ወራሽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Apr 28, 2008 2:53 pm

ጨብሲ ቀንበሩ እንደወረደለት የእርሻ በሬ እፎይ ብሎ አመስግንኖኝ እና ተሰናብቶኝ ሲህድ ከአረማመዱ ..ችግሩን ስለተጋራሁት በትንሹን ቢሆን ሀሳቡ ቀለል እንዳለው ያስታውቅ ነበር
በተለያየ ሰፈር ስለምንኖር የጉድጓዱን ባቡር በተለያየ አቅጣጫ ይዘን ተፈተለክን
ሰፈር ስደርስ ሞቅ ቢለኝም የተለመደቺውን ቢሮዬን ስላጎበኝ ወደዛች የተረገመች ትንሿ ቤቴ ገብቶ መንፈንገሉን ስላልጣመኝ ጎራ ማለቱን መረጥኩና ወደዛቺው ቢራ ቤት አመራሁ
...ቢራ ቤቷ ስደርስ መማሸት በመጀመሩ አብዛኛዎቹ ሽታም ጋስቶች የእለት ተግባራቸውን ፈስጽመው ወደ ቤታቸው ጎጇቸው ከሄዱ ትንሽ ቆየት ብለዋል ....ፕሮፌሰሩም የሉም
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu May 08, 2008 10:05 am

የታላቋ ቢራ ቤት መዘጊያ ሰአት እየተቃረበ በመሆኑ ወደታላቋ የክብር ቦታዬ ሳልሄድ በቀጥታ ወደመስተናገጃው ቦታ ሄጄ አንድ ቢራ ገዛሁና ወደ አዳራሹ ሄጄ የማውቀው ሰው ፍለጋ በአይኔ ማማተር ጀመርኩ...እንዲህ በአይኔ የማውቀው ሰው ሳፈላልግ ገብሱን ከሩቅ በሶስት ቆነጃጅቶች ታጅቦ በአረንጓዴው ጠረጴዛ ላይ የተበተኑትን ትንንሽ የድንጋይ ኳሶች በዘንግ ሲጠነቁል አየሁት .....ከዚች ትንሿ የገነት አለሙ ልረብሸው አልፈለኩም...እቅዴ ከተሳካልኝ በመጪው ቅዳሜ ሀዘን መከራ ይጠብቀዋል ..ለዛሬ አለሙን ይቅጭ ብዬ ወደሱ ሳልሄድ እንዲሁ በአይኔ ሌላ የማውቀው ሰው ፍለጋ ሳማትር ኦንድራ ቱማን አየሁትና ወደ ቱማ ጠረጴዛ ሄጄ ሰላምታ ካቀረብኩለት በኋላ በሱ ጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጥ እንደምችል ጠይቄ መልስ እንኳ ሳልጠብቅ ወንበር ስቤ ከቱማ ፊት ለፊት ተቀመጥኩ .....ገና ከመቀመጤ ቱማ ...እየተፍነከነከ ወንድሜ ገብሱ በብዙ ቆነጃጂት ሴቶች ታጅቦ የዘንግ ጨዋታ እየተጫወተ መሆኑን ነገረኝ
እኔም እንዳየሁት ነግሬ ብርጭቆዬን አነሳሁና "ናዝድራቪ"አልኩት
ናዝድራቪ በዚህ ሀገር ቋንቋ "ለጤናችን "እንደማለት ነው ..
ቱማም የተጋመሰች የቢራ ብርጭቆውን አንስቶ "ናዝድራቪ"አልኝና ብርጭቋችንን አጋጭተን ቢራችንን ተጎነጨን
ኦኛ ቱማ የኔ የረጅም ጊዜ የት/ቤት ጓደኛዬ ነው...ሁለታችንም የክርስቶስን እድሜ ከዘለልን ጥቂት ብንሰነባብትም ...እስካሁን ሁለታችንም አላገባንም ልጆችም ወደዚች ምድር አላመጣንም
ይሁንም እንጂ ..ቱማ ከኔ በብዙ መልኩ ይለያል ...በተሰቦቹ በሱ ስም በትውልድ መንደሩ መሬት ገዝተው የመኖሪያ ቤት እየሰሩለት ነው ...ምንም እንኳን እንደኔው ከዚች ቢራ ቤት የማይጠፋ ሁለተኛ ደረጃ ሽታምጋስት ቢሆንም ...የቤተሰቦቹን እዳ በየወሩ ከደሞዙ እየቆረጠ ይከፍላል ...ሚስት ልጅ ባይኖረውም እስኪሞት የሚኖርበትን የራሱን ቤት እየሰራ ነው ...ፈረንጅ ሁሌም ቀድሞ መውደቂያውን አስቦ ያዘጋጃል...እና የኦኛ ቱማ የቤት እዳ መክፈል ወይም ቤት መስራት ብዙም አያስደንቅም ...ብቻ ከኦኛ ቱማ ጋር የባጥ የቆጡንእያነሳን ስንቀባጥር ...ገብሱ ወደ ኦኛ ቱማ ጠረጴዛ መቼ እንኳን እንደመጣ ሳላስታውን ድንገት መቶ በኔ ላይ ወረደብኝ

"እናትክን ቢራ ቤትህ እርሜን ብመጣ ..ለሰላምታ እንኳን ..ትኮራብኛለህ ""ምናምን እያለ ወረደብኝ
"ኧረ ጌታው ..ላልረብሽህ አስቤ እንጂ ማየቱንስ አይቼህ ነበር ....ቆንጆዎቹን እስክጸናበት እየጠበኩ ነበር ...ምናምን እያልኩ ላስተባብለው ሞከርኩ ...ገብሱም ሁሉን ነገር ወደጎን ብሎ ...ሴቶችንም እንደነዛ የደንጋይ ኳሶች በአረንጓደው ጠረጴዛ ላይ በትኗቸው ከኛ ጋር ተቀመጠና የሶስት ጓደኛሞች ወግ ተጀመረ ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu May 08, 2008 12:12 pm

