎቶግራፍ አውጥተው እንደማስታወሻ ሰጡኝ
እኚህ ፕሮፌሰር በንጉሰ ነገስቱ ቤተመንግስት ከግብር በኋላ ንጉሰ ነገስቱ እንደማስታወሻ የሰጧቸው ፎቶግራፍ ነበር ...ከጀርባውም የንጉሰ ነገስቱ ፊርማ አለበት ..
የገዛ የሀገሬ ልጆች ንጉሱን "ሌባ ሌባ "እያሉ አዋርደው አስረው ለሞት ዳረጉት ......ይሄን ባደረጉ ገዢዎች ማንነቴን እንኳን በውል ሳላውቅ በሶሻሊዝም ርዕዮተ አለም ደድቤ ...ታላቁን ንጉሴን እንደ ሌባ ቆጥሬ አደኩ ...እነሆ ዛሬ በሰው ሀገር በሰው ሀገር ሰው የተከበረውን የሀገሬን ንጉስ ፎቶግራፍ ...ታላቁ የሀገሬ ንጉስ የፈረመበትን የራሱን ፎቶግራፍ ማስታወሻ ይሆነኝ ዘንድ ተሰጠኝ ...
የሀገረ ንጉስ ለማስታወሻ ፈርሞ የሰጣቸውን ማስታወሻ ለኔ አሳልፎ መስጠት ተገቢ እንዳልሆነ አምርሬ ተከራከርኩ ...ግን ሰሚ አልነበረኝም ...ፕሮፌሰሩ ሳቅ ብለው
"እኔ አርጅቻለሁ ...የዛሬ ልጆች ለእንዲህ አይነት ነገር ብዙም ክብር የላቸውም ...ይልቅ ተቀበለኝ "ታላቅ ንጉስ ነበር""እያሉ የገዛ ሀገሬን ንጉስ እንዳከብረው እንድመካበት እንድኮራበት ..ብዙ ብዙ አሉኝ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Apr 03, 2008 11:03 am

ጨዋታን ጨዋታ እያነሳው የዛሬው ባለ ልደት ከዛሬ ብዙ አመታት በፊት በንጉሰ ነገስቱ ጊዜ በዛሬው አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በቀድሞው ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ዪንቨርሲቲ መምህር በነበሩ ጊዜ በበርካታ ደጃዝማቾችና ሹማምንቶች ቤት እራት ተጋብዘው እንደነበረና በተለይም የኢትዮጲያውያንን የባህል ምግብ በጣም እንደሚወዱት ከሁሉም በላይ ደሞ ጥሬ ስጋ እንደሹማምንቶች ሁሉ እቆርጣለሁ ብለው ለጥቂት አፍንጫቸውን ቆርጠውት እንምደነበር እያጫወቱን ሁላችንንም አሳቁን ...
ብሮፌሰሩ በኢትዮጲያው ትዝታቸው ቀጥለው በንጉሰ ነገስቱ ቤተመንግስት የግብር አዳራሽም የንጉሱ እንግዳ እንደነበሩም ጭምረው ሲያወጉን አሁን ፊታቸው በሀዘን ጠቆር ማለት ጀምሯል ...
ፕሮፌሰሩ በትዝታ ብዙ አመታት ወደኋላ ተጉዘው ትዝታዎቻቸውን ካካፈሉንና እንባ የቋጠሩ የሽማግሌ አይኖጫጨውን በመሀረባቸው ካባበሱ በኋላ ወደ ኮት ኪሳቸው እጃቸውን ሰደው አንዲት አሮጌ ፎቶግራፍ አውጥተው ለማስታወሻ ይሆነኝ ዘንድ ሰጡኝ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Apr 03, 2008 11:16 am

የገዛ የሀገሬ ልጆች የሀገሬን ንጉስ "ሌባ ሌባ ůብለው አስረውና አዋርደው ለሞት ዳረጉት ...ይህን ወንጀል የሰሩ የሀገሬ ገዢዎች ማንነቴን እንኳን በውል ሳላውቅ በሶሻሊዝም ዕርእዮተ አለም አንጸው ታላቁን ንጉሴን እንደሌባ ቆጥሬ እንዳድግ አደረጉኝ
እነሆ ዛሬ በሰው ሀገር በሰው ሀገር ሰው የተወደደውንና የተከበረውን የሀገሬን ንጉስ ፎቶግራፍ ....ታላቁ ንጉስ የፈረመበትን የራሱን ፎቶግራፍ ማስታወሻ ይሆነኝ ዘንድ ተሰጠኝ ...
የሀገሬ ንጉስ ለማስታወሻ ፈርሞ የሰጣቸውን ፎቶግራፍ ለኔ ንጉሱን እንደሌባ ቆጥሬ ላደኩ ሰው አሳልፎ መስጠቱ ተገቢ እንዳልሆነ አምርሬ ተከራከርኩ ...ሰሚ ግን አልነበረኝም
የሽማግሌውን ፕሮፌሰር ትዝታ እንደሰረቀ ሰው እየተሰማኝ ፎቶግራፉን ተቀበልኳቸው ...ብሮፌሰሩም ሳቅ ብለው
"አየህ አንበሳዬ ...እኔ አርጅቻለሁ ..የዛሬ ልጆች ለእንዲህ አይነቱ ነገር እምብዛም ክብር የላቸውም ...ይልቅ ተቀበለኝ ቢያንስ ንጉሱ እንደ አምላክ ሆኖ ይጠብቅሀል ታላቅ ንጉስ ነበርና ሊከበር ሊመለክ ይገባዋል" አሉኝ
እንደ አምላክ ሆኖ ይጠብቅሀል "ሲሉኝ ሳቅ አልኩ ....አይ ፕሮፌሰር እግዜሩ እራሱ አምላክ መርጦ ልኮብኝ አበሳዬን እያየሁ መሆኔን ቢያውቁ ይሄን ባላሉ ነበር ....አልኩና በሆዴ ሳቅ አልኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Apr 03, 2008 12:01 pm