እንዲህ ሶስት የጥንት ጓደኛሞች በአንዲት ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠን ስናወጋ ..ገብሱ ድንገት ጨዋታችንን አቋርጦ
"መጣሁ "አለና እግረ መንገዱን እነዛን ቆነጃጂቶች በአርንጓዴው ጠረጴዛ ላይ የተበተኑትን በተለያዙ ደማቅ ቀለማት የተጌቱትን ትናንሽ የድንጋዝ ኳሶች ብቻቸውን በዘንግ እንደጠነቁሉ ይቅርታ ጠይቆና አመስግኖ ወደመስተናገጃው ቦታ ሄዶ ለሶስታችንን ሶስት መለኪያ ቮድካ ይዞ መጣና "ሁላችንም "ናዝድራቪ"ብለን መለኪያችንን አጋጨንና በአንድ ትንፋሽ ጨለጥናት ...
ኦኛ ቱማና ገብሱ በነዛ ሴቶች ዙሪያ በተነሳ ወሬ ሲተራረቡ እኔ ከጥቂት ሰአታት በፊት ከጨብሲ ጋር ተቀምጬ በሀሳብ እንዴት ገብሱን ማጥመድ እንዳለብኝ ሳውጠነጥን የነበረውን ሀሳቤን እንደገና ቀስቅሼ በድጋሚ እያውጠነጠንኩ በሀሳብ ከሁለቱ ጓደኞቼ በጣም እርቄ ሄድኩ...
ሁለቱ ጓደኞቼ በነዛ ውብ ሴቶች ዙሪያ በተነሳ ወሬ ተጠምደው እኔ በሀሳ ካጠገባቸው ብዙ እርቄ ሄጄ በጫወታቸው ሳልሳተፍ ዝም ብዬ በሀሳብ ብቻዬን ስደቅ እንኳ ሳያስተውሉ አሁንም በዛው ጨዋታቸው ቀጥለዋል
...
እንደምንም ብዬ አሳቤን ቀጨሁና
"ጎበዝ "አልኩና ከዛ ጣፋጭ ጨዋታቸው መለስኳቸው
"አቤት ፓኑ "አለኝ ኦኛ ጆሮውን ብቻ ወደኔ አቅንቶ በአይኑ ገብሱን በጨዋታቸው እንደሚቀጥሉና እንዳያመልጠው እየጠበቀ

አርብ ማታ ያለ አንዳች ግርግር በፈለጉት ቢራ ቤት ልጋብዛቸው እንደምፈልግ ነገርኳቸው ....በዛች ጣፋጭ ጨዋታቸው ለመቀጠል ፈልገው እንደሆነ ወይም ለኔ ባላቸው ወንድማዊ አክብሮት ብቻ አላውቅም ያለ አንዳች ማንገራገር በአንድ አፍ ተቀበሉኝ ...እኔም የአጋጣሚዎችን መሳካት የአምላኬ እጅ እንዳለበት እያሰብኩና እያመሰገንኩት ቢራና ቮድካ ሄዶ ከመስተናገጃው ቦታ ማምጣት የኔ ተራ ስለነበር ጓደኞቼን በነዛ ውብ ሴቶች ዙሪያ ባነሱት ጨዋታቸውእንደቀጠሉ ሳልረብሻቸው ግዳጄን ልፈጽም ተነስቼ ሄድኩ...
በዚህ መልኩ አንዴ እኔ አንዴ ገብሱ አንዴ ኦኛ ቢራና ቮድካ እያመጣን ስንጠጣና ስንጫወት ....የቢራ ቤቷ መዘጊያ የመጨረሻ ደቂቃ ተቃረበ መሰለኝ ..."የመጨረሻ ቢኦራ ውሰዱ ሲባል ሁላችንም የኦኛ ቱማን ጠረጴዛ ለቀን ወደመስተናገጃው ቦታ ሄደን የመጨረሻዋን ቢራ ወሰድን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu May 08, 2008 2:51 pm

የመጨረሻዋን ቢራ ሂሳብ ኦኛ ቱማ ካልከፈልኩ ብሎ ስከራከር ..ገብሱ ከፈለና የመጨረሻዋን የምሽቷን ቢራ አንስተን አሁን በ ናዝድራቪ ምትክ "ለጤናችን"አልንና ተጎነጨን ኦኛ ቱማና ገብሱ አሁንም በነዛ ውብ ሴቶች ዙሪያ ያነሱትን የወሬ ጥጥ ያባትላሉ ይነድፋሉ ....ወሬያቸውን በውሉ ስላልተከታተልኩ ....ጣልቃ ሳልገባ ወሬያቸው ቀዝቀዝ እስኪል ጠብቄ የአርቡን ቀጠሮ አንሳሁና
"በስካር መንፈስ እሺ ብላቹህ እንዳትቀሩ "ብዬ አስረግጬ ስናገር ....ሁለቱም በቅንነት እያዩኝ ..እዝቺው እኔ ቢራ ቤት እንዲሆንና ሽማግሌዎቹን ሽታምጋስቶች ላለመረበሽ በኦኛ ቱማ ጠረቤዛ ዙሪያ እንድንቀመጥ ተወስኖ ...ሁላችንም የመጨረሻዋን ቢራ አንጠፍጥፈን ጠጥተን ብርጭቋችንን ለቢራ ቀጂው መልሰንና አመስግነን ..መልካም ቀሪ ምሽት ተመኝተን ...ወደየ ማደሪያችን ሄድን ...አስፈሪ ህልሜን ደብቃ ለሊት በህልም ሽብር የምትነዛብኝን ትንሿን ቤቴን ከፍቼ መብራት እንኳን ሳላበራ በትንሿ አልጋዬ ላይ ከቀን ድካሜና ስካሬ ትንሽ ላርፍ ዠው ብዬ ወደኩባት ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu May 08, 2008 3:17 pm

እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም ማልጄ ተነሳሁና ለወንድ ልጅ የሚበቃውን ያህል ከተጸዳዳሁና ከታጠብኩ በኋላ ዛሬ ለሚጠብቁኝ ሁለት ቀጠሮዎች መዘጋጀት ጀመርኩ ...