እኔ ምን ጊዜም በዚህ መልኩ ስለሀገሬ አስቤ አላውቅም ....ምንም እንኳን እኔን በሶሻሊዝም ዕርእዮተ አለም አንጸው ትውልድ ለመገንባት የታገሉት የተራ ወታደሮች ንጉሶች እንዳሉኝ ንጉሱ "ሌባ"ነበር የሚል እምነት ባይኖረኝም ..በተቃራኒው ንጉሱ በሚቻላቸው እና አቅምና ጉልበታቸው በፈቀደላቸው መጠን ሁሉ ሀገራቸውን ለማሳደግ ሌት ተቀን ጥረዋል ብዬ አስባለሁ ...በአንድ ወቅት አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የታሪክ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ በመጠኑም ቢሆን እንደተረዳሁት ንጉሰ ነገስቱ ወደ ስልጣን እንዳይወጡ እንቅፋት ይሆኑባቸው ከነበሩት የወሎ ሰዎች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ ...ምንም እንኳ ንጉሱ የወሎን ሰዎች ለመያዝ የወሎዋን ልዕልት አግብተው ልጆች ቢወልዱም የወሎ ሰዎች ይለም ንግስናው የኛ ነው አይገባህም እያሉ ደንቃራ በሆኑባቸው ጊዜ በሸዋ ሰዎች ታጅበው በሰገሌው ጦርነት የወሎን ሰዎች አሸንፈው ስልጣን ላይ ወጡ
ሀገራችን በጣልያን በተወረረችም ጊዜ ንጉሱ እንደ ጥንታውያን የኢትዮጲያ ነገስታት ሁሉ ጥራቸውን ይዘው ወደ ጦር ግንባር ሲሄዱ አሁንም የወሎ ሰዎች በመሬታችን ላይ አታልፍም ብለው በጦራቸው ላይ በተደጋጋሚ አደጋ ጣሉ ...
በማይጨው ጦርነት የተሸነፈው ንጉስ ጦሩን ይዞ ወደ ሸዋ ሲመለስ አሁንም የወሎ ሰዎች አበሳውን አሳዩት ...ከአርበኝነቱ በኋላ ንጉሱ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ያለፈው አልፏል ብለው ሀገራቸውን ሲያስተዳድሩ ቆዩ ...
ንጉሱን የመጣል የረጅም አመታት የወሎ ሰዎች ቂም ግን ዋንጫዋ የሞላቺው ብዙ ብዙ ቆይቶ ነው ...በጦርነት ያልቻሉትን የሸዋ ንጉስ የወሎ ሰዎች የረሀብ አድማ መተው ጣሉት.....የወሎ ሰዎች የተመኟትን ስልጣን ግን ንጉሱን ለከዱ የተራ ወታደሮች ጥርቅም አሳልፈው ሰጧት
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Apr 04, 2008 10:32 am

ያደሬና የወሎ ሰዎች ምን ጊዜም ከቤተመንግስት እርቀው አያውቁምና በወታደሮቹ ንጉሶች ዙሪያ ቆመው ብዙ ብዙ አጨበጨቡ ...የተራ ወታደሮች ጥርቅም ንጉሶችም ሽንፈት ሲገጥማቸው የወሎ ሰዎች ተገልብጠው ስልጣን ሊይዝ የሚሮጠውን የትግራይ ሽፍታ ደጋግፈው መንገድ እየመሩ ወደ ሸዋ ላኩት
እነሆ ዛሬም የትግራይ የሽፍታ ንጉሶች በጠረፍና በጫካ አናሳ ንጉሶች ታጅበው የሀገሬን ሰው ሲያምሱት የወሎ ሰዎች ከደጃፍ ቆመው ያጨበጭባሉ ...
እንዳው አነሳሁት እንጂ ...እኔ ያቺን ሚስኪን ሀገር የወሎ...የጎጃም ...የጎንደር...የትግሬ ...የሸዋ ...የወለጋ ..የሀረር ..የሲዳሞ ወይም የከፋ ሰዎች ገዟት አልገዟት ...ነገሱባት አልነገሱባት ምን ቸገረኝ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Apr 04, 2008 11:26 am

የፕሮፌሰሩን ልደት አክብረን ከተለያየን በኋላ ፕሮፌሰሩ በስጦታ በአደራ የሰጡኝን የሀገሬን ንጉስ ፎቶግራፍ ይዤ ወደቤቴ ሄድኩ ...
ትንሿ ቤቴ ጠዋት ጥያት እንደወጣሁ ነች ....መስኮቷን ከፈት አድርጌት ስለነበር ቤቷ በቀዝቃዛ አየር ከሞሞላቷ ውጪ ምንም አዲስ ነገር የለባትም ...ከየትስ አዲስ ነገር ይመጣል...እኔ እንደሆነ ጠዋት ወጥቼ ማታ ነው የምገባው ...ብቻ ፕሮፌሰሩ የሰጡኝን የሀገሬን ንጉስ ፎቶግራፍ ለክብሩ በሚገባው ቦታ ላይ መርጬ አስቀመጥኩት ... ...ከዛ ለጥቂት ጊዜ ትኩር ብዬ ሳየው ቆየሁና ..እንደነገሩ ልብሴን አወላልቄ አልጋዬ ላይ ተዘረጋሁ ...
ለስንት ያህል ጊዜ እንደሆነ እንኳን አላውቅም ብቻ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ
ወዲያው ከፈጣሪዬ ጋር መነጋገር ጀመርኩ
አይ ፈጣሪዬ አሁን ካላጣኽው ሰው እኔን ወራሽ ታደርገኛለህ ?በስንቱ መንገድ ይሆን የምትፈትነኝ ?ኧረ ተው ፈጣሪዬ ...ኧረ ተወኝ ..ኧረ ተው አትፈትነኝ ...ኧረ ተው ተው አንጣላ ተው ፈጣሪዬ ተው አንጣላ ..
እንዲህ እያልኩ ፈጣሪዬን ስማጸን ሳስፈራራ በላብ ተነክሬ ባነንኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Apr 04, 2008 11:37 am