የመጀመሪያው ቀጠሮ ከስነ ልቦናው ሀኪሜ ጋር ነው...ሁለተኛው ያው ከ ኦኛ ቱማና ከገብሱ ጋር ነው

...ይቺ ደቃቃና ጭብራራ ሀኪሜ ዛሬ ምን ደግሳ እንደምትጠብቀኝ ስለማላውቅ ..ቅድመ ዝግጂት ማድረጉ ዋጋ ቢስ መሆኑን ተገንዝቤ ቢያንስ በመጠኑም ቢሆን አለባበሴን ለሰውዬው ክብር ሲባል ማሳመር እንዳለብኝ በመገመት ...ብሎም በሁለቱ ቀጠሮዎቼ መካከል ወደ ቤቴ ተመልሼ ልብስ ለመቀየሪያ የሚሆን ጊዜ ስለማይኖረኝ ..ለሁለቱም ቀጠሮች የሚስማማ ልብስ መረጣ ላይ ልክ እንደ ሴት ልጅ ረዘም ያለ ጊዜ አጠፋሁ ...በመጨረሻ ሸሚዝ ኮትና ጂንስ ሱሪ ከስፖርት ጫማ ጋር መልበሱና መጫሙ ..ማንንም እንደማያስከፋ አምኜ ለባበስኩና ...ወደ መታጠብያ ክፍሌ መራመድ ጀምሬ እንደገና ወደ ክፍሌ ተመለስኩና የእጅ ስልኬን አንስቼ ለጨብሲ ደወልኩለት ...ጨብሲ ገና ስልኩን እንዳነሳ የወጉን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ..ኮስተር ብዬ ..አጠር አድርጌ በዛሬው ከኦኛ ቱማና ከገብሱ ጋር ባለኝ የቢራ ቤት የቢራ ቀጠሮ ..ልክ ድንገት እኔን ፍለጋ እንደመጣ ሰው አመሻሽቶ መቶ እንዲቀላቀለን ...ከዛ በፊት መጠጥ የሚባል ነገር እንዳይቀምስ አስጠንቅቄ ነገርኩትና እሱም እግዜር ያክብረው አክብሮ ቃሉን ስለሰጠኝ..ተሰናብቼው ስልኬን ዘጋሁናጸጉሬን ለማበጣጠር ወደ መታጠቢያ ክፍሌ ስገባ በመስታወት ውስጥ እራሴን አየሁትና ወይ ጉድ አልኩ ....ትናንት አንድ ሳአድ የሚባል ጓደኛዬ ያንን አፍሮ ጽጉሬን አሳጥሮ አስተካክሎኝ ስለነበር በመጠኑም ቢሆን ውበት ጨምሬ የ25 አመት ጎረምሳ መስዬ ነበር ...ቢሆንም ቀኑ የወንድ ልጅ ውበት ማድነቂያ አይደለምና ...ቀልጠፍ ብዬ አበጣጠርኩና ፊቴን በፊት ቅባት አበስ አበስ አድርጌ አንድ ሁለት ጊዜ ... ዞር ዞር ብዬ አየሁና ያኔ ለጣሊያኖጩ የጨርቃጨርቅ ድርጅት ስሰራ ያከበትኩት ልምድ በዛሬው አለባበሴ ብዙ እንደረዳኝና ከዚህ በላይ የጨዋ አለባበስ የለም እያልኩ በውስጤ ጥሩ ስሜት አሳድሬ ለመጀመሪያዋ ቀጠሮዬ ትንሿን መከራ ሽብር ነዢዋን ቤቴን ቆልፌ ወደ አውቶብስ ፌርማታ አመራሁ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu May 08, 2008 3:59 pm

በቀጦሮዬ ቦታ ደርሼ የቪላዋን የውጭ በር ደውል ስደውል ....ዘበኛው የክብር ሰላምታ ብቻ አቅርቦልኝ ያ ፈገግታው ሳይለየው ወደ ቪላዋ የሚወስደውን መንገድ በእጁ እየጠቆመኝ ዘልቄ እንድገባ ብቻ ፈቀደልኝ እንጂ እንዳለፈው እስከ አዳራሹ ድረስ አልሸኘኝም ...እኔም አንዴ መንገዱን ስላየሁት ሳልከፋ ወደ አዳራሹ/ሳሎን/ የሚያስገባውን በር ከፍቼ ገባሁ...በአዳራሹ ጥግ ላይ ባለው ግማሽ ክብ ጠረጴዛ ጀርባ ባለፈው ተቀምጣ የነበረቺው ያቺ ወጣት ቂጠ ረጅም ቆንጆ ዛሬ የለችም ...በምትኳ የሄ ነው የሚባል ውበት የማይታይባቸው እድሚያቸው ወደ ሀምሳዎቹ መጨረሻ የሚጠጋ አንዲት ደንዳና ባልቴት ተቀምጠዋል...እኔው ወደ ባልቴቷ በቀጥታ በመሄድ ዛሬ ከሀኪሙ ጋር ቀጠሮ እንዳለኝ እና ሙሉ ስሜን ነግሬ ቆምኩ ...ባልቴቷም ብዙ ሳይጨነቁ የቀጠሮ መያዣ ማስታወሻውን ገልመጥ ብለው አይተው ብዙም ሳይጨነቁ እንድከተላቸው ብቻ አንዲት ቃል ወርውረው የ ሀኪሙን የስራ ክፍል በር ከፍተው እንድገባ ከጋበዙኝ በኋላ በሩን ዘግተውብኝ ወደ ቦታቸው ተመለሱ...
በዛች ቢሮ ማንም ሰው የለም ...እና ባለፈው ስደናገር ያላስተዋልኳቸውን ነገሮች ተረጋግቼ እየተዟዟርኩ መመልከት ጀመርኩ ...ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያ ጨብራራ ኪሲታ የስነ ልቦና ሀኪሜ አንድ እስካሁን ያላስተዋልኩትን በር ከፍቶ ሁለት ቡናዎች በትንሽ ብርማ ትሪ ላይ ደርድሮ አንዳጎበጠ መቶ ጠረጴዛ ላይ ካሳረፈ በኋላ የተለመደውን የሀገሬውን እንኳን ደህና መጣህ
ሰላምታ ልክ እንደ አብሮ አደግ ጓደኛ እየለገሰኝ እግረ መንገዱን ሶፋዋ ላይ ተቀምጬ ቡናዋን እንድጠጣ ጋበዘኝ ....እኔም በአክብሮት ተቀብዬ ዛሬ በቡና የተጀመረው የሀኪሙ ድግስ የት እንደሚያደርሰኝ ስጠባበቅ
"ጌታው የየት ሀገር ቡና ይመስልሀል?"ሲል ድንገት ጥያቀውን እንደቀልድ ሰነዘራት

"የሲዳሞ ቡና ይመስላል "አልኩትና አይኔን ወደ እቃ መደርደሪያው ወረወርኳት ..ኮሳሳው ሀኪሜም አይኔን ተከትሎ የገዛ መደርደሪያውን አያትና በሳክ ተንፈራፈረ
እኔ ወደ ቢሮው በዛች ባልቴት ተገፍቼ ስገባ ኮሳሳው ሀኪሜ በርነቷ በውል በማትታይ ግዋዳ ውስጥ ቡና ለማፍላት ሲንደፋደፍና እኔ የነበረጪኝን አጭር ጊዜ ተጠቅሜ የሀኪሜን ቢሮ ስቃኝ በቃ መደርደሪያው ውስጥ የሲዳሞ ቡና የሚል በአማርኛ በ እንግሊዘኛም ፊደል የተጻፈበት ቆርቆሮ አይቼ እንጂ ..ቡናው በእውነት የሲዳሞ ቡና መሆኑን በጣሙ አውቄው አልነበረም ..."የሲዳሞ ቡና ይመስላል "ያልኩት ..ብቻ ይቺ ኮሳሳ ሰውዬ እንደቀልድ እየተፈታተነችኝ እየፈታተሸችኝ እንደሆነ ገብቶኛል
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu May 08, 2008 4:19 pm