ወይ የድሀ ህይወት ...እስቲ ይቺም ኑሮ ሆና ቀኑን በቢራ ቤት ተደብቄ እየቀመቀምኩ መሮሬን መፈጠሬን እረስቼ ሳሳልፍ ለሊቱን የማሳልፍባት ትንሿ ቤቴ እንኳን አልደብቅ አልሸሽግ ብላኝ ይህእው ለሊቱን የህልም ሽብር ትነዛብኛለች ...

እስቲ ሰው ካላጣው ባላጋራ ከፈጣሪው ጋር አታካራ ይገጥማል?እንዴት አይነት ግራ የገባው ነገር ነው

እስቲ ልነሳና በውሀ ተለቃልቄ እራሴን ወደምሸሽግበት ወደምደብቅበት እኔነቴን ወደምረሳበት ቢራ ቤቴ ልሂድ ...እብደት ቢጤ ሊጀምረኝ ነው መሰለኝ ..ኧረ እንዳውም ሳላብድ አልቀረሁም ....አብጄ መሆን አለበት እንጂ እንዴት እኔ እራሴ እራሴን ለመደበቅ ..እኔ እኔነቴን ለመሸሽ እሮጣለሁ ...የምር አብጄ መሆን አለበት እንጂ ..እንዴጽ ከገዛ ፈጣሪዬ ጋር ሙግት እገጥማለሁ ...በትክክል አብጄ መሆን አለበት እንጂ ፈጣሪዬ አምላክ መርጦ ባላከብኝ ነበር ...

እስቲ ይሁን አሁን የጠፋውን የማላውቀውን እኔነቴን ፍለጋ ልሂድ አሊያ ምንጊዜም እፎይታ አላገኝም ...የፈጣሪዬም አታካራ ይሄው መሰለኝ ....አዎ እኔነቴን ቆፍሬ ማውጣት አለብኝ ...እኔነቴን የገባሁበት ገብቼ ሳገኘው ያኔ ፈጣሪዬም ይታረቀኛል ...ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ...ግን ከየት ነው የምጀምረው ???
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Apr 04, 2008 12:40 pm

ሰሞኑን ፕሮፌሰሩ ልደታቸውን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሲያከብሩ ሰንብተው እኔም አዋያቸዋለሁ ብዬ በልቤ የያዝኩትን ..የአምላኬን የህልሜን የእኔነቴን ጉዳይ ለማንም ሳልተነፍስ ቀናቶች ተቆጠሩና እነሆ ዛሬ ፕሮፌሰሩ ብቅ ሲሉ ዛሬ ላዋያቸው ቆርጬ ተነሳሁና የተለመደውን የባህሉን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ዛሬ ይመቻቸው እንደሆነ ልጠይቃቸውና ጉዳዬን ከምን መጅከመር እንዳለብኝ ሳውጠነጥን ፕሮፌሰሩ ገላገሉኝ
"ታዲያስ አንበሳዬ ...ያቺን ጉዳይ ዛሬ በንወያይባት ምን ትላለህ ?አሉኝ
እኔም ሰሞኑን ስጨንመቅበት እንደሰነበትኩና ዛሬ ጥሩ የህልም መፍቻ ቀን ሳይሆን አይቀርም ምናምን እያልኩ ትንሽ ፈገግ አስባልኳቸውና ..ወንበሬን ስቤ ከፊት ለፊታቸው ተቀምጬ ታሪኬን ..ህልሜን አምላኬ የነገረኝ እኔነቴን ሰሞኑን እንደተዘጋጀሁበት ረጋ አብዬ አወራዋቸው ..
ስለ አምላኬ ሳወራቸው ሳቃቸውን ለማፈን እየታገሉ በጸጥታ አዳመጡኝ ....የአስፈሪዋን ህልሜን ጉዳይ አንስቼ ስለዛች አጭር ግን በጣም አስፈሪ ህልሜ ሳወራቸው ግን ፊታቸው ሀዘን አይሉት ብስጪት ቁጭት አይሉት ንዴት ብቻ እኔ እኔ በውል ያለየሁት ሁኔታ እየታየባቸው አሁንም በጥሞና አዳመጡኝ ....ከዛም በእማሆይ ቤት ሳድግ ስላሳለፍኩት ደስታ ያልተለያት ህይወት አጫወትኳቸውና ያቺን ቁራጭ ወርቅ አያቴ እማሆይ በሞት አልጋ ላይ ሆነው
"ያኔ ሲያመጡህ ይቺን አንገትህ ላይ አንጠልጥለህ ነበር "ብለው እንደሰጡኝ አጫወትኳቸው
ታሪኬን በታላቅ ትግስት ሲያዳምጡኝ የነበሩት ፕሮፌሰር ምንም ነገር ምንም አይስተያየት ሳይሰጡኝ ድንገት ተነስተው ወደ መጽዳጃ ክፍል ሄዱ ...