ዛሬም ያው የመጣሁበትን ጉዳይ ምንም የረባ ነገር ሳናነሳ በኢትዮጲያ ቡና ወሬ ዙሪያ ስናወራ የተፈቀደችልኝ ሁለት ሰአት ተገባደደች ...ነገሩ ባልከፋ ነበር ...ጨብራራው ኮሳሳው ሀኪሜ ሲጃራ አጫሽ መሆኑ በከንፈሮጩ ጠባሳ ቢያስታውቅም እሱም ስላለኮሰ እኔም ድፍረቱ ኖሮኝ ማጨስ እንደምችል እንኳ ሳልጠይቀው የዛሬው ቀጠሮዬ አለቀች ....ይቺ ኮሳሳ ሰውዬ ዛሬ ያለ ወትሮዋ እስከ ውጪው በር ድረስ ሸኘችኝና ...ለስንብት እጄን ስዘረጋ
ůቆይ አትቸኩል "አለኝና በመቀጠል
"ስጃራ ይዘሀል "ሲል በልመና መልክ ጠየቀኝ
እኔም ሀኪሜን ተሰናብቼ ስጃራዬን የምለኩስባትን ሰከንድ በታላቅ ትግስት ስጠብቅ ስለነበረ ደስ እያለኝ ለሀኪሜ አንድ ሀባ ካቀበልኩት በኋላ ለራሴም አወጣሁና መጀመሪያ ለሱ ከዛ ለራሴ ለኩሼ ከግቢ ውጪ ከአንዲ ዛፍ ስር ቆመን ማጨስ ጀመርን


ሀኪሜ ሲጃራዋን ደጋግሞ በረጅሙ ከሳበ በኋላ
ůአየህ ጌታው ያቺ የተቀበለችህ እንግዳ ተቀባይ አሮጊት ...ሚስቴ ናት ......ማጨስ ከልክላኝ መከራዬን እያሳየችኝ ነው "አለና በሳቅ ተንከተከተ ...እኔ የምር ሲጃራ ጠምቶኝ ስለነበረ ሁለተኛዋን ሲጃራ ሁለታችንንም ለኮስንና ጥቂት ተጫውተን ለሁለተኛው ቀጠሮዬ በሰአት ለመድረስ የሚያመቸኝን አጭር መንገድ አስልቼ ሀኪሜን ስሰናበት ...
"የዛሬ ሳምንት ስለዛች አስፈሪ ህልምህ እናወጋለን ...ከቻልክ በጥቂቱ ማስታወሻ ብጤ ነገር ለመያዝ ሞክር ..ካልሆነም ግድ የለም "አለኝና መልካም ቀሪ ቀን ተመኝቶልኝ የሲጃራዋን ቁራጭ ወርውሮ ማስቲካ እያኘከ ወደዛች ሰፊ ቢሮው አመራ ...
እኔም ሀኪሜን ተሰናብቼ ወደ ሜትሮ ጉድጓድ ስገባ ...
"ወይ ጉድ በገዛ ቪላው እግዜሩ አምባገነን ሚስት ልኮበት ይሄው ሲጃራ ማጨስ መጠጥ መጠጣት ከልክላው ...የአለም ዜና ማሰራጫዎች እንደታላቅና እውቅ የነ ልቦና ሀኪም የጻፉለትንና የተናገሩለትን ሰው በአንዲት አሮጊት በአንዲት ቪላ ውስጥ በቁም እስር ወድቆ ይንገላታል ...ይሄስ ህይወት ነው ?ምናምን እያልኩና አጉል እየተፈላሰፍኩ በሁለተኛው ቀጠሮዬ በሰአቱ ለመድረስ የሚያስችለኝን የምድር ውስጥ ባቡሬን ይዤ ተፈተለኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu May 08, 2008 5:10 pm

ከርሰ ምድርን በርቅሶ በሚበር ትራፊክ በማያቆመው ባቡር ስጓዝ ቆይቼ በሁለተኛዋ ቀጠሮዬ ማለት ከ ኦኛ ቱማና ከገብሱ ጋር በነበረኝ ቀጠሮ መድረስ ከሚገባኝ ሰአት ግማሽ ሰአት ያህል አርፍጄ ብደርስም ኦኛ ቱማም ሆነ ግብሱ በቦታው አልነበሩም ...ብቻ ፕሮፌሰሩን በክብር ቦታቸው ተኮፍሰው ቢራቸውን ሲያጣጥሙ ስላያዋቸው ለክብራቸው የሚገባውን ሰላምታ ለማቅረብ ወደተከበረ ዙፋናቸው አመራሁ ...
እኔ ወደሳቸው ማምራቴን ያዩት ፕሮፌሰር አስተናጋጁን ቢራ እንዲያመጣልኝ በምልክት ነግረው በታላቅ ልባዊ ፈገግታ ከዙፋናቸው ፊት ለፊት እንድቀመጥ ጋበዙኝ .....የለም አልቀመጥም ቀጠሮ አለኝ ማለቱ ከብዶኝ ከፊት ለፊታቸው ባለች ወንበር ላይ ተቀምጬ አስተናጋጁ ያመጣልኝን ቢራ አረፋው እስኪረጋጋ ጠብቄ
"ውድ ፕሮፌሰር ናዝድራቪ" አልኩና ብርጭቆዬን ሳነሳ እሳቸውም ብርጭቋቸውን አነሱና "ናዝድራቪ"ብለው አጋጨንና ብራችንን ተጎነጨን ...
ከፕሮፌሰሩ ጋር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ከስነ ልቦናው ሀኪሜ ማለት እሳቸው መርተው ከላኩኝ ሀኪሜ ጋር ስላሳለፍኩት ነገር አጠር አድርጌ ጥቂት አወራዋቸው..
ፕሮፌሰሩ ሳቅ ብለው ..የወሬ መስመራቸውን ድንገት ለውጠው ሁለቱ ጓደኞቼ ኦኛ ቱማና ገብሱ እዚህ እንደነበሩና እራት ሊበሉ ወደ ተማሪዎች ክበብ እንደሄዱ..እና እንደሚመለሱ እሳቸውም የወንድማቸው ልጅ ዛሬ ከእንግሊዝ አገር ሊጎበኛቸው እንደሚመጣ እና በግዜ ወደ ቤት መግባት እንዳለባቸው ..እና ሌሎች ቀልዶች ቀላልደውብኝ አሁንም ሳቅ ሳይለያቸው እዛች ቢራ ቤት ብቻዬን ጥለውኝ ወደ ቤታቸው ሄዱ ...
የፕሮፌሰሩን ግብዣ ጠጥቼ አሁን በራሴ ሂሳብ አንድ ቢራ በቀጥታ ከመስተናገጃው ቦታ ገዝቼ ወደ ኦኛ ቱማ ጠረጴዛ አመራሁ ... ...በኦኛ ቱማ ጠረጴዛ ዙሪያ አመቺ ነው የምለውን ወንበር መረጥኩና በዛች ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጬ ስለ ገብሱ እያሰብኩ ሁለቱን ጓደኞቼን መጠበቁን ቀጠልኩበት...ትንሽ የዘገዩ መስሎ ስለታየኝ የእጅ ስልኬን አውጥቼ ለጨብሲ ደወልኩና ከቻለ ከአንድ ሰአት በኋላ ስልክ እንዲደውልልኝ ነገርኩት ጨብሲም እንደሚደውልልኝ ቃል ገብቶ ስልኩን ሲዘጋ ..ኦኛ ቱማና ገብሱ እየተሳሳቁ ወደ ቢራ ቤቷ ሲገቡ ከርቀት አየዋቸውና እፎይ አልኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat May 10, 2008 9:41 am