ከመጸዳጃ ቤት ተመልሰው ቢራቸው ጎንጨት ካሉ በኋላ
"አይዞህ አንበሳዬ ...እንደኔ እንደኔ ህልምህ ህልም ብቻ ላትሆን ትችላለች ...ምናልባትም በውነቱ አለም ባነ ላይ የተከሰተች ቁራጭ ታሪክ ልትሆን ትችላለች .....ወርቋንም አገላብጠው ካዩ በኋላ ...አይ ኢትዮጲያ ሚስጢርሽን መቼ ይሆን ከፍተሽ የምታሳዪን አሉ ...ፕሮፌሰሩ ቁራጯን ወርቅ ..አገላብጠው ሲያዩ በደንብ ስለተከታተልኳቸው ምናልባት በዚች ቁራጭ ወርቅ ላይ እኔ ያላስተዋልኩትን ነገር አይተውባት ይሆን ስል አሰብኩ ....
ፕሮፌሰሩ በመቀጠል
"አይዞህ አንበሳዬ ለሁሉም መላ ይፈለግለታል ..አሉኝና ቀጥለው
እስቲ ይቺን ወርቅ ወስጄ ለአንድ አዋቂ አሳያታለሁ ...አሉና ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን አውጥተው እዛው እንደተቀመጡ ደውለው ከሆነ ጓደኛቸው ከሚመስል ሰው ጋር ማውራት ጀመሩና ...አመስግነው ስልካቸውን ዘግተው እዛው ጠረጴዛዋ ላይ ወርወር አድርገዋት ...
እስቲ አንድ ጓደኛዬ ጋ እልክህና እሱ ያይሀል አሉኝ ...
የስነ ልቦና ሀኪም ጋ ሊልኩኝ ነው ...በስልክ ንግግራቸው እንደሰማዋቸው ቀጠሮ የያዙልኝ የስነ ልቦና ሀኪም በዚች ሀገር አለ የሚባል ስመ ጥር ሰው ነው ይሄ የስነልቦና ሀኪም ከበሽተኞቹ የሚጠይቀው ገንዘብ የክርስቲያን ልጅ የሚከፍለው አይነት እንዳልሆነ ስለምሰማ ...
የለም አይሆንም ...እኔ ለዚህ እውቅ ሰው የምከፍለው የለኝም ስል ተቃወምኩ ...ፕሮፌሰሩም ሳቅ ብለው
"አይዞህ አንበሳዬ ይቺ ሰው የሆነች ቁራጭ ወልታ ብጤ አለባት ...ለገንዘብ አታስብ ይልቅ የሚመጭን ቀን ቁረጥና ሂድ" አሉኝ
እምቢ ማለቱን እንደ ውለታ ቢስነት ቆጥሬ እንዲህ በችግሬ የሚረዱኝን ታላቅ ሰው ከመቀመጫዬ ተነስቼ ለክብራቸው የሚገባውን ምስጋና አቀረብኩ ..
እንግዲህ እኔነቴን ፍለጋ ህልሜን ልፈታ ልቦናዬን ልመረመር ወደ ሀኪም መሄዴ ነው
አብዷል ብለው በብዶች እስር ቤት ካላሰሩኝ እመለሳለሁ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Apr 07, 2008 1:54 pm

ወደ ስነ ልቦናው ሀኪም ለመሄድ ዝግጅቴን ጨርሼ ከቤት ስወጣ ድንገት ይሁን ሆን ብሎ ወደ ሰፈሬ መቶ ...አላውቅም ብቻ የሀገሬን ልጅና የረጅም አመታት ጓደኛዬን ውጪ ቆሞ ሲጃራ ሲያጨስ አገኘሁትና ትንሽ ተጫውተንና..ቀደም ብሎ የተያዘ ቀጠሮ እንዳለኝ ነግሬውና ይቅርታ ጠይቄው ወደ ቀጠሮዬ ቦታ ለመሄድ ስነሳ ...ልሸኝህ ብሎኝ ተከተለኝ ...እያወራን በአውቶቡስ ቀጥሎም በሜትሮ አብረን ሄድን ..ካሁን ካሁን ተሰናብቶኝ ይሄዳል እያልኩ ብጠብቅም ..ዝም ብሎ እያወራ እንደ ጥላ ይከተለኛል ...ግራ ገባኝ ...ወዴት እንደምሄድ እንዳልነግረው ገና ሳይጀመር የሰሞኑ የፕራግ ቢራ መጣጫ ወሬ ሊያደርገኝ ነው ...ዝም ብዬ የሚሆነውን እንዳላይ የቀጠሮዬ ሰአት ከመድረሱም በላይ በቀጠሮው ቦታ ደርሰናል ...እና ትንሽ አቅማምቼ ...እዚች ቦታ ለሆነች አጭር ስራ ቀጠሮ እንዳለኝና ከፈለገ ቡና ምናምን እየጠጣ ሊጠብቀኝ እንደሚቺል እየነገርኩ ካጠገባችን ያለቺውን ትንሽ ባር አሳየሁት ...
እሺ እጠብቅሀለሁ አለኝና ቻዎም ሳይለኝ ወደ ቡና ቤቷ ዘው ብሎ ገባ ...
መጣሁ አልኩና እኔም ወደ ዶክተሩ ሄድኩኝ ...
ገና የቪላዋን በር ከፍቼ ስገባ ዘበኛው በጥሩ ሰላምታ ተቀበለኝና የሚረዳኝ ነገር ካለ ጠየቀኝ ..እኔም ከሀኪሙ ጋር ቀጠሮ እንዳለኝ ስነግረው በር ከፍቶ ወደ ሳሎን አስገባኝ ...ሳሎን ስገባ ከአንድ ግማሽ ክብ ከሆነ ውብ ጠረጴዛ ስር አንዲት ቆንጆ ልጅ ተቀምጣ አየሁ ...ልጂቷ በታላቅ ፈገግታ በአይኗ ተቀበለችኝና ምን ልትረዳኝ እንደምትችል ያ ፍውግውግታዋ ሳይለያት ጠየቀቺኝ ..እኔም ለዘበኛው የነገርኩትን መልሼ ስነግራት እንደተቀመጠች ስልኩን ነካ ነካ አደረገሽና ስሜን ጠየቀቺኝ ነገርኳት ...ስሜን ተናግራ ትንሽ ጠበቀችና ሌላ ቃል ሳትጨምር ስልኩን ዘግታ ከመቀመጫዋ ተነስታ እንድከተላት ነገረቺኝ ...ተቀምጣ ሳያት በዛ ውበቷ እንዳልተማረኩ ሁሉ እረጅም ቂጧን ሳይ ወዲያው ሀሳቤን ቀየርኩ ...ባለ ረጂም ቂጧን ቆንጆ ተከትዬ ወደ ሀኪሙ በሽተኛ የስነ ልቦና በሽተኛ ማስተናገጃ መታከሚያ መመርመሪያ ስፊ ሳሎን ውስጥ ገባሁ .....ያቺ ቆንጆ በር ከፍታ አስገብታኝ በልሳ በሩን ዘግታብኝ ወደ ቦታዋ ተመለሰች ....ሰፊውን ሳሎን ባይኔ ሳማትር ...
"ጌታው ኖር ...እንኳን ደህና መጣህ "...እያለ ወደኔ የሚመጣ አንድ ኮሳሳ ...ጽጉሩን እንደ አነስታዪን ያንጨበረ...በ60ዎቹ ውስጥ የሚገመት ሰው አየሁና ...ምኑም ያልገባኝ ስሜት እየተሰማኝ እኔም ሰላምታዬን ላቀርብ ቃል ሳልተነፍስ ወደ ኮሳሳው ሰው ስሄድ መሀል ሳሎን ላይ ተገናኘንና እጅ ለ እጅ ተጨባበጥን ...
ኮሳሳው ሰውዬ ልክ ለረጅም አመታት የሚያውቀኝ ይመስል እጁን በትከሻዬ ላይ ጣል አድርጎ የሆነ ነገር እየቀባጠረ ወደፊት ሄደን ከሶፋዎቹ ጋ ስንደርስ ባሻኝ ቦታ እንድቀመጥ ገፋፋኝ ...እኔም በዘፈቀደ አንዷ ሶፋ ላይ ስቀመጥ ሶፋዋ ድሎት እንዳላት ተሰማኝ ...ምንም ሳይጠይቅ ሁለት ቢራዎች ይዞ መቶ ለሁለታችንም ከፈተና ያዝ ...እስቲ ለዛሬው ዝም ብለን ቢራችንን ይዘን እንጫወት ልትውውቅ ያህል አለኝ ...ይገርማል ...ይቺ ቢራ የትም ቢሄድ እግሬን ተከትላ ትመጣለች አልኩና በሆዴ እንደመሳቅ ብዬ ቢራዬን አንስቼ አጋጨሁና ተጎንጭቼ ..ወሬውን ጨዋታውን ኮሳሳው ሰውዬ ሀኪሜ እንዲጀምር ተውኩለት ...ዞሮ ዞሮ ስራው አይደል ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby Monica**** » Mon Apr 07, 2008 2:51 pm

ፓንኬኩ ጨዋታህን ወድጀዋለሁ በርታልኝ
ግን ያገሬ ስው እንደሚለው ባይቆጭ ያንገበግባል........
ያደሬና የወሎ ሰዎች ምን ጊዜም ከቤተመንግስት እርቀው አያውቁምና በወታደሮቹ ንጉሶች ዙሪያ ቆመው ብዙ ብዙ አጨበጨቡ ...የተራ ወታደሮች ጥርቅም ንጉሶችም ሽንፈት ሲገጥማቸው የወሎ ሰዎች ተገልብጠው ስልጣን ሊይዝ የሚሮጠውን የትግራይ ሽፍታ ደጋግፈው መንገድ እየመሩ ወደ ሸዋ ላኩት

ይሄ ነገር ምነው አደሬና ወሎዬ ላይ ብቻ አተኮረ? ኦሮሞስ አቅፎ ደግፎ አይደል እንዴ ያስገባችው? ወይስ ለራስ ሲቆርሱ አይነት ነገር ነው :lol: ይቺ መከረኝኣ ኢትዮጵያ እንዲሁ እርስ በእርሳችን ስንባላ ትታዘበናለች......

Code: Select all
 እነሆ ዛሬም የትግራይ የሽፍታ ንጉሶች በጠረፍና በጫካ አናሳ ንጉሶች ታጅበው የሀገሬን ሰው ሲያምሱት የወሎ ሰዎች ከደጃፍ ቆመው ያጨበጭባሉ ...

እረ ዘመዶቼን ለቀቅ :lol: .....ለራሱ ረሀብ የጠበስው ህዝብ ለሚበላው ዳቦ ያስብ ወይስ ማን የስልጣን ረሀብ እንዳለበት ይጨነቅ? የሁሉንም ውድቀትማ ወሎ ላይ ብለም ማድረግ ሀጥያት ነው በዛ ላይ ደሞ ወሎን ማን ነው ቤተመንግስት አስጠግቶት የሚያውቀው????
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Apr 07, 2008 3:41 pm