ጨብሲን መጀመሪያ አመሻሽቶ ድንገት እንዲመጣ መንገሬምናልባት በትንሹም ቢሆን ገብሱን ጥርጣሬ ውስጥ ይከተዋል ብዬ በመፍራቴ ጨብሲ ደውሎ "የት ነው ያለኽው ?"ቢለኝ ያጋጣሚ ጉዳይ እንዲመስል ነበር ጨብሲ ከ አንደ ሰአት በኋላ እንዲደውልልኝ ማድረጌ
ኦኛ ቱማና ገብሱ በተማሪዎች ክበብ እራታቸውን በልተው ከግማሽ ሰአት በኋላ ጨብሲም ደወለልኝና ...ቢራ ቤቴ እኔ ግብሱ እና ኦኛ ቱማ አብረን እንዳለን ሁለቱ ጓደኞቼ እንዲሰሙኝ በመጠኑም ቢሆን ድምጼን ከፍ አድርጌ ከነገርኩት በኋላ መቶ ቢቀላቀለን ሁላችንም ደስተኞች እንደምንሆን ነግሬ ጋበዝኩት ...ጨብሲን ሁላችንም ከልብ በመነጨ ፈገግታ ተቀብለን ቢራችንን ይዘን የባጥ የቆጡን ስንቀባጥር ...ያልተጋበዘ ያልታሰበና ያልተጠበቀ አንድ ሌላ ሸሪፍ የሚባል የኢትዮጲያ ልጅ መቶ ተቀላቀለን ...
በመሰረቱ ሸሪፍ መጥፎ ልጅ አይደለም ...ግን እኔ የማልወድለት አንድ መጥፎ ጸባይ አለው ..ያ ጸባዩ ደሞ ለነገው በገብሱ ላይ ለጠነሰስኩት ጥንስስ ገና ሳይጀመር የሚያደፈርስብኝ ሰው መስሎ ስለታየኝ በኛ ጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጡን ጠላሁት ...ግን ምንም አማራጭ የለኝም
"ዞር በል "ብዬ ላባርረው ብችልም ያንን የሚያደርግ አንጀት የለኝም ...እና ያለኝ አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ናት ...ሸርፊን በግዜ አስክሮ ወደቤቱ መሸኘት ....አለበለዚያ በነዛ ሽርፍርፍ ጥርሶቹ መካከል ቀድማ የምትሾልከው ምላሱ ትንሽ የወሬ ፍንጭ ካገኘት ከቢቢሲ ቀድማ መላውን ፕራግ ትበጠብጠዋለች
እኔ ሸሪፍን አስክሮ በጊዜ ነገር ሳያበላሽ ለመሸኘት ሳወጣና ሳወርድ ኦኛ ቱማ ገላገለኝ .....መቼ እንኳን እንደተነሳ ሳላስተውል ..አምስት ትላልቅ ቮድካዎች ይዞ መጣ ....ሸሪፍ ደሞ አልጠጣም ብሎ ድርቅ አለ ...በኋ በስንት ልመናና ማባበል ...የብርቱካን ጭማቂ መጣለትና ያቺን መርዝ ከጣፋጯ የብርቱካን ጭማቂ ጋር ቀላቅሎ ፉት ማለት ሲጀምር በልቤ ደስታ ተሰማኝ ...ሁለተኛዋን ዙር ሸሪፍ ስላዞረ ..ሽሪፍዬም መርዟን ፉት እያለች ስታስገባ ለሶስተኛው ዙር ሳትበቃ በሁለት ቮድካ ተጠናቃ እየተወላገደች ወደ ቤቷ ሄደችልን .እፎይ አልኩ ....ግን የሸሪፍን ምሽት እንዳበላሸንበትና የማይወደውን መጠጥ እንዲጠጣ ከገፋፉት አንዱ በመሆኔ ትንሽ ቅር ቢለኝም ለጥሩ ነገር ታስቦ የተደረገ ነው ብዬ እራሴን እያጽናናሁ... ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆኑ በተለይ ጨብሲ እንዳይሰክር በአይኔ መቆጣጠሩን ሳላቆም በጨዋታው ልቤ ሌላ ቦታ ቢሆንም እየተሳተፍኩ ቢራዎች እንኳ ላመጣ ስሄድ ሽሪፍን እንዲያግዘኝ አብሮኝ እንዲሄድ እያደረኩ ...በዚህ መልኩ ስንጫወት አመሻሽተን ወጡ ሲባል ብርጭቋችንን መልሰን ቢራ ቤቷን ለቀን ወጣን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat May 10, 2008 12:24 pm