ኮሳሳውና ጭብራራው ሀኪሜ ጨዋታዋን ሲችሉባት የዋዛ አይደሉም ...በጫወታ መሀል ስለኔ ጉዳይ ያነሱና መለስ ብለው ሌላ ጨዋታ ይጀምራሉ ....ቀስ እያሉ ሁኔታዬን እያጠኑ እንደሆነ ግብቶኛል ...
ብቻ እንዲሁ የባጥ የቆጡን እያወራን ...እዚህ ገባ የማይባሉ ጥቃቅን ነገሮችን ሲጠይቁኝ ብዙም ሳልጨነቅ ስመልስላቸው...ሶስት ጠርሙስ ቢራዬን ልሼ ሌላ ቀጠሮ ወስጄ አመስግኜ ተሰናበትኳቸውና ወጣሁ ...ያቺ ቂጠ ረጅም ቆንጆ ሴትም በቦታዋ እንደተቀመጠች ፈገግታ ሳይለያት ተሰናበተችኝ ...ዘበኛውም እስከ ውጪው በር ድረስ ሸኝቶኝ መልካም ቀሪ ቀን ተመኝቶልኝ እኔ ከግቢው ስወጣ እሱ የግቢውን በር ዘግቶ ወደ ቦታው ተመለሰ ...እኔም ሁኔታዎችን እያሰላሰልኩ ወደ ሜትሮ ሳዘግም ...ያ ያገሬ ልጅ እኔን በዛች ትንሽ ቡና ቤት ተቀምጦ መጠበቁ ደብሮት ወደ ሜትሮው መግቢያ አካባቢ ካለች አንዲት የቻይና ፈጣን ምግብ መሸጫ ሱቅ ደጃፍ ላይ ቆሞ ቢራ እየጠጣ ሲጃራውን ሲያቦን አገኘሁት ...
ይገርማል ..ዘገየህ ብሎ እንኳን አንዲት ቃል አልተነፈሰም ...ትግስቱ ከመግረም በላይ አስፈራኝ ...ብቻ አሁንም የሆነ ነገር እያወራን ብቻ ተያይዘን ወደ ሜትሮ ጉድጓድ ውስጥ ገባን ...
ከጓደኛዬ ጋር ሳንነጋገር የተግባባን መሰለኝ አንዲት ቃል ሳንተነፍስ ሀበሾች ወደሚያዘውትሯት ቢራ ቤት በቀጥታ ሄደን ቢራችንን አዘን ከተቀመጥን በኋላ ነበር
"ለምን ዛሬ እንደፈለገኝና እንዲህ በትግስት እንደጠበቀኝ ማወቅ ፈልጌ በቀጥታ
"ለምን ጉዳይ ፈለከኝ አባ ?"አልኩት
"ምንም ጉዳይ የለኝም ...እንዲሁ ዝም ብዬ ቢራ አብሬህ መጠጣት ፈልጌ ነው "አለኝ ....
ችግሩ ምን እንደሆን በትኪኪል ባላውቅም ...እንደዋሸኝና ..እንዳው ዝም ብሎ ቢራ ብቻ አብሮኝ ለመጠጣት እንዲያ በታላቅ ትግስት እንዳልጠበቀኝ አውቄአለሁ ...
ብቻ እኔም እስቲ እራሱ ባለጉዳዩ ይጀምረው ብዬ ሁሉንም ለሱው ትቼ ...ቢራዬን እየለጋሁ ሲጃራዬን ማቡነኑን ተያያዝኩት
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue Apr 15, 2008 11:13 pm

የጓደኛዬ እንዲህ ትግስተኛ መሆን እየገረመኝ እኔም ትግስቴን ገዝቼ የሚሆነውን እየጠበኩ ..ሲጃራዬን እያቦነንኩቢራዬን እየለጋሁ በታላቅ ትግስት ብጠብቅም ...ጓደኛዬ በራሱ የሀሳብ ባህር በራሱ አለም ጠልቆና ሰምጦ ከሚያስፈራ ጸጥታ ውስጥ እኔንም ከተተኝ ...አልቻልኩም
ሁለት መለኪያ ቮድካ አዘዝኩና በትግስት ብጠብቀውም ፈጽሞ መፈጠሬን እንኳ እረስቶ በራሱ የሀሳብ ባቡር ነጉዷል...አስተናጋጁ ቮድካዎቹን ሲያቀርብልን ...ከተዘፈቀበት የሀሳብ አዘቅት ውስጥ እንደምንም ቀስቅሼ
"ለቴናችን" አልኩት የቮድካዋን መለኪያ እያነሳሁ
ጓደኛዬም እንደመባነን ብሎ መለኪያዋን አፈፍ አድርጎ ወደላይ በማንሳት "ለጤናቺን "ብሎ ከነ መለኪያ ጋር መለኪያዋን አጋጭቶ በአንድ ትንፋሽ ጨለጣት እኔም እሱን ተከትዬ የራሴን መለኪያ በትንፋሽ ጨለጥኳት ...

አሁን ጓደኛዬ ተመልሶ ወደዛች የሀሳብ ባህር ውስጥ ተመልሶ እንዲገባ መፍቀድ እንደሌለብኝ ተረዳሁና
"ታዲያስ ጨብሲ... ?"ስል አለዝቤ ጠየኩት
,እንደተከዘ
"አለን"አለኝ
"ችግር አለ...?"ስል እስቲ እንዲህ በትግስት እኔን ሲጠብቅ የዋለበትን የመጣበትን ጉዳይ ቢነግረኝ ብዬ ጥያቄዬን እንደ ቀልድ ወርወር አደረኳት
"አዎ"አለኝና ምንም አይነት ማብራሪያም ሆነ ስለ ችግሩ ፍንጭ ሳይይሰጠኝ ዝም አለ ...
የጨብሲ እንዲያ ያለ ወትሮው መተከዝና የቃላት ቁጥበኛ መሆን ከፍ ያለ ችግር ቢገጥመው እንጂ የጤና አይሆንም ብዬ አሰብኩ...
እንደማውቀው ጨብሲ ለማንም ለምንም ደንታ የሌለው ሰው ነው ...የመሰለውን ፍርጥርጥ አድርጎ በደቂቃዎች ውስጥ የመሰለውን የሚያስበውን የተሰማውን ዱቅ ያደርገዋል...ዛሬ ግን ሁሉም ከሚቻለው በላይ ሆነበት መሰለኝ ዝምታን መርጦ ቡዝዝ ብሎ ቴሌቪዥን እያየ ቢራውን ይስባል