እኔ ግብሱና ኦኛ ቱማ የምንኖረው በአንድ ህንጻ ውስጥ ነውና ጨብሲን አስከትለን ወደ መኖሪያ ቤታችን ሄድን ...ግብሱም ሆነ ኦኛ ቱማ የኔ ቤት ጠባብና ትንሽ መሆኗን ስለሚያውቁ ...ጨብሲ እኔጋ ይደር እኔጋ አይነት ነገር ሙግት ገጥመው መሀል መንገድ ላይ ቆሙ ...ግብሱ እየሄደ ማውራት የማይሆንለት ግራ ሰው ነው ...ታዲያ የምሽቷ ቀዝቃዛ ንፋስ ስትኮረኩረኝ ..."እረ ባካችሁ እየሄዳችሁም ማውራትኮ ትችላላችሁ" ስል ጮክ ብዬ ተናገርኩ
ፓኑሻ አይዞን ለብርዷ አንዲት የሀበሻ አረቅ አስጨልጥሻለሁ እያለ አላገጠብኝ ...በመጨረሻም የምሩን አንድ ጠርሙስ የጎጃም ዳግም አረቄ እንዳለው እየማለ እየተገዘተ እንድናምነው እና አብረን እቤቱ ሄደን እንድንጋበዝለት ለመነን ...እኔ ባይለምነኝም እቤቱ የማድርበትን መንገድ ስቆፍር ስለነበር ያለምንም ማመንታት ግብዣውን ተቀብዬ ኦኛ ቱማንም አብሮን እንዲሄድ ገፋፋሁት ....ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በግብሱ ሰፊ እልፍኝ ውስጥ ተቀምጠን የጎጃሟን ዳግም አረቄ ተቀዳልንና "ለጤናችን" አጋጭተን እንደ ቮድካዋ በአንድ ትንፋሽ እንዳይጨልጥ ኦኛ ቱማን አስጠንቅቄው ስለነበር የመለኪዋ ወገብ ድረስ አጋምሶ ሲውጥ ያ ነጭ ፊቱ በርበሬ እየመሰለ መምጣት ጀመረ ...ነበሩ ቢያስቀኝም ሳቄን አፍኜ እንቅልፍ እንደያዘው ሰው ደረጃ በደረጃ በገብሱ ሶፋ ላይ ጋደም ማለት ጀመርኩ ...
"አንበሳዋ በአንድ የጎጃም ጥይት ወደቀች"መሰለኝ እያለ ገብሱ ሲቀልድብኝ ብሰማውም ...ምንም እንዳልሰማ ሰው ድምጼን አጥፍቼ ተኛሁ ...ዛሬ ማንኮራፋት ብችል ኖሮ ያለምንም ይሉንታ የውሸቴን አንኮራፋ ነበር .....ብቻ ኦኛ ቱማ ተሰናብቶ እስኪወጣና ጨብሲም እንግዳ ክፍል ገብቶ እንዲተኛ አንሶላና ብርድልብስ ሲሰጠው ..ገብሱም ወደመኝታ ቤቱ ግብቶ በሩን ሲዘጋ እፎይ ብዬ እቅዴ ሁሉ እንደተሳካልኝ በማመን በገብሱ ሶፋ ላይ ከነልብሴ ተኛሁ ....ጨብሲ እግዜር ይስጠው ጫማዬን አውልቆልኝ ግብሱም እናቱ በቅርብ የላኩለትን አዲስ ጋቢ ደርቦልኝ ስለነበር ብዙም ሳልከፋ እንቅልፍ ልመናዬን ተያያዝኩት ....ክብዙ ልመና በኋላ ..የጎጃሟም አረቄ ተባበረችኝ መሰል ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ...ያቺ የተረገመች በገዛ ቤቴ ፍዳዬን የምታሳየኝ ህልሜ ዛሬም የገብሱን ቤት በር ከፍታ ገብታ ከገብሱ ሶፋ ላይ ወርውራ ጣለችኝ ...ዛሬ ግን ያቺን መከረኛ ህልሜን አልረገምኳትም እንዳው ላመሰግናት ዳዳኝ ......ያኔ ለማስመሰል ገብሱ ሶፋ ላይ ጋደም ስል የጅ ስልኬን ከኪሴ ሳላወጣና ጠዋት እንድትቀሰቅሰኝ ሰአት ሳልሞላት ለማስመሰል ስጣደፍ በመርሳቴ ተናድጄ ነበር ...ቢሆንም መከረኛዋ ህልሜ በምፈልገው ሰአት በዱላም ቢሆን ቀሰቀሰችኝ ...ወዲያው ተነሳሁና ...ፊቴን ታጥቤ አደራረኩና ወደ እንግዳ ክፍል ሳመራ ጨብሲን ኩርምት ብሎ ተቀምጦ ሲተክዝ አገኘሁት ...ሚስኪን እንቅልፍ ባይኑ እንዳልዞረት በርበሬ የመሰሉት አይኖቹ ይመሰክሩ ነበር ...በል ና አልኩና ተያይዘን የገብሱን የመኝታ ቤት በር አንኳኩተን ገባን ...ገብሱም እንደሁልጊዜው ልማዱ ሁሉ ማልዶ ይነቃና ከአልጋው ውስጥ ሳይወጣ መጽሀፉን እያነበበ አገኘነው
"ተነስ ልብስህን ልበስ "አልኩት ኮስተር ብዬ
ለምን?ብሎ እንኳን ሳይጠይቀኝ ቀልጠፍ ብሎ ለባበሰና
"እራባቹህ አይደል?"አለን
በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ላረዳ ነው ....ምን ልበለው ???
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ትርንጎ 123 » Tue May 27, 2008 12:45 am

እጅ ለመንሳት ነው
ትርንጎ 123
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 253
Joined: Sun Feb 03, 2008 6:14 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Jun 23, 2008 11:10 am

በቅድሚያ በህይወት ጣጣ ስለጠፋሁ እጅጉን በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ
...ወራሽ...ይቀጥላል
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Jun 23, 2008 11:35 am

ገብሱ ቀልጠፍ ብሎ ከለባበሰ በኋላ የራበን የጠማን መስሎት በየዋህነት ወደ ማድቤት ሊያመራ ሲል ....
""ቁጭ በል የምነግርህ ነገር አለ "አልኩና ትከሻውን ይዤ አልጋው ላይ አስቀመጥኩት
ጥቂት ፍጥጥ ብሎ ሲያየኝ ቆየና
"ፓኑ ምንም ነገር አትንገረኝ ....ያ ልክስክስ ወንድሜ ሞተ አይደል ?"አለኝ
""አዎ አርፏል ....እርምህን አውጣ ""አልኩት
ገብሱ አላለቀሰም ...አልተናደደም ...ትንሽ ኮስተር ብሎ አየኝና የእጅ ስልኩን አነሳና ደወለ ...የተደወለለት ሰው ከጥቂት ቆይታዎች በኋላ አነሳ መሰለኝ ...
"እኔ ነኝ ...መቼ ሞተ ?"ብሎ በአጭሩ ጠየቀና ...የተደወለለት ሰው የሚነግረውን ማዳመጥ ጀመረ ....የስልኩን ተቀባይ ወሬ ሲሰማ የገብሱ ገጽታ ለማየት ለማጥናት ብሞክርም ...ምንም የሚነበብ ነገር አላየሁም ....
እንዲሁ ሲያዳምጥ ቆይቶ ...
"መቼ ቀበራችሁት ሲል ለሁለተኛ ጊዜ ጠየቀና እንደገና ማዳመጥ ጀመር ...በዚህ መሀል በጁ ስልክ ውስጥ ያለው ገንዘብ አለቀ መሰለኝ ስልኩ ተቋረጠ ...
ስልኩን በስጨት ብሎ ወደ አልጋው ወረወረና ፊቱን ወደኛ ሲመልስ ...ጨብሲ ኩምትር ብሎ እንደተቀመጠ ስቅስቅብ ብሎ እያለቀሰ ስነፈርቅ
"ምናባክ ታለቅሳለህ ?"አለና አንድ ጊዜ በካልቾ አነሳው

ጨብሲ ካልቾ ሲቀምስ መነፍረቁን አቆሞ ተኮማትሮ ከተቀመጠበት እንደ አቦ ሸማኔ ተወርውሮ የገብሱን አንገት አነቀው ...ምን አይነት ተአምረኛ ሀይል እንደከለከለኝ እንጃ ..ለመገላገል እንኳ ሳልሞክር እንደተናነቁ ትቻቸው ወደ ማድ ቤት ገባሁ...
ማቀዝቀዣውን ከፍቼ ሶስት ቢራዎች አወጣሁና ወደ ገብሱ የመኝታ ክፍል ስመለስ ተቃቅፈው ሲላቀሱ አገኘዋቸው ......ከዛ በባዶ ሆዳችን አፋችንን በጥርስ ቡርሽ ፋንታ በቢራ ተግሞጥሙጠን ወደ ሳሎን ሄደን ተቀመጥን ...የሚያወራ የለም...ያንን አስፈሪ ዝምታ ደፍሮ የሚሰብር ሰው ጠፋ ...ዝም እንደተባባልን ተፋጠን ተቀመጥን ...
ግራ ቢገባኝ የተቋረጠውን የሀገር ቤት ስልክ እንዲቀጥል የራሴን የእጅ ስልክ አቀበልኩት .....ምንም ሳያንገራግር ተቀበለኝና ደወለ...አሁን እናቱ አነሱ መሰለኝየአነጋገሩ ለዛ ተለወጠ ...ደጋግሞ ደጋግሞ እናቱን አበረታታቸው ...
"አይዞሽ እማ ....አይዞሽ እማ ......ጠንከር በይ እማ ..."እንዲሀይነት በሀዘን የተሞሉ ቃላቶችን ለእናቱ ሲናገር ሰማነው ....ያ ጠንካራ ብረት ሰው በአንድ ጊዜ የተፈታ የተረታ እስኪመስል ድረስ አይኖቹ በንባ ተሞልተው እናቱን በተደጋጋሚ ካበረታታ በኋላ ...በኋላ እንደሚደውል ቃል ገብቶ ስልኩን ዘጋ ..
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Jun 23, 2008 12:07 pm

በዚህ መሀል እኔ ፈጣን ቁርስ አዘጋጀሁና ቁርሷን ቀማምሰን ቡና እየጠጣን
"ለመሆኑ በምን በሽታ ሞተ ይላሉ?"ሲል ገብሱ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ ጨብሲን ጠየቀው
"በሳንባ ምች ነው አሉ"አብሎ መለሰ ..አሁንም አይኖቹ እያረገዙ የሚወልዷቸውን እንባዎች በእጁ እያበሰ ..
ገብሱ አሁን የንዴት ሳቅ ስቆ
"የማትረቡ ...ደደቦች ...ውሸታሞች ...ሞቶ እንኳን የሞተበትን በሽታ ለመደበቅ ለመሸፋፈን ትሞክራላቹህ ...ምናለ አንድ ቀን እንኳን እውነት ለመናገር ብትሞክሩ ...ነገሮችን በእውነተኛ ስሞቸው ለመጥራት ብትደፍሩ ......እኔ እንደሆነ በዛች ልክስክስ ጠራርጌ በሽታ እንደሞተ አሳምሬ አውቃለሁ ....አንቺም እድሜ ለኔ በይ ባላወጣሽ ኖሮ ......እንደሱ ስትልከሰከሽ ፍግም ብለሽ ነበር ..."ምናምን እያለ በጨብሲ ላይ ወረደበት
ጨብሲ ምንም አልመለሰለትም ...ብቻ የበለጠ ሆድ ባሰው መሰለኝ እንዴ ሴት ልጅ እንደተቀመጠ መነፍረቅ ጀመረ
ግብሱን ይሄ ተገቢ እንዳልሆነ ከሱም የማይጠበቅ መሆኑን ለመናገር አስቤ ...ወደ ገብሱ ፊቴን ስመልስ ..ገብሱ ከተቀመጠበት ተነስቶ ከጨብሲ ጎን ተቀመጠና ትከሻውን ይዞ ...
"አይዞህ አታልቅስ ...ወንድማችን ወደማይመለስበት አለም እኛን ጥሎን ሲሄድ ቢያሳዝንም ..ቢያስለቅስም ..እዬዬ ቢያስብልም ...እኛ ጠንካሮች መሆን አለብን ...ሌሎች ብዙ ትናንሽ ወንድሞችና እህቶች ስላሉን ቢያንስ ለነሱ ስንል ጠንካሮች መሆን አለብን .....አይዞህ "እያለ አበረታታው ...
በመጨረሻ ይቺ የመርዶ ወሬ ከዚች ቤት ጓዳ ወታ ወደ ሌሎች ጆሮ እንዳትደርስ ደጋግሞ አስጠነቀቀውና
"በሉ ተነሱ እንውጣ "አለን
በዚህ መሀል ኦኛ ቱማ መጣና አራት ሆነን ከቤት ወተን ወደ ቢራ ቤቷ ስናመራ ..መንገድ ላይ
ገብሱ ኦኛ ቱማን እጁን ይዞ ...
"ኦኞ የማታው የፓኑስሀ ቲያትር የኔን ወንድም መሞት ለመንገር ነበር ...በማይድን በሽታ ተይዞ ታሞ እንደነበረ ከማወቄም በላይ የሚሞትበት ጊዜ እንኳ እሩቅ እንደሞይሆን አውቅ ነበር ..ቢሆንም ሁለተኛ አይኑን ማየት እንደማልችል ...ወንድሜ እስከመጨረሻው ወደማይመለስበት አለም መሄዱን ስረዳ አዝናለሁ ..."እያለ ስለወንድሞ መሞት በግልጽ አጫወተው