ግራ ቢገባኝ
"ጨብሲ ...ችግሮች የሚፈጠሩት እንዲፈቱ ነውና እስቲ ስለተፈጠረው ችግር አውራኝ...የምችል ከሆነ እረድሀለሁ ...ካልቻልኩም የሆነ መላ እናበጅበታለን "ምናምን እያልኩ ጨብሲ ችግሩን እንዲነግረኝ አበረታታሁት
ይቀጥላል............
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed Apr 16, 2008 8:03 am

"
..."አየሽ ፓኑ..."አለና ሊናገር የፈለገውን መልሶ ተወው ...ጨብሲ ሁሌም እኔን አየሽ...አንቺኮ...እያለ እንደሴት ወይም እንደ ህጻን ነው የሚያየኝ የሚጠራኝ ...
ምንም እንኳን አንድ ሁለት አመት ቢበልጠኝም በቁመና የማንተናነስ ከመሆናችንም በላይ እኔ ትንሽ በስፖርት የተገነባ ፈርጠም ያለ ሰውነት ሲኖረኝ ..ጨብሲ የቢራዋ ቦርጭ ገባ ገባ ያሉት የራስ ጸጉሮጩ ...ያለ እድሜው ሽማግሌ አስመስለውታል ...ቢሆንም ምንም ቢለኝ አንድም ቀን ተቀይሜው አላውቅም ..
"በል እንጂ ንገረኝ ...ምን ተፈጠረ ::?"በድጋሚ አፋጠጥኩት

"ፓኑ ዛሬ በጠዋት ተነስቼ ወደ ስራ ለመሄድ ስዘጋጅ ...ያለወትሯቸው ከሀገር ቤት ስልክ ደወሉልኝ ...እና ስራ ቦታ ደውዬ ስራ እንደማልገባ ነግሬ ግራ ቢገባኝ አንተን ፍለጋ ወደ ሰፈርህ መጣሁ ...በራፍህ ግ ከደረስኩ በኋላ ሳልደውል እንኳን መምጣቴ እራሴን መልሷ አሳፈረኝ እና እራሴን ወቅሼ ወደ ሰፈሬ ልመለስ ሳቅማማ አገኘሁህ ..."ምናምን እያለ የተፈጠረውን ችግር ፍንጭ ጠቁሞኝ ዝም አለ ..
"ይቅርታ ጨብሲ ...የሆነች ቆራጣ ቀጠሮ ስለነበረችብኝ ...ይሄን ያህል ጊዜ ስላጉላላሁህ ..."እያልኩ ደጋግሜ ይቅርታ ጠይቄ ወደ ተፈጠረው ችግር እንዲመለስ ..
"እና ምን አሉህ ...ማለቴ በስልኩ ?ůአልኩት
"እ.. አዎ በስልኩ ...የልጅነት ጓደኛዬ አብሮ አደጌ የወንድም ያህል የምወደው ጓደኛዬ ..ታሞ መሞቱን እንደ ተራ ነገር ስልክ ደውለው ነገሩኝ "አለና በስጨት አለ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed Apr 16, 2008 3:20 pm

ወይ መከራ ....የሞወዱት ሰው ከዚች አለም ተሰናብቶ ሲሄድ ..እንደ ሀገራችን ባህልና ወግ ዑዑዑዑ ..ተብሎ የማይለቀስበት ሀገር ተሰደን ...ይሄው ጨብሲ ሀዘኑን የሚካፈለው ሰው ፍለጋ ሌላ መንደር ድረስ ቢመጣ ...እኔም በራሴ ጉዳይ ተወጥሬ ሳንከራትተው ውዬ በቢራና በቮድካ ሀይል ቀኑን ሙሉ ሰላም የነሳውን የአብሮ አደግ ጓደኛውን ሞት... የገዛ ዘመዶቹ በስልክ እንዳረዱት ...ሀዘኑን እንድካፈለው በትግስት ጠብቅ ለኔም አረዳኝ ..ለማላውቀው የጨብሲ አብሮ አደግ ጓደኛ ጨብሲን ብቻ ስለማውቀው አዘንኩ...
"አይዞህ ...ይሄ በማንም ላይ ሊደርስ የሚችል መከራ ነው ...አይዞን በርታ በርታ በል እግዜሩም ጥናቱን ይሰጥሀል አይዞን .."ምናምን እያልኩ ላጽናናው ሞከርኩ ...ጨብሲ ግን በአብሮ አደግ ጓደኛው ሞት ቢያዝንም የሆኑ ነገሮች እየከነከኑት በሀሳብ እርቆ ሄደብኝ ...

ቢቸግረኝ ሁለት መለኪያ ቮድካ አዘዝኩና ...መለኪያዎቹ ሲቀርቡ በደመነፍስ ያነሳትን መለኪያ አጋጨሁና
"የሞቹን ነብስ እግዜሩ ይምራት ዘንድ ተመኘንና" መለኪያችንን አጋጭተን በትንፋሽ ጨለጥናት
የጨብሲ ስምታ እያስፈራራኝ ...አሁን በምን መልኩ እንደማጽናናው የሲጃራዬን ጭስ በአይኔ እየተከተልኩ ሳሰላስል..