ኦኛ ቱማም "ሀዘንህን እግዚያብሄር ያቅልልህ..."ብሎ ከአበረታታው በኋላ እሱም የሀዘኑ ተካፋይ እንደሆነ ከልቡ ገለጸለት
...እንዲህ ገብሱና ኦኛ ወደኋላ ቀርተው የሆነ ነገር ሲነጋገሩ እኔና ጨብሲ ወደ ቢራ ቤቷ ገብተን በኔ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀመጥን ...እነ ገብሱም መጡና ቢራችን ሲቀርብልን ሁላችንም ከመቀመጫችን ተነስተን ብርጭቋችንን ከራሳችን በላይ ከፍ አድርገን አንስተን ለሞች የገብሱ ወንድም ነብስ አጋጭተን ቢራችንን ተጎነጨንና ተቀመጥን ...እግዚያብሄር ነብሱን ይማራት
አሁን ትንሽ ዝምታ የሰፈን ሲመስል ...
"ጎበዝ..እንግዲህ የሆነው ሆኗል ...እኔ ምንም ግርግር አልፈልግም ...ይቺን የሀዘን ወሬ ሁላቹህም ለራሳቹህ ተዋት..".እያለ ደጋግሞ አስጠነቀቀን ...ለነገሩ ጨብሲ እንዳያወራ ቀደም ብሎ ተነግሮታል የአሁኗ ለኦኛ መሰለችኝ...እኔ ትንፍሽ እንደማልል ገብሱ አሳምሮ ያውቃል
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Jun 23, 2008 12:54 pm

ሁላችንም ይሄ "እንዳታወሩ"የገብሱ ፍላጎት ከሆነ ፍላጎቱን ማክበር ግዴታችን መሆኑን ገልጸን ..ለማንም እንደማናወራ ቃል ገብተን አረጋገጥንለት ..
ግብሱ ትንሽ ቢራዎች ከወሳሰድን በኋላ ወደ ልጅነት ዘመኑ ተመልሶ ከሟች ወንድሙ ጋር ያደርጉት ስለነበረው የልጅነት ዘመናቸው ከጨብሲ ጋር እየተቀባበሉ ሲያወሩን በሳቅ አለሞሞታችንንም ጉድ ነው እንዲህ አስደሳቹን የልጅነት ታሪካቸውን ስሰማ እና ስስቅ አልፎ አልፎ ሀዘንም ይሰማኝ ነበር .....ምንም እንኳን እንደነገብሱ አይነት አስደሳችም ይሁን አሳዛኝ የልጅነት ዘመን ታሪክ ሊኖረኝ እንደሚችል ብገምትም ...አለማወቄ ከአስር አመቴ ጀምሮ ከሴት አያቴ ጋር ብቻዬን ያደኩ ሰው መሆኔ ትዝ ሲለኝ ትንሽ አዘን አልኩ .....

እኔ እንዲህ ስለራሴ እያሰብኩ ስተካክዝ ..ኦኛ ቱማ አንድ የአውሮፕላን ትኬት መሸጫ የጉዞ ወኪል ቦታ ደውሎ ..ከብዙ ንትርክ በኋላ አንድ ትኬት ማለት ወደ ኢትዮጲያ ማግኘቱን ገለጸልን ...

ወዲያው ገብሱ ወደ ጨብሲ እያየ
"ጨብሲ ቢራ ደጋግሚና ..ወደ ቤትሽ ሄደሽ ለጉዞ ተዘጋጂ ...ከነገ ወዲያ ወደ ኢትዮጲያ ትበራለህ "..አለው ...ከኦኛ ቱማ የቀበለውን ማስታወሻ አጣጥፎ ወደ ኪሱ እየከተተ
"አንተስ?"ሲል ጨብሲ ላቀረበው ጥያቄ
ግብሱ ትንሽ በስጨት ብሎ
"እኔ ብዙ ጣጣ አለብኝ ...ከመስሪያ ቤትም በአፋጣኝ ፈቃድ የማገኝ አይመስለኝም ...ደሞም ለሁለት ሰው በአንድ ጊዜ ትኬት መግዛት ሊከብድ ይችላል ..ሆነ ቀረ አንተ ትሄዳለህ ...እኔ ቀስ ብዬ እመጣለሁ ...ሌላውን ቀስ ብለን እንነጋገራለን ..አሁን ቢራህን ጨርስና ሄደህ ተዘጋጅ "አለው ...
ጨብሲ ቢራውን ጨርሶ ሂሳብ ልዝጋ እያለ ሲግደረደር
"ግዴለም ..ተማሪ እዚህ ቤት አይከፍልም "ብሎ ኦኛ ቱማ አሰናበተው ...ጨብሲም ሁላችንንም ተሰናብቶ ..ወደ ሀገር ቤት ከመሄዱ በፊት እንደምንገናኝ ተናግሮ ወደ ቤቱ ሄደ
ሶስታችን የመጨረሻዎቹ የቅርብ ጓደኛሞች ወንድማማቾች በአንዲት ጠረፔዛ ዙሪያ ተቀምጠን የባጥ የቆጡን ስንቀባጥር
ገብሱ ድንገት የወሬ መስመሩን ለውጦ
"ፓኑ ..አንድ እኛን የቅርብ ጓደኞጭን ...ወንድሞችህን የምትደብቀን ነገር ያለ መሰለኝ ?..ልታጫውተን ፈቃድህ ቢሆን ደስ ባለን"ሲል ..ወዲያው ኦኛ ቱማ ከአፉ ተቀብሎ .."ኧር በጣም እንጂ ...የሆነች ነገር ሰምቼ ..ባላምንም ያው ካንተው ይምጣ ብዬ ነበር ዝም ያልኩት "አለኝ
የሁለቱ ወንድሞቼ አራት አይኖች አፍጥጠው ሲያዩኝ
"ምንድን ነው የደበኳቹህ ?"ስል የሰሙትን የወሬ ጫፍ ከነሱ እንዲመጣ ጠየኳቸው ...
ይቀጥላል
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests

cron