"አየሽ ፓኑ ...ከልጁ አብሮ አደግ ጓደኛዬ ጋር ከልጅነት እስከ እውቀት ብዙ ብዙ ነገሮችን አሳልፈናል ...እንደ ታላቅ ወንድም ቆጥሬው ነው ያደኩት ....መሞቱ ከማንም ሰው በላይ አሳዝኖኛል..አፌን አውጥቼ ባልጮህም ዑዑዑ ባልልም የእንባ ከረጢቴ ቢደርቅም ....ይሄው ቀኑን ሙሉ በውስጤ እያለቀስኩ እየተንጨረጨርኩ ባይሰማም በውስጤ ዑዑዑኡ እያልኩ እየጮህኩ ነው ...ግን ሰላም የነሳኝና እግዜሩ ድፍረቱን ነስቶኝ ...የገዛ ዘመዶቼ በስልክ ከምችለው ..ከምሸከመው በላይ የጣሉብኝ የዚህ አብሯደግ ጓደኛዬ አንድ ሌላ ሚስጢር አለው"አለኝ


ወይ ጉድ ይቺ ምድር በሚስጢር ተጥለቅልቃ ተተብትባ ነው ማለት ነው የምትኖረው ....ሰው ሞቶም ሚስጢሩ አብሮት የማይሞተው ጉድ ነው ...ምን አይነት ነገር እየተፈላሰፍኩ እንደሆነ ለራሴም ባይገባኝም ...ብቻ ጨብሲ የሟችን ሚስጢር ...ዘመዶቹ በስልክ የጫኑበትን ሊሸከመው የማይችለውን እዳ እንዲነግረኝ
"ምንድንነው ሚስጢሩ?"ስል ጨብሲን ሚስጢሩን አውጥቶ እንዲተነፍስ ወጥሬ ያዝኩት ..."ፓኑ ....ሟች.....የኔ አብሮ አደግ ጓደኛ ...ያንተ የቅርብ ጓደኛ የገብሱ ታላቅ ወንድም ነው ....ታላቁ ሚስጢር ይሄ ሆኖ የኔ ዘመዶች የማልችለውን አደራ የጫኑብኝ ደሞ በቅርብ ቀን ብሱ ወንድሙ እንደሞተ ማርዳት አለብኝ ....መርዶ ነጋሪነት ...የማልችለው ምንግዜም ልወጣው የማልችለው እዳ ነው ..."ምናምን እያለ ከኔ ምንም አይነት መልሶች አስተያየቶች ሳይጠብቅ ቢራውን አንስቶ በረጅሙ ሳበና ůእና ገብሱን ...ወንድሙ መም ኦቱን ማርዳት አለብኝ ..."አለና ርንባ ያረገዙ አይኖቹን በመሀረቡ ማሸት ሳይሆን ፈተጋቸው ነው የሚባለው
አሁን የጨብሲ ጭንቀት ግልጥ ብላ ታየችኝ ...የገዛ አብሯደግ ጓደኛውን ሞት ሀዘን አልበቃው ብሎ ...የሟችን ወንድም የስደት ሀገር ጓደኛውን ወንድምህ ሞቷል ..እርምህን አውጣ ብሎ መናገር አለበት ...ይሄ ደሞ ከሚቻለው በላይ ሆነበት ...አፉን አውጥቶ አንተ አርዳው ባይለኝም ..የዚች የጨብሲ መከራ ተካፋይ መሆኔን ሳልጠየቅ ተቀበልኩትና...ገብሱን በምን ወጥመድ አጥምጄ በመጪው ቅዳሜ የታላቅ ወንድሙን ሞት እንደማረዳው ማውጠንጠን ጀመርኩ ....
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Apr 17, 2008 10:11 pm

""ጨብሲ....ይሄን ነገር ለሌላ ሰው ተንፍሰሀል""ስል አጥብቄ ጠየኩት
""ኧረ በፍጹም ...የመጀንመሪያው ሰው አንተ ነህ ...ደሞስ እያወከው....ምን ሰው አለና ለማን ይነገራል...ፓኑ ..መቼም ከዚህ ጭንቀቴ እንደምትገላግለኝ አምናለሁ ...ሁሉንም ባንተ ልጥል ነው ...እኔ ወኔው የለኝም ""አልůአለኝ የሚለምኑ አይኖቹን በኔ አይኖች ላይ ተክሎ
"ግዴለም ...ለማንኛውም ሰሞኑን እኔ ሰፈር ማዘውተሩን አቁመህ ስልክ ስደውልልህ ...ለግል ጉዳይ የሚያስፈልጉህን ነገሮች ተቅልለህ ብቅ ትላለህ ....ለማደሪያ የኔ ትንሿ ቤት ትበቃናለች :::"ምናምን አልኩት ..ያው ቢያንስ እሱ በኔ አልጋ ይተኛል እኔ በፈረደባት አሮጌዋ ሶፋዬ ላይ እፈነገናለሁ ...ለነገሩ ያቺ መከረኛ አስፈሪ ህልሜ ሰላም ብትጸጠኝ አይደል ...አምላኬስ አንዴ እስከወዲያኛው ተሰናብቶኝ ሄዷል....አሁን አምላኬ መቶ መርዶ እንዴት እንደሚረዳ ቢነግረኝ ምንኛ በወደድኩ...ግን እሱ አንዲት ሚስጢር ነግሮኝ ሄዷል...ጨንሲ ወኔ ቢስ ሆኗል ...አሁን በታላቅ ድፍረት የምወደውንና ብቸኛውን ጓደኛዬን የሀገሬን ልጅ እንደ ወንድም የምቆጥረውን ታላቅ ሰው ....ወንድምህ ሞቷል እርምህን አውጣ ብዬ አይኑን እያየሁ መንገር አለብኝ ...አስቸጋሪ ነገር ...ግን የሆነ ሰው ሊነግረው ይገባል ...እናም ...ጭብሲ ወኔ ብያጣ ገብሱን ከኔ በላይ የሚቀርበው ሰው የለምና ....ቢጠላኝ ይጥላኝ እንጂ ይቺን ቁርጧ የታወቀች እውነታ እነግረዋለሁ ....እኔንስ አንድ ቀን አምላኬ የነገረኝን የማላውቃቸውን ወንድሞቼን አድራሻ አንድ ሰው ያበስረኝ ይሆኝ?...እግዜሩ ያውቃል ...አሁን ገብሱ ወሬ ሳይበዛ የውንድሙን መርዶ መስማት አለበት ....ለሌላው ጊዜ በሽ ነው ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest